1088
https://telegram.me/quranhkmna ቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያርጉት አላማችን በሲህር በጅን ባይንናስ የታመሙ ሙስሊሞችን ወደ ሽርክና ፀበል እዳይሄዱ ወደ ቁርአን ፈውስ ብቻ እዲጠቀሙ ማመላከት ነው ‹‹ከቁርዓን ለሰዎች መድሀኒትና እዝነት የሆነ ቁርዓን አውርደናል፡፡›› ኢስራእ ለጥያቄ ለአስተያየት https://t.me/Bequranhkmna
ከሚስትህ ይልቅ ስልክህን ያገባኸው ባለትዳር ሆይ!
ይህቺን ምክር ከልብህ አዳምጣትና ተግብራት‼
ቁርአን በኦላይን ቀጥታ ከኡስታዝ ጋ የሚገናኝ አሪፍ አፕ ነው
Читать полностью…
"አንድ ባል ሚስቱን 'ሁለተኛ ላገባ ነው' ብሎ ሊቀልድባት ሞከረ።
ቀን 1፡ ምንም አላየም።
ቀን 2፡ አሁንም ምንም አላየም።
ቀን 3፡ በግራ ዓይኑ በትንሹ ማየት ጀመረ!" 😂 🥊
3ቱ የዕድለኝነት ምልክቶች
በድሎትና ምቾት ጊዜ ጌታቸውን ከሚያመሰግኑ፣ በችግርና መከራ ጊዜ ከሚታገሱ፣ ሲሳሳቱና ሲያጠፉም ፈጥነው ወደ ጌታቸው ከሚመለሱና ምህረት ከሚጠይቁ ባሮቹ አላህ ያድርገን🤲
ትልቁ የዕድለኝነት ምልክትም ይህ ነው።
እነዚህን ማጣትም የዕድለ ቢስነት ምልክት ነውና እራሳችንን እንፈትሽ!
ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem
የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ መጋቢት 11 ቀን ይከበራል!
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ የጨረቃ መመልከቻ ጣቢያዎች ሱደይር እና ታሚር ዛሬ ምሽት የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ፦
🔹 ነገ ሐሙስ (መጋቢት 10)፦ የረመዳን 30ኛው እና የመጨረሻው ቀን ይሆናል።
🔹 አርብ መጋቢት 11፦ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በድምቀት ይከበራል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም በቅርቡ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ኹጥባ ስለ ጂኖች
https:/t.me/SadatKemalAbuMeryem
የዛሬ የቁርኣን ተፍሲር ደርስ የሚጀምረው ከሱረቱል-ሙእሚኑን አንቀፅ 73 ነው::
Читать полностью…
ቁርአን ለመቅራት እያሰብን በsocial media ምክንያት የምንዘናጋ ሰዎች አንድ ናይጄሪያዊው ወንድማችን የሚገርም አፕ ሰሮቷል።
ቁርአን መቅራት የምንፈልግበት ወቅትና ለስንት ደቂቃ መቅራት እንፈልጋለን የሚለውን set እናደርጋለን ከዛ ፌስቡክ ወይም ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ለመግባት set ያደረግነው ደቂቃ ያክል ቁርአን መቅራት ይጠበቅብናል ካልሆነ አይከፍትም።
በዚህ ሊንክ ተጠቀሙ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.app.quranunlock
ለአይፎን:- https://apps.apple.com/ng/app/quran-unlock/id6754449406
ግዜው ሳይረፍድ !
ቅፅበታዊ ስሜትን መቆጣጠር እየተሳነህ ወደ ረከሱ ፊልሞች አትመልከት .... ስሜትን ባልተፈቀደ ነገር ላይ ማዋልህ አንተን ከማርከስ ያለፈ ፋይዳ የለውም !
አይኖችህንና ብልትህን በመጠበቅ ክብርህንና ዲንህን ጠብቅ!
ያለፈው አልፏም ! አዲስ የተቅዋን ዘመን ሀ ብለህ ጀምር ! ሞት ... ቀብር አለብህ ! ግዜው ሳይረፍድ ተመለስ !
/channel/msirage4
📜 በዚህ ቻናል የተለቀቁ አርቲክሎችን ያንብቡ።
1▸ ኢየሱስ አይመለክም ሱራ 9/31
2▸ በእኔ ምን እንደሚሰራ አላውቅም
3▸ የብሉይ ኪዳን መበረዝ እውነታው
4▸ ያልተሳካው ከንቱ ትችት ሲመዘን
5▸ አል-ሐጃጅ ቁርዓንን ለውጧልን ?
6▸ የአላህ ረህመት የተፈጠረ ነውን ?
7▸ መንፈስ - ቅዱስ ፈጣሪ ነውን ?
8▸ የአልመሲሕ ዒሣ ትርጉም
9▸ በእስልምና ምድር ዝርግ ናት ?
10▸ ኢየሱስ አምላክ አይደለም
11▸ ጎልማሳ ወንዶችን ማጥባት
12▸ ሰልመናል በሉ ? (49:14)
13▸ ኢየሱስ ቃል እና መንፈስ ነውን ?
14▸ ምሁራን ስለ ሥላሴ ምን አሉ ?
15▸ ዮሐንስ ራዕይ መፅሐፍ ውግዘት
16▸ ለዓለማዊ ቁስ አብዝቶ ማሰብ
17▸ አዳምን በራሱ መልክ ፈጠረው
18▸ በእስልምና ውሸት ይፈቀዳል ?
19▸ የወር አበባ እርግማን ውጤት ?
20▸ ሱረቱል ተሕሪም እና መሪያ (ረ.ዐ)
21▸ የነቢዩን ንጽሕና በተመለከተ
22▸ አራተኛው አልጋ ለሰይጣን
23▸ የዙልቀርነይን ታሪክ ተኮርጇል ?
24▸ የባይብል ጽሑፎች ብርዘት
25▸ ኢየሱስ ዳግም ይመጣል ?
26▸ አንድ ማይል መቀመጫ
27▸ ያልተቀነነው የጳውሎስ መልዕክት
28▸ የቁርኣን አሕሩፍ ምንድነው ?
29▸ የቁርኣን ቂርኣት ምንድነው ?
30▸ የከዕብ ኢብኑ አሽረፍ ግድያ ?
31▸ የስቅላት ታሪካዊ ውዝግብ
32▸ ሥላሴ ማቴዎስ 28/19 ላይ አለ ?
33▸ የቁርኣን ትውፊታዊ መጠበቅ
34▸ የታላቁ መመሪያ አጣብቂኝ
35▸ ኢሥቲንካህ ምንድነው ?
36▸ ከአይሁድ የተቀዳ ነው 1
37▸ ከአይሁድ የተቀዳ ነው 2
38▸ ባይብልን ዳግም መገንባት !
39▸ እውነተኛ ነቢይ ስለመሆናቸው
40▸ የማርቆስ ወንጌል አጨራረስ
41▸ ጳውሎስ በቁርኣን ተጠቅሷልን ?
42▸ ቁርኣናዊያንና ክህደታቸው
43▸ አምልኮተ-ማሪያም በክርስትና
44▸ ሰባ ሁለት ደናግላን በጀነት :)
45▸ ሥላሴ አረማዊ ባዕድ አምልኮ
46▸ ባይብል እና ታሪካዊ ዳራ
47▸ የገጣሚዋ ዓስማ ግድያ
48▸ ለምን በገነት ፈጠራቸው ?
49▸ አንድያ አምላክ ወይስ ?
50▸ የፈርዖን ወይስ የአርጤክስስ ?
51▸ ቀዳማይ የሐዲስ ምንጮቻችን
52▸ የወንጌላት ደራሲያን እነማናቸው ?
53▸ ሥላሴ በማቴዎስ 28:19 ላይ
54▸ ኢየሱስ የተፈጠረ ፍጡር ነው።
55▸ ታሪኽ ሲራቱል አል-ጠበሪ
56▸ በተፍሲር መፅሐፍት ማመን
57▸ ኢብኑ ኢስሓቅ ተዓማኒ ነውን ?
58▸ የትንሳኤው ሁኔታ እና ቅጥፈት
59▸ የጠፋው አንቀጽ ? ለክርስቲያኖች
60▸ ባይብል እና ታሪካዊ ዳራው²
61▸ ሱረቱል ኒሳዕ 4/157 በተመለከተ
62▸ መንፈስ (ሩሕ) ፈጣሪ አይደለም
63▸ ኢየሱስ የተፈጠረ ፍጡር ነው
64▸ የመጽሐፍ ቅዱስ ብርዘት
65▸ አላህ ለነቢዩ ይሰግዳል ?
66▸ ሰመድ አላህ ወይስ የጣዖት
67▸ ሰውን በመግደል መፅደቅ ?
68▸ አል-ሙፋኸዛህ ለክርስቲያኖች
69▸ የነቢዩ ሕልውና ታሪካዊነት p¹
70▸ የተወገረችውን ዝንጀሮ በተመለከተ
71▸ የጨረቃ መከፈለ 'የነቢዩ ተዓምር'
72▸ የመጽሐፍ ቅዱስ ግልባጮች ?
73▸ ወንድ ልጅ በጀነት ይወልዳልን ?
74▸ የሐፍስ ቂርዓት ተዓማኒ አይደለም
75▸ የኸዲጃ ጋብቻ እና ቅጥፈቶች
76▸ የጠፉ የቁርኣን ክፍሎች አሉን ?
77▸ የውግረት አንቀጽ ዛሬ የት ገባ ?
78▸ የእግዚአብሔርና የሰይጣን ሴራ
79▸ የግመል ሽንት-ዘመናዊው ሳይንስ
80▸ አምስቱ ጥቢዎች ተሽረዋልን ?
81▸ የባይብል ጭማሪ 'ዮሐንስ 8:1-11'
82▸ የፎቶዎች ገበያ በሙስሊሙ ገነት
83▸ ድንጋይ (ከዕባ) ታመልካላችሁ !
84▸ ቁርዓን ሚስቶቻችሁን ምቱ አለ
85▸ የኢየሱስ ስቅለት በሐዲስ ላይ ?
86▸ በእስልምና ውሻ ይገደል ተብሏል
87▸ የዕብራውያን ደራሲ ማነው p¹
88▸ የአዒሻ እድሜና እውነታው ክፍል¹
89▸ የአዒሻ እድሜና እውነታው ክፍል²
90▸ የአዒሻ እድሜና እውነታው ክፍል³
91▸ ያልተከበረው የባይብል ትዕዛዝ !
92▸ መካ ጥንታዊ ቤተመቅደስ ነው
93▸ ያሲን ሐበሻዊ የሆነ የአላህ ስም ?
94▸ የቁረይሾች የእንስማማ ድርድር
95▸ ኢየሱስ እና ፍቅረኛው መግደላዊት
96▸ ግልጽ አምልኮተ ማሪያም በክርስትና
ባለፈ ስለ አሻዒራና ማቱሪዲያ ምንነት፣ ከትክክለኛ የአህሉ ሱንና መንገድ ያላቸውን ልዩነት በተመለከተ በጨረፍታ ጽሑፍ አጋርቻችሁ ነበር።
ጽሑፉ ረዘመ ስላላችሁ አንድ ወንድም በዚህ መልኩ ወደ ድምፅ ቀይሮታል። አዳምጡት። ወደ ድምፅ ይቀየር ዘንድ ያስተባበረ ወንድም አለ። ሁለቱንም ዱዓእ አድርጉላቸው።
√ ክፍል ①: /channel/MuradTadesse/45496
√ ክፍል ②: /channel/MuradTadesse/45497
√ ክፍል ③: /channel/MuradTadesse/45498
√ ክፍል ④: /channel/MuradTadesse/45500
ለግንዛቤ ማስጨበጫ ይሆን ዘንድ ለሌሎችም አሰራጩት።
ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع:
እኔም በየጊዜው በጅህልና መስፋፋት ከምቃጠልና ያለማጋነን በጣም ብዙ ሰው በተናጥል አስቀራኝ ከማለቱ ዘንድሮ ለምን በተለያየ የኢልም ዘርፍ የዲፕሎም ደረጃ ት/ት ባላችሁበት አላስተምራችሁም ብዬ ነበር ምን ትላላችሁ ?!
ትምህርቱ ከአመት በላይ የሚፈጅ ሲሆን ሙሉ በአረቢያ የተዘጋጁ pdf አለው
በሀዲስ
በሙስጠለሁል ሀዲስ
በኡሱል ፊቅህ
በነህውና
በመሳሰሉ ኢልሞች የተቀረጸ ሲሆን
ትምህርቱን በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት በሚነገራችሁ ሰአት የምንጀምር ይሆናል ፤
ምናልባት ያለፈው ሰው ካለ ሪከርዱን ሁሌ ለዚሁ አላማ በሚከፈት ግሩቭ የሚለቀቅ ይሆናል ፤
ክፍያን በተመለከተ ለአንድ ተማሪ ወርሀዊ 500ብር ብቻ ነው
ይህንን ኢልም በአረቢያ ያዘጋጁት ኡለሞች ሌላ ሲሆኑ የኔ ስራ የሚሆነው ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተዘጋጀውን ኢልም በበቂ ትንታኔ እናንተን ማስተማር ነው፤
በነገራችሁ ላይ ይህ ሁሉ አመት ደርሶች ሲደርሳችሁ ሁሉንም ወጪዎች ከኛው ነበር፤አሁን ግን በተለይ ከቪዲዮ መለቀቅ ጋርና ከወረቀት ህትመት ጋር ተያይዞ ካልተረዳዳን ሊከብድ ስለሚችል ትንሽዬ ክፍያ ለኢልሙ ተደራሽነት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ፤
አንዳንድ ነገሮችን ሊያግዝ የሚችል ሰው ሊያናግረኝ ይችላል
ሀሳባችሁን በኮመንት አስቀምጡ የሚስተካከል ነገር ካለም እናየዋለን ፤
ከዚህ በፊትም ይሁን አሁንም ይህንን አካውንት የሚቆጣጠሩ ደርሱን የሚቀዱ ሰዎች ስላሉ አሁንም ይህንን ፕሮግራም አብረን የምናስኬደው ይሆናል
አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው
👆ከላይ ባለው ኢእላን መሰረት ፍቃደኛ የሆናችሁ ሰዎች ከዚህ በታች ባለው አካውንት እየገባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ፤ምዝገባው በቴሌግራም ሲሆን አብረን ይህንን ኺዲሚያ እንሰራበታለን፤
በዚህም መሰረት ትክክለኛ ሸሃዳ የሚሰራበትን ስም እስከ አያት ማስመዝገብ ትችላላችሁ ያም ወደ አካውንቱ ሙሉ ስም ስትልኩ ፈቃደኛ መሆናችሁን እናውቃለን
ለመጀመር የሚያስችለን የተማሪ ቁጥር ስንደርስ እያንዳንዱን ተመዝጋቢ መልእክት ይደርሰውና
ቀጥታ ወደ ትምህርት እንገባለን إني عبدك ابن عبدك
የሚለው አካውንት የምትመዘገቡበት ስለሆነ በኮመት ሰላም ሲላችሁ ስም የምትልኩ
ይሆናል 👇👇
👆ከላይ ያሳለፍነው በሳምንት አራት ቀን የሚሰጥ ሲሆን፤
እኛ የመረጥነው ሰአት ከኢሻ ሰላት ቡኃላ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 3_4 ሰአት ያለውን የአንድ ሰአት ቆይታ ነው፤
የትምህርቱ ደረጃ ሁሉንም አይነት እንዲይዝ
ሞክረናል ፤
በዝርዝር እነዚህ ናቸው👇
1_البداية في العقيدة
2_البداية في الأصول
3_بداية المتفقه
4_البداية في مصطلح الحديث
5_المختصر في النحو
6_جني الثمار في الحديث
ትምህርቱን በአሏህ ፈቃድ በላቀ የሸርህ ብቃት እናስተምራለን፤
አሏህ ለሁላችንም ጤናውንና መመቻቸቱን ይወፍቀን
ትርጉም
ቁርኣንን በበለጠ ባነበብክ ቁጥር...
በሕይወትህ ውስጥ በረከቱ የበለጠ ይሆናል።
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላልና፦
{كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ})
'ይህ ወደ አንተ ያወረድነው (አንተ ሙሐመድ) የተባረከ መጽሐፍ ነው፤ አንቀጾቹን እንዲያስቡበት (እንዲመረምሩበት) እና የአዕምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰጹበት።'
የተባረከ መጽሐፍ ነው።
በበለጠ በተጠጋኸው ቁጥር፣ የበለጠ በረከት ታገኛለህ። በማለዳህ ሁለት ገጽ ከቁርኣን አንብብ።( ልብ በሉ ሁለት ገፅ )በዚያን ቀን ያለውን በረከት ተመልከት። በቀጣዩ ቀን ጨምር፣ አራት ገጾች አንብብ። በዚያን ቀን ያለውን በረከት ተመልከት። ከእሱ ቀጥሎ ባለው ቀን ግማሽ ጁዝ አንብብ። በዚያን ቀን ያለውን በረከት ተመልከት።
በበለጠ ባነበብክ ቁጥር... የበለጠ በረከት ይመጣልሃል።
በረከት ማለት ምን ማለት ነው? በረከት ማለት ጉዳይህ እንዲቀልልህ ማድረግ፣ በሮች እንዲከፈቱልህ ማድረግ ማለት ነው። ሌላ ሰው በሳምንት ውስጥ የሚያደርገውን ነገር፣ አንተ በአንድ ቀን ውስጥ ትጨርሳለህ ማለት ነው።
በእያንዳንዱ ሱጁድህ ይህንን አላህን ለምነው። በል፦ "አላህ ሆይ! ቁርኣንን የልቤ የጸደይ ( መርጊያ )አድርግልኝ" እናም በሐቀኝነት ጠይቀው። የዚያን ጊዜ ቁርኣን እንዴት የልብህ የጸደይ ወቅት እንደሚሆን ትመለከታለህ።
አላህ ሆይ! ታላቁን ቁርኣን የልቦቻችን ጸደይ( መርጊያ)፣ የልቦቻችን ብርሃን፣ የሐዘናችን ማስወገጃ፣ የጭንቆቻችንና የሐሳቦቻችን መጥፊያ፣ ወደ አንተም የሚመራን መሪ አድርግልን።
እዚህ ሐዲስ ላይ "ላይ" ወይም "በላይ" ለሚለው የገባው ቃል “ፊ” فِي ሲሆን “ፊ” فِي ሁል ጊዜ “ውስጥ” ማለት ብቻ ሳይሆን እንደየ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም ይዞ ይመጣል፥ ለምሳሌ “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል መጥቷል፦
2፥154 *"በ-አላህ መንገድ የሚገደሉትን ሰዎችም «ሙታን ናቸው» አትበሉ፡፡ በእውነቱ ሕያዋን ናቸው፤ ግን አታውቁም"*፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَن يُقْتَلُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتٌ ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ وَلَـٰكِن لَّا تَشْعُرُونَ
"ፊ" ሠቢሊሏህ" فِي سَبِيلِ اللَّه የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! “ፊ” فِي ሌላ ቦታ "ዐን" عَنْ ማለትም “ስለ”about" በሚል መጥቷል፦
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ "ስለ" እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ
"ፊ-ሂ" فِيهِ የሚለው ኃይለ-ቃል አሁንም ይሰመርበት! “ፊ” فِي ሌላ ቦታ “ፈውቅ” فَوْق ማለትም “በላይ” በሚል መጥቷል፥ ለምሳሌ ፈርዐውን፦ "በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ" ብሏል፦
20፥71 *"በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ"*፡፡ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِي جُذُوعِ النَّخْلِ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ላይ" ለሚለው የገባው ቃል "ፊ" فِي ሲሆን “ፈውቅ” فَوْق ለማለት ነው፥ ስለዚህ "ፊሥ ሠማእ" فِي السَّمَاء ማለት "በሰማይ ውስጥ" ማለት ሳይሆን "ከሰማይ በላይ" ወይም "በሰማይ ላይ" ማለት ነው፦
67፥16 *"በሰማይ ላይ ያለ በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? አትፈሩምን?* أَأَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاءِ أَن يَخْسِفَ بِكُمُ الْأَرْضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُ
67፥17 *"ወይም በሰማይ ላይ ያለ በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ቢልክባችሁ ትተማመናላችሁን? አትፈሩምን? ማስጠንቀቄም እንዴት እንደኾነ ወደፊት ታውቃላችሁ"*፡፡ أَمْ أَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاءِ أَن يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِبًا ۖ فَسَتَعْلَمُونَ كَيْفَ نَذِيرِ
እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ "መን" مَّن የሚለው ኢሥሙል መውሱል "ማንነት" ያለው ኑባሬን ያሳያል፥ ይህም ከሰማይ በላይ ያለው ማንነት ምድርን መገለባበጥ እና ጠጠርን ያዘለች ነፋስን መላክ የሚችል ማንነት ነው። በሉጥ ጊዜ ምድርን የገባበጠ እና ጠጠርን ያዘለች ነፋስን የላከ እራሱ አሏህ ነው፦
15፥74 *"ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው"*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
54፥34 *"እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ
17፥68 *"የየብሱን በኩል ምድርን በእናንተ መገልበጡን ወይም ጠጠርን የያዘ ነፋስን በእናንተ ላይ መላኩን ከዚያም ለእናንተ ጠባቂ አለማግኘታችሁን አትፈሩምን?* أَفَأَمِنتُمْ أَن يَخْسِفَ بِكُمْ جَانِبَ الْبَرِّ أَوْ يُرْسِلَ عَلَيْكُمْ حَاصِبًا ثُمَّ لَا تَجِدُوا لَكُمْ وَكِيلًا
"አሏህ ከሰማይ በላይ ነው" ብሎ ማመን የሙእሚን ዓይተኛ ጠባይ ነው፥ አሏህ እስከመጨረሻው ሙእሚን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
/channel/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
https://youtu.be/bdi877qwKgM?si=Qpy8IL2EVbsvKFca
Читать полностью…
Quran Mobasher
https://play.google.com/store/apps/details?id=maknoon.student
ትልቅ ሰው ማነው?
🌳 ደጋግ ቀደምቶቻችን አንድን ሰው ሰው ብለው ይቆጥሩት የነበረው የነቢዩን ﷺ ሱንናህ (ሸሪዓን) ሲያውቅና ሲተገብር ብቻ ነበር።
የአላህን ﷻ ሕግ (ሸሪዓን) የማያውቅና የማይከተልን ሰው እንደ አዋቂና ትልቅ (ሙሉ) ሰው አይቆጥሩትም ነበር!
🌳 የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚገባው ክብር ቢኖርም ክብሩ ሙሉ የሚሆነው ግን አላህን ሲያውቅና ሕጉን ሲያከብር ብቻ ነው።
ይህ እስካልሆነ ድረስ የሰው ልጅ በእድሜ ቁጥር ትልቅ ቢሆንም ብዙ ነገር እንደ ሚጎድለው ምንም የማያውቅ ሕፃን ነው የሚታየው!
🌳 በቅርብ ዘመን የነበሩ አንድ ዓሊም (በር ላይ 3 ወንዶች አሉ፣ እርሶን እየፈለጉ ነው) ሲሏቸው "ሶስት ሰሓባዎች በር ላይ ቆመዋል እያልከኝ ነው!?!" ብለው ጠየቁ፤ እኔ ሰሓባ አላልኩም፣ 3 ወንዶች ነው ያልኩት ሲሏቸው "ሶስት ሰዎች ካልክ ይበቃል! ወንድ ሰሓባዎች ናቸው እንጂ እኛ ምናችን ወንድ ነው?!" ብለው የወንድነትን መመዘኛ ልክ እንደ ሰሓባዎች ዲንን ማወቅና ለዲን መልፋት አድርገውታል።
🌳 እንግዲህ የብዙ ዲግሪዎች ባለቤት መሆን፣ ባለሀብትና ባለስልጣን መሆን፣ ታዋቂና ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው መባል ወዘተ ዱኒያዊ የትልቅነት መለኪያዎች ያለ ኢማንና መልካም ስነምግባር አላህ ዘንድ ምንም ዓይነት ዋጋ አይኖራቸውም ማለት ነው።
🌳 ዲኑን በሚገባ ያልተረዳ ሰው ከእንስሳት ብዙም እንደማይለይ ቁርኣንም ጠቁሟልና የሁለት ዓለም ደስታና ክብርን ለማግኘትና የምር ትልቅ ሰው ለመሆን ለሙስሊም የሚፈቀድና የማይፈቀደውን ለይተን አውቀን የአላህን ሕግ/ሸሪዓን አክብረን እንኑር።
እንደፈለጉ መኖር ከአላህ ﷻ ጋር ያጣላል፤ ዱኒያና ኣኺራንም ያበላሻል።
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ዛዱል-መዓድ
🌐 https://zadulmead.org/
✔️/channel/ahmedadem
✔️https://facebook.com/yenegew
✔️Zadul-Mead" rel="nofollow">https://youtube.com/@Zadul-Mead
✔️ https://x.com/zadul__mead
✔️https://instagram.com/zadulmead
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ
🔖መልካም ሚስት በጅንጀና አትገኝም።
📍ኢብኑል አረብይ አልማሊኪይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።
«መልካም ሚስት የምትገኘው ባንተ ጥረት አይደለም። እሷ ማለት አላህን ለሚፈራ ሰው የምትሰጥ የአላህ ሲሳይ (ሪዝቅ) ናት።»
📖أحكام القرآن (1/536)
ኹጥባ ስለ ጂኖች
/channel/SadatKemalAbuMeryem/8194
አደራህን ዛሬ ዱንያ ላይ ሰዎች በማይረባ ስራቸው በተሰጣቸው ደረጃና ዝና እንዳትሸወድ ፣ በዕለተ ትንሳኤ ሁሉም በሚገባው ቦታና ደረጃ መቀመጡ አይቀርምና ለዚያች ቀንህ ስራ።
Читать полностью…
የዛዱል መዓድ መድረሳን ግንባታ አልረሳችሁትም ኣ ያ ጀማዓህ⁉️
የሚፈለገው 25 ሚሊዮን ብር ቢሆንም እስካሁን 7 ሚሊዮንን አልፈን ግና ገና 8 ሚሊዮን እንኳ አልገባንም።
የጎደለንን ሁላችንም ተረባርበን ብንሞላው፤ ቋሚ ሶደቃ ይሆንልናል። ኢስላምን ከትክክለኛ ምንጩ ተምረው ለኡማው የሚጠቅሙ ትውልዶች የሚመነጩበት ይሆናል።
በተለይ አላህ አቅሙን የሰጣችሁ ወንድምና እህቶች አላህ ከሰጣችሁ ላይ እንደዚህ የርሱ ተውሒድ ለሚሰበክበት መድረሳ ብትሰድቁ፤ ከምንም በላይ እድለኝነቱ ለናንተ ነው።
አሁን የሚቀሩበት መድረሳው ይህ የምትመለከቱት ነው።
ሁሉም ሌላ ሰው ሳይመለከት የራሱን 5 አስር ሳይል አላህ ያገራለትን ያክል ቢሰድቅ፤ በአላህ ፈቃድ ተባብረን እናሳካዋለን።
የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች:
✅ ንግድ ባንክ: 1000574989691
✅ አዋሽ ባንክ: 014251609676900
✅ አቢሲኒያ ባንክ: 230756627
(የሂሳብ ስም፡ ዛዱል መዓድ የቁርኣን እና የተርቢያ ማዕከል)
📸 የላካችሁበትን ስክሪንሹት በዚህ ላኩልኝ ⬅️ t.me/Murad_Tadesse
ቡሪክቱም➡️
የማይጠቅም ዕውቀት...
የማይጠቅም (የማይሰሩበት) ዕውቀትና የማይወስዱት (የማይውጡት) መድሃኒት አንድ ናቸው።
አንድ ታማሚ መድሃኒቶችን አጠገቡ በማስቀመጥ ብቻ ሊድን አንደማይችለው ሁሉ ዒልምም በማዳመጥ ብቻ መጠቀምና መለወጥ አይቻልም። ለመለወጥና ለመጠቀም የግድ መስራትና መተግበር ያስፈልጋል።
ስለዚህም በተለያዩ አጋጣሚዎች የምናገኘው እውቀት እንዲጠቅመን እንስራበት!
የቂያም ቀንም (ባወቅከው ሰርተሀልን?) ተብሎ መጠየቅ እንዳለ እናስታውስ!
ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem
ሰላሳ ጁዝ ቁርዓን ተፍሲር በኡስታዝ አቡያሲር አብዱልመናን #ያለኔት
ቁርዓኑ እየታዬ ደስ በሚል አቀራረብ
👇📚📚📚📚🎵🎵👇
/channel/hussenapp/6972
ከጎግል ድራይቭ ለማውረድ
👇📚📚📚📚👇
https://drive.google.com/uc?export=download&id=1F_wtvLC7NwcQO6R4vvtDMWfoHK4jvZkP
ስለአጠቃቀሙ እና ይዘቱ ያስረዳሁበትን ቪድዮ ለማዬት
👇📚📚📚📚👇
https://youtu.be/86b9oyYiyS0
• ኢላሂ…እኔ ያ አንተ የፈጠርከው ደካማው ባሪያህ... ነፍሴ አሸንፋኝ፣ ሸይጣን አታሎኝ፣ የዱንያ ጌጥ አታሎኝ... ይኸው በወንጀል ተዘፍቄ በፊትህ ቆሜያለሁ።
ኢላሂ...
ስንት ጊዜ «ተውበት አድርጌያለሁ» ብዬ ቃል ገባሁልህና ቃሌን አፈረስኩ?
ስንት ጊዜ «ከእንግዲህ አልመለስም» ብዬ ማልኩልህና ወደዛው ኃጢአት ተመለስኩ?
ስንት ጊዜ እዝነትህን እያወቅሁ በድፍረት አምጽኩህ?
ጌታዬ ሆይ!
በዓይኔ ያየሁት ሀራም ልቤን አሳውሮታል።
በምላሴ የተናገርኩት ውሸት ኢማኔን አደብዝዞታል።
በጆሮዬ የሰማሁት ከንቱ ወሬ ከቃልህ አርቆኛል።
የበላሁት የ ሹቡሃ ገንዘበ የዒባዳዬን ጣዕም ነስቶኛል።
ልቤ በጥቁር ነጥብ ተሸፍናለች... ነፍሴ በኃጢአት ዝገት ተበክላለች። እዝነትህ ባይኖር ኑሮ፣ ከፊትህ ለመቆም አቅምም ድፍረትም ባልነበረኝ። ነገር ግን የእዝነትህን ስፋት ሳስብ፣ የይቅርታህን ታላቅነት ሳስታውስ፣ ተስፋዬ ይለመልማል።
ኢላሂ…
አለባበስሽ እዳ ነው ወይስ ዒባዳህ?
🔅አላህ ያዘዛትን አለባበስ ትታ የፋሽንና የባህል አለባበስ በመልበስ ኢስላም እንድትሸፍነው ያዘዛትን የሰውነት ክፍል ገልጣ፣ ወይም ለስሙ ያክል ብቻ ስስና ጠባብ ልብስ ተጠቅማ ከቤት የምትወጣ ሴት በሄደችበት ሁሉ ወንጀለኛ ስትሆንና መላዕክትም ሲረግሟት፤ አላህ ﷻ እና መልእክተኛው ﷺ
ያዘዟትን ዓይነት ሙሉ ሒጃብ አድርጋ ምትንቀሳቀስ ሴት የትም፣ ምንም ላይ ሆና ዒባዳህ (ሰላት) ላይ እንዳለች ነው የሚቆጠረው (ትክክለኛ ሒጃብ በማድረጓ ሁሌም/ የትም ሆና አጅር ታገኛለች)።
ይህም ትክክለኛና የተሟላ ሒጅብ አላህን ﷻ የሚያስደስት ሥራና ልክ እንደ ሰላት፣ ጾምና ሐጅ ትልቅ ወደ አላህ የሚያቃርብ ዒባዳህ በመሆኑ ነው።
🔅ተገላልጦ መሄድ፣ ውበትና ፈታኝ የሰውነት አካልን ማሳየት ደግሞ አላህን ﷻ የሚያስቆጣ ትልቅ ወንጀልና የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን ሸይጣንን የሚያስደሰት ተግባርም ነው።
🔅 እህቴ ሆይ የቱ ይሻልሻል?
አጭር የዱንያ ቆይታ ላይ አላህ ﷻየሚወደውን ዓይነት አለባበስ ለብሶ ኣኺራህ ላይ ከአላህ ቁጣ ድኖ ጀነትን መሸለም? ወይስ ለትንሽ ጊዜ እንደፈለጉ በመሆን አላህን ﷻ አስቆጥቶ ነገ ኣኺራህ ላይ መቀጣት?!
ከቀልብሽ ሁኚ! ሁሉም (መልበስና መሰተሩም፣ መገላለጥና እዩኝ እዩኝ ማለቱም) ያልፋል፤ ግን አላህ ዘንድ ተፅፎ ይቀመጣል!!
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ዛዱል መዓድ
🌐 https://zadulmead.org
✔️ /channel/ahmedadem
✔️https://facebook.com/yenegew
✔️Zadul-Mead" rel="nofollow">https://youtube.com/@Zadul-Mead
✔️ https://x.com/zadul__mead
✔️https://instagram.com/zadulmead
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ
የብዙሃን መጥፊያ የሆነውን ሞባይል መልካምን ነገር መጠቀሚያ እናድርገው
መእሀዱ ፈትሂል ዋሲእ እናንተን በስርዓት ከተከታተላችሁ በቂ እውቀት ያላችሁ ኡስታዞች እንድትሆኑ በትላልቅ የዘርፉ ኡለሞች የተዘጋጁ መማሪያ መፅሃፍትን ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ ኢልም ሊያስተምራችሁ ዝግጅቱን ጨርሷል፤
📌📌የፕሮግራም ቀናት፦ በሳምንት አራት ቀን
ሰኞ ማክሰኞ ረቡእ እና ዓርብ
🔗⌚️የት/ት ሰአት፦ከምሽቱ 3_4
ሰአት ለአንድ ሰአት ያህል
📚አዘጋጅ እና አቅራቢ ፦ ኡስታዝ አብዱልዋሲእ ሸይኽ ነስሮ የረጅም ጊዜ የዲን ት/ት
አስተማሪ ኢማም እና ኸጢብ
Fath al-wasie academy
ቁርኣን ያኸተመ ሁሉ ሊጠቀመው የሚገባ እድል እንደሆነ ይሰማኛል
ለምዝገባ ወይም ለበለጠ መረጃ
@mezgeba3236 ተጠቀሙ
ጀግና ማለት አላህን በድብቅም በግልጽም የሚፈራ ሰው ነው
اتق الله حيثما كنت
(رواه الترمذي)"
የትም ብትሆን አሏህን ፍራ!
በዘንድሮው የማትሪክ ውጤት አልመጣልህም ? ‼‼
በስሙ ከአንድ ሺህ በላይ የፈጠራ ስራዎችን ያስመዘገበው the father of modern innovation በሚል ስም የሚታወቀው ቶማስ ኤድሰን ፡ አደለም ዩኒቨርስቲ ፡ አደለም ኮሌጅ ፡ በህይወቱ የትምህርት ቤት ደጃፍ ረግጦ አያውቅም ።
አምፖል ፡ የኤሌትሪክ ጄኔሬተር ፡ ተንቀሳቃሽ ምስል ካሜራ እና ሌሎቹም የፈጠራ ስራዎች የበሩለት እናቱ ቤት ውስጥ ባስቆጠረችው መሰረታዊ ትምህርት በመጠቀም በንባብ አዳብሮ ባገኘው እውቀት ነው ።
......
ሳይማሩ አለምን መለወጥ የቻሉት እነዚህ ብቻ አይደሉም የማይክሮሶፍቱ መስራች ቢልጌትስ ... የአፕል መስራቹ
ስቲቭ ጆብስም ፡ ይህን የምንጠቀምበትን ፌስቡክ የሰራልን ማርክ ዙከርበርግ ዲግሪ የሚባል ነገር አያውቃቸውም ።
....
የፎርድ ካምፓኒ መስራች ሄነሪ ፎርድ በ16 አመቱ ትምህርቱን ያቋረጠ ሰው ነበር ። ሪቻርድ ብራንሰን ፡ ኦፕራ ዊንፍሬ የኮሌጅ ሽፍታ ናቸው ።
...
እዚህ ላይ መማርን ፡ ተምሮ ለኮሌጅ መብቃትን የምናበረታታው ነገር ቢሆንም ፡ የስኬት ዳር ፡ የብቃት እና የመቻል ብቸኛ መለኪያ ግን አይደለም ።
...
በዘንድሮው የማትሪክ ውጤት አልመጣልህም ? በቃ ያንተ መክሊት እዛ አይደለም ። እና የተዘጋብህ የኮሌጅ በር ብቻ እንጂ ሺህ የስኬት መንገዶች ከፊትህ ተዘርግተው የሚጠብቁትን አንተን ነው ።
...
ውጤት ስላላመጣህ ተናደሀል ? ይህንን ንዴት ወደ እልህ ቀይረውና ፡ ወደውስጥህ እይ ፡ መክሊቴ ምንድነው ? አዲስ ነገር መፍጠር ? የተፈጠረን ነገር ማሻሻል ነው ? ወይስ ንግድ ወይስ ምን ብትሰራ የሚሳካልህ ይመስልሀል ፡ ይህን አጥና ።
....
ደሞ ስልክ ይዘህ መፍትሄ ይጠፋሀል እንዴ ? ስልክህን ክፈት ፡ ስልክህ ኮሌጅ ነው ። እንደዝንባሌህ የፈለከውን ነገር መማር የፈጠራ ስራዎችን እየየህ አዶፕት ለማድረግ ሞክር ፡ አእምሮህን በይቻላል ስሜት ሙላው ፡ እንጂ አትቆዝም ።
አሏህ ከሰማይ በላይ ነው!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
67፥16 *"በሰማይ ላይ ያለ በእናንተ ምድርን ቢደረባባችሁ ወዲያውም እርሷ የምታረገርግ ብትኾን ትተማመናላችሁን? አትፈሩምን?* أَأَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاءِ أَن يَخْسِفَ بِكُمُ الْأَرْضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُ
“ሠማእ” سَّمَاء የሚለው ቃል “ሠማ” سَمَا ማለትም “ከፍ አለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ከፍታ” ወይም “አርያም” ነው፦
88፥18 *“ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች”*። وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ
ቁርኣን ላይ “ሠማእ” سَّمَاء የሚለው ቃል "ሠማዋት” سَمَاوَات የሚባሉትን ሰባት ሰማያት ለማመልከት ይመጣል። የሰማያት የመጨረሻው ሰማይ ሰባተኛው ሰማይ ነው፥ ያ ሰማይ መጠናቀቂያው ዐርሽ ነው፥ አምላካችን አሏህ ከአርያም በላይ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3519
አነሥ እንደተረከው፦ "ስለ ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ፦ "ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ እርሷን አጋባንህ" የሚለው አንቀጽ በወረደ ጊዜ እርሷ በነቢዩ”ﷺ” ባለቤቶች ፊት በኩራት፦ *“እናንተን ቤተሰቦቻችሁ ዳርዋችሁ፥ እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው አላህ ዳረኝ” እያለች ትናገር ነበር"*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ فِي زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ : (فلَمَّا قَضَى زَيْدٌ مِنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا ) قَالَ فَكَانَتْ تَفْتَخِرُ عَلَى أَزْوَاجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تَقُولُ زَوَّجَكُنَّ أَهْلُكُنَّ وَزَوَّجَنِي اللَّهُ مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَوَاتٍ
እዚህ ሐዲስ ላይ "በላይ" ለሚለው የገባው ቃል "ፈውቅ" فَوْق ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" አንዲት እንስትን፦ "አሏህ የት ነው ያለው? ብለው ጠይቀዋት "ከሰማይ በላይ" ብላ ስትመልስ "አማኝ" ናት ብለዋል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 41
ሙዓዊያህ ኢብኑ አል-ሐከሙ አሥ-ሡለይሚይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ለእኔ በጥፊ የመታኃት ሴት አገልጋይ አለችኝ" አልኩኝ፥ ይህ ጉዳይ የአሏህን መልእክተኛን"ﷺ" አሳዘነ። እኔም፦ "ነጻ ማውጣት የለብኝምን? አልኩኝ፥ እርሳቸው፦ "ወደ እኔ አምጣት" አሉት። እኔም አመጣኃት፥ እርሳቸውም፦ *"አሏህ የት ነው ያለው? ብለው ጠየቋት። እርሷም፦ "ከሰማይ በላይ" አለች፥ እርሳቸውም፦ "እኔ ማን ነኝ? ብለው ጠየቋት። እርሷም፦ "አንተ የአሏህ መልእክተኛ ነህ" አለች፥ ነጻ አውጣት! እርሷ አማኝ ነች" አሉ"*። عَنْ مُعَاوِيَةَ بْنِ الْحَكَمِ السُّلَمِيِّ، قَالَ قُلْتُ : يَا رَسُولَ اللَّهِ جَارِيَةٌ لِي صَكَكْتُهَا صَكَّةً . فَعَظَّمَ ذَلِكَ عَلَىَّ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ أَفَلاَ أُعْتِقُهَا قَالَ : " ائْتِنِي بِهَا " . قَالَ : فَجِئْتُ بِهَا قَالَ : " أَيْنَ اللَّهُ " . قَالَتْ : فِي السَّمَاءِ . قَالَ : " مَنْ أَنَا " . قَالَتْ : أَنْتَ رَسُولُ اللَّهِ . قَالَ : " أَعْتِقْهَا فَإِنَّهَا مُؤْمِنَةٌ "