- አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ ፣ ወልድም በአብ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ ሕልው እንደሆነ እናምናለን ይህች ሦስትነት ያለመለየት ያለመለወጥ በሦስት አካላት በአንድ መለኮት የተካከለች ናት ፡፡
- አንዲት አገዛዝ አንዲት ፈቃድ አንዲት ሃይል አንዲት መንግሥት አንዲት ስግደት አንዲት ምሥጋና አንዲት ክብር አንድ ጽንዕ ለሥላሴ ይገባል ፡፡ አንዲት ምክር አንዲት ሥልጣን አንድ ክብር አንዲት ጽንዕ አንድ አኗኗር አንድ ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ ነው ፡፡
- አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም ፡፡ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ እሊህ ሦስቱ አካላት በጌትነት በክብር ፍጹማን ናቸው ፡፡ በአንድ መለኮት አንድነትም አንድ ናቸው ፡፡
- ይኸውም ሦስትነት ከእርሱ የሚገኝ አንድ ብርሃን ነው ፡፡ በዓለሙ ሁሉ መሉዕ ነው ፡፡ ከምድር በታች ላሉትም ያበራል ፡፡ በሰማይ በምድር ምሉ ነኝ እኮ ! በሲኦልም ያሉ ጌትነቱን አዩ ተብሎ እንደተፃፈ ፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 9 ገፅ 23
https://bit.ly/መልዕክት_10_ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_pdf
http://bit.ly/መልእክት_10_ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_በድምፅ
👆👆👆
ፌስቡክ ፣ ኢሞ ፣ ዋትስአፕ ላይ ለማሰራጨት ለምትፈልጉ።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 10 በፒዲኤፍ እና በድምፅ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
🇲🇱 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው
መገለቸጫና
መመስገኛ ምድር
🇲🇱ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
🇲🇱ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
🇲🇱ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለጾመ ፍልሰታ ፆመ በሰላም አደረሳችሁ ::
የተወደዳቹህ የሀያሉ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት በኵራት ልጆች የቅዱሳን መላእክት የጻድቃን የሰማእታት ወዳጆች ቤተሰቦቼ በዚህ ሱባኤ በእኔ በደካማ በሀጥያተኛ በደለኛ ወንድማቹህ ያሳዘንኳንቹህ የበደል ኳቹህ ቤተሰቦቼ ስለ ሐያሉ ልዑል እግዚአብሔር ብላቹህ ይቅር በሉኝ
ስለ ድንግል ማርያም ብላቹህ ይቅር በሉኝ
ስለ ቅዱሳን መላእክት ብላቹህ ይቅር በሉኝ ::
🔑 በየትኛውም ቦታ ያላችሁ ከአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ከሆነው በአባቶቻችን አማካኝነት በተሰጠን በዚህ ቃልኪዳኑ የምታምኑ ሁሉ ባላችሁበት መኖሪያ ቤት ይህንን የኪዳን ቃል
ስቀሉ !ስቀሉ !ስቀሉ !!!
በየትኛውም ስፍራ ላላችሁ የእምዬ ኢትዮጵያ ልጆች ፣ የተዋህዶ አርበኞች ፣ የአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የተገፋችሁ ባንዲራችን ወዳጆች በየትም አካባቢ ብትሆኑ ይህንን ቃልኪዳን በልባችሁ በህሊናችሁ እንዲሁም በኪሳችሁ በእምነት ያዙት ከኃይል ወደ ኃይል ያሸጋግራችዋል ከመቅሰፍቱም ትጠበቁበታላችሁ ።
ይህ ቃልኪዳን ቃል ከነ ሰንደቁ ባለበት የልዑል እግዚአብሔር ታማኝ መላዕክ የዕራማው ቅዱስ ሊቀ መላዕክት ገብርኤል አለ ይህም የሚሆነው በእምነት ለተቀበሉ ብቻ ነው።
+ ኢየሱስም ሖምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ተፈጸመ አለ፥ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
ዮሐ 19:30
+ መልካም እረኛ እኔ ነኝ።መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ዮሐ 10:11
+ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦቻችን በሙሉ
ካለንበት ቦታ ኔትወርክ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የጥያቄዎቻችሁ መልስ
ከጥር 30 ጀምሮ የምንጀምር መሆኑን በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።