መጣያ
( በእውቀቱ ስዩም)
እኛ ቤት አንድ ብረትድስት ነበረ! ብረት ድስቱ የቆየ ነው! በእድሜ ሁለት አመት ታላቄ መሰለኝ! መቼም የማይሰራው ስራ አልነበረም! ገንፎ ይገነፋበታል፤ ንፍሮ ይቀቀልበታል፤ የጎመን ወጥ ይሰራበታል ፤ አንዳንዴ ወግ ደርሶት ፓስታም ይቀቀልበታል፤ ወላጆቻችን ቤት ውስጥ ከሌሉ እንደ ከበሮም እንጠቀምበታለን! ብርታቱ እንደ ኤሊ ድንጋይ ነው! ያ ብረትድስት ህይወት ቢኖረው ኑሮ፤ “ችግርሽ በኔ አልፏል” የሚለውን ያለማየሁ እሸቴን ዘፈን ይጋብዘኝ ነበር! ውይ ረስቼው! ለካ ችግር መልኩን ይቀይራል እንጂ አያልፍም!
የአፍሪካውያን ችግር የእቃ እጥረት ሲሆን የአመሪካ ወይም ካናዳ ችግር የእቃ መጥለቅለቅ ነው! ለምሳሌ አንዲት አማካኝ ኑሮ ያላት አመሪካዊት በቤቷ ቢያንስ አራት አይነት ጉዋንት ይኖራታል! የእቃ ማጠቢያ ጉዋንት የተጣደ ድስት ከምድጃ ላይ የምታነሳበት ወፍራም ጉዋንት - ገላዋን ስትታጠብ ብብቷን የምታሽበት ጉዋንት- አሁን ደግሞ የጀርም መከላከያ ጉዋንት መጥቶላታል ፤
ባንፃሩ፤ እኛ ቤት ለረጅም ጊዜ ያገለገለቺው ሰራተኛ አጀቡሽ ሁሉን ነገር በሌጣ እጇ ነበር የምታከናውነው ! በባዶ እጇ እቃ ታጥባለች! በሌጣ መዳፉዋ የጋመ ድስት ታወጣለች! መዳፏ የእሳት ወላፈን የሚሰማው አይመስልም! በልማድ እሳት- ከል ( fire-proof ) ሆኖ ቀርቷል::
ሰዎች የተወሰነ ፍላጎት ይዘው ነው እሚወለዱት! ገናናው ገበያ ግን መአት አይነት ፍላጎቶችን ፈለፍላል! የሀብታም አገሮች ዜጎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይሸምታሉ፤ ይሄንንም ያንንም ቅራቅንቦ ያግበሰብሳሉ ! በአሜሪካና በካናዳ እቃ ከመግዛት ይልቅ እቃ መጣል ብዙ ወጭ ያስወጣል! ለምሳሌ በኛ አገር ተለቅ ያለ ቲቪ መግዛት ከፈለግህ ሚጢጢውን ቲቪ ለዘመድህ ትሰጠዋለህ! አሁን እኔ የተጎለትሁበት ከተማ ውስጥ ግን ከመጣል ውጭ አማራጭ የለህም! ብትጥል ደግሞ ከተማ በማልከስከስ ሊከሱህ ይችላሉ!
ባለፈው ባልንጀራየ በየነ ደወሎ “ጉድ ሆንኩ “ አለ
“ ምን ሆነህ ነው?” አልኩት!
“ የሆኑ ሰዎች ቤቴን ሰብረው ገብተው “
“ ዘረፉህ ?”
“ የለም! ሁለት አሮጌ ሶፋ ጥለውብኝ ሄዱ”
💥💥ገምሃልያ💥💥
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል1⃣
ፀሃፊ ረምሃይ
እንደወትሮዬ ሁልግዜ ቅዳሜ ወይ እሁድ ከሰአት እምሰራው ስራ ከሌለኝ ከመፅሃፍ መደርደሪያዬ ላይ ውድ ጓደኞቼ በስጦታ መልክ ከሰጡኝ መፅሃፎች አንዱን አነሳና ቦሌ ማተሚያ አከባቢ ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝ ደስ እሚል በዛፎች የተሞላ ፓርክ አለ። ብዙ ግዜ እዛ ሄጄ መፅሃፍ ማንበብ እወዳለው። ዛሬ እለቱ ቅዳሜ ነው እዛ ሄጄ ለማንበብ የመረጥኩት ብርቅርቃ እሚለውን መፅሃፍ ነበር አሜን እምትባል ጓደኛዬ የሰጠችኝ መፅሃፍ ነው እሚገርመው ብርቅርቅታን የመሰለ አሪፍ መፅሃፍ እስከዛሬ አላነበብኩትም ነበር ከመደርደሪያው ላይ ስቤ ጠቅለል አድርጌው ይዤ ወጣው። መንገዴን ከቦሌ ድልድይ ጫፍ ወደ ስታዲየምና ሚክሲኮ በሚወስደው መስመር ታክሲ ተሳፍሬ ወደ ማተሚያ ቤት ሄድኩ። ማተሚያ ቤት ጋር ስደርስ ወርጄ በእግር መንገድ ወደ ውስጥ ወደፓርኩ ገሰገስኩ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ ሳልወድ በግድ ያሯሩጠኛል። እዛ ሰፈር ያሉት ፍየሎች ሁሌም ሳያቸው ያስቁኛል በጣም ትልልቅ ጥጃ ነው እሚያክሉት ምን እንደሚቀልቧቸው እንጃላቸው። እነሱን በአይበሉባ እየታዘብኩ ፓርኩ ጋር ደረስኩ ለመቀመጥ ሁለት ብር ከከፈልኩ በኃላ ሁሌም ወደምቀመጥባት ሰላማዊ ቦታ አቀናው ቦታዋ ጥግ ላይ ሁና ከሁሉም እይታ ገንጠል ብላ ጀርባዋን ሰጥታ ያለች ቦታ ናት ከፊትለፊቷ እሚያምር፤ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኝ የሙዝ እና የበቆሎ እርሻ ማሳ ይታያል። እናም ወደቦታዬ እየሄድኩ በልቤ ሌላ ሰው እንዳይቀመጥባት እየቋጠርኩ ሄድኩ ቦታዬ ላይ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ ከጀርባ ከሚታዩት ክብ መቀመጫዎች ላይ አንዲት በግምት በእኔ እድሜ አከባቢ እምትሆን ሴት ሲጋራ እያጨሰች አየኃት ለሽራፊ ሰከንዶች ቆም ብዬ ካየኃት በኃላ ወደቦታዬ ሄድኩ ማንም አልተቀመጠባትም ደስ አለኝ። በሸክላ ጡብ እና በሲሚንቶ የተሰራችውን መቀመጫ በሶፍት ጠረግኩና ተቀመጥኩ ቦታዋ ደስ ትላለች ሙሽሮች ሲጋቡ ለመድረክነት የሚጠቀሙባት ባለግርማሞገስ የድንጋይ ዙፋን ትመስላለች መደገፊያዋ ረጅም ስለሆነ ካልቆምኩ በስተቀር ከኃላዬ ምን እንዳለ አይታይም ያውም በኔ መለሎ ቁመት።
ቦታዬ ላይ ተረጋግቼ ከተቀመጥኩ በኃላ መፅሃፌን ከፈትኩና ሀ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ.... ግን ቅድም ሲጋራ እያጨሰች የነበረችው ሴት በአእምሮዬ ተመላለሰች ፊቷ የተከፋ ይመስላል ሲጋራውን በብሽቀት እየማገች ጭሱን ሽቅብ ትለቀዋለች ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት አሰብኩና ምን አገባኝ ብዬ መልሼ ተውኩት መፅሃፌን ማንበብ ቀጠልኩ። ግን የልጅቷ ሁኔታ አእምሮዬ ውስጥ እየተመላለሰ ሰላም ነሳኝ በመጨረሻም ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት ወሰንኩና መፅሃፉን ከድኜ አስቀመጥኩት። ወደሷ ሄድኩ እሷ የተቀመጠችበት ቦታ ከኔ ጀርባ ሆኖ ቅርብ ርቀት ላይ ነው ሄጄ ሰላም አልኳት የደረቀ ሰላምታ ሰጠችኝ። ሲጋራ ማጨስ እችላለው አልኳት ገልመጥ እያለች በእጇ መሃል የሚጤሰውን ሲጋራ ሰጠችኝ ተቀበልኳትና በጣቶቼ መሃል አድርጌ ጭሱ ሲበን ትንሽ ተከዝ ብዬ አየሁት በጎን በኩል የሸክላው ጡብ ወንበር መደገፊያ ላይ ወጥቼ እግሬን ደግሞ መቀመጫው ላይ አድርጌ ተቀመጥኩ። እሷን ምንም ሳልናገራት ሲጋራውን ዝም ማየት ቀጠልኩ ውስጡ የሷን ጭንቀት ይሁን ሃሳብ ይነግረኝ ይመስል ከጭሱ ውስጥ መልስ ፍለጋ ገባው። ልጅቷ ከሁኔታዋ ማውራት እምትፈልግ አትመስልም እንዲያ ባይሆን ኖሮ እንደዚ አይነት በብቸኝነት ሰላም እሚሰጥ ቦታ ባልመጣች ነበር። እሷ ማውራት ባትፈልግም እኔ ግን ማውራት ነበረብኝ። ሲጋራውን ትንሽ ካየሁት በኃላ ወደታች ዘቀዘቅኩት እሳቱ ሲጋራውን በፍጥነት ወደላይ ይበላው ጀመር ጭሱ ወደላይ ይበናል አመዱ ደግሞ ወደመሬት ይወድቃል። ልጅቷ እማደርግውን ዝምብላ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ምን ይታይሻል አልኳት ሲጋራ አለችኝ። እኔ ግን ህይወት ይታየኛል ምስቅልቅሉ የወጣ ህይወት ከላይ ወደታች የተገለበጠች ህይወት አመድ እና ጭስ የሆነ ህይወት እሳት የሆነ ፈተና። ህይወት እንደሲጋራው ቀጥ ተደርጋ በምቾት ስትያዝ እኛ የህይወትን ትርጉም አናውቅም እሳቱ ቀስ እያለ ሲጋራውን ይጨርሰዋል ነገር ግን ሲጋራው ሲገለበጥ መከራ ሲበዛብን እሳቱ ቶሎ ሲጋራውን ይበላዋል በመከራ ውስጥ ሆነን የህይወት ትርጉም ይገባናል ህይወታችችንን አጣጥመን ቶሎ ቶሎ እንኖራታለን እዚች ምድር ላይ ያለን ግዜ ውስን ስለሆነ ሲጋራው ወደታች ቢዘቀዘቅም ጭሱ ግን ወደላይ ነበር የሚጨሰው ፈተናውን የሚያልፍ ሰውም እንደዛ ነው ግን...... አልኳትና ዝም አልኩ ሲጋራውን ለልጅቷ መለስኩላት እና ተነስቼ ወደቦታዬ ለመመለስ ስዘጋጅ ግን ምን? አለችኝ ፈገግ ብዬ አየኃትና መልስ ሳልሰጣት ቦታዬ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ መፅሃፌን እንደነገሩ ከፍቼ ቁጭ አልኩ ልጅቷ እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ አንዳንዴ ሰው እንዴት እንደሚያስብ ስናውቅ ሰውን ማሞኘት ቀላል ይሆናል ልጅቷ መጀመሪያ ላይ ማውራት እንደማትፈልግና ብቻዋን መሆን እንደምትፈልግ ከሁኔታዋ ያስታውቃል ግን ደግሞ እኔ ምን እንደሆነች ማወቅ ፈልጊያለው ምን ሆነሽ ነው ብላት ቀጥታ እንደማትነግረኝ አውቃለው ማንያውቃል ምን አባህ አገባህ ብላ ታባረኝም ይሆናል ስለዚ የጭንቅላት ጨዋታ መጫወት ነበረብኝ ግን ብዬ የጀመርኩትን ሳልጨርስላት ተመለሼ ቦታዬ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ ስለዚህ አሁን ውሳኔው የሷ ይሆናል ማውራት ከፈለገች ትመጣለች ካልፈለገችም ሙከራዬ ከሸፈ እኔም ማውራት እማይፈልግን ሰው መጨቅጨቅ አልፈልግም።
እንዳቀድኩትም ልጅቷ ትንሽ ቆይታ ከተቀመጥኩበት ቦታ መጥታ ፊትለፊቴ ቆማ ግን ምን? አለችኝ እንደቅድሙ ፈገግ እያልኩ መፅሃፌን ዘግቼ ሲጋራውን ተቀበልኳትና እንድትቀመጥ ጋበዝኳት ከአጠገቤ ትንሽ ፈቀቅ ብላ ተቀመጠች። ሲጋራውን መሬት ላይ ጣልኩትና በእግሬ ጨፈለቅኩት ልጅቷ እንደመቆጣት እያለች ለምን አጠፋኀው አለችኝ በአንዴ ሁለት ጥያቄ መጠየቅ አይቻልም አሁን ከጠየቅሽኝ አንዱን ምረጭ አልኳት ከንዴቷ በረድ እያለች እሺ ግን ምን? አለችኝ። ሌላ ሲጋራ ይዘሻል ብዬ ጠየቅኳት አው ብላ ቦርሳዋ ውስጥ ገብታ ከፓኮው ውስጥ አንድ ፍሬ ሲጋራ አውጥታ ሰጠችኝ። ሙሉ ፓኮውን ስጪኝ አልኳት ምንም ሳትል አውጥታ ከነካርቶኑ አስረከበችኝ። ግን ምን? የሚለውን መልስ እየጠበቅች ነው። ግን ምን አለ መሰለሽ እኛ እንደጭሱ ጠንካራ ሆነን የተመሰቃቀለ የተገለባበጠ ህይወታችንን ተቋቁመን ወደላይ ስንወጣ ደካማ አመድ የሆነው ደግሞ ወደታች ይወድቃል ትቢያ ይበላል። ህይወት እንደዚ ናት ህይወት ብትገለባበጥ ብትመሰቃቀል አንቺ ጭሱን ወይ አመዱን ትሆኛለሽ ከሁለቱ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም! ስለዚ አንቺ ከየትኛው ወገን ነሽ አመድ ወይስ ጭስ አልኳት እንደማዘን እያለች አመድ አለችኝ ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ታዲያ ለአመድ ጭስ ምን ይሰራለታል አልኳትና በፓኮ ያለውን ሲጋራ አንድ ፍሬ አስቀርቼ የተቀረውን አርቄ ወረወርኩት የሲጋራው ካርቶን የፓርኩን የዛፎች አጥር አልፎ ወደ ውጪ ወደቀ እንዴ ለምን ወረወርከው አለችኝ እየተናደደች። እዛው እንደቆምኩ ወደሷ እያየው አመድ ከሆንሽ ጭስ ምንም አያደርግልሽም አይደል ሁለቱ በምንም እማይገናኙ እሚቃረኑ ተፈጥሮዎች ናቸው በከሰለ አመድ ውስጥ ጭስ የለም አልኳት እየተናደደች እሺ ጭስ ብልህስ ኖሮ አለችኝ።
.........ይቀጥላል.........✍
Like👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩@Kirubeljr አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@Readersworld11
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን
ወጣቱ ዶክተር ቢሮውን እንደከፈተ ዘና ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀምጧል፡፡ ፀሀፊው አንድ ሰው መግባት እንደሚፈልግ ስትነገረው እንድታስገባው ነገራት፡፡
ተንደላቆ ተቀምጦ የነበረው ዶክተር ወዳው ስራ የበዛበት ለመምሰል መራወጥ ጀመረ፡፡ ወዳው የቢሮ ስልኩን አንስቶ "አዎ ልክ ነው፤ ያው ክፍያው 2000 ብር ነው፤ 2:10 ላይ እጠብቅሀለው፤ አይ አሁን ቢዚ ነኝ በኀላ" እያለ መቀባጠር ጀመረ፡፡
ልክ ስልኩን እንደዘጋ ሁሉን ሲያዳምጥ ወደ ነበረው እንግዳ ዞሮ "ምን ልርዳክ?" ብሎ ጠየቀ፡፡
በፀሀፊዋ እንዲገባ የተነገረው ሰውም "አይ የተበላሸውን የቢሮክን የስልክ መስመር ልሰራ ነው የመጣውት" አለው፡፡ 😜😂
#ጭብጥ ፡- ያልሆንከውን መስለክ ለመታየት አትሩጥ ፊልም ሰሪ ሚደነቀውም ሆነ የሚወደደው ፊልሙ እስኪያልቅ ብቻ ነው፡፡
በሰዎች ለመወደድ፤ ዝናን ለማትረፍ ስትል ጭምብል ለብሰክ አትዙር፡፡ ተዋናይ መሆንክ የታወቀ ዕለት የሀፍረት ካባን ትለብሳለክ። ስለዚህ ከቦታና ከሁኔታዎች ጋር አብረክ አትለዋወጥ፡፡
@Readersworld11
@Readersworld11
@Readersworld11
በአለማችን ላይ ስለስኬት ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ቁጥር አንድ እንደሆነ የሚነገርለት የ “Thinkand Grow rich” ደራሲ ናፖሊዮን ሂል፤ ምንም እንኳን የምንፈልጋቸው ነገሮች ቢለያዩም ሁላችንንም ለስኬት የሚያበቁ ድንቅ መመሪያዮችን በመጽሃፉ አስፍሯል።
:
☞እናም እኛንም በመረጥነው የህይወት ጉዞ ላይ ከረዳን ብዬ አስሮቹን የስኬት መርህዎች ኸርል ናይቲንጌል ካሰናዳው ላይ እንዲህ አቀናብሬ አቅርቤያቸዋለው።
~
1."ፍላጎት(Desire)!"
:
☞የመጀመሪያው ደረጃ ፍላጎት ነው። ከልብ የመነጨ ፍላጎት፤ፍላጎታችንን እንደ ዘር ልናየው እንችላለን። ፍሬ እንደሚያፈራ አምነን የምንዘራው ዘር። ዛሬ ዘርተነው ዛሬውኑ ፍሬ የሚሰጠን ተክል የለም።
:
☞ፍላጎታችንም ልክ እንደ በቆሎ ወይም ማንኛውም ዘር ዛሬ ተዘርቶ በቂ ውሃ፤ በቂ ጸሃይ፤ በቂ እንክብካቤ ፤ካገኘ በኋላ በግዜው የሚያሽት ነው።
:
☞የምንፈልገውን ነገር ጥርት ባለ መልኩ ማወቁ ይጠቅመናል።
:
☞ለመረጥነው ነገር ምን ያህል ፍላጎት እንዳለን ለማወቅ የምናደርጋቸውን ነገሮች መቃኘት ያስፈልገናል።
:
☞ከምንም በላይ በውስጣችን ያለው የትዕግስት መጠን ፍላጎታችን ምን ያህል እንደሆነ ያስረዳናል።
:
❀ለምሳሌ ሰዓሊነት ፍላጎቱ የሆነ ሰው ባይከፈለው እንኳን ስዕል መሳሉን አያቆምም።
:
☞አላማ ብለን ለመረጥነው ነገር በቀላሉ ሊገደብ የማይችል ፍላጎት ሊኖረን ይገባል።
:
☞ጥልቅ ፍላጎት ማለት ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ የመመለሻውን ድልድይ እንደማቃጠል ያህል ነው።
~
2."እምነት(Faith)!"
:
☞እምነት አላማችን የሚገነባበት መሰረት ነው። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል።
:
☞ደግነቱ እምነት በመጀመሪያ ባይኖረንም፤ በሂደት ልንገነባው የምንችለው ጥበብ ነው።
:
☞ለአይምሮዋችን ቀና የሆኑ ነገሮችን በመመገብ እምነትን በሂደት ማዳበር ይቻላል።
:
☞የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት እምነት እጅግ ወሳኝነገር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
:
☞ማርቲን ሉተር ኪንግ ስለ እምነት ደስ የሚል አባባል አለው ” እምነት ማለት ሙሉውን ደረጃ እስከየት እንደሚደርሰን ባናውቅም እንኳን የመጀመሪያውን ደረጃ መውጣት ነው” ይላል።
~
3."እራስን ማሳመን-Auto Suggestion (አውቶ ሰጀሽን)!"
:
☞አይምሮዋችን እውነት ብሎ የሚቀበለው ነገር ደግመን ደጋግመን የምንመግበውን ነው።
:
☞እዚህ ላይ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ።
:
# ታሪኩ እንዲህ ነው:-
:
<ሁለት ውሾች የነበሩት አንድ ሰው ነበር።አዘውትሮ እኒህን ውሾች አደባባይ እየወሰደ እንዲደባደቡ ያደርግ ነበር። ታዲያ ተመልካቾቹ የትኛው ውሻ በእለቱ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቁት “በደንብ የምመግበው ውሻ ነው” ሲል መለሰላቸው። >>
:
☞ሁላችንም ውስጥ ሁለት ዉሾች አሉ:-
:
✔ የመልካም እና የክፋት፤
:
✔ የልማት እና የጥፋት፤
:
✔ የእውቀት እና የድንቁርና፤
:
✔ የውድቀት እና የድል ውሾች።
:
✔ የበላይ ሆኖ የሚመራን ውሻ ዘወትር የምንመግበው ነው።
:
☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል “አውቶ ሰጀሽን”ወይም ለራስ መልካም ነገሮችን ደጋግሞ በመንገር አይምሮዋችንን ወደፈለግነው መንገድ መምራት እንደምንችል የሚነግረን።መንገር ብቻም ሳይሆን የሚያሳስበን!
~
4."በአንድ ነገር ላይ እራስን የተካኑ ማድረግ(ስፔሻላይዝድ ኖውሌጅ)!"
:
<“Mastermind group- associate with men who know what you want to specialize in” ልንሰማራበት በመረጥነው ወይም ፍላጎት ባለን ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መተዋወቁ እና ቅርርብ መፍጠሩ ወሳኝ ነገር ነው።>
:
ጊዜያችንን የምናሳልፈው ከነማን ጋር ነው?
:
የምናውቃቸው ሰዎች ወይም ጓደኞቻችን ለምንፈልገው ሙያ የሚያግዙን ናቸው?
:
☞ለምሳሌ፦
፡
✔ ፕሮፌሰር ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው በተቻለው መጠን ዩንቨርሲቲ አካባቢ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነቱን ቢያዳብር ይጠቅመዋል።
:
✔ ተዋናይ መሆን የሚመኝ ሰው እራሱን ከቲያትር መድረክ አካባቢ ማራቅ የለበትም።
:
☞ሁላችንም የምንማረው ቀድመውን ካወቁት ነውና፤ የምንፈልገውን ነገር በቅጡ የሚያውቁ ሰዎችን ማወቁ ይጠቅመናል።
~
5."ነገሮችን በህሊናችን መሳል!"
:
☞“Imagination- It’s the workshop, the impulse. men can create what he can imagine. what the mind conceives it achieves”. ሁሉም ነገር ሃሳብ ነበር። ምንም ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በአንድ ሰው አይምሮ ውስጥ የተጠነሰሰ ሃሳብ ነበር።
:
☞የምንፈልገውን ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በህሊናችን መሳል ትልቁ የስኬት ሚስጥር እንደሆነ ብዙዎች የተስማሙበት ነው።
:
☞አላማችን ቁልጭ ብሉ በህሊናችን ከታይን ለጉዞዋችን ትልቅ ጉልበት አገኘን ማለት ነው። ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚሳካ አይምሮዋችን እየነገረን ነው።
~
6."እቅድ ማውጣት-Organized planning!"
:
☞እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ከማድረጉም በላይ፤ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ እየወጣን ጉዞዋችን አድካሚ እንዳይሆን ያደርግልናል።
፡
☞እቅድ ስናውጣ ነገሮች ሳይደራረቡብን ቀስ በቀስ ወደ ግባችን እንደርሳለን።
፡
☞እቅድ ስናወጣ ግን እራሳችንን በሚያጨናንቅ እና ካልፈጸምነው የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን በሚያደርግ ሁኔታ ሳይሆን፤ ከጊዜያችን ፤ ከባህሪያችን እንዲሁም ከማንነታችን ጋር የሚስማማ እቅድ ነው ማውጣት አለብን። ምክንያቱም ሌላው ያቀደበት መንገድ ለኛ ላይስማማ እና ከግባችን ላያደርሰን ስለሚችል።
~
7."ውሳኔ-Decision!"
:
☞“lack of decision is the top reason for failing. if you make a decision its worth sticking toit. don’t let others opinion to sway you” .የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስዔ የውሳኔ ማጣት ነው። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው፤ ምንም ይህል የሚያስደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም።
፡
☞ውሳኔ በማጣት የተነሳ ብዙ ሙዚቃዎች ሳይሰሙ፤ ብዙ መጽሐፎች ሳይጻፉ፤ ብዙ ግኝቶች ሳይገኙ፤ ወደ መቃብር ይወርዳሉ።
፡
☞በሁላችንም ውስጥ ለኛ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አለ፤ ይህን ስጦታ ግን አውጠን ሌሎች እንዲያዩት ማድረግ የምንችለው ውሳኔ መወሰን ስንችል ብቻ ነው።
፡
☞የምንወስነው ምንድን ነው ካላችሁ፤ መልሱ የምንወስነው መሆን የምንፈልገውን ነው።
~
8."ጽናት-(Persistence)!"
:
☞“the power of will. This quality distinguishes the success from the failure. it’s a state of mind and can be cultivated”. ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም። ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው። ብዙዎⶭችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን አንገፋበትም።
:
☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የወድቀት እና የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው።
:
✔ለምሳሌ ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንምዋጋ የለውም።
:
☞ስለዚህ በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው።
~
9."ጥምር ሃይል-(Power o
።።።።።።።።።።።ሞሮ።።።።።።።።።።።።
።።።።።።፡።።።ክፍል 2።።።።።።።።።።፡፡
✍✍✍✍ፀሃፊ ረምሃይ✍✍✍✍
በላይ ኤቤጊያ ብሎ ሲጣራ በድንጋጤ ብዛት ጭልፊት እንዳየች አይጥ ዘልዬ ወደውስጥ ገብቼ አልጋዬ ውስጥ ተደበቅኩ። በላይ ማለት በጣም እሚያናደኝ ልጅ ነው ኤቤግያን እንደምወዳት አውቆ ሁሌም ይፈታተነኛል ሞኝ የሆነ ልጅ ነው ፍቅር የማይገባው ብዙ ግዜ አንስማማም። ሁሉም የዶርም ልጆች ሁኔታዬን እያዩ ይበልጥ ተሳሳቁብኝ ተናድጄ ተነሳውና በላይን ምን መሆንህ ነው ምትጠራት አልኩት መልስ አልሰጠኝም ዝምብሎ ይገለፍጣል ድሮም እንዲው ነው ከማግጠጥ ሌላ ምንም አያቅም ጅል!!! ወደ አልጋዬ ተመለስኩና በመስታወቱ በኩል ሆኜ ስታልፍ አየኃት አዬ እዳ ምን ቀን ነው ያየኃት። ኤቤጊያ ካለፈች በኃላ ሁሉም ወደ ውስጥ ገቡ ኪያር ና ምሳ እንብላ አለኝ ወደ አልጋዬ አጮልቆ እያየ አልበላም አልኩት እሺ ብሎኝ ሄደ ኪያ ደስ እሚለኝ ለዚ ነው መጨቃጨቅ መጋተት ምናምን አይመቸውም እኔም አልወድም አልፈልግም ካልኩ አልኩ ነው ተመልሼ እንቅልፌን ለጠጥኩ። 10፡00 ሰአት አከባቢ ከእንቅልፌ ነቃው ዶርም ማንም የለም ሁሉም ክላስ ሄደዋል ከአልጋዬ ተነሳውና ወደሎከሬ ሄድኩ ልክ ሎከሩን ስከፍተው ሁለት ትንንሽ አይጦች ጫማዬን እያጣጣሙ ሲግጡት አየው ልክ እኔን ሲያዩ ተፈትልከው በእግሬ ስር እየተሽሎከሎኩ ፈረጠጡ እማማዬ .... ብዬ ለጉድ ጮህኩ ሲያስጠሉ ቀፋፊዎች ነብሴ መለስ ስትል ዝርክርክ ካለው ልብሶቼ ውስጥ እምለብሰውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ ሁሉም ልብስ ከታጠበ በጣም ቆይቷል በግ በግ ይሸታል ደና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ አደል ያለችው አያቴ ከበክት ውስጥ ትንሽ የበከተውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ አንድ ድሮ ሳውቀው ነጭ የነበረ አሁን ግን መንችኮ ቡኒ የሆነ ሰፊ ሸርት አገኘው ለበስኩት ከታችም ቆሻሻ የቃመ ሰፊ ሰማያዊ ጅንስ አርጌ ቅድም አይጦቹ የገጠቡትን ጫማ ያለካልሲ አድርጌ ከዶርም ወጣው ወዴት እንደምሄድ አላውቅም እግሬ ወደመራኝ ብቻ ከዚ ግቢ ውጪ ብቻ ይሁን ድንዝዝ ብዬ ከግቢያችን ወጣው ናዝሬት የለመደባትን ፀሃይ በአናት በአናቴ ትለቅብኛለች። የግቢያችንን በር አልፌ ፊትለፊት ወዳለው ሱቆች ሄድኩ ባለሱቁ ደስታ ሁሌም ያቀኛል ሳልጠይቀው አንድ ፓኮ ሲጋራ እጄ ላይ አስቀመጠልኝ ብሩን ከኪሰ በርብሬ አውጥቼ ከፍዬው መንገዴን ቀጠልኩ የግቢያችን ተማሪዎች ታክሲ አጥተው መደዳውን በር አከባቢ ተደርድራው ይጠብቃሉ አንድ ኮሳሳ ታክሲ ስትመጣ ተሯሩጠው እየተጋፉ ይገባሉ። በእግር መንገዴን ወደ መብራት ሃይል አደረኩ ደስታ ከሰጠኝ ፓኮ ሲጋራ ፈልቅቄ አንዷን አውጥቼ አፌ ላይ ሰክቼ ኪሴ ውስጥ ክብሪት ፍለጋ ማሰንኩ የቅድሙ ሱሪ ውስጥ እንደረሳሁት ትዝ አለኝ ተበሳጨው አከባቢዬ ላይ የእሳት ምንጭ የሚገኝበት መንስኤ ማሰስ ጀመርኩ ከርቀት አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ልጅ በተሰበረ ምድጃ እሳት ስታቀጣጥል አየው እየሮጥኩ ወደሷ ሄድኩ እሙዬ እሳት ልጫር አልኳት እሺ አለችኝ ሲጋራውን ከአፌ ሳልነቅል አጎንብሼ አፌ ላይ እንዳለ የእንጨቱን ጭስ እየታጠንኩ ለኮስኩት ልጅቷ ገርሟት ታየኛለች እኔ ግን መንገዴን ቀጠልኩ ብቻዬን በሃሳብ አለም እየዋለልኩ እግሬ ወደሚወስደኝ ቀጠልኩ። ኤቤጊያን እንዴት እንደዚ እስከምሆን ድረስ ላፈቅራት ቻልኩ ሁሌም ስለሷ ሳላስብ አይነጋም አይመሽም እሚገርመው ግን እሷ እኔ አይደለም እንደምወዳት ቀርቶ ማን እንደሆንኩ እንኳን አታውቅም ኤቤግያ የአዲስ አበባ ልጅ ናት እኔም የዛሬን አያድርገውና የፒያሳ ልጅ ነበርኩ ነቄ ሁሉን ያየው ግን ምን ያደርጋል ፍቅር ሲይዝ ሳያስጠነቅቅ ነው ልክፍት ነው የኔማ ሳያት ሁላ እምገባበት ነው ሚጠፋኝ። እንዲ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ መብራትሃይል አከባቢ ደረስኩ ግማሹ ፓኮ ሲጋራ አልቋል ሆዴን በምግብ ሳይሆን በጭስ የሞላሁት መሰለኝ ከነጋ አልበላሁም 11፡30 ሆኗል ሆዴ ያኮረፈ ይመስል ያጉረመርማል አስፓልቱ ዳር ካሉት የተቀቀለ ድንች ሻጮች ጋር ሄድኩና ሁለት እንቁላል በዳባና ሚጥሚጣ እዛው አጠገባቸው አስፓልት ዳር ሆኜ በላውና ተነስቼ መንከራተቴን ቀጠልኩ ድንገት የሞባይል ቤት አየውና አንድ ሃሳብ መጣልኝ ለአቤጊያ ብቻ እምደውልበት አዲስ ሲም ማውጣት! ወደሱቁ ገብቼ አንድ አዲስ ሲም ገዝቼ ወጣው ከዛ ወደለመድኩት ባር ሄድኩ ድራፍቴን ስጋት ስጋት ስጋት አመሸው ማታ ላይ ወደግቢ ስመለስ አዳልጦኝ አንድ ቱቦ ውስጥ ወደቅኩ በቆሻሻ ውሃ ጨቅይቷል ኤጭ የራሱ ጉዳይ! እዚው አድራለው ቀን የገዛሁትን ሲጋራ በጣም የሚሸተው ውሃ ውስጥ ካለው ኪሴ አውጥቼ ያልበሰበሱትን አውጥቼ ባር ውስጥ በተቀበልኩት ላይተር ለኩሼ ሁሉንም አፌ ውስጥ ሞጀርኳቸው ....
@Readersworld11
@Readersworld11
ክፍል ሶስት እንዲቀጥል
ከተመቻችው #Share
#Share
Inbox 👉@Kirubeljr
ƒrom my memo page
"ምንም እንኳን ብሩህ አዕምሮ ቢኖርህም ይህ አዕምሮህን የምታቆጣጠርበት ታላቅ ሃይል ያስፈልግሃል እሱም አስተዉሎትህ ነዉ።" @Kirubeljr
©✍Kirubel
❤️❤️❤️❤️❤️ ❤️ ❤️❤️❤️❤️❤️
❤️❤️❤️❤️ ትርታዬ ❤️❤️❤️❤️
❤️❤️❤️ የመጨረሻ ክፍል ❤️❤️❤️
❤️❤️❤️❤️❤️ ❤️ ❤️❤️❤️❤️❤️
ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ
ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ
አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን
አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው
ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው
የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ
የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ
በፀሎት አልተለዩትም እንደምታስታውሱት በክፍል ሀያ አምስት
ላይ ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት
አንስቶ አስታማሚው ብሩ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ
ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን
ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን
ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ
ታጥበው ነበር.............
@Readersworld11
.........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል
እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው
አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ቅዱስን
አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ
ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም
የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን
ለመዋጥ ስታስብ ብሩክ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ቅዱሴ
ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ
ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ
ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት
እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ
ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ
ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች
ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም
አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ
እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ
ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም
ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ
በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ብሩክ ነኝ በቤትስልክ
ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የ ብሩክ ድምፅ
ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም
አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ
12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ
አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ
እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ቅዱስ ተመልሶ
መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም
ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ..........
ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው
ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ
ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን
እያየች ብሩክ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት
ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ
ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች......
......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም
ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር
ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ብሩክ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን
ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮን ነበረ
ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም
ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ
የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ
በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ
ድኖ ጋቢ ለብሶ ከ ብሩክ ቡሀላ እየተራመደ መጣ...........
............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ
በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው
መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ
ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮን
አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮ
እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ
መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ
ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ
እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮ
አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር
በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ
ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች
ጌዲዮ ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ
ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም
እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ
አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር
የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው
ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው
የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮም ቤተሰቦቿ
መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ
ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን
ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ
ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ
እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር
ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ ቅዱስ ሲያይ ጠጋ ብሎ
እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው
ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ
ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ
አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም
አላቸው..............
@Readersworld11
.............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ
እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ
እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ
ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ
እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት
በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ
ስለሚውምመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ
ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ
አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች
አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር
እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮ የመቅደስ
ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት.......
........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም
በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ
አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ
ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር
አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ
ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........
@Readersworld11
.......በተባሉበት ቀንም አ.አ ተመለሱ ሲመጡም እየተደገሰ
የነበረው ድግስ የሰርግ ይመስል ነበር ከዛም የጌዲዮም
የመቅደስም ጉዋደኞች የ
የመቅደስ እናት
https://telegra.ph/ሰዎች-ስለአካባቢያቸው-ስለኀብረተሰቡና-ስለ-ቁስ-አካላዊው-ዓለም-ባጠቃላይ-የሚኖራቸው-አስተሳሰብ-ርዕዮተ-ዓለም-ይባላል-የእርስዎ-ርዕዮተ-ዓለም-ምንድነው-10-30
@Readersworld11
@Readersworld11
።።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።ክፍል 23።።።።።።።።።።
.......መቅደስና ጌዲዮ በብዙ ፈተና ሶስት አመት በፍቅር አሳልፈው አራተኛው አመት ግን አስጊ ሆኗል ጌዲዮ የጓጓለትን ያምስተኛ አመት ትምህርቱን መጨረስ አልቻለም ዋና የሚባለውም ፈተና አምልጦታል ከሆስፒታ ወጥቶ እንዲፈተን መቅደስ ዶክተሩን ብትለምነውም ለሂወቱ አስጊ ስለሆነ እንደማይወጣ ነግሯት እሷም አልፈተንም ብትልም ጌዲዮ በፍቅሩ ለምኗት ፈተናዋን ለመፈተን ጅማ ተመልሳ ዛሬ ወደ አ.አ መጥታለች ሙሉ የህክምናውን ወጪ ችለው እያስታመሙት ያሉት የመቅደስ ቤተሰቦች ናቸው እናቱም ከክፍለ ሀገር መጥተው አብረውት ነው ያሉት ጌዲዮ ከራሱ በላይ የናቱን ህልም አለማሳካቱ ተስፋ አስቆርጦታል መቅደስም በሱ መታመም ሌት ተቀን እያለቀሰች በድን ብትሆንም ዛሬም ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚመረቅ ተስፋ ትሰጠዋለች.......
......ዛሬ ውጤትህ ይመጣል ስለዚህ ለዩኒቨርስቲው አሳውቀን ብትዘገይም ትፈተናለህ እሪሰርችህንም ቢሆን ትጨርሰዋለህ አለችው መቅደስ የፍርሀትና የደስታ ስሜት እየታየባት የጌዲዮ እናትም እንዳፍሽ ያርገው አሏት የሱዋም አባት እንደዛው ጌዲዮ ግን ውስጡ ጤነኝነት እየተሰማው ስላልሆነ የሚመጣው ውጤት ጥሩ ይሆናል ብሎ መገመት ተስኖታል ብቻ ባጠቃላይ አፋቸው መልካም ቢናገርም ውስጣቸው ፈርቷል ሰአቱ ሲደርስም መቅደስና አባቷ ውጤቱን ለመስማት የዶክተሩ ቢሮ ሄዱ እንዲቀመጡም ከጋበዛቸው ቡሀላ ዶክተሩ ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶት አይን አይናቸውን ያያቸው ጀመር ውስጣቸው ይበልጥ ተረበሸ ዶክተር ችግር አለ እንዴ አሉት ........
.......እየውላቹ ይህ ዜና ለናንተ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ግዴታ መናገር ስላለብኝ ስሙኝ ጌዲዮ የጭንቅላት እጢ ታማሚ ነው መቅደስ አፏን ይዛ እየተንቀጠቀጠች ምን አለች አዎ ህክምናውን በጊዜ ጀምሮ መዳኒት ስላልወሰደም በሂወት የመኖር ጊዜውን አጥቦታል መቅደስም ሆነች አባቷ እንባቸው ድንገት እንደሚጥል በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ዱብ ዱብ ይል ጀመር መቅደስ በልህ ድምጿን ከፍ አድርጋ እና ይሞታል ልትለኝ ነው አለችው ዶክተሩም አላልኩም የምትችሉት ከሆነ አንድ እድል አላችሁ አላቸው አባቷ እንደምንም አረጋግቷት ምንድነው ንገረን ብቻ ጌዲዮ ይዳን እንጂ የሆነውን ይሁን ለመፈፀም ዝግጁ ነን አሉ ባስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት መቅደስ አይሆንም ብላ ይበልጥ ጮኸች ችግሯ ህመሟ ቢገባውም መረጋጋት ባለመቻሏ ዶክተሩ ተናደደ መቅደስ አዳምጪኝ ቀዶ ጥገናው እዚህ ሀገር አይሰጥም ይህ ማለት በዚህ አራት ወር ውስጥ ካገር ወጥቶ ቀዶ ጥገናውን ካላደረገ በሂወት መኖሩ አስጊ ነው ለህክምናው ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብሎ ሃሳቡን በቁጣ ገልፆ ቁና ተንፍሶ ላንዴ ዝም አለ መቅደስና አባቷም በህልማቸው እስኪመስላቸው ደርቀው ቀሩ ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ..........
......ከወጡ ቡሀላ መቅደስ ተዝለፍልፋ ወደቀች ነርሶችም ተሯሩጠው አንስተው አስተኟት ስትነቃም ሁሉም ቤተሰቦቿ ተሰብስበው ነበር አባቷ ነግሯቸው ስለነበር ሁሉም አይናቸው በንባ ብዛት በርበሬ መስሎ ነበር እማ ሁለት ሚሊዮን ያስፈልጋል አሉ እኮ አለቻት የቤተሰቦቿን አይን አይን እያየች እህቷም እሷን ለማፅናናት ያንቺ እንዲህ መሆን እኮ ብር አይሆንም ይልቅ ብሩን እንዴት ማግኘት እንዳለብን ብናስብ ነው የሚሻለው ስትል እንዴ ከየት ነው የሚመጣው አለች መቅደስ ቀጥሎም ቅብጥብጡ ወንድሟ ሲስቱ ተነካሽ እንዴ ሁለት መቶ ሺ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሀገር እንዴት ብለሽ ነው ሳይጨርሰው የሁላቸውም ታላቅ የሆነው በረከት ከየትም ብለን አግኝተን መታከም አለበት እናትየዋም አዎ ቤታችንንም ቢሆን ሸጠን እናሳክመዋለን ማሟያ ደግሞ ሁላችንም አካውንት ያለውን ብር እናወጣለን ካልሞላም ብድር አናጣም የሚል ተስፋ ለመቅደስ ሰተዋት ከዛን ቀን ጀምሮ በየፊናቸው ብሩን ማፈላለግ ጀመሩ ብዙ ወጪ ስላወጡ የሁሉም አካውንት ውስጥ የተገኘው ብር ስድስት መቶ ሺ ብቻ ነበር ቤቱም ያሰቡትን ብር ሊያወጣ አልቻለም........
.........ሌላ ህመም እንዳይሆንበት ስለፈሩ ነገሩን ለጌዲዮ እስካሁን አልነገሩትም እናቱ ግን ቢሰሙም ደጀ ሰላም እየሄዱ ደጅ ከመፅናት ፈጣሪን ከመለመን ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም ዘወትር የመቅደስን ቤተሰቦች ሲያዩ እንዲህም አለ ወይ ይላሉ ጌዲዮንን ለማሳደግ ያዩትን መከራ እሳቸውና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው እንኳን የባለቤታቸው ዘመዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸውም ሰላምታ ሰተዋቸው እንኳን አያውቁም የጌዲዮ እናት ያለፉትን አመታት ሲያስታውሱ ደም እንባ ያለቅሳሉ ቢሆንም ፈጣሪ እንደሰው አይደለም ይኸው እነመቅደስን ሰጣቸው እውነት በዚህ ሰአት ብቸኛ ቢሆኑ ኖሮ ጌዲዮ ነብሱ ባልተረፈች ነበር ግን ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ..........
.......ግን ምንም እንዳሰቡት ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ቤቱንም የሚገዛ አጡ ቢያገኙም የሚጠሩላቸው ዋጋ ለቤቱም ለህክምናውም አይመጥንም በቲቪና በራዲዮንም ማስታወቂያ ሊያሰሩ ቢጠይቁም የጠየቋቸው ገንዘብ ከባድ ነበር በዛላይ ዶክተሩ ያለው ግዜ አጭር ስለሆነ በፍጥነት ፕሮሰስ መጀመር እንዳለበት እየነገራቸው ነው አሁንማ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው የሚገቡበት ጠፍቷቸው ወደፈጣሪ እግዚኦ እያሉ ነው........
.........ሁኔታቸው ግራ ያጋባው ጌዲዮ ቅብጥብጡን ቅዱስ ብቻውን ሲያገኘው ቅዱሴ አለው ወዬ ጌዲ አለው የህክምናውን ውጤት ንገሩኝ ስላቸው ደና ነው አሉኝ ደና ከሆንኩ ለምን አልወጣም ስላቸው አይ ትወጣለህ ይሉኛል ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም ተረብሻችኋል ምን ሆናችሁ ነው በጭንቀት ማለቄ እኮ ነው ሲለው ያው ቅዱስ እስካሁንም ያላወራው አፉን ይዘውት እንጂ ወሬ የሚባል አይደብቅም እናም ምን ባክህ የጭንቅላት እጢ አለበት ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ለዛ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለውን ተፍ ተፍ እያልን ነው ብሎ ካልታከመ መሞቱ እንደማይቀርም ፍርጥርጥ አርጎ ነገረው ጌዲዮ ተስፋ ቆርጦ እና እሞታለሁ አለው አረ ላሽ ትታከማለህ ደሞ ቤታችን ሊሸጥ እየተስማማ ስለሆነ እግዚያብሄር ከረዳን ብሩ ይገኛል ጌዲዮ ከመቅፅበት ህመሙ ተነሳበት.........
ይቀጥላል 👍
ሼር በማድረግ ሌሎችን ወደ ቻናላናችን ይጋብዙ
@Readersworld11
@Readersworld11
Inbox @Kirubeljr
💥💥💥ገምሃልያ 💥💥💥💥
#ክፍል 2⃣ መልካም ንባብ
#ተከታታይ ልቦለድ
ሲጋራውን ተቀብላኝ መሬት ላይ አስቀመጠችው እጇን ለሰላምታ ዘርግታልኝ ፅናት እባላለው አለችኝ የዘረጋችው እጇን ጨብጬ ሰላም አልኳትና ረምሃይ ብዬ ስሜን ነግሪያት ቦታዬ ላይ ተቀመጥኩ። ያመጣሁትን መፅሃፍ ገፆች ገልጬ ማንበብ ቀጠልኩ ብዙም ሳይቆይ ግን ፅናት መናገር ጀመረች። ብዙ ግዜ ሰው ራሱ እስካልነገረኝ ድረስ በግድ እንዲያወሩ ማድረግ ብዙም ደስ አይለኝም። ምን እንደሚያስገርመኝ ታውቃለህ አለችኝ ወደሷ ዞሬ እያየኃት ምን አልኳት። ታውቃለህ ህይወት ለኔ በጣም በፈተና የተሞላች ናት አንድም ቀን እንኳን ለራሴ ኖሬ አላውቅም ሁሌም ለታድኤል ስል ነበር እምኖረው እሱ ግን እሱ....ግን.... አለችና ትካዜ በተቀላቀለበት ሃሳብ ውስጥ ተዋጠች።
ከታድኤል ጋር ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቅንበትን ቀን መቼም አልረሳውም አስታውሳለው እለቱ ቅዳሜ ነበር ጠዋት ከስራ እንደወጣው ሜክሲኮ አከባቢ የምትገኝ ሃናን የምትባል ውድ ጓደኛዬ ቤት ሄጄ ከሷ ጋር ስንጨዋወት አረፋፍደን ምሳ ሰአት አከባቢ ወደቤቴ ልሄድ ተሰናብቻት ወጣው። ሜክሲኮ አከባቢ ወደ ፒያሳ የሚወስደኝን ታክሲ የምይዝበት ቦታ ሄድኩ ታክሲዎቹ ምን እንደነካቸው አላውቅም አለወትሮዋቸው ጥፍት አሉ። ብቻዬን በዛ በጠራራ ፀሃይ ታክሲ መጠባበቅ ጀመርኩ የፀሃዩ ብርታት ነው መሰለኝ ራሴን ያመኝ ጀመር በዚ አጋጣሚ አንድ ረዘም ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ሰው ከኃላዬ መጥቶ ቆመ ደንገጥ ብዬ ዞሬ አየሁት ጥቁር ኮፍያ እና መነፅር አድርጓል ሰውነቱ የለበሰውን ነጭ ቲሸርት ውጥርጥር አድርጎታል እሚያምር ችምችም ያለ ፂም አለው እንዳየሁት ሌቤ ደንገጥ ሲል ታወቀኝ። ሳላስበው ብዙ እንዳፈጠጥኩበት ሲገባኝ እንደማፈር እያለኩ ዳግም ጀርባዬን ሰጥቼው ቆምኩ። ሁለታችንም ፊትና ኃላ ሆነን ታክሲዎቹን ብንጠብቅን ምንም ሊመጡ አልቻሉም ነዳጅ ጠፍቶ ይሆናል እንዲ የጠፉት አልኩ በልቤ። ወደኃላ ዞሬ አየት አድርጌው ተመለስኩ ላወራው ፈለግኩ ግን ፈራሁት ሁሉ ነገሩ ልብ እሚያስደነግጥ ግርማ ሞገስ አለው። ድንገት ሳላስበው ከኃላዬ ጎርነን ያለ ድምፅ ዛሬ ፀሃይዋ ከነቤተሰቦቿ ነው መሰለኝ ተጠራርታ የመጣችው አለኝ ዞር ስል እሱ ራሱ ነበር ፈገግ ብዬ እንደመሳቅ እያልኩ አው ዛሬ ሃይለኛ ሆናለች ምን እንደታያት አልኩት እሱም መልሶ እየሳቀ ከታላቅ እህቷ ጋር ነው መሰለኝ የመጣችው አለኝ። ምን ለማለት እንደፈለገ ባይገባኝም ከት ብዬ እንደሞኝ ሳቅኩ። የኔ አሳሳቅ እሱንም አሳቀው መሰለኝ እሱም ሳቀ። ሲስቅ ጥርሶቹን በጨረፍታ አየኃቸው በጣም ያምራሉ በጣም ማረከኝ ያደረገው ጥቁር ኮፍያና የፀሃይ መነፅር፤ ቅርፅ የተበጀለት ችምችም ባለው ፂሙ መሃል ጥርሶቹ ፍልቅቅ ብለው ሲታዩ ልብን ያሸፍታሉ የደስደስ ያለው ደስ እሚል ሰው ይመስላል። እሱን ሳስብ ራስምታቴ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ረስቼው ነበር ድንገት ትልቅ ህመም ተሰማኝ ቀጥሎ የተፈጠረውን አላውቅም ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር ወደራሴ ተመልሼ ስነቃ ጣላ ያለበት ዛፍ ስር ተኝቻለው መጀመሪያ የየሁት የእሱን ፊት ነበር! ቀና አድርጎኝ የያዘውን ሃይላንድ እላዬ ላይ እያርከፈከፈልኝ ነበር ፊቱ ላይ ድንጋጤ ይነበባል። መንቃቴን ሲያይ ደና ነሽ እሙዬ ምን ሆነሽ ነው አለኝ ለመነሳት እየተጣጣርኩ ፀሃዩ ነው መሰለኝ አልኩትና ለመነሳት ስንደፋደፍ አይቶኝ ቆይ ተረጋጊ አሁን ጥላ ቦታ ላይ ነን ትንሽ አረፍ ብለሽ ራስሽን ካረጋጋሽ በኃላ ትሄጃለሽ አለኝ እምቢ ብዬው ተነስቼ እምሄድበት አቅም አልነበረኝም ከአፉ የሚወጡት ቃላት የንጉስ ትእዛዝ ይመስል እምቢ ማለት ከበደኝ።
..........ይቀጥላል.......
✍ፀሃፊ - ረምሃይ
ቀጣዩን#ክፍል3⃣እንዲቀጥልLike👍ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Kirubeljrአድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@Readersworld11
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖📖
🙏ሰላም ዉድ የ ደራሲዉ ቤተሰቦች #ከዛሬ ጀምሮ አዲስ ተከታታይ ልቦለድ የምናቀርብላቹ መሆኑንን ስንገልፅ በደስታ ነዉ ።
📖ልቦለዱ ዘወትር ከሰኞ~እሁድ ምሽት ላይ ይቀርባል ።
👉አብሮነታቹን አሳዩኝ🤙
#ርዕስ#
(ገምሃልያ)
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@Readersworld11
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖📖📖
።።።።።። ሞሮ ።።።።።።።።።።።።
።።።።።።ክፍል 4 ።።።።።።።።።።፡
ልቤ በጣም ይመታ ጀመር ከኤቤጊያ ጋር ያለው ራስታ ፀጉር ወንድ እጁን ቀስ ብሎ ወገቧ ላይ ጣል አረገው እሷም ወደሱ ተጠግታ እቅፉ ውስጥ ገባች በልቤ የአጎቷ ልጅ እንዲሆን ፀለይኩ እኔና ኪያር እሚሆነውን ነገር በፅሞና እያየን ነው እኛ እናያታለን እሷ ግን አታየንም። ራስታው ልጅ ወደጆሮዋ እየተጠጋ የሆነ ነገር ያንሾካሹካል እሷ በሳቅ ትፈርሳለች ልቤ ይቃጠላል ልጁን ጠላሁት ቀጥሎ ቀስ እያለ ፀጉሯን በእጁ ይጠቀልለው ጀመር። ወደ ኪያ ዞሬ እየተበሳጨው ይሄንን ራስታ ታቀዋለህ ምኗ ነው አለኝ ኪያ ራሱን በአሉታ ነቀነቀ። ራስታው ልጅ ጅንን ብሎ እያዋራት እያለ ኤቤጊያ ድንገት ከንፈሩን ስትስመው አየው ከዚ በላይ መቀመጥ አልቻልኩም ተነስቼ እየሮጥኩ ስሄድ ኪያ ናዲ ብሎ ሲጠራኝ ልሰማው አልፈቀድኩም እነኤቤጊያም መሳሳማቸውን አቁመው አዩን ወዱያው ከአከባቢው ጠፋው ጨለማ ውስጥ ብቻዬን ቁጭ ብዬ እንደጉድ ተነፋረቅኩ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዚ አለም ላይ ትልቁ ህመም የሚወዱት ሰው ሌላ ሰው ሲወድ ማየት ነው ቅስሜ ተሰበረ እንደዛ ሆኜ ወደ ዶርም መመለስ አልፈለኩም ከግቢ ወጣው። ከግቢያችን ፊትለፊት የሚገኘው የሓና ባርና ሬስቶራንት ሄጄ ሙሉ ኮኛክ አውርጄ አንጀቴ እየተቃጠለ ገለበጥኩት ሙሉ ሰውነቴ ሲደነዝዝ ቀስበቀስ ይሰማኛል እኩለ ለሊት ላይ ጠርሙሴን ይዤ እየተንገዳገድኩ ወጣው ሁሌም ከራሴ መደበቅ ስፈልግ እምሄድባት ሺሻ ቤት አመራው ቤቷ ባለሁለት ክፍል ሆና በብዙ ጀዝባዎች ታጭቃለች የሺሻው የሲጋራው የጋንጃው የአጠፋሪሱ ጭስ ማንንም ከማንም እንዳይተያይ የጋረደው ይመስላል በዛ ላይ በዛ ለሊት በደብዛዛ መብራት ጭሱም ተደምሮ ለመተያይተ ከባድ ነው። እየተንገዳገድኩ ገብቼ ባዶ ፍራሽ ላይ ተቀመጥኩ ቤቷ በዝምታ ተውጣለች ሁሉም በየራሱ አለም ይማትታል ትንሽ እንደተቀመጥኩ ገራቢዋ መጥታ ምን ላምጣልህ አለችኝ የተለመደውን አልኳት የገለምሶ ጫትና ሺሻዬን ይዛልኝ ከተፍ አለች እያፈራረቅኩ እየነፋው እዛው ተኛው። ጠዋት ላይ ከፍተኛ ሁካታ ሰምቼ ደንግጬ ተነሳው ቤቷ ፀጥ ብላለች ማንም የለም ከውጪ አንድ አራት ወንዶች እየተንጫጩ ወከባ እየፈጠሩ ገቡ ከነሱ ውስጥ ትናንት ማታ ከኤቤጊያ ጋር የነበረው ራስታ ልጅ ነበር ገብተው እየተንጫጩ ፊትለፊት ተቀመጡ ደንዤ ስለነበር የልጆቹን ማንነት መለየት አልቻልኩም ዝም ብዬ ለሊት የጀመርኩትን ጫት መቃም ቀጠልኩ ልጁ እንዲው ለአይኔ ቀፎኛል አስጠልቶኛል ትንሽ እየተንጫጩ በሃላ ሺሻቸውን እየነፉ በመሃል አንደኛው እእእእ እንዴት ነበረች ኤቤጊያ ትናንት ማታ እ ሸራ ስትጓተች አለው ስሟ ሲነሳ ድንግጥ አልኩ ራስታው ልጅ ጅንን ብሎ የሳበውን ጭስ ሽቅብ እየለቀቀ ባክህ ተዋት ምንም አትልም አለው ልጁም ቀበል አድርጎ አረ ... ኤቢን የመሰልች ልጅ አጊንተህማ ሲለው ባክህ ከሌሎቹ አትለይም ተራ ሴት ናት ሲል ደሜ ፈላ ድንገት ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩና ተራ ሴት አይደለችም እሺ...!! ብዬ ጮህኩበት ሁሉም ሳያስቡት ስለጮህኩ ደነገጡ ራስታው ልጅ ከደነገጠ በኃላ መሳቅ ጀመረ ድጋሚ ሺሻውን እየማገ ጭሱን ወደላይ እየተፋ ሃ..ሃ..ሃ..ሃ.. የት ታቃታለህ ምን ያገባሃል ስለሷ አለኝ በንዴት በቆምኩበት የሺሻውን እቃ አነሳሁት ሁሉም ከመቀፅበት ብድግ ብድግ አለና ምን ልትሆን ነው? እእእ ምን ልትሆነው አሉ ለመደባደብ እየተዘጋጁ ሁሉም ቢያቅቱኝም ራስታውን ልጅ እንደምፈነክተው እርግጠኛ ነበርኩ ንዴቴ ረገብ አለልኝና የሺሻውን እቃ አስቀመጥኩና ወደበሩ አመራው እነሱም እየተሳሳቁ ተቀመጡ የማን ድምፅ እንደሆን ባላቅም "ሞሮ" አለኝ ወደበሩ ከዞርኩበት በመቀፅበት ተመልሼ የሺሻውን ጠርሙስ የራስታው ልጅ አናት ላይ በተቀመጠበት ከሰከሱበት ድብድብ ተጀመረ ቤቷ በአንድ እግሯ ቆመች።
ክፍል 5 ይቀጥላል..........
ፀሃፊ አል ረምሃይ
ከተመቻችው 👍👍👍 ማድረግ አትርሱ ለጓደኞቻችሁም ሸር ማድረግ አትርሱ
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
👉 @Readersworld11
👉 @Readersqorld11
👉 @Reafersworld11
for ur suggestion
👉@Kirubeljr
።።።።።።።።።።።ሞሮ።።።።።።።።።
።።።።።።።ክፍል 3።።።።።።።።።፡፡
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ያለሁበትን ቦታ በደምብ አላውቀውም ብቻ ግማታም ቱቦ ውስጥ ተኝቼ እንዳደርኩ ገባኝ ሰውነቴ በጣም ይሸታል ለእይታም ደስ አይልም ተነስቼ ታክሲ ወደምንይዝበት ቦታ አመራው ሰዉ እያየ ሲጠየፈኝ በደምብ ይታወቀኛል ታክሲው ጋር ደርሼ ልገባ ስል ወያላው አፍንጫውን ይዞ አይቻልም ብሎ በሩን ዘጋብኝ ምንም አልመሰለኝም እንደለመድኩት በእግር መንገዴን ቀጠልኩ ግቢ አከባቢ ስደርስ ኤቤጊያ ከጓደኞቿ ጋር ከግቢ ሲወጡ ከርቀት አየኃት በጣም ደነገጥኩ እየሮጥኩ ወደኃላ ተመልሼ እየሮጥኩ ጠፋው እሷን ሳያት ለምን ፍርሃት እንደሚከበኝ አላውቅም አይደለም በቅርበት አይቻት ቀርቶ በሌለችበት ስሟ ሲነሳ እደነግጣለው ምን እንደሚሻለኝ አላውቅም። በራሴ በጣም ተናደድኩ ለአንዲት ሴት እንደዚ እሆናለው? ኤቤጊያ አይነጥላ ሆነችብኝ ራሴን ወቀስኩት የዛሬ አመት የነበረውን ናኦድ አስታወስኩት የድሮ ማንነቴ ናፈቀኝ ደፋር፣ ከሰውጋ ተግባቢና ተጫዋች በትምህርቱ ጎበዝ ራሱን የሚጠብቅ..... ከአንድ አመት በፊት ኤቤጊያ ይህንን ግቢ ስትቀላቀል ልቤ ከሷ ጋር አብሮ ሄደ አስታውሳለው እንደሁልጊዜዋ ሰማያዊ ጅንስና ጥቁር ሸርት አድርጋ ሻንጣዋን ይዛ እዛ ረጅም አስፓልት ላይ እየጎጠተች ስትገባ እኔ ከግቢ ስወጣ ነበር ያየኋት ከዛን ግዜ ጀምሮ ልቤን የሰረቀችው ቆንጆ እንስት ሌብነቷን እንኳን ሳታውቅ ልቤን አልመለሰችልኝ እኔም ከግዜ ግዜ ፍቅሯ እየባሰብኝ ሄደ ሁሉም ነገር ቀስበቀስ እየተቀየረ ሄደ የዛሬ አመት የነበረው ናኦድ አሁን የለም አባይ ጓደኞቼ ከኪያር ውጪ ተዘባበቱብኝ ከኔ ተለዩ ይባስ ብሎ ኤቤጊያን እንደምወዳት እያወቁ በስሟ መጫወቻቸው አደረጉኝ። ኤቤጊያ ታክሲ ውስጥ ገብታ ከሄደች በኃላ ራሴን አረጋግቼ ወደግቢያችን በር እያመራው አስፓልት ዳር ከቆሙት መኪናዎች አንዱ በመስታወቱ ራሴን ድንገት አየሁት ደነገጥኩ ራሴን በመስታወት ካየሁት በጣም ቆየው ድሮ የማውቀው ፊት ሳይሆን ሌላ ሰው የቆመ መሰለኝ ይህንን መልክ አላውቀውም በጣም ገርጥቶ የከሳ ጥቁር ፊት የተንጨባረረ ፀጉርና ፂም ቀጫጫ ሰውነት በዛ ቀጫጫ ሰውነት ላይ ሰፊ የቆሸሸ ልብስ ሰው ሁላ ጀዝባ ወይም ሞሮ ቢለኝ አይገርምም እውነትም ሆኛለው። ወደ ድሮ ማንነቴ መመለስ እንዳለብኝ ገባኝ ኤቤጊያ ለኔ ያላላት የፍቅር መርዝ ናት ከልቤ ቆርጬ ላስወጣት ለመጨረሻ ግዜ ለራሴ ቃል ገባው ወደ ግቢ እየሄድኩ የነበረውን ሃሳብ ቀይሬ ወደኃላ ተመለስኩ አንዱን ባጃጅ ኮንትራት አናግሬ ባያምነኝም ቅድሚያ ከፍዬው ቅር እያለው ወደ መብራት ሃይል ወሰደኝ። ኤቲኤም ብር አውጥቼ ወደ ቡቲክ አመራው ልብሶች ጫማ ሁሉንም ገዛዛው ራሴን በአዲስ መልኩ ማየት እፈልጋለው። ልብሶቹን ይዤ አንድ ሆቴል ገብቼ አልጋ ያዝኩ ሻወር ገባው ከላዬ ላይ የተራገፈው የቆሻሻ መአት እኔና ባኞ ቤቱ ነው ምናውቅው ራሴን ታዘብኩት በጣም! ከሻወር ስወጣ ሁሉም ነገር ቅልል አለኝ ነገሮች ጥርት ብለው ይታዩኝ ጀመር አዲሱን ልብስ ለብሼ ፀጉሬን ለመስተካከል ወደፀጉር ቤት ሄድኩ ያ ጅብ የዋለበት እርሻ የሚመስለውን ጨበሬ ፀጉር በአግባቡ ተስተካከልኩት ፂሜንም እንደዛ ትንሽ መለስ ያልኩ መሰለኝ ግን አሁን ድሮ የቀይ ዳማ የመሰለው መልኬ ጠቁሮ እንዳልተመቸኝ በደምብ ያሳብቃል ፀጉር ቆራጩን አመስኜ ወጣው። እንደሌላ ግዜ ሰው እየተጠየፈ አያየኝም ትንሽ ደስ አለኝ ወደ ቀድሞ ግብሬ መመለስ ጀመርኩ ሁሌ መብራት ሃይል ስመጣ መፅሃፍ ደርድረው ከሚሸጡት ውስጥ ራስተም ጋር ሄጄ አንድ አሪፍ መፅሃፍ ገዝቼ ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል በአንደኛ መንገድ ላይ ወክ እያደረግኩ ሰዉን እየታዘብኩ እሄዳለ ዛሬም እንደዛ ማረግ ፈለግኩ። ራስተም ጋር ስሄድ መፅሃፎቹን እያስተካከለ ሲደረድር አገኘሁት ቀና ብሎ ሲያየኝ ደስ አለው እንዴ ናኦዴ ሰላም ነው ምነው ጠፋህ አለኝ ብዙ ግዜ ሆኖኝ ነበር ራስተም ጋር መፅሃፍ ከገዛው ሰላም ተባብለን ከጨረስን በሃላ አዲስ መፅሃፍ ገዝቼ መንገዴን ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል በአንደኛ መንገድ ላይ አድርጌ ሄድኩ ወደ ሆቴሉ ስገባ እንድወትሮው ሰላሙን የጠበቀ ሆኖ አገኘሁት ከራስ ጋር ለማውራት ደስ እሚል ሰላማዊእና ተፈጥሮአዊ ቦታ ነው የዛሮቹ ብዛት የወፎቹ ዝማሬ ሰላም ይሰጣል እኔም ሰላሜን አገኘው አዱስ የገዛሁትን መፅሃፍ ገልጮ ትንሽ እንዳነበብኪ አስተናጋጇ መጣች ትዝ ሲለኝ ደህና ምግብ ከበላው በጣም ቆይቻለው የቤቱን አሪፍ ምግብና መጠጥ አዝዤ መፅሃፌን እያነበብኩ ዘመትኩበት ለዚች ቅፅበት ኤቤጊያን ረስቻት ነበረ። 12፡00 ሲል ወደ ግቢ ተመለስኩ ስደርስ እየጨላለመ ነበር ግቢ ውስጥ ስገባ መንገድ ላይ ከኪያር ጋር ተገጣጠምን ሲያየኝ ንፁህ ልብስ ለብሻለው ፀጉሬ ተስተካክሏል በዕጄ መፅሃፍ ይዣለው ተገረመ እየሳቀ ምን ተገኘ አለኝ ምንም አልኩት እየተቻኮለ ነበር አቅፎኝ ዶርም ጠብቀኝ እመለሳለው አሁን እያለኝ ፈገግታውን ሳይነፍገኝ እየተጣደፈ ሄደ ዶርም ስገባ ሁሉም መሳሳቅ ጀመሩ እንደ ኪያ የደስታ ሳይሆን የፌዝ እንደነበር በደምብ አውቃለው። አንደኛው በጣም እየሳቀ ሞሮሮሮ.... ምን ተገኘ ኤቢን ጠበሻት እንዴ አለኝ ተናደድኩ ሞሮ እሚለው ስድብ አናደደኝ ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ከዚ በኃላ ሞሮ ብትለ ኝ እንጣላለን አልኩት እየሳቀ እሺ አለኝ ተናድጄ ልወጣ ስል ኪያር በሩን ከፍቶ ገባ ያለው ነገር ወዲያው ስለገባው ይዞኝ ወጣና ወደ አም ፊ አከባቢ ያሉት ደረ ጃዎች ጋር እያረጋጋኝ ሄደን ተቀመጥም። አሁን ባየው መስተካከል እንደተደሰተ ነግሮኝ እንድበረታ እያፅናናኝ ስለ ኤቤጊያ ምን ማድረግ እንዳለብኝና እሱ ለኔ እንደሚያናግራት እየነገረኝ እያለ ኤቤጊያ ከሌላ ወንድ ጋር ሆና ከኛ ፊትለፊት ደረጃዎቹ ላይ ስጥቀመጥ ድንገት አየኃት።
ክፍል አራት እንዲቀጥል👍👍👍👍👍👍
ፀሃፊ - አል ረምሃይ
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
👉 @Readersworld11
👉 @Readersworld11
👉@Readersworld11
Comment @Kirubeljr
አል ረምሃይ:
።።።።።።።።።።።።ሞሮ።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።ክፍል 1።።።።።።።።።፡
ከደስታ ብዛት ሳይታወቀኝ ያ ቀጭን አለንጋ የመሰለ እጇን ጥብቅ አርጌ ይዣት አብረን እየሄድን ነው እንደሞኝ ያረገኛል ዝም ብዬ እየተገላፈጥኩ ከራስ ፀገሯ እስከ እግር ጥፍሮቿ አተኩሬ አያታለው ፀጉሯን ብኒ ቀለም ተቀብታው ተፈርዟል ከሩቅ ሲታይ የዛገ የእቃ ማጠቢያ ሽቦ ይመስላል ደነገጥኩ እን ደዚ ስላት ሰምታኝ ይሆን ሆ..ሆ..ሆ አፌን ብሰበስብ ይሻላል በስንት ስለት ያገኘኃትን ልጅ የዛገ ሃገሬ ሽቦ ብያት ልጣት እንዴ! ፊቷ ደሞ እንዴት እንደሚያምር ውውውይ ቀይ ረዘም ያለ ፊት ነው ያላት አይኖቿ ትላልቅ ከንፈሮቿን ደማቅ ቀይ ቻፒስቲክ ተቀብታዋለች የለበሰችው ጥቁር ቦዲ እና ሰማያዊ ጅንስ እላይዋ ላይ ጥብቅ ብሎ እሚያምረው ሰውነቷን ጉልት አድርጎ ያሳያል ፍዝዝ ብዬ እያየኃት እያለ አውራ እንጂ አለችኝ እ...እእ እሺ አወራለው አልኳትና ድጋሚ ዝም አልኩ ምን እንደማወራት አላውቅም ኤቤጊያ በጣም እምታምር ልጅ ናት አልመጥናትም አውቀዋለው እሷ የቆንጆዎች ቆንጆ እኔ ደግሞ ገጣባ!! የጀዝባዎች ጀዝባ ሞሮ አዬዬዬ መከራ አለች አያቴ እንዴት ይሆን እንደምወዳት እማስረዳት ዝም ብዬ ስብሰለሰል ሳመኝ አለችኝ እ.. ም ምን አልኳት አይኗን ጨፍና ከንፈሯን አሹላ ወደኔ ስትጠጋ ደነገጥኩ ፍርሃቴን እየደበቅኩ እኔ አይኔን ጨፍኜ ወደሷ.... ጀርባዬ ቅቤ ይወጣው ይመስል እንደጉድ ይንጠኛል ናዲ... ናኦድ!! አንተ ናኦድ አረ በጌታ ክላስ ረፈደ ተነሳ አንተ ምናባክ ነው ማትነሳው! ትከሻዬን ለጉድ ይነቀንቀኛል ከንፈሬን እንዳሾልኩ አይኔን እያጨናበስኩ ነቃው አጠገቤ ኤቢጊያ የለችም ያለው በእጄ ጭምቅ አርጌ የያዝኩት በላብ የሞጨሞጨ ትርሃስ ብቻ ነው ከወገቤ ቀና እያልኩ ወደኃላ ዞርኩ እንደቅቤ እሚንጠኝ ልጅ ጓደኛዬ ኪያር ነው። ከጣፋጭ ህልም ውስጥ ስለቀሰቀሰኝ በጣም ተበሳጨው ምናባክ ላርግህ ማን ቀስቅሰኝ አለህ አንተ የኔ አላርም ማናባክ አረገህ ብዬ ቀወጥኩት። ባክህ አትጩህብኝ ክላስ እየረፈደብን ነው ተነሳና እንሂድ አለኝ አልሄድም! ብዬ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠሁት አንተ ጀዝባ ፈተና አለን እኮ ዛሬ ተነስ ብሎ ብርድልብሴን ገፈፈኝ። ውውውውይ ኪያ በናትህ ተወኝ ምን እኔ ፈተና ሲያመልጠኝ መጀመሪያዬ ነው እንዴ ብርቅ አስመሰልከው እኮ ብዬ ብርድልብሱን በሃይል ነጠቅኩትና ድጋሚ ተጠቅልዬ ተኛው ኪያር ደብተሩን አንስቶ ጥሎኝ ወጣ። ኪያር ጥሩ ጓደኛዬ ነው ብዙ ግዜ ስድብና ቁጣ ይቀናዋል ልቡ ግን የዋህ ነው ደስ እሚለኝ የባህርዳር ልጅ ነው ከፍሬሽ ጀምሮ ስከአሁን አራተኛ አመት ድረስ አንድም ቀን እንኳን ሳንቀያየም አለን የዛሬን አያድርገውና በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ ሁሉ እሚቀናብኝ ብዙ ጓደኞች የነበሩኝ ግን ምን ያደርጋል ኤቤግያን ካፈቀርኩ በኃላ ሁሉም ገደል ገባ እኔም ራሴን ጣልኩ ጀዘብኩ ሁሉም ሰው ጀዝባው! ሞሮ! እያለ ሲጠራኝ ኪያር ብቻ ነው በስሜ ሚጠራኝ እሱም ሲበሳጭብኝ እንደነሱ ጀዝባው ይለኛል ግን ምንም አይመስለኝም እውነትም ጀዝቢያለው ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም ቀኑን ሙሉ አልጋዬ ላይ ተሰፍቼ ስለ ኤቤግያ ብቻ ሳስብ እውላለው ማታ ደሞ ራሴን በአልኮሆልና በጭስ ውስጥ ተደብቄ አገኘዋልው ቀንና ለሊት ኤቤግያን ሳስብ እውላለው አድራለው እሷ ግን ማን እንደሆንኩ መፈጠሬን እንኳን አታውቅም! ኤቤግያ ኤቤግያ ኤቤግያያያ.... እንደው ምን ልሁን ምን ይሻለኛል ኤጭ ብርድልብሴን ሸፈንኩና የቅድሙን ህልም ፍለጋ ተመምኩ ግን ቴዲ ህልም አይደገምም ብሎ የለ አጣሁት ከየት ይምጣ ተበሳጨው እርሜን ኤቢን ከጎኔ ሁና ባያት ልስማት ስል ኪያ ቀሰቀሰኝ ተኛው። ምሳ ሰአት ኪያር እየሮጠ መጥቶ ድጋሚ ቀሰቀሰኝ ለጉድ ጮህኩበት አንተ ቃጭል ታወኝ በቃ ልተኛበት አልኩህ አይደል እንዴ ምን ላርግህ አልኩት እየሳቀ ናዲ ኤቤግያ በኛ ብሎክ ጋር እያለፈች ነው አለኝ ከምኔው ተስፈንጥሬ ከአልጋዬ ወርጄ የዶርማችን በረንዳ ጋር እንደተሰየምኩ አላውቅም ኪያ ከት ብሎ ሳቀ ሁሉም የዶርሜ ልጆች ነገረ ስራዬ አስቋቸው እየሮጡ መጥተው አብረውኝ ቆመው እኔን ማየት ጀመሩ ግድ አልሰጠኝም። አቢ ቀይ ቅድም በህልሜ ያየኃቸውን ልብሶቿን ለብሳ በኛ ዶርም አከባቢ እያለፈች ነው ልቤ ፍስስ ሲል ተሰማኝ ድንገት አንዱ የዶርሜ ልጅ ጮክ ብሎ ኤቤግያ ብሎ ተጣራ.....ይቀጥላል
እንዲቀጥል #Share
@Readersworld11
@Readersworld11
ከመደመር ቀጥሎ ማካፈልን አይርሱ!
Inbox @Kirubeljr
ካነበብኩት ታሪክ ውስጥ በጣም ትርታዬ🌍 በጣም ነው 🏆የወደድኩተት🌻 በተለይ 🤹♂ የመቅደስ 🌷ቤተሰብ በጣም የተባረኩ ናቸው ግን የእውነት💥 ምርጥ ድርሰት🌹 ነው እኔ ምለው እውነተኛ ታሪክ ነው🌹🙏😃❤️🌹
Читать полностью…from my memo page
"እዉነቱ ይህ ነዉ እኔ አቅሜ እና አላማዬ ተዋህደዉ የፈጠሩኝ የዚች ምድር አስደናቂ ገፀ ባህሪ ነኝ።" @Kirubeljr
©✍Kirub.el
አባት ወገን ዘመድ
የህት ወንድሞቿ የቅርብ ጓደኛ ጎረቤት የጅማ ዩኒቨርስቲ ትላልቅ
መስተዳድሮች ማለትም ለጌዲዮ ህክምና የተሯሯጡ በጠቅላላ
በተገኙበት የቀወጠ የንኳን ደና መጣህ ዝግጅት ተበላ ተጠጣ
ተጨፈረ ጌዲን እንኳን እግዚያብሄር ማረህ መቅደስን እንኳን ደስ
አለሽ ብቻ የተጨበጨበለት ደስ የሚል ቀን አሳለፉ......
........ከዛም መቅደስም ጌዲዮ ትምህርታቸውን ያቆሙበትን
ምክንያት በመረዳት ያምስተኛ አመት ትምርታቸውን እንዲቀጥሉ
የጅማ ዩኒቨርስቲ ፈቀደላቸው ከዛም ለደቂቃ እንኳን ሳይለያዩ
አንድ ላይ ጥናት አንድ ላይ ምግብ አንድ ክፍል ትምርት አጠገብ
ላጠገብ ተቅምጠው እንኳን እሱ ዶርም አይተኙም ነበረ እዛው
የዩኒቨርቲው አካባቢ ቤት ተከራይተው አንድ ላይ እያደሩ
እንደከረባት ካንገቱ ተጠምጥማ ተማሪውን የግቢውን ሰራተኞች
የጅማን ህዝብ እንዳስቀኑ አስቀንተውም ካይን ያውጣችሁ
እንደተባሉ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን በሚገርም ውጤት
አጠናቀቁ ከዛም በከፍተኛ ማእረግ ሁለቱም ተመረቁ ........
@Readersworld11
........የምርቃታቸውም ቀን ያኔ ቃል እንደገባችለት ያኔ ቃል
እንደገባላት በዝና በሞገስ ተጠርተው ዋንጫቸውን ወርቃቸውን
ሲወስዱ የሁሉም ሽልማት ተሰጥቶ አልቆ ስለነበረ ጌዲዮ
ማይኩን ወሰደና አንዴ አላቸው ከዛም ሄዶ ከመቅደስ ፊት
ተንበረከከና መቅዲ አንቺ ለኔ የሆንሽውን እንዲ ነው ብዬ
መግለፅ አልችልም በማህፀንሽ አልተሸከምሽኝም እንጂ
ማንነቴን ሙሉ ተሸክመሻል አገር የናቀውን ጌዲዮን በፍቅርሽ
ሰው አርገሽዋል አንቺ ማለት ለኔ እናቴ ነሽ አለና ከኪሱ ቀለበት
አውጥቶ የፍቅርሽ ምርኮኛ ነኝ እናት ፍቀጂልኝና ባሪያሽ ሆኜ
እድሜዬን ሙሉ ልታዘዝሽ ታገቢኛለሽ አላት መቅደስ በደስታ
እንባ ታጠበች ተመራቂው አስመራቂው ቲያትር እንደሚያይ
መስሎ እስከሚሰማው ድረስ ፈዞ ቀረ እንኳን እሱ የምርቃታቸው
ፕሮግራም የቀጥታ ስርጭት ስለነበረበየ ቲቪው መስኮት
የሚያያቸውም አነባ ከዛም መቅደስ አዎ አገባሀለሁ እኔም
ስጠበቅልህ እኖራለሁ አለችው ቀለበቱን እንዳጠለቀላት አዳራሹ
በጭብጨባና በእልልታ ቀወጠ እሷም ተንበርካ አቀፈችው እሷም
ያኔ ቃል የገባችለትን እቅፍ አበባ አስታቀፈችው................
@Readersworld11
..............ወጥ ያለጨው ሂወትም ያለፈተና አይጣፍጥምና
ያን ሁሉ መከራ አልፈው የነመቅደስ አዲሱ ህይወት ያማረና
የሰመረ ሆነ ሀብቱን መልኩን ሳታይ በሽተኛ መሆኑ ፍቅሯን
ሳይቀንሰው ታምና ስላፈቀረችው ዛሬ ያሁሉ አለፈና ጌዲዮም ዳነ
በዛ ላይ በተማሩበት የስራ ዘርፍ የዛው አመት በከፍተኛ ደመወዝ
ስራ ተቀጠሩ ድርጅቱም ቤት ሰጣቸው ሰርጋቸውንም ያለምንም
ሀሳብ በጌዲዮ በኩል የሱ ቤተሰቦች በመቅደስ በኩል የሷ
ቤተሰቦች ቅውጥ ያለ ሰርግ ሰርገው መርቀው ጨፍረው
በደመቀ መልኩ መቅደስና ጌዲዮ ተጋቡ አዲስ ጎጆም መሰረቱ።
አየሁት ምኞቴን ተሳክቶልኝ ማታ የልጅነት ህልሜ በግዜ ተፈታ
ናበራሁኝ ሻማ ሞቅ አለ ጎጆዬ በራሴ ተማመንኩ ኮራሁ
በምጫዬ ጌዲዮ መቅደስን ባንድ ቃል ግለፃት ሲባል እስትንፋሴ #ትርታዬ አላት መቅደስም ጌዲዮን ባንድ ቃል ግለጪው ስትባል እስትንፋሴ #ትርታዬ አለችው።
✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️
💚💛❤️#ተፈፀመ💚💛❤️
✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️
እንግዲ ደራሲው እዚህ ላይ አበቃ ማንኛውም አስተያየት ካላችው እንቀበላለን ከተመቻችው ሼር አድርጉ እናመሰግናለን፡፡
@Readersworld11
@Readersworld11
።።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።ክፍል 25።።።።።።።።።።
ጌዲዮ ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ
ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ
ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ
የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው
ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና
አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ
ነች........
.....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ
የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው
ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን
አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ
ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን
መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ
ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ
ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው
ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ
የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን
የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ..........
.......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ
ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት
አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት
ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች
ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ
አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው
ጥላሁንስ ቢሆን........
.........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ
ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ
አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ
እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም
ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን
እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት
ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው
ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ
የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን
መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ
በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ
ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ
ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም
ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን
ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል ........
........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ
አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ
ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና
ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው
በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው
በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም
ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ
አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት
ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው
እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው
ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው
አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ
መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ
አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር
ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ
ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው
መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው
መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ
ብለው አስታወሱ............
........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት
ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል
በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው
ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት
አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው
ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ
የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት
መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት
አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ...........
..........የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት
ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን
ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን
ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም
ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት.................
.........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት
ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ
ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር
ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት
ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት
እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ
ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች
ነው........
.....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን
መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች
ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ
በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ
እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን
ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች
ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ
ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት
ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ
ቢወድቁም አልማርም አለች .........
........ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና
በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው
ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል
አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር
ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም
ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት
አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ
ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ
ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ
መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ
ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ
መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት
እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ
የመጨረሻ ክፍል ይቀጥላል
@Readersworld11
@Readersworld11
Inbox 👉🏼@Kirubeljr
"እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል።
መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል።
ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ።
ባለቀ ትናንት አትታሰር፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን፤ ይልቅ ወደማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ።
አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።"@Readersworld11
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
"የአዲስ አበባ ውሾች"
✍በዳንኤል ክብረት
ሐምሌ 2010 ዓ.ም.
ከ ገፅ 171 የተወሰደ
።።።።።።።።።።።ትርታዬ።።።።።።፡።።።።
።።።።።።።።።።፡ክፍል 24።።።።፡።።።።።
ወዲያው ዶክተሮቹ ተሯሩጠው ህክምና አደረጉለት ብዙም
ሳትቆይ መቅደስ መጣች መታመሙን ስታይ ወዲያው ቅዱስ
እንደነገረው ገባትና አንተ ነገርከዋ አለችው ወንድሟ ቅዱስም
መቅዲ ሙች ጠይቆኝ ነው ሲላት አረ ነው እንዴ ድሮም
ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ አንተን ሰው ብዬ አምኜህ መሄዴ አሁን ላባ
ሳልናገር ቀጥ ብለህ ውጣ አረ መቅዲ በጥፊ ያላልኩህም
ታላቄ ስለሆንክ ነው ቆይ ቢሞትስ አታስብም እንዴ ስትለው እሺ
ይቅርታ አርጊልኝ ሁለተኛ አይደግመኝም አላት ሁሌ እንዲህ
ትላለህ ግን ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነህ ስትለው እንደምንም
አግባብቷት ይቅርታዋን አገኘ....
......ጌዲዮ ሲነቃ መቅደስ እጆቹን ተንተርሳ ተኝታ ነበር ከዛም
እጁ ሲንቀሳቀስ ነቃች አይኖቿን በንባ ሞልታ ጌዲዬ ደናነህ
ስትለው መቅዲ እሞታለኋ አላት መቅደስ ደንዝዛ ማነው ያለው
ደሞስ ቢሉስ ሰው ፈጣሪ ነው እንዴ አትሞትም ተጋብተን ልጆች
ወልደን አርጅተን ነው የምንሞተው ጌዲዬ ትተኸኝ አትሞትም
ብላ እያለቀስች ፊቱን እየተሽከረከረች ሳመችው ጌዲዮ አለቀሰ
መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ
እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም መቅደስ ተስፋዋ ተሟጦ ጮኸችበት ጌዲዮ
አትሞትም አትሞትም ብላ እያለቀስች ትታው ወጣች........
.......ወዲያውም ባስ ይዛ ቀጥታ ጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው
አስተዳዳሪ የዲን ቢሮ ሄደች እንባዋ ያለማቋረጥ ይፈስ ነበር
ሰውነቷ ከስቶ አይኗ ጎርጉዶ ጉንጯ ሟምቶ በተስፋ ማጣት
ተጎሳቁላ ጭራሽ መቅደስ አትመስልም አስተዳዳሪው ደንግጦ
መቅደስ አላት አዎ መቅደስ ነኝ የኔ እንደዚህ መሆን ገረመህ
አዎ ሊገርምህ ይችላል ምክንያቱም አባይን ያላየ ምንጭ
አመሰገነ ጌዲን አላያችሁትማ ካልጋ ተጣብቆ ሞቱን
እየተጠባበቀ ነው አያችሁ የዚህን ዩኒቨርስቲ ስም አራት አመት
ሙሉ አስጠራ ዘንድሮ በመመረቂያው ሲጠፋ ግን ምን ሆኖ ነው
እንኳን አላላችሁትም እሱ ባመጣው ውጤት ለስማችሁ
ለማስጨብጨብ ግን አንደኞች ናችሁ አስተዳዳሪው እንደምንም
አረጋግተዋት ስለተፈጠረው ነገር ለመረዳት ጠየቋት እሷም
ሁኔታውን በሙሉ በዝርዝር ነገረቸው ከዛም የዩኒቨርሲቲው
ኮሚቴዎች ሰብስበው መልስ እንደሚሰጧት ነግረዋት ወጣች
ስትወጣ ወይንሸትና በለጠው አንድላይ እየሄዱ አገኟት
ስለጌዲዮ ሲጠይቋት ሁሉንም ነገረቻቸው ከዛም ተመልሳ አ.አ
መጣች.................
...........ከዛም ጉዋደኞቻቸው እንዳቅማቸው ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመሩ የዩንቨሪስቲው አስተዳዳሪ እንዳሉት ተሰብስበው አንድ
ሀሳብ ላይ በመድረስ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ለቀቀ በዚህም
የተነሳ ቤታቸውም ሳይሸጥ ሌላም ከባድ ወጪ ሳያወጡ
የጌዲዮን ሙሉ ህክምና ወጪ የሚችል እስፖንሰር ተገኘ........
......ወዲያውም መቅደስ ጋር ተደውሎ የምስራቹ ተነገራት
ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት ሰአት አዲስ ተስፋ በእውነት ደግማ
የተወለደች ያክል ነው የተሰማት ደስታዋንም ለሁሉም አጋርታ
አንድ ላይ ጮቤ እረገጡ ....።
......ዶክተሩም ጋር ሄዳ ገንዘቡ ተገኘ ይድናል አይደል አለችው
መቅደስ ይድናል ብዬ ተስፋ እንጂ እውነታውን ልነግርሽ
አልችልም ምክንያቱም ጌዲዮ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቀዶ ጥገና
ነው የሚያደርገው ለዚም ካስር ወር እስከ አንድ አመት
በህክምና ሊቆይ ይችላል አላት የዶክተሩ ንግግር ደስታዋን
ቢያደፈርሰውም ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ ነገንም አይጥለንም ብላ
ተስፋዋን ፈጣሪን አደረገች......
አብሮት ለማስታመም ማን መሄድ እንዳለበትም አባቷና እናቷ
ሲጠይቁ መቅደስ እኔ ነኛ አለች ቅዱስ እንዴ አንቺማ አትሄጂም
ልታስታምሚው ነው ወይስ በለቅሶ ልትደፊው መቅደስ ተናዳ አረ
ባክህ ስትለው እህቷም ብሩክም ሁሉም እሷ መሄድ እንደሌለባት
እና የጌዲዮን ቃል ለማክበር መማር እንዳለባት ነገሯት ከዛም
እኔ እኔ በሚል ክርክር ብዙ ከቆዩ ቡሀላ ብሩክ እንዲሄድ ተወስኖ
ፕሮሰሱ ተጀመረላቸው........
........ከዛም የበረራው ቀን እቤት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ሁሉም
ዘመድ ጓደኛ ተሰብስቦ ቤቱ በንባ ታጠበ ጌዲዮ እቤት የመጣው
ባልጋ እየተገፋ ነው ቀና ብሎ እንኳን ቻው ሊላቸው አልቻለም
ነበር መቅደስማ ደግማም የማታየው እየመሰላት ነው በተለይ
ዶክተሩ በቀዶ ጥገና ወቅት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት
ከባድ ነው ያላት ትዝ ብሏት ለቅሶዋ እርም የምታወጣ ነበር የሚመስለው...........
............ከዛም ጓደኞቻቸው ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡት
ብቻ ሁሉም የበኩላቸውን እያበረከቱ ሰላም እንዲመለስ
መልካም ምኞት ተመኙለት መቅደስ ግን እንደሌሎቹ ጥቅማ
ጥቅም ሳይሆን በጀሪካን ፀበልና እምነት አርጋ ለወንድሟ አደራ
ሰጠችው.....ኤርፖርትም ስትሸኘው ያንገቷን ማህተብ አውልቃ
ሂወቴ ያላንተ ባዶ ናት እኔ የምኖረው አንተ ስትኖርልኝ ነው
ተመልሰህ ከመጣህ ይህን ማህተብ ታስርልኛለህ ያለበለዚያ
ግን እኔም ተከትዬህ በሰማይ እምነቴን ማህተቤን
ትመልስልኛለህ ብላ ባንገቱ ላይ አሰረችለት ይህን ስትለው
ጌዲዮ ከተወለደ እንደዚህ ቀን አምርሮአልቅሶ አያውቅም አለቀሰ
እጇን እንደምንም ጨብጦ አደራ እግዚያብሄር ያረገውን
ቢያረገኝም እንዳትሸነፊ ነገ አዲስ ቀን ነው ትምርትሽንም አደራ
ተምረሽ የኔን ህልም አንቺ አሳኪልኝ አላት እንኳን እናቱ እንኳን
ቤተሰቦቿ በኤርፖርቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉም በንባ ታጠቡ
ወንድሟም እያለቀሰ ሁሌም በዋታሳፕ በቫይበር ሁሌም
እንደሚገናኙ ቃል ገብቶላቸው በለቅሶ ተሰናበቱት........
እውነት ጌዲዮ ድኖ ይመጣ ይሆን????........
ይቀጥላል 👍
@Readersworld11
@Readersworld11
ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ
ትቆዪና መንገድ ዳር ቆመው ተሳፋሪ ከሚጠብቁ ታክሲዎች ወደ አንዱ ዘው ብላ ትገባለች።
የገባችበት ታክሲ ቻይናዊ ሹፌርም ግራ በመጋባትና በመገረም ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በጥያቄ ስሜት መላልሶ ማየት ይጀምራል። አጅሪት ግን ምንም ያልተፈጠረ በማሥመሰል መሄድ የምትፈልግበትን ተናግራ እንዲንቀሳቀስ በዓይኗ ምልክት ትሰጠዋለች።
ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር ግን ያልተመለሠለት ጥያቄ ነበርና አሁንም ከእግር እስከራሷ መላልሶ ማየቱን
ይቀጥላል። ይኼኔ ቆንጂት በሷ ብሶ በስጨት እንደማለት እያደራረጋት "ልብስ
ያልለበሰች ሴት አይተህ አታውቅም???" ብላ ታፈጥበታለች።
ቻይናዊው ባለታክሲ ግን እንዲህ በማለት በትህትና መለሠ....... "የኔ እህት... እኔ ግራ ተጋብቼ የማይሽ እርቃንሽን መሆንሽ ገርሞኝ ሳይሆን... ለአገልግሎቴ ልትከፍዪኝ የሚገባኝ ገንዘብ የቱጋ እንዳለሽ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው።"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
*አየህ ወንድሜ... በዚህች ዓለም ስትኖር ልክ እንደቻይናዊው ታክሲ-ሹፌር ማተኮር ያለብህ ስለሚመለከትህ ጉዳይ ብቻ ነው። ስለማያገባህ ጉዳይ ስትፈተፍት በመዋልና በማደር በራስህ ህይወት ላይ የምትጨምረው ምንም
ዓይነት ጠቃሚ ነገር የለም። አቅምህ እስከቻለው ለሌሎች መልካምን አድርግ
የሌሎችን ግላዊ ህይወት ግን ለባለቤቶቹ ተውላቸው።
ይቀላቀሉን
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
@Readersworld11
@Readersworld11