ብዛዕባ ተውሒድን ሽርክን
ዓብዱሶመድ ሙሐመድ ኑር
Telegram:/channel/AbdusomedMNur_Video/1013
YouTube:https://youtu.be/Qx8LKW51Y0A?si=o5DivwvrxDX8oETm
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።
Читать полностью…አስደንጋጭ ቪድዬ
አማራ ክልል ያለ በአላህ ላይ ማጋራት፡፡
ይህን ቀብር አምላኪዎች አላህን ትተው እንዲህ ይላሉ
“ጤና ስጡን እንላለን፣ ጤና እናገኛለን፡፡….”፣
ከአላህ ውጭ ይህን ቀብር ውስጥ ያለ ለራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ሙት “ልጅ ስጠን ብለው” ስለት ይሳሉለታል፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በአላህ ላይ ማጋራት ለሁለት ሀገር ውርደት ይዳርጋል፡፡
የአላህን እርዳታ ከሺርክ፣ ከቢድዓ፣ ከወንጀል እና አላህ ከጠላው ሁሉ ካልራቅን ማግኘት አንችልም፡፡
አላህ የተውሒድ እና ሱና ዘቦች፣ ሺርክ እና ቢድዓን የሚፀየፉ፣ የሚርቁ፣ የሚጠነቀቁ እና የሚያስጠነቅቁ ያድርገን፡፡
/channel/SadatKemalAbuMeryem
የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-
* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]
* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]
* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]
* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።
* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]
2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።
3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-
* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።
1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
/channel/IbnuMunewor/893
2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
/channel/IbnuMunewor/869
3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
/channel/IbnuMunewor/876
4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
/channel/IbnuMunewor/884
5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2227
6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
/channel/IbnuMunewor/2214
7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
/channel/IbnuMunewor/2261
8, ዓሹራን ለመውሊድ?
/channel/IbnuMunewor/2269
9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
/channel/IbnuMunewor/2294
10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
/channel/IbnuMunewor/882
11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
/channel/IbnuMunewor/2298
12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
/channel/IbnuMunewor/886
13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
/channel/IbnuMunewor/2234
14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
/channel/IbnuMunewor/898
15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2277
16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
/channel/IbnuMunewor/878
17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
/channel/IbnuMunewor/34
18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
/channel/IbnuMunewor/1624
19, መውሊድ ተከሽኖ
/channel/IbnuMunewor/2309
20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
/channel/IbnuMunewor/918
21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
/channel/IbnuMunewor/2302
የመውሊድ ውድድር
ፈተና አንድ
1) ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንት ጊዜ ነው መውሊድ በኣል ላይ የተሳተፉት?
___________________
2) የትኛው ከተማ ላይ ነበር መውሊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሃባዎች የተከበረው?
_____________________________________
3) ሰሃባዎች የትኛውን አይነት የመውሊድ አወጣጥ ነበር ለታቢኢኖች ያስተማሩት?
________________________________________________________
4) ምን አይነት ምግብ ነበር በመውሊድ ወቅት ሲመገቡት የነበረው?
________________________________________________________
5) መውሊድ ላይ በሰሃባዎች ሲዜሙ ከነበሩ ዘፈኖች ውስጥ ዋናዋናዎቹን ጥቀስ
___________________________________
___________________________________
• አስታውሱ ሁሉም መልሶች ከሚከተሉት መሰረታዊ ምንጮች ነው መሆን ያለባቸው፡
1. ከቁርኣን፣
2. ከሀዲስ፣
3. ከሰሃባዎች ንግግር
በደንብ አስባችሁ፣ ጊዜያችሁን ውሰዱና ቁርኣንን ፈትሹ፣ ቡኻሪ ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ መዛግብትን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡
የተተረጎመ
/channel/SadatTextPosts
********** ነጯ መስገጃ? **********
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ።
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ።
የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ ላይ ይሁን።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነዚህን ሁለት ፎቶዎች ተመልከቱ። ሀገራችን ላይ መውሊድ አክባሪዎች ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ይመጣሉ" ብለው የሚያምኑ ሰዎች "ሀድራ" ላይ ነን ብለው በሚከተለው ሁኔታ ይቀመጣሉ ይቆማሉ።
ነጯን ምንጣፍ ሰው አይቀመጥባትም። "ነብዩ ከነሶሀባዎቻቸው ሲመጡ የሚያርፉባት ናት።" ብለው ስለሚያምኑ።
ሌሎች የሚሉዋቸውን አባባሎች ቁጭ ብለው ይሉና፣ የሚከተሉትን ስንኞች ሲያነቡ ይቆማሉ።
1) "መርሃባ ነቢ መርሃባ፣
መርሃባ ነቢ መርሃባ።"
ትርጉሙ "ነብዩ ሆይ! እንኳን ደህና መጡ።"
2) "አርሂቡ ነቢ፣
አርሂቡ ነቢ፣
ያ ሀቢቢ።"
ትርጉሙ "ነብዩ ሆይ ግቡ፣ ግቡ።"
ነብዩ ይመጣሉ ብለው ያምናሉ ስንል በማስረጃ ነው። አላህ ይምራውና ስንት ሰዎችን በክህደት መንዙማው ያጠመመው ሙሐመድ አወል ሐምዛ እንዲህ ይላል
"አይዟችሁ ተደሰቱ መውሊድ የመጣችሁ፣
ከነ አስሀቦቹ (ከሰሀቦችም ጭምር) ነቢ መጡላችሁ።"
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ግን እንዲህ ይላሉ
"የቂያማ ቀን መጀመሪያ ቀብሪ ተከፍቶልኝ የምወጣው እኔ ነኝ።"
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህን ሁሉ ከሸሪአ የሚጋጩ እምነቶች እና ተግባራትን እያያችሁ አሁንም የሰይጣንን ጥሪ ተቀብላችሁ መውሊድ ታከብራላችሁ?
ለነፍሳችን እንዘንላት። ነብዩ አይመጡም። ሱናቸው ግን ይሀው ፊት ለፊራችን ቀርቦልናል የህይወት ስንቅ አድርገን እንተግብረው።
አላህ በነብዩ ሱና ከሚብቃቁት ያድርገን።
/channel/SadatKemalAbuMeryem
የሰኞ ፆም እና መውሊድ
~
የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦
1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?!
እናንተ'ኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው።
2. እናንተ'ኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት!
ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ!
ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር አይደለም ወይ?
3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም!
ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።
4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም!
የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላልን? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን?
{يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ}
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው።} [አልሑጁራት፡ 1]
ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782]
5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም!
ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ሁሉ ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር።
6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም
በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና።
7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም!
በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ መፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም። እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሕ ሙኽተሶሪል ኸሊል" የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ?
ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም።
ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014)
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
እንዲህም የሚል አለ
“መውሊድ ለማክበር ሰሂህ ሀዲስ ሳይሆን፣
ሰሂህ ቀልብ ነው የሚያስፈልገው፡፡”
እውነታው ግን ሰሂህ ቀልብ ያለው ሰው ያለ ሰሂህ ሀዲስ (ያለ ቁርዓን ማስረጃ፣ ያለ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና) በልብ ወለድ ተነስቶ አምልኮን አይፈፅምም፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትዕዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙትን ነገር መስራት ስራን ማበላሸት ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል
[47:33] ۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوٓا۟ أَعْمَٰلَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ (ያልታዘዛችሁትን በመስራት) ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡
/channel/SadatTextPosts