#ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
⬇⬇⬇⬇⬇⬇
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
ትግስት አልባው ሆዴ እዮብን ያስቀናል
የጠጠረው ልቤ
ከፈሳሹ ውሃ እጅጉን ይቀጥናል
:
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
አኩርፌም ስቃለው
በጣር ውስጥ እያለው
ደና ነኝ እላለው
:
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
ቁልቁሉን ከጠላሽ ሽቅብ እወጣለሁ
ሽቅቡን ከጠላሽ አዘቅጥ እወርዳለሁ
ቀልብሽ ባረፈበት እመላለሳለሁ
:
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
ታዋቂ ሁን ብትህ
አክተር እሆናለው የፊልም ባለ ሙያ
መጽሐፍ እጽፋለው ልገኝ ባንባቢዎች ጉያ
ታሪክ እሰራለው በዓለም መጽሐፍ ሚመዘገብ
እፈላሰፋለው በተላላቅ አውታር እስክዘገብ
:
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን
ጀገና ሁን ብትይኝ
ማላውቀውን ባህር እቀዝፋለሁ
የዱሩን አንበሳ ገነጣጥላለሁ
ለብቻዬ ሁኜ ጁንታን እገጥማለሁ
:
ላንቺ_ላንቺ_ሲሆን እማልሆነው የለም
አጥንቴ ነሽና ልውደድሽ ዝንት ዓለም
:
ⒶⓈ
አስቻለው @aschalewgtm
#እባክህ_አንድዬ 🙏🇪🇹
ሁሉንም አድራጊው የበላዩ ዳኛ
ህመመችን ፀንቷል ላክልን መዳኛ
በክፋት ተነክረን ጨቅይተን በ በደል
እጅግ ቆሽሸናል ስራ ሁኗል መግደል
🙏 እባክህ አንድዬ 🙏
በማያልቅ እዝነትህ በምረትህ አፅዳን
'ሰው' ነት አላብሰን እውሬነቱ ይብቃን
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
😘 😘 😘
እኛን እንዲያምርብን እሷን አደርታ
አንሰን አንዳንታይ ደክማ ተንከራታ
ስንስቅ የምትስቅ ሲያመንም የሚያማት
እናት ብቻኮ ናት ወረት የማያውቃት
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
😘 😘
አብሮ ለመደሰት የኔ ካሉት ጋራ
ከንፁህ ፍቅር ጋር ይበቃል ሽንብራ
#እኛም_ሳቅ_ይቅረበን 🙏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#ከትክክለኛው_ሰው_ጋር_ስትሆኑ ✋
ከትክክለኛው ሰው ጋር ስትሆኑ ደስተኛ ለመሆን አትጣጣሩም፣ እንዲሁ ደስተኛ ናችሁ፡፡ ከትክክለኛው ሰው ጋር ስትሆኑ ያንን ሰው ለማስደሰትም አትጦዙም፣ ያ ሰው ከእናንተ ጋር በመሆኑ ብቻ ደሰተኛ ነው፡፡ ይኸው ነው!
#መልካም_እንቅልፍ 🙏
👇👇👇
@seanlph
#ብርቅ_ሆነብን 😢 🇪🇹 😢
ከሰላም ተኳርፈን ለጠብ ተዋድቀናል
ከቸር ወሬ ይልቅ ለመርዶ ቋምጠናል
አደን አድሩስ ቀርቶ ባሩድ ሁኗል ጭሱ
ጥላቻና መግደል ሁኗል የሰው ሱሱ
የአዛን ቅዳሴ ድምፅ ተውጧል በሩምታ
ቢሰማ ጥይት ነው ቢደመጥም ዋይታ
መሳቅም ዘበት ነው አይን ለምዷል ማንባት
አሁን አሁን ጭራሽ ብሶ የኛ መአት
አንዳች ብርቅ ሆነብን በደግ ውሎ መግባት
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#አንቃን_በጥበብህ 🙏
መውደድ ስንችል ጠልተን ፣
መሆን ሳለም መስለን ፣
አስታርቁ ስንባል ለማኳረፍ ቋምጠን፣
ከቦታችን ወርደን ሰው ከመሆን ጎለን ፣
ከሙገሳ ይልቅ ቀሎን መወቃቀስ ፣
በእልህ ተቃርኖ አብሮነት ስናፈርስ፣
በሳቃችን ጀርባ ቅናት ተለጥፎ ፣
ባንደኛው መደሰት ሌላኛው አኩርፎ፣
ደርሰን ተከፋፍለን ፀንተን በልዩነት፣
ድንበር እያበጀን ርቀን ከእምነት ፣
የውሼት እንደኖርን እንዲሁ እንዳንሞት
አንቃን በጥበብህ ሰው አርገን የእውነት
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#አንተው_ምረጥልን 🙏
የሰው ዋጋ ወርዶ ኑሮ እንዳይወደድ
በዘር በጎጥ ሀሳብ ሰው እንዳይታረድ
የግፍ በደል ግንዱ ከስሩ እንዲነቀል
የፍትህ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲሰቀል
ማንን ነው የምንመርጥ ? 🤔
የቱ ነው ሚሻለን የቱ ነው የሚበልጥ ?
ያጠላብን ሀዘን ብሶቱ እንዲገፈፍ
ባላጠፋው ጥፋት ህዝብ እንዳይገረፍ
ከተራ መግለጫ እንዲያልፍ ኑሯችን
ሰላም እንዲነግስ ዳግም ባገራችን
ማንን ነው የምንመርጥ ? 🤔
የቱ ይሻለናል የቱ ነው የሚበልጥ ?
ሀዘን ዋይታ እሪታ ሙሾውና መርዶ
በደስታ እንዲቀየር አዲስ ህግ ወርዶ
የሚስኪን ደም እንባ በከንቱው እንዳይፈስ
በሆድ አዳሪዎች ኢትዮጲያ እንዳትፈርስ
ማንን ነው የምንመርጥ ? 🤔
የቱ ነው ሚሻለን የቱ ነው የሚበልጥ ?
አንዱ አገር ተረስቶ ሌላው እንዳይለማ
ድሀው በቀን ፀሀይ ቤት እንዳይቀማ
እውቀት ያለው ቤቱ ዘመድ ያለው ቢሮ
መኖር እንዲያበቃ በሙስና ታጥሮ
ማንን ነው የምንመርጥ ? 🤔
የቱ ነው ሚሻለን የቱ ነው የሚበልጥ?
ሁሉም አንድ አይነት ነው ፖለቲካ ወጉ
አለየንም ፍፁም ክፉው እና ደጉ
እባክህ ፈጣሪ የበላዩ ዳኛ
አንተው ምረጥልን
እንባችንን አባሽ የሚበጀን ለኛ 🙏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#ለውድ_የግጥሞቼ_ተከታታዮች_የተፃፈ ✍
ጠፋተሀል ፣ ግጥሞችም እንደቀድሞው በብዛት ፖስት አታደርግም የሚሉ መልእክቶች በውስጥ መስመር ተበራክተዋል በመሆኑም ለሁሉም መልስ ይሆን ዘንድ ይሄን ማለት ወድጃለሁ አዎን ልክ ናችሁ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ጠፍቻለሁ ፖስቶችም ላይ እንዲሁ የመቀዛቀዝ ሁኔታ ታይቷል ነገር ግን የመጥፋቴ ሚስጥር ለበጎ ነው በጎው ምን ይሆን ካላችሁ ደግሞ ለመጀመሪያው የግጥም መድብል መፅሀፌ የሚሆኑ ስራዎችን በመጫር ላይ ስላተኮርኩ ነው መቼም ማሳተሜን እናንተም በጉጉት እንደምጠብቁት ሙሉ ተስፋ አለኝ 😍 በአላህ ፍቃድ ብዙ ሳይርቅ የመፅሀፍን #የሽፋን_ምስል እና #ርዕስ ይፋ ሁኖ ታዩታላችሁ 🙏 እስከዛው ከተቀደደው ማስታዎሻዬ ላይ የቀሩትን ግጥሞቼን በቻልኩት አቅም ለእናንተ እንዲደርሱ አደርጋለሁ ✋
ላቅ ያለ ክብር ለውድ አንባቢዎቼ 📚
👇👇👇
@seanlph
#አንዳንዴ_ስትኖር 🥺
እንዳሰብከው ሳይሆን አንተ እንደጠበከው
ፍፁም ተቃራኒ ሁኖ ነው ሚገኜው
ጎንህ ላለው በርቶ ላንተ ይጨልማል
ሌትተቀን እየጣርክ ጠብ የሚል ይጠፋል
ያቀድከው ያለምከው አልሳካ ብሎህ
መጣ ያልከው ቀርቶ፣ደግ ያልከው ከፍቶብህ
የኔ ያልከው ወዳጅ የሩቅ ሰው ሁኖብህ
ውስጥህ ብቸኝነት ይሞላል ባዶነት
ድንግርግር ይልሀል ትርጉሙ የሂዎት
በዚህ የተነሳ ••••
አላስተኛ ብሎህ ሀሳቡ ጭንቀቱ
ከንቅልፍ ተኳርፈህ ይነጋል ለሊቱ
ከሰው ጋር መደብለቅ ማውራትና መሳቅ
ደርሶ ያስጠላሀል ልብህ ይሻል መራቅ
ግን የትስ ትሄዳለህ 🤔
የትም 🤷♂
ያኔ•••••
ከመኖር ብዙ አለ ካለመኖር ምንም
በማለት ዋጥ አርገህ አፍነህ ሁሉንም
የደስታ ወራትህ እስኪመጣ ድረስ
ብሶቱን ሀዘኑን ችለህ በመታገስ
ከክፍ ቀን ጋራ ድልባን ትኖራለህ
ወትሮስ ከግዜ ጋር
በየትኛው አቅምህ ጠብ ትጋበዛለህ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
ዋሽተሽኛል
ያኔ በፍቅር ምጥ በነበርነበት ወቅት
ፍቅር ፍቅር እያልን ስንጫወት
በነዚያ ውብ ግዝያት ውስጥ
ፍቅር ስሰጭኝ አኔም ላንቺ ስሰጥ
አንድ ቀን ማታ የነገርሽኝ ቃል
ዛሬ ሲታወሰኝ በጣም ይደንቀኛል ።
"እኔን ላተወኝ በሀዘን በደስታ ግዝያት
አሮጌውን ትተን ልንኖር አዲስ ህይወት
ተጋብተን ልጆች ሊኖሩን ለወደፊት
አኔን ላትረሳኝ ለደቂቃ፣ለሰዓታት "
ብለሽ ካስማልሽኝ በኋላ ሁሉን እንደማልኩት
አንችም ምለሽልኝ ነበር በጨረቃይቱ ፊት ።
ግን!
አንቺ ዋሽተሽኛል የዛን ዕለት
ያን ሁሉ መሀላ የማልሽበት
አንድ ምክንያት ነበረሽ የጓጓሽለት
ፍቅርን ተንተርሶ ገንዘብ መገብየት።
By #blue_fish ✍
👇👇👇
@seanlph
💝የሰርግህ ለት ልምጣ !!💞
እንደ አደይ አበባ ፣በአመት እንደሚታይ
ከምሽት ጨረቃ ፣ከማለዳ ፀሀይ
ትፈካለህ በጣም
የገላህ መአዛ ፣ ሽቶን አይወክልም
ቃላት ብደረድር ፣አንተን አይገልፅህም
እባክህ የኔ ዉድ፣ ለምን አትበለኝ
🙄የሰርግህ ለት ልምጣ
ለምን አትበለኝ፣ ለምንስ ልበልህ
ማንም ሰዉ የለኝም ፣እንዳተ የምወደዉ
እኔ የምወደው ፣አንድ አንተን ብቻ ነዉ
❤️
ሌላ እንዳላፈቅር ፣አንተን የሚያስረሳ
ልቤ ተሰቀለ፣ እንደቀላል ቦርሳ
በልብ አልባ ምኞት ፣ሌላ ሰዉ አፍቅሬ
መኖር እንደማልችል ፣ ታውቀዋለህ ፍቅሬ
ስለዚህ አለሜ ፣ለሰርግህ ለት ልምጣ
ግልምጫ እችላለሁ ፣የፈለገው ይምጣ
ቃል ካፍህ ይውጣና ፣ ወይ ያንችው ነኝ በለኝ
ወይ ፍቅርህን ፣ወስደህ ልቤን ካልሰጠህኝ
አንተ ሰርግ መምጣቱ፣ መቸም አይሰለቸኝ
ግን ልንገርህማ 😭
ከኔ ርቆ መሄድ ፣አንትን ደስ ካለህ
የኔ መበሳቆል፣ አንተን ካላመመህ
በቃ እኔ ማንባቴ፣ ምንም ካልመሰለህ
ደፍረህ ከነገርከኝ፣ ላገባ ነው ብለህ
ሰርግ ላይ ልምጣ !!
ታዳሚ መሆኔ፣ አንተን ካልደበረህ
ከጀርባህም አልሆን፣ ፊት ለፊትህ ቆሜ
ልመለከትህ ነዉ ፣ባልበረታው አቅሜ
ማዱን ልትቋደስ ፣ ተከተይ ስትላት
እኔ ልመልከትህ ፣የሷን እጅ ይዘህ
የቤሎ ጫፍ ይዥ፣ እልልልልልል ልበልልህ
ለእዉተኛ ፍቅሬ ፣ምስክር ይሁንህ
✍️የሚገርመው ነገር ?
ሰርግህ መምጣቴ ፣ደስታ ተሰጠህ
ልዘፍን ነው በቃ፣ አሁኑ ታያለህ
🎤🎼🎧
ለዉነተኛ ፍቅር ፣ነበረ ምኞቴ
ሳይገባህ ቀረ ፣እንጅ ይህ መንከራተቴ
እያልኩኝ ፣አዜምልሀለሁ
ማልቀስ እያማረኝ ፣ እገለፍጣለሁ
ሀዘን የተባለ ፣ከፊቴ አርቃለሁ
ትልቁ ደስታህ ፣የሰርግህ ለት ላንተ
በቃ እጨፍራለሁ፣ አላስብም እንዳንተ
ልቤን እያመመኝ ፣መቆየት ቢያቅተኝ
በግድ እስቃለሁ ፣ አታየኝም ከፍቶኝ
✍️የኔ ምኞት ላንተ
በህይወት ዘመንህ ፣ ላፍታ እንዳትከፋ
ወልዳችሁ ከብዳችሁ ፣ልያችሁ በይፋ
ስጦታ ሰጥቸህ ፣መብሩክም ልበልህ
ስታየው በድንገት፣ እኔ ትዝ እንድልህ
ካለሁበት ቦታ ፣ዳግም እንዳላይህ
እኔ በትዝታህ፣ ልሙት እያለምኩህ
✍️ የዘገየ ተስፋ የከበረ ቀን አለዉ
#ሂኩ_ነኝ Feb 24/2021
👇👇👇
@seanlph
ለሱ
ህልሜ እውን ሆኖ ቢፈጥርልኝ ደስታ
የየቀኑ ማለም ሆኖልኝ እርካታ
የት አድርሶኝ ነበር የማልመው ደስታ
ግና ሆኖ ቀርቷል የተጨበጠ ጭስ
እሱም ላያስበኝ ዳግም ላይመለስ
ምነው ባያደክመኝ ህልም ብሎ መንፈስ
ማሂ
08/06/2013

👇👇👇
@seanlph
በፈገግታ ግርዶሽ ብሶት ተደብቆ
የደላው ይመስላል ሰው ሲታይ ስቆ
#በደግ_እደሩ 🙏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ፀሀፊና ከንባቢ
ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋
✍ @surabirabiro 🦋
#ልቤ_ነው_ህመሜ 😢
ጎኔ ችሎበታል ታሞ ደህና መምሰል
ለ ጥርሴም አይገደው መሳቁ የይምሰል
ሆዴም ቆዬ ለምዷል እራብን መታገስ
አይኔም እንባ ቢያቁር ያቆያል ሳያፈስ
እግሬም ካልጠሩበት ተነድቶ አይጎዝም
ጆሮዬም በወሬ ቂም በቀል አይዝም
ልቤ ነው ህመሜ እንደዚህ ያረገኝ
የማይመጣን ናፍቆ አንገቴን ያስደፋኝ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#ለምን_ዝም_አልካቼው ? 😢
#እናቱ_የተገደለችበት_ህፃን_ለጌታ_የፃፈው 😰
ድሄ እንኳ ሳልጨርስ እግሮቼ ሳይጠኑ
ሀዘን ጥላ አጥልቶ ሲጠቁርብኝ ቀኑ
ሲቀጥፉት በጧቱ እንቡጥ ጨቅላነቴን
አይቻት ሳልጠግብ ሲነጥቁኝ እናቴን
ለምን ዝም አልካቼው 😢
እንባዋን በማዝነብ ወድቃ እየለመነች
ለልጄ ስትሉ የዛሬን እያለች
ከምንም ሳይቆጥሯት በለቅሶዋ ስቀው
በግፍ ብትራቼው ሲገሏት ቀጥቅጠው
ለምን ዝም አልካቼው 😢
ሰውነት በራቀው እምነት የለሽ ምግባር
ምንም ሳታጠፋ ሳደርስ ከሰው ዳር
ዘርና ብሄሯ ተቆጥሮ እንደ ወንጀል
በግፍ ስትገደል አውሬ በሆነ አመል
ለምን ዝም አልካቼው 😢
እነሱ ባይራሩ ቢጨክኑ እኔ ላይ
አንተ አንዴት አስቻለህ እያየህ ከበላይ
በማን ልትክሰኝ ነው አሁን በሷ ቦታ
ያለ እናት ሲያስቀሩኝ ያለስቆምከው ጌታ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
👫 💓 👫
ርቀት ገድቦት : ትዝታ ሚቃትት
በማግኜት ምኞት : ሀሳብ ሚዋትት
አለ ብዙ ፍቅር : አለ ብዙ መውደድ
ሁሌ ነጋ ጠባ : በናፍቆት የሚነድ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#የዋህ_ህዝብ_እኮ_ነን 👨👨👦 😢😢
ቁሞ ሚያሳርደን የመጣ የሄደው
ጉሬ ሚምስልን ይበጀናል ያልነው
ለሁሉ አሚን ባዮች ለርግማን ምርቃን
የግፍ በደል ብትር መቶን ያላበቃን
የዋህ ህዝብ እኮ ነን 😏
አይዟችሁ የሚል መግለጫ እያወጋ
በማግስቱ እኛኑ ከጀርባ ሚያስወጋ
ሳቃችንን ነፍጎ እንባ የሚያድለን
የሰላም ተጠሪ ትጉህ መሪ ያለን
የዋህ ህዝብ እኮ ነን 😏
በኑሮው ባንወድቅ እንዲጥለን ጥይት
እቅድ ተነድፎልን በገዳይ ውይይት
ብስራት እያለምን መርዶ ሚጠብቀን
ሳንኖር የምንሞት ሰርክ በሰቀቀን
የዋህ ህዝብ እኮ ነን 😏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#በሂዎት_ጉዞ_ውስጥ_ሁሉም_የሚሆንበት_የራሱ_ምክኒያት_አለው 🤷♂
#ጨለማን ባናውቅ ኑሮ #የብርሀንን ዋጋ ባልተገነዘብን ነበር ፣ #ማጣትን ባናይም #የማግኛት ትርጉም በቅጡ ባልገባን ነበር ፣ #የደግ_ሰዎችን ግምት አንድናቅ የሚያደርገንም #የክፉወች መኖር ነው።
ሁሉም የሚሆንበት የራሱ ምክንያት አለው በቃ አየህ የሂዎት ገፆች ብዙና የተለያዩ ናቸው ሁሉም ገፆች #መልካምና_ጥሩ እንዲሆኑ ግን መጠበቅ የለብህም። የንጋቷን ፀሀይ ለመሞቅ የለሊቱን ጨለማ በትግስት ማሳለፍ የግድ ነውና ስለዚህ አንድ የመኖር እንቅፋት አደናቀፈኝ ብለህ በፉፁም እንዳትቆም ። #ልብ_በል ወዳጄ ባንተ መቆም የሚቆም ባንተ መኖር የሚኖር በመሳቅህ የሚስቅ ቢያንስ አንድ ሰው አለ ስለዚህ የፈለገውን ያክል ነገሮች አሰልቺ ቢሆኑብህ እንኳ #ተስፋ_መቁረጥን የመጨረሻ ምርጫህ እንኳ አታድርገው ። ከፈጣሪህ አትራቅ ፣ ዛሬ ላይ ማድረግ ያለብህን ካንተ የሚጠበቀውን ያቅምህን እያደረክ ነገን መልካም እንደሚሆን #ተስፋ አድርግ ። ሁሉም ወቅቱን ጠብቆ መልካም ይሆናል 👍
#መልካም_ምሽት
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
😢 😢 😢
ያለንበት ዘመን እጅግ ከመክፋቱ
ከመኖሩ ይልቅ ተላምዶናል ሞቱ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
#እሞታለሁ_እኔ 😢
አሁን በዚ ሰአት ወይ ቆየት ብሎ፣
ካልሆነ ነገ ላይ እንዲያም ካለ ዘሎ፣
ሰኞ ወይ ማክሰኞ ካልሆነ ሮብ ሀሙስ ፣
ወይ አርብ ወይ ቅዳሜ ወይ እሁድ ሲደርስ ፣
ዘንድሮ ወይ ከርሞ ብቻ የሆነ አመት
እሞታለሁ እኔ አንድ ቀን በድንገት
መስከረም ወይ ጥቅምት አልያም በህዳር፣
እንዲያም ካለ በጥር ወይ በየካቲት ዳር ፣
ወይ መጋቢት ሚያዚያ ፣ ወይ በግንቦት ሰኔ፣
የሆነ አንድ እለት እሞታለሁ እኔ
በውል ባላውቀውም 🤔
ቀን ይሁን ሌት ይሁን ሀምሌ ወይ ነሀሴ
አዎ እሞታለሁኝ ትወጣለች ነፍሴ
ታዲያ ለምን ይሆን •••• 🤷♂
ማን አለብኝ በሚል ሰው ላይ የምከፋው፣
መጥቀም እየቻልኩኝ ልጎዳ ምለፋው፣
ምክኒያት መሆን ስችል ለደስታና ሳቁ፣
መጣሬስ ለምን ነው አዝኖ ለመውደቁ ፣
መምከር ሲኖርብኝ ሀሜት አሳድጄ ፣
ደርሼ ማስከፋው እያለኝ ወዳጄ ፣
ቅንነት እያለ ክፍትን መርጬ ፣
የእውነትን መንገድ ሳለ ውሼት አቋርጬ፣
በመሆን ገላዬ ማስመሰል ለብሼ፣
ለግዚያዊ ኑሮ ውስጤን አቆሽሼ ፣
መውደድ እየቻልኩኝ ቁሜ በጥላቻ፣
ከይቅርታ ይልቅ የቀለለኝ ዛቻ ፣
ምን ይባላል ኧረ •••• 😞
የኔ ግድ ማጣት የኔ ገደብ ማለፍ ፣
ደግነትን ጠልቶ ለክፋት መሰለፍ፣
እኔ ብቻ በሚል ራስ ወዳድነት ፣
ለማላቀው ነገ መውረድ ከሰውነት፣
ድንገት ተሰባሪ ይዤ ፈራሽ ገላ ፣
በጭፍን መጓዜ ማለፍ ከምነት ኬላ፣
ከቶ ለምን ይሆን ምን ተማምኖስ ጎኔ
የኔም ተራኮ አለ እሞታለሁ እኔ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph
ሀገር በኔ ቀለም፦
💚💛❤️
.. በደም ነጠብጣቦች የተሞላች ሸራ
በአጥንቶች ቁርኝት የቆመች ተራራ
ሀገር ማለት ለኔ...🤗
የደስታ ድንቅ አምባ የመወደድ ውበት
የከፍታ መረብ የተስፋ ጕልላት
የድንቅ ውበት ጥምር የተፈጥሮ ፍካት
ሀገር በኔ ቀለም፦
የመጨረሻይቱ የእስትንፋስ ስቅታ
የፍቅር ልህቀት ጫፉ የደስታ
...
እናም ኢትዮጵያዬ፦
የሳቄ ጥግ ናት የመኖሬ ቅመም
እንዲህ ተስላለች ሀገር በኔ ቀለም።
💚💛❤️
ተጻፈ በሀይሚ ጥር 28 /2013 ደ/ታቦር ከሰዓት✍️
@haymihabeshawit
👇👇👇
@seanlph
ዳግምሽ አትቀስቅሰኝ
ዳግምሽ አትቀስቅሰኝ
አታንቃኝ ልተኛ
ወሬህም ይቅርብኝ አርፌ እንድተኛ
ትላንት ስለ ዛሬ ባታዉቅም ጠንቅቃ
የወደፊትዋንም ባታስብ አርቃ
ሁሌ ትማራለቸ ካለፈዉ ሂወትዋ
እና እልሀለዉ አብረን ሳለን ያኔ
በጣፋጭ ቃላትህ በማስመሰል ዘዴ
ተክነህ በፍቅር ስትመጣ ወደኔ
በማሬ በውዴ በውሸት መውደድህ
በማያልቀው ወሬህ ስትማርክ መኖረህ
በውሸት ፈገግታህ ልቤን ያንተ አረገሀት
ያላንቺ ጎጆዬ ፍፁም አይሞቃት
የመኖሬ ሚስጥር ግራ ጎኔ ነሽ
እያልክ እንዳልነበር አበድኩ ሞትኩልሽ
ታዲያ ይሄ ፍቅርህ ወዴት ገባ ዛሬ
ከሰው ወደ አውሬነት እንዲህ የለወጠህ
ሁሌ ከኔጋ ነህ ብዬ ስጠብቅህ
ዛሬ ከሌላጋ ሆነህ አየውህ
ምንድነው ጥፋቴ ልቤን የሰበርከው
ከሰዎች አርቀህ ብቸኛ ያረከዉ
እካ ለምን እስኪ ንገረኝ ላድምጥ መልስህን
ምክኒያቴ ይህነዉ በልና እስኪ አስረዳኝ
ቢገባህ አምኜህ ነበረ ልቤ ተቀብሎህ
በዉስጤ ቤትህን ጥሩ አርገህ ሰርተህ
በሀዘን በደስታህ ሊቆም ከጎንህ
ከሰው መሀል መርጦ ለየት ያረገህ
ትሆናለህ ብሎ ፍቅር የቸረህ
አንተ ግን
ልቤ የቸረህን ንፁ ፍቅር ጥለህ
እንዳሻህ መሆኑን ከተመኝው ልብህ
ጊዜያዊ ከሆነ ያንተ ፍቅር ለኔ
ይቅርብኝ ፍቅርህም ያዛልቅህ መንገድህ
ቸር ይግጠምህ ብዬ መርቄ ሸኝውህ
በቃ አትቀስቅሰኝ ልተኛ እንቅልፌን
ዳግምሽ እየመጣህ እረፍት አታሳጣኝ
ልቀመጥ አርፌ ተንፈስ ይበል ልቤ
ለኔ የሚሆነኝ እስካገኝ የራሴ
#ፋሲካ ✍
👇👇👇
@seanlph
ጭፍን መውደድ
ማይቀየር ስሜት ደርሶ የማይጠፋ
የማይፋቅ መውደድ በመነነ ተስፋ
የተለየ ፍቅር የተለየ መውደድ
ራስን የሚያስት የሚያስቀር ከመንገድ
ተትቶም የማይተው ዘመን የሚሻገር
ፍፁም ማይረሳ በልብ የሚቀበር
ማይደበዝዝ መውደድ ካንጀት የሚታሰር
ለቆም የማይወጣ ርቆም የማይርቅ
ጭፍን መውደድ አለ ሕይወትን የሚሰርቅ
ጭፍን ማፋቀር አለ ከራስ የሚያኳርፍ
ደስታን እያስረሳ ሀዘን የሚያሳቅፍ
ጭፍን መውደድ አለ መኖርን የሚንድ
ራስን አስትቶ ሌላ የሚያስወድድ
#ሊሊ_ከተማ ✍
👇👇👇
@seanlph
አለሜ አንዳንዴ ወፈፍ ሲያደርገኝ
ፍቅርሽ ከህልሜ አለም ሲያባንነኝ
ስለአንቺ ልገጥም ብዕሬን አነሳለሁ
አንችን ለመሳልም ብሩሼን አዘጋጃለሁ
ግን ውዴ
አንዱንም ሳላከናውን ሁሉን እተወዋለሁ
ምክንያቱም
አንችን ለማድነቅ በቃላት ለማስዋብ
ቅኔ ለመዝረፍ ግጥም ለመክተብ
በደማቅ ቀለም አንቺ ለመሳል
ስሞክር
ቃላቶች ትርጉም~ያጣሉ
ጣቶቼም ሼባ~ይሆናሉ
ብዕሬም ~ይደክማል
ብሩሼም~ይለግማል
#እናቴ_በስምሽ_ልጠራ
👇👇👇
@seanlph
🖍🖍🖍🖍🖍🖍🖌🖌🖌🖌🖌📝
#የዚህ_ቻናል_አባል_ለሆኑ_ብቻ 🙅♂
የራሳችሁ የሆነ ( በእናንተው የተፃፈ) #ግጥም አልያም ሌላ #ታሪክ ያላችሁ እና ቻናል ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉ ✍ ከግጥማችሁ ስር ላይ #ስማችሁን በአማርኛ በማስገባት በውስጥ መስመር 👉 @seanpoems ላይ ላኩልኝ ወደቻናሉ ላይ በመልቀቅ ከታዳሚያን አስተያየት እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ 🙏🙏🙏
😳😳😳😳😳😳 #የራስ_ያልሆነን_ግጥም_የኔ_ነው_እንደማለት_ጥልቅ_ነውር_የለምና_አደራ 😡😡
👇👇👇
@seanlph
#ብቻ_አንተ_ታገሰው 🤭
ጨለማው መንጋቱ ላይቀር ማስፈራቱ
ሊያልፍ ቀን በጊዜው ሆድን ማራራቱ
ሀዘን ከጭንቅ ጋር ሊያብር መዳራቱ
ይቺ አለም እንዲህ ናት ፊቷ ዠጎርጓራ
ያሽመደምድሀል ጩኸቷ እያጓራ
አንተ ግን አትስማው ይህም ቀን ያልፍ የለ
ያፅናናሀል ጌታ እኔ አለሁ እያለ
ብቻ አንተ ታገሰው ውጣና ውረዱን
ያኔ ትረዳለህ ጌታ አንተን መውደዱን
#ዘታዲያን ✍
👇👇👇
@seanlph
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
በመሀመድ ሙፍቲ (ጀዋድ)
ተፅፎ
በሱራፌል ጌትነት(ሱራ ቢራቢሮ🦋)
የቀረበ
✅🗣 @surabirabiro ✅🦋
#ልብ_ካለህ 😜💪
ከኒያ ሁላ እለት አንዱን ብቻ መርጠህ
ከሞሉት ልብሶችህ ቀዩን ተጠቅልለህ
ሲያደርጉ ስላየህ ሌሎችን ልትመስል
ስጦታ አታምጣልኝ ልቤን ልትደልል
ይ
ል
ቅ
መውደድ ቀን ገድበህ ከምትለኝ በአል
የእውነት ካፈቀርከኝ አግባኝ ሁንና ባል
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph