seanlph | Unsorted

Telegram-канал seanlph - የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

7500

በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም

Subscribe to a channel

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ይቅርታ......🚶‍♂
እንዲያ ላፈቀርኩሽ _ ከራሴ አስበልጬ 
  ስርሽ ስርሽ ላልኩት _ አንቺኑ መርጬ
   የግሌ ላደርግሽ _ እየተፍጨረጨርኩ
     ያለፍላጎትሽ  _ አንቺን ስላደከምኩ
ይቅርታ ...... 🙏
ስትዋሺ አምኜ  _ ስትንቂኝ አክብሬ
እየተለማመጥኩ _  ከጎንሽ አድሬ
እስክትሰለቺኝ  _ ችክ ስላልኩብሽ
ግድ የኔ ሁኝ ብዬ _ ለተለጠፍኩብሽ
ስላለፈው ሁሉ _ ፍቅሬን ስል ላረኩት
ይቅርታ አድርጊልኝ _ ትናንት ለሰራሁት
ዛሬ ሄጃለሁኝ  _ አረብሽም ዳግም
መቸም አልመለስ _ ካለሽበት ግድም
   #ሼን ✍

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

👆👆👆👆👆👆👆
በዚህ ቻሌንጅ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴቶች ካላችሁ ቪዲዮውን ስሙትና መስፈርቱን አምናችሁበት ከተቀበላችሁት 👉 @gitmsetim ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMNKbKw1n/

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

"ናፍቀኸኛል አትበይ"
አንቺ እንደፈለግሽው ሲያሻሽ ስትመጪ፣
ሲያሻሽ ደግሞ ስቴጅ የሚሻል መረጣ ፣
ካኖርሽበት ቦታ ቁሞ ሚጠብቅሽ ፣
ያ የድሮው ወዳጅ እንዲያ የሚወድሽ ፣
ይኖር የነበረው ያንቺንም የሱንም ፣
ደስታ ሚለግስሽ ያለምላሽ ጥቅም፣
ነገ ላይ እንድረስ ዛሬን እንሻገር፣
ይልሽ የነበረው ያ ያንቺው ገራገር፣
ያንኳን የማይርቅሽ በደግ በክፉ፣
ወዳጄ ያልሻቸው እንዳላዬ ሲያልፉ፣
አዎ ያንቺው ወዳጅ ህመምሽ የሚያመው
ላገኜሽ እንቅፋት አብሮ ሚያነክሰው
ምቶጂውን ወዶ ስጠይም እርቆ ፣
ወረት ሳይለውጠው ከጎንሽ ተጣብቆ ፣
ቀድሞ ሚሞትልሽ ስላንቺ ተጨንቆ፣
ያ የዋሁ ጎንሽ
ኗሪው እንዳመልህሽ
ድግምግም ጥፋትሽ ሳያሳጣው ተስፋ፣
ፍቅሩን ቤቱን በሚል ዕልፍ ቀን ሲገፋ፣
የሆዱን በሆዱ አፍኖ እንደምንም ፣
ሲስቅ የምታቂው ፀብ እንዳይለመልም፣
ያ የዋሁ ጎንሽ የተውሽው አቅለሽ፣
የትም አይሄድ ያልሽው መውደዱን ኮንነሽ፣
ላሳለፈው ስቃይ ለታገሰው መአት
ፍቅር ግፉን ቆጥሮ ክሶት እኒያን ትናንት
አዲስ ሂዎት ሰጥቶት
ዛሬ ሌላ ሰው ነው አታውቂውም ከቶ
ፍፁም ተቀይሮ ከልቡም ሰው ገብቶ
አንቺን ላንቺነትሽ ለምኞትሽ ትቶ
ከነምናምንሽ ትናንትን ረስቶ
ሌላ አለም ውስጥ ነው የልኩን አግብቶ
እናም እየውልሽ
የማይመስል ምክኒያት ደርሶ በመቆለል
መመለስ አስበሽ ናፍቀኸኛል አትበይ
እውነታው ወዲህ ነው
መመለስ ያሻሽው ሳይሆን ስለናፈቅሽ
የኔ አይነት አጥተሽ ነው ሁሌም ላንቺ ኗሪ
እንዳልሽ ይሁን ብሎ ለሳቅ ደስታሽ ጣሪ
ያንቺን ቀን ለመውለድ የራሱን ቀባሪ
አዎን ስላጣሽ ነው
አንቺን የሚችልሽ ከናለሽ ባህሪ
#ሼን✍✍

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

"ሁኔታችን እያማረኝ አይደለም "
.......... ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት እርግፍ አድርጌ መቁረጡ ከብዶኝ አልያም ከተለየሁህ በዃላ ያለው የብቸኝነት ሂወቴ አስጨንቆኝ አይደለም : ወይ ደግሞ አንተ ከኔ ውጭ የሌላ ሴት ብትሆን ቅናቱ አያስቀምጠኝም የሚል ፍራቻ ውስጤን ሞልቶትም አይደለም ........ ግን እንዴት አድርጌ ፍቅሩን ከልቤ ላይ መፋቅ እችላለሁ ? " በየትኛውስ አቅሜ " 🤔 እንዴትስ አድርጌ እኒያን ሁሉ ትዝታዎች በቀላሉ መርሳትና እንዳልነበሩ አስቤ መኖር እችላለሁ ?🤔 የሚሉት ነገሮች ናቸው ሁሌም የሚያስፈሩኝ ... አየህ ያም ነው ዛሬ ጓንህ የመሆኔ ምክኒያት የሆነው ......... ነገስ ???? እንጃ 🤷‍♀
#ሼን ✍

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMN7n8Qgr/

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMNGfhWUq/

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMNsrynoT/

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ፍቅር_እንዳይወድቅ 👫🌹💓
አብሮነቱ ደክሞት ፍቅር እንዳይወድቅ
ስናጠፋ እንመን ፣ ይቅርታን እንጠይቅ
ንትርክ አናብዛ ፣ በትንሽ በትልቅ
ችሎ ማሳለፍን ፣ በልብ እንሰንቅ
ጥሩው ጎን ይታየን ፣ እንከን ብቻ አናሳድ
ሆደ ሰፊ እንሁን ፣ መውደድ እንዳይናድ
ኩርፊያን አናሰንብት፣ ፀብን እናቆረፍድ
በወቅት እንታረቅ ፣ በእልህ አናርፍድ
መግባባት አያለ ፣ አውርቶ በጋራ
ለወቀሳ አንሩጥ ፣ እንደ ባላንጋራ
እኔ ብቻ ከሚል ፣ ራስ ወዳድነት
እኛ የሚለውን ፣ እንመን አንድነት
አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እንባባል
በሀዘንም በደስታውም አብረን እንዋል
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ሌላ_ጎጆ_ሰራህ 🏠👫🥀
እዛና እዚህ ሳልል ባንተው ረግቼ
የብቻህ ለመሆን ምየ ተገዝቼ
በብሶት በደስታህ ከጎንህ ቁሜያለሁ
ስትስቅ እየሳኩ ሲያምህ ታምሚያለሁ
ስጠላ ጠልቼ ስትወድ ወድጄ
በሄድክበት ሁላ አብሬ ነጉጄ
አንተኑ መስዬ አንተኑ ሩሪያለሁ
ብቻ ምን አለፋህ •••😏
ያልከውን ቃል ሁላ ከልቤ አምኛለሁ
ብዙ ብዙ አጥፍተህ ስቄም አልፊያለሁ
ነገ አብረን እንድኖን ዛሬን ገድያለሁ
አዳም ካንተ ወዲያ ለኔ ሁኖ ዘበት
ፍቅርህን አክብሬ ሁኛለሁ እመቤት
አንተ ግን ያንሁሉ ከቁብ ሳትቆጥር
መውደዴን አርክሰህ ቀልደህ በፍቅር
ልቤን ልትሰብር •••
እንዲህ ሆንኩ ሳትል ጠፋህ ከጎኔ ስር በደሌን ሳላቀው ምክንያቱም ሳይገባኝ
ከብቸኝነት ጥግ ለብቻዬ ተውከኝ
አለሁልሽ እያልክ ባዶ ተስፋ ሞልተህ
አንቺ ነሽ ሄዋኔ እያልክ ቀባጥረህ
ሲመችህ ጠብቀህ ሌላ ጎጆ ሰራህ
😢
••• ግዴለም ካዋጣህ •••
ተመለስም አልል ግድም አላቆይህ
እኔን ገፍተህ ሂደህ ቤቱ ከቆመልህ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

አርቆ ማሰብ ጠፍቶብናል ፣ መኖር ለዛሬ ብቻ መስሎናል ፣ መኖር ግን በእውነቱ ” ዛሬ ብቻ” ነው። ነገ እና ትላንት ሁለቱም ” አለመኖር” ናቸው። በመወለዳችን ምን ያህል እድለኞች እንደሆንን አናውቅም። እስኪ ያልተወለዱትን አስቧቸው፤ መኖር እኮ በአለመኖር ጥልቅ ውስጥ የተሰጠን ስጦታ ነው። ከዚህ በፊት አልነበርንም፣ ወደፊትም አንኖርም። ይህን ማስተዋል ለምን ተሳነን? ምክንያቱም ከሁሉም ህመማችን ስር የተሰወረብን እውነት ይኽ ነው።

ከ- አለመኖር
(ገፅ፡ 149)
ዳዊት ወንድምአገኝ(ዶ/ር)

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹👇👇👇
#ቲክ_ቶክ ላይ የራሳችሁን ቪዲዮ ለምትሰሩ ሴቶች እንዲሁም ለግጥም የሚሆን ድምፅ አለኝ ለምትሉ በኔ የተፃፉ #አጫጭር_ግጥሞችን በድምፅ እና በምስል እያነበቡ የማቅረብ #ቻሌንጅ በዚህ ቻናል ላይ ሊጀመር ስለሆነ በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከአሁን ሰአት ጀምሮ በውስጥ መስመር 👉 @seanpoems ላይ በመግባት መመዝገብ ትችላላችሁ 🙏
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

🤔
ገዳይ ተርመስምሶ ሟች በበዛው አለም
ደህና እንደመሰንበት የላቀ ሀብት የለም
#በደህና_ሰንብቱ_ክፉን_ይያዝላችሁ 🙏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

😂 😜 😂
ድሮም ወጥሽ አይጥም ፣ እንኳን ጠፍቶ ዘይት
ጤፍም ዋጋው ንሯል ፣ ጭንቅ ነው ግብይት
ከንግዲህ እንጀራ ፣ እርም ነው ለኔ ሆድ
ይልቅ ደፍተሽ ስጭኝ ፣ ከዳቦሽ ልላመድ
#ይሄንም_ቅኔ_ነው_በሉ_አሉ 😏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

😘 ❤️ 💓
ባሳብ የለሽ ውሎ መፍለቅለቅ መቦረቅ
በንፁህ ህሊና እንቅልፍ ላይ መውደቅ
ደስ ይላል ልጅነት
ክፋትም የለበት
#በደግ_እደሩ 🙏
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በዚህ ቻሌንጅ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴቶች  👉 @gitmsetim ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

👆👆👆👆👆👆👆
ለአዲስ አመት አዲስ ሴት 👌 ሴቶች አዳምጡት

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMNckBDEE/

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

"ያቺ ሴት"
በልኩ ተሰርቶ
ልቧ ሰው አግኝቶ
ያለፈን ሰርዛ ዛሬን ብታፀድቅ
የትዝታ ቁስሏን ችላ ብታደርቅ
ሀዘኖቿን ሽራ ሳቋን ብታነግስ
ከብሶት ተላቃ ደስታዋን ብትመልስ
ዳግም ካሻት ጋራ ተሳስራ በፍቅር
አብሮነትን ለምዳ ጎጆ ብታዋቅር
ደስታው ለሷ ነበር
ምኞት ሁኖ ባይቀር
።። ግና ምን ዋጋ አለው ።።።
ትናንት የመጣችው የውሻሸት ጉዞ
እምነቷን አሟጦ ተስፋን አደብዝዞ
ውስጧን አዳክሞታል እንደምን ትበርታ
በምን አቅሟስ ትቁም ካዲስ ሂዎት ተርታ
#ያቺ_ሴት_ታሳዝነኛለች 😢
#ሼን ✍

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

ሞኝ ......
ያቺን ላንተ ደስታ ካሏት ዲንጋ የምትፈልጥ የነበረችን ፣ ላንተ በማለት ሁሉ ነገሯን የተወችልህን ያቺን "የዋህ አፍቃሪህን" ገፍተሀት መሄድህን እንጂ ማን ላይ እንደጣልካት ዞረህ አላየሀትም.... "የወደቀች" መስሎህ ነዋ ስቀህ የሄድከው 🤔 " ሞኝ " ስትገፋት ማን ላይ እንዳረፈች በቅርቡ የምታውቅ ይሆናል ያኔ ምን ያክል ታላቅ ውለታን እንደዋልክላት በደንብ ይገባሀል ...........ሞኝ 🤷‍♂

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

ቲክ ቶክ ያላችሁ ኮሜንት አድርጉ 👌

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

የአመቱ ምርጥ ምክር ለሴቶች 👇👇👇

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

https://vm.tiktok.com/ZMNpw1YwH/?k=1

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

💎ፊት ለፊት ትይዩ የተገነቡ ሁለት ቤቶች አሉ ። በሁለቱ ቤቶች ጣሪያዎች ላይ ደግሞ የእግር መርገጫ ስፋት ብቻ ያለው የጣውላ መረማመጃ ድልድይ ቢጋደምና በላዩ ላይ ተራምዳችሁ ከአንዱ ጣርያ ወደሌላው እንድትሻገሩ ብትጠየቁ ፈቃደኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ይኸው ጣውላ መሬት ላይ ተጋድሞላችሁ እንድትራመዱበት ብትጠየቁ ግን ህፃን ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳይባል ፣ ሁላችሁም ሳትወድቁ ትራመዱበታላችሁ ።

📜 የጣውላ መረማመጃው ያው ነው ፤ እናንተም ያው እናንተው ናችሁ ፤ ታድያ ጣውላው በቤቶቹ ጣሪያዎች ላይ በተጋደመ ጊዜ እንድትራመዱበት ስትጠየቁ ለምን እምቢ አላችሁ? መሬት ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሳይወድቁ ተረማምደውበታል ። ታድያ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው ።

🔑 መሬት ላይ ተጋድሞ ሳለ ጣውላው ላይ ለመረማመድ ንቁ መሆን አያስፈልግም ።ንቃት አልባ ሆናችሁ ልትራመዱ ትችላላችሁ ። በጣውላው ላይ ተረማምዳችሁ ከጣሪያ ጣርያ ለመሻገር ግን ንቁ መሆን ይኖርባችኋል ። ንቃት እንደሌለን እናውቃለን ፤ በዚህም ምክንያት ወድቀን እንዳንሞት እንፈራለን ። መሬት ላይ ስንራመድ ግን ብንወድቅ እንኳን እንደማንሞት እናውቃለን ።

💎 አልፎ አልፎ አደጋ በሚያጋጥመን ቅፅበት ንቃት ይኖራል ። ሌላ ግዜ ግን እንቅልፍ ላይ ነን ። ሞት ሲቀርበን ንቃት ይኖራል ፤ አለዚያ ግን ንቁ አይደለንም ። ልማዶቻችንን መቀየር የማንፈልገው ለዚህ ነው ፤ ምክንያቱም ልማዶች ሲለወጡ ንቁ መሆን ያስፈልጋል ። አሮጌ ልማዶች የእናንተን ንቃት አይፈልጉም ።

📖 የንቃት ፀሃይ /ኦሾ/
ገጽ 99-100
ትርጉም ✍ መርሻ በነበሩ
ምንጭ - ከስብዕናችን ገፅ

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ነይልኝ 🤪
እወድሻለሁ ስል እያነሰኝ ቃላት
ሁሌ እጨነቃለሁ ብዬ ምን ልበላት
አንችን ስለማይገልፅ ቃል በቃል ቢተካ
ወር ሞልቶ አገኝቸሽ ምኞቴ ይሳካ
ባንችኮ ናፍቆት ነው ማሰብ መተከዜ
እዳም በዝቶብኛል ነይልኝ ደሟዜ
#ሼን ✍

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#አለ_ወይ_የኔ_አይነት😞
ፈች ያጡ ችግሮች በመዳፎቹ አቅፎ
ውስብስብ ሀሳቦች ውስጡ ላይ ቆልፎ
ግዜ የሚሉት ቁልፍ ይፈታዋል በሚል
በጭላንጭል ተስፋ ነገን ሊያለመልም
በነጭ ጥርሶቹ የውሸት ሳቅ ስቆ
ደልቶት ነው እስኪባል የይምሰል ቦርቆ
ብዙ የቀን ጥቁሮች ብቻውን የገፋ
አለ ወይ የኔ አይነት
ብሶትና ሀዘን ደራርቦ ያጣፋ
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ማደግ_ፈርቻለሁ 🤦‍♀
መማር ነፍስ ማወቅ ፣ ክፍ ደግ መለየት
ነገ ሰው ለመሆን ፣ ነበር የኔ ምኞት
ዛሬ ግን በማየው ፣ በምሰማው ወሬ
አድገናል የሚሉት ፣ እየሆኑ እንዳውሬ
ከሰውነት ጎለው ፣ ህሊናን ሲቀብሩ
በዘር በጎጥ ሀሳብ ፣ ደርሰው ሲታወሩ
መግደል ስራ ሲሆን፣ ፈጠሪ ተረስቶ
መርዶ ብቻ ሲሆን ፣ የሚወራው ነግቶ
••• ማደግ ፈርቻለሁ •••
ትልቅ ለመሆንም የነበረኝ ተስፋ
'ሰው'ነትን ፈርቶ ተቃርቧል ሊጠፋ
#ሰላም_ለኢትዮጲያ 🇪🇹
#ሼን✍✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#ልመርቅሽ_በይኝ_ጀባ 🙏💓🌷
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ
ያብብ መልክሽ እንዳበባ
እንዳደሱ እንደ ጪስሽ
ያውድ ጥሩ ፌስቡክ ቤትሽ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
ካርድ አትጪ ዳታሽ ይብራ
ላይክ አድራጊሽ ይበል ጎራ
ሼር ኮሜንትሽ አያባራ
ጠላትሽም ይሁን ተራ
አዎ እቴዋ 🙏
ዙሪያ ገባው ቆላም ደጋም
ሀገር ቀየሽ ይሁን ሰላም
ሁሌም ሳቂ አትዘኚ
በሀቅ ሚዛን ተመዘኚ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
ግዜን አጨልሞ አንፖል ነን ከሚሉ
በሰው እንባና ደም ስቃይ ከሚስሉ
በግፋቼው ብትር ደርሰው ከሚመቱሽ
ፈጣሪ በጥበብ አርቆ ያኑርሽ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
ይሰውርሽ ከጂል ፍሬንድ ከዘረኛ
የሰው እምነት ከሚሳደብ በሽተኛ
በፖሰትሽው ከሚናደድ ቀናተኛ
ይጠብቅሽ ••••••••• ከምቀኛ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
ካዲስ ጀንጃኝ ከሆነ አዛ
ማሬ ውዴ ከሚያበዛ
ይጠብቅሽ ከሞዛዛ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
ስልክ ቁጥር ላኪ ከሚል
ቢሰጡትም ከማይደውል
በባዶ አንጀት ከሚያደርቅሽ
ልብ አውላቂ ይደብቅሽ
ልመርቅሽ በይኝ ጀባ 😂
እንደፈላው ቆንጆው ቡና
የኔ አይነት ልጅ መልከቀና
ላግባሽ ብሎ ይላክልሽ ሽምግልና 😜
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

#የኛስ_የት_ድረስ_ነው 😭 🤔
ሯንዳም በአንድ ወቅት ስጀምር የዘር ጥል
ልክ እንደኛ እንዳሁን ነበር የሚመስል
እየዋል እያደር ነገሩ ተካሮ
እንደዋዛ ገኖ መልኩንም ቀይሮ
ምድሯን ደም ጨቀየው እልቂት ነገሰ
እልፍ የሰው አስክሬን አፈር ተለወሰ
አጥንት እንደ ጠጠር ረክሶ ተንቆ
በወግ ሳይቀበር ተረሳ እዛው ወድቆ
እናት ልጇን አጣች ልጅ ያለናት ቀረ
ሀዘን ቅጡን አጣ ለወሬም ቸገረ
በጥቂቶች ስተት በጥቂቶች ችግር
ሺ ዎች ተማገዱ ከሞቱ ግርግር
የኛስ የት ድረስ ነው የዛሬው ጉዟችን ?
ቆም ብለን እናስብ 🤔
በኛው እንዳይማስ የገዛ ቀብራችን
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

😢 😢
ተበዳይን ገፍቶ ግፈኛን በማክበር
ግዜም አሽቃበጠ ለገዳይ በማበር
#ሼን ✍
👇👇👇
@seanlph

Читать полностью…
Subscribe to a channel