ተሰምቷቹህ ያውቃል ...🤔
ምን እየሰራሁ ነው _ የት ጋር ነው የቆምኩት
እያሉ ከራስ ጋር _ መሟገት ቀን ከሌት
ግራ ግብት ያለው _ ዥዋዥዌ ስሜት
ተሰምቷቹህ ያውቃል ...🤔
እቅዳችሁ ሌላ _ የሚሆነው ሌላ
ጠበቀ ስትሉት _ መልሶ እሚላላ
በማድረግ በመተው _ መሀል መወዛገብ
መልስ አልባ ጥያቄን _ ቀን ከሌት መሰብሰብ
ዝም ብሎ መተኛት _ ሲነጋ መነሳት
ያለቅድ ተጉዞ _ ተመልሶ መምጣት
በውሸት ፈገግታ _ አስመስሎ መዋል
ምን አለበት እሱ _ እንደደላው መባል
ብዙ አይነት ሀሳቦች _ እያነሱ መጣል
የተደጋገመ አንድ _ አይነት ቀን መግፋት
ነገን አለመዋቅ ....
ለብዙ ነገሮች _ ደርሶ ትርጉም ማጣት
ተሰምቷቹህ ያውቃል ...🤔
#ሼን ✍️
#ለሰላም_ከሆነ_አዎ_አሽቃብጣለሁ
ሲናቅ ዝም ካልኩኝ ያብሮ አደጌ ማተብ
ሲጣስ ዝም ካልኩኝ የቤተስኪያን አደብ
ያ ሰው ሰነባብቶ ሴራ በመሰብሰብ
የኔንም መስገጃ ይቀማኛል በደንብ
አየህ አይከብደኝም ነግበኔዬን ማሰብ
በዳይ ቢሆኑ እንኳ እናትና አባቴ
ከተበዳይ ጎን ሁን ብሎኛል እምነቴ
ታዲያ
ቤተ እምነት ታውኮ ሀዘን ባጠላባት
ኦርቶዶክሱ ጓዴ አንገት በደፋበት
በዚህ የቀን ጥቁር
በምችለው ካልቆምኩ ካልሆንኩኝ ከጎኑ
ምኑ ላይ ሰው ሆንኩኝ
ብሶቱ ካልባሰኝ ካልገባኝ ሀዘኑ
እናም እልሀለሁ......
በኔ ካልደረሰ ምን አገባኝ እኔ
ብዬ ዝም አልልም ይሄን አረመኔ
ህመሙ ያመኛል ኦርቶዶክስ ወገኔ
ደግሞ.....
ሰላም ከጠፋኮ ግማሽ ወገን ታሞ
ለኛም ይቸግራል
ከመስጊድ ለመስገድ በጀመአ ቁሞ
#ሼን ✍
#የውድድሩ_አጠቃላይ_መግለጫ 👌
🎁 ስታነቡ ከፈለጋችሁ በቃላችሁ አልያም ወረቀት ይዛችሁ በሁለቱም ይቻላል
🎁 ግጥሙን በቪዲዮ ስትሰሩ ሌላ የሚረብሽ ድምፅ ባይገባና ጥራት ያለው ቢሆን ይመረጣል
🎁 ማጀቢያ ሙዚቃ( ክላሲካል) ብትጠቀሙ ይበልጥ ሀሪፍ ነው
🎁 የምትመርጡት ግጥም አጪር ቢሆን
የተሻለ ነው
🎁 ግጥሙን አንብባችሁ ስትጨርሱ ይሄን ማለት ግድ አለባችሁ ___ እባላለሁ #የሼን ግጥሞችና እይታዎች የቲክቶክ ገፅ ተወዳዳሪ ነኝ
🎁 ግጥሙን የምታስገቡት እስከነገ ማለትም ረቡዕ 10 ሰአት ድረስ ነው
🎁 የሰራችሁትን ቪዲዮ ከስር ባስቀመጥኩት የኔ የቴሌግራም አካውንት ነው የምታስገቡልኝ
👉 @gitmsetim
👉 @gitmsetim
👉 @gitmsetim
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
ያልገባችሁን ነገር ለመጠየቅ 👉 @gitmsetim ላይ ታገኙኛላችሁ
"እመንና ሸኜኝ"
አብሬህ መሆኔ _ ደስታህን ካጠፋ
ከጎንህ ማደሬ _ ውስጥህን ካስከፋ
የሰጠሁህ ቦታ _ ካልጎላ ለልብህ
የሴትነት ምስሌ _ ካነሰብህ ላይንህ
እቅድህ ካልሆንኩኝ _ ለነገው ሂወትህ
አድሜዬን አልፍጅ እኔም _ አንተም አትቸገር
" አልወድሽም ብለህ "
እመንና ሸኜኝ _ እውነቱን ተናገር
#ሼን ✍
...... አላጋጠማችሁም.......
ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታል ፣ በተስፋ ይሞሉናል ፣በምኞት እሩቅ ያሳዩናል ፣ምርኩዝ የሆኑ መስለው እጃችንን አጥብቀው ይይዙታል ፣ያን ሰሞን ሆን ብለው ቀድሞ የማናውቀውን አለም ያሳዩናል ያው ሰው አይደለን እኛም 🤔 ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ያ አርፎ የተኛ ልባችን ዳግም ይቀሰቀሳል ፡ትናንትናውን ረስቶ አዲስ የሂዎት መንገድ ይጀምርና ፡ አሻግሮ ነገውን ያልማል፡ አጥብቆ የያዘን እጃቸው የማይለቀን የማይተወን መስሎን ሙሉ እኛነታችንን እነሱ ላይ እንጥላለን ፡ እነሱን እንደገፋለን .... ያን ጊዜ ድንገት እንደመጡት ድንገት ምስስ ብለው ከሂወታችን ይወጣሉ... ውረድ ብንለው በዋዛ የማይወርድ የትዝታ ጓዝ አሸክመውን ፡ የማይመለስ ጥያቄ ሰጥተውን እንዲህ ነው ብለው እንኳ ምክኒያታቸውን ሳይነግሩን ድንገት እንደገቡት ድንገት ጥለውን ይወጣሉ ...🚶♀🚶
አልነግርህም እንጂ በከፋህ ሰአትና ባመመህ ጊዜ ለኔ ያድርገው እያልኩ ለሊቱን ሙሉ እፀልይ ነበር .... አልነግርህም እንጂ ጥሩ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ምነው ለእሱ በሆነ ብዬም ደጋግሜ እመኝ ነበር ....አልነግርህም እንጂ እያስለቀስከኝ እንኳ ፊትህ ላይ ሳቅህን ነበር እፈልግ የነበረው .... አልነግርህም እንጂ ማፍቀሬ እንዳነሰብህ በድርጊቶችህ እያሳየኸኝ እንኳ እኔ ግን ስለወደፊታችን አልም ነበር ....
አልነግርህም እንጂ ስትዋሸኝ እውነታውን አውቅ ነበር .... አልነግርህም እንጂ እኔ ላንተ ብዙ ብዙ ነበርኩ .....
#ሼን ✍
"እየነገርኩሽ ነው "
አንዳንዴ ሰዎችን ከሂዎትሽ የምታስወጫቸው ስለማትወጃቸው ብቻ አይደለም የሚገባሽን ቦታና ክብር ሳይሰጡሽ ሲቀሩም ነው 🤷♂ አየሽ አብዝተሽ ስለወደድሻቸው ብቻ የትም አትሄድም በሚል የጂል ተረት እንዳሻቸው እየሆኑ ስሜትሽን ሲጎዱትና ክብርሽን ዝቅ ሲያደርጉት ደጋግመሽ እያየሽ አሁንም እዛው ቦታ ላይ መገኜት ትእግስት ሳይሆን "ሞኝነት" ነው ስለዚህ ዋጋሽን ጠንቅቀሽ እወቂ 🤔 እነሱን ካጣሁ በዃላ ምን እሆናለሁ ከሚል አጉል ፍራቻ ውጪ 😏 እነሱን ካጣሽ በዃላ ትክክለኛዋን አንቺን ነው የምታገኚው ...
"አንቺ ጀግና ሴት ነሽ"
አንቺ ጀግና ሴት ነሽ _ ፍፁም የበረታሽ
ውስጥሽ ያለን ህመም _ ለብቻሽ የረታሽ
ለሌላ ማይገባ _ ከሰው ያልደረሰ
ስቃይ ቁስል አዝለሽ _ ልብሽን ያራሰ
እጅሺን ያልሰጠሽ _ ለሂዎት ፈተና
ዕልፍ እሾህ ተሻግረሽ
ከዛሬ የደረሽ _ አዎ አንቺ ነሽ ጀግና
ሰው ቀርቦ ቢሸሽሽ _ እምነትሽን ቢያጓል
የነገው ሂዎትሽ _ የማይስተጓጎል
አጨለምናት ሲሉ _ ፈክተሽ የምትደምቂ
አስለቀስናት ሲሉ _ ንቀሽ የምትስቂ
ማለፍ የምታውቂ _ሁሉን ፈገግ ብለሽ
አንቺ ጀግና ሴት ነሽ
#ሼን ✍
"ሳቄ አይበረክትም"
ሰላም ሂወቴ ውስጥ _ ድንገት ጓራ ብለህ
አርፎ የነበረን _ ያን ልቤን ቀስቅሰህ
በተስፍ ሞላሀኝ _ ምኞት አሳለምከኝ
ትናትናን እርሺው _ ነገን እኑር አልከኝ
እጄን አጥብቀህ ያዝክ _ አምኜኝ ተደገፍኩ
ቁስሌን እረስቼ _ አዲስ ጉዞ ጀመርኩ
ሁሉን ላንተ ተውኩኝ _ ሰጠሁህ እራሴን
አንተን ማቀፍ ጀመርኩ _ ተውኩና ትራሴን
በሀሴት ተሞላሁ _ ተነነ ብሶቴ
አርቄም አቀድኩህ _ ለቀጣይ ሂወቴ
ያን ጊዜ ጠብቀህ _ ድንገት እንደመጣህ
እንዲህ ሆንኩኝ ሳትል _ ከሂዎቴ ወጣህ
ጥያቄ ሰተኸኝ _ ለመልስ የሚቸገር
እላዬ ላይ ጭነህ _ የትዝታ ክምር
ለብቻዬ ተውከኝ _ ሄድክ ከጓኔ ስር
ለምን እንዴት ብዬ _ ከቶ አልጠይቅህም
እድሌ ነው እኔ _ ከድሮም አሁንም
ሀዘኔ ነው እንጂ _ ሳቄ አይበረክትም
#ሼን ✍
"መስሏት ነበር እሷ"
ያኔ ጥላኝ ስትሄድ _ ከጎኔ ስትርቅ
ሁሌም የማለቅስ _ደግሜ የማልስቅ
መስሏት ነበር እሷ 😏
ያኔ ስትገፋኝ _ ቀልዳ በፍቅሬ
ወድቄ የምቀር _ እዛው አቀርቅሬ
ቆይ ምኔ ሞኝ ነው 🤔
አንድ ሴት ብትሄድ _ ሊያውም የማትወደኝ
አንገቴን ደፍቼ _ ሁሌ እንባ ሚወርደኝ
😜
ንገሯት ለዛች ሴት _ ለዛች ለማታውቀኝ
አንድ ተራ እንቅፋት
ከሂወት መንገዴ _ አይችልም ሊያግደኝ
#ሼን ✍
አንዳንድ ሴት የምታወራትን ቶሎ የማትቀበልህ በተፈጥሮዋ ተጠራጣሪ ሁና አይደለም ትናንት ያረፈበት የክህደት ብትር ዛሬም ድረስ ጠባሳው ከልቧ ላይ ስላለ ነው 🤔
አንዳንድ ሴት አብሮነትን ፡መቃረብን የምትሸሸው አንተ እንደምታስበው ጉረኛ ሁና አይደለም ተላምዶ መለያየትን አብዝታ ስለምትፈራ ነው 🤔 እሷ ያለፈችበትን ትናንትና በውል አታውቅምና በዛሬዋ ልትፈርድባት አትቸኩል ይልቅ ከቻልክ ህመሟን አብረህ አስታምና የድሮ ጠባሳዋን ፍቃ አዲስ ሴት ትሆን ዘንድ እገዛት 🙏
#እኔ_ሴቶችን_እወዳቸዋለሁ 😍
#ሼን ✍
አንዳንዴ ......
የራስህ ልታደርጋቸው በብዙው ከጣርክላቸው፣ ዕልፍ ጊዜ ከደከምክላቸው ፣ራስህን አሳልፈህ ከሰጠሀቸው አንዳንድ ሰዎች በተሻለ መልኩ ድንገት በሆነ አጋጣሚ ምንም ሳትጠብቀው ወደ ህይወትህ ብቅ የሚሉ ሰዎች የ "ሰውነትን " ትርጉም ኑረው ያሳዩሀል፣ ልባዊ መውደድንና የማይዛነፋ መልካምነትን ፣ ምላሽ ሳያሰሉ ያለወረት ማፍቀርን በውስጥህ ዘርተው ጠወለገ ያልከውን ህይወትህን ዳግም ያለመልሙልሀል 👌
#ሼን ✍
" አዎን አንቺ "
ታውቂያለሽ ..... ወደ ሂወትሽ እየገቡ የሚወጡት ሰዎች ብዙ አስተማሩሽ መሰል የሚያስታውቅ የባህሪ ለውጥ እያየሁብሽ ነው 🤔 በትንሽ ትልቁ መናደድ ትተሻል ፣ለራስሽ ጊዜ እየሰጠሽ ነው ፣ ሳቅና ደስታሽን ከሌላ መጠበቅን አቁመሻል ፣ የኔ የምትያቸውን ሰዎች ማኩረፍ አቁመሻል ፣ ነገሮችን ችላ ብሎ ማሳለፍ፣ ሰዎችን ሲሄዱ መሸኘትና ሲመጡ መቀበል ጀምረሻል ማንንም ለምን እንዴት ብለሽ መጠየቅም ትተሻል ፣ ላንቺው አንቺው መቆም እንዳለብሽ በደንብ ገብቶሻል .... ልክ ነኝ አይደል 🤔
#አንተ_በሂወት_እያለህ_አባትህ_የሚለብሰው_ቸግሮት_ሲበርደው_ብታይ_ምን_ታደርጋለህ ❓❓❓
ከጧቱ 4: 00 ሰአት አከባቢ ዝናብ እያካፋ ነው ከጓደኛዬ ጋር ከአንድ መንገድ ዳር ካለ የጀበና ቡና መሸጫ ቦታ ተቀምጠን ቡና እየጠጣን ነው ።ቦታው ላይ ሌሎች ሰዎችም እንደኛ ለቡና ተቀምጠዋል ድንገት አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ወደኛ ጠጋ ብለው እጃቸውን ለምፅዋት ዘረጉ በዛ ካፊያና ብርድ የለበሱት
ቁራጭ ልብስ እንኳን ከብርዱ ሊያድናቸው ይቅርና ሰውነታቸውን እንኳ በቅጡ አይሸፍንም 😢 ፋዘር ቡና ይጠጣሉ ብለን ጠየቅናቸው እሳቸውም መጠጣት እንደሚፈልጉ አሳውቀዉን ወንበር ስበንላቸው ጎናችን ኩርምት ብለው ተቀመጡ ...ለቡና ቀጂዋ እንድትቀዳላቸው አዘናት ወደራሳችን ጨዋታ ተመልሰናል በዚህ መሀል ነበር ታዲያ "የኔ ልጅ" የሚለው የአዛውንቱ ድምፅ በወሬያችን መሀል የገባው እኔና ጓደኛዬን ጨምሮ ከኛ ትይዩ የተቀመጠ አንድ ወጣት ልጅ እኩል ወደሰውየው ፊታችንን አዞርን ከሶስታችንም ለሰውየው ቅርብ የነበርኩት እኔ ነበርኩና እይታቸውን እኔ ላይ አድርገው "እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ" አሉኝ እኔም እሺ ፍዘር ጠይቁኝ ምንድን ነው አልኳቸው ለመስማት እየተጣደፍኩ እንደው እዚች ምድር ላይ ከሁሉ አብልጠህ የምትወደው ማንን ነው አሉኝ ?
እኔም ምድር ላይ ከሁሉ አብልጬ የምወደው ሰው አባቴ እንደሆነ መለስኩላቸው ፡ አስከትለው እንዲያ የምትወደው አባትህ አንተ በሂወት እያለህ የሚለብሰው አጥቶ ሲበርደው ብታይ ምን ታደርጋለህ አሉኝ በሰአቱ ጥያቄው አስደንግጦኝ ነበር... እኔ እርቃኔንም ቢሆን እሄዳለሁ እንጂ አባቴንማ እንደዛ ሁኖ ማየት አልፈልግም ስል መልስ ሰጠዃቸው አተኩረው እያዩኝ አየህ እኔ እንዲህ የሚለኝ ልጅ የለኝም ግን "በርዶኛል" አሉኝ 😢 ሰውነቴን ውርር ነበር ያደረገኝ አስቡት በዛ አይነት ሁኔታ እንደዛ ብትባሉ ሊሰማችሁ የሚችለውን ስሜት 🤔 በጣም ልብ ይነካል .... ወዲያው ግን ደስ የሚል አጋጣሚ ተፈጠረ እዛው ከኛ ጎን ለቡና ተቀምጦ የሰውየውን ንግግር እየሰማ የነበረ አንድ ወጣት አባቱ ካረፉ ስድስት ወራት እንዳለፋቸውና የአባቱ ብዙ አልባሳት ስላለ ለአዛውንቱ ሊሰጣቸው እንደሚችል አበሰረን በሀዘን ክስም ያለው ፊቴ በወጣቱ ልጅ ሀሳብ ፍክት አለ
ወዲያው ራይድ ጠርተን አዛውንቱን ይዘን ወደልጁ ቤት አመራን ፡ ከቆይታ በዃላ ከወጣቱ ቤት ደርሰን ካፖርትና ሱፍን ጨምሮ ሌሎች ብዙ አልባሳትን አውጥቶ ሰጣቸው
በሰአቱ አዛውንቱ ፊት ላይ ያስተዋልኩትን ፈገግታ እንዲህ ብሎ በቃላት ለማስቀመጥ ይቸግራል 👌 የምርቃት አይነት አዘነቡብን በመጨረሻም በደስታ ወሬ የታጀበ ምሳ አብረን በልተን ተለያየን ። እኔ ግን ከአዛውንቱ ጋር ከተለያየን በዃላ አንድ ንግግራቸው ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ "ፈጣሪ እናንተን ባይጥልልኝ ኖሮ የጥቅምትን ብርድ እንዴት እችለው ነበር "
የአዛውንቱ አይነት ልብስ የሚያስፈልጋቸው ስንት ችግረኞች በየቦታው ይኖሩ ይሆን ስል አሰብኩኝ በዛ ላይ በዚህ የብርድ ወቅት 🤔
በዛው ቅፅበት አንድን ሀሳብ አሰብኩኝ ሁላችንምኮ ረዝሞን ወይ አጥሮን አልያም ፋሽኑ አልፎበታል ብለን የማንለብሰው እንዲሁ የተቀመጠ አልባሳት በየቤታችን አለን ለምን እኒያን አልባሳት ሰብስበን ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች አናለብሳቸውም 🤔 ይህን ሀሳብ የዛኑ ቀን ማታ ላይ የአዛውንቱን ገጠመኝ ጠቅሼ አዲስ አበባ ላይ ይህን ስራ አብረን እንስራው ስል ቲክቶክ ላይ ቪዲዮ ሰርቼ ለቀኩኝ ። የሰራሁት ቪዲዬ ላይ ስልክ አስቀምጬ ስለነበር ብዙ ሰዎች እየደወሉ አብረውኝ ሊሰሩ ፍቃጀኛ እንደሆኑ አሳወቁኝ አንዳንዶች ደግሞ አልባሳቶችን ያለንበት ድረስ እያመጡልን በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን 🙏
ይህን ፅሁፍ ያነበባችሁ አዲስ አበባ የምትኖሩ በዚህ ስራ ላይ አብራችሁን ለመስራት ከፈለጋችሁ አልያም አልባሳትን ለመስጠት የምትፈልጉ ከስር ባለው ስልክ ቁጥር ልትደውሉልን ትችላላችሁ 🙏
📞 09 39 00 64 88
#ለእኛ_ትርፍ_የሆነው_ለሌሎች_ዋናቸው_ነው
#ያሸንፉና_ይሸለሙ 🙏
#በቻሌንጁ
አንደኛ የወጣው 3000 ብር
ሁለተኛ የወጣው 2000 ብር
ሦስተኛ የወጣው 1000 ብር ተሸላሚ ይሆናል
🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥
ቻሌንጁ ከኔ ግጥሞች ውስጥ ደስ ያላችሁን አንድ ግጥም መርጣችሁ እያነበባችሁ ቪዲዮ መስራት ሲሆን ውድድሩ የሚደረገው ደግሞ በቲክ ቶክ ነው 👌
🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥
👉 ስታነቡ ከፈለጋችሁ በቃላችሁ አልያም ወረቀት ይዛችሁ በሁለቱም ይቻላል
👉 ግጥሙን በቪዲዮ ስትሰሩ ሌላ የሚረብሽ ድምፅ ባይገባና ጥራት ያለው ቢሆን ይመረጣል
👉 ማጀቢያ ሙዚቃ( ክላሲካል) መጠቀምም አለመጠቀምም ትችላላችሁ
👉 የምትመርጡት ግጥም አጪር ቢሆን የተሻለ ነው
🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥🎥
በዚህ ቻሌንጅ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከአሁን ሰአት ጀምሮ #በቴሌግራም አካውንቴ ላይ ልታሳውቁኝ ትችላላችሁ የቴሌግራም አድራሻ ከስር link አስቀምጫለሁ
👉 @gitmsetim
👉 @gitmsetim
👉 @gitmsetim
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#ለአዲስ_አመት_ለወዳጃችሁ_ስጦታ_ከፈለጋችሁ 👌👌👌
✅ለእናት
✅ ለአባት
✅ ለወንድም
✅ ለእህት
✅ ለአያት
✅ ለባል /ለሚስት
✅ ለጓደኛ
✅ ለፍቅረኛ
ስሜትዎን የሚገልፅ የግጥም ስጦታ ማበርከት ከፈለጉ ባሻዎት ቀንና ሰአት እንዲደርስ ተደርጎ በተመጣጣኝ ዋጋ ይፃፍልዎታል 🌹🌹🌹🌹
በ 👉 0939006488 ቴሌግራም ላይ ያናግሩኝ 🙏
✝ 🙏☪🇪🇹
በምነቴ ሙስሊም ነኝ_ በማንነቴ ሰው
ኦርቶዶክስ ወንድሜን
ሲከፍው የማልወድ _ ሆዴን የሚብሰው
" አዎ ሰው ነኝ እኔ "
ግፍን ለመቃወም _ በደልን ለማውገዝ
በኔ ካልደረሰ _ ብዬ ዘር የማልመዝ
ያንተ ቤት ሲንኳኳ _ ይሰማል እኔም ቤት
ነው እና ከድሮም _ ያገሬ ሰው ተረት
ዛሬ የኦርቶዶክስ _ ቤተ እመነት ሲታመስ
ዝም ብዬ ባልፍ _ ደርሶ በማድበስበስ
ነገ ይቀጥላል _ የኔ _መስጊድ ድረስ
እናም እጮሀለሁ ...
ስቃይ እንግልቱን _ ግፉን ተቃውሜ
ኦርቶዶክስ ወገኔን _ አግዛለሁ ባቅሜ
ቤተ እምነት መተንኮስ _ ነውና አገር ማፍረስ
እባካችሁ ተው _ ብዙ ደም እንዳይፈስ
#ሼን ✍
አንዳንዶች ከመሄዳቸው በላይ የሄዱበት ምክኒያት ነው እጅጉን የሚያመው ......
ሁሉ ነገርሽን ሳትሰስች ሰጥተሻቸው እነሱ ህመም ብቻ አስረክበውሽ ይሄዳሉ ፣ለሳቃቸው ደፋ ቀና እያልሽ እየደከምሽ እነሱ በምላሹ የምታለቅሽበት ምክኒያት አስረክበውሽ ይሄዳሉ ፣አንቺ ለነሱ ብለሽ ሁሉን ነገር ትተሽላቸው እነሱ ለአንድ ተራ ነገር ሲሉ ጥለውሽ ይሄዳሉ ፣ በቃ አንዳንዶች እንዲህ ናቸው እየኖርሽላቸው ከእድሜሽ ላይ ቀን ሰርቀው ይሄዳሉ .......🤔
😉
ልቡ እንደሚወዳት _ እያወቀች በደንብ
ልብሱ ስላደፈ _ ስለሌለው ገንዘብ
ብ...ር ብላ ሄዳ _ ከሱ ተለይታ
የማይወዳትን ሰው _ ለንብረቱ አግብታ
ፍቅርን ተርባ _ ጮማ የጠገበች
አንዳንድ እንከፍ አለች 😏
#መኪናው_የኔ_አይደለም 🤷♂
#ሼን ✍
አንዳንድ ሰው ደህና ነኝ የሚለው የእውነት ደህና ስለሆነ ሳይሆን አሞኛል ቢልም ህመሙን የሚረዳለት ሰው ስለሌለው ነው ..... 🤔አንዳንድ ሰው ዝም የሚለው የሚያወራው ስለሌለው ሳይሆን የሚያወራለት ሰው ስላጣ ነው .....🤔 አንዳንድ ሰው ብቸኝነትን የሚመርጠው ሰው ጠፍቶ ሳይሆን ለእርሱ ልክ የሚሆን እርሱን በእርሱነቱ የሚቀበለውና የሚረዳው ሰው ስላጣ ነው ......
Читать полностью…" በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ሁሌም ጥፋተኛዋ አንቺ ነሽ " 🙃
ጥፋታቸውንና በደላቸውን ሆነ ብለሽ አውቀሽ እንዳላወቀ ስታልፊ ሞኝ አድርገው ያስቡሻል ፣ መሳሳታቸውን ስትነግሪያቸው ደግሞ ተጨቃጫቂ ያደርጉሻል ፣ አብረሻቸው መሆንን በፈለግሽበት ሰአት ቢዚ እንደሆኑ ነግረውሽ ለራስሽ ጊዜ መስጠት ስትጀምሪ ተለውጠሻል ምን አግኝተሽ ነው ይሉሻል፣ አንሱው እንድትርቂ ምክኒያት ሁነው ከአይናቸው ዘወር ስትይ ተውሽን ብለው ሊወቅሱሽ ይዳዳሉ 🤔 በቃ ምንም አይጨበጡም እነሱው አስለቅሰውሽ እነሱው ካላባበልንሽ ይላሉ 🤷♂ እነሱው ሳቅሽን ሰርቀው እነሱው አኩራፊ ይሉሻል ፣ እነሱ ያሻቸውን ተናግረውሽ ቆየት ብለው አፌ ነው እንጂ ሆዴኮ ባዶ ነው ብለው ይሸነግሉሻል አንቺ ተስቶሽ የተናገርሻትን አንድ ቃል ግን ሁሌ እያነሱ ሊያሸማቅቁሽ ይሞክራሉ ..... በቃ በአንዳንዶች ዘንድ አንቺ መቸም ልክ አትሆኚም
#ሼን ✍
"የዝምታ_ህመም"
ምንም እንዳልሆኑ _ ደህና እየመሰሉ
ውጋትን ደብቀው _ እንዲህ ነኝ ሳይሉ
ዝም ፀጥ ብሎ _ ሁሌ መሰቃዬት
ቀን የይምሰል ስቆ _ ማንባት ጠብቆ ሌት
ከባድ ነው ህመሙ _ ያቅታል ለማንም
ትንሽ ሰው ብቻ ነው _ ለዚህ ያለው አቅም
#ሼን ✍
....... የኛ ነገር .......
ተዋወቅን _ ተሳሳቅን
ተጣበቅን _ ተላቀቅን
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ደግሞ _ ደግሞ
ከርሞ _ ከርሞ
ተኳረፍን _ ተታረቅን
ዃላ ዃላ _ ተናናቅን
መጨረሻ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
ተ
ራ
ራ
ቅ
ን
😏
#ሼን ✍
ፈርቻለሁ ......✍️
ልቤ ውስጥ ለአንተ ያለኝ እምነት ብዙ ተሸረሸረ መሰል በወሬህ ውስጥ እውነት አልታይሽ ብሎኛል ፣ መለማመጥ ውስጤን አደከመኝ መሰል እንደበፊቱ አሁን ስታኮርፈኝ ብዙ እየጨነቀኝ አይደለም ፣ ነገሮችን ካንተ መጠበቅ ታከተኝ መሰል ኦላይን ገብተሀ እያየሁህ እንኳ ቴክስት ትልክልኛለህ ብዬ እንደ ሌላው ጊዜ አልጓጓም ፣ ደወልክም አልደወልክም ግድ እየሰጠኝ አይደለም 🤷♂እንጃ ተስፋ እየቆረጥኩብህ ነው መሰል ፈርቻለሁ 😏
" ለምን ይመስልሀል "
ችላ እንዳልካት በድርጊቶችህ ደጋግመህ እያሳየሀት ፣ አብዝተህ ስሜቷን እየጎዳኸዉ እንደሆነ ልቦናዋ እያወቀ እንኳ ዛሬም ጎንህ ያለችው ፣ ያንተን ነገር ከውስጧ ለማጥፍት አቅም ያጣችው ፣ አንተን ከመርሳት ይልቅ ማስታወሱ የሚቀላት ፣ አንተን እርግፍ አድርጋ ትታ ከሌላ ሰው ጋር ሂዎትን ማሰብ ገደል መስሎ የሚታያት ፣ያን ሁሉ ነገር እያደረካት እንኳ ስምህን በክፉ ለማንሳት የማትደፍረው አንተ ማንም ስለሆንክ አልያም ከሌላው ወንድ የተለየ ነገር ኖሮህ አይደለም 🤷♂እውነታው እሷ የምር ከልቧ አፍቃሪ ሴት ስለሆነች ነው ።
አየህ የዚች አይነት አፍቃሪ ሴት ስትወድ በሙሉ ልቧ ስለሆነ ዛሬን ብቻ ሳይሆን እሩቅ ነው ህልሟ፣ ግዙፍ ነው ምኞቷ በዛም ምክኒያት ሁሉነገሯን ለአብሮነቱ ሳትሰስት ስለምትሰጥ አየተበደለችም ፍቅሯን በቀላሉ ከደሟ ውስጥ ቶሎ ማውጣቱ አይቻላትም ...የኖረችው ትዝታም እንዲህ በቀላሉ በአእምሮዋ መመላለሱን አያቆምም አየህ በቃ ለዛ ነው ከድግምግም ጥፋትህ ይልቅ ትንሽየዋ መልካም ነገርህ ለአይኗ የሚጎላው 🤷♂ በተሳሳተ ሚዛን እራስህን እየመዘንክ አጉል አትቆለል 😏 ያቺ ሴት እንዲህ የመሆኗ ሚስጥር አንተ ትክክለኛ ሰው ሁነህ ሳይሆን እሷ ወረትን የማታውቅ ትክክለኛና ልባም አፍቃሪ ሴት ስለሆነች ብቻና ብቻ ነው
" ይልቅ ሳይረፍድ አትነቃም ወይ" 🤔
#ሼን ✍
" ዋጋህን እወቅ "
የቱንም ያክል ከነሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስታ ቢሰጥህም እነሱ ካንሀ ጋር መሆኑ ምቾት የሚነሳቸው ከሆነ አታግኛቸው 🤷♂
የቱንም ያክል ድምፃቸውን መስማት ቢያጓጓህም እነሱ ሊያወሩህ ካልፈለጉ አትደውልላቸው 🤷♂
የቱንም ያክል ብትወዳቸውም በነሱ ያለመፈለግ ስሜት ከተሰማህ ግን ተዋቸው 🤷♂
የቱንም ያክል ለነሱ የገዘፈ ቦታ ቢኖርህም የማያከብሩህ ከሆነ ፣ለስሜትህ የማይጨነቁ ከሆነ የሚንቁህ ከሆነ ተዋቸው 👌
አየሽ አይደል እኔ
ትናንት
መለየትን ማሰብ _ መሮሽ ሁኖ እንዳሞት
ያለነሱ መኖር _ ሁኖብሽ የቁም ሞት
ከጎንሽ ከሌሉ _ ቀኑ የሚጨልም
እቅድና ተስፋሽ _ የሚተን እንደጉም
በሂወት መቆምሽ _ የሚያጣብሽ ትርጉም
የመሰለሽ ትናንት_ ሳለሽ ባብሮነቱ
ይሄውና አሁን _ ሌላ ነው እውነቱ
እነሱ ባይኖሩም _ ቢሄዱም እርቀው
እንባ ቢያስነቡሽም _ ያን ሳቅሽን ሰርቀው
ሁለተኛ አልቆምም _ አልሺርም እስክትይ
ብዙ ብትደሚም _ ብትገፊም ስቃይ
ቀን በቀን ሲተካ _ ወቅት ነግቶ ሲመሽ
ቀስ ቀስ እያለ _ ያንቺም ህመም ሲሸሽ
ከመቆየት ብዛት _ ቁስልም ተወግዶ
ሰነባብቶ ከርሞ _ ጎንሽም ሰው ለምዶ
ዛሬ እየኖርሽ ነው _ አለሽ ያው እንደቆምሽ
በተሻለ ተስፋ _ ነገሽን እያለምሽ
ለካ .....
ሰው ተለየኝ ብሎ _ ከመኖር መቆሙ
ሞኝነት ብቻ ነው _ ሲፈታ ትርጉሙ
#ሼን ✍
"አሁን ደህና ናት"
ከግንኙነቱ መፍረስ በላይ አብሮነቱ ይሆናል ብላ በማሰብ ያባከነቺው እድሜዋ ትንሽ ትንሽ ቢያማትም አሁን ደህና ናት .... ስለተዋሸችና ስለተከዳች ድጋሚ ሰው መቅረብና ማመንን ልቧ እየፈራ ብቸኝነትን መርጣለች እንጂ አሁን ደህና ናት ...... ለብቻ ሁኖ ቁስል ማስታመሙ ያለ አይዞሽ ባይ መጥፎ ቀናት ጋር መታገሉ ትንሽ ቢያደክማትም አሁን ደህና ናት.... አልፎ አልፎ ለሰው ስትል ያጣቻት የድሮዋ ሳቂታዋ እሷ ትናፍቃታለች እንጂ አዎን አሁን ደህና ናት .......
#ሼን ✍
👆👆👆👆👆
አዲስ አበባ ያላችሁ ይህን ቪዲዮ ትሰሙት ዘንድ በፈጣሪ ስም አጥብቄ እጠይቃችዃለሁ 🙏 ከሰማችሁት በዃላ በዚህ ስራ አብራችሁ መስራት የምትፈልጉ 0939006488 ላይ ደውላችሁ አሳውቁኝ 🙏
"ታሳዝነኛለች"
ለሷ እንደማይሆናት _ውስጧ ይነግራታል
ወስና እንዳትሄድ_ ፍቅሯ ይይዛታል
ደግሞ ባንድ በኩል _እድሜዋን ስታስብ
በቁጭት በንዴት _ ትላለች እንግብግብ
ልቧ እየዋለለ _ በመሄድ በመቅረት
ትርጉሙ ጠፍቶባት_ የመንጋት የመምሸት
ከደስታ ተኳርፋ _ ሂዎት ትገፋለች
ይቺ አይነት አፍቃሪ _ ታሳዝነኛለች 😢
#ሼን ✍