shelela | Unsorted

Telegram-канал shelela - 🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

367

🙏ሺሊላ ያአብሬትዬ 👳werabe yehadra jema 🙏ሺሊላ ያአልከስዬ 👏Ysolewat wedeta 🙏ሺሊላ ያሳዳትዬ 👳Ymwelid fekr 🙏ሺሊላ ያቃጥባርዬ 👏Nurachinen yabran 🙏ሺሊላ ያአንዬ 👳Ahlel betoch nen 🙏ሺሊላ ያዳንዬ የዉሀቢይ👺 ደርስ ወይም ሊንክ መልቀቅ አይቻልም

Subscribe to a channel

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የቄሱ_ልጅና_ቶፊቅ
              ክፍል ሁለት

✍️አብዱ ኤምሬ

       
               ስሜ ቶፊቅ ኑረዲን ይበላል፤ ኑሮዬ ድንቅ ምድር ከሆነችው ፍቅረ ሰላም ከተማ ሲሆን፤ ለአባቴ ባላምባራስ ኑረዲን እና ለእናቴ እመት ኑሪያ ስድስተኛ ልጅ ነኝ.. በአጠቃላይ ሶስት ወንድምና ሁለት እህቶች አሉኝ። ቤተሰባችን አባቴ የከተማዋ አስተዳዳሪ ስለሆነ በተሟላ ሁኔታ ውስጥ ነው ያደግነው ይህ ማለት ግን ከሌሎች ልጆች እንድንርቅ አላደረገንም.. ቤታችን ለከተማዋ ህዝብ ሁሉ ክፍት ነው.. እከሌ ብሎ አይመረጥም የራበው በልቷ፣ ችግር ያጋጠመው ተፈቷለት የመጣ ሁሉ በመጣበት አኳኋን ተስተናግዶ የሚወጣበት ቤት ነው። ከተማዋን የማስተዳደር ሀላፊነት ከአያቶቼ ሲዋረስ አባቴ ላይ ደርሷል አባቴም ልክ እንደቀድሞዎቹ ከተማዋ እንድታድግ ብዙ ሰርቷል እየሰራም ይገኛል። በተለይም "እድገት የሚመጣው የሰውን ማህበራዊ ትስስር በማጠናከር ነው፤ ብሎ ስለሚያምን ህብረተሰቡን አንድ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ ይሰራል።" በጣም ከሚያስገርሙኝ ነገራቶች መሀከል የሃይማኖት በአላትን እንኳን ሙስሊም ክርስትያን ሳይባል በአንድ ላይ ማክበር መቻሉ ነው፤ እናም በጥምቀት ሰሞን የከተራ ቀን ታቦት ከየቤ/ክኑ እየወጣ በአንድ ማደሪያ ከተራ ሜዳ የሚባል ቦታ ይሰበሰቡና በማግስቱ ባሉት ቀናት ወደ ቤተ-ክርስቲያናቱ ይመለሳሉ።

እኛ ሰፈር የሚገኘውም የመድኃኒአለም ታቦት መግባቱን እትዬ ጥሩ ስትከንፍ መጥታ ለእናቴ ትነግራለች፤ ይህን ስትሰማ እናቴ ላይ የነበረው ደስታ በቃላት የሚገለፅ አልነበረም "አልሀምዱሊላህ ታቦታችን ገባ..!" ስትል ተነፈሰች ነገሩ ትንሽ ግራ ስላጋባኝ እትዬ ጥሩ ከቤት ከወጡ ቡሀላ "እናቴ ሙስሊም ሆነን ሳለ ለምን አልሀምዱሊላህ ትያለሽ እኛ የእነሱ ሀይማኖት አይመለከትንም" አልኩ የምትለኝን ለመስማት እየተጣደፍኩ እናቴ ሳቅ እያለች "አንተ ልጅ ሞኝ ነህ መሰለኝ የእኛ አንድ ክፋይ ናቸው.. እነሱ ሰላም ካልሆኑ እኛ ሰላም የምንሆን ይመስልሀል.. የእኛ ሰላም ለእነሱ የእነሱ ሰላም ለእኛም ጭምር ነው።" ከዚህ ቀን ቡሀላ ነው የዚህ ፍቅር ምክንያት የገባኝ..  እድሜዬ ስድስት አመት ከደረሰ ቡሀላ አባቴ ወደ ቄስ በላይነህ ጋር ለት/ት ላከኝ.. የከተማዋን ልጆች ሁሉ ቋንቋና ፅህፈት የሚያስተምሩ እሳቸው ናቸው። መማሪያ ክፍሎ በቅጡ ሙሉ እቃ የተሞላላት አይደለችም፤ ሁሉም ልጆች ቀስ በቀስ ወደ ክፍሉ ከገቡ ወዲያ በመጨረሻ አባባ በላይነህ ጭራቸውን እያወዘወዙ ወደ ክፍሎ ብቅ አሉ..

         ሲገቡ ብቻቸውን አልነበሩም አብራቸው አንዲት በእኔ እድሜ የምትገኝ ልጅ ነበረች፤ መምህር ሲገቡ ተማሪዎቹ በሙሉ ከመቀመጫቸው ተነሱ ሁሉም መቀመጫ በተማሪ መሞላቱን ሲያስተውሉ እኔ ጋር ባለው ወንበር እንድትቀመጥ አመላከቷትና አብራኝ ቆመች .. "እንደምን አደራችሁ ልጆች..?" አሉ ተማሪዎቹን አትኩረው እየተመለከቱ "ፈጣሪ ይመስገን መምህር፣ በአንድ ድምፅ መለስን። "ጎሽ ቁጭ በሉ ልጆቼ.." እያሉ ፈገግ አሉ ሁሉም ተማሪ ከመቀመጫው ላይ ተቀመጠ፤ ዛሬ አዲስ ልጆች መጥተዋል የእኔ ልጅ ማክዳ እንዲሁም ከአጠገቧ የሚገኘው የውዱ መሪያችን ልጅ ቶፊቅ ተቀላቅሎዋችሆል እዚህ የቆያችሁ ልጆች የሚቸግራቸውን ነገር ሁሉ በተቻለችሁ መጠን ንገሮቸው። "እሺ መምህር." ሲሉ በአንድነት አስተጋቡ "አው አሁን ወደ ትምህርት እንገባለን የምነግራችሁን ነገሮች በአግባቡ መስማት አለባችሁ በት/ት ሰአት ረብሻ በፍፁም አልፈልግም" ብለው ካስጠነቀቁ ቡሀላ ትምህርታቸው ጀመሩ..

      ትምህርት ከጀመርን ቀናት አልፈዋል አሁን ላይ በጣም ደስተኛ ሆኜለሁ የዚህ ሁሉ መንስኤ ሌላ ሳይሆን ማክዳ ነች፤ መጀመሪያ ላይ ለመተዋወቅ ትንሽ ፍርሀት ብጤ አድሮብን የነበረ ቢሆንም..
ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የቄሱ_ልጅና_ቶፊቅ
           ክፍል አንድ

✍️አብዱ ኤምሬ


         "ሀገር ማለት አፈርና ውሃ ብቻ... አይደለም ይላሉ ታላላቆቹ፤ ሀገር የሚያሰኘው ህዝቡ ነው፤ ለዚህም ነው ሀገሩን የሚወድ ሰው ህዝቡን የሚወደው፤ ሰውን ጠልቷ ሀገር መውደድ ታስቦም ታልሞም የማያውቅ የአላዋቂዎች ብሂል ነው። ከዚህም በላይ ደግሞ አንዱ የአንደኛውን አስተሳሰብና አመለካከት ሳይገፋ በፀጋ እየተቀበለ ሲኖር እድገት ይመጣል፤ ሁሉ ጠግቦ ያድራል።..." እያሉ ያማረ ለዛ ባለው ድምጣቸው ቄስ በላይነህ ከአባቴ ባላምባራስ ኑረዲን ጋር ይመክራሉ፤ ጓዳ ላይ የመድረሳ ትምህርቴን እያጠናሁ ቢሆንም መሳጭ የሆነውን ውይይታቸውን ጆሮዬን ቀስሬ አንድ በአንድ እሰማለሁ፤ አባቴ ከቄስ በላይነህ ጋር መማከርና አብሮ መሆን በጣም ያስደስተዋል። ለሌላ ለማንም ቤታችን ውስጥ የማይፈቀደውን ጠጅ እንኳን ለእሳቸው ከሆነ ያለምንም ቅሬታ ነው የሚቀርብላቸው። በወሪያቸው የተነሳ የማጠናውን ዘንግቼ ትኩረቴን እነሱ ላይ ማድረጌን በበሩ በኩል የተመለከቱት ቄስ በላይነህ "ልጄ ለወሬ የለውም ፍሬ.. ጥናቱ ነው የሚበጅህ.." አሉ ውብ ፈገግታቸዉን እያሳዩ....

          ውልደቴ የአብሮነትና የፍቅር እሴት ከሆነችው "ፍቅረ ሰላም" ከተማ ነው፤ የዚህችን ከተማ ስም ያወጡት ቅድመ አያቴ ራስ ዑስማን ነች.. ከተማውም አሁን ላለችበት እንድትበቃና እንድትቆረቆር ያደረጉት እርሳቸው ናቸው። ከምንም በላይ ደግሞ ጎልቶ የሚነሳው ታሪካቸው በጦርነት ላይ ያላቸው ጀግንነት ነው፤ ከአንድም ሶስት ከተማዋ ከተቃጡባት ወረራዎች በአሸናፊነት ጠብቀዋል.. ይህንም ወረራ ለመከላከል በማሰብ በከተማዋ ዙሪያ ያሰሩት ትልቅ እርዝመት ያለው የድንጋይ አጥር ተጠቃሽ ነው። ከአባቴ እንደሰማሁት ይሄ አጥር ሲገነባ የከተማዋ ነዋሪ ከትንሽ እስከ ትልቁ ያልተሳተፈበት አንድም ሰው እንደሌለ ነው፤ የግንቡ ስም ከከተማዋ ስም የመጣ ሲሆን ይህም "የሰላም ግንብ.." ይባላል። ያኔ ከጠላት እራስን ለመጠበቅ  ታስቦ የተሰራው አጥር ዛሬ ላይ የአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሮ ከሩቅ ሀገር ሰዎች ለመጎብኘት የሚመጡበት ስፍራ ሆኖል...

          ከተማዋ በተለያዩ የተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለች ናት፤ ከምንም በላይ የግብርና ምርቶቾ ውጤታማ ናቸው... መሬቱ ተዘርቷ የማያበቅለው ምንም የለም። ለዚህም ነው ከተማዋ ከራሷ አልፋ ሌሎችንም ለመመገብ የደረሰችው፤ ከተማዋ የበለፀገች መሆኖ ታላላቅ ነጋዴዎች እንዲፈሩባት አድርጓል፤ ለምሳሌ: ሀጂ ሙሳ፤ ጋሽ መኮንን.. ብዙዎችን መጥቀስ ይቻላል፤ ንግዳቸው ከከተማዋ ባለፈ በሌሎች ግዛቶችም የሚገኝ ነው። ከነጋዴዎቿ የሚያስደንቀው ነገር በእስልምና እምነት የሚታዘዘውን ዘካ (ሀብታሞች ከሀብታቸው ለደሆች የሚያካፍሉበት ስርአት) ክርስትያኖቹም በአመት ዘካ ማውጣታቸው ነው። ይህን በመመልከት ብቻ በህዝቡ ዘንድ ያለውን ጥልቅ ትስስር መገንዘብ ይቻላል። በሃይማኖት ደረጃ ሁለት እምነት ብቻ ነው የምናገኘው፤ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው ማለትም (60%) የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ሲሆን ቀሪው ደግሞ የክርስትና የተዋህዶ ሃይማኖትን የሚከተል ነው።

           ከተማችን ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ የሃይማኖት ስፍራዎች ሲገኙ ዋናዋናዎቹን ለመጥቀስ፦ ኑር መስጂድ፣ መድኃኒአለም ቤ/ን.. ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህም በላይ ደግሞ አብዛኛው ቤ/ንና መስጂድ የሚገኙበት ቦታ ተቀራራቢ ከመሆኑም ባሻገር፤ ሩፋኤልና ቢላል መስጂድ አጥር ነው የሚለያቸው...

                 ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ኢንቲሳር ሱልጣን

ከአሸዋ ሜዳ ገብሬል  አከባቢ   ትላንት ሰኞ ጥቅምት 4 /2017 እንደወጣች አልተመለሰችም

ለአላህ ብላቹ ፍንጭ ይሆናቸዋል ምትሉን ነገር ካለ በነዚህ አድራሻዎች አሳውቁን 👉
0922 15 16 25
0910928364

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

https://app.binance.com/my/wallet/account/payment/binancepay/sharecryptoboxes?&ref=LIMIT_CB25SB3R&registerchannel=321801148650905600&_dp=L3dlYnZpZXcvd2Vidmlldz90eXBlPWRlZmF1bHQmbmVlZExvZ2luPWZhbHNlJnVybD1hSFIwY0hNNkx5OTNkM2N1WW1sdVlXNWpaUzVqYjIwdmJYa3ZkMkZzYkdWMEwyRmpZMjkxYm5RdmNHRjViV1Z1ZEM5aWFXNWhibU5sY0dGNUwzTm9ZWEpsWTNKNWNIUnZZbTk0WlhNX0puSmxaajFNU1UxSlZGOURRakkxVTBJelVpWnlaV2RwYzNSbGNtTm9ZVzV1Wld3OU16SXhPREF4TVRRNE5qVXdPVEExTmpBdw==

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

በዒራቋ ከተማ በስራ ዉስጥ የሆነ ታሪክ ነው አሉ፡፡ ሰዎች ለአንድ ከገጠር ለመጣ እና ስለ ዲኑ ብዙም የማያውቅን ሰው “ጀነት እገባለሁ ብለህ ዉስጥህ ያስባልን?” አሉት፡፡ “በአላህ እምላለሁ! በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ታክል ተጠራጥሬ አላውቅም፤ አዳራሿ ላይ ስቦርቅ፣ ከሐውዷ ስጠጣ፣ በጥላዋ ሥር አረፍ ስል፣ ከፍራፍሬዋ ስቀጥፍ ስበላ፣ በቪላዋና ፎቋ ዉስጥ ሰንፈላሰስ ይታየኛል፡፡” አላቸው፡፡

“አለኝ ብለህ በምታስበው በጎ ሥራ ነው ጀነትን የምታስበው?” አሉት፡፡

“እንዴ! በአላህ ከማመን እና ከአላህ ዉጭ የሆነዉንና በሐሠት የሚመለከዉን ነገር ሁሉ ከመካድ በላይ ምን መልካም ሥራ ይኖራል?፡፡” አላቸው፡፡

“ወንጀልህን አትፈራም ወይ?” አሉት፡፡

“አላህ ለወንጀል ምህረትን አኖረ፤ ለስህተት እዝነትን መደበ፣ ለጥፋት ደግሞ ይቅርታን አስቀመጠ፡፡ እሱ የሚወዱትን ከጀሀነም እሣት በመጠበቅ ረገድ ቸርነቱ ከፍ ያለ ጌታ ነው፡፡” አላቸው፡፡

በበስራ መስጂድ ዉስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው በርግጥም በአምላኩ ላይ ያለው ጥርጣሬ ምንኛ መልካምና ከፍ ያለ ነው!!፡፡” አሉና ተደመሙ፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ አንስተዉም ብዙ አወሩ፡፡ ወዲያዉኑ ከአላህ እዝነት ተስፋ የመቁረጥ ዳመና ከላያቸው ላይ እየተገፈፈ ሲሄድ ተሰማቸው፡፡ በእጅጉ ተረጋጉ፤ እዝነቱን አብዝቶ የመከጀል ድባብ ሸፈናቸው፡፡

“ፈማ ዘኑኩም ቢረቢል ዓለሚን …” ስለዓለማቱ ጌታ ምን ትጠረጥራላችሁ! ምንስ ታስባላችሁ!!!

ከሰባሐል ኸይር መጽሐፍ የተወሰደ
@heppymuslim29

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

Coding ለመማር የሚጠቅሙ የmobile መተግበሪያዎች

#Mimo ጀማሪ ከሆናችሁ እና እንደ JavaScript, typescript, python ያሉ courses የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። በተጨማሪም puzzle በመስራት practice ማድረግ ትችላላችሁ።

#Enki የበርካታ programming language concept የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። የተለያዩ ከጀማሪ እስከ Advanced የcoding challenges puzzle ጨምሮ አሉት።

#Codecademy go Python, HTML/CSS, JavaScript, SQL እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ መማር ትችላላችሁ። እንዲሁም በርካታ videos እና articles ተካተውበታል።

#encode web development እዛው እየሰራችሁ የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። encode ጥራት ባላቸው content ይታወቃል።

#Programming Hub የCoddingን ትንሽ concept ከተረዳችሁ ቡኋላ እዚህ ላይ ራሳችሁን challeng ማድረግ ትችላላችሁ። በተጨማሪም አንዳንድ የcoding courses አሉት።

/channel/W3SSU
/channel/W3SSU

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

Yekelakelut aref jemea new

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ታሪኳን ስትነግረን እንዲህ ትላለች:-✈️
ኡስታዛችን ነበርና ወደ ስምንት ጁዝዕ እሱ ዘንድ ካስደመጥን በሇላ በድንገት ሙሉ በሙሉ ሴቶችን ማሳፈዝ እንዳቆመ የመድረሳው ሀላፊዎች ያሳውቁናል።
በዚህን ጊዜ እኔ እና ጓደኞቼን ሴት ኡስታዛ ጋር ያዘዋውሩናል። እሷም የቀደመው ኡስታዛችን እናቱ ናት!!

ሁላችንም ጭራሽ እስከምንረሳው ድረስም የኡስታዛችን ዜና ይቋረጣል ። ከአስር ወራት በሇላም እኔ እና ጓደኞቼ ቁርዓን ሙሉ በሙሉ ሀፍዘን ድል ያለ የሂፍዝ ምርቃት ድግስ ተደረገልን። በድግሱም ዕለት ኡስታዛዬ ከጓደኞቼ አርቃ ይዛ ወሰደችን እና «አንቺን ከቤተሰቦችሽ ሊያጭሽ የሚፈልግ ወጣት አለ» አለቸኝ ስለ ወጣቱ አንዳንድ ነገር ነገረችኝ እና ከሱ ጋር ይወያዩበት ዘንድ የአባቴን ስልክ ቁጥር ሰጠዋቸው እንደተባለውም አወሩ እና ከሁለት ቀን በሇላ ቤታችን መጡ

ከዛማ የመጡት ...ሴቷ ኡስታዛዬ ባለቤቷ እና ልጃቸው [ከአስር ወራት በፊት የነበረው ኡስታዛችን!!! ] ሆኑ እላቹሃለው

🟤ድንጋጤዬማ ዛሬ ድረስ ትዝ ይለኛል...

.....ብቻ ቤታችን መቶ ኒቃቢስትም ስለሆንኩ ሸሪዓዊ እይታ ከተያየን በሇላ እንዲህ አለኝ «ባንቺ እንደተፈተንኩ ባወቅኩ ግዜ ከሸይጣን በሮች መካከል አንዱ ሊከፈት እንደሆነ ተሰማኝ ...
እናማ በአሏህ እርዳታ ሴቶችን ማሳፈዝ ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ..... ይህም ሸይጣን አነስተኛ መንገድም ቢሆን ወደኔ እንዳያገኝ ነበር.... በዚህን ግዜ አንቺን ኒካህ ለማሰር ዝግጁ እንዳልሆንኩም ስለማውቅ ከአንቺ ጋር ሊያገናኘኝ የሚችልን መንገድ በሙሉ ገታው...ልቤንም ዲኔንም አንቺንም ጭምር እንዳላበላሽ ስል...ነገር ግን በተውኩሽ ግዜ በምድር ላይ እጅግ ከማምናት ፍጡር ....እናቴ ጋር ነበር የተውኩሽ
ጎበዝ ተማሪ ናት ወደ ፊት ላይም ታታሪ የዲን አስተማሪ መሆን ትፈልጋለች ብዬ አደራ አልኳት...» አሏህም የመልካም ሰሪዎችን ስራ ከንቱ የሚያደርግ አልነበረም።
ራሳቸውን አስጠበቁ ጥብቆችም ገጠማቸው ..."መልካሞችስ ለመልካሞቹ የተገቡ አይደል"

@heppymuslim29

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ከእለታት አንድ ቀን ሁለት ሰሀቦች ወደ ረሱል ﷺ ተወዳጅ ሚስት አኢሻ ጋር መጡና ጥያቄ ጠየቁ አኢሻ ሆይ! እስኪ ረሱል ﷺ ላይ ያየሽውንና በጣም ያስገረመሽን ነገር ንገሪን አሏት አኢሻ እንባዋ ቀደማት አለቀሰች ከዛም እንዲህ አለች አንድ ቀን ማታ ረሱል ﷺ ከኔ ጋር ነበሩ አኢሻ ሆይ! ይችን ለሊት ፍቀጂልኝ ከጌታዬ ጋር ላሳልፈው አሉኝ" እርስዎን የሚያስደስቶት ነገር ከሆነ እኔም ደስተኛ ነኝ ስላቸው ተነሱና ተጣጥበው መስገድ ጀመሩ ከዛም ጉንጫቸው እስኪርስ ድረስ አለቀሱ አሁንም ጉልበታቸው እና መሬቱ በእንባቸው እስኪታጠብ ድረስ ማልቀሳቸውን ቀጠሉ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቢላል ለሰላት ሊጠራቸው መጣ እያለቀሱም አገኛቸው ከዛም እንዲህ አለ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ያለፈውንም የሚመጣውን ወንጀል ተምሮሎት እንዲህ ይሆናሉ? ታዲያ አመስጋኝ ባሪያ መሆን የለብኝም እንዴ የሳቸው መልስ ነበር:: ከዛም የሚከተለውን ንግግር ተናገሩ:-…
ዛሬ ለሊት የተወሰኑ አንቀጾች ወርደውብኛል እነሱን አንብቦ ያላስተነተነ ሰው ወየውለት አሉና"
ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺧَﻠْﻖِ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺍﺧْﺘِﻠَﺎﻑِ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﻭَﺍﻟْﻔُﻠْﻚِ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﺗَﺠْﺮِﻱ ﻓِﻲﺍﻟْﺒَﺤْﺮِ ﺑِﻤَﺎ ﻳَﻨﻔَﻊُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱَ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧﺰَﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻣِﻦ ﻣَّﺎﺀٍ ﻓَﺄَﺣْﻴَﺎ ﺑِﻪِ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﺑَﻌْﺪَ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ ﻭَﺑَﺚَّ ﻓِﻴﻬَﺎ ﻣِﻦ ﻛُﻞِّ ﺩَﺍﺑَّﺔٍ ﻭَﺗَﺼْﺮِﻳﻒِ ﺍﻟﺮِّﻳَﺎﺡِ ﻭَﺍﻟﺴَّﺤَﺎﺏِ ﺍﻟْﻤُﺴَﺨَّﺮِ ﺑَﻴْﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻟَﺂﻳَﺎﺕٍ ﻟِّﻘَﻮْﻡٍ ﻳَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ
ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትንና ቀንንም በማተካካት፣ በዚያቸም ሰዎችን በሚጠቅም ነገር (ተጭና) በባህር ላይ በምትንሻለለው ታንኳ፣ አላህም ከሰማይ ባወረደው ውሃና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ በርሷም ውስጥ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በመበተኑ፣ ነፋሶችንም (በየአግጣጫው)በማገለባበጥ፣ በሰማይና በምድር መካከል በሚነዳውም ደመና ለሚያውቁ ሕዝቦች እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡
«ሱረቱል አል-በቀራህ 164» አነበቡ።

@heppymuslim29

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ይሄ ወርቃማ እድል እንዳያመልጣቹ!!😳
ግሩፕ መግዛት ጀምረናል💵💵
●2019 500 ብር💸
●2020 450 ብር💸
●2021 400 ብር💸
●2022 300 ብር💸
●2023 100 ብር💸
◇ፍጠኑ ይህ እድል የሚቆየው ለትንሽ ግዜ ብቻ ነዉ።
የክፍያ አማራጮች👇
□CBE
□TELE BIRR


@Teenage_hab
@Teenage_hab

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

طفلة من غزة إنا لله وإنا إليه راجعون
ከጋዛ ህፃናት ውስጥ አንዷ

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

"ረቢዓል አወል"ምርጥ መንዙማ
ግጥምና ዜማ ማዲህ ሙሐመድ አብዱሏህ"የዓለሙ ዘውዱ እሰይ ተወለዱ👏👏👏👏👏👏👏
መውሊዱ ደረሰልን🙏ሸቀዋን ሊጨርስልን👏ባዓንቱ ፍቅር በረካ ስንቶች ተማረኩልን👏 መውሊዳችንን ያማረ አሏህ ያድርግልን ውዶችዬ❤️አሚሚንን መውውሊሊድድ👇👇👇👇👇👇👇👇/channel/muneshidmuhammed
/channel/muneshidmuhammed

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የችሎት_ንግስት
              ክፍል አስራ ሁለት

✍️አብዱ ኤምሬ

 
          ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላት ላይ ስቆም የነበረኝን የደስታ አለም ለመግለፅ ይከብዳል፤ ሱጁድ ላይ ለአመታት ከደጁ እርቄ ሳምፀውና፤ ያልተገባ ነገር ሁሉ ሳደርግ እሱ ለሰከንድ ሳይርቀኝ ዛሬ ደግሞ ይሄን የመሰለ ክብር እንደለገሰኝ ሳስብ የደስታ እንባዬ ይወርድ ጀመር፤ እስከዛሬ ስፈልገው የነበረውን ደስታ በሰአታት ውስጥ አገኘሁት፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ በዚህ አለም የኖሩ እንዴት አይነት እድለኞች ናቸው።  እስከ ምሽት ድረስ መስጂድ ውስጥ ነበር ያሳለፍኩት፤ የተለያዩ ትምህርቶችንና ቁርዐን ሲነበብ እየሰማሁ መንፈሴን አድሰው ጀመርኩ፤ ልብን ሰርስሮ የመግባት ሀይል ያለው እንደ ቅዱስ ቁርዐን አልሰማሁም። ከምንም በላይ ግን መጀመሪያ ላይ መስጂድ ስገባ ላየው የፈለኩት.. በአባቶች ሲነገር የሰማሁትን ሙስሊሞች ከሚሰግዱበት ፊት በጣውላ የተሰራና የተሸፈነ ነገር መኖሩን ነበር፤ ወደ መስጂድ ስገባ ቀጥታ አይኖቼ ያንን ለመመልከት ቋምጠው ነበር፤ ምንም ያህል ብዞዞር አንድም ነገር አላየሁም..

            ቡሀላ ላይ ለጎደኛዬ ሀናን ስለሚባለው ነገር ጠየቅኳት? በሳቅ ነበር የፈረሰችው.. ሳቋ በኔም ተጋባና አብረን መሳቅ ጀመርን ሳቋን እንደምንም እየገታች "አረ እዚህ በፍፁም ምንም አይነት ነገር የለም እንደምታይው ባዶ ነው.. የምታይው ሲሰግድና ሲፀልይ ልቡን ወደ ፈጣሪ አድርጎ ብቻ ነው፤ ይሄ ሁሉ ህዝብ ሞኝ ይመስልሻል እንዴ ለጣኦት የሚሰግድ..?" በነገሩ ትንሽ ፍርሀት ተሰምቶኝ ስለነበር ንግግሯ ሙሉ ለሙሉ የነበረኝን ፍርሀት አጠፋልኝ፤ ቀናት አለፈው በወራት ተተክቷል ከሀናን በስተቀር ማንም ሙስሊም ስለመሆኔ የሚያውቅ ሰው አልነበረም፤ ይሄም እንዳይታወቅብኝ ስል አለባበሴ ከወትሮ የተለየ አልነበረም መስጂድ ስሄድ ብቻ እነ ሀናን ቤት ልብሴን ቀይሬ እወጣለሁ.. በወራት ውስጥ ስለ እስልምና ማውቅ ያለብኝን መሰረታዊ እውቀቶችን ቀስሜለሁ፤ የነበሩብኝን ጉድለቶች ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከሞላ ጎደል በተቻለኝ አቅም ለመቅረፍና ለማስተካከል ጥረት አድርጌለሁ። ብቻ ከዚህ በፊት ከሳለፍኩት ሁሉ ይበልጥ  አስደሳች ጊዜያትና ህይወት እያሳለፍኩ እገኛለሁ..

            ሙስሊም ከሆንኩ ቡሀላ መጀመሪያ ያቆምኩት ነገር ቢኖር ሱሶቼን ነው፤ ቃላት ከሚገልፀው በላይ ከባድና አስከፊ ነው.. ያም ሆኖ አልሀምዱሊላህ ተሳክቶልኛል፤ ብቸኝነትን ማብዛቴ፣ ቤት መዋሌ፣ ሱሱንም እርግፍ አድርጌ በመተዌ ሰዎችን በጣም አስገርሞቸው ነበር፤ እናቴም ለማመን አልፈለገችም ሌላ ቦታ እየሄድኩ የማደርግ እስኪመስላት፤ የፀባዬ መለወጥ ማለትም በጥሩ ባህሪ ላይ መገኘቴ እናቴን በጣም አስደስቷታል... የታላቁ ረመዳን ወር ሊገባ ከወር ያነሱ ቀናት ቀርተውታል.. ስለረመዳን ትሩፋቶች ብዙ ሰምቼለሁ እናም ይሄ ወር በዋዛ እንዲያመልጠኝ አልሻም፤ አሁን ሁሉም ሰው ሙስሊም መሆኔን ማወቅ የሚገባው ሰአት ነው ብዬ ወሰንኩ፤ በንጋታው ጠዋት እናቴ አባያ ለብሼና ሂጃብ አድርጌ ስታይ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች.. ከደቂቃዎች ቡሀላ "ይሄ ምንድነው?" እየተንተባተበች፤ <ይህውልሽ እናቴ ከእንግዲህ ማወቅ ይገባሻል፤ ሙስሊም ሆኜለሁ..> "ሙስሊም.." <አዎ..> ብዬ መለስኩ ያለ ምንም ፍርሀት "አንቺ ዲቃላ ከቤት ውጭልኝ፣ ወራዳ.." እያለቀሰች መሳደቡን ተያያዘችው ላረጋጋት ብሞክርም ፍቃደኛ አልሆነችልኝም ጥያት ከቤት ወጣሁ..

         ከቤት ስወጣ ሰፈር ላይ የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ አይናቸው ሊበላኝ ደረሰ፤ አስተያየታቸው በጣም ያስፈራ ነበር። ሀናን ጋር ሄጄ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት.. እሷም "ታድያ ሰብሪና (ትግስተኛ) የተባልሽው እኳ ዝም ብሎ አይደለም መታገስ ይኖርብሻል.." ሀናን ቤት ለአስራ አምስት ቀናት አሳለፍኩ በመሀል ረመዳን ገብቶ ሁለት ቀን ፆሜለሁ፤ የሀናን አባት እናቴን ከስንት ልመና ቡሀላ ወደ ቤት እንድገባ አደረጉ፤ እናቴ እንደበፊት ባትሆንም አፍጥር ምታዘጋጅልኝ እሷ ነበረች፤ ከሱስ መራቄ ይመስለኛል ከሀሳቧ መለስ እንድትል ያደረጋት፤ የሰውን ወሬ ግን እንዲህ ማለት አይቻልም  አንዱ ይመጣና "ለወንድ ብለሽ ነው.. ሌላው ገንዘብ ተሰጥቷሽ ነው።" ሁሉም በማያውቀው ነገር የእራሱን ሀሳብ ይደመድማል፤ ከቤት መውጣትና የሰዎችን ፊት ማየት እስኪያስጠላኝ ደረጃ፤ የሆነው ሆነና አሁን ሙስሊም ሆኜ ዳግም ከተወለድኩ አራት አመታት ተቆጥረዋል.. ከመጥፎ ወደ ጥሩ፤ ከመውደቅ ወደ መነሳት ከክፋት ወደ በጎነት ለመራኝ ሀያሉ አላህ ተቆጥሮ የማያልቅ ምስጋና ይድረሰው፤ አልሀምዱሊላህ!
 
*ይሄን ታሪክ ላጋራችሁ ያሰብኩት፤ የትኛውንም ለማሳነስ ሳይሆን ከኔ ትንሽም ብትማሩ ከሚል ቅንንነት መሆኑን ትረዱልኝ ዘንድ አደራ እላለሁ!!

                 *ተፈፀመ*

*ታሪኩን ላጋራችን እህት🙏 በተለየ ታሪክ እስከምንገናኝ መልካም ጊዜ! ታሪክ ልታጋሩን ካሻችሁ 👉@ABDU_EMRE

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የችሎት_ንግስት
             ክፍል አስር

✍️አብዱ ኤምሬ


      የሰው ልጅ የማመርና እራሱን የመለወጥ ሃሳብ ካለው፤ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከትልም ይማራል። በህይወቴ በጣም ደስ ከሚሉኝና ነገን ተስፋ ከሚሰጡኝ ስብዕናዎች ቅዱስ ያሬድ ትልቁን ደረጃ ይይዛል። ለሀገሩና ለሀይማኖቱ ተቆጥሮ የማይዘለቅ አያሌ ስራዎችን አበርክቷል፤ አሁን ላይ ለሚገኘው የተዋህዶ የማድመቅና የውብ መዝሙሮቿ መነሻና መስራች የሆነ ሰው ነው። ይሄ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን ደካማና ምንም ማሳካት የማይችል ተራ ሰው ነበር፤ እንኳን ለቤተሰቡ ለራሱም የማይጠቅም ልጅ ነበር። የሰው ልጅ እራሱን ከሌሎች ደረጃ ጋር የሚለካ ከሆነ ሊያድግ አይችልም፤ ምክንያቱም ማንም እከሌን መሆን አይችልምና እራስህን ብቻ ነው መስለህ መገኘት፤ እንደሚችልና አቅም እንዳለው የሚያስብ ሰው ግን በብዙ ልፋትና መከራዎች ውስጥ ቢያልፍም ነገሮችን ማሳካት የማይችልበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ አንተ ማድረግ የማትችለው ነገር የለም.. ብቻ "አትችልም.. ከባድ ነው.." የሚል የሰዎችን ዘፈን ማዳመጥ የለብህም።
   
             ለሀይማኖቶች ሁሉ ክብር አለኝ፤ ምክንያቱም ሰው ያድነኛል፣ ይጠቅመኛል፣ እውነት ነው ብሎ እስካመነባቸው ድረስ ሊከበርለት ይገባል፤ ሌሎች ያንተን አመለካከትና አስተሳሰብ ሲያንቆሽሹ እንደማትወደው። በዚህ ምድር ላይ ሀቅ የሆነ ነገር ቢኖር ለዚህች አለምና በውስጧ ላሉ ሁሉ መገኘት ባለቤትና ፈጣሪ አለ፤ ምንም ነገር የፈጠረው አካል እስከሌለ ድረስ በራሱ ምንም መሆን አይችልም፤ ግን ዋናው ጥያቄ የዚህ ሁሉ መገኘት ትክክለኛው ባለቤት ማነው? የሚለው ነው። ሁሉም በእራሱ አመለካከት የተለያየ መልስ ይሰጣል፤ ግን ትክክለኛውን መፈለግ የእራሱ ግዴታ ነው.. አባት እናት የሰጡኝን አስቀጥዬ.. ተቀብዬ እኖራለሁ አይሆንም፤ አእምሮ እስከተሰጠህ የትኛው እውነት ነው ብለህ እያመዛዘንክ ሁሉንም መቃኘት ይገባል። ለዚህም ነው በተቻለኝ አቅም ሁሉ ሚዛናዊ የሆነውን እምነት ለመምረጥ የምሞክረው፤ በእምነታቸው ጠንካራ ከሆኑ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ጓደኞቼ ጋር ሰፊ ውይይቶችን ማድረግ ያስደስተኛል..

                 ከዮናስ ጋር ያለን ግንኙነት ከቀን ወደ ቀን እየሻከረ ከመጣ ሰንብቷል፤ ለአይን እንኳን እስከሚያስጠላኝ ድረስ.. ለእርሱ ያለኝ ስሜት የፍቅር መስሎኝ እንደሆነ ነበር የማስበው፤ ነገር  ግን ከክብር የመጣ ብቻ እንደሆነ አሁን ነው የገባኝ። አጥብቄ እንዲይዘኝ ከምፈልጋቸው ስሜቶች አንዱ ፍቅር ነው፤ መቼስ ተፈልጎ አይገኝም፤ ፈልጎም ያገኘው የለምና። እስካሁን ድረስ ዝር ብሎብኝ አያውቅም። ከበፊትም ጀምሮ ጎደኞቼ እከሌን ወድጄ አፍቅሬ ሲሉ ምንም ማይገባኝ ነገር ነበር.. ልክ አሁን እኔ ሱሰኛው ስለ ሱስ ሳወራ  እንደማይገባችሁ ሁሉ። በየቀኑ በቴክስትና በአካል ወደድኩሽ.. አበድኩልሽ እንዳለኝ፤ ሁልጊዜም ሰዎች እንደዚህ ሲሉኝ ወደ ጥላቻ ይቀየርብኛል። ኩሩና ደፋር ይመስለኝ የነበረው ሰው አሁን ሲያለቃቅስ ሳየው ለራሴ እንኳን ግርም ይለኛል፤ በአንድ በኩል ግን የፍቅር ጉልበት ይገርማል ጀግና ነው? ስልጣን አለው? ሀብታም ነው? ለምን? እንዴት? ሳትል ነው የሚጥልህ፤ በፍቅር ውስጥ የተሸነፉ እንጂ ያሸነፈ አልታየም..

           አሁን ላይ ምክንያታዊ ከምላቸው የሀይማኖት መምህሮች ውስጥ ዶ/ር ዛኪር በጣም ልዩ ነው። ጎደኛዬ ሀናን ቤት በሄድኩበት አጋጣሚ ነበር በሲዲ ተከፍቷ ያየሁት፤ ለሚሰጣቸው እያንዳንዱ መልሶች ያለው በክብር የተሞላ ንግግር ያስደስታል፤ ከዛን ቀን ወዲህ የሱን ጥያቄና መልሶች ማየት ልምድ አደረጉት...
                    *ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የችሎት_ንግስት
               ክፍል ዘጠኝ

✍️አብዱ ኤምሬ


         "ህመምን ማውጋት ከታመመው ጋር ነው፤ ላልታመመው መንገር ትርፉ ለድካም ነው።" ሰዎች ሁለወ ጊዜም የራሳቸውን እይታ ሊያንፀባርቁበህ ይፈልጋሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ጫና ለመራቅ ስትል ያልሆንከውን ልትሆን ትችላለህ። በምድር ላይ ስትኖር ማወቅ የሚገባህ ሁልጊዜም የራስህን ስሜት ማዳመጥና ማስቀደም አለብህ፤ ይሄ ማለት በተሳሳተ አመለካከት ላይ ከተገኘህ የሌሎችን አዎንታዊ ምክር አትስማ ማለት አይደለም፤ የሚጠቅምህን ይዘህ የማይጠቅምህን ታፈሰዋለህ፤ ሌላው ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር የምትፈልገውን ሁሉ አታገኝም፤ ነገር ግን የምትፈልገውን ለማግኘት ጥረት ማድረግ አለብህ። ጊዜያት ካለፉ ቡሀላ ሞክረህ አለማግኘትህ አሉታዊ ነገር ውስጥ አይከትህም፤ ምንም ሳትሞክር ግን ብታጣ ቁጭት ታተርፋለህ። ባለፈ ነገር የሚቆጭ ሰው ደግሞ ልቡ በጭንቀትና በመረበሽ ይሞላል.. ወደፊትም እንደማይሳካለት ስለሚፈራ ነገሮችን አይደፍርም በአጭሩ ደስታን ማግኘት አይችልም..

         ቢቆይ እንጂ ከሰዎች የሚደበቅ ነገር የለምና ሱሰኛነቴ ገሀድ ሲወጣ ከባድ ጫና ውስጥ ነበር የከተተኝ፤ አያቶቼ ጋር ለመሄድ እስከማፍር ደረጃ ደረስኩ፤ የሚመጣውን ለመቀበል እንደምንም እሁድ ቀን አያቴ ጋር ሄድኩኝ ሀገር አማን ብዬ ነበር የገባሁት የሁሉም ፊት ተቀያይሯል አባቴም ነበረ.. ሰላምታ ሳቀርብ ማንም የመለሰልኝ አልነበረም፤ ምንም ነገር ሳልናገር ቀጥታ ወደ ሶፋው ሄጄ ተቀመጥኩ.. አፉ ታስሮ የነበረው አባቴ ገና ከመቀመጤ ማውራት ጀመረ "ደግሞ ምን ልሁን ብለሽ ነው የመጣሽው፤ የሰፈር ሰው ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ያደረግሽን ሳይበቃ ንቀት መሆኑ ነው.." የማሽሞጠጥ ሳቁን ለቀቀው ውስጤ ምንም የህል ቢቃጠልና መልስ መስጠት ብፈልግ እንደምንም ዝምታን መረጥኩ፤ በዚህ አላበቃም አያቴም ቀጠለች "ድሮስ የባለጌ ልጅ ጨዋ ይሆናል እንዴ?. አንተም ከእርሷ የባስክ አለነበረክ እንዴ? መጀመሪያ ነው እንጂ መጥኖ መደቋስ፤ ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥሎ ማልቀስ። አለ የሀገሬ ሰው.. አትመለከትም ድፍረቷን ምንም ሳታፍር ሰተት ብላ መጣች እንደው አፈር ሆና በቀረች ነበር.."

           በእውነት መፈጠሬን ጠላሁት ምነው አርፌ ቤቴ ቁጭ ብልስ የዚህ ሁሉ ጥፋት መንስኤ የኔ ብቻ ይመስል አሉኝ የምላቸው ሰዎች ሁሉ ከኔ ራቁ ፤ ሁሉም እራሱን ፃድቅ አድርጎ ይቋጥራል። ይሄ ሁላችንም ቤት ያለ ነገር ነው፤ ለልጅ መበላሸት ዋናው ተጠያቂ ወላጅ ነው.. አባትና እናት ለልጃቸው ያላሳዩትንና ያላስተማሩትን ነገር ሲያድግ ይጠብቃሉ፤ ይሄ ሊሆን የማይችል ህልም ነው፤ "ትልቅ በሚሆንበት ጊዜ ጥሩና መልካም ልጅ እንዲሆን ከፈለክ፤ ልጅነቱ ላይ መልፋት አለብህ.." በስርአት ያልተከሉት ዛፍ ተጣሞ ቢያድግ ተካዩ እንጂ ዛፉ አይጠየቅም፤ በበጎ አይታ ያዩኝ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስሜታቸው ወደ ጥላቻ ተቀየረ.. ብሶት ደግሞ ወደ መጠጥ ይመራሀል.. በሀይለኛው መጠጣት ጀመርኩ በየቀኑ በሰዎች እየተደገፍኩ ነበር ወደ ቤት እገባ ምገባው፤ ውሎዬ ሁሉ ከቤታችን አጠገብ የነበረው መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነ። የኛ ሰው ምግብ ልጋብዝህ አይልም መጠጥ አልያም ጫት ልጋብዝህ ነው የሚለው፤ ለምግብ የሚጠፋው ብር ለሱስ ሲሆን ከየት እንደሚመጣ ለራሴ ይገርመኛል..
  
               ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ የንፅፅር መፀሀፎችን ከማንበብ ሰንፌ አላውቅም፤ እራሴን ከዚህ ቅጡን ካጣ አለም ለማውጣት የተቻለኝን ሁሉ እየደረግኩ ነው፤ ቢያንስ ለመኖር በህይወት ለመቆየት ምክንያት የሚሆን ነገር ካገኘሁ በሚል፤ አሁን አሁን እየተገነዘበኩት የመጣሁት ነገር ቢኖር..
               ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

"እንደ ሃይማኖት ያለንበት ደረጃ የማንም አይሁድ መጫወቻ የውርጋጥ አፍ መክፈቻ ሁነናል፤ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ የመን፣ ፍልስጤም.. ወዘተ እየሆነ ያለው ይሄው ነው። በቁጥር አንሰን አይደለም ግን ታላቁ ነብይ ሰዐወ እንዳሉት "የባህር ላይ አረፋ ሆነናል.."። መስጂድ ገብቼ ኢማኔን ላድስ ስትል የእገሌ ግሩፕ እያሉ ግራ ያጋቡሀል፤ ኹሩጅ ስትል የእነንትና ጀመዓ እያሉ ይወሰውሱሀል። ሌላው እንደ ሀገር ያለንበት አዘቅት እጅግ የከፋ ነው፤ ነገ የአላህ ነው እንጂ ነገን የሚያጨልም በሚመሰል መልኩ ነው እየተሰራ ያለው። ከዚህ ሁሉ መውጣት የሚቻለው እራስህን በመገንባትና ለቁርዐን፣ ለአዝካር ጊዜ መስጠት ይገባል.. የሆኖ ሆኖ ብሩህ የሆነውን ቀን አላህ ያሳየን።"
አላሁመ ሷሊ አላ ሀቢቢከል ሙስጠፋ!

@abduftsemier
@abduftsemier

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

🍀ቅምሻ🍀

🌿....ኹሩጅ ፊሰቢሊላህ🤍

አላህ ኹሩጅ ፊሰቢሊላህ(በሱ መንገድ መውጣትን) ያደለው ምንኛ እድለኛ ነው። ነፍሱን፣ጊዜውንና ገንዘቡን መስዋዕት አድርጎ ይንቀሳቀሳል። ራሱን ለማስተካከል፣ የአላህንﷻ ትዕዛዝ ለመፈፀም፣ የነቢንﷺ ሱናህን ለመፈፀም እና ራሱም ተጠቅሞ ሌላውን ለመፈየድ። ፈጅሩን ሰግዶ በቁድረቱሏህ በያን ቀኑን ይጀምረዋል፣በተዕሊሙ ቀልቡ ኑር በኑር ይሆናል።  ጀውላ ወጥቶ ሰዎችን ከአላህና ከመስጂድ ያስታርቃል፤ ጭንቀቱ ከዱንያ ወደ አኺራህ፣ ከፍጡር ወደ ፈጣሪ ይቀየራል።የነቢﷺ ውዴታና ሱናህ አጣምሮ ይፈፅማል፦አዳበ ጠዐም(የአመጋገብ ሥነ ስርዓት) አዳበ ነውም(የመኝታ ሥነ ስርዓት) ሌሎችም ሱናዎችን ተግባራዊ ያደርጋል።ሶላቱን ለማስተካከል ይለፋል፤ ነገራቶችን በሶላቱ አማካይነት ለማምጣት ጥረት ያደርጋል።በቁርአንና በዚክር ቀልቡን ያረጥባል፤ ለሁሉም አዛኝ ይሆናል ከኔ ወንድሜ ብሎ ያስቀድማል ሙሐባ ይመጣለታል። ማንንም አይነካም ፤ ሙገሳውም ትችቱም ለሱ አንድ ነው። ሰዎችንም ተሽኪል ያደርጋል ልክ እንደሱ እንዲወጡ። በኺድማና ከመተኛቱም በፊት ሓያቱ ሶሓባ በማድመጥ የተኮፈሰችው ነብስያውን ዝቅ ያደርጋታል። በጊዜ ተኝቶም ሌሊት ተነስቶ ያ አላህ! ዑመት እያለ ያነባል። ኧረ ስንቱን! የፊሰቢሊላህ ሐያት በዚህች በዱንያ ላይ ውድ የሆነ ሓያት ነው!

ያ ረቢ ወፍቀን
ከغፍላህ አላቀን

                   💚💚💚

/channel/kOTEBARAHM

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

☘️ቅምሻ☘️


ሴትን በሴት ይቀጣል አሉ።

...ብትርህን  ቀጥል አላለችም😄

አንድ ሰው በመንገድ ላይ እየተጓዘ ሳለ የሆነ ሰው ሚስቱን ሲደበድብ ያየዋል

يا هذا الضرب للحيوانات
أما النساء فتضرب من بالنساء
🍀ሰውየውም
አንተ ሰው ዱላ ለእንስሳቶች ነው
ሴቶችን በሴቶች ነው የሚቀጡት ይለዋል።

🍀 فقال الرجل:
لم أفهم ما قلته
🍀ሰውየው
የተናገርከው አልገባኝም አለው

ሴቷም ፈጣን ነች እና ገብቷት እደዚ አለችው

🍀 فقالت زوجته:
أكمل الضرب،يا هذا
اترك هذا الأحمق

🍀ይህን ሞኝ ተወውና ብትርህን ቀጥል 😁😁


ሴቶች ሁለተኛ  ባሎቻችሁ ሲያገቡ ለምን አትወዱም አሳውቁኝ አስኪ በinbox  እውቀት ልውሰድ😉



                     💚መልካም ምሽት💚


👇👇👇join👇👇👇
/channel/kOTEBARAHM

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#ሀበሻ ኢጅቲማዕ
ትኬቶች በመሸጥ ላይ ይገኛሉ!
ትኬቶችን ለማግኘት👇👇👇
#0994455832
#0920375467

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

http://T.me/pdf_manzuma

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

➤AI በመጠቀም ኦንላይን ላይ ገንዘብ ልታገኙበት የምትችሉበት አንድ መንገድ ልጠቁማችሁ።

https://www.videotoblog.ai/
ይህንን AI Tool በመጠቀም ማንኛውንም የYouTube Video ዝርዝር ወደሆነ ፅሁፍ ወይም blog ይቀይርላችኋል።

ለምሳሌ ከታች ያለው YouTube video iphone 16 pro Max እና Samsung Galaxy S24 Ultra የሚያነፃፅር video ነው።
https://www.youtube.com/watch?v=muIrYd4csAM

የቪዲዮውን ሊንክ AI ዌብሳይቱ ላይ በማስገባት የቪዲዮውን ፍሬ ሃሳብ generate ያደርግላችኋል።

ይህንን ፅሁፍ ቀላል ድረገጽ በመስራትና ወደ Blog በመቀየር በGoogle AdSense ገንዘብ መስራት ትችላላችሁ።

ለምሳሌ ከላይ ያስቀመጥሁላችሁ video ወደ blog ሲቀየር ይህን ይመስላል።
https://www.videotoblog.ai/blog/xWcjmXcm5IvHfyNe6iNX

የተለያዩ ቴክኖሎጂ፣ የሳይንስ፣ የታሪክ የመሳሰሉ የYouTube ቪዲዮዎችን ወደ blog ቀይራችሁ መስራት ትችላላችሁ።

/channel/W3SSU
/channel/W3SSU
/channel/W3SSU

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

https://youtu.be/RUZjk2aGULQ?si=8Evd4pOK70UVmIxu

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

t.me/catsgang_bot/join?startapp=9K_0ny6MPI_CqznP6u08O
Meow, lets see who is OG 😼

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ቻናላችንን ተቀላቀሉ Yaltekorart Ena Fetan Merja Tageghalachu.👍 Link t.me/selke5

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ተለቀቀ 💥ተለቀቀ 💥ተለቀቀ
👇👇👇👇👇
መሀመድ አብደላ አልበም መንዙማ
አጂብ የሆነ ማሻ አላህ

https://youtu.be/JRWqZMVqYoI?si=KGI0Hyp2uV3a0w7l

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ዛሬ የወርሀ ረቢዐል አወል ሌሊት አሀዱ ብሏል።  ለሰው ልጆች እንደ አዲስ ውልደት ሊቆጠር የሚችል ሁለንተናዊ ለውጥ ያመጡት ታላቁ ሰው (ሶ ዐ ወ) ወደዚህች ዓለም የዘለቁበት ወር። መሻኢኾቹ የህልውናቸው ሶስተኛ እርከን የተጀመረበት ክስተት አድርገው ይቆጥሩታል። እኛ ሀበሾች በአሳዳጊያቸው በኡሙ አይመን ተወክለን ያን  ታላቅ ሁነት የታደምን ከመሆኑ አኳያ ልዩ ትርጉም ይሰጠናል። የረህመት ንፋስ የጀመረበት ወር። የማዲሆች አውራ እንዳሉት፦

ዙሪያውን ነፋፈሰ፣
በምርቱ እየታፈሰ፣
በጁዱ ተነፈሰ፣
የኻሊቃችን ቁድራ፤

መልካም ወርሀ  ረቢዕ!!!

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

አንድ ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ ቤት ይሄዳል። እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል።

ጸጉር አስተካካይ፦ ታውቃለህ አላህ የለም

ተስተካካይ፦ በመገረም እንዴት?

አስተካካይ፦ አይታይህም?

ተስተካካይ፦ ምኑ?

አስተካካይ፦ እንዴ አላህ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ ጦርነት ፣ረሀብ፣ ችግር፣ ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ
ፈጣሪ አንዴ ፈጥሮን ትቶን ሄዷል ወይ ሞቷል።

ተስተካካይ፦ ታውቃለህ ጸጉር አስተካካይም የሚባል የለም እኮ።

አስተካካይ፦ ግራ በመጋባት እንዲህም በመገርም እንዴት?

ተስተካካይ፦ ጸጉር አስተካካይ ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ሰው አይኖርም ነበር።

አስተካካይ፦ እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ጸጉር አስተካካይ አለመምጣታቸው ነው እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ
የተንጨባረረ ጸጉር አታይም ነበር።

ተስተካካይ፦ትክክል ብለሃል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው ነው ሰው ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ አላህ ስለሌለ አይደለም።''

@heppymuslim29

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የችሎት_ንግስት
               ክፍል አስራ አንድ

✍️አብዱ ኤምሬ


           በህይወት ውስጥ ደስታን ማግኘት ትልቁና ቅድሚያ የሚሰጠው ግብ ነው ብዬ አምናለሁ። ስኬታማነት የሚገለፀው በደስታ ውስጥ ነው፤ የህሊናና የልብ ደስታ የሌለው ሰው ስኬታማ ሊባል አይችልም። ደስታ ምንድ ነው? ከተባለ፤ ደስታ ብሎ ማለት እስልምና ነው፤ ከኢስላም ውጭ ደስታ የለም ምክንያቱም ይሄ ደስታ ሀዘን አይሽረው መከፋት አይበግረው ዘላለማዊ ነውና። እያንዳንዷ ደቂቃ ዋጋ አላት፤ ባሪያው ቅርብ ወደሆነው ፈጣሪ ለመቃረብ በየቀኑ አምስት ጊዜ መስጂድ ይመላለሳል። ከምንም በላይ አምሰት ጊዜያት ንፅህናውን ይጠብቃል፤ በእጥበት የውጭ፤ በስግደቱ የውስጥ አካሉን ንፁህ ያደርጋል፤ ይሄን ሙስሊም የሆነ ሰው ላይ ብቻ የምትመለከተው ድንቅ ፀጋ ነው።  በእስልምና እንድትማረክ የሚያደርጉ አያሌ ተግባራቶች ይገኛሉ፤ አሁንም ለሰከንድ ከልቤ ጠፋቷ የማያውቀው የታላቁ መልዕክተኛ ንግግር አለ "ለራሰህ/ሽ የምትወደን/ጂውን ለወንድም(አህት) እስካልወደድክ/ሽ አላመንክም/ሽም... "

          በታላቁ ቁርዐን ላይ መጀመሪያ የወረደው አንቀፅ "አንብብ.." የሚለው ነው። በአጠቃላይ እስልምና ለእውቀትና ለምርምር የሚሰጠው ቦታ ከሌሎች ሃይማኖቶች ሁሉ የላቀ ነው። እንዴት ወደ እስልምና ገባሁ? ይሄ የማይጠየቅ ነው ብዬ አምናለሁ.. ምክንያቱም እስልምና ምንድነው? ብሎ መዛግብትን የተመለከተ ሰው ድርቅና ካላጋጠመው በቀር ሙስሊም የማይሆንበት ምክንያት ይኖራል ብዬ አላምንም። ይሄ ሃይማኖት እንዲህ ነው፤ ክፍተቱ ብዙ ነው ትንሽ ነው.. ብሎ ማነፃፀር የእስልምናን ትልቅነት ማሳነስ ስለሚሆንብኝ እተወዋለሁ፤ ምክንያቱም የእውነትና የውሸት ልዩነት ይሄ ነው አይባል፤ ገሀድ የወጣ ሁሉም የሚያውቀው ሚስጥር ስለሆነ። በዚህ ዙሪያ ቅዱስ ቁርዐን የእስልምናን የበላይነትና የሌሎች ሃይማኖትን ጉዳይ በማያሻማ መልኩ በብዙ ቦታዎች ላይ ገልፆታል፤ እውነትን ለሚፈልግ ሰው ሁሉ ይህንን መመልከት በአጭሩ ለመመራት ቀላል ይሆናል።

                  የመጀመሪያ ወደ እስልምና የገባሁበት ምስካሬን የሰጠሁበት ቅፅበት አሁንም ድረስ ለኔ የተለየ ነበር፤ በዛች ሰአት የተሰማኝን ስሜት ከአሁን ቡሀላ ዳግመኛ የማገኘው አይመስለኝም፤ ስለ እስልምና ያለኝን ሀሳብና መስለም እንደምፈለግ ለጎደኛዬ ሀናን ስነግራት ቀጥታ ስድስት ኪሎ ከሚገኘው አቅሷ መስጂድ ወሰደችኝ ሁኔታውን ሁሉ እዛ ለሚገኙ ሴት መምህር ከነገረች ቡሀላ መምህሯ የምትለውን እየደገምኩ ወደ እስልምና ሲገባ የሚሠጠውን ምስካሬነት ሰጠሁ፤ ከዚህ ቡሀላ አዲስ ስም እፈልግ እንደሆነ ስትጠይቀኝ ደስ እንደሚለኝ ነገርኳት ትንሽ ካሰበች ቡሀላ "ሰብሪና.." አለችኝ ትርጉሙን ስሰማ ደግሞ ስሙን ይበልጥ ወድጄ ተቀበልኩት፤ እዛው መስጂድ ውስጥ አንዳንድ መሰረታዊ የእስልምና ት/ት አስተማረችኝ፤ ብዙ የሃይማኖቱን መፀሀፍቶች ስላነበብኩ የምትለኝን ነገሮች በሙሉ ቶሎ ለመረዳት ጊዜ አልፈጀብኝም፤ እንደ አዲስ ገቢ ብዙ ግር አላለኝም... ከሰአታት ቡሀላ የአዛን የሰላት ጥሪ ተሰማ..

               ወደ መስጂድ ስመጣ የሀናን ልብስ ይዤ መጥቼ ስለነበር፤ እዛው ሻውር ከወሰድኩ ቡሀላ ያመጣሁትን ልብስ ለብሼ ለሰላት የሚደረገውን እጥበት (ዑዱእ) አሞልቼ፤ ነበር የአስር ሰላት ጥሪ የተሰማው ሰዎች ቀስ በቀስ ለስግደት ወደ መስጂድ መግባት ጀመሩ..
                 ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

ታላቁ ሌባ በሚል ስያሜው ድፍን ሃገር የሚያውቀው አንድ ሌባ ነበር። ታዲያ ታላቁ ሌባ የሌብነት ተግባሩን ሊፈፅም አንድ ቤት በር ላይ ደርሷል፣ አዩኝ አላዩኝ በሚል ዙሪያ ገባውን አማተረና ማንም እንዳላየው ሲያረጋግጥ ወደ ዛ ቤት ዝው ብሎ ገባ። ዳሩ ቤቱ ኦና ነው። ሚዘረፍ አንጡር ሃብት ይቅርና ሚላስ ሚቀመስ ያለበት እንኳን አይመስልም።
«ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል » እንዲሉ ሌባው ላመል ልሸው የምወጣው ባገኝ ብሎ ቤቱን ሲመነቃቅር የቤቱ ማዕዘን አቅራቢያ ሆነው ሲሰግዱ የነበሩት የቤቱ ባለቤት ሶላታቸውን ሲጨርሱ ሌባው የሚሰረቅ አንዳች ነገር አጥቶ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲሰናዳ ያዩታል። በእድሉ ያዘነው ሌባ ለመውጣት ወደ በሩ ሲያመራ። «ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ አንዴ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርድና አስር ሀሰናት (ምንዳ)ይዘህ ውጣ»የሚልን ድምፅ ሰማ። ሌባው ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ ሲዞር አንድ ግርማ ሞገስ የተላበሱ ሰው ያያል። የቤቱ ጌታ ናቸው። ይህ ክስተት ለታላቁ ሌባ ፍፁም እንግዳ ነው። ሊሰርቅ የመጣንና እጅ ከፍንጅ የተያዘን ሌባ ጠፍረው ወደ ህግ በሚገትሩበት አሊያም እዛው ቀጥቅጠው አፈር ድሜ በሚያስግጡበት ሀገር። ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ እንዲህ ያለ መልካም ስራ ስራና ሰዋብ(ምንዳ) ይዘህ ሂድ» የሚልን ሰው ማግኘት የሰራቂውን ልብ ሰረቀው። በንግግራቸው የተማረከው ሌባም በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ ካጠገባቸው ተቀመጠ። የቤቱ ባለቤት ታላቁ ታቢኢን ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረዲየሏሁዓንሁ ናቸው።

እንደሚታወቀው « ማሊክ ኢብኑ ዲናር» ደግሞ የሀገሩ ታላቅ አሊም ናቸው። ከዚያም ሌባው ኢማም ሆይ! ምከሩኝ? አላቸው። እሳቸውም በዛች ንግግር አንዴ ልቡን ሰርቀውታልና ምርኮኛቸውን ይመክሩት ያዙ።
በዚህ መካከል የሶላት ወቅት ደረሰና ኢማሙ ሌባው ጋር ሆነው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የቤቱን በር ሲከፍቱ ኢማሙን አጅበው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የተዘጋጁት ጎረቤቶቻቸው ነበርና አይናቸው ጉድን አስተዋለ « የሀገራችን ታላቅ አሊም ከሀገራችን ታላቅ ሌባ ጋር! » ሲል አንደበታቸው ገለፀው። ኢማሙም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው « ሊሰርቀን ሲመጣ ሰረቅነው! » ታዲያ ያ ታላቅ ሌባ ከኢማሙ ስር በመክረም ታላቅ ደረሳቸው ለመሆን በቃ።

@heppymuslim29

Читать полностью…

🍀ሺሊላ ሺሊላ🍀

#የችሎት_ንግስት
              ክፍል ስምንት

✍️አብዱ ኤምሬ


              ደስታን ከሚፈጥሩልኝና ጭንቀቴን ከምረሳባቸው ነገሮች ዋነኛው ዳንስ ነበር። ከልጅነቴ ጀምሮ የተለየ የዳንስ ፍቅር ነበረኝ.. በዚህም የተነሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር ውስጥ free dance አገልግሎት እየሰጠሁኝ ቆይቻለሁ። ሲጨንቀኝና ውስጤ ሲረበሽ ቶሎ የምገባው ዳንስ ውስጥ ነው፤ የነበረኝ ጭንቀቴ ሁሉ በአንዴ ከላዬ ይጠፋል። እንደኔ መደነስን የመሰለ አለም ላይ በጣም አስደሳች እንቅስቃሴ ያለ አይመስለኝም፤ ከትጉህነቴና ካለኝ ፍቅር የተነሳ አሰልጣኜ በጣም ነበር የሚወደኝ፤ በተለያየ ጊዜያት ብዙ መድረኮችና ዝግጅቶች ላይ ዳንሴን አቅርቤለሁ። ከሁሉም አገኘው የነበረው ግን ተመሳሳይ የአድናቆት መልእክቶችን ነበር፤ አሁን ላይ ግን ስልጠናውን ከተውኩት 3 ወራት አልፈውኛል፤ ለምን? አይባልም ምክንያቱም ሱሰኛ ለራሱ እንኳን ጊዜ አይሰጥም፤ አሰልጣኜ ደጋግሞ እንድመለስ ቢጠይቀኝም እሺ ብዬው በቀጣዩ ቀን ግን ስልጠና ለመሄድ ምን አንደሚይዘኝ አላውቅም።

             በኔ አመለካከት የሰው ልጅ እዚህ አለም ላይ ሲመጠሰ የራሱ ተልእኮና የመኖር ምክንያት ይኖረዋል፤ እስካሁን ግን ያን ተልዕኮና ምክንያት ካላገኙ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ፤ ይሄን ምክንያት ለማግኘት ብዙ የሀይማኖት መፀሀፍትን አገላብጫለሁ.. በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ውስጤ ያለውን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ምንም ነገር አላገኘሁም። ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስጤ በጥያቄዎች ይሞላ ጀምሯል፤ አንዱን ጥያቄ ልመልስ በተጣጣርኩ ቁጥር መልስ ሳይሆን ሌላ ጥያቄ የሚፈጥር ነገር ያጋጥመኛል። አሁን ላይ እምነት የለሽ ነኝ ማለት ይቻላል፤ ሁሉም ከማስመሰል ውጭ ልቤን የሚያረጋጋ አንዳቸውም ስርአት አላገኘሁም.. ሃይማኖት ሰዎችን ለማጃጃል የተፈጠረ ትርክት አድርጌ መውሰድ ከጀመርኩ ሰንብቼለሁ። ሃይማኖተኛ የተባለውም ሰው ለሆዱና ለአለማዊ ነገር ቀን ተሌት ሲኳትን ይገኛል.. ታድያ ጥያቄዎችን መመለስ ቀርቷ የሚገድብ ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል..?

            አንዳንድ ጊዜያት እራሴን የት እንዳለሁ እስከማላውቅ ድረስ በነገራቶች ግራ እገባለሁ፤ የማን ድርሰት ነኝ? ማነው ሁሉን ነገራት የፈጠረውና አንዱን አስበልጦ አንዱን አሳንሶ የፈረጀው.. እውነት ምን አይነት አድሎዊነት? በኔ ድርጊቶች እየተመለከተ የሚስቅ አከሰል ያለ እስኪመስለኝ ጭንቅላቴ በጥያቄዎች ሊፈነዳ ይደርሳል፤ ብቻዬን ከሆንኩማ አእምሮዬ ምንም ፈታ ማግኘት አይችልም፤ "አእምሮ ሰላም ከሌለው የትኛውም አካል ሰላማዊ አይሆንም።" ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁሉነገራት እያስጠሉኝ መጡ፤ "በህይወት ስትኖር አንድ የሚጨነቅልህና የሚያስብልህ አካል ከሌለ ምንድነው ትርጉሙ።" እራሴን ለማጥፋት ብዙ ጊዜያት አስባለሁ ግን የመኖሬን ምክንያት እንኳ ሳላውቅ ብዬ በየጊዜው ለራሴ እስትንፋሴን አራዝማለሁ። አእምሮ ሊመልሳቸው የማይችላቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ የበሽታዎችን መገላገያ ተፈጥሮ መድሀኒት እንደሚያመላክት ሁሉ፤ ተፈጥሮ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ብታመላክት ምን ያለ መልካም ነገር ነበር።

       አእምሮ በጭንቀት በሚሞላ ቁጥር የመኖር ፍላጎትህ አነስተኛ ስለሚሆን የሱሰኝነት ገደብህ ያልፋል፤ አብዛኛው ሱሰኛ የማበዱ ምክንያት ሌላ አይደለም ወይ አለማዊ ጥያቄዎቹን የሚመልስ አልያም መንፈሳዊ መልስ በማጣቱ ነው፤ ሀይማኖት ሱሰኛን ካራከሰና ካራቀ ወዴት መሸሺያ አለውና?
                  ይቀጥላል...

@YEFKIR_MENGED
@YEFKIR_MENGED

Читать полностью…
Subscribe to a channel