slehiwetwe | Unsorted

Telegram-канал slehiwetwe - ቅድስት ፌብሮኒያ

-

ይህ ቻናል ስለ ህይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፋልበት ነው እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል ለማንኛውም ሀሳብ ጥያቄ እና አስተያየት

Subscribe to a channel

ቅድስት ፌብሮኒያ

|<<-በጸሎትህ ውስጥ ባለ አንድ ቃል #ጣዕም ወይም #ጸጸት ከተሰማህ በእርሱ ላይ ቆይ ፤ #ጠባቂ_መላእክቶቻችን ከእኛ ጋር አብረው እየጸለዩ ነው!!->>|

+_ዮሐንስ ዘሰዋስው

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስንት ሰው ነው?" ቢባል [ይህን ያህል] አይባልም። ሊቁ አካሉ አንድ ይኹን እንጂ ብዙ ሰው ነው። መምህር፣ ባሕታዊ መልአክ፣ ካህን፣ መነኩሴ፣ ጳጳስ፣ ሊቀ ጳጳስ ሰማዕት ነው። በባቢሎን ወንዞች መካከል ኾኖ ጽዮንን የሚያስብ ጎርፍ የማያናውጠው ጽኑ ቤት፣ ውኃ የማያጠፋው የፍቅር እሳት፣ ጨለማ የማያደበዝዘው የወንጌል ኮከብ ነው። ዮሐንስ አፈወርቅ የመጽሐፍ ተርጓሚ ብቻ ሳይኾን ራሱ የመጻሕፍት ትርጓሜም ነው።"

መጋቢ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

https://youtu.be/wYw6G4_F1rE

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#እግዚአብሔር #ይጠብቅሀል።

ከዳዊት መዝሙር አንድ ጥቅስ ልስጣችሁና አብረን እናብሰልስል ቃሉ "ዓይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ ፤ረዳቴ ከወዴት ይመጣልኛል?" በማለት ይጀምራል /መዝ 121፥1/። ስለዚህ የመዝሙር መፅሀፍ ጥቂት ልበላችሁና አስከትዬ በምዕራፍ መጨረሻ ስላሉት "እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሀል፤ ነፍስህንም ይጠብቃታል፤ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ፤እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።"/መዝ 121፥7-8/ ስለሚሉት ሁለት ጥቅሶች ልነግራችሁ እወዳለሁ።ይህ መዝሙር የ"መጠበቅ" መዝሙር እንለዋለን "እግዚአብሔር ይጠብቅሀል" የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ በውስጡ ተጠቅሷል።ይህ የባህታውያን መዝሙር ከሚባሉትና ተራራ ላይ ወዳለው መቅደስ ሲወጡ የሚፀልዩት ነው።ይህ ፀሎት በአንዳንድ አጋጣሚዎችም ይደገማል።በሽኝት፣በቡራኬ፣በምርቃት ይደርሳል።ልጇ ተለይቷት የምትኖር እናትም የምትጸልየው ነው። ከቤቱ ውጭ የሚያጋጥመውን ለማያውቅ ፣በጉዞም ላይ ላለ ሰው ሁሉ መልካሙን የምንመኝበት ነው።መዝሙሩ ብቸኛ አስተማማኝ ጠባቂ እግዚአብሔር መሆኑን ይመሠክራል። ምናልባትም ይሄ ጸሎት ከሚወደድ ሰው ብቻ የሚጠበቅ አይደለም፤ቅዱሳን መላዕክትም ተስፋና ረድኤት ሊያደርሱለት ለተዘጋጁለት ምእመንም ይጸልዩለታል እንጂ።እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሀል....."ይሉታል።እርሱ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ ማለታቸው ነው።
ይኸው መዝሙር በሌላ መዝሙር ክፍል " በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምልህ፣ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ" ተብሎ የተነገረውን ቃል ያስታውሳል /መዝ 20፥1/ ይህ የጸሎትና የቡራኬ መዝሙር ነው።ይህ ወደ ጦር ግንባር ለሚሔድ ንጉሥም ይዘመር ነበር። ነገር ግን ለማንም ቢሆን መቼም ቢሆን ሊደገም የሚገባው ጸሎት ነው።
#የኤልኬራዝ #በረከቶች ቁጥር 2

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

......ሕሙማነ ልብ......

ስለ-ባልንጀራው በታመመ ልቦና የሚጸልይ ክርስቲያን ክርስቶስን የሚመስል ነው። ክርስቶስ በመስቀል የእኛን ሸክም እንደተሸከመ ልቦናውን ቀራንዮ ላይ የተከለም በልቦናው መስቀልነት የባልንጀራውን ሸክም ይሸከማት ዘንድ ከጌታው ያያት ፍቅር ታስመኘዋለች። ያቺ ሕመም የባልንጀራን መከራ ምነው ለኔ ባደረገው እያሉ የምንታመማት ቅድስት ሕማም ናት። በባልንጀራው ስቃይ ራሱን ጨምሮ ባልንጀራውን ማርልኝ ከሚል ሰው መዓዛ ክርስቶስ ይሸተታል!!

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ልብህ ከዚህ ዓለም ጋር ተጣብቆ ሳለ ስለ እግዚአብሔር ማውራት አይቻልም ፤ ልብህ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣበቀ ከሆነም ስለዚህ ዓለም ማውራት አይቻልም!❞

-ብሂለ አቶሳውያን-

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"ኃጢአትህን ፡ ትሸፍንልሃለችና ፡ ትህትናን ፡ መውደድ ፡ ተማር።"

+ ቅዱስ አባ እንጦንስ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ሁለት ቤተመቅደስ

ኢያቄም ወሐና
በአምላክ ቢታመኑ ፆም ፀሎት ቢወድዱ፣
ድንቋን ቤተመቅደስ
ማህደረ ፀሐይዋን ሰማይን ወለዱ።

ትጉሃነ ሰማይ ቁመት ሚቆሙባት፣
ቅዳሴ መላዕክት የሚደመጥባት፣
የእግዚአብሔር ዙፋኑ
መቅደስ ሆና ሳለች ቤተመቅደስ ገብታ፣
በቅድስና እና
በትህትና ኖረች በፆም ፀሎት ተግታ።

ወንድሟም ፋኑዔል..

ስቴ ሰማያዊ
ወኅብስተ መና ሁሌ እየወረደ፣
ይመግባት ነበር
አንዱን ክንፍ አንጥፎ በአንዱ እየጋረደ።

ከመ አዋልደ አይሁድ
ወራዙት ስፉጣን ያፅናኗት አይደለም፣
ዕድሜ ልኳን ሙሉ
ከመላዕክት በቀር የምታውቀው የለም።

ያ የአምላክ አገልጋይ
ካህኑ ዘካርያስ ከቶ እንዴት ታደለ፣
ማንም ያልቻለውን
ሁለት ቤተመቅደስ በአንዴ ማጠን ቻለ።

✍ አብርሃምን አግማስ(ቴቄል)
ታኅሣሥ 1-2013 ዓ.ም

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ስሚ እህቴ ይሄ መልእክት ላንቺ ነው🙏

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

✍️ቀላልና ያልተሸላለመ የልጆች መኮላተፍ ዘወትር የሰማያዊ አባታቸውን #ልብ ያሸነፈ ነውና ፤ ስትጸልይ በምትጠቀማቸው ቃላት ከመጠን በላይ #አትራቀቅ!!

+_ዮሐንስ ዘሰዋስው

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ተወዳጆቼ ፡ ሆይ! #በኢየሱስ_ክርስቶስ ፡ ስም ፡ እለምናችኋለሁ! የመዳናችሁን ፡ ነገር ፡ ከቶ ፡ ቸል ፡ አትበሉ!!

+ርእሰ-መነኮሳት አባ እንጦንዮስ [እንጦንዮስ እንጦንስ ፣ እንጦኒ] በኹሉም ቦታ ለሚኖሩ ዝርዋን ወንድሞች ከላከው ሁለተኛ መልእክት...

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

|<<ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን>>|

+. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜

|<<የእግዚአብሔር ቃል የመላዕክት ምግብ ነው፡፡ ይኽም ነፍስን የሚመግብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ነፍሱን የሚጠግን (የሚመግብ) ከኾነ በጎነትን በመረዳት ይሞላል፡፡ ክፋትንም ይጸየፋል፡፡>>|

+. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#እግዚአብሔር #ይጠብቅሀል።

ከዳዊት መዝሙር አንድ ጥቅስ ልስጣችሁና አብረን እናብሰልስል ቃሉ "ዓይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ ፤ረዳቴ ከወዴት ይመጣልኛል?" በማለት ይጀምራል /መዝ 121፥1/። ስለዚህ የመዝሙር መፅሀፍ ጥቂት ልበላችሁና አስከትዬ በምዕራፍ መጨረሻ ስላሉት "እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሀል፤ ነፍስህንም ይጠብቃታል፤ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ፤እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።"/መዝ 121፥7-8/ ስለሚሉት ሁለት ጥቅሶች ልነግራችሁ እወዳለሁ።ይህ መዝሙር የ"መጠበቅ" መዝሙር እንለዋለን "እግዚአብሔር ይጠብቅሀል" የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ በውስጡ ተጠቅሷል።ይህ የባህታውያን መዝሙር ከሚባሉትና ተራራ ላይ ወዳለው መቅደስ ሲወጡ የሚፀልዩት ነው።ይህ ፀሎት በአንዳንድ አጋጣሚዎችም ይደገማል።በሽኝት፣በቡራኬ፣በምርቃት ይደርሳል።ልጇ ተለይቷት የምትኖር እናትም የምትጸልየው ነው። ከቤቱ ውጭ የሚያጋጥመውን ለማያውቅ ፣በጉዞም ላይ ላለ ሰው ሁሉ መልካሙን የምንመኝበት ነው።መዝሙሩ ብቸኛ አስተማማኝ ጠባቂ እግዚአብሔር መሆኑን ይመሠክራል። ምናልባትም ይሄ ጸሎት ከሚወደድ ሰው ብቻ የሚጠበቅ አይደለም፤ቅዱሳን መላዕክትም ተስፋና ረድኤት ሊያደርሱለት ለተዘጋጁለት ምእመንም ይጸልዩለታል እንጂ።እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሀል....."ይሉታል።እርሱ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ ማለታቸው ነው።
ይኸው መዝሙር በሌላ መዝሙር ክፍል " በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምልህ፣ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ" ተብሎ የተነገረውን ቃል ያስታውሳል /መዝ 20፥1/ ይህ የጸሎትና የቡራኬ መዝሙር ነው።ይህ ወደ ጦር ግንባር ለሚሔድ ንጉሥም ይዘመር ነበር። ነገር ግን ለማንም ቢሆን መቼም ቢሆን ሊደገም የሚገባው ጸሎት ነው።
#የኤልኬራዝ #በረከቶች ቁጥር 2

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ከ"ዮሐንስ ዘሰዋስው" መጽሐፍ ከገረሙኝ እና
ነፍስን ብርክ ውስጥ ከሚከቱ ክፍሎቹ መካከል!
#አቤት_ንስሐ እግዚኦ!🤔 ወይ ልየ🙏
[መጽሐፉን ብናነበው #ዮሐንስ_ዘሰዋስው "ትርጉም በሳሙኤል ፍቃዱ"]

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"ስለ እግዚአብሔር ብለህ ለሰዎች ታዘዝ እንጂ ስለ ሰዎች ብለህ ለእግዚአብሔር አትታዘዝ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

አንድ አረጋዊ መነኩሴ ከበኣቱ ወጥቶ ሳለ "የሰው ልጆችን ሥራ አሳይኽ ዘንድ ና" የሚል ድምፅ ሰማ፤ ርሱም ከበኣቱ ወጥቶ የጠራውን ድምፅ ተከትሎ ተጓዘ።

👉 ያ ድምፅ ወደ አንድ ቦታ አደረሰውና አንድ ኢትዮጵያዊ እንጨት እየፈለጠ ሲከምር አሳየው፤  ያ እንጨት የሚፈልጠው ሰው፣ የፈለጠውን እንጨት ሊሸከመው ሞከረና አቃተው፤ ይኹን እንጂ በመቀነስ ፈንታ አኹንም እየቆረጠ መከመር ቀጠለ።


👉 ጥቂት አለፍ ብሎ ደግሞ፦
አንድ ሰው በሀይቅ አጠገብ ቆሞ፣  በተሰበረ ማሰሮ ውሃ ሲቀዳ ተመለከተ፤  ማሰሮው የተሰበረ በመኾኑ ውሃው እንደገና ወደ ሐይቁ ይመለስ ነበር፤ 


👉 በሌላ ሥፍራ ደግሞ፦ 
ኹለት ሰዎች ጎን ለጎን ኾነው መጡ፤  በትከሻቸውም በትራቸዉን(ዱላቸዉን) ጫፍ እና ጫፍ ላይ አጋድመው ይዘውት ነበር፤
በመቅደስ በሩ ወደ ውስጥ ሊያልፉ ቢፈልጉም፣  በትራቸውን አግድም ስለያዙት ያግዳቸው ነበር
አንዳቸውም ከሌላኛው ኋላ በመኾን በትሩን ፊትና ኋላ አድርገው ሊገቡ አልፈለጉም፤ ስለዚኽ በፉክክር ከውጪ ቀሩ።

፨ ☝️እንዚኽ ሰዎች የጽድቅን ቀንበር በትዕቢት ተሸክመውታል፤  ራሳቸዉን ዝቅ ዝቅ አላደረጉም፤  ራሳቸዉን ለማረም እና በክርስቶስ የትሕትና ጉዞ ለመጓዝ አልፈለጉም፤ 
ስለዚኽ ከመንግሥተ ሰማያት በአፍኣ/በውጪ/ ይቀራሉ።

፨ እንጨት የሚቆርጠው ሰውም፥ በኀጢአት ላይ ኀጢአት የሚጨምር ሰውን ይመስላል፤  ንስሓ ከመግባት ይልቅ ሌሎች ኀጢኣቶችን እንደገናን ይጨምራል።

፨ ውሃ የሚቀዳውም ሰው፣   መልካም ሥራን የሚሠራ ሰውን ይመስላል፤ 
ነገር ግን መልካም ሥራው ከክፉ ሥራው ጋር የተቀላቀለ በመኾኑ ጥቂቱ መልካሙ ሥራው ይበላሽበታል፤

👉 ስለ ኾነም እያንዳንዱ ለሚሠራው ነገር ሊጠነቀቅ እና በከንቱ እንዳይደክም ሊያስብበት ይገባል" አለው።


[ በበረሓው ጉያ ውስጥ፤ ( የቀደምት አበው እና እማት መንፈሳዊ ኑሮና ምክር )፤ አርታኢ፦ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤  ገጽ ፲፭/15፤  ፲፱፻፺፰/1998 ዓ.ም. ]

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

+. ጌታ ሆይ! ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ። ቅዱሳንህ አንተን ያወቁባት ጽድልት ከኃጢአት የነጻች ሰብእና ግን በእኔ ዘንድ የለችም።

+. እንደ-ምንም ብዬ ወደ-አንተ እጠጋለሁ ኀጢአትም በእኔ ላይ በርትታ ካንተ ታርቀኛለች ፤ እንደገና ተመልሼ ወደ-አንተ እጠጋለሁ ኃጢአቴም ዳግመኛ ካንተ ሳልወድ በጭንቅ ታርቀኛለች።

+. ጌታዬ ሆይ! አንዴ ወደ-አንተ አንዴ ደግሞ ወደ-ኃጢአት በመመላለስ ደከምሁ ፤ አንተን በፍጹም ንጽሕና ፈጽሜ እፈልግህ ዘንድ በፍኖተ-አሚን ለመራመድ እግሬን ሳነሳ ኃጢአት ፊት ለፊቴ እየቆመች አስቸገረችኝ።

+. ፈጽሜ እንዳልተውህ ደግም ያቀመስኸኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ነፍሴ ተጨነቀች ፤ አቤቱ አንተስ እስከመቼ ነፍሴን ዝም ትላታለህ...? እስከ-መቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ...?

#ጌታ_ሆይ_ኀጢአቴ_አንተን_እንዳትቀማኝ_እባክህ_ከልክላት!!

ለዓለመ-ዓለም አሜን🙏

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ያዕቆብ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
¹⁸ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።
-------------

እንኳን ለታላቁ ቁጠኛ/ቀናዔ-አምላኩ ለሆነው ነቢይ ለነቢየ-ልዑል #ቅዱስ_ኤልያስ በዓለ-ልደት አደረሰን!!
ኃይል አድራጊ በሆነች ክብርት ጸሎቷ እንታሰብ!!

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel