~◉ትምህርት እንዲሆነን ፥ ደዌን ታመጣብናለህ ፤ ልትፈውሰን ታቆስለናለህ ፤ ከአንተ ተለይተን እንዳንሞት ፤ ሞትን ታመጣብናለህ◉~
-አውግስጢኖስ-
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” /ማቴ.10፡16/
እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#የሚጠብቀኝ_አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም
ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ለሊት ከኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የለሊት ግርማ
ወደኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ
አዝ
መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
አዝ
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
አዝ
የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ለሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ
አዝ
እንቅልፌን ባርኮ ለሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም
መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ
"እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።"
👉 መዝሙረ ዳዊት 121:4
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈
ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡
👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ
👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!
👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"
ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡
የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡
በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)
ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡
#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት
ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ፣ ድርሳን 3፥8
ቀንህን በምስጋና ጀምር!👆
ለማዘንና ለመቆዘም፥ለመተከዝም ከፈለክ ሩቅ መሄድ ሳይጠበቅብህ የለለህን ፣ የጎደለህን፣ ያልተሳካልህን ነገር ችግር ደርድረህ አስቀምጠህ ልታለቅስና ልትቆዝም ትችላለህ።
ነገር ግን ስታስበው የምያስደስትህ ምንድ ነው ብትባል 😳
እኔ እንጃ ምን ልያስደስተኝ እንደምችል አላውቅም ልትል ትችላለህ
አሁን ግን ልንገርህ ከሁሉም የበለጠ ልትደሰትበት የምገባህ ነገር ቢኖር እስትፋስህ ነው
እስትንፋስ ስላለህ ብቻ አመስግን ደስም ይበልህ
ምክንያቱም እስትንፋስ እስካለህ ሁሉንም የመሆን እድል አለህ
እንደ ገና ለመነሳት ፣ እንደ ገና ለመስራት፣ እንደ ገና ለመሮጥ ፣ እንደ ገና ለማሰብ፣ እንደ ገና ለመጓዝ፣ እንደ ገና ለመማር፣ እንደ ገና ለማፍቀር እንደ ገና ለመፈቀር እንደ ገና ስኬት ለማግኘት እድሉ አለህ
ስለዝህ ደስተኛ ለመሆን ቁስ አትቁጠር
ያለህ በቂ ነውና አመስግን።
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ጸሎት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምታደርስ ቀጭኗ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት በመራቅ የሚቀርብ ጸሎት ፍጹም የሆነ ሥራን
ይሰራል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርክ በእግዚአብሔር ስም ለጸሎት የምትቆም ከሆነ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ ህሊናህም
ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ በጸሎት ተመስጠህ ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ፡፡
አጠገብህ ስሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠኸው ቁጥር ነው፡፡ ጥላቻ
በልቦናህ ነግሶ ከሆነ የዳቢሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡
የተንኮል ቃልን አትናገር፤ ለባልንጀራህ ጉድጓድ አትቆፍር፤ ወደ አመንዝራም ሴት አትመልከት የፊቷም ደምግባት አያጥምድህ፡፡ በእርሷ መረብ
እንዳትጠመድ ከአንደበቷ ከሚፈልቁት ጣፋጭ ቃሎች ተከልከል፡፡ ከእርሷ ፈጽሞ ሽሽ፡፡
በሰዎች ውድቀት አትደሰት፡፡ በደለኛ እንዳትሆን ጠላትህ ክፉ ሲደርስበት አይተህ ደስ አይበልህ፡፡ ጠላትህ በኃጢአት ተሰነካክሎ ብታይ ስለ
እርሱ እዘንለት አልቅስለት፡፡ እጆችህን ለሥራ አትጋቸው፤ ከንቱ ንግግር አትውደድ ለነፍስና ለሥጋ ብሩህነት በሥራ መጠመድን ውደድ፡፡
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን
#እናንተ_ማግባትን_የምትሹ_ወጣቶች_ሆይ፦ ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡
#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ፦ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡
የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
ወዳጄ እስኪ ልጠይቅህ፥ አንተም አንቺም መልሱልኝ! ጌታችን ዛሬ ቢመጣ የምትመልሰው መልስ ምንድን ነው? "ንስሐ ያልገባሁት፣ ሥጋ ወደሙን ያልተቀበልሁት፣ ምግባር ትሩፋት ያልያዝሁት ዕድሜዬ ገና ነው ብዬ አስቤ ነው፤ ሥራ በጣም በዝቶብኝ ስለ ነበረ ጊዜ አጥቼ ነው፤ ዛሬ ነገ እያልኩ እየረሳሁት እንጂ እንደዚያ ማድረግ አቅቶኝ አልነበረም፡፡"
ምክንያትህ እነዚህ ናቸው? እኅቴ! ሰበቦችሽ እነዚህ ናቸው? በዚያ ሰዓት ግን እነዚህ ኹሉ ጥቅም የላቸውም፡፡ እናት ልጇን በማታድንበት ሰዓት እነዚህ ምክንያቶች ምንም አይረቡም፡፡ ታዲያ ለምን ትዘገያለህ? እኮ ለምን ትዘገዪያለሽ? ያኔ ዋይ ዋይ ከምትዪ...ያኔ የማይጠቅም ጸጸት ከምትጸጸት ለምን ዛሬ አትጠቀምበትም? ለምን ራስህን አታድንም?
#ከገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ
@Slehiwetwe
የቀጠለ...
ማተብ ሚስጢሩ እርስዎ ያስተማሩት
የላይ ምልክት ነው በልብ ላመኑት
ከቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ
እንደ ተማረነው ወግ ከአበው መጻኢ
እውነተኛው እምነት በልባቸው ሆኖ
ለፈጣሪ ሲታይ በልበ ተአምኖ
ማተብ ግን ለሰው ነው ልቡን ለማያይ
የውስጣችን እምነት በተግባር እስኪታይ።
ይህ ነበር እውነቱ የኔ ጥቅም ለሰው
ወንጌሉን እንዲኖር ሁሌ ላስታወሰው።
ዛሬ ግን ብዙዎች ይህን ሳይረዱ
ባንገት እያመኑ በምግባር የካዱ።
ውስጣቸውን ዘግተው ከውጭ እያሰሩኝ
መገለጫ ሳይሆን መሸፈኛ አረጉኝ።
ይህም ሰው አባቴ ከእዚህ አንዱ ነው
በኔ ተሸፍኖ ውስጡ ግን ሌላ ነው
እርሱ እንደ ነገርዎት ብዙም አይወደኝም
ከነመኖሬ እንኳ አያስታውሰኝም
ለባለንጀሮቹ ሲናገር በሐሰት
ምንም አይመስለውም በስሜ ሲገዝት።
እኔን ያየ ሁሉ ክርስቲያን ሽፍኜበት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀደሱ።
ምግብ ቤት ነው ተብሎ ከውጭ ከተጻፈ
እንጀራ ይገኛል ወደ ውስጥ ላለፈ።
እንዲሁም አንገት ላይ ማተብ መታስሩ
ወደ ታች ወደ ልብ ጣቱን መቀሰሩ።
ውስጥ ያለውን ሊያሳይ መሆኑን ንገሩት
ክርስቶስን ለብሶ እንዲኖር ምክሩት።
ብዙ ሰው አታሎአል አባይ ነው ምላሱ
ውስጡን ያሳልሙልኝ ልቡን ይቀድሱ።
ተፈፀመ!
፨ግጥማዊ ተውኔት፨
አባ ይፍቱኝ
መስቀሉን ያሳልሙኝ
ልጄ የተባረክህ
እማይሰራ ኃጢአት
እግዚአብሔር ይፍታህ
እስኪ ጠጋ በለኝ
ክርህን አሳየኝ።
አንገትህን ልየው
ማተቡን አስረሃል?
እንዴታ አባቴ
ማተብ ምልክቴ
መቼ ትለያለች
በጭራሽ ካንገቴ
ማህተቤ እኮ ናት
እጅግ የማከብራት
ክርስቲያን መሆኔን
በጌታ ማመኔን ምመስክርባት
የውስጥ እምነቴን ለሰው ማሳይባት
መናገሪያ ቃሌ
ይችናት መስቀሌ
በልቤ ያለውን
ውስጤ የሚያምነውን
እንዴት አሳይ ነበር
ማተቤ ከሌለች
እንዴት ልመስክር
አባ ማተቤማ ምስክሬ እኮናት
የመጣው ይምጣ እንጂ ካንገቴ አለያት።
በማለት ሲናገር ለንስሐ አባቱ
አቶ ግብዝነት ሐይማኖት ባንገቱ
አፍ የላትም ብሎ በማተብ ሲደበቅ
ድንገት አፍ አውጥታ "አ" ከማለትዋ
ዝም በይ ብሎ በጁ አፍዋን ሊይዝ ሲል
መናገር ቀጠለች ማተብ የእውነት ቃል
ይቀጥላል....
ጾመ ነነዌን በማስመልከት ቅዱስ ሲኖስ የሦስት ቀን ጾምና ጸሎት አወጀ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ! ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።
በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ
(ማኅበረ ቅዱሳን)
ደጋግመን እንደ ተነጋገርነው የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ #ጽድቅን #መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ የትዳር ዓላማዎች ኹሉ በዚህ የሚጠቃለሉ ናቸውና፡፡ ስለዚህ አንድ ወጣት፡-
☞ ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት የለበትም፤ የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ፥ ላይወልድም ይችላልና፡፡
☞ “በየምግብ ቤቱ መብላት ወጪውን አልቻልኩትም” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ “በገንዘብ እንድንረዳዳ” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ ወጪ መቀነስ መልካም ቢኾንም፥ የትዳር ዋናው ዓላማ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነውና፡፡ እንዲያውም ሊቁ፡- “ክርስቲያን ኾነህ ሳለ ከትዳር አጋርህ ገንዘብ ለማግኘት ብለህ ወደ ትዳር ከምትገባ ምድር ተከፍታ ብትውጥህ ይሻላል” ይላል፡፡ ስለዚህ “ገንዘብን አትሹ፤ የወላጆቹን ባለጸግነት አትመልከቱ፡፡ የትውልድ ቀዬውን ታላቅነትም አትዩ፡፡ እነዚህ ኹሉ ዋና ነገሮች አይደሉምና፡፡ ከትዳር አጋራችሁ ጋር በተድላ በደስታ መኖርን ስትሹ ማየት የሚገባ’ችሁ ንጽሃ ነፍስን፣ ደግነትን፣ ልባምነትንና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ነው፡፡”
☞ አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ ነው በሚል ብቻ ማግባት የለበትም፡፡ ይህ በራሱ መልካም ቢኾንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልኾነ አንድ ለአንድ መወሰን ብቻውን የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ አይደለምና፡፡ ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው አንድ ለአንድ የሚወሰኑ አሉና፡፡
☞ ዕድሜዬ እንዳያልፍ ብሎም ኾነ ሰው አግባ ብሎ አስጨንቆት ማግባት የለበትም፡፡ ትዳር ከ “ለምን አታገባም?” ጭቅጭቅ ለማምለጥ የተሰጠ አይደለምና፡፡
☞ “መልኳን ወደድኳት” ብሎ ማግባት አይገባም፡፡ ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለምና፡፡ ይህን አድንቆ ወደ ትዳር ከገባ ያ የማረከው ውበት ከሃያ ወይም ከሠላሳ ቀናት በኋላ አይማርከውምና፤ ይለምደዋልና፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ጸሎት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምታደርስ ቀጭኗ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት በመራቅ የሚቀርብ ጸሎት ፍጹም የሆነ ሥራን
ይሰራል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርክ በእግዚአብሔር ስም ለጸሎት የምትቆም ከሆነ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ ህሊናህም
ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ በጸሎት ተመስጠህ ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ፡፡
አጠገብህ ስሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠኸው ቁጥር ነው፡፡ ጥላቻ
በልቦናህ ነግሶ ከሆነ የዳቢሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡
የተንኮል ቃልን አትናገር፤ ለባልንጀራህ ጉድጓድ አትቆፍር፤ ወደ አመንዝራም ሴት አትመልከት የፊቷም ደምግባት አያጥምድህ፡፡ በእርሷ መረብ
እንዳትጠመድ ከአንደበቷ ከሚፈልቁት ጣፋጭ ቃሎች ተከልከል፡፡ ከእርሷ ፈጽሞ ሽሽ፡፡
በሰዎች ውድቀት አትደሰት፡፡ በደለኛ እንዳትሆን ጠላትህ ክፉ ሲደርስበት አይተህ ደስ አይበልህ፡፡ ጠላትህ በኃጢአት ተሰነካክሎ ብታይ ስለ
እርሱ እዘንለት አልቅስለት፡፡ እጆችህን ለሥራ አትጋቸው፤ ከንቱ ንግግር አትውደድ ለነፍስና ለሥጋ ብሩህነት በሥራ መጠመድን ውደድ፡፡
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን
ጾም በአንተ ውስጥ የሆነ አንድ ነገር መለወጡን ተመልከት።
ከጾም የምታገኝው ነገር የምግብ ለውጥ መሆኑን ብቻ አትመልከት። ለተሻለ ህይወት የሚደረግ ለውጥ መሆኑን ተመልከት። ይህም ማለት በአንተ ውስጥ ያለ ጉድለትንና በውስጥህ እንዳለ የሚሰማህን ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር የሚሆን ድክመት ተመልከት ማለት ነው። ይህ ሳይሆን ከቀረ በሃምሳ አምስቱ የሁዳዴ ጾም ቀናት ውስጥ ራስህን አሸንፈህ ከቆየህ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ዝምድና እና የተረጋጋ ግንኙነት ሳትፈጥር ከጾሙ አስቀድሞ የነበረህን አቋም ሙሉ ለሙሉ ይዘህ ለመውጣት ከሆነ የነፍስህ ጥቅም ምን ሊሆን ነው? አንተ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳታመጣና አስቀድመህ በነበርህበት ሁኔታ ውስጥ እያለህ እስከ አሁን ድረስ ስንት አጽዋማት እንዳለፉህ አስብ!
በሁሉም አጽዋማት ውስጥ ፈቃድህ ደካማ ጎንህን ለማሸነፍ ስኬታማ እንድትሆን አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር እንድትታረቅ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ወይም የእርሱን ፈቃድ ጣፋጭነት እንድትቀምስ አድርጎህ ቢሆን ኖሮ ከእግዚአብሔር። ጋር የሚኖርህ ዝምድና እስከ አሁን ድረስ እንደምን የሰፋና የጠለቀ ይሆን ነበር!
ስለዚህ ንስሃ በመግባት ጾምህን ጀምር። ጾምህን በጸሎት በምጽዋት በስግደት በመንፈሳዊ ንባባት በቅዳሴ በኪዳን ጸሎቶች አጅበው። እነዚህን ሁሉ በማድረግህ ከእግዚአብሔር ጋር ትወዳጃለህ የሁዳዴ ጾም የያዛቸው በረከቶች ብዙ ናቸውና። እኒህን ካደረክ በመጨረሻ ላይ ውጤቱን ከአምላክህ ትቀበላለህ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
በዚህ ዘመን የገጠመን እውነተኛው ፈተና ይህ ነው።
ንስሓ የሚገባ ምእመን አላፈራንም።
ይልቁንም ቃለ እግዚአብሔር ተለማምደው ፣ተረት ካልተነገረ ቃሉ አይስባቸውም። እንደ ሰይጣን ጥቅስ የሚያውቁ ክርስቲያን መሰል ክርስቲያኖችን አበራክተናል
አስመሳይነትና አድርባይነት ክርስትናውን ጠላልፎ አስሮታል።
እውነቱን ሲነግሯቸው የሚያኮርፉ፣ ለውዳሴ ከንቱ የመጡ ምእመናን በልብስ አሸብርቀው በምግባር ደርቀው የሚታዩበት ዘመን ሁኗል።
መምህር ወመገሥጽ የሚለው እውነትኛው የማስተማሪያ መመሪያችን ባለመጠበቁ ነው።
ሙሉውን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/abagebrekidan/1921
በጾም ሰዓታችሁ ጊዜ ይሁንም አይሁንም ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡
እነርሱም፡-
☞ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣
☞ ማንንም ሰው እንደ ጠላት ከማየት መቆጠብንና
☞ እንደ ልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ሰንበተ_ክርስትያን
በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ
አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
✝️ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ✝️ የሌላ እምነት ተከታይ ሰው ማግባት ይቻላል? |
ከዝሙት ሽሹ | ራሳችሁን አትመኑ!
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።
²⁶ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤
²⁷ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
|<<ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን>>|
+. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
|<<የእግዚአብሔር ቃል የመላዕክት ምግብ ነው፡፡ ይኽም ነፍስን የሚመግብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ነፍሱን የሚጠግን (የሚመግብ) ከኾነ በጎነትን በመረዳት ይሞላል፡፡ ክፋትንም ይጸየፋል፡፡>>|
+. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
✍️ቀላልና ያልተሸላለመ የልጆች መኮላተፍ ዘወትር የሰማያዊ አባታቸውን #ልብ ያሸነፈ ነውና ፤ ስትጸልይ በምትጠቀማቸው ቃላት ከመጠን በላይ #አትራቀቅ!!
+_ዮሐንስ ዘሰዋስው
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
....የቀጠለ
አባ እኔን ይስሙኝ
ከልብዎ ያድምጡኝ
ሰዎችን ሳይፈራ እግዜርን ሳያፍር
በስንቱ ሰዎች ፊት ሐሰት ሲመሰክር
እኔን እያሳየ ስንቱን ሰው አሞኘ
ብዙ ታግሻለሁ አንገቱ ላይ ሆኜ
በድፍረት ሲያታልል የሐይማኖት አባቱን
ዛሬ ግን አልቻልም ልናገር እውነቱን።
ያለሁበት ሥፍራ ይህ ደንዳና አንገቱ
መካከለኛ ነው ለልብ ላንደበቱ።
ስለዚህ ልቡ ላይ ሲያስብ ሚውለውን
ደግሞም ባንደበቱ የሚናገረውን
እመሰክራለሁ ያየሁትን ሁሉ
በኔ ተሸፍኖ እንዳይጠፋ ዉሉ
ሐይማኖትን ትቶ ቅዱሱን ያምላክ ቃል
ከንቱ ሐሳብ ሲያስብ ራሱን ሲያታልል
አንዱን በሌለበት በሐሰት እያማ
ሌላውን ባፍ ቃል ክፉኛ እያደማ
ሲወረወር ቀስቱን የሾሉ ቃላቱን
በመርዝ አንደበቱ የነደፈው ስንቱን
ውስጡ ክፋት እንጂ ወንጌል ካልተሞላ
ያምላክን ቃል ትቶ የሰውን ከበላ
እንዴት እሆናለሁ የእምነት ምልክቱ
መሸፈኛው እንጂ እንዳይታይ ፊቱ።
ይቀጥላል..
የአንድ አባት ልጆች ናቸው ሁለቱም ደግሞ አገልጋዮች ናቸው።የመንፈስ ክፍፍል ወይም ሥጋ የለም እነርሱ በእውነት በአንድ ሥጋ ውስጥ ያሉ ሁለት ሰዎች ናቸው-----እነርሱ አብረው ይሠራሉ፣ እነርሱ አብረው ይፆማሉ፣አንዳቸው አንዳቸውን ያበረታታሉ፣አንዳቸው አንዳቸውን ይደግፋሉ።በችግር ፣በስደትና በደስታ ጊዜ በቤተክርስቲያን መሠዊያ ፊት አብረው ይገኛሉ።አንዳቸውም ለአንዳቸው ሸክም አይሆኑም።እነርሱ በነፃነት የታመሙትንና የተቸገሩትን ይጠይቃሉ።እነርሱ ያለምንም ጭንቀት መባ ያቀርባሉ፣መሥዋዕታቸውንም ያለ ምንም ጥርጥር ይሠዋሉ፣የዕለቱን ሥራዎቻቸውንም ያለ ምንም ተግዳሮት ያከናውናሉ።ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ስራዎች ሲመለከትና ሲያደምጥ ሐሴት ስለሚያደርግ ለእነዚህ የትዳር አጋሮች ሰላሙን ይልክላቸዋል እነዚህ ሁለቱም ባሉበት ቦታ ላይ ክርስቶስም አለ።
ክርስቶስ ባለበት ቦታ ላይ ደግሞ ለክፉው ለዲያቢሎስ ምንም ዓይነት ቦታ አይኖርም።
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ፖፕ ዘእስክንድርያ ወፓትርያርክ ዘመንበረ-ቅዱስ ማርቆስ!
🎤 #ጾም
+++++++++++
ጾም በእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ ጥንታዊ ትእዛዝ ነው።
ሥጋቸውን ለመመገብ እንደምታስብ ሁሉ መልካም ሴት የሰዎችን ይልቁንም የቤተሰቦቿን ነፍስ ለመመገብ ትጥራለች።ለዘመናት ስንቅ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያገኙም ቤቷን ታመቻቻለች።ማርያም እና ማርታ ጌታ በቤታቸው እንዲያርፍ እና ቃሉንም እንዲያስተምር ተግተው እንደነበረ ወደቤታቸውም እንዲገባ እንደጋበዙት መልካም ሴቶችም ይህን ያደርጋሉ።#ወንጌል #በመልካም #ሴት #ቤት #ይሰበካል።በፅኑ መሻት እና የማያቋርጥ ጥረት ብንኖር በቸርነቱ
እግዚአብሔር ለእኛም ይህን ሊያድለን ይቻለዋል።
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
#ትንሿ #ቤተክርስቲያን
ይህ ቻናል የተከፈተው ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መስርተን ክርስቶስን የሚሰብክ፤ በክርስቶስ ቃል የሚመራ መዳረሻው መንግስተ ሰማይ የሚሆን ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንመሠርት ዘንድ ነው......
ይህ ማለት ግን ምንኩስናን በፍፁም የሚፃረር አይደለም....
የምንኩስናን ሕይዎት መኖር ቢያቅተን እንዴት ማድነቅ ያቅተናል❓(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ታላላቅ ቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታት የተገኙት በቅዱስ ጋብቻ ነው፤ መነኮሳትንም ማፍራት የምንችለው በዚሁ ነው።
"ጋብቻ እንደ ምንኩስና ነው፤የእግዚአብሔር መንግስት ምልክት ነው፤ምክንያቱም በኃጢአት አማካይነት ተቋርጦ የነበረው የሰው ልጆች አንድነት በድጋሚ ሊቀጥል ችሏልና።ስለዚህ ጋብቻ በራሱ ታላቅ ምስጢር ነው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ለሰው ልጆች የሆነ አንድነት ነው።ከመንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው ላይ ተነስተው አንዳቸው አንዳቸውን ያስተምራሉ ወይም ሁለቱም በአንድነት ልክ እንደ መነኮሳት የጋራ ሕይዎታቸውን በቅድስና ይሞላሉ።"(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ቤተክርስቲያን በቅዱስ ቁርባን ቁርባን መሥዋዕት አንድ የምትሆንበትና የምትበረታታበትን፣በበረከት ማኅተም የምትባረክበትን፣መላዕክት የሚያበስሩትንና እግዚአብሔር አብ የሚያጸድቀውን የዚህን ጋብቻ ደስታ እንዴት ነው ልናገረው የምችለው❓ሁለት አማኞች የሚያበጁት ጥንድ ምንኛ የተዋበ ነው❓እነዚህ ጥንዶች የሚጋሩት አንድ እምነትን፣ አንድ ቃልኪዳንን፣አንድ የሕይዎት መንገድንና አንድ የእግዚአብሔር አገልግሎትን ነው........( ጠርጡለስ)።
እናም የዚህ መንፈሳዊ ቻናል አላማ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በፅሁፍ፣በድምፅ እና በምስል እየለቀቅን በእግዚአብሔር ቸርነት ሰዎችን በመንፈሳዊ ሕይዎትና እውቀት አጎልብቶ መልካም ኦርቶዶካሳዊ ቤተሰብ እንዲመሰርት ማስቻል ነው እንዲሁም እንድወያይበት የሚፈልጉት ጥያቄ፣ምክር እና ሀሳብ ካለ በተዘጋጀው ግሩፕ አስተያየት አጋርቶ ሀሳብ መለዋወጥ ይቻላል።
የግል ጉዳዩ በተመለከተ ምክር የሚፈልግ ካለ ደግሞ የገጠመውን ችግር በነፃነት በውስጥ መስመር ይልክና ማንነቱ እንዳይታወቅ አድራሻውን አጥፍተን ቻናሉ ላይ በመልቀቅ እህት ወንድሞች መንፈሳዊ ምክራቸውን እንዲፅፉ በማድረግ ምክር እንዲያገኝ እናደርጋለን።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡
#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን፣ ገጽ. 507-508
@TnshuaBetechrstian