slehiwetwe | Unsorted

Telegram-канал slehiwetwe - ቅድስት ፌብሮኒያ

-

ይህ ቻናል ስለ ህይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፋልበት ነው እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል ለማንኛውም ሀሳብ ጥያቄ እና አስተያየት

Subscribe to a channel

ቅድስት ፌብሮኒያ

✝✝✝
6.አንተ ታካች፥ወደ ገብረ ጕንዳን ኺድ፥መንገዷንም ተመልክተኽ ጠቢብ ኹን።
7.አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት
8.መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች።
9.አንተ ታካች፥እስከ መቼ ትተኛለኽ፧ከእንቅልፍኽስ መቼ ትነሣለኽ፧
10.ጥቂት ትተኛለኽ፥ጥቂት ታንቀላፋለኽ፥ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅኽን ታጥፋለኽ
11.እንግዲህ ድኽነትኽ እንደ ወንበዴ፥ችጋርኽም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብኻል።
12.ምናምንቴ ሰው የበደለኛም ልጅ በጠማማ አፍ ይኼዳል
13.በዐይኑ ይጠቅሳል፥በእግሩ ይናገራል፥በጣቱ ያስተምራል
14.ጠማማነት በልቡ አለ፥ዅልጊዜም ክፋትን ያስባል ጠብንም ይዘራል።
15.ስለዚህ፥ጥፋቱ ድንገት ይደርስበታል ድንገት ይደቃል፥ፈውስም ከቶ የለውም።

ምሳሌ ፮÷፮-፲፭

@slehiwetwe ይቀላቀሉን።✝

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ወሬን ማብዛት ሀጥያት ስለመሆኑ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ብዙ ጊዜ የተነገረ ጉዳይ ነው። የሚከተሉት ጥቅሶችስለወሬኛነት በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ናቸው።"በቃል ብዛት ውስጥ ሀጥያት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።"ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው።"..."የሰነፍ ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል ።"[ምሳ 10÷19,17÷27],[መክ 5÷3]....
ወሬን ስለማብዛት ከበድ ያለ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ግን ከራሱ ከክብር ባለቤት ክርስቶስ ነው።በማቴ 12...ላይ እኔ እላችኋለሁ ፤ሰወች ስለሚናገሩ ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል ።"ከቃልህ የተነሳ ትፀድቃለህ፤ከቃልህ የተነሳም ትኮነናለህ።"ብሏል።
ይህም ማለት እንደዋዛ ብምንናገረው እያንዳንዱ ነገር እንጠየቅበታለን ማለት ነው። እንዴት ያስፈራል ?
....አባቶቻችን ይህንን ሀጥያት  በጥብቅ ተቃውመው የዝምታን በጎነት በተለያዩ መንገዶች አሳይተዋል ።በአንድ ወቅት ቅዱስ አርሰኒዮስ "ብዙ ተናገርሁ ተፀፀትኩም፤በዝምታ ግን ተፀፅቼ አላውቅም።"ብሏል።

ተግባራዊ ክርስትና በዲን ሄኖክ ሀይሌ
✝@slehiwetwe ይቀላቀሉን።✝

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ


የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤ ዘሌ 11:44 “እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና”

@slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

🌿🌿🌿ፀጋ ሀብትን ለሚሰጥ መሃል እጅሽ ሰላምታ ይገባል።የጥበብ መብራቶችም ለሚሆኑ ጣቶችሽ ሰላምታ ይገባል ።የቅዱሳን መመኪያ ቅድስት አርሴማ ሆይ!እንደ ሰማእታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁሉ ጌጥ ራሶችና አራዊትን እርግጥ ዘንድ የአብ ሥልጣንን (ፈቃድ )ለእኔ ላኪልኝ።🌿🌿🌿
መልክዓ ቅድስት አርሴማ

እንኳን አደረሳችሁ .....ለሀገራችን ሰላሙን ትላክልን ቅድስት አርሴማ በፆም በፀሎት ተወስነው ስለኛ ስለሀጥያተኞቹ የሚፀልዩትን የእናት የአባቶቻችን ፀሎት ተቀብላ የኛንም ትቀበለን በረድኤት በረከቷ ትጎብኘን።አሜን።
    @slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

`አንድ የጥንት አባት "በቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቁ ችግር የሚፈጠረው መንፋሳውያን ያልሆኑ ሰወች መንፈሳዊ ስራ ሲሰሩ ነው"ብለው ነበር። ያልመነኑ ሰወች ከመነኮሱ፤ክርስቲያን ያልሆኑ ሰወች ከቀሰሱ፤እግዚአብሔር የማያውቁት ሰወች ካስተማሩ፤ደመወዝ፣ቤትና መኪና የሚያጓጓቸው ሰወች ከዸዸሱ፤ፍትፍት ያልሰለቻቸው ሰወች ባህታውያን ከሆኑ ፤የዘር ዛር ያልለቀቃቸው ሰወች የሁሉ አባት ከተባሉ፤ከራሳቸው ጋር ያልታረቁ ሰወች ለተቃራኒነት እና አስታራቂነት ከተቀመጡ፤መንፈሳዊነት ምልክቱም፤ሽታውም ጠፍቷል ማለት ነው።ለዚህም ይሆናል ለመንፈሳዊ ችግሮች የታክቲክ እእና ቴክኒክ እንጂ የመንፈስ መፍትሔ ስንፈልግ የማንገኘው።!!

@slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

12.ስሕተትን ማን   ያስተውላታል፧ከተሰወረ ኀጢአት አንጻኝ።
13.የድፍረት ኀጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያኽን ጠብቅ የዚያን ጊዜ ፍጹም እኾናለኹ፥ከታላቁም ኀጢአት እነጻለኹ።
14.አቤቱ፥ረድኤቴ መድኀኒቴም፥የአፌ ቃልና የልቤ ዐሳብ በፊትኽ ያማረ ይኹን።
✝መዝሙር ምዕራፍ 19

@slehiwetwe ይቀላቀሉ ።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

እንኳን አደረሳችሁ ለበአታ ማርያም
ረድኤት በረከቷን ታሳድርብን ፤ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን🙏

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

Ethiopia_ታህሳስ_1_ነብዩ_ቅዱስ_ኤልያስ_ለምን_ይከበራል_

ለሌሎች ማጋራት አይረሳ
@slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

አንድ አባት ወጣኒ ደቀመዝሙሩን አለው''ሂድና ሙታንን ተሳደብ ''ወደ መቃብር ሄዶ ቀኑን ሙሉ ሙታንን ሲሳደብ ዋለ።
`በቀጣዩ ቀን ደቀመዝሙሩን አለው ''ሂድና ሙታንን አመስግን!'' ወደ መቃብር ሄዶ ምስጋናውን ሲያቀርብ ዋለ።
ማታ ሲመለስ መምህሩ
ጠየቀው''በሰደብካቸው ጊዜ ሙታንን ተሰማቸው?''
''የለም አልተሰማቸውም''አለና መለሰ
''ባመሰገንካቸው ጊዜስ?''አለው
''የለም አልተሰማቸውም ''ብሎ መለሰ
አረጋዊውም ''''ሂድ አንተም እንዲሁ ሁን!!'''ብሎ ነገረው።
ስለዚህ ከመመስገን ይልቅ መነቀፍ ይበልጥ ብፅዕና ነው...ሰወች ሲያመሰግኑን ለኛ መንፈሳዊነት አደገኛ እንደሆነና ሲነቅፉን ደግሞ ማመስገንን በአእምሯችን ልንተክል ይገባናል ....

አቡነ አትናቴዎስ እስክንድር እንደፃፉት

🍂
መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ🍂
@slehiwetwe ይ🀄️ላ🀄️ሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

እንኳን ለአእላፍ ሰማዕታት: ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ቀሌምንጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

#ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕት

ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ጴጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ጳጳሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ጴጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ጵጵስናው ላይ አልተቀመጠም::በኋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::
ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
@Slehiwetwe ይ🀄️ላ🀄️ሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"ከጥፋቱ መንገድ"

አንተ አውጣኝ ከጥፋቱ መንገድ (፪)
በሲኦል በሳት ሳልማጋድ(፪)
አንተ አውጣኝ ከጥፋቱ መንገድ
🥺🥺🥺
ዘማሪ ይትባረክ ተገኝ🌸💙

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

የስክንድስ ምሳሌ
[፤በከተማ ዳኛ ነበር እንግዶች ሰወችም በእኩለ ቀን ወደሱ መጡ፤ላሞችም በበረሀ ነበሩት ፤ሰራተኛውንም ላከ፤እንዲህም አላት፤እረኞች ወዳሉበት ሂጂ በዚህ ወተት ዕቃም ከላሞች ወተት እንዲሞሉልሽ ጥሪያቸው ።
ወደኛ ለመጡት እንግዶች እንዲመገቡ እንሰጣቸው ዘንድም አምጪልኝ አላት።ሰራተኛዋም እንደጌታዋ ትእዛዝ ወደ እረኞች ሄደች ፤ጌታዋ እንዳዘዛትም የወተት እቃዋን ሞላች ፤ሳትከድነውም በራሷ ላይ ተሸከመችው ፤ወደጌታዋ ቤትም ልትመጣ ትሄድ ነበር።በእግዚአብሔር ፈቃድም ታላቅ ወፍ (አሞራ )ከዛፍ ላይ ተቀምጦ ነበር።
ከዛፍ ላይም የሚያስፈራ ከይሲን(እባብን)አየ፤ያ አሞራም ያን ከይሲ በጥፍሩ ነጥቆ ይበላው ዘንድ ወደ አየር ወሰደው ፤ያ ከይሲም ከነበረበት የሕማምና የጭንቀት መከራ ብዛት የተነሳ አፉን ከፍቶ መርዙን ከአየር ላይ ጣለ ፤በሰራተኛዋ ራስ ላይ ባለው ወተት በውስጡ በያዘው እቃ ላይ ወደቀ።እሷም የሆነውን አላወቀችምወ ነበር ።ያንን ወተትም ወደ ጌታዋ ባመጣች ጊዜ ለእንግዶች ይሰጧቸው ዘንድ አዘዘ።እንግዶችም በጠጡ ጊዜ ከወተቱ ላይ ከወደቀው ከዚያ እባብ መርዝ የተነሳ ሁሉም ሞቱ።

ሃጥያትን እንደምናደርግ አናውቅም።ይህ ሀጥያት ከነዚህ መካከል ለማናቸው ይሆናል ?።በዳኛው ላይ ፤ወይም በሰራተኛዋ ላይ፤ወይስ በእረኞች ላይ፤ወይስ በአሞራው ላይ፤ወይስ በከይሲው ላይ ይሆናልን?

ይህች ሀጥያት ምናልባት በዳኛው ላይ እንደሆነች አድርገን ብንናገርም እኛ ይህ እውነቱ እንዳልሆነ እናያለን ፤እርሱ ወንድሞቹን ያሳርፋቸው ዘንድ ታላቅ ፍቅርን አደረገ እንጂ የሆነውን አላወቀም ።
ሀጥያት በእረኞች ላይ ናት እንዳንልም በእነርሱ ላይ ነውር የለም፤እነርሱየጌታቸውን ትእዛዝ ሰምተው አድርገዋልና።
ሀጥያት በወፉ ላይ ነው ብለን ብናስብም በደሉ ምንድን ነው እርሱ ምግቡንና መብሉን ፈልጓልና ።ሁሉም  ፍጡራን ምግባቸውን ይፈልጋሉና ።
የእነዚህ ሰወች ሞት ከእርሱ መርዝ የተነሳ ስለሆነ ሀጥያቱ ከይሲው ላይ ሊሆን ይገባል ብለን እንዳናስብም በደሉ ምንድን ነው?እርሱ ከነበረበት ፍርሀትና ፀእረ ሞት የተነሳ መርዙን ጣለ እንጂ በተንኮልና ክፉ በማሰብ አይደለም።የሚወድቅበትንም ቦታ አላወቀም ።ስለዚህ በእርሱ ላይ ሀጥያት የለም።ከዚህ ሁሉ በኋላ ሀጥያት በሰራተኛዋ ላይ ነው ብንልም እውነት አይደለም  እርስዋ መልእክቷን ያለ ተንኮል ጌታዋ እንዳዛዘት አድርጋ ፈፅማለችና።]

ይህ ሃጥያት ከነዚህ መካከል ለማን ይሆናል ?

ታላቁ ስክንድስ /skendes the wise/ ስለእናቱ አሟሟት እና ስለራሱ ለመግለጽ የተጠቀመው ምሳሌ።
✝@slehiwetwe ይቀላቀሉን✝

ለሌሎችም ማጋራት አይረሳ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

✝@slehiwetwe ይቀላቀሉን✝

6.ለውዴ ከፈትኹለት፥ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ ዐልፎ ነበር።ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች ፈለግኹት፥አላገኘኹትም ጠራኹት፥አልመለሰልኝም።
7.ከተማዪቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥አቈሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዐይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።
8.እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነዣዥት ሆይ፥አምላችዃለኹ ውዴን ያገኛችኹት እንደ ኾነ፥እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።
    
  መሓልይ ምዕራፍ 5

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#በነገስታት ፊት የሚቆሙ -ነገስታት የምለውስ ለምንድን ነው?-ኧረ ዝቅ ያለ ማዕረግ ባላቸው ሹሞችና ጌቶች ፊት ልመናቸውን የሚያቀርቡ ባሪያዎች ÷ይህንንም የሚያደርጉት ሌሎች ሰወች ስለጎዷቸው ወይም ለራሳቸው አንዳች ነገር እንዲደረግላቸው ስለፈለጉ ወይም በእነርሱ ላይ ያነጣጠረን ማንኛውም አይነት ቁጣ ሊያስወግዱ ቢፈልጉ ÷አይኖቻቸውን እና ትኩረታቸውን ሁሉ ወደ ጌቶቻቸው ያደርጋሉ።በዚህ መንገድ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ።በአንዳች ነገር ግዴለሽነት ቢያሳዩ ልመናቸው ተቀባይነት አያገኝም #ብቻ ሳይሆን ይባሱኑ ተገፍትረው እና ተመተው ይወጣሉ ።#እንግዲህ እነዚህ ባሪያዎች የሰወችን ቁጣ ላለመቀስቀስ ሲሉ ይህን የሚያህል መጠን የሚጠነቀቁ ከሆነ ደካሞች ፍጡራን የምንሆን እኛ የሁሉም ጌታ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር እጅግ በግዴለሽነት የምንቀርብ ከሆነ የሚያገኘን ቁጣ እንደምን የፀና ይሆን?#እኛ ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን የምናሳዝነውን ያህል አንድ አገልጋይ ጌታውን ወይም ተራው  ዜጋ ንጉሱን አያሳዝነውምና።

-ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው
በእንተ ድንግልና
@Slehiwetwe ይቀላቀላሉን✨

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ብሒለ_አበው
1."ፀጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ፀጋ አመስግን  ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን ፀጋ እንዳታጣ።"
                   /ማር ይስሀቅ/
2."አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኃልዮ ኃጥያት ያርቀዋል።"
               /አረጋዊ መንፈሳዊ/
3."ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለ ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለና። "
                /ቅዱስ አትናቲዮስ/
4."እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ እንደፃድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰወች አድነኝ።"
                  /አባ እንጦንስ/
✨@Slehiwetwe ይቀላቀላሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ስለ ዝምታ ካነሳን ዘንድ ሁልጊዜም ከህሊናችን የማይጠፉት ድንቅ አባት
አባ ዮስጦስ ✝✝✝
ነገ አመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸው ነው።
እንኳን አደረሰን ✝✝✝
በዝምታህ አለምን ያሸነፍክ አባ ዮስጦስ
እኛም በዝምታ አለምን እናሸንፋት ዘንድ እርዳን
በረከታቸው ይደርብን 🙏🙏✝✝✝

ስንት ሰአት ነው?

@slehiwetwe ይቀላቀሉን።🦋🦋

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

°አትለየኝም ወይ
ናፍቆት ባዛላቸው ደጅ የጠኑ ጣቶች የበሬ መቃኑ ሰርክ ቢቀረቀር
አትዘን ጌታዬ ከፍቼ ብትገባስ ምን አሳይሃለሁ ከበደሌ በቀር!
ጣትህ እስኪቆስል ታንኳኳለህ አንተ
ሀጥያት ለጠፈራት የመከነች ፍሬ
ተኝቼ እንዳይመስልህ ክፋት ያከረፋው አያስጠጋም ነውሬ
መቼ ትሄዳለህ !!
ከደሳሳው ቤቴ ተስፋ ማድረግ ትተህ
ካልጎደለ በረት ለአንዲት ግልገል ፍቅር ምን አንከራተተህ
አትፈልገኝ ልቅር ይደብቀኝ ቤቴ ሽፍንፍኑን ታኮ
በሚሰጡ እጆች ፊት ለመቀበል ማነስ ያሳፍራልኮ
መቼ ትሄዳለህ !!😔😔

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

አንድ መነኩሴ ብቻውን ተመስጦ ለማድረግ ወሰነና ከገዳሙ 'ርቆ ታንኳ ይዞ ወደ ሀይቁ መሃል ሄዶ አይኑን ጨፍኖ ማሰላሰል ጀመረ።

ከተወሰኑ ሰዓታት ካልተረጋጋ ጸጥታ በኋላ በድንገት ሌላ ጀልባ ሲመታው ተሰማው። ዓይኖቹ አሁንም እንደተዘጉ ቢሆንም ቁጣው ሲነሳ ይሰማዋል እና ዓይኖቹን ሲከፍት፤ ተመስጦውን ለመረበሽ የደፈረውን ጀልባው ላይ ለመጮህ ተዘጋጀ። ነገር ግን ዓይኖቹን በገለጠ ጊዜ አንዲት ያልታሰረች ባዶ ታንኳ  በሐይቁ መካከል እየተንሳፈፈች ነበር. .

በዚህን ጊዜ መነኩሴው እራስን ወደመገንዘብ ይደርሳል እና ቁጣ በእርሱ ውስጥ እንዳለ ይረዳል። እሱን ለመቀስቀስ በቀላሉ ውጫዊ ነገር ሊመታው ያስፈልጋል።


.  .  .ከዚያ ጊዜ በኋላ የሚያናድደው ወይም የሚያበሳጨው ሰው ሲያጋጥመው“ The other person is just an empty boat. Anger is inside me. በማለት ያልፈዋል።

`` ሌላው ሰው ባዶ ጀልባ ነው፤ ቁጣ ግን ውስጤ ነው: : ``


@slehiwetwe ይቀላቀሉን።
       

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#የታህሳሥ_ወር_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላት

- ታህሳሥ 6 ፦ ቅድስት አርሴማ (ቅዳሴ ቤቷ)
- ታህሳሥ 12 ፦ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
- ታህሳሥ 13 ፦ ቅዱስ ሩፋኤል
- ታህሳሥ 15 ፦ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘሀገረ አርማንያ (ዕረፍቱ)
- ታህሳሥ 19 ፦ በዓለ ቅዱስ ገብርኤል
- ታህሳሥ 22 ፦ ብስራተ ገብርኤል (ለእመቤታችን ክርስቶስን እንደምትወልድ ያበሰረበት)
- ታህሳሥ 24 ፦ አብነ ተክለ ሃይማኖት (ልደታቸው)
- ታህሳሥ 28 ፦ ቅዱስ አማኑኤል (በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ) /ገና/
- ታህሳሥ 29 ፦ ቅዱስ በዓለ ወልድ (ተዝካረ ልደቱ ለእግዚእነ) /ገና/

#ለሌሎች_ሼር_ማድረጎን_አይዘንጉ

   @slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

🌸 ሚስትህን በጎደኞችህ ፊት አክብሮትን ስጣት ከእርሷ ከወለድካቸው ልጆችህም በላይ አክብራት በአንተ ዘንድ ልጆችህን መውደድህ በእርሷ ምክንያት ይሁን።
🌸ከእርሷ የማይጠበቅ ሥራ ስትሰራ ብታገኛት በፍቅር በመሆን ምከራት ። ደግማም እንዳትፈፅመው አሳስባት።
🌸ባለጸጋ ለመሆን መሻትና በቅንጦት መኖርን መፈለግ ከአንተ ዘንድ የራቁ ይሁኑ።
🌸በንጽሕና በትህትና እንዲሁም በጥንቃቄ ስለ ጌታጌጦች አላስፈላጊነት አስገንዝባት ። ስለሚጠቅማትም ነገሮች ያለመሰልቸት አስተምራት።

@TnshuaBetechrstian

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

🍀🍀ድንግል ሆይ ሰውነቴ ሁሉ አንደበት የተሞላ ቢሆን  ፤በአጥንቶቼም ቁጥር እውቀት ቢሰጠኝ ፤የራሴ ፀጉርም ሁሉ መናገር ቢሰጠው፤በዚህም ውዳሴሽን ለመፈፀም አልችም።🍀🍀
  ✝✝
መፅሐፈ አርጋኖን

@slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ከመንፈሳዊ አባቱ ጋር ሚኖር አንድ ወጣኒ መነኩሴ ነበር፤ይህ መነኩሴ ሳይሰግድና የአባቱን ቡራኬ ሳይቀበል አይተኛም ነበር።አንድ ምሽት ከሰገደ በኋላ "አባቴ ይባርኩኝ "ሲል አባ ከሱ በፊት እንቅልፍ ጥሏቸው ነበር።ይነቁ ይሆናል በሚል ተስፋ እሳቸው ሳይባርኩት ላለመተኛት ከአጠገባቸው ሊቆይ ወሰነ ።ሆኖም አባ ሙሉ ሌሊቱን ተኙ።ይህ ወጣኒ መነኩሴ በዛው እንቅልፍ አሸለበው።አባ ሲባንኑ ሰባት መላእክት ሰባት በዚህ ወጣኒ መነኩሴ ራስ ላይ አክሊላትን ሲያደርጉ ተመለከቱ።እኚህ አባት በጠዋት "ማታ ምን ተፈጥሮ ነበር?" ብለው ጠየቁት። "ይቅር በሉኝ አባቴ ማታ የእርስዎን ቡራኬ ሳልቀበል እንድሄድ የሚገፋፋ ክፉ ሀሳብ ሰባት ጊዜ መጦብኝ ነበር ፤ይህንን ሀሳብ ተቃውሜው ቆየሁ" አላቸው።እኚህ አባት ሰባቱ አክሊላት ክፉ ሃሳቦቹን በመቃወሙ ያገኛቸው መሆናቸውን አወቁ።ይህንን ታሪክ ለሌሎች መነኮሳት ነገሯቸው።በትእቢት እንዳይወድቅ ሲሉ ግን ለዚህ ወጣት ደቀመዝሙራቸው አልነገሩትም።

ጠላታችን በኛ ላይ የሚተክለውን ክፉ ሀሳብ መቃወም ዋጋ የሚያስገኝ ነው።

✝"ንፅህት ድንግል ማርያም ሆይ የከለላነትሽን ጥላ በእኔ ላይ ዘርጊ፤የክፉ ሀሳቦችንም ማእበል ከእኔ አርቂ።"✝
@slehiwetwe ይ🀄️ላ🀄️ሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

21.ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ዅሉ ቀርቦ፦እስከ መቼ ድረስ በኹለት ዐሳብ ታነክሳላችኹ፧እግዚአብሔር አምላክ ቢኾን ርሱን ተከተሉ በዓል ግን አምላክ ቢኾን ርሱን ተከተሉ አለ።ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
....

26.ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፥ከጧትም እስከ ቀትር ድረስ፦በዓል ሆይ፥ስማን እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ።ድምፅም አልነበረም፥የሚመልስም አልነበረም በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር።
27.በቀትርም ጊዜ ኤልያስ።አምላክ ነውና፥በታላቅ ቃል ጩኹ ምናልባት ዐሳብ ይዞታል፥ወይም ፈቀቅ ብሏል፥ወይም ወደ መንገድ ኼዷል፥ወይም ተኝቶ እንደ ኾነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል እያለ አላገጠባቸው።
.....
36.መሥዋዕተ ሠርክ በሚቀርብበት ጊዜ ነቢዩ ኤልያስ ቀርቦ፦አቤቱ፥የአብርሃምና የይሥሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ኾንኽ፥እኔም ባሪያኽ እንደ ኾንኹ፥ይህንም ዅሉ በቃልኽ እንዳደረግኹ ዛሬ ይገለጥ።

37.አንተ፥አቤቱ፥አምላክ እንደ ኾንኽ፥ልባቸውንም ደግሞ እንደ መለስኽ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፥አቤቱ፥ስማኝ አለ።

38.የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፥የሚቃጠለውን መሥዋዕቱንም ዕንጨቱንም ድንጋዮቹንም ዐፈሩንም በላች፥በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውሃ ላሰች።

39.ሕዝቡም ዅሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው።እግዚአብሔር ርሱ አምላክ ነው አሉ።

መፅሐፈ ነገስት ቀዳማዊ

✝✝እንኳን ለነብዩ ኤልያስ አመታዊ በዐል በሰላም አደረሳችሁ ከነብዩ ረድኤትና በረከት ይክፈለን አሜን።✝✝

💒@slehiwetwe ይ🀄️ላ🀄️ሉ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ዼጥሮስን ለንስሓ የቀሰቀሰ አምላክ
እኛንም ያንቃን🙏
@Slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

25.ስለዚህ፥እላችዃለኹ፥ስለ ነፍሳችኹ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ወይም ስለ ሰውነታችኹ በምትለብሱት አትጨነቁ ነፍስ ከመብል፣ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን፧
26.ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ አይዘሩም አያጭዱምም በጐተራም አይከቱም፥የሰማዩ አባታችኹም ይመግባቸዋል እናንተ ከነርሱ እጅግ አትበልጡምን፧
27.ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው፧
28.ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችኹ፧የሜዳ አበባዎች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችኹ ተመልከቱ
29.አይደክሙም አይፈትሉምም ነገር ግን፥እላችዃለኹ፥ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ዅሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።
30.እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከኾነ፥እናንተ እምነት የጎደላችኹ፥እናንተንማ ይልቁን እንዴት፧
31.እንግዲህ፦ምን እንበላለን፧ምንስ እንጠጣለን፧ምንስ እንለብሳለን፧ብላችኹ አትጨነቁ
32.ይህንስ ዅሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ ይህ ዅሉ እንዲያስፈልጋችኹ የሰማዩ አባታችኹ ያውቃልና።
33.#ነገር ግን፥አስቀድማችኹ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ይህም ዅሉ ይጨመርላችዃል።
34.ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፥ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።
  የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 6
እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ እኛ ከምናስበው በላይ የሚያስብና ከለመነው በላይ የሚያደርግ አምላክ ነውና፤ሁልጊዜም ማመስገንን ይልቁንም መንግስቱንና ፅድቁን አብዝተን ልንፈልግ ይገባል።

     
✝🕊🕊🕊🙏🥰
የምስጋና ቀን ይሁንልን

       @slehiwetwe ይቀላቀሉን

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ሰካራሙ መነኩሴ

በአቶስ ተራራ ላይ በካሬስ የሚኖር አንድ መነኩሴ ነበር።  በየቀኑ ይጠጣ ነበር፣ ከዚያም በመነኮሳትና በመንፈሳዊ ተጓዦች(pilgrims) ላይ ችግር ይፈጥራል....ይኽንን እያደረገ ሰነባበተ...በገዳሙ የሚኖሩ መነኮሳት በሙሉ በሰካራምነቱ ስለሚያውቁት "ሰካራሙ መነኩሴ" በሚል ነበር የሚያውቁት...ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይኽ መነኩሴ አረፈ።

👉በሞተም ጊዜ ከመነኮሳት መካከል የተወሰኑት ወደ አባ ፓይሲየስ ዘአቶናዊው ፈጥነው ሄዱና በደስታ ሆነው የገዳሙ ችግር አሁን ማብቃቱን ነገሩት(ሰካራሙ በመሞቱ)።

አባ ፓይሲየስ ስለ መነኩሴው ሞት አስቀድሞ ያውቅ ነበር፤ የመላእክት ጭፍሮችም የመነኩሴውን ነፍስ ለማግኘት ሲመጡ አይቶ ነበር። እነዚያም መነኮሳትና መንፈሳዊያን ተጓዦቹ ግራ በመጋባት በመሆንና አባ ፓይሲየስ ለመልካሙ ዜናቸው በሰጠው ምላሽ ሲናደዱ፣ ቅዱስ ፓሲዮስ የሚከተለውን ነገራቸው፡-

"ይህ መነኩሴ በታናሿ እስያ ነው ከእልቂቱ
(Holocaust) በፊት ብዙም ሳይቆይ የተወለደው።  ወላጆቹ ልጃቸውን ብቻውን መተው ስላልፈለጉ አዝመራውን ለመሰብሰብ(harvest) ሲሔዱ ይወስዱት ነበር፤ በዚኽም ልጃቸው እንዳያለቅስ እና እንዳይያዙ ወተቱ ላይ ጠንካራ የአልኮል መጠጥ ጨምረው እንቅልፍ እንዲተኛ በተደጋጋሚ ያደርጉት ነበር።  በዚህም ምክንያት ይኽ መነኩሴ የአልኮል ሱሰኛ ሆነ...ሐኪሞችም ቤተሰብ እንዳይመሰርት  ስለመከሩት፣ ወደ አቶስ ተራራ(Mount Athos) በመምጣት መነኩሴ ሆነ።  ሰካራም መሆኑንም ለአንድ ሽማግሌ ካህን ተናዘዘ።  ሽማግሌው ካህንም በየቀኑ እንዲሰግድ አዘዘው እና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የአምላክ እናት ድንግል ማርያም(Theotokos) እንዲጸልይ እናም ቀስ በቀስ መጠጥ እንዲቀንስ እንድትረዳው እንዲጠይቃት እንዲለምናትም ነገሩት...ይኽንንም በብዙ ጥረት ማድረጉን ቀጠለ። 

ከአንድ አመት ተከታታይ ተጋድሎ እና ንስሃ በኋላ በየቀኑ የሚጠጣውን 20 መጠጥ ወደ 19 ዝቅ ማድረግ ቻለ። ትግሉ ቀጠለ እና ከዛ ሁሉ መንፈሳዊ ጦርነት ዓመታት በኋላ መነኩሴው በቀን የሚጠጣው ከ2-3 ጊዜ ብቻ ነበር። ለዓመታት ሰዎች እንደ ሰካራም መነኩሴ እና ችግር ፈጣሪ ያውቁታል <ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ አንድ ተዋጊ ስሜቱን ለማሸነፍ በታላቅ ቅንዓት ሲታገል ተመለከተ።> በዚኽም በከበሩ መላእክት ነፍሱ ታጅባ ሔደች" አላቸው።

ይኽንን የሰሙት መነኮሳቱ እና መንፈሳዊያን ተጓዦቹም ምን ያኽል በሰው ድካም ሲፈርዱ እንደነበር አውቀው ተጸጸቱ ለዚህም ነው ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።" ያለው
@slehiwetwe ይቀላቀሉን...

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

አቡነ ሐብተማርያም

አቡነ ሐብተማርያም የዓለም ብርሃን ናቸው
ይኸው ለዘለዓለም ያበራል ስራቸው/2/

ተዓምረኛው የወንጌል አባት
ሐብተማርያም ናልን በምሕረት
ስንጠራህ ስንማፀንህ
ይታደገን ይርዳን ፀሎትህ


   
የተገባ አለህ መሐላ
ስምህን ጠርቶ ጥቂት ላበላ
በረከትን ብዙ ያተርፋል
በሰማያት ክብሩ ይጻፋል

   
ተሸክመህ የጌታን ስም
ስትሰብክ ታየ በአለም
ቅድስናህ ታየ ሲያበራ
የዘራኸው የጽድቅ አዝመራ

   
አልመከነም ጸሎቴ አባቴ
አላፈርኩም ሰምሯል መሻቴ
ላነሳሳህ እያልኩ ሐብትዬ
ስላየሁኝ ታብሶ እንባዬ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

መርቆርዮስ
==//==//

መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ ፪
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ
አዝ ========
ባስልዮስ ጎርጎርዮስ ሰምሯል ልመናችሁ
ስህሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናተን የረዳ መቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ
አዝ========
ኦላኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆሬዎስ ሀያል
ገፀ ከለባቱ ባህሪ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ
አዝ=======
ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ
አዝ=======
ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዮስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋር
አዝ=======
አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቀሬ አብ ካለ ያፕሎ ጳድር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወይኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ
አዝ=======

ዘማሪ ዲ/ን ታድዮስ ግርማ

ኦ! በኅሊናህ ቂም በቀል የሌለብህ!
መዓዛህ እንደ ጣፋጭ ሽቱ የሆነ!
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ (ከሃዲዎች) እንደ ደመና የበተኑህ!
የተጋድሎ ምስክርነትን የፈጸምህ!
ኦ! መርቆሬዎስ ዘሮሜ! (አርኬ)

#እንደልማድህ ፈጥነህ እርዳን!

" ✞እንኩዋንለ ታላቁት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

"' ኦ ሱራፊ! ዘበሰይፈ እሳት ኅድገነ ንባእ ወንርአያ ለማኅደረ ሕይወት . . . "'
(#ADAM  #HEWAN)

[የእሳት ሰይፍን የያዝክ (መልአኩ) ሱራፊ ሆይ! የሕይወት ማደሪያ የሆነች (ገነትን) ገብተን እናያት ዘንድ አትከልክለን:: ተደብቀን የምንቀር አይደለንምና:: ይልቁኑ ሽቱዋ ይድረሰን (እናሽትት) : መዓዛዋም በልባችን ውስጥ ይደር እንጂ::]
(ቅዳሴ አትናቴዎስ)

" መልካም ያልሠራ : ንስሃም ያልገባ ሰው ወደዚህች የሕይወት ማደሪያ ውስጥ አይገባምና ለበጐነት እንፋጠን:: "

" ቸሩ አምላክ ደግሞ እድሜ ለንስሐ አይንሳን:: "
     Dn Yordanos Abebe
እንኳን ለ24ቱ ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል) አደረሳችሁ
✨@Slehiwetwe ይቀላቀላሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

እንደምን ሰነበታችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

Читать полностью…
Subscribe to a channel