ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሕያው ቃልህን እንደ ጥዑም ዜማ በዓለም ጆሮ ላፈሰሰ ለቅዱስ ጳውሎስ ጸጋህን እንዳፈሰስህለት ምርጢራተ ሃይማኖትን እንድገነዘብ ልቦናዬን አብራው፤ከአንተ ዘንድ በሆነው ጥበብም አክብረኝ። የአንተን ነገር (ዜና) በአሕዛብ መካከል ለመሸከም የተመረጠ ዕቃ እንደሆነው የተወደደ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ በቅዱስ መንፈስህ እኔንም ቅረፀኝ።
በክቡር ዳዊት ጥልቅ ልቦና ውስጥ የፍቅርህን አሳት የለኮስህ፣በቅዱስ ስምህ እንዲያንፀባርቅ እንዳደረግኸው፤አቤቱ ሰው ወዳጅ ሆይ እለምንሀለሁ! ኅሊናዬንና መላ ሕዋሳቴን ሁሉ ከአንተ ዘንድ በሆነው በፈቃድህ እሳት አቀጣጥል።አፅናኝ የእውነት መንፈስህ የሆነው እርሱ በውስጤ ይኖር ዘንድ ስለ አንተ ሁልጊዜ እንዳስብና በትጋት እንድፀልይ ልቤን በመለኮትህ ኃይል እሳት እየጋለ ከፍ ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ላክልኝ።
#ራዕየ #ኒፎን
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
ሴቶች አግቡ ባለ ሀብት እያላችሁ አታማርጡ....
ሽንት ቤት የሚያጸዳው ጳጳስ.....
በ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
-ገሃድ-
ገሃድ፦ ሁለት ምሥጢር ተሸካሚ ፍችዎች ያሉት ቃል ነው። አንዱ ከበዓሉ ተቀዳሚዋ ቀን (ዋዜማዋን ዕለት) የሚያመለክት ሲሆን በዚህ ጊዜ ገሃድ፦ ለውጥ የሚል ፍች ይይዛል። ይህም በዓለ-ጥምቀት ዓመት ዓመት በተለያዩ ዕለታት ስለሚያርፍ ጻመ-ድኅነት ተብለው በሚጠሩ ዕለታትም ማረፉ አልቀረም በዚህም ጊዜ ጾም እንዳይጾም ዋዜማው በገሃድ/በለውጥ ጾምነት ታስቦ እንዲውል ተደርጓል። ኦርቶዶክዊ በዓላት የተሸከሙት የየራሳቸው ምሥጢር አላቸው ፤ መሰል በዓላት በመጭዋ ዓለም የሚኖረንን ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያዘክሩ ስለሆነ በተቻለ ያንን ሕይወት ይገልጣሉ ተብለው በሚታሰቡ ኩነታት ታስበው ይውላሉ ፤ ጾም ፣ ስግደት ... መሰል መንፈሳዊ ተግባራት ድካም አለባቸው ፤ በዓላቱ ደግሞ ዘለዓለማዊውን ሕይወት የምንዘክርባቸው ናቸው ካልን በድካም ካሰብናቸው ነጻ የምታወጣዋ መጭዋ ዓለምም ድካም አለባት እንዳያሰኝበን ፤ በሌላ ዘለዓለማዊውን ሕይወት በሚያዘክሩ ኩነታት አስበናቸው እንውላለን። በዚሁ ምክንያት በእነዚህ ዕለታት ጾም እንዳይጾምባቸው ተደንግጓል። አንድም፦ በዓላቶቹ የሰው ልጅ ደስታ ከእግዚአብሔር የተቀዳባቸው ዕለታት መዘከሪያዎች (ዝክሩ ላይ የምንቀር ብቻ ሳይሆን የኩነቱ ተካፋዮቹ መሆናችን እንዳለ ሆኖ) ስለሆኑ በመንፈሳዊ ደስታ ይከበራሉ።
በሁለተኛ ደረጃ (በቅድም ተከተል መሠረት) ገሃድ የሚለው ቃል ጎላ ያሉ በዓሉን ገላጭ የሆኑ ፍችዎችን ይሰጠናል ፤ ገሃድ እንዲህ የሚሉ ፍችዎችን ይሰጠናል፦መገለጥ ፣ መታየት ፣ ግልጥ ፣ ገሃድ መሆን/ግልጥ መሆን ፣ መታወቅ ፣ መረዳት... እኒህ ፍችዎች ቀጥታ የወልደ-አብን በሥጋ መገለጥና እሱን ተከትሎ ግልጥ የሆነው የምሥጢረ-ምሥጢራት የምሥጢረ-ሥላሴን ነገር የሚገልጥ ሆኖ እናገኘዋለን! [ይህን መገለጥ እንመለስበታለን]
ለበዓሉ የሚመጥን [ከእኛ የሚጠበቀውን] ሰብእናን ገንዘብ አድርገን በዓሉን በመንፈሳዊ ሐሴት ለማክበር እንበቃ ዘንድ ይህን ድምጽ እንስማ <<በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት [መንግሥተ-ሰማይ በልጅነት ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ፥ አንድም በመንግስተ-ሰማይ ክርስቶስ ልጅነት ልትሰጥ] ቀርባለችና ንስሐ ግቡ>>
[ማቴ ፫፥፩]
◉◉◉ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን። ◉◉◉
.....۞ የጊዜያት ሁሉ ጊዜ ۞.....
❀ በጠዋቱ
ከቤተ መቅደስ የምታውድ....... የማለዳ መዓዛ
❀ በቀትሩ
ከሃሩር ድካም ማረፊያ.......... መጠለያ ታዛ
❀ በጨለማው
ከድካመ ሃኬት የምታነቃ........ የብርሃን እናት ፋኖስ
❀ በድቅድቁ
ለትግሃ ሌሊት ጸሎት ......... ድካም ድል መንሻ ምርኩዝ
❀ የየዕለቱ
ለስደተኛው ልቤ ቀለብ .......... የነፍስ ጥሪት ጓዜ
❀ የዕድሜ ልክ
የጾም የጸሎት ትሩፋቴ ........ የሥግደት የተጋድሎ ወዜ
❀ የነገዋ
የመንግስተ ሰማይ ዋጋዬ ........ የተስፋይቱ ርስት ደምወዜ
❀ ፍጻሜዬ
የጽድቅ መደምደሚያ ልኬት ....... የጊዜያት ሁሉ ጊዜ
.........................................ድንግል!
ወልድ፥ አምላክነቱን እንደ መቀማት ሳይቆጥረው ልጆቹን (ሰውን) ለማዳን - ስለ ፍቅር - ራሱን ባዶ አደረገ እንላለን (ፊልጵ2:6)። ጋብቻም እንዲህ ነው። ወላጅ ወላጅነቱን እንደ መቀማት ሳይቆጥረው ልጆቹን [እና ራሱን የትዳር አጋሩንም] ለማዳን - ስለ ፍቅር - ራሱን ባዶ የሚያደርግበት ምሥጢር ነው። ራሱን ባዶ በማድረጉ ብዙ መከራ ቢቀበልም ልጆቹን [እና ራሱን የትዳር አጋሩንም] ለማሳደግ መከራውን በደስታ በትዕግሥት የሚቀበልበት ምሥጢር ነው።
-------
" ወርቅ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግርም ተኛ፤
አይሁድ ጨርቁን አይተው ፣ አልፈው እና ተራምደው ሔዱ፤
ሰብአ ሰገል ግን፣ ጨርቁን ገልጠው ወርቁን አጌጡበት"
-ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ-
[ ሕይወተ ክርስትና፥ በዐውደ ኮረና ፤ በመጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዶ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ ፤ ገጽ ፻፳፯/127፤ ፳፻፲፬/2014 ዓ.ም.]
❝በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምህ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም #ጸሎት_ራሱ_የእውነተኛ_ንስሓ_መግቢያ_በር_ነውና።❞
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
#ነገረ_ሥጋዌሁ ፥ #ለወልደ_እግዚአብሔር!!
✍️በሊቃውንተ-ቤተክርስቲያን
[[ክፍል ኹለት]]
🔖ከድንግል መሬት አዳምን ያስገኘ እርሱ ኹለተኛ አዳም ሆኖ ያለ-ወንድ ዘር ከድንግል ተወለደ።
🔖የቀድሞው አዳም ለሔዋን የአባትነትንና የእናትነትን ድርሻ ተወጣ፤ ድንግል ማርያም ደግሞ #ለጌታ የእናትነትንና የአባትነትን ድርሻ ተወጣች።
🔖ዮሴፍ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሷ እንደተከናወነ በተረዳ ጊዜ ከእርሷ ጋር በአንድነት መኖር አንዳች ፍርድን እንዳያመጣበት ሰግቶ ነበር።
🔖[ዮሴፍ] አምላክ ለሆነው ልጇ አባት ተብሎ ለመጠራት ለእኔ ድፍረት እንዳይሆንብኝ። [ብሎ አስቦም ነበር]
✞✞✞~★✤✤✤★~✞✞✞
➦ከድንግል መሬት አዳምን ያስገኘ እርሱ ሁለተኛ አዳም ሆኖ ያለ-ወንድ ዘር ከድንግል ተወለደ። የቀድሞው አዳም ተመልሶ ወደ-እናቱ ማኅፀን [ወደ-ምድር] ገባ። በእናቱ ማኅጸን ተቀብሮ የነበረውን የቀድሞውን አዳም ከተቀበረበት ከእናቱ ማኅፀን መልሶ ሊያስነሣው እርሱ በሞት ወደ-መቃብር ወረደ።
➦ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር መጽነሷን ለዮሴፍ ለማስረዳት አሰበች። ነገር ግን በእርሷ የተፈጸመው ከመረዳት በላይ ስለሆነ እርሷን እንደ-ማይቀበላት ተረዳች። ምንም እንኳን የድንግል ሆዷ ቢገፋም በእርሷ ገጽታ ላይ የሚነበበውን ፍጹም የሆነ እርጋታና ሰላም ዮሴፍ ባየ ጊዜ ⁽⁽ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። ማቴ ፩፥፲፱⁾⁾ ነገር ግን ከሌላ ጸንሳ ይሆናል የሚል ሐሳብም በሕሊናው ስለገባ እርሷን እንደ-እጮኛው አድርጎ ሊቀበላት አመነታ። እንደ-ጻድቅነቱ ወደ-እርሱ ሊወስዳት አልፈቀደም፤ እርስዋንም ለሌሎች አጋልጦ ሊሰጣት አልወደደም። በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ ሳለ መልአኩ በሕልም ተገልጦ ⁽⁽የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ!⁾⁾ ብሎ ጠራው። ዮሴፍ ከዳዊት ወገን እንደሆነ ለማስታወስ ሲል መልአኩ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ብሎ መጥራቱ የተገባ ነበር። ምክንያቱም ለአያቶቹ ራስ ለሆነው ዳዊት እግዚአብሔር ከወገቡ መሢሕን እንደሚያስነሣለት ቃል ኪዳን ገብቶለት ነበርና። ስለዚህም መልአኩ ⁽⁽ከእርሷ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ለመውሰድ አትፍራ ማቴ ፩፥፳⁾⁾ አለው። ከእርሷ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑን ተጠራጥረህ ከሆነ ኢሳይያስ ስለ-እርሷ የተናገረውን ስማ እርሱ፦ ⁽⁽እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ኢሳ ፯፥፲፬⁾⁾ ብሎ አስቀድሞ ተናግሯል። ዳንኤል ደግሞ ⁽⁽እጅ ሳይነካው የተፈነቀለው ድንጋይ ዳን ፪፥፴፬⁾⁾ ብሎ በምሳሌ መስሎ ተናግሯል። [[ይህን የዳንኤልን ራእይ ለወልደ-እግዚአብሔር ሰጥቶ በማግሰኞ ውዳሴ-ማርያሙም ላይ ገልጾቷል]] የዚህ ቃል ትርጒም፦ ⁽⁽ከእርሱ የተቆረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቆፈራችሁበት ጉድጓድ ተመልከቱ ኢሳ ፶፩፥፩⁾⁾ ከሚለው ጋር አንድ አይደለም። ይህ ለባልና ለሚስት ተሰጥቶ የሚተረጎም ነውና። በዳንኤል የተነገረው ግን ⁽⁽እጅ ሳይነካው የተፈነቀለ ድንጋይ⁾⁾ ድንግል ማርያም ያለ-ወንድ ዘር ጌታን መጽነሷን የሚያረጋግጥ ነው። የቀድሞው አዳም ለሔዋን የአባትነትንና የእናትነትን ድርሻ ተወጣ፤ #ድንግል_ማርያም ደግሞ #ለጌታ የእናትነትንና የአባትነትን ድርሻ ተወጣች። [ንጽጽሩን ልብ ብላችሁ አስተውሉልኝማ]
➦አንድም ወንጌላዊው፦ ⁽⁽እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ⁾⁾ ሲል የዮሴፍ ጽድቅ ከኦሪቱ ሕግ ጋር ተቃራኒ መሆኑን ለማሳየት ነው። ሕጉ በስውር እንዲተዋት ወደ-ውጪ አውጥቶ በድንጋይ እንዲወግሯት ሊተዋት እንዲገባ የሚያዝዝ ነው። ቢሆንም ዮሴፍ የድንግል መጽነስ ያልተለመደ ፣ ተፈጥሮአዊ ከሆነውም ከሴቶች ሥርዐት የተለየ ፣ ካገቡትም ሴቶች የማይመሳሰል እንደ-ሆነ አስተዋለ ፤ ወዲያውም ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆነ ተረዳ። እርሱም አንድም ጊዜ በእርሷ ላይ ነውር አይቶባት አያውቅም። በእርግጥ እርሷ እንዲህ እንዳልሆነች ብዙ ብዙ ምስክሮች አሉና ዮሴፍ ድንግል ማርያምን በምንዝር ይጠረጥራት ዘንድ አንዳች ምክንያት አልነበረውም። የካህኑ ዘካርያስ ድዳ መሆን ፣ የኤልሳቤጥ በእርጅና መጽነስ ፣ የመልአኩ የምሥራች ቃል ፣ በማኅፀን ሳለ የዮሐንስ በደስታ መዝለል ፣ የካህኑ ዘካርያስ የትንቢት ቃል ሁሉ ስለድንግል ማርያም በድንግልና መጽነስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይመሰክራሉ።
➦ዮሴፍ የድንግል ማርያምን ጽንሰት በመንፈስ ቅዱስ ግብር እንዳልሆነ ቢያምን ኖሮ እንደ-ሕጉ ያስጠይቀው ነበር። ነገር ግን እርሱ ይህ ድንቅ የሆነ የአምላክ ሥራ እንደሆነ ተረዳ። ቢሆንም በሰው ዘንድ እንግዳ ነገር ስለሆነም እንዲህ ዓይነት ነገር ሲገጥመው የአንድ ጻድቅ ተግባር ሊሆን የሚገባው በስውር መተው ነው ብሎ አሰበ። ይህ እንደ-እርሱ መረዳት ነው።
➦ዮሴፍ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሷ እንደተከናወነ በተረዳ ጊዜ ከእርሷ ጋር በአንድነት መኖር አንዳች ፍርድን እንዳያመጣበት ሰግቶም ነበር። እርሱ በሕሊናው ⁽⁽አምላክ ለሆነው ልጇ አባት ተብሎ መጠራት ለእኔ ድፍረት እንዳይሆንብኝ⁾⁾ ከዚህ ሁሉ እርስዋን በስውር መተው ይገባል ብሎም አስቦ ነበር። ለእርሱ የድንግልን ልጅ ስም የሚያጠፋ መስሎ ስለታየው ከእርሷ ጋር በአንድ ቤት መኖርን ፈራ። ስለዚህም መልአኩ ⁽⁽እጫኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ⁾⁾ ብሎ ተናገረው።
[[ድኅረ-ልደተ-ክርስቶስ በ306 ዓ.ም የኤዴሳ ክፍል በሆነችው ንጽቢን የበቀለው ሊቅ አፈ-በረከት #ቅዱስ_ኤፍሬም ፥ በ፩፻፲--፩፻፳ ባሉት ዓመታት መካከል እንደተወለደ የሚታመነው ሊቁ ታቲያን አራቱን ወንጌላውያን አሰባጥሮ ያዘጋጀው ሥራውን በተረጎመበት ድርሳኑ #ዴያቴሳሮን.. ]]
✞✞✞~★✤✤✤★~✞✞✞
✍️ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ። [ገላ ፬፥፬]
◉◉◉ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን። ◉◉◉
በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥናት በማድረግ የታወቀው የካይሮ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩ ጀርመናዊው ኦቶአ ሜናድረስ የአቡነ ሺኖዳን መሾም ሲሰማ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል ደብዳቤ ላከላቸው። ሺኖዳ ግን የመለሱለት የሚከተለውን ነበር
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ካንተ ጋር ይሁን። እንኳን ደስ ያለዎት ብለህ በቅንነት ስለላክህልኝ መልእክት አመሰግንሃለሁ። ያንተን ወዳጅነት እና ፍቅር መቼም አልዘነጋውም። እውነቱን ለመናገር ግን ለእኔ መላክ ያለበት የኀዘን ደብዳቤ እንጂ የደስታ ደብዳቤ አይደለም። አንድ መነኩሴ ጸጥታ የተሞላበትን የጸሎት በረሃ ለቅቆ ጫጫታ እና ሁካታ በተሞላበት ከተማ እንዲኖር ሲደረግ እንዴት እንኳን ደስ ያለህ ይባላል? ማርያምን ከክርስቶስ እግር ሥር ተነሥታ ማርታን ልታግዝ ወደ ጓዳ ስትገባ ማነው እንኳን ደስ ያለሽ የሚላት? ለእኔ ይህ ደስታ ሳይሆን ሀፍረት ነው። እኔ ኤጲስ ቆጶስ ሆኜ የተሾምኩበትን ቀን በደስታ ሳይሆን በኀዘን እና በለቅሶ ነው የማስታውሰው። ብሕትውና እና የተጋድሎ ጸሎት ከምንም በላይ የሚበልጥ ነገር ነው። ብሕትውና እና ምናኔ ከኤጲስ ቆጶስነት ቀርቶ ከፓትርያርክነት ጋር እንኳን የሚወዳደር አይደለም። «ወዳጄ ሆይ እውነተኛው ቅድስና ሲመት ሳይሆን ልብን ቤተ መቅደስ አድርጎ ለክርስቶስ መቀደስ ነው። ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም። ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልህ በምወድዳት ዋሻዬ፣ በባሕር አል ፋሬግ፣ በዋዲ ኤል ናትሩን ውስጥ ሆኜ ነው። እዚህም እስከ ጥምቀት ድረስ ለመቆየት አስባለሁ። ከዚያም ወደ ካይሮ እመለሳለሁ።
አቡነ ሺኖዳ እያለቀሱ ያቺን የዋዲ ኤል ናትሩን ዋሻ ትተው ካይሮ ቢመጡም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወደ ዋሻቸው መሄድ ያዘወትሩ እንደ ነበር ታሪካቸውን የጻፈላቸው የቅርብ ወዳጃቸው እና በእምነቱ ፕሮቴስታንት የነበረው ኦቶአ ሜናድረስ ይናገራል።
ምን ጥቂት ነገር አለህ?
ጌታችን እርሱን ተከትለው የወጡትን የአምስት ገበያ ህዝብ(አምስት ሺ አባውራ) አመሻሹ ላይ ሐዋርያት የሚበላ ስለሌላቸው እንዲያሰናብታቸው ጠየቁት። እርሱ ግን የሚበሉት እንዲሰጧቸው ነገራቸው አሁን ጌታችን ያላቸው ምግብ ለህዝቡ እንደማይበቃ ጠፍቶት አይደለም ነገር ግን ችግራችንን ጉድለታችንን ሊሞላልን ሲፈልግ አስቀድመን ችግራችንን ልንነግረው ይፈልጋልና ሐዋርያቱ ያላቸው ምግብ ትንሽ መሆኑን እንዲነግሩት ነበር ። ወዳጄ አንተስ ችግርህ ምንድን ነው? ልታደርገው አቅደህ አልበቃ ያለህ ምንድን ነው? በአገልግሎት በመንፈሳዊ ህይወት ልትተጋ አስበህ ምን ጎሎህ ነው የነበሩህን እቅዶች ለመሸኘት የተገደድከው? ከቃሉ ከአገልግሎቱ የራከው ምን አንሶህ ነው? ጊዜ አጥሮህ ነውንን? ትጋት አጥሮህ ነውን? ትዕግስት አጥተህ ነውን? ምንድን ነው ያነሰህ? ብቻ ችግርህን ንገረው እርሱ ያነሰህን ነገር አበርክቶ ተትረፍርፎህ ታየዋለህ። ለጌታችን ሐዋርያት ያለን ሁለት ዓሳና አምስት እንጀራ ብቻ ነው አሉት። አሁን ይህ ምግብ እንኳንስ ለህዝቡ ይቅርና ጌታችንንና ደቀመዛሙርቱን እንኳን በቅጡ የሚያጠግብ አልነበረም ነገር ግን ሐዋርያቱ እጅ ላይ የነበረውን ጥቂቷን ነገር ሠጡት እርሱም ባርኮ አበርክቶ አምስትሺውን ህዝብ አብልቶ 12መሶብ ከተረፈው ተሰበሰበ።
ወዳጄ እጅህ ላይ ምን አለ? በእጅህስ የያዝከው ምን አለ? ጥቂት ነው ለምንም አይበቃም ያልከው ምናልባት መኖሩንም የረሳኸው ሊሆን ይችላል እርሱን ይዘህ ቅረብ ለእርሱም ስጠው እርሱ ባርኮ መልሶ ይሰጥኻል። ከብዙ የዓለም መባዘን የተረፈህ ትንሽ ጊዜ አለህ እርሱን እስኪ ለእግዚአብሔር ስጠው ያን ይባርክልኻል። ጉልበት አለህ እርሱንም ለእግዚአብሔር ስጠው አገልግልበት እውቀት አለህ እርሱንም ቢሆን ለእግዚአብሔር ስጠው። ያለህን ጥቂት ነገርም ቢሆን ስጠው እርሱ ባርኮ ሲመልስል ትልቅና ካሰብከውም በላይ ነው።እመ ሣሙኤል ሃናን ተመልከት ህፃኑን ሣሙኤል ለእግዚአብሔር ሰጠችው እርሱም በሞገስና በጥበብ አሳድጎ ታላቅ ነቢይ የእስራኤልም አባት ንጉስን ቀብቶ የሚሾም አደረገው ። ኢያቄምና ሃናንም ተመልከት የ3 ዓመት ህፃን እመቤታችንን ሰጡት እርሱም የዓለም እናት አድርጎ ሠጣቸው የወለዷት እናት ሆነቻቸው መርታም ወደ ገነት አስገባቻቸው። አንተም ያለህን ጥቂት ነው የምትለውንም ቢሆን ስጠው ካሰብከው በላይ አድርጎ ይሰጥኻልና። ወዳጄ ሆይ አንተስ ምን አለህ? መቼም ምንም የለኝም አትለኝም ሰጪው እግዚአብሔርን በሐሰት መክሰስ ይሆንብሃልና ቢያንስ ሕይወት አለህ፤ ይህን ጹሑፍ ማንበብህ በራሱ ማንበብ የምትችል በመሆንህ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁሉ አንተ መኖሩን እንኳን የረሳኸው ያም ባይሆን ጥቂት ነው ይህማ ለምንም አይበቃም ያልከው ነገር አይጠፋምና እርሱን ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ ያ ጥቂት ነው ያልከው ተትረፍርፎ ትመለከታለህ።
ወዳጄ ሆይ ምን ጥቂት ነገር አለህ?
.
.
ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ
ታዲያ በአንድ ወቅት ንጉሡ ናቡከደነፆር ዱራ በሚባል ሜዳ ላይ ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነ ጣዖት አቁሞ ለዚህ ጣዖት የማይሰግድ ወደ እቶን እሳት ይጣላል የሚል አዋጅ አስነገረ ነገር ግን አናንያ ሚሳኤልና አዛርያ አንሰግድም አሉ ነቢዩ ዳንኤል ከባቢሎን ጠበብት መካከል አንዱ ነበረና ለመስገድ አስገዳጃ ቦታ ላይ እንዳልነበረ አባቶች ያስተምራሉ።
ለንጉሡም እነዚህ በባቢሎን አውራጃ የሾምሃቸው ሦስቱ ሰዎች አናንያ ሚሳኤልና አዛርያ አንስግድም ማለታቸውን ነገሩት ንጉሡም የማትሰግዱ ከሆነ ወደ እቶን እሳት ትጣላላችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ አይኖርም አላቸው እነርሱም የምናመልከው አምላክ ከእቶን እሳት ያድነናል ባያድነንም እንኳን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም አሉት። ከዛም ንጉሡ እሳቱን ሰባት እጥፍ እንዲያደርጉትና አስረው ወደ እሳቱ እንዲጥሏቸው አዘዘ አስረውም ወደ እሳቱ ጣሏቸው ነገር ግን እሳቱ የጣሏቸውን ሲያቃጥል ሠለስቱ ደቂቅን ግን አላቃጠላቸውም።
በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተደንቆ ወደ እሳቱ ቢመለከት አራት ሰዎችን ተፈተው በእሳቱ መካከል ሲመላለሱ ተመለከተ እንዲህም አለ ሦስት ሰዎችን አስረናል አላላችሁም ወይ እኔ ግን የተፈቱ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን አያለሁ የአራተኛው መልኩ ግን የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል አላቸው። የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሜሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሜሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው የራሳቸውም ጠጉር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ።
ናቡከደነፆርም መልሶ መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሥንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ አለ።
እንግዲህ በንጉሡ ቃል የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል የተባለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል መባሉ በዘመነ ሐዲስ የአምላክን ሰው መሆን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያበሰረ መልአክ ነውና። ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳናቸው ታሕሳስ አራት ቀን ነው ነገር ግን ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ሲመቱ በታሕሳስ አስራ ዘጠኝ ነውና አባቶቻችን ሊቃውንት ከባዓለ ሲመቱ ጋር አብሮ እንዲከበር አድርገዋል። እግዚአብሔር አምላካችን ከሊቀ መልአኩ ከራማው ልዑል ከአርባብ አለቃ ከቅዱስ ገብርኤል በረከት ያሳትፈን ረድኤቱ ጠባቂነቱ ከሀገራችን ይልቁንም ከሕዝበ ክርስቲያኑና ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጋር ለዘልዓለሙ ይሁን አሜን።
ስለቅዱሳን መላእክት ስለነገዳቸውና ስለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት በጥቂቱ
ሦስቱ ዓለመ መላእክት።
እግዚአብሔር መላእክትን በሦስቱ ሰማያት በ10 ከተሞች በ100 ነገድ አኖራቸው።
ኢዮር፦በ4 ይከፈላል በ10 በ10 ነገድ አድርጎ አኑሯቸዋል በኢዮር ያሉትን ሌሊት 10 ሰዓት ፈጠራቸው።
1 በዚህ የሚገኙት 10 ነገድ ስማቸው አጋዕዝት ይባላሉ አለቃቸው በቀድሞ ሳጥናኤል ነበር።
2 10 ነገድ ስማቸው ኪሩቤል ይባላሉ አለቃቸው ኪሩብ ይባላል።
3 10 ነገድ ስማቸው ሱራፌል ይባላሉ አለቃቸው ሱራፊ ይባላል።
4 10 ነገድ ስማቸው ኃይላት ይባላሉ አለቃቸው ሚካኤል ይባላል።
ራማ፦በ3 ይከፈላል በ10 በ10 ነገድ አድርጎ አኑሯቸዋል። በራማ ያሉትን ሌሊት 10 አንድ ሰዓት ፈጠራቸው።
5 10 ነገድ ስማቸው አርባብ ይባላሉ አለቃቸው ገብርኤል ይባላል።
6 10 ነገድ ስማቸው መናብርት ይባላሉ አለቃቸው ሩፋኤል ይባላል።
7 10 ነገድ ሰማቸው ሥልጣናት ይባላሉ አለቃቸው ሱርያል ይባላል።
ኤረር፦ በ3 ይከፈላል በ10 በ10 ነገድ አድርጎ አኑሯቸዋል በኤረር ያሉትን ሌሊት 12 ሰዓት ፈጠራቸው።
8 10 ነገድ ስማቸው መኳንንት ይባላሉ አለቃቸው ሰዳካኤል ይባላል።
9 10 ነገድ ስማቸው ሊቃናት ይባላሉ አለቃቸው ሰላታኤል ይባላል።
10 10 ነገድ ስማቸው መላእክት ይባላሉ አለቃቸው አናንኤል ይባላል።
እነዚህ በጠቅላላ 100 ነገድ ይሆናሉ።
7ቱ ሊቀ መላእክት ስማቸውና የስማቸው ትርጉም:-
1) ቅዱስ ሚካኤል - ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው።
2) ቅዱስ ገብርኤል - የእግዚአብሔር ኃይል(ጌታና ባርያ አምላክ እና ሰው) ማለት ነው።
3) ቅዱስ ራጉኤል - ብርሃንን የሚመግብ ማለት ነው።
4) ቅዱስ ዑራኤል - እግዚአብሔር ብርሃን ነው ማለት ነው።
5) ቅዱስ ሩፋኤል-እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ማለት ነው።
6) ቅዱስ ፋኑኤል- እግዚአብሔር መጋቢ ነው ማለት ነው።
7) ቅዱስ ሳቁኤል - የእግዚአብሔር ጸሎት ማለት ነው።
አጥንት የሚጠብቁ መላእክት
የሊቃናት አለቃ ሰላትያኤል
የመኳንንት አለቃ ሰላትኤል
የመላእክት አለቃ አናንኤል
በኢዮር የነበረው አንዱ ነገድ በዲያብሎስ ምክንያት ሲወርድ መቶ የነበረው ነገድ 99 ሆነ ከሳጥናኤል ጋር የነበሩ ያልበደሉ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ነገድ ጋር ተደርበዋል በዚህ ምክንያት በኢዮር የነበረው ለ4 የተከፈለው በ3 ሆነ ከሌሎቹ ጋር አጠቃላይ 9 ሆነ ቤተክርስቲያን በሦስት ክፍል በኢዮር በራማ በኤረር አምሳል መቅደስ ቅድስት ቅኔ ማኅሌት ሆኖ ይሰራል የክህነት ደረጃዎችም ዘጠኝ የሆኑት ለዚህ ነው።
እነርሱም:-
1) ሊቃነ ጳጳሳት የኪሩቤል
2) ጳጳሳት የሱራፌል
3) ኤጲስ ቆጶሳት የኃይላት
4) ቆሞሳት የአርባብ
5) ቀሳውስት የመናብርት
6) ዲያቆናት የሥልጣናት
7)ንፍቅ ዲያቆናት የሊቃናት
8) አናጎንስጢስ የመኳንንት
9)መዘምራን የመላእክት ምሳሌ ናቸው።
በ መምህር ዘለዓለም ለገሠ ከመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ትምህርት ክፍል ታሕሳስ 19/2015 ዓ/ም
|<<-በጸሎትህ ውስጥ ባለ አንድ ቃል #ጣዕም ወይም #ጸጸት ከተሰማህ በእርሱ ላይ ቆይ ፤ #ጠባቂ_መላእክቶቻችን ከእኛ ጋር አብረው እየጸለዩ ነው!!->>|
+_ዮሐንስ ዘሰዋስው
ስታማርሪ ለሰይጣን ፀሎት እያደረግሽ ነው::ሳታውቂው የጨለማውን ንጉስ እያመለክሽ ነው::
-
ወደ እግዚአብሔር የምትናገር ሴት አንደበቷ አዎንታዊ ቃላትን ብቻ ይናገራል::በነገር እና በሁኔታው ውስጥ የማይጠፋውን አምላክን እያሰበች ትደሰታለች::
-
ከማማረር ምን አተረፍን? ከዚህ ወዲያም ባጋጠመን ሁሉ ብናማርር ሽልማቱ ምንድን ነው? ምንም!
-
እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ መልካም ነገር በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ አለው::ለሁላችንም እቅዱ የተሻለ ፍቅር እና ሰላም ነው::እስቲ አመስግነን እንሞክረው::
-
የምታማርር ሴት የአምላክን መልካም ነገር ሳታገኘው ትኖራለች::በአንደበቷ እኩይ ቃላት ወደ እኩይ ሰይጣን ትቀርባለች::በገዛ አንደበቷ ተጠልፋ ትወድቃለች::
-
የብልህ ሴት አንደበት ግን በሚያምሩ አዎንታዊ ቃላቶች የተዋበ ነው::እርሷም የሚጋረጥባትን የህይወት ፈተና በምስጋና አንደበት ትሞግታለች::መንፈሷን በመልካም ቃላት ታርሳለች::
-
ምስጋና የህይወት ስኬት ስንቅ ናት::ለውስጥም ለውጪም ችግር መድሃኒት ናት::
-
ምንም በዙርያችን መጥፎ ነገሮችን ብናይም በውስጣችን ወዳለው አምላክ እንመለስ::በምስጋና ቃላት መንፈሳዊነታችንን እናድስ::
-
እግዚአብሔር ይመስገን!
#የክርስቲያኖች_ማኅፀን!!
✍️የቅዱሱ አባታችን የአዳም ማኅፀን ምድር ነበረች ፤ ብጹዕ አዳም ከምድር ተገኝቶ ሕይወት ተችሮት በአምላካዊ ፍስሓ ሲኖር ያልጠበቀው ድቀት በሕይወቱ ተከስቶ ፣ ከዘለዓለማዊነት ጎድሎ ቀሪ እንጥፍጣፊ ዘመኑን ምድረ-ፋይድ ተብላ በምትጠራዋ ዓለም ጨርሶ ፤ ተመልሶ ወደተገኘባት ማኅፀን ወደ-ምድር ተመልሷል።
✍️በአንዱ አዳም ምክንያት ሞት ወደ-ዓለም በመግባት ልጆቹን ሥጋቸውን ለመቃብር ነፍሳቸውን ለአስጨናቂዋ ዓለም ሲኦል አሳልፎ ሲሰጥና ያለማንም ተገዳዳሪ በሰው ልጆች ላይ ነግሦ ዘመናትን ሲገፋ ኑሯል። የሰው ልጅ በራሱ ጥበብ ከዚህ አስጨናቂ የሕይወት ዑደት መውጣት እንደማይችል ተገንዝቦ ኑሮ ረድኤተ-እግዚአብሔርን አንጋጦ "አንሥእ ኃይለከ ወነአ አድኅነነ" እያለ በመጠባባቅ ላይ ነበር።
✍️የዓለም ድኅነት በመለኮታዊ ዕቅድ እየተቃረበ ነበር ፤ የሰው ልጅ ከደረሰበት የባሕርይ ድቀት እና ውርደት ወደ-ቀደመ ክብሩ ልጅነት ፣ ወደ-ቀደመ ቦታው ገነት ሊመለስ የሚችለው በእሱ ላይ የተላለፉ መለኮታዊ ፍርዶች ተፈጻሚነት ሲያገኙ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ እንዳይሆን ሁሉም በምልዓተ-ኃጢአት ተይዞ መንፈሳዊ ቁመናው ጎብጦ ስለነበር ይህን ፍርድ ሊያስወግድ የሚችል ከሰው ወገን አንዳች አልነበረም።
✍️"እንዘኢኮነት ንጽሕት ድንግል እምኢፈጠርክዎሙ ለአዳም ወሔዋን...የነጻች የተለየች የተጠበቀች ባትሆን ኑሮ [ድንግል ማርያም] አዳምንና ሔዋንን ባልፈጠርኳቸው ነበር" እንዲል አስቀድሞ በመለኮታዊ አሳብ የተለየች ንጽሕት ድንግል ማርያም ምክንያተ-ድኂን ለዝንቱ ዓለም በመሆን በሥጋ ሥርዐት ይህቺን ዓለም ተቀላቀለች ፤ ምድር ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አስተናግዳው የማታውቀውን ሰው ያየችው ቅድስት ድንግል ማርያምን ነው።
✍️እመቤታችን፦ በእንግዳ ሥርዐት በመለኮታዊ ግብር አምላክ ወልደ-አምላክ እግዚአብሔር ወልድን በተለየ አካሉ ፣ስሙ፣ አካላዊ ግብሩና ከዊኑ በተተነበየው መሠረት በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወልዳ ለዓለም ሕይወትን አስረከበች።
✍️የሰው ልጅ እንደገና መወለድ ስላለበት እና ቀድሞ ወደታሰበለት ልዕልና ይመለስ ዘንድ ይገባ ስለነበር ዳግም የሚወለድባት አዲስ ማኅፀን በወልደ-እግዚአብሔር ተፈጠረለት። ይህቺም ማኅፀን ጥምቀት ናት። አዳማዊ ፣ ባሕርዩ የጎሰቆለ ፣ መንፈሳዊ ሕይወቱ የተበከለ ፣ ኃይሉ ደካማ ፣ ጸሎቱ የማይሰማ የነበረ ሰው ወደዚህች ማኅፀን ሲገባ ... ወልደ-አምላክ እግዚአብሔር ክርስቶስ ኢየሱስ ሲጠመቅ በጥምቀት ማኅፀን ዘለዓለማዊነትን ፣ አዲስ ማንነትን ፣ እራሱን ህልው አድርጎ ስለሆነ የወጣው [የእሱ መጠመቅም ምክንያቱ ይህ ነው] እያንዳንዱ ክርስቲያን ወደዚህ ማኅጸን ሲገባ ምን ሊሆን እንደሚችል ሊናገር የሚችል ከመካከላችን ይኖር ይሆን?
✍️የተጠመቀ ሰው ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት ይወለዳል። የሥጋ ሞቱ ጥቅም ይሆንለት ዘንድ ክርስቶስ የሞትን ሁኔታ ቀይሮታል። ይህ በጥምቀት የምናገኘው ምሥጢር መጨረሻ ወደሌለው ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚመራን ነው።
✍️በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን። በውሃው ውስጥ ሦስት ጊዜ በመነከር በመቃብር ከቆየበት ሞቱ ጋር እንተባበራለን። ዳግመኛም ከውሃው ውስጥ በመውጣት ከትንሣኤው ጋር እንተባበራለን።
✍️ይህን ሐዋርያው እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፦ "ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን?... ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።" ሮሜ ፮፥፫-፭
✍️ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ-እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ዮሐ ፫፥፭
እንኳን ለበዓለ-ጥምቀት / አስተርእዮ በሰላም አደረሰን!!!
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++
"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
---------------
ሰላም ለከ ሶበ ሰማዕከ ዐዋዴ፡
እምቃለ ወንጌል ዘወርቅ እንበለ ተምያን ወመፍዴ፡
ዮሐንስ ዘኮንከ በእንተ ጽድቅ ነጋዴ፡
መኒነከ እመ ወላዲተ ወአበ ወላዴ፡
ምስለ ነዳያን ነበርከ በዴዴ፡፡
[አዋጁን በሰማህ ጊዜ ያለ ግብዝነትና ያለ ክፍያ ወርቃማ ስለሆነው የወንጌል ቃል ብለህ የምትወልድ እናትና የሚወልድ አባትን ትተህ ስለጽድቅ ነጋዴ የሆንክና ከነዳያን ጋር በደጅ የኖርክ ዮሐንስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን]
ሰላም ለዮሐንስ ዘተለዓለ መጠኑ፡
በነሢአ ጸጋ ወክብር እንተ ኢተውህበት ለካልኣኑ፡
ዘሥጋ ወደም እንዘ ውእቱ አኮኑ፡
አመ ሰዓሞ በአፉሁ ወአመ አርፈቆ በሕፀኑ፡
ለእሳተ መለኮት መፍርህ ኢውዕየ በርስኑ፡፡
[ ለማንም ያልተሰጠውን ጸጋና ክብር በመቀበሉ ደረጃው ታላቅ ለሆነ ዮሐንስ ሰላም እላለሁ፤ በአፉ ቢስመውም ከጎኑ ቢያስቀምጠውም ሥጋና ደም ሆኖ ነውና የሚያስፈራው እሳተዊ መለኮት ግለቱ አላቃጠለውም]
ሰላም ለክሙ ጽጉባነ ምዑዝ ጽጌረዳ
ዘረከበክሙ ክርስቶስ ለባህረ ገሊላ በዐውዳ
አመ ሰዓተ ደይን ያዕቆብ ወዮሐንስ በዕለተ ፍዳ
በሉኒ ሊተ ዘዚአነ ወለትምህርትነ ወልዳ
እንዘ ትእኅዙ ለነፍስየ እዳ።
[ መልካም መዓዛ ያለውን ጽጌረዳ ለጠገባችሁት ለእናንተ ሰላም እላለሁ። ክርስቶስን በገሊላ ባህር አጠገብ ያገኛችሁት ቅዱስ ያዕቆብና ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በቁርጥ የቅጣት ሠዓትና በፍርድ ቀን ነፍሴን በእዳ ይዛችሁ እርሱ እኮ የእኛ ነው የትምህርታችን ልጅ ነው በሉልኝ]
ሰላም እብል ዘሥጋከ ፍልሰተ
ኀበ ኢይጥዕም ሞተ፡
ዮሐንስ ንጹሕ ዘኢተአምር ጥልቀተ፡
አርፈቀከ ውስተ ሕፅኑ ወሰዓመከ ስዕመተ
መለኮት ወልድ ዘለብሰ ትስብእተ፡፡
[ሞት ወደማያገኘው (ብሄረ ኅያዋን) ሥጋህ ለመፍለሱ ሰላም እላለሁ፣ ማደፍን የማታውቅ ንጹሕ ዮሐንስ ወልድ የተባለ መለኮት ሰውነትን የለበሰ ከእቅፉ አስቀመጠህ መሳምን ሳመህ]
ጌታችን እኛን ለማዳን ሲል ስለሀጢያታችን ብዛት ሳይሆን ስለፍቅሩ ኋያልነት ሰው ሆኖ ተወልዶ ስቃያችንን ሊሰቃይልን ሞታችንን ሊሞትልን መጥቶ የፍቅርን ጥግ አስተምሮናልና !
ለሰዎች ያለንን ፍቅር ምን ያህል መሆን ይገባዋል ስንል ጌታችን ምን ድረስ ሰጠን ብለን እንመልከት ያኔ የፍቅር ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ገብቶን እርስ በእራስ ስንፋቀር እንኖራለን ! ፍቅር በምድራችን ይብዛልን !
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
|<<የተሸከመችውን ማኅፀን እናመስግን ፤ ላቀፉት ጉልበቶች እንስገድ ፤ ላሳደጉት ጡቶች እንዘምር ፤ የዳሰሱትን እጆች እናመስግን ፤ ለሳሙት ከንፈሮች እናሸብሽብ ፤ ከእረኞች ጋር ምስጋናን እናቅርብ ፤ ከሰብአ ሰገል ጋር እጅ እንንሣ ፤ እንደ ዮሴፍ እናድንቅ ፤ እንደ ሰሎሜም እናገልግል ፤ በተኛበት በረት እንስገድ ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ በተቀመጠበት በረት እንንበርከክ ፤ #ለእግዚአብሔር በሰማይ ምስጋና ይሁን ፤ በምድርም ሰውን ለወደደው እንበል ፤ #እግዚአብሔር_ሰው_ሆነ ፤ የሴት ልጅም #የእግዚአብሔር_እናት ሆነች ፤ ለርሱም ምስጋና ይሁን ለእርሷም ስግደት ይገባል ፤ ለዘለዓለሙ አሜን!!>>|
+አባ ጊዮርጊስ መፍቀሬ-ድንግል
(መጽሐፍ ምሥጢር የልደት ምንባብ)
የንጹሕ እሳት ወላፈኖች ዝማሬያቸውን አሰሙ፤ የሰው አንደበቶችም በደስታ ጩኸት አስተጋቡ፤ መላእክት በማስተዋላቸው በጥበብ ድምፆችን ሰጡ፤ የተናቁ ሰዎችም በንግግራቸው ትሑት ምስጋናን ሰጡ፡፡
የሰማይ ሥልጣናት በልዩ ልዩ መልካቸው ትንሹን ግርግም ከበቡት፤ የመላእክት እና የሰዎች ሰልፎችም (ስብስቦችም) በአክብሮት ተዋሐዱ፤ ዋሻው በመንፈሳውያን መላእክት እና በሰዎች ጉባኤ ተመላ የሰማይና የምድር ልጆች አንደበቶች አስተጋቡ፤ ሰማይ እና ምድር፤ ለምስጋና ተያያዙ፨
+ያዕቆብ ዘሥሩግ
"ነገር ግን ለእኛ ያለውን ፍቅሩን ያሳይና ይጎበኝ ዘንድ ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ ከአባቱ ሳይለይ ወደ እኛ መጣ። ሞት በእኛ ላይ በመሠልጠኑ የተነሣ ጠፍተን እንዳንቀር የእኛን ሥጋ ገንዘብ አደረገ። ሰው ለመሆን ምክኒያቶቹ እኛው ብቻ ነን። እኛን ለማዳን ሲልም በእኛ ባሕርይ ሰው ሆኖ እስከመገለጥና ሰው ሆኖ እስከ መወለድ ድረስ በርኅራኄ ተመለከትን።"
+ቅዱስ አትናቴዎስ
ተወልደ-በአምሳሊከ ከመ-ይለድከ በአምሳሊሁ!
/በመልኩ ይወልድህ ዘንድ በመልክህ ተወለደ።/
[አረጋዊ መንፈሳዊ]
ሰማይ ምድር ፣ ምድር ሰማይ ለሆነባት ፤ መድኅን ክርስቶስ የወደቀውን አዳም ለማንሣት በድንግል ማርያም በርነት ወደ-ዓለም ለገባባት ፣ ዕለተ-አድኅኖ ተብላ ለምትጠራዋ ለአስደናቂዋ ዕለት ለዕለት-ልደት እንኳን አደረሰን!!!
#በዓሉ_ለሥጋችን_ጽርየት_ለመንፈሳችን_ሕድሰት_ለነፍሳችን_ቅድሰት_ይሁንልን።🙏
✍️#መንክር_ልደትከ_ኦ_ወልደ_እግዚአብሔር!
[ወልደ-እግዚአብሔር ሆይ! ልደትህ ድንቅ ነው]
============================
🔖በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ ሲሆን ፥ እንዲሁም በግርግም በከብቶች በረት ተኝቷል። ግን ደግሞ አይመረመርም።
🔖በልዑል ዙፋን ላይ የተቀመጠ ሲሆን ፥ በበረት ተጣለ። ሥጋ [ሰው] ሳይሆን የማይዳሰስ የነበረ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ።
🔖በዘር ከመወልድ የራቀ በሰው ሕሊና ከመታሰብና በመላእክት አእምሮ ከመመርመር በላይ የሆነ አንዱ ወልድ ሰውን ለማዳን ያለመለወጥ ከሰማይ ወርዶ ጉድለትና መወሰን ሳይኖርበት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማኅፀን አደረ።
===========================
🥀 ጌታችን መድኃኒታችን ያለ-ሕማም በተወለደ ጊዜ [[ሳታምጥ ወለደች ፥ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች። {ኢሳ ፷፮፥፯}.. ወእምድንግል ተወልደ ዘእንበለ ሕማም እንዳለ አፈ-በረከት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ።]] በምድር ተወልዶ ስታየው ከሰማይ ከክብሩ የተለየ አይምሰልህ። ሲል ሊቁ ቴዎዶጦስ ወእንቆራ እንዲህ አለ፦
🥀ከአንደበታችን የሚወጣ እርስ በእርሳችን የምንናገርበት የእኛ ቃል አለ ፤ ማንም ማን ሊያየው አይችልም ፤ ለቃል ግዘፍ የለውምና ፤ ለማንም ለማን አይታይምና ፤ በእጅም አይዳሰስምና ፤ ቃል በብራና በተጻፈ ጊዜ ቅርጽም በሆነለት ጊዜ ያን ጊዜ የተገለጠ የታየ ይሆናል።
🥀ለወዳጁ መጽሐፍ ሊጽፍ የሚወድ ሰው ቢኖሩም ቃል የማይታይ የማይዳሰስ ነውና ያ'ሰው በብራና በጻፈው ጊዜ ቀድሞ ልታየው የማትችለውን ያንጊዜ ታየዋለህ። ቀድሞ ልትዳስሰው አይቻልህ የነበረውን የቃልን አካል ዛሬ በብራና በጽሕፈት ትዳስሰዋለህ። ለቃል ግዘፍ የለውምና ጽሕፈት በሚያስገኘው መልክ በተጻፈ ጊዜ ያን ጊዜ ልታየው ልትዳስሰው ተገባህ። እነሆ አሁን ምሳሌው የተለየ የተረዳ ሆነ። [[ሃይማንተ-አበው ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ ምዕራፍ ፶፫ ቁጥር ፲፫-፲፬]]
🥀ማለትም ቃል ሥጋ ሲሆን ፥ በግርግም ተወልዶ ባየኸው ጊዜ ከሰማያዊ ክብሩ የተለየ ሰው ብቻ የሆነ አይምሰልህ። አንድ ሰው ለወዳጁ ደብዳቤ ሊጽፍ ቢወድ ሃሳቡን በወረቀት ላይ ያሰፍረዋል። ያን ጊዜ አያየው የነበረው ሃሳቡን በወረቀት ላይ ያየዋል። ረቂቅ የነበረው ሃሳቡን በወረቀቱ ይወስነዋል ይዳስሰዋል። ወረቀቱም ሃሳብን ስለያዘ ይረቃል። ነገር ግን ሃሳቡን በወረቀት ላይ ስለጻፈው ሃሳቡ ከአእምሮው አይጠፋም። ወረቀቱ ላይ የጻፈው አእምሮውም ውስጥ ይኖራል። #ቃል_ሥጋ ሲሆንም እንዲሁ ነው። ሰውም ሲሆን ፍጹም ከአብ የተወለደ ቃል ሆኖ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ መንፈስቅዱስ ጋር መላእክት ያመሰግኑታል እንጂ።
🥀ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም እንዲህ ብሏል፦ ⁽⁽እርሱ እሳትን ለብሷል ፤ በመጠቅለያ ጨርቅም ተጠቅሏል ፤ ግን ደግሞ ከመታወቅ በላይ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል ፤ እንዲኹ በግርግም ተኝቷል። ግን ደግሞ አይመረመርም። በኪሩቤል ጀርባ ላይ ተቀምጧል ፤ እንዲኹም የድንግል ጉልበቶች ተሸክመውታል። እናም በዚህ ምክንያት እርሱ ታላቅ ነው። እርሱ የተፈጠሩ ፍጥረታትን ያላውሳቸዋል ፤ እንዲሁም እርሱ አካለ-ሥጋን ተዋሕዷልና እናም እነርሱ ድንቁን ይናገራሉ። እርሱ ወገኖችን ያኖራቸዋል ፤ እንዲሁም እርሱ ወተትን ይጠባል። እርሱን ይረዳው ያውቀው ዘንድ ማን ይችላል!? እርሱ ዝናብን ያዘንባል ፤ እርሱ ደግሞ ጡት ይጠባል። እናም ድንቁን ተመልከቱ እርሱ ልዑልና አስፈሪ ነው። ሰማይ ለእርሱ እጅግ ያንሰዋል። እናም እርሱ መኖሪያን ፈለገ። እነሆ እንዴት ያለ ጸጋ ነው!? ሱራፌል ራሳቸውን ይሸፍናሉ ፤ ዮሴፍ ይሰግዳል ፤ ልዑል በድንግል እቅፍ ዙፋኑን ዘርግቷልና። ሥልጣናት ተዘርግተዋል ፤ ሰዎችም ደካማዎች ናቸው ፤ ያስተውል ዘንድ ግን ማን ይችላል!?
🥀አፈ-ዕንቍ ዮሐንስም እንዲህ ይላል፦ ⁽⁽ምን ብዬ ልንገራችሁ!? እንዴትስ ብዬ ልግለጽላችሁ!? #የወለደች_ድንግል እመለከታለሁ። የተወለደ ሕጻንም አያለሁ ፤ እንዴት እንደተጸነሰ ግን አላውቅም። የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ-ድካም መጣ ፤ ፍጥረትም ከድካሙ አረፈ። ሊነገር የማይችል ጸጋ ፤ በልዑል ዙፋን ላይ የተቀመጠ ሲሆን በበረት ተጣለ። ሥጋ ሳይሆን የሚይዳሰስ የነበረ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ። ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ በጨርቅ ተጠቃለለ። ለምን!? የሚታይና የሚዳሰስ ሆኖ መጥቶና ወኔጌልን አስተምሮ ሰዎች ልናየው ወደማንችለው ይመራን ዘንድ።
ሰዎች ከሰማነው ነገር ይልቅ ያየነውን እናምናለንና ጥርጣሬያችንን ያስወግድ ዘንድ ራሱ በሚታይ ሥጋ መታየትን ወደደ።
=========================
✍️ተወልደ በአምሳሊከ ፤ ከመ-ይለድከ በአምሳሊሁ። /በአምሳሉ ይወልድህ ዘንድ በአምሳልህ ተወለደ።
+. አረጋዊ መንፈሳዊ
◉◉◉ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን። ◉◉◉
#ነገረ_ሥጋዌሁ ፥ #ለወልደ_እግዚአብሔር!!
✍️በሊቃውንተ-ቤተክርስቲያን
[[ክፍል ሦስት]]
🔖እግዚአብሔር አምላክ ሥጋን ሳይለብስ ዲያብሎስን ድል ቢነሣው ምን ይደንቃል? አምላክነቱን ድል የሚነሳው ከቶ የለምና።
🔖ከመረዳት በላይ የሆነው እርሱ በሚረዳ አካል በመገለጥ ሥጋን ከመረዳት በላይ አደረገው።
🔖እርሱ እንደ-ጦረኛ ከሰማያት ወረደ ፤ ከድንግል በነሣው ሥጋም ዓለምን ድል ነሥቶ የነበረውን ጠላት ዲያብሎስን ድል ነሣው።
✞✞✞~★✤✤✤★~✞✞✞
➾ስለምን ጌታችን ሥጋን መልበስ አስፈለገው? ምክንያቱም ይህ ሥጋ ድል መንሣትን ገንዘቡ ያደርግና የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን የጸጋ ስጦታዎችን ይረዳ ዘንድ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሥጋን ሳይለብስ ዲያብሎስን ድል ቢነሣው ምን ይደንቃል? አምላክነቱን ድል የሚነሣው ከቶ የለምና። ሥጋን የመልበሱ ሁለተኛው ምክንያት ግን አዳም አምላክነትን መሻቱ እግዚአብሔርን በቅናት እንዳላነሳሳው ያስገነዝበው ዘንድ ነው።
➾ክርስቶስ ራሱን ዝቅ በማድረግ አዳምን [የተዋረደውን አዳም] በገነት ሳለ ታላቅና ክቡር ከሆነው አዳም [ከስሕተት በፊት ከነበረው አዳም] ይልቅ በእጅጉ አላቀው። ስለዚህም ⁽⁽እኔ ግን አማልክት ናችሁ ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ መዝ ፹፪፥፮⁾⁾ ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ። እንዲህም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቃል ከላይ ከአርያም በመምጣት ሥጋን መልበስ አስፈለገው። በዚህም ከመረዳት በላይ የሆነው እርሱ በሚረዳ አካል በመገለጥ ሥጋን ከመረዳት በላይ አደረገው። የሰው ልጆችም የምሥጢራት ሁሉ ፍጻሜና የምሳሌያት ሁሉ ትርጓሜ ወደ-ሆነው ወደ-እርሱ በጸጋ ክንፎቻቸው በመክነፍ [በመብረር] በእርሱ አንድ አካል ይሆኑ ዘንድ እርሱ በእውነት የበጎ ነገሮች ሁሉ ግምጃ ሆናቸው።
➾የእግዚአብሔር ጥበቡ የሆነውና ስለወደቀው አዳም ራሱን ዝቅ ያደረገው እርሱ አንድዬ ፣ ስለእርሱ ተዋርዶ የተዋረደውን አዳም ከውርደቱ ሊያነሣው ወደደ። ነገር ግን የአዳምን ባሕርይ ገንዘቡ ሲያደርግ ኃጢአትን የሚያውቀውን የአዳምን ተፈጥሮ ከነ-ኃጢአት ፈቃዱ ሊለብስ አልፈቀደም። አዳም ጤናማ በሆነው ተፈጥሮ ውስጥ ባዕድ የሆነ የኃጢአት ፍምን አኑሯልና ስለዚህ ጌታችን አዳምን ወደ-ቀድሞ ጤንነቱ ይመልሰው ዘንድ ጤናማ የሆነውን የቀድሞውን የአዳምን ባሕርይ ለበሰ።
➾የአውሬው ሰራዊት በሰይፎቻቸው ክፉኛ ቢያቆስሉንም ከቊስላችን ይፈውሰን ዘንድ መድኃኒታችን ሰው ሁኖ ተገለጠ። ምክንያቱም የሰው ልጅ ተፈጥሮ አንዱ ካንዱ በጥብቅ የተቆራኘ ከመሆኑ የተነሣ ያለ-ፈቃዱ በአንዱ መተላለፍ ሁሉ የቅጣቱ ተካፋይ ሆኖአል።
➾አዳምን ከሕማሙ ለመፈወስ ጌታችን በአዳም የተዋለለት ውለታ እንደሌለ እንዲሁ እርሱን ያሰናከለው ሰይጣንም አዳምን ያሰናክለው ዘንድ አንዳች ምክንያት አልነበረውም። ሶምሶን በአህያ መንጋጋ ብዙ ሰዎችን እንደገደለ እንዲሁ ሰይጣን ሔዋንን ክንዱ በማድረግ የሰውን ዘር ሁሉ ገደለ። ስለዚህ ጌታችን ያለ ዘርዐ-ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለድ ከእርሷ በነሣው ሥጋ በተቃዋሚው ላይ ድልን ተቀዳጀ ፤ በዓለሙም ላይ ፈረደ። እርሱ እንደ-ጦረኛ ከሰማይ ወረደ ፤ ከድንግል በነሣው ሥጋም ዓለምን ድል ነሥቶ የነበረውን ጠላት ዲያብሎስን ድል ነሣው ፤ በከሳሻችንም ላይ ፈረደ።
➾ይህ ድኅነታችን እስኪፈጸምልን ድረስ ግን ቤተክርስቲያን በኅቡዕ ነበረች አልተገለጠችምም ነበር። ምሥጢራቱ በክርስቶስ ሰው መሆን በመገለጣቸው ምክንያት ግን ቤተክርስቲያን ለሁሉ ተጋለጠች። እንዲሁ ቤተክርስቲያን ለሁሉ እስክትገለጥ ድረስ ተርጓሚያንም ዝምታን መርጠው ነበር። ነገር ግን ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ለሁሉ ከተገለጠች ወዲህ ምሥጢራት ሁሉ መተርጎም ጀመሩ።
[[አፈ-በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ከዲያቴሳሮን (ኅብረ-ወንጌል) መጽሐፉ የተቀነጨበ።... ተጠልቆ የማያልቅ የቅዱሱን አስተምህሮ እዚህ ላይ ገታ እናድርግና ወደ-ሌሎች አበው እንሻገር። የቅዱስ ኤፍሬምን ሥራ እንድታነቡት በዚሁ ላሳስብ እወዳለሁ። የቅዱሱ ሥራ ከእሱ በኋላ ለተነሡ ለነቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ሳይቅር መሠረት የሆነ ተወዳጅ ሥራው ነው]]
✞✞✞~★✤✤✤★~✞✞✞
✍️እግዚአብሔር ከልዑል መንበሩ ወደ-ምድር ወረደ። ከቅድስት ድንግል ማርያምም ሥጋ ለብሶ ነቢያት እንደሰበኩት በቤተልሔም ተወለደ። (ቀሌምንጦስ)
@Slehiwetwe ቤተሰብ ይሁኑ!!
#ነገረ_ሥጋዌሁ #ለቃለ_እግዚአብሔር!!
✍️በሊቃውንተ-ቤተክርስቲያን
[ክፍል አንድ]
🔖እስክትወልድ ድረስ እንዲንከባከባት ጻድቅ ለሆነው ለእርሱ እንድትታጭ ሆነች።
🔖ቀዳማዊቱ ሔዋን ነፍሰ-ገዳይ የሆነ ልጅን ወለደች፤ ድንግል ማርያም ግን ሕይወትን የሚሰጥ ጌታን ወለደች።
+++ ================+++
➾ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንዲህ ነበር። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ #በመንፈስ_ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። [ማቴ ፩፥፳፱] ወንጌላዊው ያለ-አንዳንዳች ምክንያት እንዲህ አላለም። አሕዛብ ስለ-አማልክቶቻቸው ሲተርኩ እነርሱን ለማግነን ሲሉ ከሰዎች ጋር ተራክቦ በመፈጸም ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ ልጆችን ወለዱ ብለው ስለሚያስተምሩ ከዚህ ለመለየት ነው። የድንግልም ያለ-ወንድ ዘር ጌታን በድንግልና መጽነስና መውለድ ከአሕዛብ አፈ-ታሪክ ጋር እንዳናዛምድ ሲል ወንጌላዊው፦ ⁽⁽ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ተገኘች⁾⁾ ብሎ ጻፈልን። እርሱ በሁለት አካላት መካከል በተፈጸመ ተራክቦ የተጸነሰ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተጸንሶ በድንግልና የተወለደ ሲሆን በእርሱ ባመኑት ላይም የሚያድር ነው።
➾ ድንግል ማርያም ለዮሴፍ መታጨቷና ከእርሱ ጋር ሳለች ጌታን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ጸንሳ መውለዷ ትውልዱ ከነገሥታት የዘር ሀረግ ይቆጠር ዘንድ ስለሚገባው ነው። ትውልዱ [በዮሴፍ በኩል] ከዳዊት ዘር ሀረግ ተካቶ ካልተቆጠረ በቀር በእናቱ በኩል ስለትውልዱ መናገር የአይሁድ ልማድ አይደለም። እንዲሁም ኃጢአት በሰለጠነባቸው ሰዎች በሐሰት አመንዝራለች ተብላ እንዳትከሰስ ሲባል ለዮሴፍ ታጨች። በመንፈስ ቅዱስ ጸንሳ ባየ ጊዜ እስክትወልድ ድረስ እንዲንከባከባት ጻድቅ ለሆነ ለእርሱ እንድትታጭ ሆነች። እርሷን ከቤቱ ሊያወጣት አልፈቀደም። ከእርሷ ጋር መኖር መረጠ እንጂ። እርሱ #በእጮኛ_ስም ከእርሷ ጋር ተቀመጠ ፤ ስለዚህ እርሷን በተመለከተ ለሚነሡ ማንኛውም ጥያቄዎች ማለትም ከእርሷ ተጸንሶ የተወለደው ልጅ በምንዝር የተገኘ ሳይሆን #በመንፈስ_ቅዱስ_ግብር እንደሆነ ምስክር ሆነ።
➾ያለ-ተራክቦ ከአዳም ሔዋን እንደተገኘች እንዲሁ ጌታችንም ያለ-ወንድ ዘር ከድንግል ማርያም ተገኘ። በዮሴፍ እና ለእርሱ በታጨችው ድንግል መካከል የሆነው ይህ ነው። ቀዳማዊቱ ሔዋን ነፍሰ-ገዳይ የሆነ ልጅን ወለደች፤ ድንግል ማርያም ግን ሕይወትን የሚሰጥ ጌታን ወለደች ፤ ቀዳማዊቱ ሔዋን የወንድሙን ደም የሚያፈሰውን ወለደች ፤ ሁለተኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን ስለወንድሞቹ ደሙን የሚያፈሰውን ወለደች። የቀዳማዊቱ ሔዋን ልጅ ምድር በእርሱ ምክንያት በመረገሟ ኮብላይ እና ተቅበዝባዥ ሆነ ፤ የሁለተኛይቱ ሔዋን የድንግል ልጅ ግን ስለ-እኛ እርግማን በመስቀል ላይ ዋለ።
[በቅዱስ ኤፍሬም]
+++==============+++
✍️እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ኢሳ ፯፥፲፬
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሚያለሁ
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሚያለሁ
ካለኝ ነገር ሁሉ አንችን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ።
+◉መሣል◉+
ሥዕል የሠዓሊው ረቂቅ አሳብ ተሸካሚ ነው። ሰዓሊው ሊገልጠው የፈለገውን አሳብ በሸራ ላይ በቀለም አስውቦ ይገልጥና በሥዕሉ አማካኝነት ተመልካቾችን ጎትቶ የራሱ አሳብ ውስጥ ይከታቸዋል! ይህን ለማድረግ [ሰዎችን የአሳቡ ምርኮኞች ለማድረግ] ኃይል መጠቀም አያስፈልገውም። ሥዕሎቹን ሥሎ ለእይታ ማቅረብ ብቻ ነው የሚጠበቅበት።
ክርስቲያን ወላጆችም ተመሳሳዩን መንገድ መጠቀም አለባቸው። ልጆቻቸው ቀለምን ለመቀበል እንደ-ተወጠሩ ሸራዎች ናቸው ፤ የሣሉባቸውን ያንኑ ሥዕል በወደ-ፊቱ የሕይወት ዘመናቸው ገልጠው ለዓለም የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ሥዕሎች። ሥዕሎቹ እንደየ-ሠዓሊያቸው ዓላማ/ማንነት የተለያየ ይዘት ያላቸው መሆናቸው አይቀርም።
ኦርቶዶክሳዊ ወላጅ፦ በመስቀሉ ብሩሽ #ፍቅረ_መለኮትን እየጠቀሰ በደማቁ በልጆቹ ልብ ላይ #ቤተክርስቲያንን አጉልቶ የሚስል ከሣለም በኋላ #በድንግል_ማርያም ሐረግ ዙሪያያዋን ሸልሞ #በቅዱሳን ፍሬም አስውቦ ለእይታ የሚያቀርብ ሠዓሊ ነው!!
ወላጆች....
ዓለም እነሱን [ልጆቻችሁን] ተመልክቶ ቤተክርስቲያንን አለማየት እስከማይችል ድረስ ሕያው መንፈስ ቅዱስ የሚሠራባቸው ተንቀሳቃሽ ቤተክርስቲያን በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ግዴታችሁን ተወጡ!!
--------------
“ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።”
— ምሳሌ 22፥6
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++
"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡
"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"
© ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
---------------
✍️ቀላልና ያልተሸላለመ የልጆች መኮላተፍ ዘወትር የሰማያዊ አባታቸውን #ልብ ያሸነፈ ነውና ፤ ስትጸልይ በምትጠቀማቸው ቃላት ከመጠን በላይ #አትራቀቅ!!
+_ዮሐንስ ዘሰዋስው