ቀን በቀን የከሳንበት ምክንያት ?
የንጉሥ ዳዊት ልጅ አምኖን የንጉሥ ልጅ እንደመሆኑ የተመጣጠኑ ምግቦች ፣ ከሁሉም የተለየ እና የተመቻቸ አልጋ ፣ እንዲሁም የሚዝናናበት መናፈሻ ከዚህ የበለጡ ብዙ ነገሮች የተሟሉለት ልጅ ነበረ ። ነገር ግን የተመጣጠነ እና ብዙ አይነት ያላቸውን ምግቦች በቀን በቀን እየተመገበ ፣ የተንደላቀቀ እና ውብ የሆነ አልጋ ላይ በቀን በቀን እየተኛ ፣ በሰፊ ቤተ መንግሥት ውስጥ እየኖረ ቀን በቀን ከመክሳት ውጪ በሰውነቱ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም ። ለዛም ነው ይህንን ነገር ያስተዋለው የአምኖን ጓደኛ ኢዮናዳብ <<የንጉሥ ልጅ ሆይ ስለምን ቀን በቀን ትከሳለህ ? >> ብሎ አምኖንን የጠየቀው ።
አምኖን የንጉሥ ልጅ ሲሆን በምን ምክንያት የከሳ ይመስላችሗል ? እስቲ አምኖንን የንጉሥ ልጅ ሆነህ ሳለህ ለምን ቀን በቀን ከሳህ ? ሁሉ በደጅህ ሁሉ በእጅህ ሆኖ ሳለ ምንም ነገር እንዳላገኘ ሰው ለምን ከሳህ እንበለው ? በዚህ ጊዜ አምኖን እኔ የከሳሁት <እኅቴ ትእማርን ወድጄያት ነው> ብሎ ይመልስልናል ።
እውነቱን ነው አምኖን በዛ በሰፊው ቤተ መንግሥት ሰውነቱ የከሳው የተለያዩ ምግቦች አጥቶ አልያም የማይመች አልጋ ላይ ተኝቶ ወይም ደግሞ ሚዝናናበት ቦታ አጥቶ አይደለም ። ይልቁንም እነዚህን ነገሮች በአባቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ በስፋት ና ሁል ጊዜ ቢያገኛቸውም ቅሉ ግን አምኖን ሐሳቡን ሌላ ቦታ አድርጎ ስለሚጠቀምባቸው ነው ቀን በቀን ሊከሳ የቻለው ።
እኛ እንደ አምኖን የንጉሥ ልጅ አይደለን ? ስለምን ይህን ነገር ለእኛ ትነግረናለህ ልትሉኝ ትችላላችሁ ? እኔም እላችሗለሁ እናንተ የአምኖን አባት ንጉሡ ዳዊት ንጉሤ ፣ አምላኬ ፣ መጠግያዬ ብሎ የጠራው የነገሥታት ንጉሥ ፣ የጌቶች ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ።
ንጉሡ ዳዊት ለአምኖን ልጁ ስለሆነ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ብዙ ነገሮችን አርግቶለታል የእኛ ንጉሥ እግዚአብሔርም ዳዊት ለአምኖን ካደረገው የበለጠ ለእኛ ብዙ ነገሮችን አርጎልና ።እግዚአብሔር ለእኛ ምድር ላይ ባለችው አገልጋዩ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ያላደረገልን ነገር አለ ? ከመዝሙሩ መዝሙር አልከለከለን ዘማሪዎች ነን ፣ ከአብነት ትምህርቱ አብነት ትምህርት አልከለከልን ዲያቆናት ነን ፣ እንደ ዳዊት በገና አልከለከለንም ፣ እንደ ሰሎሞን ጥበብን አልነፈገንም ፣ ጃንጀረባው ባኮስን እንዲያስተምረው ፊልጶስን እንደላከለት ለእኛም የሚያስተምሩን መምህራንን አልከለከለንም ።
ይህ ሁሉ ነገር ታርጎልን ሳለ ግን ለምን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ቀን በቀን እንከሳለን ? ለምንስ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለውጥ አላመጣንም ? እስቲ መለስ ብለን የአምኖንን ታሪክ እንመልከት ? አምኖን ምንም እንኳን የተመቻቹ ነገሮችን ቢያደርግም እኅቱ ትእማርን በመውደዱ እነዚያን ነገሮች ከልቡ አልነበረም ያደርጋቸው የነበረው ምግብ ቢበላም ፣ የተመቻቸ አልጋ ላይ ቢተኛም ከልቡ አልነበረምና ሀሳቡ ሌላ ነገር ላይ ስለነበረ እነዚህ ነገሮች ለእሱ ለውጥ ሊያመጡለት አልቻሉም።
እኛም ትምህርትን ብንማርም ፣ በገናን ብንደረድርም ፣ መዝሙረ ዳዊትን ብንደግምም ፣ መዝሙርን ብንዘምርም ይህን ሁሉ ነገር በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ እንደ ልባችን አግኝተን ብናረጋቸውም ሀሳባችን ሌላ ነገር ላይ ስለሆነ ለውጥ ልናመጣባቸው አልቻልም ። በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለውጥ የማናመጣው ሀሳባችን ሌላ ሆኖ ተግባራችን ሌላ ስለሆነ ነው እንጂ ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳጣችን ነገር ኖሮ አልያም ሳንማር ፣ሳንዘምር ቀርተን አይደለም ።
ለአምኖን የተጠየቀውን ጥያቄ እስቲ እኛም እንጠየቅና ችግራችንን እንቅረፍ ። ጥያቄውም ምንድነው ?ክርስቲያን ሆነህ(ሽ) ይልቁንም የሰንበት ተማሪ ሆነህ(ሽ) ቀን በቀን መንፈሳዊ ሕይወትህ(ሽ) ስለምን ለውጥ አላመጣም ? ለምን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሳን። አምኖን የተጠየቀው ይሄንን ነው። << የንጉሥ ልጅ ሆይ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ >> 2 ኛ ሳሙ 13 ፥ 4
የነገሥታት ንጉሥ አምላካችን ሀሳባችንን ሰብስበን በምንማረው ትምህርት፣ በምንዘምረው መዝሙር ፣በምንጸልየው ጸሎት ፍሬ እንድናፈራ ይርዳን ። አሜን !!!
ዲ/ን ምንተስኖት ደንድር
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን❤
""🛑 የዐቢይ ጾም መግቢያ ትምህርት ""
✝እንዴት እንጹም?
(መጋቢት 1 - 2016)
በዩቲዩብ ለምትፈልጉ👉https://youtu.be/3TJdP3s6PB8?si=6oGh5kG5IFTh0s46
ዝክረቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር
/channel/zikirekdusn
4Mb አዳምጡት
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
🗣 << ሰማይ ይስማ ምድርም ታድምጥ👂
የሰማይም መሠረቶች ይደንግጡ።
✝️ በአባቱ ፈቃድ ወረደ። #በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ። #እግዚአብሔር በንጹህ ድንግልናዋ ተወለደ::
✝️ በእንስሳት በረት ተጨመረ። የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ ከእናቱ ጡት ምግብን እየለመነ እንደ ሕጻናት አለቀሰ። >>
•• ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
@slehiwetwe
ታህሳስ 24
በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።
ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።
በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።
ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።
ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
#ሼር
@slehiwetwe
....የቀጠለ 👆
@slehiwetwe ይቀላቀሉን...✝✝
ቅዱስ ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡
#የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)
ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)
ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)
ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)
ቅዱስ ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)
ቅዱስ ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው ቅዱስ ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-
ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ
ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ
ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ
አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ
ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ
ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡
በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)
የቅዱስ ገብርኤል በረከት ይደርብን 🙏
አለም በሰላም እንደማትለቅ ንፁሆች ሲጨማለቁ አየሁና ለኔም ፈራሁ!!
`ብዙ ነገሮች ድርግም ሲሉብኝ እጄን ይዘህ ትመራኛለህ
ከኖርኩ ለክብርህ አኑረኝ አሊያ ግን በሰላም አሰናብተኝ !😔
,,,,,,,,,,
ጌታዬ ወዴት ነው ሀገርህ ?አጠገቤ እንዳለህ ባምንም ልፈልግህ ተገኝተህም አዲስ አንተ ብቻ ነህና!!
@slehiwetwe ይቀላቀሉን
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
`የኀጥእን መመለሱን ነው እንጂ ሞቱን የማትዎድ ሆይ አቤቱ የሚያገለግልህ ልቦናን ስጠኝ።
(ቅዱስ ባስልዮስ)
@slehiwetwe ይቀላቀሉ
`የፈጣሪ እናቱ እመቤቴ ማርያም ሆይ ፤የዘወትር ጥበቀሽ እንዳይለየኝ በምጓዝበት ተጓዥ ፤በማድርበትም ሁሉ ማደሪያሽ በዚያ ይሁን፤በምናገርበትም ጊዜ ተናገሪ፤በተሰማራሁበትም ተሰማሪ፤ጎዳናዬን አስተካክለሽ አሳምሪ ፤.....አሜን
@slehiwetwe ይቀላቀሉን።
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
መልክህን ማየት ተለል ተለል ያደርገኛል።ፍቅርህም ያዝለኛል፤ አንተን መዘከር ያቃጥለኛል። ሁል ጊዜ ስራ ለመስራት ያነቃቃኛል ።አቤቱ ፍቅርህ በልቦና ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ።ሕዋሳቴን ጸጥ አደረጋቸው።
አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን ፳፩
@slehiwetwe
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
በጥንቷ ኢየሩሳሌም ከተማ በጽዮን ተራራ የሚገኝ አንድ ታዋቂ መቃብር አለ። የዲያስፖራ የሺቫ አካል የሆነው ይህ መቃብር በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎችን በየዓመቱ ይቀበላል። ብዙዎቹ ወደ ቦታው የሚሄዱት የጥንታዊው ንጉሥ የዳዊት አፅም በውስጡ እንዳለ በማመን ነው፣ ምንም እንኳን ጥንታዊው ንጉሥ በዚያ እንዳረፈ ምንም ዓይነት አርኪኦሎጂያዊ ማረጋገጫ ባይኖርም። ይህ መቃብር ከእስራኤል በጣም ውድ ሀብቶች አንዱ ነው። ...
@slehiwetwe...ይቀላቀሉ
ጸሎት በምታደርስበት ወቅት ማንም ሰው ሊያናግርህ ቢፈቅድ ወደ መረበሽ እንዳታመራ ጸጥ በማለት መልስ ላለመስጠት አትሞክር። ላናገረህ ሰው አጭርና ግልጥ የሆነ መልስ ሰጥተህ ወደ አቋረጥከው ጸሎት ተመለስ።
(አቡነ ሽኖዳ)
@slehiwetwe
ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
♡YAHWEH PROMOTION♡
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel :- +251943686155
:- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ
ምን ላድርግ..❓
[ በዚህ ዘመን ፈተና የሆነብን ነገር ነው ]
" የዝሙት አሳብ እኔ ሳልፈልገው ይመጣብኛል ከዛም ወደሱ እሳባለሁ.. ምናልባትም ከሃሳብም ዘልዬ የሆኑ ነገሮችን አደርጋለሁ.. ልክ ሲያልፍ መጸጸት እጀምራለሁ..
ምን ላድርግ❓"
1. ሚስት ከሌለህ በጭራሽ ስለ ግንኙነት አታስብ
2. የምታየውን ነገር በጣም ምረጥ.. ፊልም የምታይ ከሆነ ፊልሙ ወደ እንደዚህ አይነት ሙድ ውስጥ የሚከት ነገር በፍጹም ሊኖረው አይገባም.. ትንሽ እንኳን ካለው በቃ አእምሮህ ላይ ተቀምጦ ለወደፊትህም ሌላ ፈተና ይሆንብሃል.. ስለዛ ገና ከጅምሩ አሳቦቹ እንዳይመጡ ተከላከል
3. አንተ ባትፈልገውም አዎ አሳቡ ሊመጣ ይችላል ግን ደግሞ ለዛ አሳብ ተባባሪ አትሁን.. አልወድቅም ብለህ በማሰብ ወይም ማሰቡ ብቻ ችግር የለውም ብለህ ተዘናግተህ በአሳብ ወደዛ አትወሰድ.. ይልቁንም ገና አሳቡ ሲመጣ ራስህን በሌላ ነገር ቢዚ አድርግ..
4. ፈተናው በጣም የከበደ ሲመስልህ የጌታን የስቅለት ስእል እያየህ እንዲህ ብለህ ተናገር፡ "አዎ ፈተናው ብርቱ ነው.. አንተ ግን ከፈተናዎችም ሁሉ በላይ የበረታህ ነህ" ስለዚህም የመስቀሉን ኃይል ትታጠቃለህ
5. ጦርነት ሜዳ ውስጥ ነህና ሁሌም ክርስቶስ በአንተ ኖሮ እንዲዋጋልህ ፍቀድለት.. እርሱ በአንተ ይኖር ዘንድ ንስሐ እየገባህ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ደጋግመህ ተሳተፍ.. ሁሌም አጫጭርም ቢሆን ጸሎት አድርግ..
እና ደግሞ ብቻችሁን አትሁኑ ከሰው ጋር መቀላቀል ያስፈልጋል
እግዚአብሔር ፈተናዎችን ሁሉ ምንቋቋምበት ጽናቱን ይስጠን🙏
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴