slehiwetwe | Unsorted

Telegram-канал slehiwetwe - ቅድስት ፌብሮኒያ

-

ይህ ቻናል ስለ ህይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፋልበት ነው እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል ለማንኛውም ሀሳብ ጥያቄ እና አስተያየት

Subscribe to a channel

ቅድስት ፌብሮኒያ

ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልላክነት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ምሳሌ 5 (Proverbs)
1፤ ልጄ ሆይ፥ ወደ ጥበቤ አድምጥ፤ ጆሮህን ወደ ትምህርቴ መልስ፥
2፤ ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።
3፤ ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና፤
4፤ ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው፥ ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም የተሳለ ነው።
5፤ እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፤
6፤ የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፤ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።
7፤ አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ ከአፌም ቃል አትራቁ።
8፤ መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ፥
9፤ ክብርህ ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ዕድሜህም ለጨካኝ፤
10፤ ሌሎች ከሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም በባዕድ ሰው ቤት እንዳይሆን።
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ምሳሌ 4 (Proverbs)
1፤ እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰባት ነገሮች።

1 ትዕቢተኛ ዓይን
2 ሐሰተኛ ምላስ
3 ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ
4 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ
5 ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር
6 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
7 በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16-19

ከሁሉም ደግሞ 7ተኛውን አብዝቶ ይጠላል።
👉@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

የጊዜያት ባለቤት እግዚአብሔር ሆይ የጨለማውን ግርማ ገፈህ ብርሃኑን እንድመለከት ሰለረዳህኝ በኃጢአቴ ብዛት በሰውነቴ ክፋት ተስፋ ሳትቅርጥ በእድሜ ላይ ይችን ቀን ለንስሐ ሰለጨመርከኝ አመሰግንሃለሁ ።


በመኝታዬም ስለጠበከኝ ከሞት ስለሰወርከኝ እጅ መንሳቴን ለአንተ አቀርባለሁ፡፡ ቸር እረኛዬ ትጉህ የማታንቀላፋ ነህና ሌሊቱን ከእኔ ጋር ሆነህ እንደጠበቅኸኝ ይህንን ማለዳ ባርከህ ቀድስህ የሰላም ውሎ እንድውል ቀኝህ ትርዳኝ፡፡ መንገዴን ሁሉ ከፊት እየሆንክ ምራኝ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ዮሐንስ 15 (John)
18፤ ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።
19፤ ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
👉@Sleiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

1 ቆሮንቶስ 3 (1 Corinthians)
6፤ እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ኢዮብ 42 (Job)
5፤ መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፤
6፤ ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክርስቲያን ቤተሰብ የተወለደ ሰማዕት ነው። አባቱ ዞሮንቶስ እናቱ ቴዎብስትያ ይባላሉ፡፡ አባቱ የዲዮቅልጥያኖስ ሰው ነበር፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአባቱ ሞት በኋላ የአባቱን ሹመት፣ የዓለምን ክብርና ደስታ ንቆ የክርስቶስ ምስከር ሆነ፡፡ በዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ ብዙ መከራ ቢቀበልም እስከ ሞት ድረስ ጸንቶ ለክርስቶስ ታምኖአል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ መከራና ሞት ያልበገረው የክርስቶስ ምስክር ነው፡፡ በጽናቱ በእምነቱ በትዕግሥቱና በፍቅሩ አብነታችን ነው:: በረከቱ አይለየን፡፡

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

መዝሙር 73 (Psalms)
28፤ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ፊልክስዩስ_ክፍል ፪
#ክፍል #ካዕብ
ተስእሎ 17፦ መላእክት ቅዳሴ ቀድሰው ያቆርቡ ዘንድ፣ ሥጋውን ደሙን ለሰው ያቀብሉ ዘንድ ሥልጣን መዓርግ የላቸውም፡፡ ተስእሎ 19፦ ሰው የሚሠራት ትሩፋት ሁሉ በእግዚአብሔር አጋዥነት ትፈጸማለች፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር ሰውን የምትስበው ስለሦስት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ሰውየው ራሱ አስቦ ነው፡፡ ሁለተኛው በትምህርት ነው፡፡ ሦስተኛው መጽሐፍ በመመልከት ነው፡፡ በጎ ሥራ ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሣና ከሰው በጎ ፈቃድ የተነሣ ይፈጸማል፡፡ ሕሊናው ወደበጎ ነገር ሳይሳብ ጸጋ ሰውን አትረዳም፡፡ ወደ ክፉ ነገር ሳይሳብም ጸጋ ሰውን አትለየውም፡፡ ተስእሎ 20፦ በጥምቀት ሥጋውን ደሙን በመቀበል የምትገኝ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ናት እንጂ የራሱ ድካም ብቻ ለሰው አትጠቅመውም፡፡ ከሰይጣናት ጋር የሚዋጋ ሰው ትእዛዛተ እግዚአብሔርን ይጠብቅ፡፡ ተስእሎ 25፦ መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ የሚያደርጉን የትሩፋት ሥራዎች ተስፋ መንግሥተ ሰማያት፣ ይቅርታ፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ሰውን እግዚአብሔርን መውደድ፣ ልበ ሰፊ ነገር አላፊ መሆን፣ ንጽሕና፣ በጎነት፣ ጸሎትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ተስእሎ 26፦ ዘጠኙ ትሩፋት የሚባሉት መንኖ ጥሪት፣ እስከ ሠርክ መጾም፣ ትጋሀ ሌሊት፣ በሰባቱ ጊዜያት መጸለይ፣ መጻሕፍትን መመልከት፣ የውሃት፣ ትሕትና፣ አፍቅሮ ቢጽና አርምሞ ናቸው፡፡ በመንኖ ጥሪት ፍቅረ ንዋይን፣ በከፊለ ኅብስት ሆዳምነትን፣ በትጋህ እንቅልፍን፣ በጸሎት ጨዋታን፣ መጻሕፍትን በመመልከት ክፉ ኅሊናንና ውዳሴ ከንቱን፣ በየውሃት ቁጣ ብስጭትን፣ በትሕትና ትዕቢትን ትዝኅርትን፣ በፍቅረ ቢጽ መጣላትን ምቀኝነትን፣ በዝምታ ነገረ ዘርቅን ድል መንሣት ይገባል፡፡ ተስእሎ 27፦ ሥጋ በሚቀበለው መከራ ነፍስ ብቻ ስለተዋሐደችው የምታዝን የምትደክም አይደለም፡፡ የሚዋጓት አጋንንትም ከእርሷ ይልቅ ይደክማሉ እንጂ፡፡ ጻማሆሙኬ ለቅዱሳን ዘለዓለም ያደክሞሙ ውእቱ ለሰይጣናት፡፡ ባሕታውያን በትሩፋት የሚደክሙት ድካማቸው ሰይጣናትን ያደክማቸዋል፡፡ መላእክት ከእግዚአብሔር ታዘው ሥቃይ ያጸኑባቸዋልና፡፡ ሁለት ታላቅና ታናሽ ወንድማማቾች በአንድነት ሲኖሩ ታላቁ መጽሐፍ እንድመለከትበት መብራት አምጣልኝ አለው፡፡ አብርቶ ሲመጣ ሰይጣን ሰርጅቶ ጣለው፡፡ እርሱ ሲወድቅ መብራቱ ጠፋ ይህ ሊል ብሎ በጥፊ መታው፡፡ ሰይጣን እንዲህ ማድረጉ ብወድቅ ማዘን ይመስል ይመታኛልን ብሎ መልሶ ይመታዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ይለያያሉ ብሎ ነው፡፡ እርሱ ግን ማረኝ እኔ መልሼ አበራዋለሁ አለ፡፡ ጌታም የታናሹን ትዕግሥት አይቶ ያን ሰይጣን በታናሹ መልአከ ዑቃቢ ሲያስገርፈው አድሯል፡፡ ተስእሎ 28፦ ሰይጣናት እንዲፈሩህ ብትወድ ፈቃደ ሥጋን ናቅ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጣንን በስስት ቢመጣት በትዕግሥት፣ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣበት በጸሊአ ንዋይ፣ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና ድል ነሥቶታል፡፡ ሰይጣናት በእጅ ሲያማትቡባቸው ብቻ ሳይሆን እንደ መስቀል ያለ የተመሳቀለ እንጨት የተመሳቀለ ጎዳና ቢያዩ ይፈራሉ፡፡ ሰይጣናት በሐሳብ በፈተኑን ጊዜና በእነዚያ ሐሳቦች ተድላ ደስታን የምናደርግ ከሆነ ኃጢአት ይሆንብናል፡፡ ተስእሎ 29፦ ሰይጣናት የጌታን ስም ሲጠሩባቸው መስቀል ቢያማትቡባቸው አይወዱም፡፡ ለእኛ ጥቅም መከራ ሲያመጡብን ግን ብናማትብባቸውም ላይርቁ ይችላሉ፡፡ ምንም ቢሆን ግን በመስቀል ምልክት ማማተባችንን፣ የክርስቶስን ስም መጥራታችንን መተው የለብንም፡፡ ተስእሎ 30፦ ሰይጣናት አንዳንድ ጊዜ ከተማረው የተማረ ካልተማረው ያልተማረ ጨዋ መስለው ይሄዳሉ፡፡ መላእክትም ዓለማውያን መስለው የሚታዩበት ጊዜ አለ፡፡ የሰይጣናት ሐሰተኛ ምትሐት ነው፡፡ የመላእክት ግን ምትሐት አይደለም፡፡ /channel/slehiwetwe/3235 #መልካም_ቀን ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ሰማዕቷ ፌብሮኒያ

መግቢያ፦ ሰይጣን አራት ነገሮችን ይጠላል እነሱም፦ ትህትና፣ ድንግልና እወቀትና ንጽሕና እነዚህ የምግባራት አምዶች ናቸው፤ በዚህ ዘመን ንጽሕናን ጠብቆ ማቆየት በሰነፎች ቋንቋ "ፋርነት" ሆኗል፡፡ ጠላት በቀላሉ የሚማርካቸው (የሚነጥቃቸው) ተራ ነገሮች ሆነዋል፡፡ በሚያሳዝን መልኩ በዚህ ዘመን ንጽሕናን መጠበቅ የሚታፈርበት የሚያሸማቅቅ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በተለይ በሴት እህቶቻችን የሚስተዋል ነው፡፡ 

ድንግል በዚህ ዘመን ልብስ ክብረ ሳይሆን ግልበ-ክብረ፣ በዕለ-ክብረ ከመሆን ኀሳረ-ክብር ወደ መሆን ተለውጧል፡፡

ራስን መግዛት፦ በክርስትና ሕይወት ራስን መግዛት (መቆጣጠር) ለመንፈሳዊ ሕይወት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ ብዙዎች በኃጢአት ለመውደቃቸው ቃላትን በማሰማመር ካቅሜ በላይ ስለሆነ፣ ስሜቴን መቆጣጠር ስላቃተኝ፣...ወዘተ በሚሉ ቃላት ስንፍናቸውን ለመሸፋፈን፣ ሲሞክሩ እንመለከታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነገረን እግዚአብሔር ራስን የመግዛት መንፈስ ነው የሰጠን፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክታቱ ራስን ስለመግዛት በሰፊው ጽፏል፡፡ "ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ.." (1ቆሮ.7፥5) ብሎም ይመክረናል፡፡ በሌላም ሥፍራ "ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርን በመምሰል በአሁኑ ዘመን አንድንኖር ያስተምረናል..." (ቲቶ.2፥12-13) እውቀት ራስን ከመግዛት ጋር ካልሆነ ከንቱ ነው፡፡ ለዚህም ነው፣ ብዙ ያውቃሉ የምንላቸው ሰዎች ራሳቸውን መግዛት ባለመቻላቸው ክብራቸውን፣ ጸጋቸውን፣ ቅድስናቸው አጥተዋል፡፡ ስለዚህም ነው ሐዋርያው ጴጥሮስ በመልእክቱ "በበጎነትም፣ እውቀትን፣ በእውቀትም፣ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛትም መጽናትን..." (2ጴጥ.1፥6) ጨምራችሁ ያዙ የሚለን፡፡ በአሪት ዘፍጥረት ላይ ተከትቦ የምናነበው የወጣቱ ቅዱስ ዮሴፍ ራስን ስለመግዛት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ በማር ይስሐቅ አባ መትርያኖስ የተባለ መነኮስ የገጠመውን ፈተናና እንዴት ራሱን በመግዛት ራሱንም ሌላውንም ሰው እንዳተረፈ ታሪኩ ከምንጩ እጠቅሳለሁ፡፡ "ከተግባሩ ወደ ቤቱ ሲመለስ ዘማት ተሰብስበው ይህ መነኩሴ ኃያል ነው የሚያስተው የለም አሉ፡፡ አንዲቱ እኔ ባስተውስ ባታስችውስ ተወራርደው መጣች ቀን የሆነ እንደሆነ አይቀበለኝም ብላ ሲመሽ ከደጅ ቆማ እጅ ጸፋች (አንኳኳች)፡፡ ወጽቶ ምንድርነሽ አላት ከሩቅ ሀገር የመጣሁ የእግዚአብሔር እንግዳ የምጸጋበት አጥቼ አለችው ያወጣ ያወርድ ጀመረ ብትገባ ፆር ይነሣብኛል አይሆንም ብላት ነግደ ኮንኩ (እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበልኸኝም) ብሎ ይፈርድብኛል ብሎ ኪፈርድብኝ እታገሠዋለሁ እንጂ ምን አደርጋለሁ ብሎ ይዟት ገባ እሳቱን አነደደላት ተቀመጠች እሱ ጸሎቱን ያዘ ሠውራ ይዛለችና የምትቀባውን ትቀባ የምታጤሰውን ታጤስ ጀመረ እግሩን ከእሳት ጨመረው የሷን መዓዛ እስኪያጠፋው እስኪለውጠው እሷም ይህን ተመልክታ ከዚህ ሁሉ ያደረስኩ እኔ እንጂ ነኝ አባቴ አላበጀሁም ማረኝ ብላ ንስሐ ገብታለች፤ አንድም ገልጻ እንተኛ አለችው ከእሳቱ አንጥፊ አላት ይህማ እሳቱ ይፈጀን የለም አለችው፡፡ የዚህን ዓለም እሳት ካልቻልነው የወዲያኛውን እንደምን እንችለዋለን ይሆንልሽ እንደሆነ አንጥፊው አላት፡፡ ነገሩን አይታ አባቴ አላበጀሁም ማረኝ ብላ ንስሓ ገብታለች ራሷን ላጭቶ አመንኵሶ በዓቱን ለቆ ወፅቶ ሂዷል፡፡" ( ማር ይስሐቅ፣ ገጽ14 1982 ከፊል አጽንኦት የእኔ ነው) ራስን መግዛት ከላይ እንደተመለከትነው ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ከኃጢአት መጠበቅ፣ መጽናት ወሳኝ ምግባር ነው፤ ፈጣሪ ይህንን እንዲሰጠን መለመን መማጸን በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡

     ፌብሮኒያ ስለ ንጽሕናና ስለ ድንግልና ስትል ሞትን የመረጠች የሴት ጀግና ናት፡፡

በ749 ዓ/ም በግብጽ ላይ ስቃይ በወረደ ጊዜ በላዕላይ ግብጽ ከነገሱት የአማዊን ገዥዎች መካከል የመጨረሻው ገዥ የነበረው ማራዋን ኢቢን መሐመድ ኤክሚም የምትባለው ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች ገዳም ገቡ፡፡ በገዳሙ ውስጥ ያለውን ማንኛውም ዓይነት ንብረት ከዘረፋ በኋላ ፌብሮኒያ የተባለችውን ቆንጆና ድንግላዊት መነኩሲት ሊደፍሯት ፈለጉ፡፡

.
ፌብሮኒያ ራሷን ጨካኝና ግፈኛ የሆኑት ወታደሮች ፊት ለፊት አቀረበችና ወደ በአቷ ደርሳ የምትመለስበትን ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዲሰጧት ጠየቀቻቸው፡፡ ወደ በአቷ ከገባች በኋላ ራሷን በእግዚአብሔር እጆች ላይ በመጣል አለቀሰችና እርሱ እንዲመራትና አብሯት እንዲሆን ጠየቀችው፡፡

.
ከዚህ በኋላ ከበአቷ ወጣችና አስቀድማ በምሥጢር ጠብቃ ያቆየችውን በብልቃጥ ውስጥ የታሸገ ዘይት አሳየቻቸው፡፡ ከዚያም ማንኛውም ሰው በዚህ ብልቃጥ ውስጥ ያለውን ዘይት በሰውነቱ ላይ ቢቀባው የተቀባውን የሰውነቱን ክፍል ሰይፍ ሊቆጥረው አይችልም አለቻቸው፡፡ ይህን ለእነርሱ ለማረጋገጥም አንገቷን በዘይቱ ቀብታ ስታበቃ ከወታደሮቹ አንዱ ሰይፉን በአንገቷ ላይ እንዲቃጣ ጠየቀችው፡፡

ወታደሩ የተነገረውን ሲያደርግ ወዲያውኑ ጭንቅላቷ ከሌላው የሰውነቷ ክፍል ተከልሎ ወደቀ፡፡ በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ የሆነውን ነገር ሲመለከቱ እጅግ ስለ ተሰቀቁ የዘረፉትን ንብረት በሙሉ እዚያው ተዉና ከገዳሙ ወጥተው ሄዱ፡፡


#መልካም_ቀን!

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

♡YAHWEH PROMOTION♡

↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
              ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel      :- +251943686155
  :- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ቀን በቀን የከሳንበት ምክንያት ?


          የንጉሥ ዳዊት ልጅ አምኖን የንጉሥ ልጅ እንደመሆኑ የተመጣጠኑ ምግቦች ፣ ከሁሉም የተለየ እና የተመቻቸ አልጋ ፣ እንዲሁም የሚዝናናበት መናፈሻ ከዚህ የበለጡ ብዙ ነገሮች የተሟሉለት ልጅ ነበረ ። ነገር ግን የተመጣጠነ እና ብዙ አይነት ያላቸውን ምግቦች በቀን በቀን እየተመገበ ፣ የተንደላቀቀ እና ውብ የሆነ አልጋ ላይ በቀን በቀን  እየተኛ ፣ በሰፊ  ቤተ መንግሥት ውስጥ እየኖረ ቀን በቀን ከመክሳት ውጪ በሰውነቱ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም ። ለዛም ነው ይህንን ነገር ያስተዋለው የአምኖን ጓደኛ ኢዮናዳብ <<የንጉሥ ልጅ ሆይ ስለምን ቀን በቀን ትከሳለህ ? >> ብሎ አምኖንን የጠየቀው ።

አምኖን የንጉሥ ልጅ ሲሆን  በምን ምክንያት የከሳ ይመስላችሗል ? እስቲ አምኖንን የንጉሥ ልጅ ሆነህ ሳለህ ለምን ቀን በቀን ከሳህ ? ሁሉ በደጅህ ሁሉ በእጅህ ሆኖ ሳለ ምንም ነገር እንዳላገኘ ሰው ለምን ከሳህ እንበለው ? በዚህ ጊዜ አምኖን እኔ የከሳሁት <እኅቴ ትእማርን ወድጄያት ነው> ብሎ ይመልስልናል ።

እውነቱን ነው አምኖን በዛ በሰፊው  ቤተ መንግሥት  ሰውነቱ የከሳው የተለያዩ ምግቦች አጥቶ አልያም የማይመች አልጋ ላይ ተኝቶ ወይም ደግሞ ሚዝናናበት ቦታ አጥቶ አይደለም ። ይልቁንም እነዚህን ነገሮች በአባቱ  ቤተ መንግሥት ውስጥ  በስፋት ና ሁል ጊዜ ቢያገኛቸውም ቅሉ ግን አምኖን ሐሳቡን ሌላ ቦታ አድርጎ ስለሚጠቀምባቸው ነው ቀን በቀን ሊከሳ የቻለው ።

እኛ  እንደ አምኖን የንጉሥ ልጅ አይደለን ? ስለምን ይህን ነገር ለእኛ ትነግረናለህ ልትሉኝ ትችላላችሁ ? እኔም እላችሗለሁ እናንተ የአምኖን አባት ንጉሡ ዳዊት  ንጉሤ ፣ አምላኬ ፣ መጠግያዬ ብሎ የጠራው የነገሥታት ንጉሥ ፣ የጌቶች ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ።

ንጉሡ ዳዊት ለአምኖን ልጁ ስለሆነ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ብዙ ነገሮችን አርግቶለታል የእኛ ንጉሥ እግዚአብሔርም ዳዊት ለአምኖን ካደረገው የበለጠ ለእኛ ብዙ ነገሮችን አርጎልና ።እግዚአብሔር ለእኛ ምድር ላይ ባለችው አገልጋዩ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ምን ያላደረገልን ነገር አለ ? ከመዝሙሩ መዝሙር አልከለከለን ዘማሪዎች ነን ፣ ከአብነት ትምህርቱ አብነት ትምህርት አልከለከልን ዲያቆናት ነን ፣ እንደ ዳዊት በገና አልከለከለንም ፣ እንደ ሰሎሞን ጥበብን አልነፈገንም ፣ ጃንጀረባው ባኮስን እንዲያስተምረው ፊልጶስን እንደላከለት ለእኛም የሚያስተምሩን መምህራንን አልከለከለንም ።

ይህ ሁሉ ነገር ታርጎልን ሳለ ግን ለምን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ቀን በቀን እንከሳለን ? ለምንስ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለውጥ አላመጣንም ? እስቲ መለስ ብለን የአምኖንን ታሪክ እንመልከት ? አምኖን ምንም እንኳን የተመቻቹ ነገሮችን ቢያደርግም እኅቱ ትእማርን በመውደዱ እነዚያን ነገሮች ከልቡ አልነበረም ያደርጋቸው የነበረው ምግብ ቢበላም ፣ የተመቻቸ አልጋ ላይ ቢተኛም ከልቡ አልነበረምና ሀሳቡ ሌላ ነገር ላይ ስለነበረ እነዚህ ነገሮች ለእሱ ለውጥ ሊያመጡለት አልቻሉም።

እኛም ትምህርትን ብንማርም ፣ በገናን ብንደረድርም ፣ መዝሙረ ዳዊትን ብንደግምም ፣ መዝሙርን ብንዘምርም ይህን ሁሉ ነገር በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ እንደ ልባችን አግኝተን ብናረጋቸውም ሀሳባችን ሌላ ነገር ላይ ስለሆነ ለውጥ ልናመጣባቸው አልቻልም ። በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለውጥ የማናመጣው ሀሳባችን ሌላ ሆኖ ተግባራችን ሌላ ስለሆነ ነው  እንጂ ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳጣችን ነገር ኖሮ አልያም ሳንማር ፣ሳንዘምር ቀርተን አይደለም ።

ለአምኖን የተጠየቀውን ጥያቄ እስቲ እኛም እንጠየቅና ችግራችንን እንቅረፍ ። ጥያቄውም ምንድነው ?ክርስቲያን ሆነህ(ሽ) ይልቁንም የሰንበት ተማሪ ሆነህ(ሽ) ቀን በቀን መንፈሳዊ ሕይወትህ(ሽ) ስለምን ለውጥ አላመጣም ? ለምን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሳን። አምኖን የተጠየቀው ይሄንን ነው። << የንጉሥ ልጅ ሆይ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ >>  2 ኛ ሳሙ 13 ፥ 4

የነገሥታት ንጉሥ አምላካችን ሀሳባችንን ሰብስበን በምንማረው ትምህርት፣ በምንዘምረው መዝሙር ፣በምንጸልየው ጸሎት  ፍሬ እንድናፈራ ይርዳን ። አሜን !!!

ዲ/ን ምንተስኖት ደንድር

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን❤

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

""🛑 የዐቢይ ጾም መግቢያ ትምህርት ""

✝እንዴት እንጹም?

(መጋቢት 1 - 2016)

በዩቲዩብ ለምትፈልጉ👉https://youtu.be/3TJdP3s6PB8?si=6oGh5kG5IFTh0s46


ዝክረቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

/channel/zikirekdusn

4Mb አዳምጡት

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

https://vm.tiktok.com/ZMhrYMHrp/

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንኳን አደረሳችሁ
‹‹ቅዱስ መስቀል ››
‹‹…ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠኀቸው …›› መዝ 59፣ 4
ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያቢሎስ እናመልጥ ዘንድ ድል እናደርገው ዘንድ የተሰጠን ነው ፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን ፣የሰላም አርማችን ነው፤፡፡‹‹..እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው፡፡ ›› ኤፌ 2፣14-16
ቅዱስ መስቀል በዘባነ ኪሩብ ላይ የሚቆም የጌታችን እግሮች ተቸንክረው የዋሉበት የመድኅን ዓለም ክርስቶስ ዙፋን ነው፤ቅዱስ መስቀል ዲያቢሎስ ያፈረበት ሞተ ነፍስ ድል የተደረገበት ፣የሕይወት መንገዳችን እንቅፋት የነበረው ጠላታችን ዲያቢሎስ ከመንገዳችን ተጠርቆ የተወገደበት ፣በእኛ ላይ የነበረው ኃይል የተነጠቀበት ነው ‹‹… በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዝት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወገደው….›› ቆላ 2፣14 ፤
ቅዱስ መስቀል የመድኃኒታችንን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የተፈተተበት  ፣የእናቱ እመቤታችንን እናትነት የምናስታውስበት ነው፤‹‹ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ የእናቱም እኅት የቀለዮጵያም ሚስት ማርያም መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ አላት፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን እናትህ እነኋት አለው›› ( ዮሐ 19፣27)
ቅዱስ መስቀል በበደላችን ከገነት በወጣን ጊዜ በእሳት ሰይፍ ታጥራ የነረችው ገነት በክርስቶስ ሞት እንደተከፈተችልን ዳግመኛ እንኖርባት ዘንድ እንደተሰጠችን ያስታውሰናል‹‹…ኢየሱስም እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው…›› ( ፤ሉቃ 23፣43)
ቅዱስ መስቀል ሥራችንን ሁሉ የምንባርክበት ትምክህታችን ነው ፤ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናንን በላከው መልእክቱ ‹‹..  ዓለም ለእኔ ተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልኩበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ ›› ገላ 6፣14 
‹‹…እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን ..›› መዝ 131፣7
የመድኅን ዓለም ክርስቶስ እግሮቹ በቅዱስ መስቀል ላይ በዕለተ ዐርብ ተቸንክረውበታል በክቡር ደሙ ተቀድሷልና የጸጋን ስግደት እንሰግድለታለን ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን በጸሎቷ ምስጋናን ስታቀርብ ‹‹..እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር…›› ‹‹ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት በክቡር ደሙ ለቀደሰው  መስቀል እሰግዳለው በማለት ምዕመናንን ለቅዱስ መስቀሉ የአክብሮት ጸጋ ስግደት እንዲሰግዱ ሥርዓትን ያበጀች፡፡
         መልካም በዓል !
በዲ/ን ተስፋዬ ቻይ( ሱላሜ)
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።🔥✝️✝️🔥

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87 @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ውድ እህቴ ኦርቶዶክሳዊ ኑሮ ለመኖር የምትፈልጊ ከሆነ የምነግርሽን ነገር አድምጪኝ። ሁልጊዜም በተወሰነ ሰዓት የመንቃት ልምድ ይኑርሽ :: በማለዳ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ከአልጋሽም ለመነሳት ምክንያተኝነትን ከአንቺ አስወግጂ :: ከእንቅልፍሽም በነቃሽ ጊዜ የተሰቀለውን ጌታችንን በመስቀል ላይ እንዳለ አድርገህ አስቢ :: ራስሽን በብርድ ልብስ ሙቀት አታታይ :: ከመኝታሽ አፈፍ ብለሽ ተነሽ :: በሠራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሐር ፊት ልትቆሚ መሆኑን አስቢ:: ሁልጊዜም የእናትሽን የሔዋንን ውድቀት ያስታውሽ :: አምላክሽን የሚያስብ በጎ ኅሊና እንዲኖርሽ አባትሽ አዳም ተጠልፎ በወደቀበት የሥጋ ሐሳብ ተጠልፈሽ እንዳትወድቂ ፈጣሪሽን ለምኝው።
👉@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ
ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ የሚደሰትባችሁ ለመሆን ያብቃችሁ
ክርስቲያን ለመሆን ሁላችንም ያብቃን መልካም አዲስ አመት🤗።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
             ወርሐ ጳጉሜ
ወርሐ ጳጉሜ በዓመቱ መጨረሻ የምትገኝ በአገራችን ኢትዮጵያ እንደ 13ኛ ወር የምትቆጠር ናት ፤ወርሐ ጳጉሜ 5 ቀናት ያሏት ስትሆን በ4 ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ሉቃስ መውጫ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ያለው 6ቀን ይሆናል፡፡ ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ተውሳክ 5ቀን፣ ሩብ ፤ከዐውደ ወር ተርፎ በዓመቱ መጨረሻ የተጨመረ ስለሆነ ትርፍ ተጨማሪ ይባላል፤ወርሐ ጳጉሜ ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች በዚህ ወቅት ጻድቁ ኢዮብ በባህረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ በሰውነቱ የነበረው ደዌ ዘለክብር የዳነለት ወቅት በመሆኑ እንዲሁም ብዙዎችም ከህመም የተፈወሱባት ወቅት በመሆኗ ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች ፤ምዕመናን ይህን ትውፊት መሠረት አድርገው በዚህች ወቅት ፀበል ይጠበሉባታል( ይጠመቁበታል) ፡፡
በወርሐ ጳጉሜ ምዕመናን በፈቃዳቸው ይጾሙባታል ፤መጪው ዘመን እንዲባረክ ፣ስለቀደመው ኃጢአት እያዘኑ በጾም በጸሎት ፈጣሪን እየተማጸኑ ያሳልፏታል፤በትውፊት በዚህች ወር የሚጾመውን ጾም ጾመ ዮዲት ይባላል ፤ሆሊፎርኒስ የተባለ የናቡከደኖጾር ቢትወደድ የእስራኤልን ልጆች ምንጭ ይዞ ሕዝቡን ባስጨነቀ ጊዜ ተስፋ ቆርጠው ለጠላት ምርኮ እንግባ አሉ አግዚአብሔርን የምትፈራ በጾም በጸሎት ተወስና የምትኖር ዮዲት የተባለች ደገኛ ሴት ሕዝቡ እንዲጾም እንዲጸለይ አስደርጋ  ከጠላት ከተማ ገብታ በጥበብ የአስጨናቂዎቻቸውን የሆሊፎርኒስን  ቸብቸቦ( ራስ ቆርጣ) ወገኖቿ ድል እንዲቀዳጁ አደረገች ፡፡ ( መጽ ዮዲ 13፣4-5) ምዕመናን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ፣የዮዲትን የእምነት ጽናት፣የጾም ጸሎትን ጥቅም ተረድተው ስለ ግል ሕይወታቸው ፣ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ አገር ፍቅር ሰላም ብለው በፈቃዳቸው ወርሐ ጳጉሜን በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ ፡፡
ይቆየን !
ሱላሜ( ዲ/ን ተስፋዬ ቻይ)

👉 @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

የጳጉሜን ወር ለፍጹም የንስሐ ሕይወት!

+++

"ስለ ምን ትሞታላችሁ?"

+++

"... ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ
አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤
የእስራኤል ቤት ሆይ፥
ስለ ምን ትሞታላችሁ?

የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤
ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።"

ትንቢተ ሕዝቅኤል 18 : 30 - 32

+++

መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

ሰቆቃው ኤርምያስ 3 : 40

+++ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ልደቱ_ለአቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ

በትንቢት ‹‹ከአንዲት ሴት ልጅ በጸሎቱ ዓለምን የሚያድን፣ በአማላጅነቱ ነፍሳትን የሚዋጅ ልጅ ይወለዳል›› ተብሎ ከተነገረ ከብዙ ዘመን በኋላ እግዚአብሔርን የምታመልክ ስሟ ማርያም ሞገሳ የምትባል ሴት ልጅ ተወለደች ያችንም ሴት ልጅ እናትና አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በዕውቀት አሳደጓት ዕድሜዋም ለትዳር ሲደርስ እናትና አባቷ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ስሙ ደመ ክርስቶስ ለሚባል ሰው ዳሯት በዚያን ጊዜ ስልጣኑ ከሰማይ የሆነና ክብሩ እጅግም የሆነ ልጅ ጸነሰች እርሱን ከጸነሰች ጊዜ ጀምሮ እስክትወልደው ድረስም ልብሷን አትታጠቅም፤ ለወገቧም መቀነትን አትፈልግም ነበር በእናቱ ማኅፀን ተአምራትን እንዳደረገ እንደ ዘካርያስ ልጅ እንደ ዮሐንስ በደስታ እየሰገደ በእናቱ ማኅፀን ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ነበርና እርሷም የመውለጃዋ ቀን እስኪደርስ በጾምና በጸሎት ተወስና ስታገለግል ኖረች።

በነሐሴ ፳፯ ቀን በሰው ዘንድ የተናቀ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ይህንን ክቡር ጻድቅ ወለደችው በተወለደም ጊዜ በእናትና አባቱ እንዲሁም በሀገሩ ሰዎችም ዘንድ ደስታ ሆነ እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ግብዣ አደረጉ ይህም ጻድቅ ባሕታዊ በተወለደበት (ክርስትና) በተነሳበት ቀን በካህናት አፍ ጸጋ ክርስቶስ ተባለ የኃጢአት ማሠሪያን ሁሉ ያሥርና ይፈታ ዘንድ ጵጵስና በሾመው ጊዜ እግዚአብሔር ያወጣለት ሁለተኛው ስሙ ዘርዓ ቡሩክ ነው ሦስተኛ ስሙ ደግሞ ጸጋ ኢየሱስ (በጸሎት ተደጋግሞ ብዙ ይገኛል) ይባላል።

ከልደቱ በኋላ ያንንም ሕጻን አባቱና እናቱ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በአምልኮት እና በዕውቀት አሳደጉት:: ሰባት ዓመት ሲሆነው የሚያልፈውንና የሚጠፋውን ዓለም ሁሉ እንዳያይ ዓይኖቹ ታወሩ የልጃቸው ዓይኖች በጠፉበት ቀን እናትና አባቱ አዘኑ ታውሮም በቤታቸው አንዲት ዓመት ኖረ ከተወለደ ሰባት ዓመት ሲሆነው ረቡዕና ዓርብን መጾም ጀመረ እናትና አባቱም በተወለደ በሰባት ዓመቱ ሲጾም ባዩት ጊዜ ኀዘናቸው ወደ ደስታ ተለወጠ ከዚህም በኋላ በእኒህ እንዲተዳደር ብሎ እንደተናገረው መጽሐፍትን ቢማር ያለበትን ነውር እንደሚሰውር እና በእነዚህም እንዲተዳደር አውቀው የቤተ ክርስቲያንን መጽሐፍት ሁሉ እንዲያስተምረው ለመምህር ሊሰጡት ተማከሩ እርሱ ሲማር እግዚአብሔር ብርቱ መከራንና የሚያስጨንቅ በሽታ አመጣበት አባትና እናቱም በልጃቸው ላይ የሆነውን ነገር አይተው ዓይኖቹ የታወሩ ‹‹ይህ ልጃችን በምን ይተዳደራል? በዚህ ዓለምስ አኗኗሩ እንደምን ይሆናል?›› ብለው ታላቅ ኀዘንን አዘኑ እግዚአብሔርም ከእርሱ (ከእግዚአብሔር) በቀር መጻሕፍትን ሁሉ ከማንም እንዲማር እንዳልፈቀደለት ፈጽመው አስተውለው አላወቁም ነበር ይህ ትንሽ ሕጻን ግን ለአባትና ለእናቱ ሲታዘዝ (ሲያገለግላቸው) ኖረ::

ሐዋርያትም በሲኖዶሳቸው እንዳዘዙት ከተወለደ ፲፪ ዓመት ሲሆነው ይጾም ነበር
ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነውም በኋላ የጌታችንን ጾም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ማርያምን ጾም፣ ሐዋርያት የሠሩትን ጾም፣ ሁሉ መጾም ጀመረ አባትና እናቱም በዐሥራ ሁለት ዓመቱ ጾሙን ሁሉ ሲጾም አይተው ተደሰቱ ይህ ሕጻን ልጃቸው በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንደጸና አላወቁም እግዚአብሔር አምላክም ለዚህ ጻድቅ አባት መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን፤ መጻሕፍተ ሊቃውንትንና መጻሕፍተ መነኮሳትንም፤ አዋልድ መጻሕፍትንም፤ የመላእክትንና የሰውን ነገር (ፍትኅን ሁሉ፤ የማኅሌታይ የቅዱስ ያሬድንም ዜማ) ገለጠለት፤ እግዚአብሔር ይህንን ድንቅ ተአምራት ለወዳጁ ለብፁዕ አባታችን ለአቡነ ዘርዐ ብሩክ የሰጠው ገና በልጅነቱ ነበር።

ለእኛም ፈጣሪያችን እንዲሁ ተአምራትን ያድርግልን፤ በመከራችን ጊዜ ደስታን ያሰማን፤ ለእርሱ እንደገለጠለት መጻሕፍትን ሁሉ ይግለጥልን፤ መታሰብያውን ለምናደርግ፣ ስሙንም ለምንጠራ እና በጸሎቱ ለምንማጸን ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቹ በጻድቁ ጸሎት ነፍሳችንን ይማርልን!

#በፍኖተ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀ። @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ፊልክስዩስ_ክፍል ፬
#ክፍል #ራብዕ
ተስእሎ 39፦ ወጣንያን መነኮሳት በማኅበር ሳሉ ፍቅረ ቢጽን ለመፈጸም ጸንተው ይረዳሉ፡፡ በተባሕትዎ ጊዜ በፍቅረ እግዚአብሔር ፍጹማን ይሆናሉ፡፡ ፍቅር ፍጹም ሕግ ነውና፡፡ ክፉ ፈቃዱን ክፉ ልማዱን ያልተወ ፍቅረ እግዚአብሔርን ይፈጽም ዘንድ አይቻለውም፡፡ ተስእሎ 44፦ የአበው ነገራቸው አይለያይም፡፡ ለሰው ሁሉ ለአንዱም ለአንዱም የሚሻለውንና የሚበልጠውን እንዲሁም ለእርሱ የሚስማማውን የሚረባውን የሚጠቅመውን ሥራ ያስተምሩታል እንጂ፡፡ ተስእሎ 47፦ የቀደመችዪቱ ሕገ ኦሪት ከኀልዮ ኃጢአት ከፈቃደ ሥጋ ትከለክል ዘንድ አይቻላትም ነበር፡፡ ለክፉ ኅሊናህ እሺ በጎ ብለህ አትታዘዝለት፡፡ ልቡናህም በኀዘን በቀቢፀ ተስፋ አትበጣበጥ፡፡ ተስእሎ 49፦ ከቀሩት ኃጣውእ ሁሉ ውዳሴ ከንቱ ፍጹማንን ይጎዳቸዋል፡፡ ውዳሴ ከንቱ ትዕቢትን ያመጣል፡፡ አባ ወቅሪስ ትዕቢትን ዳሞትራ እባብ ይለዋል፡፡ ዳሞትራ ከአንድ ላይ የነደፈ እንደሆነ በሰውነት ሁሉ ተሰራጭቶ ይገድላል፡፡ ውዳሴ ከንቱ ኃይለኛውን ደካማ ያደርጋል፡፡ ብዙ ምሕረት ብዙ ተግሣጽ የውዳሴ ከንቱ ጾርን ያጠፋል፡፡ ከውዳሴ ከንቱ ምቀኝነት፣ ፉክክር፣ ተንኮል፣ እኔ ያልኩት ይሁን ብሎ በነገር ማሸነፍን መውደድ፣ መጣላት፣ ማድላት፣ ቂም፣ በቀል፣ ሐሰት፣ አጥብቆ ድፍረት እና የመሳሰሉ ኃጢአቶች ይወለዳሉ፡፡ ውዳሴ ከንቱን ያሸነፈ ሰው ስድቡን ተዋርዶውን ቸል ይላል፡፡ አባ ታድራ እኛስ የጌታን ፈቃድ መፈጸም እንጂ የሰውን ፈቃድ መፈጸም የምንወድ አይደለንም አለ፡፡ ተስእሎ 51፦ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለበቁ ሰዎች በልዩ ልዩ አምሳል ትታያለች፡፡ ተስእሎ 52፦ ሰይጣናት ድኩማን አኃውን ጋሻ መከታ አድርገው አንዳንድ ጊዜ በመንቀፍ አንዳንድ ጊዜ በሌላ ጾር ፍጹማንን ይዋጓቸዋል፡፡ ተስእሎ 54፦ የነፍስ ሕይወቷ ወደጌታ መቅረብ ነው፡፡ ይህም ሁልጊዜ ጌታን በማሰብ ይገኛል፡፡ ተስእሎ 58፦ ለትዕግሥት በኵር የሆነንን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት እናድርግ፡፡ እኛ እርሱን መስለን መከራን ብንቀበል ከእርሱ ጋራ እንደ እርሱ እንከብራለን፡፡ እርሱን መስለን ስድቡን ብንታገሥ ከእርሱ ጋራ እንደእርሱ እንሠለጥናለን፡፡ ሥቃይ ለሚያጸኑባችሁ ሰዎች ሥርየት ለምኑላቸው፡፡ ስንታገሥ ሰይጣናት የሚያመጡብንን ጦር ድል እንነሣለን፡፡ ሲሰድቡን ደስ ይበለን፡፡ ለሰደቡን ሰዎችም ሥርየትን እንለምንላቸው፡፡ ተስእሎ 61፦ አባ አጋቶን በአንደበቱ እንዳይናገር ሠላሳ ዓመት ሙሉ ጠጠር ጎርሶ ይኖር ነበር፡፡ ሊመክር ሲፈልግ፣ ለጸሎት ሲነሣና ማዕድ ሲቀርብ ግን ጠጠሯን አውጥቶ ይይዛት ነበር፡፡

© በትረ ማርያም አበባው @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ፊልክስዩስ_ክፍል ፫
#ክፍል #ሣልስ
ተስእሎ 31፦ ሰው ራሱን ንጹሕ ነኝ ካለ ትዕቢተኛ ነው፡፡ ከኃጥኣን ይልቅ እኔ ፍጹም ነኝ ካለ ትዕቢተኛ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወፍ ጫጩቶቿን እናት ልጆቿን እንደምትጠብቅ ምእመናንን ይጠብቃቸዋል፡፡ ሐዋርያም ብትሆን ይሁዳ በፍቅረ ንዋይ እንደተሰነካከለ አስብ፡፡ ወንበዴ ብታይ ነፍሰ ገዳይም ብታይ በል በአይቴ አአምር ለእመ ኮነ ይበድረኒ በዊአ ኀበ ገነት ከመ ፈያታዊ ዘየማን፡፡ አዳምን ቀድሞት እንደገባው ወንበዴ ንስሓ ገብቶ ቀድሞኝ ገነት ይገባ እንደሆነ እኔ ምን አውቃለሁ በል፡፡ ዘማዊ ብታይ ኃጥእም ብታይ ክርስቶስን ይወደው እንደሆነ በምን አውቃለሁ በል፡፡ ከእኔ ይልቅ ስለኃጢአቱ ያዝን ያለቅስ እንደሆነ ምን አውቃለሁ በል፡፡ ሁልጊዜ እንዲህ የሚያስብ ሰው ከፍቅረ እግዚአብሔር ተለይቶ አይወርድም፡፡ ተስእሎ 32፦ ከገቢረ ኃጢአት ለማድረስ መጀመሪያ የታሰበችውን ነቅዐ ኀልዮ ድል የነሣ ከእርሷ በኋላ የሚመጣው ጾር ይጠፋለታል፡፡ ተስእሎ 34፦ ትእቢትና ከንቱ ውዳሴ ከእግዚአብሔር ይለያሉ፡፡ ቁጣ የሚፈትነውን ሰው ሰይጣነ ቊጥዓ ከልቡ ላይ ሆኖ ተቆጣ ተቆጣ ይለዋል፡፡ ጠማማ ነገርን የሚናገረውን ሰው ደግሞ ከአንደበቱ ላይ ሆኖ ተናገር ተናገር ይለዋል፡፡ በጸሎት ጊዜ የሚያንቀላፋውን ደግሞ ከዓይኑ ላይ ሆኖ ተኛ ተኛ ይለዋል፡፡ ሌባውን ከእጁ ላይ ሆኖ አንሣ አንሣ ይለዋል፡፡ ተስእሎ 38፦ ከምግቡ የማይከፍል ይልቁንም ብዙ ውሃ ከመጠጣት የማይከለከል ሰው ሰይጣነ ዝሙትን ድል አይነሳውም፡፡

© በትረ ማርያም አበባው /channel/slehiwetwe/3235 #መልካም_ቀን ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

#ፊልክስዩስ_ክፍል ፩
ፊልክስዩስ ማለት ገብረ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ አንድም መፍቀሬ አኃው ማለት ነው፡፡ ሀገሩ ሶርያ ነው፡፡ ጌታ ለአበው ትምህርት የሚሆነውን ነገር በማናቸውም ባልበቃ ሰው አድሮ መናገር ልማዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር የእኛን ድኅነት ይወዳል ነገር ግን ፈቃዱን ባለመፈጸማችን ከድኅነት እንርቃለን፡፡ ዲያብሎስ ደግሞ የእኛን ጥፋት ይወዳል፡፡ እኛም ፈቃዱን ፈጽመን በፈቃዳችን እንጠፋለን፡፡ ነገር ግን እንዲህ መሆን የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ሰውን ይጠቀም ብሎ በሕገ ልቡና ፈጠረው፡፡ በዚያ መጠቀም ባይሆንለት ሕገ ኦሪትን ሠራለት፡፡ ኋላ ደግሞ በዚያ መጽደቅ ባይቻለው ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ ሰው ሆኖ ሥጋ ለብሶ ሕገ ወንጌልን ሠራ፡፡ ሥጋውን ደሙን ሰጠ፡፡
#ክፍል #ቀዳማዊ
ተስእሎ 1፦ ጸሎተ ሥጋ በአንሳሕስሖ ከናፍር ጸሎተ ነፍስ ያለ አንሳሕስሖ ከናፍር የሚጸለይ ነው፡፡ ጸሎተ ልብ ካልደረሱበት አይታወቅም፡፡ ጾም የሚለው ደግሞ ውሎ ውሎ መብላትን፣ ሲርብ መተውን፣ ምግብ አለማሻሻልን፣ ጊዜ አለመለዋወጥን ነው፡፡ ሁሉን ጥሎ ጌታን የተከተለ ሥራው ፍጹም ነው፡፡ አብርሃም እንግዳ መቀበልን ይወድ ነበር እግዚአብሔርም በረድኤት አደረበት፡፡ ዳዊትም ትሑት ነበር እግዚአብሔር በረድኤት አደረበት፡፡ ኤልያስም ከሰው መለየትን ብቸኝነትን ይወድ ነበር እግዚአብሔር በረድኤት አደረበት፡፡ ደዌ ዘንጽሕ የሚባለው እንደ ጢሞቴዎስ ግብር (ሱባኤ) ገብተው የሚያመጡት የፈቃድ ደዌ ነው፡፡ ተስእሎ 3፦ ፍቅረ ዓለምን ፍቅረ ንዋይን ተው፡፡ ጻድቃን የሰይጣንን ጾርና የባሕርይን ጾር ታገሡ፡፡ ፈቃደ ሥጋን ድል ነሡ፡፡ በትምህርት ውዳሴ ከንቱ የለም፡፡ ከትሩፋተ ሥጋ ትሩፋተ ነፍስ ይበልጣል፡፡ ወአፍቅሮ እግዚአብሔር ይኄይስ እምአፍቅሮ ፍጡራን፡፡ ፍጡራንን ከመውደድ እግዚአብሔርን መውደድ ይበልጣል፡፡ ተስእሎ 4፦ ጌታ ዋጋ የሚሰጥ እንደ ኅሊና ቅንነት መጠን ነው፡፡ ተስእሎ 5፦ በሰው ዘንድ ስሙ በበጎ የሚጠራ (ሠናየ ዝክር) ብዙ ኃጢአትን እየሠራ እግዚአብሔርን የሚያሳዝነው ሰው ነበረ፡፡ ሲሞት ወደ ገሀነም ገባ፡፡ በዓለ መቅጹትም ወርቅ ሳለው በደዌው ጊዜ የለኝም ብሏቸው አኃው በተልዕኮ ያመጡትን ገንዘብ እያወጣጡ ይረዱት ነበር፡፡ በጊዜ ሞቱ አኃውን ጠርቶ ወርቁን በአንድ ወገን ቀብሮ እንዳይታይበት ይህንም አትንኩ ይህንም አትንኩ የትሩፋት ደሜ የነጠበበት ይህ ነውና ከዚህ ላይ ቅበሩኝ አላቸው፡፡ ከቀበሩት በኋላ ወርቁ ተቃጥሎ ሬሳውን ማቃጠል ጀመረ፡፡ ቢቆፍሩት ወርቅ ሲያቃጥለው አዩ፡፡ ሠናየ ዝክርን ትዕቢት በዐለ መቅጹትን ፍቅረ ንዋይ ጎዳቸው፡፡ አባ ስልዋኖስ እስከ አፍንጫው የሚወርድ የማቅ ቆብ ሰፍቶ ምንም ምን ሳያይ ይኖር ነበር፡፡ ይቅርታህን ቸርነትህን ስጠን ብለን እግዚአብሔርን እንለምነው፡፡ ተስእሎ 7፦ አሞንዮስ ጾር በተነሣበት ጊዜ ጾር የሚነሣበትን አካሉን በእሳት ይተኩሰው ነበር፡፡ ኤጲስ ቆጶስነትንም ግድ እንሹምህ ባሉት ጊዜ ግራ ጆሮውን ቆረጠው፡፡ መልከ መልካም መባልን ስለጠላ መልከ ክፉ ይበሉኝ ብሎ ይህን አደረገ፡፡ ተስእሎ 8፦ የጻድቃን ነፍሳት ከሥጋቸው በተለዩ ጊዜ ወደ ገነት ይሄዳሉ፡፡ ተስእሎ 10፦ አባ መቃራ እለእስክንድራዊ ከተጠመቀ ጀምሮ እስከ ስልሳ ዓመት ስለክብረ ቁርባን ምራቁን እንትፍ ብሎ አያውቅም፡፡ ሥጋውን ደሙን ከተቀበሉ በኋላ ማየ መቊረርን ኅብስተ በረከትን መቅመስ ይገባል፡፡ አንድ ሰው ሥጋውን ደሙን ከተቀበለ በኋላ ትፋት ቢመጣበት በሽተኛ ቢሆን በልብሱ ቁራጭ ተቀብሎ ያሻሸው፡፡ ኋላ በውሃ አጥቦ በብርት ተቀብሎ ጨርቁንም በእሳት አቃጥሎ አመዱንም ውሃውንም አድርጎ ከወራጅ ውሃ ወስዶ ይጨምረው፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ባወቀ ይቀበለዋል፡፡ ተስእሎ 12፦ ልቡናህ በሰይጣነ ጸሪፍ እጅ እንዳይያዝ መጻሕፍትን ተምሬያለሁ ብለህ አትታበይ፡፡ ተስእሎ 13፦ ተዘክሮ እግዚአብሔር የተለየውን ልቡና ሰይጣነ ዝሙት ሰይጣነ ቊጥዓ እጅ ያደርገዋል፡፡ ተስእሎ 15፦ በጌታ ዘንድ እንደ ንጽሐ ልብ የከበረ የለም፡፡ ተስእሎ 16፦ አባ ኤዎስታጤዎስ ከትህርምት ብዛት ሰውነቱ ደርቆ ነበረ፡፡ እሳት እርጥቡን እንጨት እንደሚያደርቀው ፈሪሀ እግዚአብሔርም በሰው ስታድር ሰውነትን ታደርቃለች፡፡

© በትረ ማርያም አበባው /channel/slehiwetwe/3235 #መልካም_ቀን ይቀላቀሉን።

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

AVACOIN token $AVACN will be listed on July 30, after a week.

You can start the bot and get tokens by doing different tasks and invite friends.

⚫You can also participate on the following contests.
✔️Referel program (750M $AVACN)
✔️Telegram post contest (50M $AVACN)
✔️YouTube contest (50M $AVACN)
✔️Twitter contest (30M $AVACN)

⚫Invite at least 3 of your friends and get the token.
Read the full contest rule at @avagoldcoin

You can use the following referral link:
/channel/avagoldcoin_bot?start=8f6ee33ab74c2a71201e

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ሰው የለኝም ያለ በሰው የተረሳ
የዳነው መፃጉዕ ያዳነውን ረሳ
**
ያዳነኝን አውቀዋለሁ
የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው
ስጦታዬ ምስጋና ነው

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

ልክህን ማየት ተለል ተለል ያደርገኛል።ፍቅርህም ያዝለኛል፤ አንተን መዘከር ያቃጥለኛል። ሁል ጊዜ ስራ ለመስራት ያነቃቃኛል ።አቤቱ ፍቅርህ በልቦና ፈጥኖ አደረ በሰውነቴ ተሰራጨ።ሕዋሳቴን ጸጥ አደረጋቸው።

አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን  ፳፩

@slehiwetwe

Читать полностью…

ቅድስት ፌብሮኒያ

♡YAHWEH PROMOTION♡

↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
↪  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
              ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
☎ Tel      :- +251943686155
  :- +251977157265 📞 ያገኙናል
/channel/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ

Читать полностью…
Subscribe to a channel