እግዚአብሔር ኃጢአትህን ቆጥሮ፣ ቆጥሮ፣ ታግሶ መጨረሻ ላይ ግን ምን እንደሚያረግህ ታውቃለህ?
አትፍራ ምንም አያደርግህም! አሁንም ወደፊትም ይምራል፣ ይታገሳል፤ ምህረቱ ና ትዕግስቱ ለዘላለም ነው፤ ፍጹም አይደክምም፣ አይለወጥም።
ነገር ግን የእራሳችን ኃጢአት አድጎ፣ ሰፍቶ ና ከፍቶ ወደ እግዚአብሔርን መካድ ና የዘላለም ሞት ሊወስደን ስለሚችል በጣም እንጠንቀቅ!
እግዚአብሔርም ይጠንቀቅልን።
የእግዚአብሔርንም ጸጋ ና ወሰን የሌለውን የምህረቱን ባለጠግነት አስበን ይልቁንስ ከኃጢአት ምንርቅበት እንጂ ለኃጢአት ግብዣ እንደ ጥሪ ካርድ ተጠቅመናው ወደ ግብዣው መታደም አይሁንብን።
እወዳችኋለሁ
እግዚአብሔር ደሞ ከማንም በላይ ይወዳችኋል!
@slehiywet
በእርግጥ አዎ እውነት ለመናገር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በዚህ ዘመን እውቀት አለ ብዬ አስባለሁ፤ ስለ ኢየሱስም በደንብ ይነገራል፤ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ የተናገርነውን ነገር በተግባር ለመኖር ደሞ ለየቅል ና ቆመን የሰቀልነውን ተቀምጦ እንደማውረድ ያህል እየከበደን ያለበት ጊዜ መሆኑ ሲታይ ልብ ላይ ሀዘን ሚጭር እውነት ሁኖ ይገኛል። በአጭሩ ለመግለጽ ከዓለም ጋር በብዙ ምስስሎሽ ውስጥ እየተገኘን ነው ፤ ነገር ግን ይህንን አወዳደቅ የበለጠ መጥፎ ሚያደርገው አሁንም ትክክለኛ ቦታ ላይ እንዳለን የሚሰማን ስሜት ነው።
ብቻ እግዚአብሔር ይርዳን! ከዘመኑም ክፋት ይጠብቀን! አሜን።
የዛሬው መልዕክት በተለይ እውቀትን ይዘናል ብለው ለሚያስቡ ክርስቲያኖች ይድረስልኝ ያወራነውን መኖር ቢያቅተን አለማውራቱ አንድ ነገር ነው ብዙዎችን ከማሰናከል እንድናለን። 🙏
@slehiywet
እብዛኛው ክርስቲያኖች ጋር እንደ ቀልድ ኃጢአት ( NORMAL ) እየሆነ ነው እንዴ ? 🤔 እኛ ጋ ግን እንዳይሆንብን እሺ አደራ !
ዘመኑን እንዋጅ እንጅ ዘመኑ እንዳይዋጀን፣ ከዓለም ጋር እንዳንመሳሰል። 🙏
እወዳችኋለሁ !
@slehiywet
የዓለምን ነገር ሲያስብ ማነው እንደኔ ድክም የሚል?
ኢየሱስን ሲያስብ ደሞ ማነው እንደኔ እርፍ የሚል?
ኢየሱስ ሆይ እባክህ ሃሳቤ ላይ ብዛልኝ 🙌 አሜን
@slehiywet
😭 እግዚአብሔር እንዴት እንደሚወደኝ ሳስብ ነው ማለቅሰው ሌላስ ምንም አይደል!
ዕለት ተዕለት ሚያሳየኝ ርህራሄ፤ ጥበቃ ና ፍቅር እየበዛና ከአዕምሮዬ እያለፈ ነው በእውነቱ።
ብቻ ግን እግዚአብሔር ይመስገን በቃ ሌላም ቃል የለኝ።
አባ እወድሃለሁ❤️
ኢየሱስ እኛን እንደሚያድን አምኖ ኃጢአት የሆነው ሰርቶ ሳይሆን ተደርጎ እንደሆነ እኛም ኢየሱስ እንደሚያድነን አምነን የእግዝአብሔር ጽድቅ የሆነው ተደርገን ነው እንጂ ሰርተን እንዳልሆነ ይታወቅ።
@slehiywet
ሕይወት ኢየሱስ ነው።
2016 አለፈ ግን
እኔኮ ያልፋል የሚል ምንም ተስፋ አልነበረኝም
የእግዚአብሔር ምህረት ግን እያስነባኝ ነው
ዘንድሮ ያልጠፋው እግዚአብሔር በእኔ ላይ ትልቅ ስራ እንዳለው ይሰማኛል.. ለጥቂት ጊዜያት እንደሆነ ውስጤ ቢሰማኝም
ውሃ ሙቀትን ችሎ ችሎ ራሱን መቆጣጠር ማይችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ይፍለቀለቃል ከዛ በኋላ አርፎ ሊቀመጥ እንደማይችል ልክ እንደዛ እኛንም ዛሬ እግዚአብሔር በልጁ ፍቅር አርፎ ወደማያስቀምጥ ና ዝም ወደ ማያስብል የሆነ ደረጃ ላይ ያድርሰን በቃ 🥺
አሜን !
@slehiywet
እሺ ብለህ እምቢ በል!
በአንተ በአንዳንድ እምቢዎች ከእግዚአብሔር የምታገኘው እሺዎች አሉ ና አንዳንድ ነገሮችን እምቢ በል !
እምቢ ማለት ያለብህን ነገር መንፈስ ቅዱስ ያሳውቅሀል ና አትጨነቅ፤ ከአንተ ሚጠበቀው በሀሳቡ ተስማምቶ እምቢ ማለት ነው።
@slehiywet
የሚሄደው ይሂድ
ሚመጣውም ይምጣ
ብቻ ኢየሱስ አንተን
ክጎኔ አልጣ።
✍️ ቤኪ 11/12/2016
3:45
ኢየሱስ ሆይ ያላንተ አይሆንልኝም ብቻ ሳይሆን እኔ እራሴ አልሆንም በቃ።
@slehiywet
✋ትኩረት ፈላጊ ንባብ
እግዚአብሔር እንዴት ነው ግን ምትወደኝ ! በጊዜው አልመሰለኝም ነበር ግን ያ ሁሉ ከባድ ጊዜያት ብዙ አስተማሩኝ
ስንፍናዬ ና አንተን ማሳዘኔ ፍቅርህን አላወረደብኝም፤
ለሰው ሚያዝን ገር ልብን ሸለምከኝ፣ በእልህ አስጨራሽ ተደጋጋሚ ፈተናዎች በቀላሉ ማይነቃነቅ ትዕግስትን ተማርኩ።
በጊዜው የ ለምን ጋጋታን ና የትኩስ እንባዎች ዘለላን ወደ ሰማይ ስሰድ ዛሬ ላይ ወደ መገረም ና እንባዎቼ ወደ ደስታ እንባ እንደሚቀየሩ አላሰብኩም ነበር፤
ባይመስለንም እንዲሁም የፈተናው ማዕበል እኛ ላይ አነጣጥሮ መወርወሩን ልምዱ ቢያደርገው እንኳ እስትንፋሳችን በእኛ እስከተገኘ ድረስ ሁሌም አንድ ሚያበረታንን "ደግነቱ እግዚአብሔር አለ" የሚለውን ቃል በጉዟችን ሁሉ ስንቅ አድርገን እንበረታ ዘንድ ይህ መመሪያችን ይሁን!
አዎ አንዳንዴ ደሞ በቃ በአንድ በኩል አለመታደል በሌላ በኩል ግን እኛ ለራሳችን መሆኑ ወይም ጥቅሙ ይቀርብን ና ለሌሎች ብቻ በረከት፣ ጥቅም፣ የሳቅ ና የእርጋታ ምንጭ ሆነን ራሳችንን ከምግኘቱም በላይ እኛ እምብዛም የደስታን ጣዕም እያጣጣምን ባይሆን እንዲሁ ለብ ያለ ማይሞቅ ና ማይበርድ ስሜት ላይ ብንሆን ወይም ተከፊዎች ጭምር ብንሆን በእኛ መኖር የሚደሰት ሰው መኖሩን ስናይ ግን ይህ አንድ የሚያኖረን ተስፋ ና ስኬታችንም ጭምር ነው ማለት ያስደፍራል።
ከሌለም ወደ አንዱ ጠጋ እንበል ና በእኛ ላይ ተቆልሎ ሲነድ የሰነበተብን ፍም ጭሱ ከሩቅ ያን ሰው ሲሸተው በግልጽ እናየዋለን፤ ያም ጭስ የበሰለው ትሁት ና አስተዋይ ልቦና ነው።
ከሰውም ባንጠጋ በእኛ ህይወት የሚማር ሰው ብናጣም እንኳ ያለ ብሩህ ተስፋ ዛሬን በህይወት መድረሳችን ለነገውም መኖራችን ትልቅ ጥንካሬ አይደለምን?
ህይወት እንዲህ ናት እንግዲህ በእኛ ቃጠሎ ና ስቃይ ሚደሰት ና ሚጠቀም እልፍ ሰው ነው፤ ከእኛ የህይወት ልምድ ይማራሉ ና!
ሌላው ይቅር ና አንድን እጅግ የከፋውን ና ተስፋ የቆረጠን ሰው ማፅናኛው ትልቁ ና ውጤታማው መንገድ የእራሳችንን ከሱ የባሰ መከራ መንገር ነው። አይ እቺ ዓለም!
ያሳለፍናቸው ጎርባጣ መንገዶች ሌላ ሰውን መምሪያ ሁነው እናገኛቸዋለን፤
ምን ማድረግ እንችላለን ?ያለፍነውን እንዳለፍነው የሚመጣውንም ማለፍ፤
መቻል መቻል አሁንም መቼም መቻል፣ መጠበቅ፣ የአሜን ህይወትን መጎናፀፍ፣ ምን ልታስተምረኝ ነው ? ማለት፣
ይህ ነው ከሁሉም የተሻለው መንገድ።
ህይወት ብዙ ጊዜ ከእኛ ተቃራኒ ናት ይባላል እናም ምናልባት ችግሮቻችንን ብንወደው ትቶን ይሄድ ይሆን ? የሚል ፅሁፍ ከወራቶች በፊት ማንበቤ ይታወሰኛል፤
ለማንኛውም ግን እመኑኝ በቃ እግዚአብሔር መልካም ና ደግ ነው።
አሁን ላይ ይባስ ብሎ የምህረቱ ብዛት የተሸከምኩት ያህል እየተሰማኝ ነው በጣም በዝቶብኛል።
ሁሉም ያልፋል! ካላለፈ ደሞ እኛ እናልፈዋለን
ሰማያዊ ህይወት በክርስቶስ የእኛ ነውና!
✍️ ቤኪ ቱሊፕ
@slehiywet
የምድር ጥበብ፣ ዕውቀት ና ፍልስፍና ብዙ ጊዜ መጨረሻው እግዚአብሔር የለም ማለት ነው፤ ግን የነዚህ ሰዎች ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ስንፍና ነው! ቃሉም ''ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል'' እንዲል።
ጥበባችን የእግዚአብሔርን አለመኖር ወደማመን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ረቂቅነት የሚያሳየን ይሁንልን!
እግዚአብሔር በእውነትም አለ ፤ ለተመለከተው።
@slehiywet
ሳያግበሰብሱ
ሳያሹ በስሱ
ከእራሱ ጀምረው
እስከ እግር ጥፍሩ
ጉልበታቸው ሚሟጥ
ውቡን ለማስረዳት
ተናካሾች በዝተው
ቢጠብቁ አፍ ከፍተው
በአጠገቡ ሚያልፉ
ፍርሃትን ዘንግተው
ቢናቁ ቢወድቁ
ቢሰምጡ ቢያጡ
በመከራ ማዕበል
ተጨንቀው ቢያምጡ
ስምህ በአፋቸው
ፍቅርህ በልባቸው
ብርሃንህ በዐይናቸው
ቃልህ በእጃቸው
የሚታይባቸው
ኢየሱስ ለማለት
አንተን ለማሳየት
ማያጥሩ ማያፍሩ
ማይሰንፉ ማያድሩ
እይነት ስዎች ይብዙ
ምድርን ና ዓለምን
በአንተ ፍቅር ይግዙ።
አሜን!
✍️ ቤኪ ቱሊፕ 22/2/2017 e.c
@slehiywet
አቤት መዝሙር 😭
አዳምጦት አለመነካት አይቻልም በቃ!
ደጋግማችሁ ኡዳምጡት፤ መንፈሳችሁን የበለጠ ሲያድስ ታስተውላላችሁ።
ስለ ዘማሪዎቻችን እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት ጸጋ ይብዛላቸው።
@slehiywet
ኃጢአትን ሳደርግ ጸጋውን አስቤ ዋስትና እንዳለኝ አስቤ እፅናናለሁ ፍርሃትም አይገዛኝም፤
ነገር ግን ጸጋውን አስቤ ከዚያም በኋላ በሱ ተማምኜ ና ተደግፌበት ነፃነት ተሰምቶኝ ና ድፍረትን ሰቶኝ እግሬን ወደ ኃጢአት ለማፍጠን ማሰቡ አግባብ ሁኖ አይታየኝም።
ኢየሱስ ግን የምርም እንኳንም ሞትክልኝ
በተለይ እንደኔ አይነቱ እጅግ ኃጢአተኛ ሰው ምን ተስፋ ነበረው?
@slehiywet
ኢየሱስ ያኔ በወደቀ ና በእሳፋሪ ማንነታችን እንኳ እኛን በአብ ፊት ለማቅረብ ና ለማሳየት አላፈረብንም፤ ዕርቃኑን በአደባባይ እስከመሰቀል ድረስ።
እኛ ደሞ ፍጹም ንፁሕ የሆነውን ኢየሱስን ለሰዎች ለማሳየት በፍጹም ማፈር የለብንም።
አለማፈር ማለት በአደባባይ ስሙን እየጠሩ ወንጌልን መናገርንም ይጨምራል። 😌 ጸጋው ይብዛልን !
ዓለምም መድኃኒቷን ኢየሱስን በማወቅ ትሞላ!
አሜን 🙏
@slehiywet
እንዲሁ ወደደን
"እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"(ዮሐ 3:16)
እግዚአብሔር ሳያፈቅር አይኖርም። በእርሱ ዘንድ የፍቅር ባለጸግነት አለ። የእርሱ ፍቅር በቃላት ክምችት የማይገለጽ፣ መጡኑ፤ ስፋቱ፤ ጥልቀቱ፤ እርዝመቱ ይሄን ያህላል ተብሎ የማይታወቅ ነው።
እርሱ ሲያፈቅር ከልኬት በላይ፤ ከሁኔታ በላይ ነው። እርሱ አለሙን በሙሉ የወደደው እንዲሁ ነው።
ሲወደን ታሪካችን ማርኮት፤ ምግባራችን ስቦት አይደለም።እንዲሁ ያለ መስፈርት ወደደን።
እርሱ የመውደዱን ጥግ ያሳየን አንዲያ ልጅን ስለእኛ አሳልፎ በመስጠት ነው። የሚወደውን ልጁን፤ ደስ የተሰኘበትን ልጁን ለእኛ ሲል ለሞት አሳልፎ ሰጠው። ልጁ በመስቀል ላይ ስለእኛ ኃጢአት በሆነ ጊዜ ፊቱን ሰወረበት፤ ከጩኸቱ ድምፅ ርቆ ቆመ። እርሱ ለእኛ ሲል በገዛ ልጁ ጨከነ። ለእኛ ሲል ልጁ ያለልክ ዝቅ እንዲል ፈቀደ።
የእርሱ ፍቅር ከመናገር ብቻ ሳይሆን ከማሰብም በላይ ነው። እርሱ ሁለመናው በፍቅር የተሞላ። እርሱ ያለመታከት ዘወትር የሚወድ ነው። ያለ ዋጋ እንዲህ በልጁ በኢየሱስ የወደደን አምላክና አባት እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ። አሜን።
👇👇👇👇👇👇👇
Join now
✝✝✝✝✝✝✝✝
📥Group : @slehiywetkal 👈
📥Channel : @slehiywet 👈
✝✝✝✝✝✝✝✝
ያለ ኢየሱስ እንደኔ የምጠላው ማንነት አላውቅም፤
በኢየሱስ አማካይነት ግን ራሴን በጣም እወደዋለሁ፤ አብም እጅግ ይወደኛል።
2017 በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የሚታዩ ሰዎች ሚበዙበት ዓመት ይሁንልን! አሜን።
@slehiywet
1ኛ ጴጥሮስ 1
15 ዳሩ ግን፡— እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
17 ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
@slehiywet
ስማኝ ብዬው ቢል አልሰማ
እሱስ አልታደለ ነገው ነው ጨለማ
ጆሮን የምሻበት ትልቁ ርዕሴ
የእኔ ቁምነገር እሱ ነው ኢየሱሴ።
✍️ ቤክ
ኢየሱስ ኢየሱስ በዚህ ስም ተጠምጄአለሁ!
@slehiywet
በነገራችን ላይ ክፋት ና አመፅ፣ የፍቅር መቀዝቀዝ፣ በየቦታው ብዙ ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ዜናዎች ከዚህ በኋላ እየተበራከቱ ሊመጡ ሚችሉበት አጋጣሚዎች ሰፊ ናቸው፤ ምክንያቱም ዘመኑ እያለቀ ና ብቸኛው ና መልካሙ ተስፋችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ መምጣት እየቀረበ ነው። ና እንንቃ! ብርሃኑን ኢየሱስን በጨለመው ዓለም ላይ እናብራው።
አሜን ማራናታ ኢየሱስ
@slehiywet
የኢየሱስ ክርስቶስ
ጸጋው ተትረፍርፎ
በአይናችን አየነው
ስንቱ በሱ አርፎ።
እናንተስ ካረፉት መካከል ናችሁ?
10 ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
@slehiywet
#ደረሰላት
ታሞ ልቤ በመንገዴ
ሲወድቅ ሁሌ ሲቆም አንዴ
ተንገዳግዶ ቤት ሲገባ
እግሩ ደቆ ሲሆን ሽባ
አቅፎ ወዶት የሚያስተኛው
ራሱ አለ የሚያስጠጋው።
ሁሌ ቢያስቸግረው
ሎሌው የሚሆነው
ብርታትን ሸልሞት
ድካሙን ሚያግዘው
ደምን ረጭቶ
ሚሆን ህይወት
እስትንፋሱ እንዳይቆምበት
አፈር ሁኖ እንዳይቀርበት
የራሱን ልብ ለገሰለት።
ኢየሱስ ሁኖልኝ
ልቤ የልቤ ጌታ
ሞት ሚባለው ገዳይ
በሞት ድል ተገታ።
✍️ ቤኪ ቱሊፕ
16 / 11 / 2016
@slehiywet
💥ይህንን የምታዩ ቅዱሳን በሙሉ
ኢየሱስ የሚለውን ስም በምትጠቀሙት በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ፕሮፋይላችሁ በማድረግ ከእኛ ጋር ዘመቻውን አትቀላቀሉም? 🙏
🗣️ሚዲያውን በዚህ ድንቅ ስም እናጥለቅልቀው።
እኔ አድርጌአለሁ እናንተስ? 😍
ለምታውቁት ቅዱሳን በሙሉ መልዕክቱን አጋሩት
ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነ ስም..
#ኢየሱስ 🔥
ጸጋ ና ሰላም ይብዛላችሁ ❤️
@slehiywet