sostkilo | Unsorted

Telegram-канал sostkilo - Sost Kilo

-

| Leoulzewelde.wordpress.com

Subscribe to a channel

Sost Kilo

Feedback time: Do you like የራህባን ጭስ?

Читать полностью…

Sost Kilo

Podcast, this weekend 📻

Читать полностью…

Sost Kilo

Craft: Tsehay Tibebu 🖤

Читать полностью…

Sost Kilo

Self portrait et video | Sosina Mengistu

Читать полностью…

Sost Kilo

Follow @sostKilo on Tiktok.
#sostkilo - One Million views !

Читать полностью…

Sost Kilo

Sost Kilo blog hits19k users 🥳
sostkilo.wordpress.com

Читать полностью…

Sost Kilo

@sostkilo on Google Podcast 📻

Читать полностью…

Sost Kilo

New podcast 📻 | https://anchor.fm/sostkilo/episodes/Good-Friday-e22c6m0

Читать полностью…

Sost Kilo

Worn out, See you next month !

Читать полностью…

Sost Kilo

Message 3 - Part III ...

Читать полностью…

Sost Kilo

YouTube: sostkilo" rel="nofollow">https://youtube.com/@sostkilo

Читать полностью…

Sost Kilo

Your favorite podcast episode ? why ?

Читать полностью…

Sost Kilo

ኦቾሎኒ | አለንጋና ምስር : Ep. 01 - 09 : All Eps.

https://anchor.fm/sostkilo/episodes/------EP-01-e1lbk8n

Читать полностью…

Sost Kilo

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3 - ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ...|

( ፫ ፥ አዲስ አበባ ) ...

Читать полностью…

Sost Kilo

ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ...|

[ ልዑል ፡ ዘወልደ ]

፪. ቦኽዱ ፥ የጨረቃ ወደብ ፥ (ፈረንሳይ)*

ከአልጋ በመውረጃው ምንጣፍ ላይ የተበተኑ የኮንዶሞ ሳጥኖች አየሁ ። በደህና ያደረ ልቤ ፥ የድንገት እይታዬን ተከትሎ ርብሽብሹ ወጣ ። በእንፍቅቅ ተነስቼ በዙሪዬው ተጠልቆ የተተፋ ያለ እንደው ማሰስ ጀመርኩ ።

ሞት ከሆነ እንቅልፍ መንቃቴ ነበር ። ረጭ ባለ ክፍል ውስጥ ፥ ጣሪያው የተተራመሰ የራስጌ ሳጥን ከፊቴ አለ ። በሳጥኑ አናት ላይ ፤ ባዶ የአበባ ጡሌ ፥ የመኪና ቁልፍ ፣ አመዱ የተተደፋ አሽትሬ ፣ ሁለት ሲጋራ የተረፉት ፓኮ ፣ ተደፍቶ የደረቀ ቀይ ወይንና በላዩ ላይ የተጠባበቁ አምሳ ዩሮዎች ፥ ካኪ ሱሪዬ ከነቀበቶው ፣ የቤሎንዥ ጡት መያዣ ፣ ከከንፈር ላይ ሊፒስቲክ ያነሱ ሶፍቶች ። ይሄ ሁሉ ፥ የበሬ ግንባር በምታክል የራስጌ ሳጥን ጣሪያ ላይ !

ሌላው የቤቱ አገር ንፁህ ነው ። በክፍሉ ያለው የብርሃን ፍዘት ለአይን የሚረብሽ አይነት አይደለም ። የክፍሉ ቀለም በሶስት ሴማ ቆሟል ። አንድ ከሎሚና ጎመኔ መኀል ባለ ፥ የመስኮት ዕፆችና የራስጌው ድሮወር ። ሁለት ያልወየበ ቡኒ ፥ ደመቅ ሲል የቤቱ ወለልና ፈዘዝ ሲል የኮርኒሱ ፍሬም ። እና ደግሞ ነጭ ፥ ከመሃል ጉልት ያለ አልጋ ፣ ኮርኒስና መጋረጃው ።

ምን ተፈጥሮ ነው ? ነገር የማስታውሰው እንደቪድዮ ቴፕ በየተራ እያጠነጠንኩ ነው ። እስከመጨረሻው አጠንጠንና ከመጀመሪያው ትይንት ጀምሮ ወደፊት አንድ በአንድ እሄዳለው ። የቪድዮው መጀመሪያው ምን ነበር ?

Play | 00:00:01

ፈረንሳይ እንደደረስኩ ከፓሪ ኤርፖርት ወደ ቦኽዱ የባቡር ጉዞ አደረኩ ። ከሁለት ሰዓት ጉዞ በኋላ ቤሎንዥ ቦኽዱ - ቅዱስ ዦን ለገሀር ተቀበለቺኝ ። እንደወትሮዋ ዛሬም ዘንጣለች ። ቡኒ ክብ መነፅር ፣ ግንባሯ መጀመሪያ ላይ የተቋጠራች ቢራቢሮ ሻሽ ፥ ማሪኘኽ ቲሸርት - በኦሞ ጅንስ ።

Mon chéri ...!

ለብዙ ቀን እንደተነፋፈቀ ፥ ተቃቅፈን ቆየን ። የአንገት ሽታዎቻችንን ተማማግን ወደ ቀይ ፕዦ-205 መኪናዋ አመራን ። ቤሎንዥ ሲጋራዋን በአፍ ይዛ ፈገግ አለች ፤ ፈገግታዋ ሁሌም ድካሜን ያበንነዋል ። ለብ ያለችውን የባቡር ጣቢያ ፀሐይ በጀርባችን ትተን ወደ እናቷ ቤት ገሰገስን ።

ማማ ኤሊዝ ፥ ጎኑ ሾርባ ያለው የመግሪብ ኩስኩስ ጋበዙን ፥ ይሁን ! አመጣጣችን ድንገት ነበር ። ጭንቅላታቸውን በአለላ ቢጎዲን ጠቅጥቀው የሚንጎራደዱ ትልቅ አርበ ሰፊ ሴትዮ ናቸው ።

ቤል ፥ በስሜ ጠርታ ስታስተዋውቀኝ ምንሽ ነው ? እንዲሏት ተመኝቼ ነበር ። ሳይሆን ሲቀር በውስጤ ያለችውን ቤል በእናቷ ፈንታ ጠየቅኹ ፤ ቤል ! እኔና አንቺ ምንና ምንድነን ? እ...ቅርበታችን መሠየም ለምን ፈራሽ ?

ማማ ኤሊዝ ፥ የልጃቸውን ውሽማ በማዕረግ አስተናገዱ ። ከእማማ ጋር በሙሉ አይን የተያየነው ቤሎንዥ ሾርባ ለመጨመር ስተነሳ ነው ። ለስርዓትና ወግ በጣም ታትሬ ስለነበር መሰለኝ ። መች መጣህ ? ከተማችን እንዴት ነው ፥ ወደድካው ? ቀላል የሆኑ በአህጉር የሚያግባቡ ጥያቄዎችን እየተወራወርን አወራን ። ቤሎንዥ በመሀል ገብታ ስለአንደበቴ ጉብዝና ጠየቀች ፥ የአሮጊቷ ውረፋ አልቀረልኝም ። les vaches d'Espagne ...አለ አይደል ፥ እንደ እስፓኞል ላሞች ሃሃ

⏩ | 02:46:59

ወደ ተያዘው ሆቴል ፥ ኦቴል ዴላ ፕሬስ ጋለብን ። ቤል መኪና ውስጥ ሲዘፍን የነበረውን ካሴት ገለበጠች ። የካሴቱ አይኖች ስር Édith Piaf - Non, Je ne regrette rien የሚል ፅሁፍ ተጭሯል ። እንደከተተችው ፥ ተስረቅራቂ የሴት ድምፅ በላያችን ይፈስ ጀመር ። ቆይቼ አስታወስኳት ፥ የጥንት የጠዋቷ የላ-ቪ-ኦን-ሮዟ ዘፋኝ ነች ።

Non, rien de rien,
Non, je ne regrette rien ...!

ኖ..!
ፀፀት የለብኝም ፥
ኖ..ምንም !....ምንም ነገር ...አይፀፅተኝም ....!

ዘፈኑ ወስዶን ፥ በመንገዱ ምንም ቃል አላወራንም ። ኮብል በወረራቸው የውስጥ-ለውስጥ የቦኽዱ መንገዶች ተጉዘን ፤ ደረስን ። በበርአፉ የጣሳ አበቦች የተኮሎኩልበት የድሮ ሆቴል ነው ። ሎቢው ከባቢ ሰው ስላልነበር ፤ አልፈን ደረጆችን ወጣን ። እንደደረስን ፥ ቤሎንዥ ትልቅ ማንጠልጠያ ያለው ቁልፍ ከቦርሳዋ አወጥታ ወደ ሰረገላው ውስጥ ሰካች ። ከቀኑ አስር ሰዓት ፥ የሩም ቁጥር አንድ መቶ ሰባት ።

ከቤል ጋር ብዙ ተራርበናል ። ፊቷ ላይ ካሉ ቀዳዶች ጌጧን እያወላለቀች ተጠጋቺኝ ። ጫማዬን በእግሮቼ አክኬ አወጣኋቸው ። በየድርጊቱ መሀል ፥ አይናችን ከመተያየት አልሰነፉም ። በሁሉም ድርጊት መሀል ፥ አይኖቿን እፈልጋለሁ ። መተያየታችን በቃላት መሀል እንዳለ ክፍተት ነበር ። ካልተያየን ፥ ዝም ብሎ እን መቅጠልጠል ነበር ፤ ትርጉም አይኖረንም ።

አይኔ ወደከንፈሯ ወረደ ። ደህና ወርጄ ለምቦጯ ስር ያለች ነቁጥ ጋር ስደርስ ድንበር ትሆንብኛለች ። እመለሳለው። ቡኒ አይኗ ፥ የትም ዞሬ ማረፊያዬ ነው ።

እንደቆምን እጄን የጉንጭና ራሷ መግጠሚያ ማዕዘን ላይ አሳረፍኩ ። የተከፈለ ቡኒ ፀጉሯ መሃል ላይ የተኛ የቆዳዋ አስፋልት አለ ። ክፋዩን ተከትለው ቢሄዱ መጨረሻው አይታይም ፥ ሚራዥ እንደሆነ ይቀራል ። ከአፍንጫዋ ደረስኩ ። የአፍንጫዋ ስር ጉድጓድ ምንጭሯን የተቆለመመበት ጥበብ ተዓብ ነው ፥ ለመጉረስ እንዲመቸኝ እግዜር አስቦልኝ ይሆን ?

የቀሉ ጉንጮቿን ፥ ዳሰስኩ ። ሁሌም ስነካት ነብሷ በጣቶቼ በኩል ወደኔ ትሰርጋለች ፤ ምህዋሯን እንደያዘች ፥ ሰተተተት ። ነብሷ ከኔ መነተሆኗን ሳውቅ ፥ ደረቴ ላይ ሐር ፈታይ ትሎች ይርመሰመሱ ይመስል ፥ ውርር ያደርገኛል ።

ቶሎ ቶሎ ከሚወጣ ትንፋሽና ሂሏን ስታወልቅ ከነበረ ቋቋታ በቀር በቤቱ ድምፅ አልነበረም ። ዋሜራ አንገቴ ላይ እጇን አስተነባብራ የእንግሊት ወደአልጋው ወደቅን ። ሁለቴ ግዜ ፥ ዘፍ ዘፍ ። ስናርፍ ፤ የአንገቷ ጉድጓዶች ላይ ተዘግዝጎ የተሰመረ ሀብሏ በአንድ ጎኗ ተንሸራተተ። መልሳ ከላዬ ሆነች ። ወዲያው ደግሞ ወደጎን ።

ከኔ-አገር ውጪ ለመጀመሪያ ግዜ ከንፈር ልንቀማመስ ነው (እንደዚ ይታሰባል ? እኔንጃ ብቻ) ። ለድመት መውጫ እንደተገረበበ በር አፏን በስሱ ከፍታ ተጠጋቺኝ ። የሚቀሰም ወዝ በአፏ ላይ ነበር ፤ ቅሠም-ቅሠም አሰኘኝ ።

ሣምኳት ፤ ምህረት የሌለው አሳሳም ። ስሚያችንእዝ እንደሌለው ዳንስ ነበር ። በአፏ ማርውሃ እረጥብና ፥ በተራ ደግሞ እሷን አረጥባለሁ ።

እግሮቻችን እንደተቆላለፉ ሹራቤን ከላዬ ለማውለቅ ብዙ አታገለኝ ። ባንዲራ ሲወርድ እንኳ እንዲህ ያለ ግዜ መብላቱን እንጃ ። አውልቄ እስካሽቀነጥረው ብዙ ተዓምር ያመለጠኝ መሰለኝ ፤ ደግሞም አምልጦኛል ። ቲሸርት ከገላዋ ወደላይ ሲገፈፍ የነበረን ትይንት መታደም አያስፈልገኝም ነበር ?

ምላሶቻችን ወለው ተዟዟሩ ። የተራበ አይኗ አሁንም እየለመነ ያዘኛል። እየተለመኑ ደርቦ ትዛዝ መቀበል ከዚህ ቦታ በቀር ገጥሞኝ አያውቅም ። " ጌትዬ ፥ ዋ ! " ተብሎ ያውቃል ? አይባልም ነገር አይደል ? ይገባኛል ፤ በቦታው ላልነበር አልያዊ ሙሉቀን ቢወራ እንኳ ስሜት አይሰጥም ።

ወገቧን በእጄ ቀኝቼ ከተንጋለለችበት ተጠጋሁ ። ልቡን ከየት እንዳመጣሁት እንጃ ። የማድረገው ሁሉ ከዚህ በፊት ከቀሚስ ጋር ትውውቅ እንዳለው ነው ። ነገር ግን እንተባረረው አዳም ነበርኹ ፤ ሒዋንን በስጋ ሊያውቅ መጀመሪያ እንደሆነው ፤ እ...ን...ግ...ዳ ።

Читать полностью…

Sost Kilo

Listen to the most recent episode of sostkilo podcast:  የራህባን ጭስ  https://anchor.fm/sostkilo/episodes/ep-e28adld

Читать полностью…

Sost Kilo

https://open.spotify.com/show/5G24xZgND9Dn6ge0XSL025

Читать полностью…

Sost Kilo

Happy birthday @LeoulZewelde 🎂

Читать полностью…

Sost Kilo

የመልካም ልደት ምኞት ለአዳም ረታ...
ኦቾሎኒ (*አጭር ልብወለድ) | አለንጋና ምስር መፅሃፍ | ሆላንድ 1985 ዓ.ም.

Читать полностью…

Sost Kilo

@sostKilo Podcast 📻
New Ep: ሮዛ-ሮዚና ! https://anchor.fm/sostkilo/episodes/ep-e24286k

Читать полностью…

Sost Kilo

Sost Kilo Podcast 📻
New Ep: የመንታ እናት ፖለቲካ ! https://podcasters.spotify.com/pod/show/sostkilo/episodes/ep-e23iqoc

Читать полностью…

Sost Kilo

Good Friday | Narrator : ወ ለ ሎ ታ ት | No_lawii

Читать полностью…

Sost Kilo

Wishing you a blessed Good Friday !

Читать полностью…

Sost Kilo

⚠️ Book Alert !
📍ሀገር ያጣ ሞት | 2nd edition.

HEnock Bekele | ወ ን ድ ሜ
እንኳን ደስ ያለህ፥ እንኳን ደስ ያለን 🖤

Читать полностью…

Sost Kilo

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3  | Part II https://anchor.fm/sostkilo/episodes/--Message-3---Part-II-e1u3sh0

Читать полностью…

Sost Kilo

የተራነቴ ሄ'ህ'ሆ !

[ ልዑል ዘወልደ ]

ተራ ስለሆንኩ
( ሄ )

በቆርቆሮ ጣርያ ተከድኜ ዝንትአለሜን ስጨነቅ አልኖርም ፤ የማንጋጥበት ኮርኒስ ሳልከፍል የገዛሁት ሰማይ ነው ። ቀለሙ በየሰዐቱ 'ሚለዋወጥ ኮርኒስ . . . አይፀዳም በፈጣሪ ?

አስብ እስኪ ፥ በሰርክ ለሊት ተጋድመህ ተወርዋሪ ኮኮብ እየቆጠርክ አስራስድስተኛዋ ላይ ስትደርስ ምናምን ታዛጋና ሰላምህን ታቅፈህ ትደቅሳለህ ። ከዛ ደሞ ሲነጋ ፀሀይ በቀጫጭን በተረጩ ጨረሮቿ እየኮረኮረች . . . ነጋልሽ ነብሴ . . . ? ስትልህ. . . እግዚኦ ! ደስ ስትይ ብለሃት እየተንጠራራህ ጀርባህን ታካለህ . . . ፏ. ፏ . ፏ . ሿ . ሿ ።
.
ተራ በመሆኔ
( ህ )


ክቡርነቴ ባዮች ከእግር ስራቸው ተጋድሜ ሲሰግዱ እንኳ ዝቅ ብለው አይተውኝ አያውቁም ፤ ተመስገን ! እንኳንም ያላዩኝ ። ሲረሱኝ ሳያውቁት ነፃነቴን በነፃ ይለግሱኛል ፤ አጎፍሬ ዱር ሳልገባ ምናምን. . . ሃሃሃ ።

አዳሜ ነፃነትህን እኔጋ አራግፈህ ለተፈጥሮያዊ ፈስህ ( ሰው ሰራሽ አለ እንዴ? ) እንኳ እየዞርክ አስሬ ቼክ ታደርጋለህ ? ሰሙኝ አልሰሙኝ ። አልገባህም እንጂ ተራነት እኮ ቪ አይ ፒ ነው ፤ ምቾቱ ተ.ር.ር.ር.ር እርፍ ።

አንዳንዴ እላለው ፤ ምናለ ሲምቢሮ ወፏን ቢያረገኝ . . . ተኮፍሳቹ ስትሽቋልጡ እየተከታተልኩ ኩሴን መሃል አናታቹ ጠ...ብ ። ከዛ ፥ ሲሳይ ነው ምናምን እያላቹ ስትጃጃሉ ከት ብዬ እስቅ ነበር ፤ በወፍኛ ፂ...ው ፂ...ው ፂ...ው እያልኩ ።

ተራ ስሆን
( ሆ )

የማጣው ነገር ስለሌለ ምንም አያስፈራኝም ። ፍርሃት ከሌለህ መለኮት ባዶህን ሞልቶ በራስህ ከፈፍ ይሽከረከራል ። ፍርሃት ከሌለህ ነብስህ ህላዌ እንጂ ፆታ እንደሌላት ትረዳለህ ። ፍርሃት ከሌለህ የሰዎች ህግ ፣ ትምህርትና ትርጉሞች በጥልቅ እንዳታስብ እንዳፈኑህ ትባናለህ ። ፍርሃት ከሌለህ አገርህ ከዚህ አለመሆኑን ስለምታውቅ እንደቱሪስት እያደነቅክ ትኖራለህ ። አንተ ሆዬ የሌለህን ቤሳቢስት ላለማጣት ሳይሞላልህ እንደተንከራተትክ ነብስህን በስጋት ፉት ታረጋታለህ . . . ምፅ ።

ቆይ እንዴት እየሮጥክ ስለሌላ ሩጫ ትጨነቃለህ ፤ እንዴት እያረፍክ ስለሌላ ትልቅ እረፍት ታስባለህ ፤ አንዱን በቅጡ ሳትይዝ ሌላውንስ ለምን ታሳዳለህ ? እህ አለም 'ኮ ያለሾርት የማትሰራ ሰልፊሽ ሸሌ ነች ። ቶሎ ቶሎ ካልከካህ ሳትጨርስ ታባርሃለች . . .ምፅ . . . ከፍለሃት ሳለ ? . . . ስሜትህስ . . . ምፅ. . . ወይኔ ገንዘብህ . . .


በውኑ እኔ ድምቡሎ ጎዳና ተራ ሰው ነኝን ? (የተቀነጨበ)

Читать полностью…

Sost Kilo

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3  | Part II https://anchor.fm/sostkilo/episodes/--Message-3---Part-II-e1u3sh0

Читать полностью…

Sost Kilo

https://anchor.fm/sostkilo/episodes/ep-e1tgnnl | ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3 - ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ...| ፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ

Читать полностью…

Sost Kilo

የአንገቴን ዙሪያ-ሜዳ በከንፈራ እየጠረች ብዙ ቀላድ አክብባ መጠጠች ። ስድስት ሰባት ቦታ ከንፈሮቿ እዚህ ነበርን የሚል ምልክት እየተው ፥ ወደጆሮዬ በለብታ ወጡ ። እ...የ...ጋ...ል...ኩ ነበር ።

Pause | 08:46:59

ቤቱን ሙሉ ዞሬ ፥ የሰራ ኮንዶም ሳጣ ግዜ ፥ ሀሳብ እያውጠነጠኑ መቆየቱን አልፈለኩም ። ለደቂቃዎች ማሰብ አቁሜ ሲጋራ ለማጨስ ፥ ከአልጋው ጫፍ ዞር አልኩ ።

ቤል ፥ አሁንም እንደተኛች ነው ። ወደ በረንዳ ሳመራ ቅድም ሰጥታኝ በቅጡ ያላነበብኩትን ፖስት-ካርድ ተገልብጦ አየሁ ። መሀል ላይ ሁለት ቃል ብቻ ሰፍሮበታል ። " የኔ ነብስ...!" በተረፈው ቦታ ፥ እንደመጣልኝ ቃላት ጨመርኩ ።

የኔ ቤሎንዥ - ቀለም ነክረሽ ሰንደቅ የምትሰፊልኝ ከሆነ ምርጫዬን እነግርሻለው ። ሚስጥሬ ሁሉ በእርሱ አለ ። መጀመሪያ ፥ ደማቅ ጥቁር ጀምሮት እየገረጨ እንዲሄድ ፥ የሚነጣ ሶስተኛ ደብዝ ደሞ ትጨምሪያለሽ ፥ መጨረሻው ግን ወይን ጠጅ ይሁን ። አራት ሕብር ያለው ሰንደቅ ፤ ይኸው ነው ቤሎንዥ ፥ ይኸው !

Читать полностью…

Sost Kilo

ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤
Message 3 - ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ...|

[ ልዑል ዘወልደ ]

፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ

ከናፍራችንን ቀድመው የተሳሳሙት ጣቶቻችን ናቸው ። የዛሬ አመት ገደም ፥ የላዳ የኋላ ክፍል ውስጥ ። የዛን ለት ከየት-ወዴት እየሄድን እንደነበር አላስታውስም ። ብቻ የፑሽኪን'ን አናት ከኋላ ስንተውና ኦርቢስ ከባቢ ስንደርስ ፥ ጣቶቻችን ተፈላልገው ተገናኙ ።

በወንበራችን መሀል የተተወ አስፈሪ የይሆናል ክፍተት ነበር ። ማርያም ጣቴ ይሄን ጥሳ ወደ ግራ እጇ ጠርዝ ታከከች ። በጥፍሯ ያለን ቀይ ቀለም በማከክ የተጀመረ ወደሌሎቹ ዳበች ። ቀስ እያለ ፥ እጆቻችን ተደጋገፉ ።

ጣቶቼ በአራቱም የጣቷ ክፍተት ሲሰገሰጉ ፥ አይኖቻችን እንዳስመሳይ ቱሪስት ከመኪናዋ ማዶ የሚታይ-ማይታየውን እያደነቁ ነበር ። አላየንም አሉ ፤ ጣቶቻችንን ከኛ ወገን አይደሉም አሉ ።

ጀግና ጣቶቻችን ስንት ስጋት ጥሰው ሲሳሳሙ ፥ ከንፈራችን ገና ባላገር ነበር ። ተነካካን ። እሳት ላይ እንደተጣድን ሁሉ ደማችን ውስጥ-ውስጡን መፍላት ጀመረ ። ንኪ ፥ ስንት ፋራናይት ነው ?

ሙቀቱ የሆነ መግለፅ የሚከብድ ምቾት ነበረው ፥ የሆነ ምቾት የሚነሳ ነገርም ። የርሷ ደም ከኔ ቀድሞ ጋለ ። ጥቂት እንደተነካካን ተጠግታኝ ፥ ከንፈሬን ሳመች ። ለገላችን ሁለተኛ ስሚያው ነበር ፥ ከጣት የቀጠለ ። ስንሳሳም ከአፏ ውኃ ላይ ትኩስ ቫኒላ በማርልቦሮ ቀመስኩ ። ቤል ፥ አጭሳ ነበር ።

የሷንና የጎልዋዝ ሲጋሪቷን (*በነርሱ አገር ሲጃራ የእንስት ፆታ አላት ) ሽታ መለየት ይከብደኝ ነበር ። ሰማያዊው ካሳ ያለው ጎልዋዟ ሲያልቅ ፥ ትንሽ ቀን ብቸኛ ሽታዋን ለመድኩ ። ኋላ ላይ ለሱሷ ማርኪያ ማርልቦሮ ጀመረች ። በነበሩት የሽግግር ቀናት ግን የላቧን ሽቱ በአፍንጫዬ ሸምድጃለሁ ።

ሽታዋን ለመግለፅ ፥ ከቫኒላ ጋር አንድ ብሔር እንደሆኑ ይሰማኛል ። ረግጦ ፥ እንዲህ አይነት ነው ለማለት የሚያስችል ግን አይደለም ። ያዩትን ፥ በሥዕል ይገልፁታል ። የሰሙትን ይተርካሉ ። ያሸተቱትን ፥ በምን ይጠበቡታል ?

ትንሽ እንደተሳሳምን ፤ " ቤል ፥ የኛ አገር ሰው እንደናንተ አይደለም ፤ ደግሞ እንዳይረግሙን " አልኹ ። በለዛ ማይ ያልተነከረ ደረቅ ቀልድ እንደነበር ተሰምቶኛል ። እንደ መልስ ፥ ልዝ ፈገግታዋን ደበሰችኝ ።

ይህ ሁሉ ተዓምራዊ ኪነት ሲተወን ፥ የላዳ ሹፌሩ ከመድረክ ጀርባ እንደተቀመጠ አዘጋጅ ነበር ። አይቶ ምንም እንዳላየ ፤ ሰምቶ ምንም እንዳልሰማ ፥ አምኗል ። ቅድም ጣቶቻችን ሲሳሳሙ አይኖቻችን እንደሆኑት ፥ እንደተጠበቀልን ምቾት ...

፪. ቦኽዱ ፥ የጨረቃ ወደብ ፥ (ፈረንሳይ)*

Читать полностью…
Subscribe to a channel