ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
ትኩስ ምግብ እስኪበርድ እንደምንጠብቀው ሁሉ፤ አንዳንዴም አለመግባባቶችም እስኪሰክኑ መጠበቅ መልካም ነው።
( ባዝሙል)
ኡስታዙ በአንድ የሰርግ መድረክ ላይ ፦ «ቆንጆ የሆኑትን ሴቶች አግቡ፣ ፉንጋ … አታግቡ) ብሎ ማስተማሩ ከሸሪዓ ጋር እውን የሚፃረር ነውን?
🔴 መልስ፦ እስልምና ጋብቻን ከደነገገባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ክብረ ንፅህና ለማግኘት እና እራስን ከሀራም ለመጠበቅ እና ያልተፈቀዱ ነገሮችን ከመመልከት ለመከልከል ነው። ይህንንም ለማሳካት እስልምና ሊያጫት የሚፈልጋትን ሴት ከማግባቱ በፊት ማየትን ያበረታታል፣ ይህም በጥንዶች በመካከላቸው ፍቅርና መተሳሰብ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ በፍቅር፣ በመዋደድ እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ደስተኛ እና ስኬታማ ቤተሰብ ይፈጥራል። አሊያ ግን ዲኗን ብቻ ብሎ መልኳን ሳያይ ቢያገባት፣ አላህ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ነገር ለመስራት ይፈተናል። ስለሆነም ውበት አንድ ሰው የትዳር ምርጫው ውስጥ እንዲያካትተው ከሚበረታታ ባህሪያት አንዱ ነው።
ኢብኑ ቁዳማህ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሙስሊም ቆንጆ ሴትን መምረጥ አለበት፣ ምክንያቱም ነፍሱ የሰከነ፣ አይኑን ከሀራም እይታ የተቆጠበ፣ ፍቅሩ የተሞላ እንዲሆን ያደርጋልና። ለዚህም እኮ ነው፤ ከጋብቻ በፊት የሚያጫትን ሴት መልኳን እንዲመለከት ሸሪዓው የደነገገው።”
شرح منتهى الإرادات" (2/621) :
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከሴቶቹ የትኞቹ ምርጦች ናቸው?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም፦“ሲመለከታት የምታስስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘውን፣ እሱ በሚጠላው መንገድ ራሷም ላይ ሆነ ንብረቱ ላይ የሚጠላውን የማትፈፅም ሴት ናት” በማለት መለሱ።
አንድ ሰው ማግባት ቢፈልግ፤ መጀመሪያ ስለ ውበቷ ይጠይቅ፣ ከዛ በማስከተል ስለ ዲኗ ይጠይቅ። ምናልባት በመልኳ የተነሳ ቢተዋት ለዲኗ ብሎ እንዳልተዋት ይነገራል።
ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሀንበል ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ወንድ አንዲት ሴት ሊያገባ ሲል በቅድሚያ ስለ ውበቷ ይጠይቅ፣ ስለ ውበቷ አድንቀው ከነገሩት በቀጣይ ስለ ዲኗ ይጠይቅ፣ ዲኗን ካወደሱሉት ያግባት። ይሁንና ዲኗ ላይ ክፍተት ካለባት ስለ ዲኗ ሲል እንጂ ስለ መልኳ እንዳልተዋት ይታዋቃል። ስለሆነም በቅድሚያ ስለ ዲኗ ጠይቆ ዲኗ ላይ ጥሩ መሆኗን ከነገሩት በኋላ ስለ መልኳ ጠይቆ፣ ቆንጆ እንዳልሆነች ቢነገረው፣ ለመልኳ ሲል እንጂ ለዲኗ ብሎ እንዳልተዋት ይነገራል።”
አንድ ሰው ውበትን ብቻ ሲፈልግ እና አኽላቅ እና ዲን ችላ ሲል ነው የሚወቀሰው። ዲን እና አኽላቅ የስኬታማ ትዳር ቁርጠኝነትን ምሶሶ እና ማገር ነው። አብዛኛው ሰው በውጫዊ ገጽታ ላይ ማተኮር እና ውስጣዊ ባህሪያትን ችላ በማለታቸው የተነሳ መልክተኛው፦ "…ዲን ያላትን ፈጥነህ አግባ" የሚል መመሪያ ያስተላለፉት። ወንዶች ሀይማኖታዊ ቁርጠኝነት እና መልካም ባህሪ ያላት ሴት እንዲፈልጉ ሀዲሱ ያሳስባል።
ለሴት ልጅ የትዳር ጥያቄ ከማቅረብ በፊት፣ የተጋነነ ውበት ባይሆንም ትዳር ፈላጊው ዘንድ ባለው የውበት ተቀባይነት ደረጃ ላይ እንዳለች ማረጋገጥ ከሸሪአው የሚፃረር አይደለም። ጉዳዩ መጀመሪያ ላይ ጉጉት እና የጋለ ወኔ ( ባዶ ሀማሳህ) ብቻ እንዳይሆን፣ ከዚያም ይህ ሁሉ ወኔ ከሽፎ ቀልቡ አዲስ ሁኔታን በጉጉት መፈለግ ይጀምራል፣ በትዳር ሕይወት ውስጥ አስቸጋሪ የሆነ የችግር ጉዞ እዚህ ጋ ይጀምራል።
👉ይህ በንዲህ እንዳለ የዲንና የአኸላቅ መመዘኛ የሁሉም ነገር ገዥ ይሁን።
በዚህ ሚዛናዊ አመለካከት እና ሚዛናዊ አስተሳሰብ ደስተኛ የሆነ የትዳር ህይወት ይፈጸማል። ኢንሻ አሏህ!
"የአላህን ሸሪዓ የሚዘነጋ ሰው፤በአጉል እምነት፣ ውሸት እና ያልተጣሩ ዘገባዎችን በማሰራጨት ላይ ይፈተናል።”
الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
የሐሰን ታጁ ተልቢስ
~
"ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ። የዑለማዎች አነጋገር ነው። 'መውሊድ ሰምቶ በጆሮው፤ መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም' ብለዋል ነብያችን። ተጠርቶ ደግሞ የቀረ ይጠላኛል' አሉ።"
ይሄ ሐሰን ታጁ ደግፎ የፃፈበት የሙሐመድ አወል ንግግር ነው። በሐሰን ታጁ ሙግት ላይ ሁለት ነጥቦችን አነሳለሁ።
ሀ. እያከ .ፈሩ ነው
በመጀመሪያ ሙሐመድ አወል ህልም ነው አላለም። እሱ ህልም ነው ባላለበት ሁኔታ በምን አግባብ ነው በቀጥታ በሰማው ላይ የፈረደ ሰው አጥፊ የሚሆነው? ያውም "በከሽፍ" ታየን እያሉ ማውራት ሱፊያ ሰፈር የተለመደ በሆነበት። እሱ ራሱ በዚህ እምነት የሚያምን ነው። እንኳን በነብዩ ﷺ ስም "ሐደሠኒ ቀልቢ ዐን ረቢ" እያሉ በአላህ ላይ የሚዋሹ ናቸው። ሙሐመድ አወል በመንዙማው የሚያወድሰው አቡ የዚድ አልቢስጧሚ (261 ሂ.) በሐዲሥ ሊቃውንት ላይ እየተጎረረ እንዲህ ይላል፦
" أخذتم علمكم ميتًا عن ميت، وأخذنا علمنا عن الحي الذي لا يموت، حدثني قلبي عن ربي، وأنتم تقولون: حدثني فلان، وأين هو؟ قالوا: مات، عن فلان وأين هو؟ قالوا: مات "
"እናንተ እውቀታችሁን ከሙታን በመቀባበል ነው የወሰዳችሁት። እኛ እውቀታችንን ከማይሞተው ህያው ጌታ ነው የወሰድነው። ልቤ ከጌታዬ ነገረኝ!! እናንተ ግን 'እከሌ ነገረኝ' ነው የምትሉት። የት ነው ያለው? 'ሙቷል' ይላሉ። 'ከእከሌ ይዞ' ይላሉ። የት ነው? 'ሙቷል' ይላሉ።" [አልፉቱሓቱል መኪያ፡ 1/365]
ሰዎቹ በዚህ ርቀት የሚሄዱ ናቸው። ሙሐመድ አወል ንግግሩ ህልም እንደሆነ ገልፆ ቢሆን ራሱ ንግግሩ መተቸት ያለበት ነው። መውሊድ ተጠርቶ የቀረ ነብዩን ﷺ ይጠላል ማለትኮ በሸሪዐ ላይ መቅጠፍ ብቻ ሳይሆን የለየለት እብ.ደት ነው። እንዲህ አይነቱን የተለመደ የሱፊያ ብልግና ነው ወይ እንደ ዋዛ በህልም እያስታከካችሁ ህዝብ ላይ የምትዘሩት? ሌሎች ላይ የክህደት ብይን እያሳለፋችሁ ከዚያ ስለ ፅንፈኝነት ስታወሩ አታፍሩም። ሙሐመድ አወል ባስተላለፈውና ሐሰን ታጁ ባፀደቀው ንግግር መሰረት
1. መውሊድ ሰምቶ የቀረ ሰው ነብዩን አይወድም ማለት ነው።
2. መውሊድ ተጠርቶ የቀረ ደግሞ እሳቸውን ይጠላቸዋል ማለት ነው።
ነብዩን ﷺ የሚጠላ ሰው ሙስሊም አይደለም። ከሃዲ ነው። ይሄ ነው አቋማችሁ አይደል? መውሊድን የሚቃወምስ? የባሰ ነው ማለት ነው። በዚህ ሂሳብ መሰረት ከዑለማእ እስከ ተራ ህዝብ ስንትና ስንት ሰው እያከ . ፈሩ እንደሆነ ማሰብ ነው። በህልም ሑክም መገንባት ይቻላል ካለ በሙሐመድ አወል የተላለፈው "ህልም" ይህንን ሑክም ነው የሚሰጠው። የሐሰን ታጁ አቋም ይሄ ነው ማለት ነው። በርግጥ ሰውየው ኢብኑ ተይሚያን ጨምሮ መውሊድ የሚቃወሙ ሰዎችን የነብዩን ﷺ ቤተሰቦች በመጥላት (ነስብ) ችግር የሚከስ ነው። ይሄ የብዙ ሱፊዮች መታወቂያ ነው። መውሊድን የሚነቅፉ ሰዎችን ነብዩን ﷺ በመጥላት፣ የሞቱ ሰዎችን ከመማፀን የሚከለክሉትን ደግሞ ወሊዮችን በመጥላት ሲከሱ ማየት የተለመደ ነው።
ለ. እውነት በህልም ሑክም መገንባት ይቻላል? ከዚህ የሐሰን ታጁ ድጋፍ የምንወስደው በህልም አሕካም መገንባት ይቻላል የሚል ነው። ይሄ ብዙ ነገር ይከተለዋል።
1. አንድ ሰው ሐላሉን ሐራም፣ ሐራሙን ሐላል የሚያደርግ ህልም ቢያይ እሱን ተከትሎ ለህዝብ አዋጅ አውጆ በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጠን ጉዳይ መቀየር ይችላል ማለት ነው።
2. ህልሙን ተከትሎ ሰዎችን የነብዩ ﷺ ወዳጅ፣ የነብዩ ጠላት፣ ... እያሉ መፈረጅ ይቻላል ማለት ነው። ይህንን ነው ሙሐመድ አወል ባደባባይ ያወጀው።
3. ህልም ተከትሎ "ነገ ረመዷን ነው"፣ "ነገ ዒድ ነው" እያሉ ማወጅ ይቻላል ማለት ነው።
4. ህልም ላይ ተመስርቶ ወንጀለኛን መለየት፣ ቅጣት ማስተላለፍ፣ ... ይቻላል ማለት ነው። በነገራችን ላይ አልመህዲ በመባል የሚታወቀው ኸሊፋ ህልም ላይ ተመስርቶ ታላቁን ሰለፍ ሸሪክ ብኑ ዐብዲላህን ሊገድላቸው ነበር። "ያንተ ህልም'ኮ የ(ነብዩ) ዩሱፍ ብኑ የዕቁብ ህልም አይደለም። የሙስሊሞች ደም በህልም አይፈሰስም" ሲሉት ነው የቆመው።
እንዲህ አይነት አካሄድ ዲነል ኢስላምን ከመሰረቱ መናድ ነው። ይሄ ለአጭበርባሪዎች በር መክፈት ነው። "በህልሜ ነብዩን ﷺ አይቼ እከሌ አይወደኝም" ብለዋል ቢል፣ "ለሌሎች የተከለከለው መጠጥ፣ ዝሙት፣ ... ላንተ ግን ተፈቅዶልሃል አሉኝ" ቢለን ልንቀበለው ነወይ? እንዲህ አይነቱን አደገኛ በር በምንድን ነው የምንዘጋው? በሱፊያው ዓለም እንዲህ አይነት ዘናዲቃ በሰፊው አሉ። እንደ አሕመደል በደዊ ሶላት የማይሰግዱ፣ ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው የሚሉ ብዙ አጭበርባሪዎች አልፈዋል። በርካታ ሱፊዮች ዘንድ ከሸሪዐ የመረጃ ምንጮች ውስጥ አንዱ ህልም ነው። ሐሰን ታጁም ይህንን ነው ያንፀባረቀው።
ብዥታ!
~
ኢብኑል ቀዪም ሸይኻቸዉ ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለው ነገሩኝ ይላሉ፡-
"ሶላተል ጀናዛ የምሰግድበት ሰው አማኝ ይሁን ሙና .ፊቅ ለመለየት አንዳንድ ጊዜ እቸገራለሁ። የአላህ መልዕክተኛን በህልም አየኋቸውና ይህንን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን አቀረብኩላቸው፡፡ 'አሕመድ ሆይ! ዱዓህን ከቅድመ ሁኔታ ጋር አቆራኝ' አሉኝ።"
"ከቅድመ ሁኔታ ጋር" ማለት ምን ማለት ነው? ሶላተል ጀናዛ ማለት ለሙስሊም ሟች የሚደረግ ዱዓእ ነው። ሙስሊም ባልሆነ ላይ አይሰገድም። ሟቹ ሙና .ፊቅ ቢሆንስ የሚል ጥርጣሬ ያለው ሰጋጅ በዱዐው ላይ "አማኝ ከሆነ ማረው" እና መሰል ዱዓእ ያደርጋል ማለት ነው።
ሐሰን ታጁ ይህንን የኢብኑ ተይሚያ ህልም ከሙሐመድ አወል ንግግር ጋር ተመሳሳይ ነው ብሏል። ይሄ ድምዳሜ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው።
1ኛ፦ ሙሐመድ አወል ህልም ብሎ አላወራም። ይህንን ከያዝን ኢብኑ ተይሚያን "ተማሪዎቻቸዉ ሸኻቸዉን በነብዩ (ﷺ) ላይ ቀጠፉ ብለዉ እንዳላሟቸዉ" የሚለው የሐሰን ታጁ ንግግር ውሃ የማይቋጥር ሆኖ እናገኛዋለን። ኢብኑ ተይሚያ ህልም እንደሆነ በግልፅ ተናግረዋልና።
2ኛ፦ የቀረበው ጥቅስ ላይ ኢብኑ ተይሚያ በህልም ላይ አሕካም ገነቡ የሚል የለም። ይሄ ሐሰን ታጁ የፈጠረው ነው። እንጂ ኢብኑ ተይሚያም ኢብኑል ቀዪምም በህልም ሑክም እንደማይገባ በግልፅ ይናገራሉ። ይሄው የኢብኑ ተይሚያ ቃል፦
"ኢስራ -ኢሊያት ዘገባዎች፣ ህልሞች፣ የሰለፎችና የዑለማእ ንግግሮች፣ የዑለማእ ገጠመኞችና መሰል ነገሮች በነሱ ላይ ተመርኩዞ የሸሪዐ ብይን ማፅናት አይቻልም። ሙስተሐብነትም ይሁን ሌላ። ነገር ግን ለማነሳሳትና ማስፈራራት (ተርጊብ እና ተርሂብ) ማውሳት ይቻላል።'' [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 18/66]
ኢብኑል ቀዪምም እንዲህ ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ይናገራሉ፦
"የነብያት ህልም ወሕይ ነው። ከሸይጧን የተጠበቀ ነውና። ይሄ የህዝበ ሙስሊሙ ወጥ ስምምነት ያለበት ነው። ለዚህም ነው የአላህ ልዩ ወዳጅ (ኢብራሂም) በህልም ላይ ተመርኩዘው ልጃቸውን ኢስማዒልን ለማረድ ያመሩት። በሁለቱም ላይ ሰላም ይሁን። ከነሱ (ከነብያት) ውጭ ያሉ አካላት ህልም ግን ግልፅ በሆነ ወሕይ ላይ ይቀረቡና ከገጠሙ እሰየው፣ ካልሆነ ግን አይሰራባቸውም።" [መዳሪጁ ሳሊኪን፡ 1/51]
ልብ በሉ! ህልሙ ኖረም አልኖረም የሚሰራው በወሕዩ ነው። ህልሙ ራሱን ችሎ አዲስ ሑክም ለማስተላለፍ አይሆንም እያሉ ነው።
በደቡባዊ ሜክሲኮ በጃሊስኮ ግዛት በ2016 አ/ል ስርቆቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተሰራጭተው ፖሊስ እነዚህን ወንጀሎች መመርመርም ሆነ ሌቦችን መያዝ እስከማይችልበት ደረጃ ደርሶ ነበር።
በጓዳላጃራ (የግዛቱ ዋና ከተማ) የሌቦች ቡድኖች በየመንገዱ ከተሰራጩ በኋላ ሰዎች ንብረታቸውን እራሳቸው ለመጠበቅ ተገድደው ባንኮች እና አብዛኛዎቹ ሱቆች በራቸውን ዘግተዋል።
ስለሆነም ህዝቡ ከሀገሪቱ ህግ እና ሥልጣን ርቀው በሌቦች ላይ የማያዳገም እርምጃ ለመውሰድ ተገደዱ፣ ይኸውም ማንኛውም ሰው ሰርቆ ሲገኝ እጅ የሚቆርጥ ቅጣት ተግባር ላይ አዋሉ።
እ.ኤ.አ. በ2017 ከ688 በላይ የሌቦች እጅ እንደተቆረጠ የተመዘገበ ሲሆን በሜክሲኮ ህግ መሰረት ይህ እንደ ወንጀል ቢቆጠርም ፖሊስ እና የመንግስት ባለስልጣናት ይህን መሰል ድርጊቶችን ዓይናቸውን ጨፍነዋል፣ አልፎ ተርፎም ይህን ወንጀል ለሚፈፅሙ ግለሰቦችን ከለላ ይሰጡ ነበር።።
በተለይም በአንድ አመት ውስጥ የስርቆት ወንጀሎችን በ81 በመቶ በመቀነሱ፣ ይህን ቅጣት ተፈፃሚ ላደረጉ ሰዎች ምስጋና ይግባውቸውና ግዛቱ በሜክሲኮ ውስጥ ካሉ ግዛቶች እጅግ በጣም አደገኛ ከሆነ በኋላ በጣም ሰላም እና ደህንነት ከሰፈነባቸው ከሆኑ ግዛቶች አንዱ ሆኗል።
እንዲያውም ጉዳዩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በህዝቡ ድጋፍ ቅጣቱ ህጋዊ እንዲሆን በፓርላማ እንዲፀድቅ እስከመጠየቅ ደረሱ። ይሁንና ሊበራል ፓርቲዎች ከሰብአዊ መብት ማኅበራት ጋር አጥብቀው ተቃውመዋል። እ.ኤ.አ. በ 2018 ምንም እንኳን የሜክሲኮ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ የሌቦችን እጅ መቁረጥ እንዳለበት ድጋፉን አሳውቋል።
የሌቦችን እጅ የመቁረጥ ቅጣት (እስልምና ከ1,400 ዓመታት በፊት የደነገገው) በሜክሲኮ ብቻ ሳይገደብ በብራዚል፣ ቬንዙዌላ እና ኢኳዶር በመስፋፋት የሌብነት ወንጀሎችን በተሳካ ሁኔታ መፍትሄ ሊያመጣ ተችሏል። በሰው ሰራሽ ሕግ የተደነገጉ ሕጎች ሰዎችን መጠበቅ አልቻሉም። ከ 1,455 በላይ ሌቦች ከህግ ውጭ እጆቻቸው ተቆርጠዋል።
ለዚህም እኮ ነው አላህ የዚህን የሸሪዓ ህግ መደንገግ በቁርኣን ካወሳ በኋላ "ህይዎት" በሚል ያወሳው።
(وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ #حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ!)
«ለእናንተም ባለ አእምሮዎች ሆይ! በማመሳሰል (የሸሪዓ ሕግ) ውስጥ #ህይወት መትረፍ አላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ (ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ)፡፡»
[አል-በቀራህ: 179]
ምንጭ ፦
https://www.reuters.com/article/us-mexico-election-bronco/cut-off-hands-mexican-presidential-candidates-plan-to-deter-thieves-idUSKBN1HU0DZ
https://www.dailymail.co.uk/video/news/video-1344219/Seven-suspected-thieves-Mexico-hands-severed.html
https://www.theguardian.com/world/2018/apr/24/corpse-dumped-in-acapulco-after-presidential-candidate-says-cut-off-hands
أُعلن فرحتي بأحلى خبر وأبشركم بقدوم أغلى البشر، وصول مولودتي الجديدة، الله يحفظها لي من كلّ خطر. وينبتها نباتا حسنا.
Читать полностью…🔴የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
وفي السماء رزقكم…
❗️ሲሳያችሁ ከሰማይ ነው!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ሰፈር 10/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
📌 دورة ميراث الأنبياء العلمية الرابعة
من ١٢ صفر ١٤٤٦هے الموافق ١٦\٨\٢٠٢٤م إلى يوم الأحد ٢١ صفر ١٤٤٦هے الموافق ٢٦\٨\٢٠٢٤م
١) الدرة المضية في عقد الفرقة المرضية
🎙 د/ إسماعيل بن غصاب العدوي حفظه الله
ےے❊❊ےے
٢) منظومة القواعد الفقهية لابن سند
🎙 د/ خالد بن شجاع العتيبي حفظه الله
ےے❊❊ےے
٣) النظم المعسول في تعليم الأصول
🎙 د/ عبد الرحمن حامد آل نابت حفظه الله
ےے❊❊ےے
٤) مقدمة في أصول التفسير لابن تيمية
🎙الشيخ إلياس أحمد محمد حفظه الله
ےے❊❊ےے
٥) لامية ابن الوردي في الآداب
🎙د/عبدالرحمن بن صالح المزيني حفظه الله
ےے❊❊ےے
٦) متممة الآجرومية
🎙 الدكتور خليل حامد خليل حفظه الله
ےے❊❊ےے
👈 ملاحظة
* هناك محاضرات مختلفة تصاحب الدورة
* الخدمات للطلاب المسجلين فقط ولكن يحق الاستفادة من الدروس للجميع
* جميع الدروس باللغة العربية فقط
* الدروس تخص الرجال دون النساء
🕌 مكان إقامة الدورة
مركز ابن مسعود الإسلامي في حي ١٨
⛳️ الموقع على الخريطة
https://goo.gl/maps/oC7GZtpeLwkzxrVr8
___
🕌 Ibnu Mas'oud islamic center
t.me/merkezuna
"በአላህ እምላለሁ! በአኼራ ላይ ፍርሃት እስኪያገኝህ ድረስ በዱንያ ከሚያስተማኑ ሰዎች ጋር ከመቀላቀል በአኼራ ላይ ደህንነት እስከምትደርስህ ድረስ ዱንያ ላይ ከሚያስፈራሩህ ሰዎች ጋር ብትቀላቅል… ብትቀማመጥ
ይሻላሃል።"
(ሐሰነል በስሪይ)
ሚስት ሆይ...
የቤትሽን ምስጢሮች በወሬዎችሽ መሀል የወሬ ማጣፈጫ ላለማድረግ ፣ ሚስጥር እንዳያመልጥሽ ጥንቃቄ አድርጊ! ጓደኛሽም ልብሸ መቋጠር ያልቻለውን ሚስጥርና ገመና የምትጠብቅልሽ እንዳይመስልሽ..!!
#የትዳር_ህይወት
تعلن #الجامعة_الإسلامية عن بدء استقبال طلبات الدراسة لبرنامج (الشريعة) عن بُعد، للطلاب والطالبات الدوليين المقيمين خارج المملكة، ابتداءً من يوم الاثنين 23 محرم 1446هـ، ولمدة 30 يومًا. للتقديم:
distancelearning.iu.edu.sa
«ሚስኪን! የአደም ልጅ፤ ድህነትን እንደሚፈራ ጀሀነምን ቢፈራ ጀነት ይገባ ነበር።»
ታሪኽ ባግዳድ(14(215)
ሸይኽ ዑሠይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“አንድ ሰው ለሰዎች ቀልብ ትኩረት መስጠት አለበት፣ የአንድ ሰው ቀልብ ከተሰበረ, በተቻለ መጠን ቀልቡን ለመጠገን ከፍተኛ ጥረት ሊያደርግ ይገባል፣ ምክንያቱም በዚህ ውስጥ ትልቅ ውለታ አለና።”
📚فتح ذي الجلال والإكرام بشرح بلوغ المرام 4/ 5
/channel/sultan_54
👆👆👆 አለህን የሚፈሩ ሰዎች ደረጃ
እና ዱኒያ አለህ ዘንድ ያላት ቦታ
👉ከልባችን ልናዳምጠው የሚገባ ሙሃደራ
አደራ ለሌሎችም እናስተላልፍ
🦯በኡስታዝ መሐመድ አረቦ
"ኢላሂ!
እኛ ዘንድ ባለ ክፋት አንተ ዘንድ ያለን መልካም ነገር አትከልክለን።"🤲
«በአላህ ይሁንብኝ! ግንባሮች ከስግደት ብዛት ቢያብጡ፣ አጥንቶቹም ከመጠን በላይ በመፆም እና ለይል ሰላት በመስገድ ብዛት ቢደቅቁ፣ በተውሂድ ካልሆነ በስተቀር ጀነት እርም ነች።»
አሽ_ሸይኽ ሙሐመድ አል ፊፊይ
🎙ይህን ማራኪ ቲላዋህ እስኪ በጥሞና እናድምጥ!
አል ቃሪእ አሽ_ሸይኽ ሙሐመዱ አዩብ ረሕመቱላሂ ዐለይሂ!
3ኛ፦ በኢብኑ ተይሚያ ህልም ላይ የተገለፀው በዱዓእ ላይ ሸርጥ ማድረግ ተጨባጭ የቁርኣንና የሐዲሥ መረጃ የመጣበት ነው። [አኑር፡ 7፣ 9] [አልቡኻሪይ፡ 1162] ከመውሊድ የቀሩ ሰዎችን ነብዩን ﷺ ይጠላሉ እያሉ መፈረጅስ? ቁርኣንም ሐዲሥም ውስጥ የሌለ ከሱፊያም የሁሉም ሳይሆን የባለጌዎቹ እምነት ነው። ባለጌዎች ያልኩት በአላህ ዲን ላይ በግምት እየዘባረቁ በቢድዐቸው ላይ ያልተጋራቸውን አካል ነብዩን ﷺ በመጥላት ክህደት የሚፈርጁትን ነው። የሚከፋው አለ? ምን ገዶን!
4ኛ:- ሐሰን ታጁ ስለ ኢብኑ ተይሚያ "ተማሪዎቻቸዉም ከሸኻቸዉ የሰሙትን ለትዉልድ እንዳስተላለፉ" "ይህን ያመኑበትን ዕዉነት ለተማሪዎቻቸዉና ለህዝብ እንዳወጉ" በማለት የሙሐመድ አወል ንግግር በዚህ መልኩ ማመሳሰሉ ተልቢስ ነው፣ ማምታታት። ህልም ለምን ተወራ ያለ የለም። በነብዩ ﷺ ስም ሃሰተኛ ወሬ ማውራት፣ ያውም የመውሊድ ቢድዐ ላይ ያልተገኘ ነብዩን ﷺ ይጠላል የሚል ነውረኛ ክስ መክሰስን ነው የተቸነው። ይህንን የብልግና ንግግር እንዲያው ላመል ያህል በስሱ እንኳ አልነቀፈም።
ከላይ ኢብኑ ተይሚያና ኢብኑል ቀዪም ህልም ላይ ተመርኩዞ አሕካም እንደማይገነባ የገለፁበትን አስፍሬያለሁ። ይሄ የነሱ አቋም ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ያክል የነወዊይን ንግግር ልጥቀስ፦
"የሸዕባን 30ኛ ሌሊት ገብቶ ሰዎች ጨረቃ ባያዩና አንድ ሰው ነብዩን ﷺ በህልም አይቶ 'የዛሬዋ ሌሊት የረመዷን መጀመሪያ ነች' ቢሉት በዚህ ህልም መፆም ልክ አይሆንም። ለባለ ህልሙም ይሁን ለሌሎች። ቃዲ ሑሰይን በ'አልፈታዋ' እና ሌሎችም ባልደረቦቻችን ይህንን አውስተዋል። በዚህ ላይ ቃዲ ዒያድ #ኢጅማዕ እንዳለበት አስተላልፏል።" [አልመጅሙዕ፡ 6/284]
ኢጅማዕ የሚለውን አስምሩበት። በተጨማሪ በግልፅ አንድ ሰው በህልሙ ነብዩን ﷺ ቢያይ እንኳ "ሸሪዐዊ ብይን በሱ ላይ ማፅናት አይቻልም" በሸሪዐ የተረጋገጠ ጉዳይ በህልም እንደማይቀየር የዑለማእ ስምምነት (ኢጅማዕ) አለበት የሚል በሶሒሕ ሙስሊም ሸርሕ ላይ እናገኛለን። [1/115]
አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢይም እንዲሁ በተግባራቸው ላይ ህልም ላይ የሚመረኮዙ አካላት ሙግታቸው የመጨረሻ የደከመና የተሳሳተ ነው ብለዋል። [አልኢዕቲሷም፡ 1/331] ከዘከርያ አልአንሷሪይ እና ከሸውካኒም ተመሳሳይ ነገር እናገኛለን። [ፈይዱል ቀዲር፡ 6/132] [ኢርሻዱል ፈሑል፡ 2/291-292]
በነገራችን ላይ ህልም ዋጋ የለውም እያልኩ አይደለም። የሙእሚን ህልም ያለውን ዋጋ የሚጠቁሙ ሐዲሦች በተጨባጭ አሉና። ዋጋው ምንድነው የሚለውን መለየት ግን ያስፈልጋል። ያለበለዚያ በሸሪዐ አመሀኝቶ ሸሪዐን መናድ ነው የሚከተለው። ስለዚህ ጉዳዩ በልክ መያዝ አለበት። ነብዩን ﷺ አየሁ ባይል እንኳ ከታማኝ አካል እስከመጣ ድረስ ህልምን ማጣጣል አይገባም። በሌላ በኩል የፈለገ ታማኝ ቢሆን "ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉኝ" ቢል ህልምን የተሽሪዕ መሰረት ማድረግ፣ ሐላልና ሐራምን መበየን፣ ህግጋት ማሳለፍ፣ እከሌ የጀነት ነው እያሉ ቁርጥ አድርጎ ለመደምደም አይሆንም። ሰዎችን የነቢ ጠላት እያሉ መወንጀል ስህተት ብቻ አይደለም፤ ብልግናም እንጂ። ብቻ እንደ ማሳሰቢያ ወይም እንደ ምስራችና ተስፋ ሊውል ይችላል። ያለበለዚያ ለጋጠ ወጦች መረማመጃ ነው የሚሆነው። ኢብራሂም አልሑስሪ ሷሊሕ ሰው ነበር። ኢማሙ አሕመድ ዘንድ ገባና "እናቴ እንዲህ እንዲህ የሚል ጥሩ ህልም አይታልሃለች። የጀነት እንደሆንክ አውስታለች" አለ።
በዚህን ጊዜ፡ "ወንድሜ! ሰህል ብኑ ሰላማን ሰዎች እንዲህ አይነት ነገር ይነግሩት ነበር። ከዚያ ደም ወደ ማፍሰስ ነው የወጣው። ህልም አማኝን ያስደስታል እንጂ አይሸነግልም" አሉት። [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 11/227]
በቀጣይ ታላላቅ የሱፊያ "ወሊዮች" ነብዩን ﷺ በህልም አየን እያሉ መርዛማ እምነቶቻቸውን ወደ ህዝብ ለማሰራጨት የተጠቀሟቸውን ሴራዎች እዳስሳለሁ ኢንሻአላህ።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሃሴ 21/2016)
🖼ማስታወቂያ
ከኢማሙ ማሊክ የቁርዓን ሒፍዝ ማዕከል
ለ2017እና 2018 በአዳር መማር ለምትፈልጉ ምዝገባ ጀምረናል
🖼መሟላት የለባቸው መስፈርቶች
1 እድሜ ከ10 አመት በላይ
2 እስላማዊ ስነምግር መላበስ
3 መርከዙ የሚያስቀምጣቸውን ህግና ደንብ ታዛዥ ለመሆን ረስን መዘጋጀት
4 ቁርዓን የኸተመ ቢሆን ይመረጣል
የሚሰጡ ትምህርቶች;
🪞 ቁርዓን ሒፍዝ
🪞ቁርዓን በነዘር
🪞ቃዒደቱ አንኑራኒየህ
🪞ተጅዊድ
🪞አቂዳ
🪞ሐዲስ
🪞ኣዳብ
🪞ነህው
🪞ሲራ
መርከዙ ሚቀበለው ወንዶችን ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ +251910994001/+251912614226
አድራሻ; ፉሪ ዲያስፖራ ሰፈር
የቴሌግራም ጉሩፕ
/channel/imamumalk
/channel/imamumalk
ታላቁ ሸይኽ ሙሐዲስ አልዐስር ሸይኹ አልአልባኒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"በዚህ ዘመን ከተሰራጩ አስቀያሚ እና ትርጓመያቸውም አስጠሊታ ከመሆናቸው የተነሳ በፍጥነት መቀየር ካለባቸው እና
ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን መሰየም ከተያያዙት ስያሜዎች መካከል፦
(ዊሳል) (ሲሃም) (ኑሃድ) (ጋዳህ) (ፊትናህ) እና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
ወላሁ ሙስተዓን።
【ሲልሲለቱ አሰሒሃ (1/427)】
الشيخ الدكتور إسماعيل العدوي -حفظه الله- يواصل درسه الثالث في دورة ميراث الأنبياء العلمية بمركز ابن مسعود الإسلامي بأديس أبابا إثيوبيا.
لمتابعة الدرس على اليوتيوب
https://www.youtube.com/live/h9Gin5B_u_A?si=HTObzjmJnrj1MG-I
🔴 በቢድዓ ሰዎች ሞት መደሰት… ሸሪዓዊ አቋም
እውነተኛ ሙስሊም የነብዩን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱና የተከተሉ ሊቃውንት እና ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ዱዓቶች ሞት እንደሚያዝን ሁሉ የቢድዐ እና የጥመት ሰዎች እና ወደ ቢድዓ ጠሪዎችን በመሞታቸው ይደሰታል። በተለይም መሪዎች፣ የቢድዓ ምልክቶች ቲዎሬቲስቶች የሆኑ በመጥፋታቸው ብዕራቸው ይሰበራል እንዲሁም ሰዎችን የሚያደናግሩበት ሀሳባቸው ይገታልና የሀቅ ደጋፊ በነዚህ ሰዎች ሞት ይደሰታል።
ቀደምት ሰለፎች የቢድዓ ሰዎች በህይወት እያሉ የሚያስጠነቅቁ ብቻ አልነበሩም። ይልቁንም ከሞቱም በኋላ ከእነሱ ያስጠነቅቁ ነበር። አላህ ምህረትን እንዲያደርግላቸው እና በመለየታቸው የሚያዝኑ እና የሚያለቃቅሱ አልነበሩም እነሱ በመሞታቸው ደስታን ይፋ ያደርጉ፣ እርስ በርሳችሁ የምስራች ይባባሉም ነበር።
በአቡ ቀታዳ አል-አንሷሪ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የተላለፈ እና ቡኻሪና ሙስሊም ተዘግቦ እንደመጣው እነዚህና አምሳያቸውን ሞት አስመልክቶ ፤ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
“(በእነሱ ሞት) ሰዎች፣ ምድር፣ ዛፎቹ እና እንስሳት ከእነሱ እፎይታ ያገኛሉ። ” አንድ ሙስሊሙ የሰዎችን እምነት የበከለ እና ሽርክን በሀገሪቱ ላይ ያስፋፋ ሰው ሲሞት እንዴት ደስ አይለውም?
የጥመት አራማጅ አል-ሚር– ሪይሲይ እና የቢሽር ብን አል-ሓሪስ የሞት ዜና በገበያ ላይ በተሰማ ጊዜ እንዲህ አሉ፡-
(ዝና ይሆናል ብዬ ባልሰጋ ኖሮ! የምስጋና ሱጁድ ቦታ ይኼ ነበር። እነርሱን ለገደለው አምላክ ምስጋና ይሁን።)
ታሪኹል በግዳድ 7/ 66
ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል እንዲህ ተባሉ፡- “ሰውየው የኢብኑ አቢ ዳዋድ ተከታዮች በሚያጋጥማቸው አደጋ ይደሰታልን? ይህን ማድረጉ ኃጢአት ነውን? እርሳቸውም፡-
(በዚህ የማይደሰት ለመሆኑ ማነው?!” በማለት መለሱ።
(አስ– ሱና ሊል ኸላል፡ 5/121)
ሰሰማህ ኢቢኑ ሸቢብ እንዲህ ይላሉ፡-
“ እኔ ከአብዱረዛቅ አስ– ሰነዓኒይ ጋር ነበርኩ የአብዱልመጂድ ሞት ወደ እኛ ሲመጣ እና እንዲህ አሉ፡- ( ኡመተ– ሙሐመድን ከዐብዱል መጂድ ማደናገር ህዝቡ የገላገለ አምላክ ምስጋና የተገባው ይሁን። )
[ሲያር አእላም አኑ-ኑባላእ፡ 9/435]፣
ይህ አብዱልመጂድ ኢብኑ አብዱል አዚዝ ቢን አቢ ረዋድ የተባለው ግለሰብ የ“ኢርጃእ” መሪ ነበር።
ቀደምት ሰለፎች አላህ ይዘንላቸው ከቢድዓና የጥመት ሰዎች መሪዎች አንዱ መሞቱን በሰሙ ጊዜ የነበራቸው አቋም ይህ ነበር።
👉 አንዳንድ ሰዎች ይህንን አቋም በመቃወም አል-ሐፊዝ ኢብኑል ቀይም በ [መዳሪጅ አስ-ሷሊኪን 2/345] ላይ ስለ ሸይካቸው ሸይኽ አል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ተቃዋሚዎቻቸው ጋር ስለነበራቸው አቋም ባስተላለፉት ዘገባ እንዲህ ብለዋል፡-
“…እኔም አንድ ቀን የርሳቸውን ቀንደኛ ጠላቱን ሞት ላብስራቸውው መጣሁ፣ እሳቸውም ኢና ሊላህ… በማለት እንዴት ጠላቴ በመሞቴ ታብስረኛለህ ብለው ተቆጡኝ ገሠጹኝም…”
የሚለውን የሸይኹን አቋም በቢድዓ ሞት መደሰት እንደማይቻል መረጃ አድርገው ያቀርባሉ።
ነገር ግን ይህንን ክስተት በደንብ በማሰላሰል የተመለከተ በሁለቱ ጉዳዮች መካከል ምንም የርሰ በርስ ግጭት እንደሌለ ይገነዘባል። ሸይኽ አል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ለራሳቸው ለነፍሳቸው የሚበቀሉ አልነበሩም። ስለዚህም ተማሪያቸው ወደ እርሳቸው በመምጣት ከተቀናቃያቸው ቀንደኛ ጠላት መካከል የአንዱን መሞትና ስላበሰራቸው የወቀሱት። ተማሪያቸው የሼይኩ ተቃዋሚው እና ቀንደኛ ጠላት ሞት የተሰማውን ደስታ ብቻ ነበር ያበሰሯቸው እንጂ የቢድዓ አራማጅ ከመናፍቃንና የጥመት መሪዎች አንዱ በመሞቱ የተሰማውን ደስታ አልነበረም ያበሰራቸው።
በጣም የሚያሳዝነው ከዚህ የሰለፎች አቋም ባፈነገጠ መልኩ አንዳንድ ሰዎች የቢድዓ እና የሽርክ አራማጆች ሞት ደስታ ፈንታ -
በመጸጸት እና በሀዘን ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ ሲሞት ያለቃቅሳሉ ሞሾም ያወርዳሉ ፣ በሙስሊሙ ላይ መሰላቸውን እንዲተካላቸው አላህን ይማጸናሉ - አላህ ዱዓቸውን አይሰማቸውና! ፍላጎታቸውንአያሳካላቸውና። እንደእነዚህ አይነት ሰዎች ማቾቹ የቢድዐ ሰዎች መሆናቸው እና የእነሱን ስህተታቸውን እያወቁ ከሆነ ይህን የሚያደርጉት፣ በዲናቸው ላይ አደጋ ይሰጋባቸዋል። ምክንያቱም አላህን የሚፈራና ለዚህ ሀይማኖት ዲነል–ኢስላም የሚቆረቆር ሙስሊም ሁሉ፣ እርሱ በመኖሩ የእስልምና ደብዛው እንደሚጠፋ የሚያውቅ ሰው ሲሞት ይደሰታል። ምክንያቱም በእነርሱ ሞት የተነሳ አንዱ የኢስላም ማፈራረሻ መዶሻ ይወገዳልና። ሙስሊም ሁሉ በአህሉል ቢድዓ ሞት ይበሰራል።
አላህ የጥመት ጠሪ ሁሉ፤ በመጥፋቱ እንዲያስደስተን፣ ሀቁን እንደ እውነት እንዲያሳየንና እንድንከተለው እንዲያደርገን፣ ባጢልን ውሸት አድርጎ እንዲያሳየንና እንድንርቀው እንዲያደርገን እንለምነዋለን። በዲነል ኢስላም ቁርኣን እና የነብዩን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ላይ ፀንተን እንድንቆይ እና በዚያ ላይ እንድንሞት ሀያሉን ጌታችን እንማፀነዋለን።
قال بلال بن سعد رحمه الله :
يقال لأحدنا تريد أن تموت؟
فيقول لا.
فيقال له: لم؟
فيقول: حتى أتوب وأعمل صالحاً.
فيقال له: اعمل.
فيقول: سوف أعمل..
فلا يحب أن يموت
ولا يحب أن يعمل،
فيؤخر عمل الله تعالى
ولا يؤخر عمل الدنيا!
[العاقبة في ذكر الموت : ( ٩١ )]
جديد: تلاوة حجازية محبرة للقارئ: هشام المقدشي
Читать полностью…ሸይኽ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
“ዲን ያላት ሴት ማለት፦የአላህን ትዕዛዛትን በአግባቡ የምትወጣ፣የባሏን መኝታ፣ልጆቹንና ንብረቱን ባጠቃላይ ሐቁን የምትጠብቅ ናት፣በተጨማሪም የአላህ ትዕዛዛትን እንዲወጣ በማስታወስ የምትረዳው፣ ከዒባዳ ሲሰላች እንዲነቃ የምታደርገው ሲሆን ሲበሳጭ ወይም ሲናደድ ቁጣውን የምታበርድ ሴት ናት።"
[አዝ–ዘዋጅ ገፅ 20]
የኑሮ ውድነት እና ተውሒድ
التوحيد حل لقضية الضيق في المعايش
لفضيلة الشيخ الدكتور عبدالرحمن حامد آل نابت
ኑሮ ተወደደ? ዶላር ጨመረ? ዋጋ አሻቀበ?
እንግዲያውስ ይህ የተውሂድ መጓደል ምልክት ነው።
የተውሒድ መጓደል የኑሮ ውድነትን ያስከትላልን?
እንዴት?
መረጃውስ ምንድን ነው?
ለዚህ ሁሉ መልስ እንዲሁም ተጨማሪ ምክሮች ለዱአቶች ያዘለ
በሱዳኒው ሸኽ ዶክተር አብዱረህማን ሃሚድ አል ናቢት።
/channel/sultan_54
♻️የጁሙኣ ኹጥባ
«የኑሮ ውድነት"
🎙በኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን
🕌ፉሪ ሰልሰቢል መስጂድ
ሙሐረም 27/01/1446ዓ/ሂ
/channel/ibrahim_furii
👆👆ከሱረቱ ዐስር ጥላ ስር
ክስረት እና ስኬት
በላፍቶ ቢላል መስጂድ/አዲስ አበባ
በታላቁ ሸይኽ ዶክተር ኻሊድ ዐብዱ አል–ለጢፍ የቀረበ
ከአማርኛ ትርጉም ጋር
በሌሊቱ መጨረሻ፤ ሰዎች ይተኛሉ፣ ህያው እና ዘላለማዊው አምላክ ለርሱ ክብርና ሞገስ በማይፃረር መልኩ ወደ ሰማይ ይወርዳል፣ በዚህ ሰአት ይቅርታን ለሚለምን፣ ለሚማፀን ሁሉ የምስራች!
የሐጅ ቆይታ ትዝብቴ
~
የአላህ ፈቃዱ ሆኖ በተጠናቀቀው የሂጅራ አመት 1445 ለሐጅ ከተጓዙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ አንዱ ነበርኩ። የሄድኩት ለአንድ ወንድሜ አባት የውክልና ሐጅ ለመፈፀም ነው። ምናልባት ለሌላ ጊዜ እንደ ግብአት ካገለገለ በሚል የሐጅ መስተንግዶውና ተያያዥ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ጥቂት ማለት ወደድኩ። ዝርዝር ውስጥ ከመግባቴ በፊት አዲስ አበባ መጅሊስ ውስጥ ያለን አንድን ወንድም በተለየ ማመስገን እወዳለሁ። ስሙ ሃሺም ዐብደላህ ይባላል። ከጉዞ በፊት ጀምሮ እስከ መጨረሻ መረጃ በመስጠት ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል፣ ብዙ አይነት አመሎችን ችሎ ጠብ እርግፍ ብሎ አገልግሏል። ለአዲስ አበባ ሑጃጅ መረጃ ለማስተላለፍ በተከፈተው የቴሌግራም ግሩፕ ላይ ሌላ ሰው ያልለ እስከማይመስል ድረስ በተለየ መልኩ መረጃ መስጠት፣ ማለቂያ የሌለው ጥያቄ መመለስ፣ በስልክና በአካል ማስተናገድ፣ ... ባጭሩ አንድ ሰው እስከማይመስል ድረስ ነበር ሃላፊነቱን ሲወጣ የነበረው። ይሄ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ትልቅ ምሳሌ ነው። ሃሺም በኦንላይን ብቻ ሳይሆን በአካልም በትህትና በፈገግታ ሲቀበል ሲያስተናግድ ሁለት ሶስት ጊዜ አይቼዋለሁ። ባገኘሁት ሰዓት ከሰላምታ ባለፈ ምስጋናየን ሳልገልፅ በመቅረቴ ስለቆጨኝ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ በእጅጉ ማመስገን እፈልጋለሁ። አላህ የልፋቱን ይመንዳው።
ከዚህ በመቀጠል ጥቅል ነገር ለማስቀደም ያክል በሐጁ ጉዳይ ላይ የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን በተወሰነ መጠን ተከታትያለሁ። እንደኔ እይታ አንዳንድ በሳል ሃሳቦችን የሰነዘሩ ቢኖሩም ብዙዎቹ ግን በልክ የተያዙ አልመሰለኝም። ደጋፊዎች የመንግስት ካድሬ አይነት ባህሪ ባትይዙ መልካም ነው። በቅድሚያ ተጨባጭ የሆኑ የመስተንግዶ ክፍተቶች፣ በቀጥታ ሲገለፅ የአስተባባሪዎች መዝረክረክ ነበር። ድክመቶች መለየታቸው ለወደፊት የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ግብአት ስለሚሆኑ ሊጎረብጠን አይገባም። በሌላ በኩል አንዳንድ ትችቶች በጣም የተጋነኑ ነበሩ። በቦታውም ላይ ጭምር አንዳንዴ የሚናገሩበት ሰበብ የሚጠብቁ የሚያስመስሉ ሁኔታዎችን አይተናል። ይህንን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ከሐጅ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ያለውን ጉዳይ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ብዬ ለሁለት ከፍየ አቀርባለሁ።
ሀ - ጠንካራ ጎኖች
1- የምዝገባ ሂደቱ ምንም አይነት መጉላላት የሚባል የሌለበት ቀልጣፋ ነበር።
2- ለአዲስ አበባ ሑጃጅ መረጃ ማስተላለፊያና መለዋወጫ የቴሌግራም ግሩፕ መከፈቱም ጥሩ ነው።
3- ጉዞ ሲጀመርም ከቦሌ አየር መንገድ የነበረው የመጅሊስ አስተባባሪዎች ሚና ጥሩ የሚባል ነው።
4- የስልክ የሮሚንግ አገልግሎቱም ቢሆን ከነ ውስንነቱ ጥሩ ነው።
5- መጓጓዣ አውቶቡሶችን በተመለከተ ከሆቴል እስከ ሚና፣ እስከ ዐረፋ፣ ከዚያም እስከ ሙዝደሊፋ የማጓጓዝ አገልግሎት ነበር። የማስተባበር ችግርና መዝረክረክ ጎልቶ የሚታይበት ከመሆኑ ጋር። መጠኑም በቂ አልመስለኝም።
6- የምግብ አቅርቦቱ በአመዛኙ ጥሩና በቂ የሚባል ነው። ክፍተቶች የሉም እያልኩ አይደለም። በዚህ ላይ የሚቀርቡ ትችቶች ግን እንደኔ ምልከታ በጣም የተጋነኑ ናቸው።
7- የተያዙት ሆቴሎች ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ የሚባል ደረጃ ያላቸው ናቸው። መገኛቸውም ከመስጂደል ሐራም ብዙ ሩቅ የሚባል አልመሰለኝም። ርቀት አንፃራዊ ነውና እይታችን ሊለያይ ይችላል።
8- አስተባባሪዎችና ሆቴል ላይ አስተናጋጆች በአመዛኙ እንደ ባህሪ ጥሩ ናቸው። በቂ ቁጥር፣ ትጋት፣ አቅም፣ ቅንጅት፣ ቅልጥፍና ያንሳቸዋል ብዬ አስባለሁ። ሳይሰለቹ ስልክ ሲያነሱ፣ የሚናገራቸውን ጭምር ሲያልፉ አይቻለሁ። አንዳንዱ ሰው ለመጣላት የተዘጋጀ እስከሚመስል አቀራረቡ ይከብድ ነበር። የማይመለከታቸውን ጭምር በተደጋጋሚ ሲያዟቸው ሲታዘዙ አይቻለሁ።
ለ - ደካማ ጎኖች
1- የተጋነነ ዋጋ። ዋጋ ስል አጠቃላይ ክፍያውን ማለቴ አይደለም። ይህኛውን ከሌሎች ሃገራት ጋር በማነፃፀር ውድ እንደሆነ የገለፁ ሰዎችን ፅሁፍ አይቻለሁ። ስለሱ ለመናገር የሚያበቃ በቂ መረጃ ባይኖረኝም ትንታኔው አሳማኝ ይመስላል። በራሴ ያየሁት ግን በተሻለ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለአየር ትኬት በግል 24ሺ (?) ብር ገደማ የቆረጠ ሰው ያገኘሁ ሲሆን በመጅሊሱ ግን 55ሺ ብር ነው የተቆረጠው። ከእጥፍ በላይ ልዩነት! ይሄ ፍትሃዊ አይደለም። እየበሉን ይሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስበሉን ይሁን አላውቅም።
2- የአስተባባሪ እጥረት :- ለተለያዩ ጉዳዮች ሲፈለጉ አይገኙም። እዚያኛው ሆቴል ናቸው ይባላል። እዚያ ሲኬድ ደግሞ ሌላኛው ጋ፣ ...
3- የመጅሊስ አስተባባሪዎች በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር በኩል ጉዳያችንን ከሚይዙ አካሎች ጋር ፎርማል ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ብዙ ሑጃጅ አንገት ላይ የሚደረገውን ባጅ በጊዜ ባለማግኘቱ ሲቸገር ፈጣን መፍትሄ ማምጣት አልቻሉም።
4- ሚና ላይ የነበሩ ኸይማዎችና የፍራሽ ሁኔታ ምቾት የሚነሳና ለወረርሽኝ ሊያጋልጥ የሚችል ነበር። በግምት ከ450 የማያንስ ሑጃጅ በአንድ ድንኳን ውስጥ የታጨቀ ሲሆን መሀል ላይ ከምትኖር አንዲት ቀጭን መስመር ውጭ ለእግር መረገጫ የሚሆን ክፍተት አልነበረም። ከዳር እስከ ዳር ተገጣጥመው በተደረደሩ ቀጫጭን ፍራሾች ላይ ታጭቀን ነበር ለቀናት የሰነበትነው። ያውም ሳይበቃቸው ፍራሽ ሳያገኙ ውጭ ላይ የነበሩ ሰዎችን አይቻለሁ። ከአስተባባሪዎች ውስጥ ያለንበትን ሁኔታ የሚታዘብ፣ ተዘዋውሮ "ምን ችግር አለ?" ብሎ የሚጠይቅ አንድም አልገጠመኝም።
5- ሚና ላይ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ ምንም አይነት መድሃኒት የለም ተብያለሁ። ለበሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች በበዙበትና ብዙ ህመምተኛ በሚኖርበት ጊዜ ላይ እንዲህ አይነት መዘናጋት ሊኖር አይገባም ነበር። ወደ መካ ከተመለስን በኋላ መድሃኒት እያገኙ እንደሆነና ከኢትዮጵያ የመጣ እንደሆነ ሰዎች ነግረውኛል። ስለዚህ ችግሩ የማስተባበር መሰለኝ።
6- ሰዎች በሚጠፋፉበት ፈታኝ በሆነው 10ኛው ቀን ላይ በጣም ብዙ መንገዶች ላይ አንድም የመጅሊስ አስተባባሪ አላየሁም። አንድም!
እስከማውቀው ቀድሞ የተሰጠ ማሳሰቢያም የለም። መጨረሻ ማረፊያችን አካባቢ በተወሰኑ ርቀቶች ላይ አንድ አራት አምስት አስተባባሪዎችን አይቻለሁ። በሙቀቱ ምክንያት ስልኬ እየጋለ እየዘጋ ቢያስቸግረኝም በጉግል ማፕ ሎኬሽን የሆነ ያክል ለመጠቀም ሞከሬያለሁ። ግን ስንቱ ይህን ማድረግ ይችላል? በዚህ ቀን ብዙ ሰው ጠፍቶ ነበር። የሞቱም አሉ። አስተባባሪዎች በደረሰው ጉዳት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እፈራላቸዋለሁ።
7- የጠፉ ሰዎችን መረጃ ከጤና ተቋማት በቀጥታ ማጣራት አይችሉም ነበር። የአፋልጉን ማስታወቂያ በቴሌግራም ግሩፕ፣ በሆቴሎች በር ላይ በተደጋጋሚ ለቀናት ሲለጠፍ ነበር። መጅሊሱ እንደ ተቋም ከሳዑዲ የጤና ተቋማት ጋር ፎርማል ግንኙነት በመፍጠር በቀላሉ ሪፖርት ማግኘት እየቻለ ቤተሰብ በየ ሆስፒታሉ ፍለጋ መባዘኑ የሚያሳዝን ነበር።
ስለዚህ የአብዛኞቹ ክፍተቶች ሰበብ አስተባባሪዎች ወይም አስተናጋጆች ቦታቸው ላይ መኖራቸውን፣ ሃላፊነታቸውን ባግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን የሚቆጣጠር፣ ቁጥራቸው በቂ መሆን አለመሆኑን የሚገመግም አካል ያለ አልመሰለኝም። ለወደፊት ይሄ ጉዳይ በቂ ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው። በመዘንጋት ወይም የጎሉት ላይ በማተኮር ያልጠቀስኳቸው ደካማም ጠንካራም ነጥቦች ይኖራሉ።