ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን ይህ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር
“በነዚህ ቀናት ውስጥ በኢስላማዊ ጋዜጦች መጽሔቶች
ኢስላማዊ ቻናሎች እና ኢማሞች በኹጥባ ሚንበር ላይ የነቢዩ ﷺ መውሊድ አስመልክቶ ስለ ረሱል ﷺ የህይወት ታሪክ አኽላቃቸው በእኛ ላይ ያላቸው ሐቅ ወ ዘ ተ ይናገራሉ ይህ ተግባር እንዴት ይታያል? ለሙስሊሙ ይህን አስመልክቶ
የምታስተላልፉት ምክር ካለ::??
የረሱል ﷺ የህይወት ታሪክ መዘከር
የሚወደድ ተግባር ነው:: ይህንና ዓመቱን በሙሉ መዘከር
አለባቸው እንጂ በቀናት መገደብ አይኖርበትም:: እነዚህን ቀናት በዓመት ጠብቆ ሲራቸውን አኽላቃቸውን መጥቀስ ይህ ተግባር የመውሊድን ቢድዓ ህያው ለማድረግ መዳረሻ ነው ሊሆን የሚችለው ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ!ይህን ማድረግ ከሙብተዲኦች ጋር በመውሊድ ከመተባበር
ይቆጠራል:: ምክንያቱም የረሱል ﷺ
የህይወት ታሪክ መዘከር በነዚህ ቀናት ሊታወስህ የቻለው
በቅርቡ መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች ትዝ ስላሉህ ነው ይህ ደግሞ አብሮ የመውሊድ በዓል ከመሳተፍ እና የሚያከብሩትን
ድጋፍ ከመስጠት ይቆጠራል::
ከሸይኽ ፈውዛን ወብ ሳይት የተወሰደ www.alfawzan.af.org.sa
/channel/sultan_54
ኢማም አሕመድ ኢቢኑ ሐንበል - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ተባሉ።
🍃ሰውየው የኢብኑ አቢ ዳውድ ባልደረቦች(የቢድዓ ሰዎች) በሚያጋጥማቸው ነገር ይደሰታል፣ ይህን ማድረጉ ኃጢአት ነውን?
እርሳቸውም ፦
"በዚህ የማይደሰት እርሱ ማነው!?"
🌷አስ–ሱና ሊልኸላል (1769)
ለምን ይሆን ብዙ ግዜ የድንበር አላፊዎች ጩኸት የሚያስተጋባው?
ጀማሉዲን አልቃሲሚ እንዲህ ብለዋል፦ "በማህበራዊ ኑሮ ጥናት እንደተረጋገጠው አንድ ጭፍራ ሀይል ፣ጉልበት እና ተከታዩም እየተበራከተ በሄደ ቁጥር፤ የመጀመሪያውን መርሆ እንደያዙ የሚጓዙ እና #ሰርጎ ገብ፣ እንዲሁም #ሚዛናዊና ፅንፈኛ ፣ #ድንበር አላፊ እና ከሌሎች ጋር ተቻችለው የሚኖሩ ተቃራኒ የሆኑ አመለካከቶች ሁሌም ይኖራሉ። ስለሆነም ብዙ ግዜ ድንበር አላፊ #ጠንከር ያለ #ጩኸቱ_የሚያስተጋባ ሲሆን ብዙ (ተራ ሰዎች) ዘንድ ይህኛው አካሄድ ተቀባይነት እንደሚያያገኝ ጥናቶቹ ይጠቁማሉ። የዚህም ምክንያት ሚዛናዊነት የላቀው የፍትሃዊነት ደረጃ እና መገለጫው በመሆኑ የተነሳ በየትኛውም ከተማ እና ዘመን የሚኖሩ ጥቂቶቹ ካልሆኑ በቀር ሚዛናዊ ለመሆን አይጥሩም። #ድንበር አላፊነት የአብዛኛቹ መሸጎሪያ እና የበርካቶቹ ዝንባሌ ሆኖ እናገኘዋለን። የዚህን የሸር በር ከፋቾች የመጀመሪያዎቹ ኸዋሪጆች ሲሆን በመቀጠልም ወረርሽኙ ወደ ሌሎች ሙስሊሞች ተዛመተ።"
📚 (አልጀርህ ወተዕዲል ሊጀማለዲን አልቃሲሚ ገፅ: 4)
«ሰውዬውን ቁርኣንን ሳያዳምጥ፤ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ እና ሙዚቃ የማድመጥ ናፍቆት ዝንባሌው ኖሮት ካየኸው፣
ይህ ቀልቡ ከአላህ ቃል ፍቅር ባዶነት ጠንካራ ማስረጃ ነው።»
(ኢብኑል ቀዪም)
ኢማሙ አልቁርጡቢ ረሂመሁላህ በዚክር ሽፋን እየጨፈሩ የሚጮሁትን በተመለከተ ተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦
👇👇👇👇👇
"በዚህ አንቀጽ አላህ ተዓላ እርሱን የሚዘክሩ አማኞችን እርሱን ሲዘክሩ በፍርሃት፣ በስጋት እና በርጋታ ገልጿቸዋል። ይህም ከእምነታቸው ጥንካሬ እና ጌታቸውን በማክበራቸው እርሱ ፊት እንዳሉ... ያህል ከመቁጠራቸው የተነሳ ነው።
እንጂ……
እንደ አህያ ጩኸት የሚያናፉ፣ የሚያጓሩ፣ አላዋቂዎች ተራው ሕዝብና ሙብተዲዎች እንደሚያደርጉት አይደለም። በዚህ ( ጭፈራ፣ፉጨት፣ጩሀት…) ውስጥ ለተሰማራ፤ ይህን ድርጊቱን "ወጅድ" "ኹሹዕ" ነው ብሎ የሚሞግትን ፡- አላህን በማወቅ፣ በመፍራት እና በማወደስ የመልእክተኛውንም ሆነ የባልደረቦቻቸውን ደረጃ ላይ አልደረስክም ይባላል። ”
📚ተፍሲሩ አልቁርጡቢ (7/328)
ሱረቱ አል አንፋል አያ (2) ማብራሪያ ይመልከቱ
ኢማሙ አሰኻዊ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንዳቸውም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።”
📖(ሱቡሉልሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439)
🔁 /channel/sultan_54
ሱፊይ የሆኑት አል ፋክሃኒይ (731 አ/ሂ የሞቱ) መውሊድ ስለማክበር ሲጠየቁ፦
“ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም ሆነ በሱና ውስጥ መነሻ አላውቅልትም።
የመውሊድ ስራ በሃይማኖት አርአያ ከሆኑ እና የቀደምት የዲን አባቶች ትውፊት አጥብቀው ከያዙ ከሆኑ የሀገሪቷ ምሁራን የተላለፈ አይደለም።
ይልቁንም ከንቱ የሆኑ ሰዎች ትኩረት ያደረጉበት ፣ ሥራ ፈት ሰዎች ያመጡት አዲስ ፈጠራ እና የነፍስ ስጋዊ ፍላጎት ብቻ ነው።”
📚(አልፋክሃኒ /አልመውሪድ ፊ ዐመሊ አልመውሊድ)
ገፅ(20)
🔴 ቢድዓ የልዩነት እና አህሉ ሱና ላይ የጥላቻ ዘመቻ መክፈቻ አንዱ ሰበብ ነው። በተለይ መውሊድ።
قال عَنْبَسَةُ بْنُ سَعِيدٍ الْكَلَاعِيُّ: "مَا ابْتَدَعَ رَجُلٌ بِدْعَةً إِلَّا غَلَّ صَدْرُهُ عَلَى الْمُسْلِمِينَ وَاخْتُلِجَتْ مِنْهُ الْأَمَانَةُ."
📚ذم الكلام وأهله للهروي (5/126).
"ማንም ሰው አዲስ ፈጠራን( ቢድዓን) አይፈጥርም፣
ልቡ በሙስሊሞች ላይ ጥላቻ ተሞልቶ፤ ታማኝነት ከርሱ ቢጠፋ እንጂ።"
አንበሰቱ ኢብኑ ሰዒድ አልከላዒይ
📗ዘሙል ከላም ሊልሀረዊ (5/126)
«ነቢዩ ﷺ ሰለሏሁ ከሞቱበት ቀን የበለጠ አስቀያሚ እና በሀዘን ድባብ የተነሳ እለቱ የጨለመበትቀን አይቼ አላውቅም።»
አነስ ኢብኑ ማሊክ
ሰሃቦች ነብዩ ﷺ ሰኞ መወለዳቸውን ከነገሯቸው በኋላ እንጂ አያወቁትም ነበር፣ ስለልደታቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እውቀት ያላቸው እንደመሆናቸው መጠን ግን የትኛው ሰኞ እንደሆነ ለሰሓቦቹ አልገለጹላቸውም? ዲን ተግባር እንጂ ክስተት ስላልሆነ አልጠየቋቸውም
።
زكاة الفطر مع وجود نص صريح خالفوها.
و بدعة المولد مع انعدام نص أحيوها.
يميتون السنن و يحيون البدع نسأل الله العافية
የጁምዓ ኹጥባ
🎙 التحذير من عبادة القبور
(የቀብር አምልኮ በኢስላም የተወገዘ ስለመሆኑ…)
🕌 ሀምዛ መስጂድ ቃሊቲ ቸራሊያ
🗓 ረቢዑል አወል 02 /1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
የበደሉህን ሁሉ ብትተሳሰብ፣ የበደሉህንም ሁሉ ብትበቀል፣ በጤንነትህ ፣የአእምሮ ሰላምህ… ላይ መፅናናቱን አላህ ይለግስህ እላለሁ እንጂ ሌላ ምን እልሃለሁ?!
የምችለውን ያህል ችላ በል፣ ችላ ማለት፤ አስተዋይ እና ብልህ ሰው ብቻ የሚካነው ምርጥ ጥበብ ነው !!🍓
መውሊድ የጀነት መንገድ ቢሆን ኖሮ መልክተኛው ﷺ በጠቆሙን ነበር።
«ወደ ጀነት የሚያቀርባችሁ ነገር የለም ትሰሩት ዘንድ ባዝዛችሁ በቀር፤ ወደ ጀሀነም የሚያቃርባችሁ ነገር የለም ከርሱ ብከለክላችሁ እንጂ።»
የአላህ መልክተኛ ﷺ
📚 አልሓኪም(2136) አልበይሀቂ ሹአቡል ኢማን (10376)
አላህ ከዐርሽ በላይ ነው።
ከሱረቱ አሽ–ሹራ ተፍሲር የተወሰደ
አራት ነገሮች ሪዝቅን ያመጣሉ ፡-
«ለሊት በዒባዳ ማሳለፍ( መስገድ)፣
ሱሑር ወቅት ኢስቲግፋር ማብዛት፣
ሰደቃን በተቻለ መጠን መመፅወት
በቀኑ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ ዚክር ማድረግ።»
✍ ኢብኑል ቀዪም/ ዛዱል ሚዓድ (4/378)
ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙባረክ ሑዘይፋ ኢብኑ አልየማን በመጥቀስ እንዲህ ብለዋል ፦
"ተውበት ለማድረግ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ወንጀልን መተው እጅግ ቀላል ነው።
ምናልባትም የአንድ አፍታ ስሜት የዕድሜ ልክ ሐዘን እና ትካዜን ሊያወርስ ይችላል።"
📚【አረቃኢቅ 743】
"ኸዋሪጆች *ካ*ፊ*ሮ*ች*ን እንደተዋጉ በታሪክ አይታወቅም፣ ይልቁንም አማኙን ሁልጊዜም ይገድላሉ፣ እስከ ወዳኛውም ሙስሊምን ይዋጋሉ።"
✍ሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን)
📚ኢትሓፍ አል ቃሪ 2/225
ዓለመቱ አሽ–ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ ኢብኑ ባዲስ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
«በዚህ ዘመን ሸይኽ ኢቢኑ አብዱልወሃብ ከሌሎች ሰዎች ቀድመው ወደ ቁርኣን ፣ ሱና እና ወደ ቀደሙት ሰለፉ አስ–ሷሊሒን መመሪያ በመጣራት ፣ቢድዓዎችን እና ጥመትን በመዋጋት ላይ ይታወቃሉ ። ስለሆነም ወደዚህ ጥሪ ያደረጉ ሁሉ "ወሃቢያህ” ይባል ጀመር።»
መጀለቱ «አሽ–ሺሃብ» ቅፅ 10/ ገፅ 261)
መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም!
{ምስክር እራሳቸው!}~~~~~~~
በሺርክ የተወረረውን፣ በኹራፋት ያበደውን፣ በመውሊድ የታጀበውን የሱፍዮች እስልምና “ነባሩ እስልምና” እያሉ የሚያሞካሹ ጩኸቶችን አልፎ አልፎ እንሰማለን። ይህንን የማይቀበለውን “ወሃቢ” በማለት በሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ የተጠነሰሰ መጤ ኢስላም እንደሆነ ሊነግሩን ነው የሚውተረተሩት። ይህ “ነባሩ” የሚሉት “ኢስላም” ግን ፍፁም እንግዳ የሆኑ መጤ አስተሳሰቦችን አጭቆ የያዘ እምነት ነው። የዚህ ፎርጅድ “ኢስላም” አብይ መገለጫ የሆነውን መውሊድን እንደ አብነት ብንወስድ ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ ከነባሩ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ እንደሆነ መስክረዋል። ለምሳሌ፡-
1. አቡ ሻማ፡-
“በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95]
2. ኢብኑ ሐጀር፡-
“የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188]
3. ሰኻዊ፡-
“የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉል ሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439]
4. ተዝመንቲ፡-
“የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አሲረቱ አሻኒያህ፡ 1/441]
5. አልሓፊዙል ዒራቂ፡-
“ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136]
6. ሲዩጢ፡-
“የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አልሓዊ፡ 1/189]
(መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ንግግራቸውን ያጣቀስኩት መውሊድ የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።)
7. ዘርቃኒ፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264]
ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው።
(وَشَهِدَ شَاهِدࣱ مِّنۡ أَهۡلِهَاۤ)
የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው የሆነ ያክል ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹ ግን አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች ሲያደርጓቸው ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። አንዳንዶቹማ ከዚህም አልፈው ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ የማያመነቱ ሃፍረተ ቢሶች ናቸው። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ አንባቢ አንድ ቁም-ነገር ሊጨብጥ ይገባል። እሱም መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቀደምቶች ሙስሊሞች ዘንድ የማይታወቅ በሺዐዎች የተጠነሰሰ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው!! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአራቱ አኢማዎች፣ የነ ቡኻሪ፣ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም እንጂ የሱፍዮች ኢስላም አይደለም። ይሄ ኢስላም ነባር ካልሆነ የማን ኢስላም ነው ነባር የሚሆነው?!
እንዳየነው መውሊድ በደጋፊዎቹም በነቃፊዎቹም ኢጅማዕ ቢድዐ ነው፣ መጤ ፈሊጥ። መጤ ደግሞ በየትኛውም አረዳድ “ነባር” ሊሰኝ አይችልም። ስለሆነም መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለዚህ መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው።
ከ “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ
قال ابن القيم رحمه الله:
(لما كثر المُدّعون للمحبة، طولِبوا بإقامة البيّنة على صحة الدعوى، فتأخر الخَلق كلُهم وثبت أتباع الحبيب في أفعاله وأقواله وأخلاقه)
📚 مدارج السالكين(3/8)
የጁምዓ ኹጥባ
🎙 محبة النبي صلى الله عليه وسلم بين الاتباع والابتداع
(ነቢዩን ﷺ መውደድ ሱናቸውን በመከተል እና ቢድዓ በመፍጠር መካከል…)
🕌 ሀምዛ መስጂድ ቃሊቲ ቸራሊያ
🗓 ረቢዑል አወል 10 /1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
🔖 ቢድዓና አል-መሳሊህ አል-ሙርሰላ
🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
ነብዩም ﷺ ሆኑ ባልደረቦቻቸው የነብይ መውሊድን አላከበሩም፣ እንዲሁም ከነሱም በኋላ በሶስት ክፍለ ዘመን የነብያችንን ልደት ያከበረ ሙስሊም አልነበረም። ምክንያቱም እርሳቸውን መውደድና ማክበር በተግባር እንጂ ልደት በማክበር የሚገለፅ ስላልሆነ።
መውሊድን ማክበር ቢድዓ ነው!
ምክንያቱም ኢብኑ ከሲር በታላቁ የቁርኣን ተፍሲራቸው ላይ፤ ሱረቱል አሕቃፍ አስራ አንደኛውን አንቀፅ ማለትም፦
(لو كان خيرا ما سبقونا إليه )
(ከሃዲያንም)"መልካም (ኸይር) ቢሆን ኖሮ ( ድሆች፣ ደካሞቹ የነቢዩ ባልደረቦች) በርሱ ውስጥ ባልቀደሙንም ነበር።" አሉ።) የሚለውን ሲተነትኑ፦
“…አህሉ ሱናዎች ግን እያንዳንዱ ተግባር እና ከሰሓቦች ያልተረጋገጠ ንግግር አዲስ መጤ (ቢድዓ) ነው ይላሉ። ምክንያቱም ኸይር ቢሆን ኖሮ በርሱ ይቀድሙን ነበር። ምክንያቱም እነርሱ ለኛ ቅንጣት ታክል ኸይር ለኛ አልተዉልንም ቢፈፅሙት እንጂ።" ብለዋል።
በተጨማሪም ታላቁ ሰሓቢይ ሑዘይፋ ኢብኑ አል-የማን አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
“የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ሶሓቦች ያልፈጸሙት ማንኛውም ዒባዳ አትፈፅሙ። የመጀመሪያው ትውልድ ለኋለኛው አንድም የተወው ነገር የለም። ስለዚህም እናንተ ቁራኣዎች ሆይ አላህን ፍሩ! ከናንተ በፊት የነበሩትንም (የሠለፎች)ጎዳና ተከተሉ።"
📚 [አል ኢባናህ ሊኢብኒ በጧህ]
📚—1453—
ማሊክ ኢቢኑ ዲናር አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።
ሞት እጣ ፈንታው እንደሆነ፣ መቃብርም ማረፊያው እንደሆነ የሚያውቅ ምንኛ የሚገርም ሰው ነው ግን?!
እንዴት ለዱንያ እውቅና ትሰጣለህ? እርሷም ውስጥ እንዴት በጥሩ ሁኔታ መኖር ይችላል?!
አሉ፣ ከዚያም አለቀሱ።
ሲፈቱ አስ ሰፍዋ (3/187)
መወሊድ ሱና ቢሆን የጭቅጭቅ እና የልዩነት መንስዔ ባልሆነ ነበር።
(ሱና ከአንድነት ጋር እንደተቆራኘ ሁሉ፤ ቢድዓ ደግሞ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው! …)
[አል ኢስቲቃማ 1/42]
ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ
የጁምዓ ኹጥባ
🎙 الحب في الله
(ለአላህ ብሎ መዋደድ)
🕌 ፈትሕ መስጂድ ጎተራ ሼል ዲፖ
🗓 ሰፈር 24/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
መውሊድ ወደ አላህ የሚያቃርብ ድርጊት ቢሆን ኖሮ ነቢዩ ﷺ ይጠቁሙን ነበር።
«ከኔ በፊት አንድም ነቢይ አልነበረም፣ ለህዝቡ የሚያውቀውን መልካም ነገር በሙሉ መጠቆም እና ለነሱ መጥፎ እንደሆነ የሚያውቀውን ነገር ማስጠንቀቅ ግዴታ ቢሆንበት እንጂ።»
የአላህ መልክተኛ ﷺ
(ሙስሊም ዘግበውታል።)
ታላቅ ምስራች!
ለአላህ ምስጋና ይገባውና እኚህ ታላቅ ዓሊም አሽ– ሸይኽ ሷሊህ ኣል– ሸይኽ ከ20 አመታት በላይ ከደርስ ተቋርጠው የነበረ ሲሆን በዚህ ሳምንት ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ በነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መስጂድ ውስጥ ወደ ደርስ መድረካቸው ተመልሰዋል።
የእኚህን ታላቅ ምሁር ማብራሪያ በተለይም የዓቂዳህ ሙቱኖች ትንታኔ ያነበበ እና ያደመጠ የሳቸውን የጠለቀ እውቀት ብቃት ያውቃል።
የመጀመርያው ትምህርታቸውን መጂሊስ በሱረቱ ያሲን ተፍሲር ጀምረዋል።
ወሊላሂል ሀምድ ወነን–ኒዕማህ!