sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14577

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

#ኒቃብ@sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

https://vm.tiktok.com/ZMh4qtpKd/

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አህባሾችና አላህን ከ‘ጂሀ’ እና ከ“መካን” የማጥራት እሳቤ

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በመልእከተኛው ላይ የሁን። በመቀጠል፤

አላህ እንዲህ ብሏል፤
{الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ} [طه : 5]
«አል ረህማን ከዓርሽ በላይ ከፍ አለ» ጣሀ 5

ለማንኛውንም ጤናማ ሙስሊም ይህንን አንቀፅ በመጥቀስ ለመሆኑ ይህንን አንቀፅ ስትሰማ፤ ‘ሰማያት አላህን ተሸክመዋል፣ ፍጥረራቱ ያካብቡታል’፣ ‘አላህ ከዓርሽ ፈላጊ ነው’ ወይም ‘አላህ በፍጥረታቱ ውስጥ ሰርጿል’ የሚሉ መጥፎ መልዕክቶችን ተረድተሀልን? ብለህ ብንጠይቀው፤ “ፈጽሞ አዕምሮዬ አላሰበዉም” እንደሚለን ግልጽ ነው።
በፍልስፍና ልቡ ያልታወረ ማንኛውም ሙስሊም ይህንን እና መሰል መልእክቶችን ከጥመት በራቀ መልኩ እንደሚረዳው ግልጽ ነው። በርግጥም ከዚህ ግልጽ ቁርአናዊ መልእክት ጥመትን የሚረዳ ልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት ብቻ ነው። ስለዚህም አህሉሱና ግን አላህ ከእርሱ ክብርና ግርማ ሞገስ ጋር በሚሄድ መልኩ ከሰማያትና ከዓርሽም በላይ መሆኑን እና ከፍጥረታቱ የተለየ “ባኢን’ መሆኑን ያምናሉ።

በዚህ መልኩ ንፁህ ምልከታ ኖሮህ አላህ የተናገረውን አፅድቀህ ስትመሰክር፤ አህባሾችና ጥመትን ያወረሷቸው ቀደምት አንጃዎች «አላህ ከአርሽ በላይ ነው» ስትል በአላህ ክደሀል ይሉሀል። ለምን ብትላቸው ለአላህ ቦታ እና አቅጣጫን ስለሰጠህ ካፊር ይሉሀል። ስለዚህም ዘወትር "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚል ባዶ መፈክር ሀዲስ በማስመሰል ይደሰኩራሉ።

አህባሾች... የዚህን አንቀፅ ቀጥተኛ መልእክት በሰው አእምሮ የማይመጣን የጉድለት ባህሪ የሚያስገነዝብ የኩፍር መልእክት አድርገው ለምን ይረዱታል? ሰሀቦችና ራቢዒዮች ከአላህ የመጣውን መልእክት ተቀብለው ሳይፈላሰፉ እንዳፀዱቀት አፅድቀው በማመን ፈንታ መካን እና ጂሀ የሚል ፀጉር ስንጠቃስ ለምን አስፈለጋቸው?
የነሱን መነሻና ትክክለኛውን የአህሉሱና አቋም ማወቅ ጠቃሚ ነውና ልብ ብለህ ተከታተለኝ።

በመሰረቱ "ጂሀ" እና "መካን" እነዚህ ቃላት ሸሪዓዊ መሰረት የላቸውም። ከዚህ ርዕስ ጋር በተያያዘ በቁርዓንም ይሁን በሀዲስ አናገኛቸዉም። በተመሳሳይ መልኩ ‘ሀድ’ እና ‘ጂስም’ የመሳሰሉ ጥቅል "ሙጅመል" ቃላት ሸሪዓዊ መሰረት የላቸውም። አህሉሱና በዚህም ይሁን በሌሎች ርዕሶች ላይ መረጃን መሰረት ያደረገ አካሄድ ስላላቸው እንዲህ አይነቶቹን ጥቅል ቃላት “አል አልፋዝ አል ሙጅመላህ” መነሻ አድርገው አይናገሩም መፈተኛ አያደርጓቸውም። ነገር ግን ከቢድዓ አራማጆች በኩል ሲመጡ ለማጽደቅም ይሁን ውድቅ ለማድረግ ሳይሽቀዳደሙ ቃሉን ባለበት በመተው የሚፈለግበት መልዕክት ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ከምላሹም በመነሳት መልዕክቱ ሀቅ ከሆነ ያጸድቁታል፤ ሀቅ ካልሆነም ውድቅ ያደርጉታል።

ለምሳሌ፤ አንድ አህባሽ «ለአላህ ጂሀ ‘አቅጣጫ’ አታድርጉለት ይህ ኩፍር ነው» ቢልህ፤ ከዚህ ርዕስ ጋር በተያያዘ ‘ጂሀ’ የሚለውን ቃል በቁርአን እና በሀዲስ እንደማታውቀው በመንገር በዚህ ቃል ምን እንደተፈለገበት ጠይቀው። ሀሳቡ አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ማስተባበል ከሆነ ከቁርአንና ከሱና አረንዲሁም ከተፈጥሯዊ እምነት ጋር የሚጋጭ ተራ ወሬ መሆኑን ትነግረዋለህ። ነገር ግን የፍጥረተ ዓለሙ አካል የሆኑትን ስድስት አቅጣጫዎች ለአላህ መገለጫ ማድረግ የለብንም ለማለት ከሆነ ይህ የታወቀ እንደሆነ እና ይህ አይነት ትርጓሜ ያለዉን ‘ጂሀ’ ለአላህ እንደማናጸድቅ፤ ቀደወሞውንም ስለአላህ ስናወራ ዙሪያችን ያሉ አቅጣጫዎች ፍፁም እንደማይታሰቡን ታስረዳዋለህ።

{أَأَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاء} [الملك : 16]

«ከሰማይ በላይ ያለውን ‘አላህ’ ትተማመናላችሁን?» አልሙልክ 16

ልብ በል ወንድሜ፤ ይህንን እና መሰል አንቀፆችን ሲሰሙ የቁርአንን መልእክት በቀጥታ በመጠምዘዝ ‘አላህ ከሰማይ በላይ’ መሆኑን ሲያስተባብሉ ታይና ተገርመህ ይህ ሁሉ ልፋት እና መወራጨት ምን አመጣው ብለህ ችግራቸውን ስታጠና፤ አሁንም ለአላህ ቦታ “መካን” መስጠት አይገባም የሚሉት የፍጡራን መኖሪያ የሆኑትን ሰባቱን የቅርብ ሰማያት በማሰብ እንደሆነ እንደዚሁ ‘አላህ ከፍጡራን በላይ ነው’ ሲባሉ በዙርያቸው የሚያውቋቸውን ስድስት አቅጣጫዎች በማሰብ አላህ ከጂሀ “አቅጣጫ” የጸዳ ነዉና ከፍጡራን በላይ ነው አይባልም እንደሚሉ ትረዳለህ። የስህተታቸው ሁሉ መሰረት ይህ ነው።

☞ ጀህሚያ፣ ሙዕተዚላ እንዲሁም አሻዒራ የአላህን የበላይ መሆን የሚያስተባብሉባቸው ፍልስፍናዊ መረጃዎች ሁሉ የሚያጠነጥኑት በዚህ ብዥታ ላይ ነው። መካን(ቦታ) እና ጂሀ(አቅጣጫ) ለአላህ አይገቡም በማለት የአላህን ከፍጡራኑ የበላይ መሆን ያስተባብላሉ። እውነታው ግን፤ እነሱ ለዚህ ስለ አላህ ባህሪያት ለማወቅ መነሻ ያደረጉት ከፍጥረተዓለሙ ጋር የተያያዙትን «ዉጁዲይ» ቦታ እና አቅጣጫን ነው። ስለ አላህ የሚነገሩ እውነታዎችን ሁሉ ፍጡራን ላይ በሚያያቸው ግንዛቤዎች ከሚተረጉም እውር አስተሳሰብ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

☞ አህሉሱና አላህ ከፍጡራን ሁሉ በላይ መሆኑን ያምናሉ፤ ‘ከሰማይ በላይ ነው’ ወይም ‘ከዓርሽ በላይ ነው’ የሚለዉን ሁሉ አላህ በነገራቸው መሰረት ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ ይቀበሉታል። ስላልተነገራቸው የባህሪ ምንነት ‘ከይፊያ’ ግን ምንም አይናገሩም። አህሉሱና ከአላህ ባህሪያት ጋር በተያዘ ፍጡራዊ የሆኑትን ጂሀ እና መካን ለአላህ አያጸድቁም።
ቁርአናዊውን የ‘ዑሉው’ አስተምህሮ ተቀብለው ሲያፀድቁም፤ ሙዓጢላዎች እንደሚያስቡት...

✘ አላህ አንደኛ ሁለተኛ ተብሎ በሚቆጠረው የመላዕክት መኖሪያ ሰማይ ላይ ይኖራል እያሉ አይደለም። መላዕክትም በሰማይ ሰዎች በመሬት በሚኖሩበት መልኩ አላህም በሰማይ ይኖራል የሚል እምነት ያለው ሰው በእርግጥም በአላህ ክዷል።

✘ እንደዚሁ ሰማይ አላህን ይሸከመዋል ወይም ያካብበዋል ከሚልም አስተሳሰብ የጸዱ ናቸው። ይህ የአላህን ከፍጥረታቱ ጋር መቀላቀልን “ሁሉል” የሚያምኑ የቢድዓ አራማጆች እምነት ነው።

✘ አላህ በፍጥረተዓለሙ ዉስጥ በሚገኙት ስድስት አቅጣጫዎች ይገለጻል፤ ፍጥረተአለሙም ያካብበዋል ማለትን ፈፅሞ አያመላክትም። ይህንን ያለ ሰውም በአላህ ላይ ውሸትን ተናግሯል፣ መንገድንም ስቷል።
አህሉሱና ይህ ሁሉ ጥመት ስለመሆኑ አይወዛገቡም።
የአላህ ከፍጥረታት በላይ መሆን አላህ በተፈጥሮ በልባችን ያኖረው ግልጽ እምነት ነውና። አላህ በቁርአን እንደገለፀው የአላህን ከፍጥረታት በላይ መሆን "ዑሉው" መግልጽ ብቻ ለአህሉሱና በቂ ነው። በቁርአንም ላይ የምናገኘው አካሄድ ይኸው ነው። ‘አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጥራት’ ጥቅል በሆነ መልኩ ሲቀርብ ፤ የአላህን ባህሪያት ማጽደቅ ግን በዝርዝር ሲቀርብ እናገኛለን። ለአብነት ያክል ተከታዩን መልእክት እናስተውል፤

لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشور : 11
‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡» (አል ሹራ 11)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«በትምህርት ቤቶች በየጊዜው የሚያገረሸው የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ቋሚ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል።

ፊትን ከባዕድ ወንዶች መሸፈን ግዴታ መሆኑ የአብዛኛዎቹ ዑለማዎች አቋም ነው።
ሆኖም ሴቶች ፊትና በማይሰጋበት ሁኔታ ለአስፈላጊ ጉዳይ ፊታቸውን ለወንዶች ማሳየት  እንደሚችሉ የሁሉም የፊቅህ ሊቃውንት ንግግር ያሳያል።

በዚህ መሰረት ተማሪዋ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ስትገባ፣ ወደ ፈተና ማእድ ስትገባ፣  አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር ወይም በማንኛውም ጊዜ ማንነቷን ማጣራትና ከመታወቂያዋ ጋር ማመሳከር ሲያሰፈልግ ፊቷን ገልጣ አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች።
«ሙሉ በሙሉ ተገልጠሽ ካልቆየሽ አትገቢም!» ማለት ግን ሀይማኖታዊ መብትን በግልፅ የሚጋፋ፣ ሴኪዩላሪዝም ራሱ የማይደግፈው… ምንም አግባብነት የሌለው የግለሰቦች ድርቅና ነው።»

#ሒጃብ #ኒቃብ #ትምህርት
#ሀገራዊ_ምክክር

✍ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፦
" ዓቢድ ከሆነ የቢድኣ ሰው ፋሲቅ የሆነ አሕሉ ሱና ይሻላል።"
ይህን ከሚያጠናክሩ ገጠመኞች መካከል፦
ዐብደላህ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሐነበል እንዲህ ይላሉ ፦"አባቴ ብዙውን ግዜ እንዲህ ሲል እሰማው ነበር፦"አላህ ሆይ! አቡ አልሀይሰም እዘንለት፤ተውለት፤ወንጀሉን ደብቅለት::"
ዐብደላህ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሐነበል : አባቴ ሆይ "ማነ ው አቡል ሀይሰም?
አሕመድ ኢብኑ ሐነበል "እርሱ ማለት በቁርአን መኽሉቅ ነው በሚለው ፊትና ታስሬ በነበረበት ወቅት ልገረፍ በካቴና ታስሬ ወደ መእሙን እየተወሰድኩ ሳለ፣ እርሱ ከኋላዬ ልብሴን እየጎተተ ፦"እኔን ያውቁኛል::" አለኝ;፡"አላውቅህም" አልኩት።
ስለው፣ "እኔ ማለት አቡልሀይሰም አልሀዳድ እባላለሁ፣በአሚሩል ሙእሚን እስር ቤት 18 ሺ ጅራፍ ተገርፌለሁ። ይህ ሁሉ ነፍሳያዬንና ሸይጣን ታዝዤ ሲሆን እርሶ ደግሞ አር_ረህማንን በመታዘዝ በሐቅ ላይ ናቹና፤ ፅኑ፣ እነሱን እንዳትሰማቸው፣ እንደትታዘዛቸው።" አለኝ
እንዲዚህ ቃል በወቅቱ ፅናት የሰጠኝ ቃል አልነበረም ።”

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"ዱዓ ለተከሰተም ገና ለሚከሰትም መከራ
እጅግ ጠቃሚ ነው።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! ከዱዓ እንዳትዘናጉ አደራ!!"
ረሱል (ﷺ)
(ሰሂህ አልጃሚዕ: 3409)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

እሳት፦ ነብዩ  ﷺ  ከርሱ እና ከሌሎች ጥፋቶች አላህ እንዲጠብቃቸው ከተማፀኑት ዋና ዋና አደጋዎች አንዱ ነው። 

አቡ አል-ዩስር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተናገሩት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፡-
“አላሙማ ኢንኒ አኡዱ ቢካ ሚን አል-ተራዲ ወ አል-ሀድም ወል-ገረቅ ወል-ሐሪቅ፣ ዋ አዑዱ ቢካ አን የንታባታኒ አሽ-ሸይጣን ዒንደ አል-መውት፣ “አሏህ ሆይ! ከከፍታ ቦታ ከመውደቅ፣ ከመደቆስ (ከህንጻው ውሃ ውስጥ ከመስጠም እና ከመቃጠል ባንተ እጠበቃለሁ። በጦርነት  ጊዜ ባንተ መንገድ ከመገደል (ከጂሃድ) ከመሸሽ እጠበቃለሁ፣ በጊንጥ  ወይም በእባብ መነደፍ እንዳልሞት ባንተ እጠበቃለሁ።"
ነሳኢ (5531) እና አል-ሀኪም አል-ሙስስታራክ (1/713) ላይ ተዘግቧል።
እሳቸውም፡- ሰነዱ ሰሂህ ነው (ቡኻሪና ሙስሊም) ባይዘግቡትም። አል-ሐፊዝ ኢብኑ ሀጀር በበዝል አል-ማዑን (199) ላይ፦ የተረጋገጠ ነው። ብለዋል። አል-አልባኒ ሰሂህ አን_ነሳኢ ላይ ሰሒህ ብለውታል። 

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ‏السلف كانو يقولون :" إياك وما يفسد عليك دينك "
فكيف بمن يفسد عليك دينك ودنياك ويمسخ مروءتك ويتلاعب بعواطفك ، وهذا كله في منهج وكلام الإخوان ،ومن لف لفهم ، ومن تفرع عنهم ومن صار مطية لهم ، ومن سار في ركابهم ، ومن ذب عنهم ، ومن دندن على مقولة (لهم حسناتهم ولهم أخطاؤهم )، ومن تباكى على الإعتدال في الحكم عليهم بزعمه ، فاحذرهم ولاتسمع لهم ولاتدخل حساباتهم إن كنت تريد الصلاح لدينك ودنياك
واحذر رعاك الله كل من يخالف العقيدة السلفية بقليل أوكثير
رأسمالك الذي به ربحك عقيدتك السلفية والمنهج السلفي الصافي فلا تعرض ذلك لأي خدش

🖍️ الشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

“የተኛ ሰው ተኝቶ ህልም ማየቱን የሚያቀው ከእንቅልፉ ሲነቃ ነው።

ልክ እንደዚሁ በአኺራህ ጉዳይ ላይ የተዘናጋ ሰው የሚነቃው ሲሞት ነው።»
تصبحون على خير🌷

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة
الدعاء حق الله

❗️
  ዱዓ የአላህ መብት ነው።

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ረቢዐል ኣኺር 07/1446 አ/ሂ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ምድራዊ ጀነት!
አላህ ያድለን ለሁላችንም።
ኣሚን!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሠዒድ ኢብኑ ዓሚር አድ–ዱበዒይ (210 አ/ሂ የሞቱ) እንዲህ ይላሉ፦
“ጀህሚያ በንግግራቸው ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች እጅግ የከፉ ናቸው ።
አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እና የሌላ እምነት ተከታዮች አላሁ ተባረከ ወተዓላ  በዐርሹ ላይ እንዳለ ተስማምተዋል። እነርሱ ግን በዐርሹ ላይ ምንም የለም አሉ።»
📚ኸልቁ አፍዓሉል ዒባድ ሊልቡኻሪይ (31)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ራፊዷን በተመለከተ ንፍቅናን ቢጠቀሙ እንጂ  ከማንም ጋር አይኗኗሩም። እንዲዋሹ የሚያደርጋቸው በቀልባቸው ውስጥ ያለው ብልሹ ዲን ነው።»
| ኢብኑ ተይሚያህ/ ሚንሃጁ አስ–ሱነቲ አን–ነበዊያህ (6/425)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢማሙ አቢ ዐብዲላህ ዑበይዲላህ ኢብኑ በጥ–ጠህ አል ዑክበሪይ(304/ሂ የተወለዱ) እንዲህ ብለዋል፦
"ከሱናዎች መካከል … (ቢድዓ እና ሙብተዲዕን)፣  መተው፣ መጽ–ጸየፍ ፣ የሚደግፉትን፣ የሚወዳኙትን፣ እንዲሁም ለቢድዓ ሰሪዎቸ ጥብቅና የሚቆሙት እና እነርሱን የተጎዳኘ፤ ምንም እንኳን ሱናን ቢያንፀባርቅም እነርሱን መራቅ ይገኝበታል።”

[الشرح والإبانة (ص 282)]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

እያንዳንዱ ከቢድዓ እና ከሙብተዲዕ የሚያስጠነቅቁ ጽሑፎች እና ድምጾች በሙሉ  ሚዛናዊነት ናቸው።
የአላህ መልእክተኛ - صلى الله عليه وسلم - ከሰው ልጆች ሁሉ በላጭ ከመሆናቸው ጋር  በሳቸው ላይ ድንበር ማለፍ  መከልከሉን የሚጠቁሙ "ኑሱሶች" በሙሉ ወደ ወሰጢያህ (ሚዛናዊነት) የቀረበ ጥሪ ነው።

  ኢማሙ አል-ቡኻሪይ ኢብኑ አባስን ጠቅሰው  በዘገቡት ሐዲስ፡-
የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፡-
ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ በማወደስ ስም ወሰን እንዳለፉት እኔን በውዳሴ ሽፋን በኔ ላይ ወሰን አትለፉ። ይልቁንም እኔ ባሪያ ነኝና፣ የአላህ ባሪያና መልክተኛውም በሉኝ።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

sultan.khedir?_t=8rSyJ87OrrU&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sultan.khedir?_t=8rSyJ87OrrU&_r=1

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ይህ አንቀፅ በየትኛውም ሁኔታ በፍጡራንና በፈጣሪ መካከል መመሳሰል እንደሌለና አላህ ሰሚና ተመልካች መሆኑን ያሳያል፡፡ መስሚያና መመልከቻ የብዙ ፍጡራን መገለጫዎች ቢሆኑም ነገር ግን የአላህ መስሚያና መመልከቻ ከፍጡራኑ ጋር አይመሳሰልም፡፡ በመስሚያና በመመልከቻ አምሳያ እንዳሌለው ሁሉ በሌሎችም ባህሪያቱ አምሳያ የለውም፡፡ ይህ አንቀጽ ሙስሊሞች ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ከመረዳት አንጻር ሊኖራቸው ለሚገባው ትክክለኛ አካሄድ በመርህ መልክ ይቀርጻል። አንቀጹ የጉድለት ባህሪዎችን ጥቅል በሆነ መልኩ ዉድቅ ሲያደርግ ምሉዕ ባህሪዎችን ግን በዝርዝር ያጸድቃል።

አቅጣጫዎች ህዋሳዊ ማነጻጸሪያ reference point በመጠቀም ብቻ የሚታወቁ ናቸው። ማንኛውም ሰው የቂብላን አቅጣጫ ለማወቅ ጸሀይን ማነጻጸሪያ እንደሚያደርገው ማለት ነው። ሰዎች በአዕምሮአቸው የሚቀርጿቸው ማነጻጸሪያዎች ሁሉ በፍጥረተ አለሙ የተገደቡ በመሆናቸው ስለአላህ ለመናገር እነዚህን ፍጡራዊ ማነጻጸሪያዎችን መጠቀም አይገባም።

፨ አህሉሱና ፍልስፍዎችን በቁርአን እና በሱና ላይ አይሾሙም። አላህ ለራሱ ያጸደቃቸውን ባህሪዎች ያጸድቃሉ፤ ለአላህ ተገቢዉን ክብር ስለሚሰጡ ስለባህሪዎቹ የተነገሩ መረጃዎችን የፍጡራንን ባህሪ በሚረዱበት ሁኔታ አይረዱም። ሁልጊዜ መነሻቸው አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጽዳት ስለሆነም እነዚህና መሰል የአስተሳሰብ ግድፈቶች አይገጥሟቸውም ።
አዎን! አላህን በጉድለትም ይሁን ከፍጡራን ጋር በመመሳሰል ከመግለፅ የፀዱ ናቸው።

በአንፃሩ አህባሾችና አርአያዎቻቸው ጀህሚዮች ግን ሁሌም መነሻቸው ስለ አላህ የተነገሩ መረጃዎችን ልክ ፍጡራን ላይ በሚያውቋቸው ባህሪያት መልኩ መረዳት ስለሆነ አላህን ከፍጡራን መለየት ያልቻሉ "ሙመሲላህ" አመሳሳዮች እነሱው ናቸው።

የሰማያትና የምድር ፈጣሪ አምላክ ሰለሆነው አላህ ሲነገር እንዴት ፍጡራዊ የሆኑ ባህሪዎች ይታወሳሉ??

አላህ ከጥመት ይጠብቀን!

አቡጁነይድ
ዙልቂእዳ 17/1436 ዓ.ሂ

www.fb.com/asmaewesifat

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አል-ሐፊዝ ኢብኑ ሀጀር አል-ዐስቀላኒ አል-አሽዓሪይ እንዲህ ብለዋል፡-

“የሸይኽ ተቂዩ አድ-ዲን ኢብኑ ተይሚያህ ኢማምነት እና ዝና ከፀሀይ በላይ ታዋቂ ነው፣ የእስልምና ሸይኽ መሆናቸውም እስከ ዛሬ ድረስ በበጎ ምላሶች ላይ ሲዘከሩ ይኖራል፣ ነገም እንደ ትላንትናው ይቀጥላል፣ የርሳቸውን ማነነት ያላወቁ እና ፍትሃዊ ከመሆን የሚርቁ ካልሆነ በስተቀር...  ይህን እውነታ የሚያስተባብል የለም። ያለጥርጥር... እሳቸው በዘመናቸው የነበሩ የእስልምና ምሁራን ሁሉ ሸይኽ ናቸውና። እነዚህም የፅሑፍ ስራዎቻቸው እሳቸው "ሙጀሲም" ናቸው በሚሉ ሰዎች ላይ ውድቅ ያደረጉ ናቸው። ምክንያቱም የኢጅቲሃድ ብቃቶች በእሳቸው ውስጥ እንደተሰበሰቡ የሸሪዓ ሊቃውንት መስክረውላቸዋልና። ✍🏻

📖 •ተቅሪዝ ኢብኑ ሀጀር "አር-ረድ አል-ዋፊር" የሚለውን ኪታብ ላይ ሰፍሯል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.


/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"ባጋጠማችሁ ችግር ምክንያት ሞትን አትመኙ::"
ረሱልﷺ
‏قال رسول الله ﷺ :
لا يتمنينَّ أحدُكم الموتَ لضُرٍّ نزل به فإن كان لابد مُتمنيًا فليقُلِ :
،
اللَّهمَّ أحيِني ما كانت الحياةُ خيرًا لي ، وتوفَّني إذا كانت الوفاةُ خيرًا لي
.
متفقٌ عليه

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ማንበብ የወንዶችን ወንድነት ይጨምራል፣ የሴትን ሴትነት ይጨምራል!
- ሰላም ለነዚያ ለአንባቢያን ይሁን! በዓለም ላይ በያሉበት ቦታ.. 📚👑

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

حكم التصوير للشيخ ابن باز

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

👆🏻👆🏻👆🏻
📚የቴሌ እና ሌሎች አክሲዮኖችን ስለመግዛት


🔗 ቴሌግራም ሊንክ
/channel/ustazilyas/1279

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በባልና ሚስት መካከል ያለው መኗኗር መሠረቱ፤ ፍቅር እና መተማመን ሊሆን ይገባል።
አሊያ ግን በመካከላቸው የሚያስተሳሰራቸው ገመድ ይሳሳል።
በዚህም የተነሳ አንዱ ለሌላው የስቃይ እና የቅጣት አለንጋ ይሆናል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሙዚቃ የሚደመጥበት  ቤት፣ ሶላት አዘግይቶ የሚሰገድበት  እና ቁርኣን የማይቀራበት ቤት የቤቱ ነዋሪዎች ሩቃ ሳይሆን ተውበት ነው የሚያስፈልጋቸው። ምክንያቱም ቤታቸው ውስጥ ያለው ጭንቀት በኃጢአት ምክንያት ነው።
አላህ ሆይ ባማረ መንገድ ወደ አንተ መልሰን።
🤲

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ከቀብር ጋር የተያያዙ ክልክል ተግባራት!

2ኛ. ቀብር ዘንድ ማረድ

 ይህ የሚደረገው ጉዳይን እንዲያሳኩ በማሰብ ለቀብሮች ለመቃረብ ከሆነ ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ለሆነ ዓላማ ከሆነ ደግሞ አደገኛ የሆነና ለሽርክ የሚዳርግ ቢድዓ ነው፡፡

ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ኢስላም ውስጥ “አቅር” የለም ብለዋል፡፡ አብድረዛቅ እንዳሉት

“በጃሂሊያ ዘመን ቀብር ዘንድ ከብትና በግ ያርዱ ነበር”

3ኛ. ከወጣው አፈር ውጭ በመጨመር ከፍ ማድረግ             
   
 4ኛ. ጄሶ መለሰን          
                 
  5ኛ. ቀብር ላዩ ላይ መፃፍ      
 
     6ኛ. ከላዩ መገንባት         

    7ኛ. ቀብር ላይ መቀመጥ

 እነዚህ ሁሉ ለአይሁዶችና ክርስቲያኖች መጥመም ምክንያት የሆኑ ቢድዓዎችና ከፍተኛ የሽርክ መዘዞች ናቸው፡፡

 ጃቢር እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀብርን በጄሶ መመረግ፣ ላዩ ላይ መቀመጥ፣ ከላዩ መገንባት፣ ከአፈሩ ውጭ መጨመርና ቀብር ላይ መፃፍ ከልክለዋል፡፡››

8ኛ. ቀብር ዘንድ መስገድ

 አቡ ሙርሢድ አልገነዊይ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው

‹‹ወደ ቀብር አትስገዱ ላዩም አትቀመጡ››   

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹መሬት ሁሉም መሰገጃ ነው ቀብርና ገላ መታጠቢያ ሲቀር ፡፡”

9ኛ. ቀብር ላይ መስጂድ መገንባት

 ይህ አይሁድንና ክርስቲያናትን ያጠመመ ቢድዓ ነው፡፡ ከላይ እንዳሳለፍነው ከዓኢሻ የሚከተለው ሀዲስ ተስተላልፏል

‹‹አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነቢያታቸውን ቀብር መስጂድ በማድረጋቸው አላህ ከእዝነቱ አባረሯቸው፡፡››

1ዐኛ. ቀብርን የበዓል ስፍራ ማድረግ

 ይህ ቢድዓ አደጋው የከፋ በመሆኑ ግልፅ በሆነ መልኩ ተከልክሏል፡፡

ከአቡ ሑረይራ እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹ቀብሬን የበዓል ስፍራ እንዳታደርጉ፡፡ ቤታችሁንም መቃብር አታድርጉ፣የትም ቦታ ብትሆኑ ሰላትን አውርዱብኝ ሰላታችሁ የትም ብትሆኑ ይደርሰኛል፡፡››

11ኛ. ጓዝ ጠቅልሎ ቀብርን ለመጐብኘት መጓዝ
                                                      
   ይህም ወደ ሽርክ የሚያደርስ መንገድ በመሆኑ ተከልክሏል፡፡
በአቡ ሑረይራ እንደተላለፈው ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹ወደ ሶስት መስጂዶች እንጂ ጓዝን ጠቅልሎ ለመጐብኘት መጓዝ አይፈቀድም መስጂደል ሀራም፣ የመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)  መስጂድና የአልአቅሳ መስጂድ።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?

ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።”
📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)


/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሺዓዎች!

“እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ ስም ማጥፋት ፈልገው ነበር፣ ነገር ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው የሰሓቦቻቸውን ስም አጠፉ። እርሱ መጥፎ ሰው ነው እንጂ እርሱ ጥሩ ሰው ቢሆን ኖሮ ባልንጀሮቹም ጥሩ ይሆኑ ነበር፤ እንዲባል የነቢዩ ﷺ ባልደረቦቻቸውን ሰደቡ።”

| ኢማሙ ማሊክ/አስ – ሷሪም አል– በት–ታር (580)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" የሚሉ ሙስሊሞችን ማየት በጣም ልብ የሚያደማ ነው። ተመልከቱ ለዛፉ ሲሰግዱ! ተመልከቱ የሚሰሩትን። ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ! የብሄር አጀንዳ አቅልህን አስ፞ቶ ጀሀነም እንዳይከትህ ተጠንቀቅ። አላህን ፍራ!! መስቀልን የምንቃወመው የአማራ ስለሆነ አይደለም። የኩፍር በአል ስለሆነ እንጂ። ኢሬቻ የኦሮሞ ስለሆነ በተለየ አይን አናየውም። የኩፍር ቡላና ዳለቻ የለውም። ሁሉም ኩፍር ነው። ሁሉም የጣኦት አምልኮ ነው። ሁሉም ተውሒድን በጥብቅ ከሚያስተምረው ኢስላም ጋር ፈፅሞ የሚፃረር ነው። ሁለቱም ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ የለየት ክህደት ነው።
ዛሬ የብሄር አጀንዳ እራሱን የቻለ ጣኦት ሆኗል። ሰዎች ለብሄር ሲሉ ካፊርን ይወዳሉ። ሙስሊምን ይጠላሉ። ለብሄር ሲሉ ለመስቀል፣ ለኢሬቻ ወግነው ይሟገታሉ። የኩፍር በአል ያከብራሉ።
የሚያሳፍረው ሸይኾችና ዱዓቶች ጭምር በዘረኝነት መለከፋቸው ነው። እስኪ የመስጂድ ኢማም ሆኖ፣ ጥምጣም ጠምጥሞ የኦርቶዶክስ ሰልፍ የሚያደምቅ፣ በዘራቸው የተነሳ ሙስሊም ትግሬዎችን ጭምር የሚያጥላላ፣ ለኢሬቻ "የእንኳን አደረሳችሁ" መልእክት የሚያስተላልፍን ልክፍተኛ አስቡ። ዘረኝነት አደዛዥ እፅ ነው። በዚህ በሽታ የተለከፈ ሰው እይታው ቁንፅል ነው። አርቆ ማሰብ አይችልም። ይህንን ሀሺሽ፣ ይህንን ጣኦት አጥብቀን ካልተዋጋነው ብዙ ነገር ያሳጣናል።
ያያያዝኩት ቪዲዮ ኢሬቻ የሚያከብሩ ሰዎችን ድርጊት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢማሙ አቢ ሀፍስ ታጅ አድ-ዲን አል-ፋኪሃኒ(734 ሂ.) (አላህ ይዘንላቸው) ሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የተለያዩ የመውሊድ አከባበር ዓይነቶች እንዳለ ሲያብራሩ፡-
“አንዱ፡- አንድ ሰው ከራሱ ገንዘብ ለባለቤቱ፣ ለጓደኞቹና ለቤተሰቡ የሚያዘጋጀው ነው። በዚህም ጉባዔ ላይ ምግብን ከመብላት ላያልፍና ወንጀሎችን የማይፈፅሙ ከሆነ ነው። ይህንን ነው የተጠላ ቢድዐና አስቀያሚ ነገር እንደሆነ የገለፅነው። ምክንያቱም የዘመናት መብራት፣ የሃገራት ውበት የሆኑት ምሁራኖችና የኢስላም ሊቃውንት የሆኑት ቀደምት የአላህ ታዛዦች አልሰሩትምና።”

Читать полностью…
Subscribe to a channel