ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
ነቢያችን ﷺ በሸዕባን ወር ለምን አብዝተው እንደሚጾሙ ሲጠየቁ፣ እንዲህ በማለት መለሱ።
«ያ በረጀብና በረመዳን መካከል ሰዎች የሚዘነጉበት ወር ሲሆን በውስጡም ለዓለማት ጌታ ሥራዎች ከፍ ብለው የሚወጡበት ወር ነው።»
አሕመድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል/አልባኒ ሐሠን ብለውታል
ሰለመተ ኢብን ኩሀይል (አላህ ይዘንላቸውና)**
እንዲህ ይላሉ፡
" የሻዕባን ወር የቁርአን አንባቢዎች ወር ነው። " ይባል ነበር።"
قال رسول الله ـﷺـ
« إذا أراد الله بعبده الخير عجّل له العقوبة في الدنيا وإذا أراد الله بعبده الشر أمسك عنه بذنبه حتى يوافي به يوم القيامة » خرّجه الترمذي وحسنه 》.
“አላህ ለባርያው መልካምን ሲሻለት በዱንያ ላይ እንዲቀጣ ቀደም ያደርግለታል። በባርያው ላይ ሸርን ሲፈልግ ግን በወንጀሉ እንዲቀጣበት የቂያማ እለት ድረስ ያቆየዋል።”
የሥነ-ምግባር(የአኽላቅ) ትምህርት ከዒልም ይቀድማል!!
ዐብዱላህ ኢብኑ አል ሙባረክ እንዲህ ብለዋል፡-
"የሥነ-ምግባርን ትምህርት ለ30 ዓመታት ተማርኩ፣ ዒልምን ለ20 ዓመታት ተማርኩ፣ ሠለፎች የሥነ-ምግባርን ትምህርት ከዕውቀት በፊት ይማሩ ነበር።"
- አል-ጋያህ 446/1 | 📚
ይህ የሐዲስ በጣም ግሩም እና አስደሳች አፅናኝ ሐዲስ ነው፣ ለማንኛውም ሰው በዚህ ዱንያ ውስጥ ያመለጠው ነገር ማንኛውም ነገር መጽናናትን ይሰጣል። እባክዎ ትኩረት ይስጡት እና ፅንሰ–ሀሳቡን ያሰላስሉ።
ሐዲሱን ዐብድላሂ ኢብኑ ዑመር (ረዲዬሏሁ አንሁማ) ያስተላለፉት ሲሆን ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡
"አራት ነገሮች በአንተ ውስጥ ካሉ፣ ከዚህ ዓለም ያመለጠህ ነገር ምንም አይጎዳህም፤ አማናን(አደራን) መጠበቅ፣ እውነትን መናገር፣ መልካም ምግባር እና በምግብ ላይ ቁጥብ መሆን ናቸው።"
(አህመድ፣ ኢብኑ አቢ አድ–ዱንያ፣ አጥ–ጠበራኒ እና አልበይሃቂ በሐሠን በሚባለው የሐዲስ ደረጃ ሰንሰለቶች ዘግበውታል፣ አልባኒም ሰሒህ መሆኑን አረጋግጠዋል።)
ይህ ሐዲስ በዚህ ውስጠ-ባለ ዓለም የምናጣው ነገር ምንም ቢሆን እነዚህ አራት ነገሮች በእኛ ውስጥ ካሉ በእውነቱ ከተቀማጠሉት ነገሮች የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው።
እባክዎ ይህን ሐዲስ በልብዎ ውስጥ ያስቀምጡት እና በሕይወትዎ ውስጥ ለመተግበር ይሞክሩ። 🙏
«ነፍስህ እንደምትጋልበው ፈረስ ናት!
ቆራጥነትህን ስታውቅ ትበረታለች። ስንፍናህን ካወቀች ደግሞ ልትጠቀምብህ ትሻለች። ስሜቷን እንድታሳካላት ብቻ ትወተውታለች!»
ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል‐ሐንበሊይ
አንድ ሰው ዙሀይር ኢብኑ አቢ ኑዐይም ጋር መጥቶ፦
“አንቱ አቡ አብዲራህማን ሆይ! እስኪ ምከሩኝ!" አላቸው።
እሳቸውም፦ “በተዘናጋህበት ሰዓት አላህ እንዳይወስድህ ተጠንቀቅ።” በማለት መከሩት።
📗ሲፈቱ አስሰፍዋ (4/9)
اللهم أيقِظْنا من رقدات الغفلة، ووفقنا للتزود من التقوى قبل النقلة، وارزقنا اغتنام الأوقات في هذي المهلة، واغفر لنا ولوالدينا ولجميع المسلمين برحمتك يا أرحم الراحمين ..🤲
/channel/sultan_54
"በጭንቅ እና በመከራ ጊዜ ዱዓው ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚፈልግ በድሎት ጊዜ ዱዓ ማድረግ ያብዛ።”
ሰሒሁ አትቲርሚዚ (2382)
ፈትዋ፦ ለሞተ ሰው ሰደቃ ማውጣት ይቻላልን?
"አንተ በህይወት ያለህ ሰው ሆይ! መልካም ሥራ ላንተ ያስፈልግሃልና ሥራውን ለራስህ ሥራ፣ ለሞቱት አባቶችህና እናቶችህ ወንድም እህቶችህ እንዲሁም ለሌሎች ሙስሊሞች ዱዓ አድርግላቸው።
በመልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ሱና የተገለፀው ይህ ነው።
ይህ ሆኖ ሳለ አንድ ሰው ለሞተ ሰው ሰደቃ ቢያደርግ ወይም ስለነሱ ቢጾም ወይም ዱዓ ቢያደርግ ምንዳውን ለሞተው ሰው እንዲሆን አስቦ ማንኛውንም ዒባዳ ቢያደርግ ምንም ችግር የለበትም።"
📚ፈትዋ ኑሩን ዓለ ደርብ
(ሸይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ)
ስለ ሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ኹጥባ
የሰማያትና የምድር ንግሥና በእጁ የሆነ አምላካችን አላህ የተመሰገነ ይሁን፣ የሱ ባሪያ እና መልእክተኛ በሆኑት ሙሐመድ በእሳቸውና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም በባልደረቦቻቸውም ላይ በሙሉ ይስፈን፡-
እናንተ ሙስሊሞች ሆይ!
እናንተንም ራሴንም ሁሉን የሚችለውን አምላክ እንድትፈሩ እመክራለሁ። እሱን መፍራት(ተቅዋ) በችግር እና በመከራ ጊዜ ጠንካራ ምሽግ እና አስተማማኝ መሸሸጊያ ነው።
የሎስ አንጀለስ ከተማን የተነሳው ሰደድ እሳት፣ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች አውድሟል።
የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።
በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።
በዚህም የተሳ ተአሜሪካ ሎስ አንጀለስ ነወሪዎች ቤት አልባ እና ሀዘን ላይ የጣለውን ሁላችንም አይተናል ሰምተናል። እነዚህ ክስተቶች በአጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ወደ እርሱ ወደ አላህ እንድንመለስና ከእንቅልፋችን እንድንነቃ የሚያስገነዝበን የአላህ ምልክቶች ናቸው።
ምእመናን ሆይ!
አላህ جل جلاله እንዲህ ብሏል፡- “ተአምራቶችንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም።” (አል ኢስራእ 59)።
እነዚህ የተፈጥሮ አደጋዎች ዓለም ጊዜያዊ እንደሆነች እና ኃይል የአላህ ብቻ እንደሆነ ከአላህ ለአገልጋዮቹ ማሳሰቢያ ናቸው። የኛ የቴክኒክ ሃይል እና ሳይንሳዊ እድገታችን ሊያስደንቀን ይችላል ነገርግን ከአላህ ሰራዊቶች ፊት ግን ምንም መቋቋም አይችሉም።
ሙስሊሞች ሆይ!
ተውበት እናድርግ ከሀጡአት ብንመለስ ፍርሃትን ደኅንነትን፣ ጭንቀም በብልጽግናን ሊተካ እንደሚችል እናስታውስ። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እንዲህ ይላል።
"የሰዎች እጆች በሠሩት ሥራ ምክንያት በየብስና በባሕር ላይ ፈሳድ ጥፋት ታየ( ተንሰራፋ)። ይመለሱ ዘንድ ይሠሩት ከነበሩት ከፊሉን ይቀምሱ ዘንድ" (አል-ሩም 41)።
ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ለባሮቿ መሐሪ ነው፣ በተውበታችን ይደሰታል፣ በንስሐም ወደ እርሱ የተመለሱትን ይቅር ይላልና እነዚህን ክስተቶች ለተጠያቂነት እና ወደ አላህ የመመለሻ ዕድል እናድርጋቸው።
ሙስሊሞች ሆይ!
ይቅርታን እንለምን እና አላህ መከራውን ከእኛ እንዲያርቅልን ደጋግመን እንጸልይ፣ ለተቸገሩትም ሆነ ለተጎዱት የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ፣ ይህ ወደ አላህ የመቃረብ ትልቁ በሮች አንዱ ነውና። ለአላህ በመታዘዝ ጸንተን ለመኖር እንትጋ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም መዳን ነው።
አምላኬ ሆይ መከራውን ከኛ ላይ አስወግድ አገራችንን እና የሙስሊም ሀገራትን ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቅልን። አምላኬ ሆይ አንቀጾችህን ከሚያስተውሉ እና ወደ አንተ ከሚመለሱት ጸጸተኞች መድበን።
ይህን እላለሁ አላህንም ለእኔም ለእናንተም ምሕረትን እለምነዋለሁ። ከእርሱም ምሕረትን ለምኑት እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና።
📖 ተፍሲሩ ሱረቲ አዝ– ዘልዘላህ
🎙የሱሩቱ አዘልዘላህ ማብሪሪያ
🕌 ጎፋ ተንዒም መስጂድ የተሰጠ ደርስ
📌" የእግር ኳስ ጨዋታ ቅድም ሁኔታዎች(ሹሩጦች) ⚽
በሸይኽ ናሲሩ አድ-ዲን አል_አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና"✅
1_የጨዋታው አላማ አካልን ማጠናከር ወይም ነፍስን ማዝናናት መሆን አለበት።
2_ሀፍረት ገላ መጋለጥ የለበትም። ለምሳሌ ወንዶች ጉልበታቸውና ከዚያ ከፍ ያለው አካል መታየት የለበትም።
3_ጨዋታው መስጂድ ውስጥ ሶላትን በጀመዓ መስገድን የመሳሰሉ ሸሪዓዊ ተግባራት ላይ መዘንጋትን የሚያስከትል መሆን የለበትም።
4_ጨዋታው ዛሬ ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት ተብሎ የሚጠራው አይነት መሆን አለበት፤ ስለዚህም ኳስ መጫወት ቂም ፣ጥላቻ ፣መደባደብ ፣መመታት እና የመሳሰሉትን ሊያመጣ አይገባም።
📚 [ፈታዋ ጂድ_ዳህ ካሴት (ቁጥር 13)]
-
«ፈጅር ሰላትን በመተኛት ያሳለፈ፣እለቱን አውድሟል፤ ቀኑን ያለ ቢላ አርዷል።»
(ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር)
ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ ተውበት ለማድረግ ሰፊ ጊዜ አለን ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፤ ከዚያም እነርሱ በተዘናጉበት ሰአት ድንገት ሞት ያዘቻቸው።
ኢላሂ ከሞት በፊት ተውበተን ነሱሓን ወፍቀን።
ከአቡ መስዑድ አልአንሳሪይ ራዲየሏሁ ዓንሁ እንደተዘገበው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሶላት ወቅት ሰሓቦች ትከሻ ይነካሉ፣ ቀጥ ብለው እንዲቆሙ እና እርስ በርስ እንዳይለያዩ ያዝዙ ነበር። ምክንያቱም በሰፍ ውስጥ ያለው ልዩነት በልቦች ውስጥ ልዩነት ያስከትላል። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም፦
" ከእኔ ቀጥሎ ያለው ሰፍ አጠገብ ለመቆም ተገቢዎቹ ሰዎች የአእምሮና የጥበብ ሰዎች ናቸው፣ ከዚያም ከነርሱ ቀጥሎ ያለ ሰው ከዚያም ቀጥሎ ሰው ነው።" አሉ።
ከዚያም አቡ መስዑድ ራዲየሏሁ ዓንሁ በዘመናቸው ለነበሩ ሰዎች እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ዛሬ የበለጠ ልዩነት ያለባችሁ ናችሁ"፣ ይህም በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘመን ሲነፃፀር በአቡ መስዑድ ዘመን ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት እንደጨመረ ያሳያል።
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
شهر شعبان يغفل عنه الناس
❗️ወርሃ ሸዕባን
ብዙሃኑ የሚዘናጋበት ወር!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ሸዕባን 01/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
በወርሃ ሸዕባን ምን እናድርግ?…
⚀ ጾም ማብዛት። ሰኞና ሀሙስ እና ሌላውንም መለማመድ። ለረመዳን መዘጋጀት።…
⚁ በቀደሙ ረመዳኖች ያመለጡንን ቀዷ ማውጣት።…
⚂ ከሰዎች ጋር እርቅ መፍጠር። ጥላቻና ቂምን መተው። የሰዎችን ሐቅ መመለስ። የረመዳንን በረከት ከሚያሳጡ መካከል መጥፎ ስነምግባር እና የሰዎችን ሐቅ መጣስና በደል መፈፀም ዋነኞቹ ናቸው።
:
«አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ሸዕባን ወበሊግና ረመዳን።»
ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።
«የቁርኣን ድምፅ፤ ያረጋጋል፣ ስክነትን ይሰጣል እና ነፍስ ከፍ እንድትል ያደርጋል።»
በዳዒኡ– አት-ተፍሲር (143/2)
ኢብን ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡-**
"…እናም ስንት ሰዎች ኃጢአት ይሠራሉ፣ ከዚያም ግን ኃጢአታቸውን አስታውሰው ኢስቲግፋር ያደርጉሉ፣ ከተውበታቸው በኋላም ከበፊቱ የተሻለ እና የተቃና ህይወት ላይ ይሆናሉ።"
አልቀውል ሙፊድ ―3/178
የዑምራ ቪዛ ካስፈለገዎ
በሳዑዲ አረቢያ የሀጅና ዑምራ ሚንስቴር አስፈላጊውን ፎማሊቲ በማሟላት እውቅና አግኝቶ ለደንበኞቹ አገልግሎት በመስጠት ላይ ወደሚገኘው ሪህለቲ ትራቭል ኤጀንት ጎራ ይበሉ።
ለበለጠ መረጃ ፦
📱 0910365924
📱 0969020303
ሪህለቲ ትራቭል ኤጀንት
አድራሻ:- ቤተል አፍራን ታወር 1ኛ ፎቅ
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«ሐጅ እና ዑምራ አከታትላችሁ አድርጉ፣ የወናፍ እሳት፤ የብረት፣ የወርቅ እና የብር ቆሻሻን እንደሚያስወግድ ድህነትንን እና ኃጢኣቶችን ያስወግዳሉ።»
የፈጅር ሰላት አላህ የወደደው እና እሱን መገናኘትን የሚወድ ቀልብ ካልሆነ በቀር አይገጣጠምም። ♥
ከተገጣጠሙት አደርገን!
የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الزلزال دررس وعبر
❗️ ከመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት የምንማራቸው 3 ቁም ነገሮች
🎙 በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ረጀብ 09/1446 አ/ሂ
©️ /channel/sultan_54
®️ http://t.me/kalityhamzamesjid
قال تعالى : { حتى إذا أخذت الأرض زخرفها وازينت وظن أهلها أنهم قادرون عليها أتاها أمرنا ليلا أو نهارا فجعلناها حصيدا كأن لم تغن بالأمس ۚ كذلك نفصل الآيات لقوم يتفكرون }
Читать полностью…የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
❗️ የረጀብ ወር ታላቅነትና በውስጧ የሚሰሩ ቢድዓዎች
🎙 በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ረጀብ 03/1446 አ/ሂ
©️ /channel/sultan_54
®️ http://t.me/kalityhamzamesjid
ዐብዱል ቃዲር አል_ጀይላኒ ማናቸው?
💎“በኢማሙ አሕመድ ረዲየላሁ ዐንሁ የእምነት ጎዳና ላይ ካልሆነ በቀር የአላህ ወልይ መሆን አይቻልም።”
✍ዐብዱል ቃዲር አልጀይላኒ
📚ذيل طبقات الحنابلة لإبن رجب (2-202)
/channel/sultan_54
መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?
ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
“በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።”
📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)
/channel/sultan_54
"ነብዩንﷺ የጠላ እና የተፃረረ ሁሉ አሏህ ስሩን ይቆርጠዋል ደብዛውንም ያጠፋዋል።"
📚ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ【አስ_ሳሪሙል መስሉል】
/channel/sultan_54