ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
ረመዳን ሙባረክ!!
እንኳን ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ። አላህ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መልካም የዒባዳ ግዜ እዲያደርገው እንለምነዋለን፡፡
ከተዘነጉ ሱናዎች ውስጥ
ከኡበይ ኢብኑ ከዕብ ተይዞ እንዲህ ይላል፦
﴿كان رسولُ اللهِ ﷺ إذا سلَّم من الوِترِ قال سُبحانَ الملِكِ القدُّوسِ ثلاثَ مرّاتٍ يرفعُ في الثّالثةِ صوتَه.﴾
“የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የዊትር ሰላትን በጨረሱ ግዜ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ሶስት ግዜ እንዲህ ይሉ ነበር፦ ‘ሱብሐነል መሊከል ቁዱስ’”
📚 ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል: 1750
የረመዳን የኢፍጣር ፓኬጅ
"ፆመኛን ያስፈጠረ ከፆመኛው ሳይቀነስ ለርሱም እኩል ምንዳ ይኖረዋል"
ለ1 ቤተሰብ 5,ዐዐዐ ብር ብቻ
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
1000461657455
ለበለጠ መረጃ፦
📱+251969437984
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna
እንኳን ለረመዳን በሰላም አደረሳችሁ
አላህ ይቀበልን፤ ይቀበላችሁ!!
تقبل الله صيامكم وصالح أعمالكم 🌙
📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር
ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-
“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”
ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-
"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።
ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-
"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"
በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:
"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"
ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።
ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።
ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።
ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"
አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!
#ዝክረ_ረመዳን
_
📜 የኪታቡ አስሲያም ማብራሪያ
ከዑምደቱል አሕካም
በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር
فلَيتَكَ تَحلو وَالحَياةُ مَريرَةٌ. وَلَيتَكَ تَرضى وَالأَنامُ غِضابُ. وَلَيتَ الَّذي بَيني وَبَينَكَ عامِرٌ. وَبَيني وَبَينَ العالَمينَ خَرابُ. إِذا نِلتُ مِنكَ الوُدَّ فَالكُلُّ هَيِّنٌ. وَكُلُّ الَّذي فَوقَ التُرابِ تُرابِ
Читать полностью…የሳዑዲ የፈትዋ ሊቃውንት ቋሚ ኮሚቴ በዘመዳሞች መካከል የሚደረገው ጋብቻ፤ ልጆች ላይ አካል ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ወይ? በሚል ጥያቄ በተጠየቁ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፡-
"በዘመዳሞች መካከል ጋብቻ ከማድረግ የሚከለክሉ ትክክለኛ የሆኑ ሐዲሶች የሉም። በህፃናት ላይ አካል ጉዳት የሚከሰተው በአላህ ፈቃድ እና መሻት እንጂ በሰፊው እንደሚሰራጨው፤ በዘመዳሞች መካከል በሚደረገው ጋብቻ የተነሳ አይደለም።"
📚ፈትዋ አል–ለጅነቱ አድ–ዳኢማህ (13/18)
وقد سئل علماء اللجنة الدائمة عن الزواج من الأقارب وهل ذلك سبب لحصول الإعاقة للأولاد ؟
فأجابوا : " ليس هناك أحاديث صحيحة تمنع من الزواج بين الأقارب , وحصول الإعاقة إنما يكون بقضاء الله وقدره , وليس من أسبابه الزواج بالقريبات كما يشاع " انتهى .
"فتاوى اللجنة الدائمة" (18/13) .
👆🏻👆🏻👆🏻
📚#ፈታዋ የሚጠይቅ ሰው ሲጠይቅ የሚከተላቸው ስርዓቶች
➡️ ፈተዋ የሚጠየቀው ሰው ውጥረት ውስጥ በሆነበት ፣ ባልተረጋጋበት፣ ሀዘን ውስጥ በሆነበት ወይም በመሳሰሉት ሁኔታ ባለበት ሰዓት አለመጠየቅ
🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
🔗 ቴሌግራም ሊንክ
/channel/ustazilyas/1399
🔗 ቪዲዮውን ለመከታተል
https://www.facebook.com/ustathilyas/videos/1704645983797013/
____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አሕመድ የትምህርት መድረክ
https://www.facebook.com/ustathilyas
አነስ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
" ሙስሊሞች ሻዕባን በገባ ጊዜ በሙስሕፎች(ቁርኣን) ላይ ይደፉ ነበር፤ የሚያነቡ ሲሆን፣ ከገንዘቦቻቸው ዘካም ያወጡ ነበር። ይህንንም ያደረጉ የነበረው ደካማውን እና ድሃውን ለረመዳን ጾም ለማበረታታት ነው።
(ለጣኢፉ አልመዓሪፍ፣ ገጽ 135)
አላህ የተቀሩትን የሻዕባን ቀናቶች በረካ አድርጎልን ረመዳን ይዞት የሚመጣውን ኸይሮች ሁሉ የምናገኝ ያድርገን!!
Читать полностью…ከአቡ መስዑድ አልአንሳሪይ ራዲየሏሁ ዓንሁ እንደተዘገበው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሶላት ወቅት ሰሓቦች ትከሻ ይነካሉ፣ ቀጥ ብለው እንዲቆሙ እና እርስ በርስ እንዳይለያዩ ያዝዙ ነበር። ምክንያቱም በሰፍ ውስጥ ያለው ልዩነት በልቦች ውስጥ ልዩነት ያስከትላል። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም፦
" ከእኔ ቀጥሎ ያለው ሰፍ አጠገብ ለመቆም ተገቢዎቹ ሰዎች የአእምሮና የጥበብ ሰዎች ናቸው፣ ከዚያም ከነርሱ ቀጥሎ ያለ ሰው ከዚያም ቀጥሎ ሰው ነው።" አሉ።
ከዚያም አቡ መስዑድ ራዲየሏሁ ዓንሁ በዘመናቸው ለነበሩ ሰዎች እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ዛሬ የበለጠ ልዩነት ያለባችሁ ናችሁ"፣ ይህም በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘመን ሲነፃፀር በአቡ መስዑድ ዘመን ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት እንደጨመረ ያሳያል።
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
شهر شعبان يغفل عنه الناس
❗️ወርሃ ሸዕባን
ብዙሃኑ የሚዘናጋበት ወር!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ሸዕባን 01/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
በወርሃ ሸዕባን ምን እናድርግ?…
⚀ ጾም ማብዛት። ሰኞና ሀሙስ እና ሌላውንም መለማመድ። ለረመዳን መዘጋጀት።…
⚁ በቀደሙ ረመዳኖች ያመለጡንን ቀዷ ማውጣት።…
⚂ ከሰዎች ጋር እርቅ መፍጠር። ጥላቻና ቂምን መተው። የሰዎችን ሐቅ መመለስ። የረመዳንን በረከት ከሚያሳጡ መካከል መጥፎ ስነምግባር እና የሰዎችን ሐቅ መጣስና በደል መፈፀም ዋነኞቹ ናቸው።
:
«አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ሸዕባን ወበሊግና ረመዳን።»
ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።
«የቁርኣን ድምፅ፤ ያረጋጋል፣ ስክነትን ይሰጣል እና ነፍስ ከፍ እንድትል ያደርጋል።»
በዳዒኡ– አት-ተፍሲር (143/2)
وَالْعَصْرِ (1) إِنَّ الْإِنْسَانَ لَفِي خُسْرٍ (2) إِلَّا الَّذِينَ آَمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ (3)
«(1) በዘመን እምላለሁ፡፡ (2) ሰው ሁሉ በእርግጥ በክስረት ውስጥ ነው፡፡ (3) እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም ላይ አደራ የተባባሉት፣ በትእግስትም ላይ አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡»
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
رمضان شهر القرآن
❗️ረመዷን የቁርኣን
ወር!
🕌 ጎተራ ፈትህ 54 መስጂድ
🗓 ሸዕባን 28/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
🔴ሰበር ዜና
የዘንድሮው1446/2025 የረመዳን ወር ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ ታይቷል!
በዚህም መሰረት ነገ ቅዳሜ ረመዳን 1 ይሆናል።
የተራዊህ ሰላት ከኢሻ ሶላት በኋላ በሁለቱ ሀረመይን መስጂዶች ይጀመራል።
ሸይኽ ፈውዛን እንዲህ ይላሉ፦
እውነተኛ ሰለፊይ መሆን ከፈለክ የሚከተሉትን ማድረግ አለብህ
📒 በተጠና ሁኔታ የሰለፎችን መንሀጅ መማር አለብህ፣
📒 በሰለፎች መንሀጅ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖርህ ይገባል፣
በወሰን ማለፍና በቸለተኝነት መሃል ልትተገብረው ይገባል።
የሰለፎች ጎዳና ይህ ነው! ይህ ትክክለኛ የሰለፍ አስ–ሷሊሕ መንሀጅ ይህ ነው! አዎን፣ ነገር ግን በባዶ ወኔ ወደነሱ መንጅ እራስን ማስጠጋት ቢጎዳ እንጂ ሚፈይደው ነገር የለም።
العلامة صالح الفوزان حفظه الله المقطع كامل كلام من ذهب
https://youtu.be/W1j8dRJRqXs?si=U5LcasugEhim_N8z
ሸይኽ ኢብን ዑሠይሚን ረሂመሁ አሏህ እንዲህ ብለዋል፡-
"የቀልብ መድረቅ ለማስወገድ ከሚረዱ አንዳንድ ሰበቦች መካከል፡- ቁርአንን በ"ተደቡር" በአስተውሎት በብዛት መቅራት፣ በምታነብበት ጊዜ፤ ይህ የአሏህ የተቀደሰ ንግግር እንደሆነ ማሰብ፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ንግግር እንጂ የሰው ልጆች ንግግር አለመሆኑን ማሰብ። በዚህ መልኩ ቁርኣን ከቀራህ፣ የርሱ ቃል ልብህ ውስጥ ይገዝፋል፣ ከእሱም ተጠቃሚ ትሆናለህ"።
(ተፍሲሩ ሱራቲ አል-አንዓም ገጽ 224)
🪟ረመዳንን እንዴት እንቀበል?
🎙አሽ– ሸይኽ ዐብድሰላም አሽ'ወይዒር ሀፊዘሁሏህ
📌ማስታወሻ ትሆን ዘንድ በግርድፉ የተተረጎመ
✨@Abuhatim7
🔴« ብላቴናው እራሱን ከባእድ ሴቶች እስካራቀ ድረስ ኸይር ላይ ነው!! »
ሸይኽ ሱለይማን አሩሓይሊ
የማይሰለች ድምፅ!
ሸይኽ ሙሐመድ አዩብ ረሂመሁላህ
ሱረቱ ጣሀ
1414 አ/ሂ ከተራዊህ ሰላት የተወሰደ
/channel/sultan_54
ነቢያችን ﷺ በሸዕባን ወር ለምን አብዝተው እንደሚጾሙ ሲጠየቁ፣ እንዲህ በማለት መለሱ።
«ያ በረጀብና በረመዳን መካከል ሰዎች የሚዘነጉበት ወር ሲሆን በውስጡም ለዓለማት ጌታ ሥራዎች ከፍ ብለው የሚወጡበት ወር ነው።»
አሕመድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል/አልባኒ ሐሠን ብለውታል
ሰለመተ ኢብን ኩሀይል (አላህ ይዘንላቸውና)**
እንዲህ ይላሉ፡
" የሻዕባን ወር የቁርአን አንባቢዎች ወር ነው። " ይባል ነበር።"
قال رسول الله ـﷺـ
« إذا أراد الله بعبده الخير عجّل له العقوبة في الدنيا وإذا أراد الله بعبده الشر أمسك عنه بذنبه حتى يوافي به يوم القيامة » خرّجه الترمذي وحسنه 》.
“አላህ ለባርያው መልካምን ሲሻለት በዱንያ ላይ እንዲቀጣ ቀደም ያደርግለታል። በባርያው ላይ ሸርን ሲፈልግ ግን በወንጀሉ እንዲቀጣበት የቂያማ እለት ድረስ ያቆየዋል።”
የሥነ-ምግባር(የአኽላቅ) ትምህርት ከዒልም ይቀድማል!!
ዐብዱላህ ኢብኑ አል ሙባረክ እንዲህ ብለዋል፡-
"የሥነ-ምግባርን ትምህርት ለ30 ዓመታት ተማርኩ፣ ዒልምን ለ20 ዓመታት ተማርኩ፣ ሠለፎች የሥነ-ምግባርን ትምህርት ከዕውቀት በፊት ይማሩ ነበር።"
- አል-ጋያህ 446/1 | 📚