ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
አል-ጁነይድ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
«የመልእክተኛውን ﷺ ፈለግ ከተከተሉ፣ ሱናቸውን እና የሳቸውን ጎዳና አጥብቀው ከያዙ በቀር ሁሉም መንገዶች በፍጡራኑ ላይ የተዘጉ ናቸው።»
ኢብን ረጀብ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:**
"የሌሊትን ሰሏት መቆም ኃጢአቶችን የሚያስተሰርይ ሲሆን፣ በተጨማሪም የመልካም ምንዳዎች ደረጃዎችን ከፍ ያደርጋል። ቀደም ብለን ከዚህ በፊት እንደጠቀስነው፣ ይህን የ"ለይለ ሰላት" የሚያዘወትሩ ሰዎች ምንም ምርመራ ሳይደረግላቸው ወደ ጀነት ከመጀመሪያ ገቢዎች ተርታ የሚመደቡ ናቸው።"
ከረመዿን በኋላ ቁርኣንን የተዉ ሰዎች እና መፍትሄው
Читать полностью…የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ፤ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ፤ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል።»
(ቡኻሪ ዘግበዉታል)
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ በዚህ ቁርኣን ሰዎችን ከፍ ያደርጋል። ሌሎችን ደግሞ በርሱ ያዋርዳል።”
/channel/sultan_54
ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ አሉ፦ አምላክ ለዚህ አለም ህዝብ የዋለለት ትልቁ ፀጋ ነብዩ ሙሀመድን ለእነርሱ ነብይ አድርጎ መላኩ ነው።
ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም የኛ ውድ ነቢይ ስጦታችን❤️
በመካ ተወለዱ፣ ክብር የተሞላባት ሆነች፣
ወደ መዲና ሄዱ፣ ብርሃን የተሞላባት ሆነች፣
በልቦቻችን ገቡ፣ ቀልባችንም በንጽህና ተሞላች።
በእሳቸው ላይ ሰላዋት ያብዙ! 🤍😍
ዘከሪያ (በርሳቸው ላይ ሰላም ይሁንና) እንዲህ አሉ፦
‘ጌታዬ ሆይ! እኔ በዕድሜ ገፋሁ፣ አጥንቴም ደክሞአል፣ ራሴም በነጭ ፀጉር( በሽበት) ተሞልቷል። ከዚህ በፊት ዱዐዬን ሳትሰማ አልቀረህም።’"
(ሱረቱ መርየም:4)
ሁሉም ተፈጥሯዊ ሰበቦች በዘከሪያ ፊት ተደንቅረው ነበር፤ (ልጅን) ማግኘት ይፈልጋሉ፤ ልጅን ለማግኘት መንገዶቹ ሁሉ ተዘጋግተዋል። አጥንታቸው ደክሞ፣ ራሳቸው በነጭ ፀጉር ተነድፎ፣ ሚስታቸውም መኸን ናት! እንግዲህ ልጅ ከየት ይመጣል? እነዚህ ሁሉ እንቅፋቶች በተሰበሰቡ ጊዜ፤
ዘከሪያ (በእሳቸው ላይ ሰላም ይሁንና) አላህ ቻይ መሆኑን፣ ምንም ለርሱ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ያውቁ ነበር። ከተፈጥራዊ ሰበቦች በሙሉ ቀልባቸውን አጥርተው፣ በአላህ ኃይልነት ፊት ምንም የሚያቅት ነገር እንደሌለ ባዩ ጊዜ፣ ልባቸውን በጌታቸው ላይ ብቻ አንጠለጠሉ፣ ያን ጊዜ ውብ የሆነው ምላሽ መጣ!!
‘ዘከሪያ ሆይ! እኛ አንተን በየሕይ የሚባል ወጣት ልጅ እንበስርሃለን!’
መርየም(7)
በእርግጠኝነት(በየቂን) በእምነት ከአላህ ጋር የሚኗኗር፣ አላህ ለእርሱ ተአምራትን ያገራለታል።"
📕"ረሳኢሉን ሚነል ቁርኣን" ከሚለው መፅሐፍ ተተርጎሞ የተወሰደ
/channel/sultan_54
ባሳለፍነው የረመዳን ወር በሳዑዲ ዐረቢያ የሁለቱ ሐረም መስጆዶች (ካዕባ እና መዲና መስጂድ) ጎብኚዎች ቁጥር 122 ሚሊዮን እንደሚልቅ አል ዐረቢያ የዜና ቻናል አስታውቋል።
Читать полностью…ኢማም ኢብኑ አል_ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ባሪያው ኃጢኣትን በታዛኝነት(በምትክ) ሲቀይር፣ አላህ በእርሱ ላይ የነበረውን ቅጣት በደኅንነት፣ ውርደትንም በክብር ይቀይራል።»
📚(አድ ዳእ ወደ_ደዋእ፣ ገጽ 73)
ተክቢራ
በቃሪእ ሰዕድ አልጋሚዲይ ድምፅ
احيوا سنة التكبيــــــــــر
وذكــــــــــروا بها
الله اكبر ، الله أكبر ، الله أكبر
🍃 لاإله إلا الله 🍃
الله أكبـــــــر ، الله أكبـــــــر
🍃 ولله الحمد 🍃
🌸🍃
/channel/sultan_54
ኢድ ሙባረክ!
ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል
عاجل:
رؤية هلال شوال في تمير..
وغداً الأحد أول أيام عيد الفطر بالسعودية .
🔴 ሰበር ዜና!
የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሻዋል ጨረቃን መመልከትን በተመለከተ ስብሰባ ተጀምሯል!
🌙 ውጤቶችን በቅርብ ጊዜ እንደምናሳውቅ በአላህ ፈቃድ እንጠብቃለን።
🔴 ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች ለማግኘት ይከተሉን።
👉 [ቴሌግራም ቻናላችን](/channel/sultan_54)
አንዳንድ ቻናሎች "ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ብሩኒ፣ ባንግላዲሽ እና ማሌዥያ ኢድ ሰኞ እንደሚከበር አስታውቀዋል" የሚል ዜና አሰራጭተዋል።
ነገር ግን ይህ ውሸት ነው! በእነዚህ ሀገራት ዛሬ ቅዳሜ ረመዳን 28 ቀን ነው፤ ይህ ማለት ነገ እሁድ የሻዋል ጨረቃ ማየት ይካሄዳል፣ ከዚያም የኢድ በዓል በይፋ ይገለጻል።
በውጤቱ፣ ኢድ ሰኞ እንደሚከበር ይጠበቃል።
🔴 ለእውነተኛ ዜና በቴሌግራም ይከተሉን፡
[/channel/sultan_54](/channel/sultan_54)
🔖"…ሸዋል ስምንተኛው ቀን የአብራሮችም(የጥሩዎች) ሆነ የፋጂሮች(የጠማማዎች) በዓል አይደለም።ይህንኑ ቀን በዓል ነው ብሎ ማንም ሊያስበው አይገባም። ከዲን መገለጫዎች አንዱንም ቢሆን በዚሁ ቀን መተግበር አይገባም።"
📚【ኢኽቲያራት አልፊቂሂያ ሊኢብኑ ተይሚያ ገፅ :199】
/channel/sultan_54
«ሱን'ና ብቸኛው መዳኛ‼» (السنة سفينة النوح) በሚል ርዕስ ኡስታዝ ሱልጧን ኸድር ትናንት በአዳማ ከተማ ዑመር መስጅድ ያደረገው መሳጭ ሙሐደራ!
ብታዳምጡትና ለሌሎችም ብታሰራጩት መልካም ነው። በጣም ደስ የሚል ሙሐደራ ነበር።
ነሲሓ የዒልም ቅፍለት: ቁጥር ④
||
t.me/MuradTadesse
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
الحفاظ على الحسنات
❗️መልካም ስራችን እንዳይበላሽ
🕌 ጎተራ ሼል ዲፖ (54) ፈትሕ መስጂድ
🗓 ሸዋል 6/1446 አ/ሂ
http://t.me/sultan_54
{አላህ ከዚያ በኋላ(ከፍቺ በኋላ) አዲስና የማይታወቅ ነገር ሊከስት ይችላል…}😍❤️
( ሱረቱ አጥ_ጠላቅ:1)
ሰው በእጅጉ በተጨነቀ ጊዜ ከእርሱ መውጫ የለም ብሎ ያስባል። ነገር ግን አላህ ከሱ ምህረቱን( ፈረጃውን) ያመጣል። እንደ "ሃጀር" በሠፏ እና መርዋ መካከል ጥቂት ውሃን ለማግኘት ብላ እዚህም እዚያም ተጨንቃ በሀይል የምትሮጥ ሴት ልጅዋ ኢስማዒል እግር ሥር የዘምዘም ውሃ እንደሚፈነዳ ማን ያስብ ነበር? ይህ ውሃ ለእርሷና ለልጇ ብቻ ሳይሆን እስከ ቂያማ እለት ድረስ የሚመጡ ሕዝቦች የሚጠጡት።
እንደዚሁ አላህ ሁኔታዎች በአንድ የዓይን ብሌን ብልጭታ ነገሮችን ሊቀያይር ይችላል። ችግር ረጅም ጊዜ አይቆይም።
ኢብኑ ቀዪም እንደተናገሩት፡ “ሁላችንም ከባድ የመከራ ጊዜዎችን አሳልፈናል። እነሱም ዛሬ ላይ ተረስተው ትውስታ ብቻ ሆነው ቀርተዋል።”
ስለዚህም ተስፋ አትቁረጥ፤ በጌታህ ላይ ተማመን። ችግር ያልፋል ብሎ በትአግስት መጠበቅ ላቅ ካሉ ዒባዳዎች አንዱ ነውና።
📕- አድሃም ሸርቃዊ || ረሳኢሉን ሚነል ቁርኣን 🤍🤍
ጥያቄ፦
አልሀምዱሊላህ ረመዳንን በጥሩ ነበር ያላለፍኩት በተለይ የመጨረሻ 10 ቀኖችን አሁን ግን ከኢድ ቡሆላ በጣም ደካማ ሆንኩኝ፣ እንቅልፍ ብቻ ሆኑኩ፣ ከረመዳን ቡሗላ ረመዳን የነበረውን ተነሳሽነት ያላስቀጠለ፣ ከዒባዳው ዝንጉ የሆነ ረመዳኑ ተቀባይነት እንዳላገኘ ያሳያል፣የሚባል ነገር ሰምቼ ነበር ምን ማድረግ አለብኝ?
መልስ፦
ማንኛውም ሰው በዒባዳው ከጥረት እና ከተነሳሽነት በኋላ ድክመት እና መዘናጋት ቢያጋጥመው ተፈጥሮኣዊ ነው።
ልክ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት፣ *"ከማንኛውም የዒባዳ ጥረት እና ተነሳሽነት ጋር የሚገናኝ ዝንጉነት እና ድክመት አለ፤ ከማንኛውም ከፍተኛ ተነሳሽነት በኋላ ድክመት (ፊትራ) ይከተላል። የትኛውም ሰው ጥንካሬው ወደ ሱናዬ ከሆነ፣ እርሱ ፀንቷል(ድኗል)፤ የትኛውም ሰው ግን ከፍተኛ ተነሳሽነቱ ወደ ሌላ ከሆነ፣ እርሱ ጠፍቷል(ለጥፋት ተዳርጓል)"* (ኢማሙ አሕመድ ዘግበውታል)። ግን አንድ ሰው በጣም መጠንቀቅ ያለበት ድክመቱ ወደ ግዴታዎች መተው እና ቸልተኛ፣ ነፍሱን በኃጢኣት በማርከስ፣ መጥፎ ነገሮችን ማድረግ አይገባውም።
ኢብኑ አልቀዪም ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦ *"በዒባዳ ለሚተጉ ሰዎች (አስ_ሳሊኪን) ከዒባዳ በኃላ የድክመት ጊዜያት የማይቀር ነው። የትኛውም ሰው ድክመቱ ወደ አላህ ቅርብ ለመሆን(ሚዛናዊነት) እና ሥራውን ለማስተካከል ከተመራ፣ ከግዴታ (ፈርድ) አስካልወጣ፣ ወደ እርም (ሐራም) አስካልገባ፣ ከቀድሞው ሁኔታው የተሻለ ሆኖ መመለሱ የሚጠበቅ ነው።"*
ዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ *"ነፍስ መንፈሳዊ ጥንካሬ ላይ ሆና ወደ አላህ መቃረብ (ዒባዳ የሚገራላት) ጊዜ አላት፣ በአንፃሩም ከከፍተኛ ተነሳሽነት በኃላ ወደኃላ መጎተት ( መሳነፍ) ጊዜ አላት። በተነሳሽነቷ(በነሻጧዋ) ጊዜ፣ በቆራጥነት በተጨማሪ ዒባዳ ያዛት፤ በመዳከሟ ጊዜም፣ በግዴታዎች (ፈርዶች) እና በዋጅባት ሥራዎች ላይ ብቻ ገድባት።"*
አንድ ሙስሊም በነፍሱ ውስጥ መዳከም (ፉቱር) ወይም መሳነፍ ሲሰማው፣ ለነፍሲያው በመታዘዝ ዒባዳውን ሊያቋርጥ አይገባም። ይልቁንም በጥበብ እንዲሁ ራሱን ሊያከም ይገባዋል፤ ሐላል የሆኑ መዝናኛ ጨዋታዎች በመጠቀም ነፍሱን ሊያድስ ይገባል፤ ነገር ግን ዒባዳውን ሙሉ በሙሉ እንዳያቋርጥ ጥንቃቄ ያሻል። በተጨማሪም ሚዛን (ሚዛናዊነት) መጠበቅ አለበት፤ ይህም ሆኖ፣
1. አንድ ሙስሊም ነፍሱን በግድ በትእዛዝ ላይ በመጫን ዒባዳ እንድትጠላ እንዳያደርጋት።
2. የነፍሱንም ልጓም ፈቶ ሲያበቃ፣ በመዝናኛ እና በኃጢአት ባሕር ውስጥ ያለ ምንም ቁጥጥር እንዳትዋኝ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።
ያም ሆነ ይህ እምነታዊ ጉዞ ላይ ያለ ሰው በድክመት ወቅቱ በፅናት ከነፍሱ ጋር ሊታገል ይገባል፣ በጥበብ እና በሚዛን መርህ መንገዱን እንዲቀጥል የሚያስችል እርምጃ መውሰድ አለበት ። በአንፃሩም፣ ከግዴታዎች መዘንጋት ወይም ወደ ኃጢአት ውስጥ መዋኘት እንዳይከሰት ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው።
በማንኛውም ነገር ላይ በሚዛናዊነት ላይ አደራ!ካሰቡበት ግብ መድረስዎ አይቀርም።
/channel/sultan_54
ረመዳን ጓዙን ጠቅልሎ ከኛ ቢሸሽም**
የቁርኣን ገጾችን አትዝጉ፤
እርሱ ሕይወት ነው፣ ያለርሱ እንዴት እንተነፍሳለን? !
እርሱ ጓደኛችን፣ የሐዘን መድሃኒትም ነው!
ወዳጄ ሆይ!
በእያንዳንዱ ፍቅረኛሞች መካከል አንድ ክር አለ፤
እውነተኛ አፍቃሪያን በመሀከላቸው አለመግባበት ሲከሰት፣ ክራቸው ይበልጥ፣
ከፍ ብሎ ይጠነከራል!
አንዳንድ አፍቃሪያን ደግሞ ሳይግባቡ ሲቀር፣ ክራቸውን ይቆርጣሉ፣
ዳግም ይመጡና የቆረጡትን ክር ይቀጥላሉ፣
እንግዲህ በተጨቃጨቁ፣ በመሀከላቸው አለመግባባት በተፈጠረ ቁጥር ክራቸው ተበጥሶ ዳግም እንዳይቋጠር ጥንቃቄ ያደርጋሉ!
አንዴ ብቻ የተቋጠረ ረጅም ክር!
ወዳጄ ሆይ!
የፍቅር ቃላት በሰላም ጊዜ ውብ ናቸው፣
ነገር ግን በጥል ጊዜ የበለጠ ድንቅ ናቸው!
ልቦችን ፈታ ማድረግ በሰላም ሰዓት ጣፋጭ ነው፣
ነገር ግን በቁጣ ሰዓት የበለጠ ጣፋጭ ነው!
የጥንት አረቦች እንዲህ ይላሉ፦
*"በቁጣ ጊዜ አስከፍተሀው ግን አንተን የማይጎዳህ( የማይበቀልህ!) ከሆነ፣ እስከ ወዲያኛው ወዳጅ አድርገህ ያዘው! *"
እኔም አክልሃለሁ፡ ቅርብ ወዳጅህ፣አለኝታህ፣ ደጋፊህ አድርገው!
ሰላም ለልብህ ይሁን!
"አሰላሙ ዐለይከ ያ ሷሒቢ"
ከሚለው መፅሐፍ ወደ አማረኛ ተተርጎሞ የተወሰደ
📚📖📚📖📚📖📚📖
/channel/sultan_54
በቃ! በረመዳን ስንቀራው የነበረውን
ቁርኣን አቆምነው ማለት ነው?!
😭😭😭
الشيخ: احمد طالب
ማራኪ ድምፅ
ሸይኽ አሕመድ ጧሊብ
የመዲናው ቡልቡል!
🔴 እጅግ ማራኪ ቲላዋ
ሸይኽ ሙሐመድ አዩብ
ሱረቱ አል አዕራፍ
1430 በልዩ ድምፅ ያቀረቡት
عيد كم مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الامال
ዒዳችሁ የተባረከ ይሁን አሏህ ከናንተም ከኛም መልካ ስራችንን ይቀበለን ወድማችሁ sultan khedir
🔴ዒድ ሙባረክ!
#ትሜር ላይ የረመዳን ጨረቃ ታይቷል። በዚህም መሰረት ነገ እሑድ የዒድ አል ፊጥር የመጀመሪያው ቀን ይሆናል።
ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋዊ መግለጫ በመጠበቅ ላይ …
አላህ መልካም ስራን ይፃፍልን
🔴ሰበር ዜና!
በሁሉም የኦማን አካባቢዎች የ1446 ሸዋል ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ እሁድ የረመዳን ማሟያ 30ኛ ቀን ሲሆን ዒድ አልፊጥር ሰኞ እንደሆነ ተገልፇል።
ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋዊ መግለጫ በመጠበቅ ላይ …
/channel/sultan_54
🔴 በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በ"ስደይር" ከተማ #ሸዋል ጨረቃን ለማየት ቅጽበታዊ ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ እና ደመና ሁኔታ ተፈጥሯል! 🌩️
📡 ዜናውን የሰጠው #አል_አረብያ_ቻናል (Al Arabiya). ነው።
ዒዱ የሚታወቀው ፀሀይ ከገባች ቡሃላ 12:15 ሰአት ላይ ነው በትዕግስት እንጠብቃለን።
Читать полностью…