sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14577

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ሷሊሖች (ጻድቃን) ኃጢአት የሌላቸው ናቸው ብለህ ታስባለህን?! 
እነሱ ግን ኃጢአታቸው ድብቅ ነው በግልጽ/በአደባባይ አያደረጉትም፣ 
ምህረት ጠይቀዋል፣ ኃጢአታቸውን (ስህተታቸውን) ለመሸፈን ወይም ለማጽደቅ አልሞከሩም፣ኃጢአት ( ስህተታቸውን) አምነው ተቀብለዋል፣ 
ከመጥፎም ስራ በኋላ መልካምን ሠርተዋል።»
✍ኢብኑል ቀዪም

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኩኑዝ... የማንነት እነፃ

ልዩና ወቅታዊ የሙሀደራ መድረክ

هَـٰذَا بَیَانࣱ لِّلنَّاسِ وَهُدࣰى وَمَوۡعِظَةࣱ لِّلۡمُتَّقِینَ

በአላህ ፈቃድ እሁድ ግንቦት 17/2017  ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እንደ አዲስ በተገነባው ኡስማን ኢብኑ ዓፋን (ሸህ ደሊል) መስጂድ ልዩ የሙሀደራ ዝግጅት ይካሄዳል።

🔉የቀናቶች ንጉስ

በኡስታዝ መሐመድ ሀሰን ማሜ


እና


🔉 ብዥታና እውነታ

በአቡጁነይድ ሳላህ አህመድ


«አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ኡመታቸውን ሽንት ቤት ገብቶ ስለመጸዳዳት (ኢስቲንጃእን) አስተምረው ስለ አላህ ጌትነት፣ብቸኛ ተመላኪነት እና ባህሪያቱ (ተውሒድን) አላስተማሩም ብሎ ማሰብ ዘበት  ነው።"
ኢማም ማሊክ


قال الإمام مالك رحمه الله : (محال أن يظن بالنبي - صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -، أنه علَّم أمته الاستنجاء ولم يعلمهم التوحيد) .

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ስለ አላህ መገለጫ ባህሪያት በተነገረ ቁጥር ከፍጡራን ጋር የማመሳሰል አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎችን በተመለከተ የተሰጠ ድንቅ ምሳሌ!!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የሀዲሱ ትርጉም በአማርኛ፡** 
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"አምላካችን (በትንሣኤ ቀን) ባቱን(ሳቁን) ገልጠ ያሳያል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ  ወንድና ሴት አማኝ ይስገድለታል። ነገር ግን ዱንያ ላይ ሳለ ለይዩልኝ እና ለይስሙልኝ የሚሰግዱት ሰዎች ለመስገድ ሲሞክሩ ጀርባቸው እንደ አንድ ጠፍጣፋ ትሪ( መገጣጠሚያ የለሌው) ይሆናል። (በዚህ ሁኔታ) መስገድ አይችሉም።" 

ቡኻሪ ዘግበውታል።

ማስታወሻ፡** የአላህ ባሕርያት በተመለከተ  (እንደ "እግር" "ባት" ያሉ መግለጫዎች) እንደ አህሉ ሱናህ አረዳድ ትርጉማቸውን ሳናቆለምም፣ሳናዛባ፣ ከፍጡራን ባሕርያት  ጋር ሳናመሳስል መቀበል ግድ ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ውድ ወንድምና እህቶቼ በዚህ በተከበረ ቀን አንድ መልካም ስራ ልጠቁማችሁ!

ከ አሁን በፊት ስለ እሷ በፖስትም ዘይነባ እደሻው ትባላለች።የልጆች እናት ናት፣ ባሏ በድንገት በታመመበት እና በከባድ የገንዘብ ችግር ውስጥ በወደቀችበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ለስራ ብለው የተበደሩትን ብር መክፈል ባለመቻላቸው ትልቅ ሰላም እጦት ውስጥ ትገኛለች። ከዚህ ቀደም ጥሩ ገቢ የነበራት ቢሆንም፣ አሁን ግን የንግድ ሥራዋ በመክሰሩ ከፍተኛ እዳ ውስጥ ገብታለች። ባሏም እዳውን ለመክፈል ሲሞክር በድንገት ታምሞ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል።

ይህችን እህታችንን በምንችለው ሁሉ እንርዳ!

ለአላህ ብለን እንድረስላት! ሙእሚን መልካም ነገርን ከማድረግ አይሰለችም፣ እስከ ጀነት ድረስ።
የባንክ አካውንት: 1000449572557 (ዘይነባ እደሻው)―ደረሰኙን ከቻላችሁ በውስጥ ላኩላት!―
ስልክ: 0908509393
ደውለን እናፅናናት፣ አብሽሪ እንበላት!

ዘይነባ ስላጋጠማት ችግር በዝርዝር ለመስማት ይህንን የድምፅ መልዕክት በዚህ ሊንክ ገብተው ያዳምጡ፦
/channel/Eznetttt/442

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة
نعمة العافية
✨የ ዓፊያ ዋጋ

🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ዙልቂእዳ 12/1446 አ/ሂ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ولو كانت الدنيا تدوم لأهلها ..... لكان رسول الله حيا وباقيا


/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ነሲሓ ሪሳላ :

🔖 ሸይኽ ሙሀመድ ዓሊ አደም አል’ ኢትዮቢ ( ረህመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ :

" በዚህ ፈትና በበዛበት ዘመን እራሱን ተቆጣጥሮ እውቀትን ለመፈለግ የሚጥር (ወጣት) ከአላህ ወልዮች ይቆጠራል ። "

  [📚ፈዋኢድ አል‘ኢልሚያህ
ወዱረሩ ተርበውያ ገፅ–19 ]



🗓 ሀሙስ 30 , 2017
🗓  ዙልቂዕዳ 10 , 1446 ሒ

============

ነሲሓ ቲቪ
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!

📡 Nilesat  /11545 / V / 27500

@nesihatv

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ማለዳዎን በዚህ በሚማርክ ቲላዋ ይጀምሩና ቀንዎን ያስውቡ!

تلاوة عاطرة للشيخ علي جابر رحمه الله

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
( عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي ...)
”አደራችሁን ሱናዬን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ከእኔም በኋላ የተመሩ 
እና የተቃኑ ምትኮቼ ሱናንም አጥብቃችሁ ያዙ፡፡

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

الشيخ علي جابر رحمه الله

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ከታዋቂ የአገር ሽማግሌዎችና ምሁራን አንዱ የነበሩት ሀጂ ደርባቸው መሐመድ ዛሬ ከጁምዓ ሰላት በፊት ወደ አኼራ ሄደዋል።
አላህ ይዘንላቸው፤ ስራቸውን ይቀበላቸው ወንጀላቸውንም ይማራቸው። የቀብር ስነስርዓቱ በአላህ ፈቃድ ዛሬ አስር ላይ በኮልፌ መካነ መቃብር የሚፈፀም ይሆናል።

አል ዓፊያ አ/ማ የቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ልጃቸው ሸይኽ አዩብ ደርባቸው፣ ለመላው ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።

ረሒመሁላሁ ረህመተን ዋሲዓህ


وفاة الحاج درباتشو محمد والد استاذ أيوب رحمه الله اليوم قبل الجمعة والدفن وقت العصر إن شاء الله.

رحمه الله رحمة واسعة
إنا لله وإنا اليه راجعون

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ቃዲ ሹረይህ እንዲህ ይላሉ፦፡- 
«ፊትናዎች በመጡ ጊዜ አትጠይቁ፣ አታውሩም!»
ምንጭ፦ _ሲያር አዕላም ነብላእ
ማለትም ስለእርሷ መረጃ አትጠይቁ፤ ስለ ፊትናው መረጃ  ካላችሁም ለማንም አትንገሩ፣ ፊትናውን በማራገብ ወይም በማስፋፋትም አትሳተፉ።
በዚህ ዘመን ይህ ምክር ምንኛ  አስፈላጊ ነው!?
አሏህ ሆይ ከይፋም ሆነ ከተደበቀውም! ከክፉ ፊትናዎች  ጠብቀን።

በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ይህ ምክር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ያልተረጋገጠ መረጃ ማራመድ ህብረተሰቡን ሊያደናግር ብሎም ግዜውን ያላግባብ ሊያባክን  ስለሚችል፣ ይህን የሰለፎችን ንግግር ከግምት ማስገባት አስፈላጊ ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢስላማዊ የልጆች አስተዳደግ ዋና ዋና መርሆች** 

ኢስላም ለልጆች አስተዳደግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ሃይማኖት ነው። በቁርአን እና በሐዲስ መሠረት፣ ልጆችን በአላህ ፍራቻ፣ በአኽላቅ፣ እና በጥበብ ማዳበር ይገባል። ከኢስላማዊ ተርቢያ ዋናዎቹ መርሆች መካከል፦ 

### 1.ስለ ተውሒድ (አላህን ብቻ መገዛት) ማስተማር 
- በመጀመሪያ ልጆችን ስለ አላህ  ብቸኛ ተመላኪነት (ተውሒድ) አስተምሩ። 
  - "ልጅህ  አፍ መፍታት ሲጀምር ለእሱ 'ላ ኢላሀ ኢላ አላህ' (ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም) የሚለውን ቃል ደጋግመህ አሰተምር።"
- በተፈጥሮ ውስጥ የአላህን ምህረት፣ እና በፍጥረታት ውስጥ የአላህን  መነሩን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ያሳዩኣቸው። 

### 2. የነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ምሳሌ መከተል 
- ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ለልጆች የሚያሳዩትን ፍቅር፣ ርኅሩኅነት እና ትምህርት ይከተሉ። 

### 3. የስነ ምግባር እሴቶችን ማስተማር 
- እውነትን መናገር፣ አክብሮት፣ ምሕረት፣ እና ፍትሕ እንዲያውቁ ያድርጉ። 
  - "እውነትን ተናገሩ፣ ምንም እንኳን ከራስዎ ጋር ቢሆንም።" (ቡኻሪ ሀዲስ) 
- ሀራም ነገሮችን እና ድንጋጌዎችን (ሀላል እና ሀራም) አስረዱኣቸው። 

---

### 4. የሰላት እና የቁርአን ትምህርት 
- ልጆችን ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሰላት፣ ዚክር፣ እና ቁርአን አስተምሩኣቸው። 
  - "ልጆቻችሁን ሰላትን በሰባት ዓመት ያስተምሩ።" (ሀዲስ) 
- ቁርአንን በማንበብ እና ትርጉሙን በማወቅ እንዲያድጉ ያግዙኣቸው። 
### 5. ፍቅር እና ቅጣት መለያየት 
- ፍቅርን አሳዩ፣ ነገር ግን ስህተት ሲፈፅሙ በጥበብ የሚማሩባቸው ቅጣት ይስጡ። 
---

### 6. የቤተሰብ ግንኙነትን ማጠናከር 
- ከልጆች ጋር ጊዜ ያሳልፉ፣ የታላለቅ ስብእናዎችን ታሪኮችን ይንገሯቸው፣  በቤተሰብ ውስጥ የሰላም አካባቢ ይፍጠሩ። 
  - "እናንተ አማኞች ሆይ! ነፍሶቻችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት አድኑ።" (አትሕሪም:6) 

### 7. ኢስላማዊ ትምህርት በጥበብ ማዳበር
- ልጆችን በሥነ-ምግባራዊ ትምህርት ያንፁ።
  - "ዕውቀትን መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።" (ሀዲስ) 

### 8. የልጅን መብት ማክበር 
- ልጆች የሚገባቸውን **ፍትሕ፣ አክብሮት፣ይስጡ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«በብዙ ልፋት የተገነባን ወንድማማችነት በሆነ አላፊ ክስተት ምክንያት እንዳልነበር አድርጋችሁ አታውድሙ!»

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ (ሀፊዘሁላህ)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አል-በይሀቂ አቡ በክር አል-አሽዕሪ እንዲህ ብለዋል፡-

**ኢማም ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል፡-

የሚከተለው የቁርኣን አንቀፅ
«{مَنْ فِي السَّمَاءِ}» («በሰማይ ያለው») የሚለውን ትርጉሙ፡- 
«ከሰማይ በላይ፣ ከዐርሽ ላይ ያለ ነው»
እሱም ፦ «{الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى}» («አል-ራህማን በዐርሽ ላይ ሆነ።») የሚለው አንቀፅ ያስረዳል። 

ማንኛውም ከፍ ያለ ነገር «ሰማይ» ይባላል። ዐርሸም ከሁሉም ሰማያት በላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ከዐርሽ ላይ ከፍ ያለ ሲሆኑ «እንዴት» ወይም «አኳሃኑ» ሳይጠየቅ (بلا كيف) እንደሆነ ተገልጿል። 

(መናቂብ አሽ–ሻፊዒ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 398)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

‏قال قتادة رحمه الله:‏
والله،،لقد عَظَّمَ اللهُ حرمة‏
المؤمن،،حتى نهاك أن‏
‏تظن بأخيك إلا خيراً‏
(التوبيخ والتنبيه/٢٢٩)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ማለዳዎን በዚህ በሚማርክ ቲላዋ ይጀምሩና ቀንዎን ያስውቡ!

تلاوة عاطرة للشيخ علي حذيفي حفظه الله

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አል-ኢማም አሕመድ (241 ዓ.ሂ) እንዲህ ብለው ነበር፦
..وَلَا نُزِيلُ عَنْهُ صِفَةً مِنْ صِفَاتِهِ لشَنَاعَةٍ شُنِّعَتْ..
=› «የሚፀየፍ ተፀይፎ ስላወገዘ (ብለን) ከባህሪያቱ አንዱንም አናስወግድም!»
[ኢብኑ በጥ-ጠህ - “አል-ኢባና” ጥራዝ 3 ገፅ 326፣ ኢብኑ ቁዳማህ - “ዘም-ሙ’ት-ተእዊል” ገፅ 22]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
🌹《አንድ ሙስሊም ከወንድሙ የሚደርሰውን ወሬ በመልካም መተረጎም እየቻለ በመጥፎ ጥርጣሬ ሊያስተናግደው አይገባም።》
📚{አልአዳቡ አሸርዒያህ
ሊቢኒል ሙፍሊሕ 2/47}
#ሑስኑ_ዘን_በወንድሞች_መካከል_ቢሰፍን_ኖሮ_በርካታ_አለመግባባቶች_በከሰሙ_ነበር

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።»

ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

تلاوة خاشعة من سورة مريم

#بندر_بليلة

#اكسبلور #

اجر_لي_ولكم

#تلاوة_خاشعة

quran#

#سبحان_الله_وبحمده_سبحان_الله_العظيم

#سبحان_الله_وبحمده_سبحان_الله_العظيم

#اللهم_صل_وسلم_على_نبينا_محمد

#تلاوة_حجازية

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሀሰን ታጁ እና የኸዋሪጆች መመሳሰል!
ሐሰን ታጁ ሰሞኑን የምርጫ ግዜ ስለተቃረበ፣ በመጅሊስና አመራሮች ላይ ከባድ የማጠልሸት ዘመቻ እና ቅስቀሳ አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
እስከ ደሴው የአንድነት እና ሰደቃ ፕሮግራም ላይ አሁን ወሃቢያ እያለ ከሚዘልፋቸው እና ከሚቀጥፍባቸው ሰዎች ጋር ትግሉን ደግፎ ተሳትፎ ሲያደርግ ነበር፣ ይሁንና የኋላ ኋላ መታሰር ስላልፈለገ የወያኔ ተልእኮ ተሰጥቶት መንግስትን ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ሽማግሌ፣አስታራቂ በመመስል ከአቋማቸው እንዲመለሱ ሲወተውታቸው ስላልተቀበሉት፣ በመጅሊስ የስልጣን እርከን ላይ ስላልተሳተፈ በእልህ ከአሕባሽ ጋር ተደምሯል።
ምን ስለከሉት?!
ዲኑን በነፃነት እንዲያረምድ እንቅፋት አልሆኑበት፣ እንደልቡ ሲዛለፍና ሲቀጥፍ አልከሰሱት አላሳሰሩት፣ ይህን ያህል ጥላቻ የሚሰብከው ለምን ይሆን?

ከኸዋሪጆች አንዱ ወደ ሐሰን አል-በስሪይ መጥቶ፣ እንዲህ አላቸው፦
“በኸዋሪጆች ላይ ምን ይላሉ?” 
ሐሰን አል በስሪይም፦“እነሱ የዱንያ ሰዎች(ጥቅመኞች) ናቸው።”  በማለት መለሱ።
ሰውየውም፝ “ይህን ከየት አምጥተው ሊናገሩ ቻሉ? ከእነሱ ውስጥ አንድ ሰው ጦሩ (መሳሪያ ታጥቀው)እስኪስከበረ ድረስ ይጓዛል፣ ከቤተሰቡና ከልጆቹም ተለይቶ ለጂሃድ ይዘምታል!” 
ሐሰን አል በስሪይም ፦"እስኪ ንገረኝ አሚርህ ሶላት፣ ዘካ፣ ሐጅ ወይም ዑምራ እንዳትሠራ ይከለክልሃልን?” 
ሰውየው አለ፡ “አይ አይከለክለኝም።”  በማለት መለሰ።
ሐሰን  አልበስሪይም ፣ እርሱ (የምትዋጋው) ለዓለማዊ ጥቅም ብለህ አንተ በርሱ ላይ አመፅ የምታነሳሳወ።” በማለት መለሱለት።

📚البصائر والذخائر، لأبي حيان التوحيدي ت 400ه‍)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ጀግንነት ሁል ጊዜ በመናገር አይደለም፣ ጥበብም ሁል ጊዜ በዝምታ ውስጥ አይደለችም። አላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ ከጅለው በዒልም ለሚናገሩ እና በጥበብ ዝም የሚሉ ሁሉ የአላህ እዝነት በነርሱ ላይ ይሁን።
✍አሸይኽ ሱለይማን አር–ሩሓይሊ ሐፊዘሁላህ
ከቲውተር ገፃቸው የተወሰደ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

الشيخ عبد الودود مقبول حنيف

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

أبو بكر الشاطري
نبرة مع الخشوع

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"የመልክተኞቹ አለቃ  የሆኑት ሰይዲ ጥሪያቸው ከቁረይሽ፣ ከአይሁድ፣ ከክርስቲያኖች እና ከመናፍቃን "አዛ" (ጥቃት) አላመለጠም። ታዲያ ... የአሕሉ አስ–ሱናህ (የሰለፎች) ጥሪ ከጥቃት ነጻ እንዲሆን ትፈልጋላችሁን?!
በሱና (በነቢዩ
መንገድ) ላይ ጸኑ፤ ትዕግስትም አድርጉ።" 
አሽ–ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ  ዑመር ባዝሞል

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ፈተናዎች(ችግሮች) የሚቆዩት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፤ የሰው ልጆች ዕድሜ እንደሚጠናቀቅ ይጠናቀቃሉ።»
ስለዚህ በታጋሽነት ወደ አላህ ተጠጋ! 🌟

ኢብኑል ቀዪም /መዳሪጅ አስ–ሳሊኪን (374)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

تلاوة صباحية
بندر بليلة

Читать полностью…
Subscribe to a channel