14074
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
« ረመዳን ውስጥ በየፊጥሩ አላህ ከእሳት ነጃ የሚያወጣቸው ሰዎች አሉ። ይኸውም በየለሊቱ ነው።»
አላህ ከነሱ ያድርገን!
اللهم اجعلنا من عتقائك من النار، وأدخلنا برحمتك في عبادك الصالحين، واغفر لنا ذنوبنا، وتقبل أعمالنا، وزدنا من فضلك وكرمك، يا أرحم الراحمين.
በዚህ በፈተና ጊዜ ዱዓ ላይ እንበራታ!
ሸይኽ አል-ኢስላም ኢብን ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦
"ንጹሕ ልቦች እና መልካም ዱዓዎች የማይሸነፍ ሠራዊት እና የማይከሽፍ ሰራዊቶች ናቸው።"
📚 አል ፈታዋ፤ (28/644)
🕌 አዲስ ሙሓደራ
محاسبة النفس
💠 ነፍስን መገምገም!
⏰ ዛሬ ቅዳሜ ረመዷን 11/1447 አ/ሂ
ከዝሁር በኋላ
🕌 ቃሊቲ ገላን ኮንዶሚኒየም ሀምዛ ቁ/3
መስጂድ የተደረገ ሙሃደራ
/channel/sultan_54
اللهم بردآ وسلامآ على أهلنا في غزة
اللهم أستر عوراتهم وأمن روعاتهم
اللهم فرج كربهم وأرحم ضعفهم وأكتب لهم النصر والتمكين يارب العالمين
حسبنا الله ونعم الوكيل نعم المولى ونعم النصير🇵🇸
إنَّ الله إذا أراد بعبد خيرا سلب رؤية أعماله الحسنة من قلبه والإخبار بها من لسانه و شغله برؤية ذنبه
ابن القيم رحمه الله
ሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን የሳዑዲ ሙፈቲ ለ1447 አ/ሂ ረመዳን የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል።
Читать полностью…
🔴 ሰበር ዜና
#ሳውዲ_አረቢያ
የረመዳን 1447 ዓ/ሂ ጨረቃ መታየቷን አስታወቀች። ስለዚህ ነገ #ረቡዕ የተባረከው #የረመዳን_ወር የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።
🔴 አዳዲስ መረጃዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ በቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉን።
#ለሁሉም_ሙስሊም_ማህበረሰብ_ረመዷን_ሙባረክ
ማለት እንወዳለን።
/channel/sultan_54
🔴 በሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የሸሪዓ ፍርድ ቤት እና በሁሉም ኢስላማዊ አገሮች የሚገኙ የረመዳን ጨረቃ መታየትን ለማረጋገጥ ተዘጋጅተዋል፣ የጨረቃ ምልከታ ማዕከላት ውጤቱ ይፋ እስኪሆን በጉጉት እየተጠበቀ ነው...
.
🔴አዳዲስ መረጃዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ ይከታተሉን።
/channel/sultan_54
🌟 የጾም ፊቅህ ኮርስ 🌟
ክፍል ሦስት፦:
📌 በረመዳን ውስጥ የጉዞ ሕግጋት
📌 በረመዳን ውስጥ ማፍጠር የሚያስፈቅድ ጉዞ መጠን፦
🍀 አብዛኛዎቹ ዑለማዎች እንደሚሉት አንድ ሰው ማፍጠር የሚፈቅድለት ርቀት በግምት ሰማኒያ ኪሎ ሜትር ነው።
🍀 አንዳንድ ሊቃውንት ደግሞ ጉዞ በተወሰነ ርቀት እንደማይገደብ ተነግረዋል፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ማመሳከሪያው የሰዎች ልምድ(ዑርፍ) ነው፣ ሰዎች በተለምዶ ጉዞ ብለው የሚቆጥሩት ማንኛውም ነገር በረመዳን ውስጥ ማፍጠርን የሚያስፈፈቅድ ጉዞ ነው።
📌 ሙሳፊር የሆነ ሰው ሕግጋት በረመዳን:
🍀 1- በሰውዬው ላይ ማፍጠር እና ጾም እኩል ከሆነ፣ ማለትም ጉዞ ለአንድ ሰው ምንም ልዩነት የሌለው ወይም ችግር የማይፈጥርበት ወይም ላይጎዳው ከሆነ፣ ጾም ከርሱ የተሻለ ነው።
🍀 2- ጉዞው ሰውየው ላይ መጾም ከባድ ከሆነ፣ ማፍጠሩ የተሻለ ነው።
🍀 3- መጾሙ ከባድ ችግር አደጋ ካስከተለ፣ ጾም ሐራም ይሆናል።
🍁 - አንድ ሰው በቀኑ ውስጥ ማፍጠር በሸሪዓው የሚያስፈቅድ ጉዞ ቢያደርግ፣ ከመንደሩ ወይም ከከተማው ወይም ከሀገሩ ከወጣ በኋላ ማፍጠር ይችላል።
🍁 - በጉዞ ምክንያት አፍጥሮ ወደ ሀገሩ ቢመለስ፣ በዚያን ቀን ከምግብ እና ከመጠጥ መታቀብ አይጠበቅበትም፣ ነገር ግን ከረመዳን በኋላ ቀዳ ማውጣት አለበት።
🌟 የጾም ፊቅህ ኮርስ 🌟
የመጀመሪያው ትምህርት:
📌 ጾም ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች እና ማፍጠር የሚፈቀድላቸው ሰዎች ማናቸው?
📌 ጾም ማለት በሸሪዓዊ ፍቺው፦ ለአላህ ብሎ (አምልኮትን በማሰብ)ከፈጅር (ከጎሕ መቅደድ አንስቶ) ፀሐይ እስክትጠልቅ፤ ከመብላት፣ ከመጠጣት እና ከሌሎች ጾምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች ሁሉ መቆጠብ ማለት ነው።
📌 የረመዳን ጾም የግዴታ ጾም ሲሆን፤ አላህ ባርያዎቹ ላይ ግዴታ ያደረገው ዒባዳ ነው፣ አላህ እንዲህ ይላል፡ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከናንተ በፊት ለነበሩት እንደተጻፈባቸው(ግዴታ እንደሆነ) በናንተም ላይ ጾም ተጻፈ፤(ግዴታ ሆነ) ልትጠነቀቁ(ተቅዋ ታገኙ ዘንድ) ይከጀላልና} [ሱረቱ አል–በቀራህ፣ 183]። ነቢዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ «እስልምና በአምስት ነገሮች ተገንብቷል፡ ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑንና ሙሀመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላት መሰገድ፣ ዘካ መስጠት፣ የአላህን ቤትን መጎብኘት (ሐጅ ማድረግ) እና የረመዳንን ጾም መጾም ነው»። ሶሂህ አልቡኻሪ (8)፣ ሶሂህ ሙስሊም (16)።
📌 መጾም ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች፡-
1. ሙስሊም መሆን።
2. ወንዱለአቅመ አዳም መድረስ፣ ሴቷ ለአቅመ ሄዋን መድረስ።
3. አዕምሮ ጤናማ መሆን(አዕምሮ ህመምተኛ አለመሆን)
4. መጾም መቻል (አዛውንት አለመሆን ፣የወር አበባ ላይ እና የወሊድ ደም ላይ አለመሆን በሽተኛ አለመሆን…)
5. ሙሳፊር (ተጓዥ ያልሆነ)
📌 የረመዳንን ጾም ማፍጠር የተፈቀደላቸው፡-
1. በሽተኛ (ጾሙ ቢከብደበው ወይም ቢጎዳው)።
2. ጉዞ ላይ ያለ (ሙሳፊር)።
3. እርጉዝ እና የምታጠባ ሴት።
4· ወር አበባ ላይ ያለች ሴት።
5. ኒፋስ(የወሊድ ደም) ላይ ያለች ሴት።
📌 በሽተኛ እና ሙሳፊር ማፍጠር የተፈቀደላቸው(ሩኽሳ) ሲሆን በሌላ ጊዜ ማካሻውን መጾም ይገባቸዋል፣ ይሁንና ህመማቸው ፈውስ የለውም ተብሎ የሚታሰብ ከሆነ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ያበላሉ( ፊዳ) አለባቸው።
📌 እርጉዝ እና እየሚያጠቡ ሴቶችን በተመለከተ ለእራሳቸው ሰግተው ካፈጠሩ፣ በሌላ ግዜ ቀዳውን ማውጣት አለባቸው፣ ለጨቅላቸው ወይም ለፅንሱ ጉዳት ሰግተው ካፈጠሩ፣ ቀዳ እና ለእያንዳንዱ ላፈጠሩት ቀናት ሚስኪን ማብላት ይኖርባቸዋል።
🔴 ፊዳ፦ በእህል ግማሽ ቁና ሲሆን በግምት 1·5 ኪ·ግ ይሆናል።
"يا مَن بِدُنياهُ اِشتَغَل، وَغَرَّهُ طولُ الأَمَل
المَوتُ يَأتي بَغتَةً، والقبرُ صندوقُ العَمَل"
"ሙእሚን (አንድ አማኝ) ወዳጁ ወይም ቅርብ ዘመዱ የአላህን ትዕዛዝ ሲፈፅም ከማየት በላይ እርካታ የሚሰጠው ነገር የለም!"
✍ ሐሰነል በስሪይ
አቡል ቃሲም አል–ጁነይድ [ረሒመሁላህ] እንዲህ በማለት ተጠየቁ:‐
«ዐይንን [ከሐራም] ለመስበር በምን እንታገዝ?»
እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ:‐
«የአላህ እይታ አንተ የምታየው ነገርን ከመመልከትህ እንደሚቀድም በማወቅ!»
📚 ሸርሑል‐አርበዒን ፥ ኢብኑ ሪስላን
أدرك صلاة العصر!
الصلاة الوسطى ترفع مقامك، فلا تكن من الغافلين عنها.
ሰላት ዐሥር ላይ ፈጥነህ ድረስ!
"መካከለኛይቱ ሶላት(ሰላት ዐሥር) ደረጃህን ከፍ ታደርጋለች፣ከተዘናጋጊዎቹ አትሁን!"
ኢብን ረጀብ አልሐንበሊ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦
"ኃጢአት ከመሥራት ተጠንቀቁ፣ (ኃጢአት) በምሕረት ወቅቶች መስራት፤ ምሕረትን ያስነፍጋል።"
📚ለጣኢፉ አል መዓሪፍ 295
قال صلى الله عليه وسلم: [العبادة في الهرج كهجرة إلي.]
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
"በሁከት ጊዜ የሚደረግ ዒባዳ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።"
ይህም ማለት በፈተና ፣በጦርነት ሰአት አብዛኛው ሰው በሀሰት ወሬ እና ባልተጣራ ዘገባዎች ተጠምደው አላህን ከመገዛት በሚዘነጉበት፣ ወቅት በትዕግስት አምልኮትን መፈፀም ትልቅ ሽልማት አለው። ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ሰዎች በሐሜትና በውሸት ወሬ ተጠምደው ከአላህ አምልኮት ይዘነጋሉ፣ ከአምልኮትም ይርቃሉ፤ አምልኮትን የሚሠሩ ጥቂት ግለሰቦች ብቻ ናቸው።
💥 [ الموقف من ضرب إسرائيل وأمريكا لإيران ]
💥አንድ ሙስሊም [ እስራኤል እና አሜሪካ ኢራንን በመምታታቸው ረገድ ሊኖረው የሚገባ አቋም ]
አስርቱ የመጀመሪያ የረመዳን ቀናት…
የቀኖች መብራት፣ የሌሊቶች ሙሉ ጨረቃ ነበር፤ አሁን ደግሞ ደህና ሁኑ ፣ እያለ ረመዳን በሐር ልብሶቹ ሊሰናበተን ነው፣ ልቦች ውስጥ የማይጠፋ ሕይወትን፣ ነፍሶች ውስጥ ዳግም መገናኘትን ተስፋ ትቶልን ሊሄድ የማስጠንቀቂያ ደውሉን እየደወለ ይገኛል።
ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ለአንድ ባሪያ በጎን ነገር በሻ ጊዜ፤ መልካም ሥራዎቹን ከልቡ ማየትን ከአንደበቱም መናገርን ያስወግድበታል፤ እንዲሁም ኃጢአቱን በማየት ይጠምደዋል።"
ይህ ድንቅ ንግግር ፅንሰ ሀሳቡ፦
አንድ ሰው በራሱ መልካም ሥራ አለመደሰትንና ኩራትን እንዳይሰማው፣ በኃጢአቱ በመጸጸትና በማስተካከል እንዲጠመድ አላህ እንደሚያደርግ የሚያሳይ የታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀዪም ንግግር ነው።
🌙🌴•تلاوة رمضانية•🌙🌴
الليلة 7 | رمضان 🌙
الجزء السابع من المصحف الشريف
مـن ⇦121 📖المائدة 82
إلى ⇦141 📖الأنعام 110
⏱46:59 د
القارئ : صلاح بو خاطر👤
Te» https://t.me/sultan_54
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
رمضان مبارك ረመዳን ሙባረክ
RAMADAN MUBARAK
እንኳን ለ 1447ኛው የረመዷን ወር ጾም አሏህ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!
ወሩን በዒባዳ ከሚጠቀሙት እና መልካም ምንዳ ከሚፃፍላቸው ያድርገን! ኣሚን
አቡ ሁዘይፋ ሱልጧን ከድር
الحمدالله
شهركم مبارك!
تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال
🚨🔴 አሁን የደረሰን አስቸካይ ዜና!:
🌙 በሳውዲ አረቢያ ደማም የጨረቃ ምልከታ ማዕከል የረመዳን ጨረቃ እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልታየችም።
⏳ ቀሪ የጨረቃ ምልከታ ማዕከላት ውጤት እና በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይፋ የሚደረገውን ይፋዊ መግለጫ በጉጉት መጠበቁ ቀጥሏል…
📢 ለማንኛውም መግለጫ ሲወጣ እናሳውቃችኋለን።
🔴 አዳዲስ መረጃዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ ይከታተሉን።
/channel/sultan_54
🔴ሰበር ዜና #
ማሌዢያ
ሲንጋፖር
ብሩኒ
ኢንዶኔዢያ
የ 1447 ዓ/ሂ የረመዳን ጨረቃ አለመታየቷን አስታውቀዋሉ። ስለሆነም #ሐሙስ #የረመዳን_ወር የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።
🌟 የጾም ፊቅህ ኮርስ 🌟
ክፍል ሁለት፦:
📌 የበሽተኛ ሕግጋት በረመዳን
📌 ጾም ግዴታ ከሚሆንንባቸው ሁኔታዎች መካከል አንዱ ችሎታ አንዱ ነው፡ ይህም ያለ መቸገር የመጾም ችሎታ ማለት ነው፣ ተቃራኒውም አለመቻልና ደዌ(ህመም) ናቸው።
📌 በረመዳን ውስጥ ጾም መፍታት የሚያስችል የበሽታ ሕግጋት፡
🍀 ሀ - በድንገት መጥቶ በቶሎ የሚለቅ በሽታ ሲሆን ከእሱ ጋር መጾም የማይቻል ወይም ተመሳሳይ በሽታ ነው። ይህም እንደ ሁኔታዎች ይወሰናል።
🍁 1. በሽተኛው ጾም ጉዳት የማያስከትል ከሆነ ጾምን መፍታት አይፈቀድለትም። ይሁንና ማፍጠሩ ለእሱ የበለጠ ምቹ ከሆነ፣ መፍታቱ ለእሱ ተመራጭ ነው።
🍁 2. መጾም በእሱ ላይ ከባድ ከሆነ እና ነገር ግን ጉዳት የማያስከትል ከሆነ፣ ለእሱ መጾም የሚጠላ ሲሆን ለርሱ ማፍጠር የሚመከር ይሆናል።
🍁 3. ጾሙ በእሱ ላይ ከባድ ከሆነ እና አካሉ ላይ ጉዳት ካስከተለ፣ ጾም ለእሱ ሐራም ይሆናል። ለምሳሌ፣ መጾም ፈውስን የሚያዘገይ ወይም ህመምን የሚያስከትል ከሆነ፣ ወይም የጤና ባለ ሙያ እና ታማኝ ዶክተር ጾሙ በሽተኛውን እንደሚጎዳ ቢነግረው፣ በዚህ ሁኔታ ላይ ጾም ለእሱ እርም ይሆናል። ዶክተሩ ሙስሊም መሆን መስፈርት አይደለም፣ በሙያው ታዋቂና ታማኝ መሆኑ በቂ ነው።
🍀 ለ - መፈወስ የማይቻል ዘላለማዊ በሽታ፡ ለምሳሌ እርጅና የመሳሰሉት፣ ሰው በዚህ ምክንያት መጾም የማይችል ከሆነ፣ ገንዘብ ካለው፣ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ማብላት አለበት።
🍁 - በድሀነት ምክንያት ማብላት ያልቻለ ሰው፣ ማብላት ከርሱ ላይ ይወገዳል እና ምንም አይጠየቅበትም፤ አላህ አንዲትን ነፍስ ከችሎታው በላይ አያስገድድምና።
🍁 - በሽተኛው በቀኑ ክፍለ ግዜ ቢፈወሰ፣ ከመመገብና ከመጠጥ ራሱን መግታት አያስፈልገውም፣ ነገር ግን ከረመዳን በኋላ ቀዳ አለበት።
"በረመዳን በዲኔ ቁርጠኛ እሆናለሁ!..."
ይህ ሀረግ ቆንጆ ሆኖ ሳለ፤ እውነታው ግን አሁኑኑ በሻዕባን ወር የሚሰሩት ዒባዳ፤ የእርስዎ ሚዛን ነው።
ዛሬ የማንጠናከረው ዒባዳ... ወሩ ከመግባቱ ጋር በቀላሉ ቀላል አይሆንም።
ያለ ጫና በተቀሩት ሻዕባን ቀናት ላይ አራት የዒባዳ እቅድ ያስቀምጡ፡
ፈርድ ሶላት በጀመዓ + ሱና ሰላት + ዚክር + ዊትር ሰላት።
አስፈላጊው፡ ቋሚነት እንጂ ብዛት አይደለም... የዒባዳ ምሶሶችን የሚያስቀምጥ ሰው በረመዳን ውስጥ መጨመር ቀላል ይሆንለታል።
📃" የሸዕባንን ወር መጾም"
ሸዕባንን መጾም በተመለከተ ሁለት አይነት ሐዲሦች የተዘገቡ ሲሆን
አንደኛው ቡኻሪይና ሙስሊም ከናታችን ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ
ያስተላለፉት ሰሒሕ ሐዲሥ ነው
ነቢዩ የሸዕባንን ወር ቀናቶችን አብዛኞቹን በጾም ያሳልፏቸው እንደነበረ
ያሚያመላክት ሐዲሥ ሲሆን
ሁለተኛው ሐዲሥ ኢማም አትቲርሚዚይ፣ አቡ ዳውድና ሌሎችም
የዘገቡት ሲሆን አብዛኞች የሐዲሥ ምሁራን ደዒፍ እንደሆነ ተናግረዋል
ሀዲሡም እንዲህ ይላል
" የሸዕባን ወር ግማሽ ከሆነ በኋላ አትጹሙ"
ሁለቱንም ሐዲሦችን የሚያስታርቅውና በዚህ ነጥብ ላይ ትክክለኛ አቋም
የሆነውም የሚከተለው ነው፥
ሸዕባን ወር ከተጋመሰ (ከወሩ 15 ቀናት ካለፉ) በኋላ መጾም መጀመር
ይጠላል ከዛ በፊት የጀመረ ሰው ግን ሸዕባንን መጾም ይችላ::
አጿጿሙን በተመለከተ፥ ከፈለጉ አለፍ አለፍ እያሉ፣ ከፈለጉ ደግሞ አንድ
ቀን እየጾሙ ሌላ ቀን እያረፉ፣ ከፈለጉም የተወሰኑ ቀናትን በመደዳ
እየጾሙ ከዛም መሀል ላይ እያፈጠሩ ወዘተ ሁሉም ይቻላል::
ወሩን በሙሉ ምንም ሳያፈጥሩ መጾም ግን አይቻልም::
በቋሚነት የሚጾሙት የሱና ጾም ወይም የቀዷ ካልሆነ በስተቀር፥ ‹የውም አሽሸክ› ማለትም ረመዷን ዛሬ ነው ወይስ ነገ የሚባልበትን የጥርጣሬ
ቀን መጾም አይቻልም::
ወሏሁ አዕለም!
Te»/channel/sultan_54
وقت صلاة الظهر الآن
فيها ثترك مشاغل الدنيا، لتقف خاشغا بين يدي الرحمن،
ለራስህ ለውጥ ደንታ ከሌለህ ማንም አይቀይርህም፤ የውጤቱ ባለቤት አንተ ነህና።7122 SMS |ለውጥ
Читать полностью…
👆🏻👆🏻👆🏻
🔖#ፅናት
🎙 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
የነሲሓ ኢስላማዊ ስቱዲዮ ሙሐደራዎችና ቂርዓቶች የሚቀርቡበት ቻናል
👇🏼👇🏼👇🏼
/channel/nesihastudio
"እምነትህ አንጡራ ሀብትህ ነው! ስለሆነም እርሱን ከሚበክለው ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ልታደርግለት ይገባል... አላህ እኛንም ሁሉንም ሙስሊሞች በተውሒድ እና በሱና ላይ ያፅናን።"
✍ ሸይኽ ሙሐመድ ዩሱፍ ኸሻን