sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14074

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢብኑ ዑመር እንዲህ ብለዋል “የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከተምር አንድ ሷዕ * ከገብስ አንድ ሷዕ ዘካተል ፊጥር እንዲወጣ በባሪያም ፣ በነፃም ፣ በወንድም በሴትም ፣ በህፃንም በትልቅም በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ አድርገዋል።”
📚(ቡኻሪ 15ዐ3 ሙስሊም
🚫 ማሳሰቢያ፡ (* አንድ ሷዕ አራት እፍኞች ወይም 2.4ዐ ኪግ ማለት ነው)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

*اللهم إنا نسألك زيادة في الدين، وبركة في العمر، وصحة في الجسد، وسعة في الرزق، وتوبة قبل الموت، وشهادة عند الموت، ومغفرة بعد الموت، وعفواً عند الحساب، وأماناً من العذاب، ونصيباً من الجنة، وارزقنا النظر الى وجهك الكريم*🤲🏻🤎🍂

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በላጭ የዱዓ  ሰዓታት…

የዱዓ ሰዓታት በዘንጊነት ሊያልፉብን አይገባም፤ ምክንያቱም ዱዓ ኢባዳ (አምልኮ) ነው። በተለይ ጾመኛው አላህ በዲኑ ፅናት እንዲለግሰው እና መልካም ስራዎቹ ተቀባይነትን ለመጠየቅ  ዱዓ በጣም ይፈልጋል።
እነዚህን ሦስት ወሳኝ ጊዜያት በቀንህ ተጠቀምባቸው፦

🌇  (ኢፍጣር)፡- ሰአት
መግሪብ  ሰዓት ከማንም ትኩረት አጥፊ ነገር ርቀህ ዱዓ  አድርገው። ሐዲስ ላይ እንደመጣው፦ «ለጾመኛ የማይመለስ ዱዓ አለው» ተብሏል። እንዲሁም «ጾመኛ እስከያፈጥር(ዱዓው ተቀባይነት አለው።)» ተብሏል።

✨ ስሑር ወቅት፡-
ይህ የልብ ንጽህና እና ምሕረትን የምንጠይቅበት ጊዜ ነው። አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል፦ «በሌሊት መጨረሻ ሰዓቶችም(ስሑር) እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ።» (ዛሪያት፥ 18)

🔉 በአዛን እና በኢቃማ መካከል፡-
ነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «በአዛንና በኢቃማ መካከል የሚደረግ ዱዓ አይመለስም(ተቀባይነት አለው)፤ ስለዚህ ዱዓ አድርጉ።»

አላህ ዱዓችንን ይቀበለን እና የጊዜ በረካን ይስጠን። አሜን።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በጣም የሚያምር እና ልብን የሚነካ ጥያቄዎች… እነዚህ ጥያቄዎች የራስን ነፍስ መመርመርን የሚጠይቁ፣ ልብን ወደ ተውበት እና ወደ አላህ መመለስ የሚጋብዙ ናቸው።

እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች አብረን እንመልከታቸው፡-

«አፈኩለማ ኢሽተሀይተ ኢሽተረይተሁ?» (በተመኘሁ ቁጥር ትገዛለህን?) -

ጃቢር ኢብን አብዱላህ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ይላሉ፦

«ዑመር ኢብኑል ከጣብ (ረዲየላሁ አንሁ) በእጄ ላይ ፌስታል አንጠልጥዬ አዩኝና፡- "ይህ ምንድን ነው ጃቢር?" አሉኝ።
እኔም፡- "ሥጋን አስፈለገኝና ገዛሁኝ" አልኳቸው።
ዑመርም፡- ትላንት ገዝተህ አልነበረምን?
ጃቢርም፦ " ዛሬም ተመኘሁና ገዛሁት።" አላቸው
እሳቸውም፦
ጃቢር ሆይ!"በተመኘህ ቁጥር ትገዛለህን?"
(ጣፋጮቻችሁን በዱንያ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ፡፡ በእርሷም ተጣቃቀማችሁ፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ»)}  [አሕቃፍ:19]
የሚለውን አንቀጽ (አልትፈራም?)" አሉት።»

ይህ የሰው ልጅ ደካማነትን የሚያሳይ ነው። ነፍስ በፍላጎት ጊዜ ትዕግስትን አትማርም። ነገር ግን ነፍስ ትዕግስት የምትማረው እራስህን በምትፋለምበት ጊዜ ነው።

«አፈኩለማ ኸለውተ ዐሰይቱ?»
(ከሰዎች ገለል ብለህ ለብቻ በሆንክ ቁጥር ጌታህን ታምፃለህን?) -
ማንም ሰው ከሰው አይነ ሲሰወር ኃጢአት እንደሚሰራ ሁሉም ያውቃል።( ከአላህ እይታ ባይሰወርም) ነገር ግን እውነተኛ አማኝ የሆነ ሰው  እኔ ባላየውም አላህ ያየኛል። ብሎ ያምናል።

«አፈኩለማ ተዒብተ አስተረህተ?»
(በደከምክህ ቁጥር ታርፋለህን?) - ሕይወት ትግል ናት። ነፍስን መዋጋት ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አይቻልም።

«አፈኩለማ ዩሲረ ለከ ተማደይተ?» (በተመቸህ ቁጥር ወሰን ታልፋለህን?) - ምቾት ሰውን ወደ ዘና ማለት እና ወደ ኃጢአት ሊመራው ይችላል።

ከዚያም በጣም አሳዛኝ የሆነውን እውነታ አስታውሰናል?
ኃጢአት ስንሠራ፣ ቁርአን ከእኛ ጋር መሆን ያቆማል፣ የሌሊት ስግደት ይርቃል፣ የልብ መረጋጋት ይጠፋል፣ ኑሮ ይጠበባል፣ በረከት ይወገዳል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ በጣም አስፈሪው ነገር ያንን የኃጢአት ቅደም ተከተልን  ማየት ትጀምራለህ፦

· መጀመሪያ ከባድ ነው፣
· ከዚያም ይቀላል፣
· ከዚያም ትላመደዋለህ፣
· ከዚያም እየወደድከው ትመጣለህ፣(ሱስ ይሆናል)
· ከዚያም በልብህ ላይ ይታተማል፣
· ከዚያም ሌላ ኃጢአት ማነፍነፍ ትጀምራለህ።

ይህ እንዳይሆንብን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በመጨረሻም ነፍስህ ወደ ኃጢአት ስትጎተጉትህ፣ በዚህ የቁርኣን አንቀጽ  አናግራት፦
«ቁል አዛሊከ ኸይሩን አም ጃንናቱ አል-ኹልዲ አል-ለዚ ውዒ አል-ሙተቁን»
(በላቸው፡ ይህ(በሀጠአት  የምታገኘው አፍታዊ ደስታ) ይሻላልን ወይስ አላህ ለሚፈሩት ቃል የተገባው የዘላለም ጀነት?)

📚 [አል ፉርቃን፡15]

ይህ አንቀጽ ለነፍስ ትልቅ ማስተማሪያ ነው። አለማዊ ፍላጎትና የዘላለም ጀነት ሲነጻጸሩ፣ ማንኛውም አእምሮ ያለው ሰው ጀነትን ይመርጣል።

አላህ ሁላችንንም ከኃጢአት ይጠብቀን፣ ተውበታችንን ይቀበለን፣ ልባችንን ያንጻልን፣ ወደ ጀነቱ ያስገባን። አሚን።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

يا ربّ.. اجعلنا ممن نالوا شرف العتق، وذاقوا برد العفو، وفازوا برضاك والجنة. اللهم لا تخرجنا من هذا الشهر إلا وقد أصلحت حالنا، وغفرت ذنبنا، وجبرت قلوبنا بفيض كرمك. لعلها المنجية، ولعلها الليلة التي يتغير فيها القدر.

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

25ኛው ሌሊት፦
ልብን (ከቂም ከጥላቻ)ማጥራት ለሊት!


ወደ ሰማይ መዳፎቻችን ከማንሳታችን በፊት፣ በልባችን ውስጥ ያለውን እንመርምር። አንዳችን በአንዳችን ላይ ቂም ይዘናልን? በልባችን ውስጥ መቆራረጥ(ማኩረፍ) ወይም መራራቅ አለን?
እዝነት በእነዚህ ሌሊቶች ይወርዳል፣ ነገር ግን የተጣሉ ወይም የተኮራረፉ ሰዎች እዝነትን ሊከለከሉ ይችላል። በዛሬዋ ሌሊት አላህ ይቅር እንዲለው የሚፈልግ ሰው፣ እሱ ራሱ ለአላህ ባሮች ይቅር ይበል። በሰጁድህ ውስጥ በል፡ 'ጌታዬ ሆይ! ያንተን ፊትህን በመፈለግ ስል የበደሉኝን ሁሉ ይቅር አልኩ፤ አንተም ይቅር በለኝ'።”
ልቦቻችሁን አጥሩ፤ ሰላታችሁ፣ (ዒባዳችሁ)ንጹሕ ይሆናልና። ለይለቱ አል–ቀድር የሰላም ሌሊት ናት፤ ሰላምም የሚሰፍነው በንጹሕ ልቦች ውስጥ ብቻ ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ረመዳን ሲሰናበተን እንዲህ ያሉ ቃላትን ስትሰማ ምን እንደሚሰማህ አስብ::
ረመዳንን በአግባቡ ባለመጠቀምህ የሚሰማህን ቁጭት፣ ጉሮሮህን የሚተናነቅህ ሲቃ …
ረመዳን ገና አላለቀም፤ አሁንም በመጨረሻዎቹ አስርት ወረቃማ ቀናት ውስጥ ነን።
አሁንም ለሰላት፣ ለዱዓ፣ ለንፁህ ተውበት ቀሪ ጊዜ አለ::
እነዚህን ቀናት በአግባቡ ተጠቀምባቸው::
ምናልባት በሱጁድ ውስጥ የምታደርገው ንፁህ ዱዓ እና ተማፅኖ ዕድልህን ለዘላለም ሊለውጠው ይችላልና።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ቀልብህን በነዚህ ሦስት ስፍራዎች ላይ ፈልገው፦
ቁርአንን በምታደምጥ ጊዜ፣ አላህ የሚወሳበት መድረክ( መጃሊስ ዒልም ) ላይ እና ከሰዎች ገለል ብለህ ለብቻህን በምትሆንበትጊዜ፡፡ ቀልብህን በእነዚህ ስፍራዎች ባታገኘው፤ አላህን ልብን እንዲሰጥህ ለምነው፤ ምክንያቱም አንተ (እውነተኛ) ቀልብ የለህምና።»
✍ኢብኑል ቀዪም/በዳዒኡል ፈዋኢድ (1/149)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

▪️ኢብኑል ጀውዚ - አላህ ይዘንላቸው - እንዲህ ብለዋል፡-
*"በወሩ መጨረሻ ላይ ከመጀመሪያ ጊዜ የበለጠ ትጋት መኖር አለበት።
ለሁለት ነገሮች ሲባል፦
*አንደኛው፦-ለዚህ አስር ቀናት ክብር እና ለይለተል ቀድርን ለመፈለግ ሲባል።
*ሁለተኛው ደግሞ፡- ወሩን ለመሰናበት ሌላ የረመዷን ወር ማግኘት  አለመገናኘቱን እርግጠኛ አይደለምና።"


📚 [ አተብሲራ ሊኢብሊል ጀውዚይ (2/ 103)]።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ሌሎች ወራቶች ሁሉ ምትክ ሊኖራቸው ይችላል፤
የረመዳን ወር ግን ምትኩን ከየት ታገኛላችሁ?»
ኢብኑ ረጀብ
📚(ለጣኢፍ አል-መዓሪፍ / ገጽ 263)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة
النفس اللوامة

✨ወቃሽ ነፍስ

🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

🕌 ጎተራ ሼል ዲ ፖ ፈትሕ መስጂድ

🗓 ረመዷን 17/1447 አ/ሂ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"ፈረሶች በውድድር ላይ ሳሉ መጨረሻ ሲቀራርቡ ድልን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ስለዚህ፣ ፈረሶች ከአንተ የበለጠ ብልህ አይሁኑ! ሥራዎች በመጨረሻዎቻቸው ነው የሚገመገሙት።" 
- ኢብን አልጃውዚ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢማም ኢብኑ አል_ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡- 
«ባሪያው ኃጢኣትን በታዛኝነት(በምትክ) ሲቀይር፣ አላህ በእርሱ ላይ የነበረውን ቅጣት በደኅንነት፣ ውርደትንም በክብር ይቀይራል።» 
📚(አድ ዳእ ወደ_ደዋእ፣ ገጽ 73)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

﴿ ومن يتق الله يجعل له مخرجا * ويرزقه من حيث لا يحتسب ومن يتوكل على الله فهو حسبه إن الله بالغ أمره قد جعل الله لكل شيء قدرا ﴾

🎧 القارئ فارس عباد
📜 سورة الطلاق كاملة هنا👇💚
https://surahquran.com/65.html

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የነሲሓ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት

https://live.nesiha.tv

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

*"اللهم*
*"أنت العالم بأسرائرنا فأصلحها،*
*"وأنت العالم بجوائجنا فاقضها،*
*"وأنت العالم بذنوبنا فاغفرها،*
*"وأنت العالم بعيوبنا فاسترها،*
*"وأنت العالم بكسورنا فاجبرها،*🤲🏻🤎🍂

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በትክክለኛ ሰነድ (ሰነዳቸው በታመነ ዑለማዎች) ተረጋግጠው የመጡ ዱዓዎች በውስጣቸው ትልቅ ረድኤትና በረከት አላቸው።
​ በትላልቅ ፎንቶችና በሚያምር አቀራረብ የተዘጋጁ ከቁርአንና ከሐዲስ የተገኙ ጥቂት መሳጭ ዱዓዎችን ያጠናቀረ ኪታብ እንካችሁ፦
እናንተ በተለይ 27 ለሊት ላይ ተጠቀሟቸው ለምትወዷቸው ወዳጆች ያጋሩ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴  የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة

احسنوا توديع رمضان

ረመዳንን አሸኛኘቱን አሳምሩ!


⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️

🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር

💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ረመዷን 24 /1447 አ/ሂ

http://t.me/kalityhamzamesjid

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በቀን ከሰባ ጊዜ በላይ ተውበት ያደርጉ እንደነበር ተነግሯል። ታዲያ እኛ በሀጢአት ያደፍን ሰዎች!  ተውበት ለምንድን ነው የማናደርገው? ይሁንና ምንም እንኳ ትንሽ ቢሆንም  ከማንኛውም ኃጢአት ተውበት ለማድረግ ጥረት ብታደርግ፣ ፣ ይህ ነገር ያለ ፍልሚያ በቀላሉ ይሆናል ብለህ ታስባለህን? በእርግጥ ተውበት ለማድረግ እንደቆረጥክ ቢያውቅ አንድ አካል አለ፣ ከብስጭት የተነሳ አእምሮውን ያጣል። እርሱም ለረጅም ጊዜ ባንተ ላይ ኢንቨስት ያደረገ (አካል) ነው፣ አሁን ደግሞ ኢንቨስትመንቱን ሁሉ ሲያጣ ያለ ምንም ተቃውሞ የሚመለከትህ ይመስልሃል? ፈጽሞ አይቻልም። ይህ አካልማነው? ካልከኝ። ሸይጣን ይባላል። በእርግጠኝነት እሱ ጥርጣሬዎችን፣ ጥያቄዎችን እና ተቃውሞዎችን ያቀርብብሃል። እንደ ዝንጀሮ ዘሎ አናትህ ላይ ይወጣል!- ያም ሆነ ይህ አስፈላጊው ሃሳብህን እንድትቀይር እና ተውበት እንዳታደርግ ማድረግ ነው ጥረቱ።
ለምሳሌ፣ ኃጢአቱ ተደጋጋሚ ከሆነ ፦
“ ኃጢአት በተደጋጋሚ ትሠራለህ፣ ከዚያም ተውበት ታደርጋለህ? ከዚያም ወደ ተመሳሳይ ኃጢአት ትመለሳለህ፣ ከዚያም ተውበት ታደርጋለሁ … ይህ ንፍቅና ነው፤ አላህን አታፈረውም? አንተ ለተውበት ብቁ አይደለህም።" ይልሃል። ማሻ አላህ! ሸይጣን ላንተ ምን ያህል አጥብቆ ሲጨነቅ አስተውለሃል!?

ውድ ወንድሜ፣ ውድ እህቴ! ሸይጣን በተመለከተ አንድ አምልጦ የወጣ መረጃ አለኝ። ይኸውም የርሱን ውርደትን የያዘ ከአላህ ጋር የተደረገ ውይይት ነው። ይህ ውርደት ደግሞ ተውበት ለማድረግ ባሰብክ ቁጥር  እንዳታደርግ ሲወተውትህ ለርሱ የምትሰጠው በጣም ጠንካራ ምላሽ ይሆንሃል።
ነብዩ (ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም) ከብዙ ዘመናት በፊት ቀደም ሲል በሸይጣን እና በአላህ (ተባረከ ወተዓላ) መካከል ስለተደረገ ውይይት ተርከዋልናል።
ስለሆነም ይህን ውይይት  (ላሳውቅህ) ፍቀድልኝ፤ አንተም ይህን ሸይጣን በተመለከተ የመጣውን የውርደት  መረጃ  አጥብቀህ ይዘህ የሁል ግዜ መርህ ታደርገዋለህ። ኢንሻአላህ!💪
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ኢብሊስ (ሸይጣን) አለ፦ በክብርህ እምላለሁ! ነፍሶቻቸው በሰውነታቸው ውስጥ እስካለች ድረስ ባሮችህን ማሳሳት(መወትወት) አልተውም። አላህ (ተባረከከ ወተዓላ)ም አለ፦ በክብሬና በላቀ ማዕረጌ እምላለሁ! ተውበት እስካደረጉ ድረስ ለእነርሱ መማሬን(ምሕረትን)  ማድረጌን አልተውም።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

📍"المستمع للقرآن شريك للقارئ في كل حرف حسنه والحسنه بعشر أمثالها."
📗الشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله
🎙فتاوى نور على الدرب٣٥٠/٢٦

ሼኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁሏህ) እንደገለጹት፡- አድማጭ ከቃሪው (አንባቢ) ጋር በምንዳ ተጋሪ ነው። ስለዚህ ለአድማጭ በእያንዳንዱ ፊደል መልካም ሥራ (ሐሰና) አለው፣ መልካም ሥራም በአሥር እጥፍ ነው። ይህም (በሚከተለው) የአላህ ቃል ተገልጿል፦
{وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ}

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

*”بالأمسِ كُنا نقول:*
*اهلاً رمضانُ واليوم نقولُ مهلاً رمضانُ، اللهمَّ اغفر لنا ما مضى.. وأصلح لنا ما بقي، واختم لنا رمضانَ وأنتَ راضٍ عنا، واجعلنا ووالدينا من عتقائك من النار*🤲🏻🤎🤎🍂₎

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

”يا ابن آدم لو عرفت قدر نفسك ما أهنتها بالمعاصي"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሱፍያን አሥ-ሠውሪይ እንዲህ ብለዋል፡-

“ጓደኛህ ዱንያን ቸል እንድትል የሚያደርግህ፣
ከዱንያ ይልቅ አኼራን እንድትከጅል የሚያደርግህ ይሁን።
የዱንያ ሰዎች ስለ ዱንያ እያወሩህ ዲንህን እና ቀልብህን  ያበላሹብሃል፣
ሞትን ማስታወስ አብዛ፣
ላለፈው ኃጢአትህ አላህን ምህረት ጠይቅ።”

[ ሒልየቱ– አል-አውሊያ (7/82)]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

✍🏻 በነዚ በተባረኩ ለሊቶች በላጩ ዱዓ፡-
«አላሁ ኢነከ ዐፍዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ» የሚለው ነው። ትርጉሙም ፦ አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህና ይቅር ባይን ትወዳለህና ይቅር በለኝ* ማለት ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

#ዚክር
«ከጾመኞ ሁሉ በላጩ
አላህን በጾማቸው ወቅት
በብዛት የሚያወሱ(የሚዘክሩ) ናቸው።»

📚ኢብኑል ቀይም (አል ዋቢሉ አስ–ሠይብ / ገጽ 153)

ኢላሂ! ከጾመኞች እንጂ ከረሀብተኞች አትመድበን።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔔 የማንቂያ ደወል!

የረመዳን ቀናት እየተቆጠሩ ሲያልፉ ምንኛ ይፈጥናሉ!
በኢባዳ ለመትጋት ብርታት እንዲሆነን ይህ የትርፍ ወር የተቆጠሩ ጥቂት ቀናቶች ብቻ መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው። አላህ እንዲህ ይላል።
«أياما معدودات» البقرة 184
«የተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)» አልበቀራህ 184

የረመዳን ወቅት በመልካም ስራ የምንሽቀዳደምበት ወቅት ነው።
ሆኖም የረመዳን 1,2,3..10,15 ቀናት ሲያልፉ በጣም ይፈጥናሉ!!
የመጀመሪያው ግማሽ አልፏል። መዘናጋት በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ የተለመደ ክስተት ቢሆንም፤ መዘናጋታችን በአጨዳ ወቅት ከሆነ ግን ኪሳራው ከባድ ነውና እንጠንቀቅ!!

የተቀሩትን ቀናት በጥሩ ሁኔታ አልፎ ከሆነ አሻሽለን መልካም ስራን እንጨምር፤ በሚገባ ካልጠቀምንበትም ጉድለታችንንም አናሟላ፤ አናካክስ። አላህ ያበርታን!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«የረመዳን ወር ሊሰናበተን ተቃርቧል፤ ከእርሱም ጥቂት እንጅ አልቀረም፡፡ ከእናንተ ውስጥ በረመዳን መልካም ሥራን የሠራ ሰው በዚህ መልካም ሥራ ላይ ይጠናከር፤ ሳይጠቀምበት በዋዛ ያለፈበት ሰው ደግሞ በረመዳን መጨረሻ መልካም ሥራን በመሥራት ረመዷኑን ይፈፅም፡፡ ሥራ የሚታየው(ከግምት የሚገባው) ፍፃሜ ነውና፡፡»
📕ኢብኑ ረጀብ/ ለጣኡፉል መዓሪፍ(386)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"…ወራችሁ(ረመዳን) መጎደሉን ተያይዞታል።
እናንተ ደግሞ መልካም ስራችሁን ጨመርመር አድርጉ።"

(ኢብኑ ረጀብ/ለጣኢፉ አልመዓሪፍ /262)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

💰"ሰደቃ እና በአላህ መንገድ መጋደል (ጂሃድ)ይመሳሰላሉ። ፈሪ የሆነ  ሲርበተበት ጀግናው ደግሞ በፅናት መለገሱን ይቀጥላል።"

📖ኢብኑ ተይሚያ (አልፈታዋ: 14/95)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የገንዘብ ዘካህ ኒሷብ (የግዴታው መነሻ መጠን)
በተመለከተ ወቅታዊ ማብራሪያ


ማሳሰቢያ: ‐ ይህ ፅሁፍ የዛሬ አምስት(5) አመት በ1447 የተፃፈ በመሆኑ ስሌቱን በእለቱ (ዛሬ) ባለው ዋጋ ማስላት ግዴታ ነው!!

ያለንበትን ጊዜ የገንዘብ ዘካህ ኒሷብ (የግዴታው መነሻ መጠን) በተመለከተ ጥያቄዎች በርክተዋል፤ ይህን ከማስፈራችን በፊት ሁለት ቁም ነገሮችን ማስተዋል ያስፈልጋል፦

#አንደኛው፦ ይህ የሚመሰረትበት የወርቅ እና የብር ዋጋ ቋሚ ባለመሆኑ በየአመቱ የዘካው ግዴታ በደረሰበት ጊዜ (በረመዳንም ይሁን በሌላ ወር) የሚኖረው እለታዊ ዋጋ ላይ መመርኮዝ ተገቢ ነው። አንድ ጊዜ ተሰልቶ የተነገረ የገንዘብ ኒሷብ ለሁል ጊዜ አይሰራም።
በዚህ መሰረት ሰሞኑን በነሲሓ ቲቪ የተላለፈው ፕሮግራም ከአመት በፊት የተቀረፀ በመሆኑ ያኔ የተገለፀው የገንዘብ ኒሷብ ለዘንድሮ እንደማይሆን ልብ ይሏል።

#ሁለተኛው፦ ስሌቱን ስንሰራ የምንመረኮዘው በጌጣጌጥ መሸጫ ዋጋ ላይ ሳይሆን ማዕድኑ ከተጣራ በኋላ ሳይቀረፅ በፊት ባለው ቱባ ዋጋ ላይ ነው። ዘካህ የሚደነገገው በጌጣጌጥ ላይ ብቻ ሳይሆን በተጣራው ጥሬ ማዕድን ላይም በመሆኑ የዋጋ ልዩነቱን ማስተዋል ያሻል። ይህን ለማወቅ በየአገሩ ያለውን ዋጋ በየቀኑ፣ ብሎም በየሰዓቱ በሚያቀርቡ አስተማማኝ ድረ ገፆች (websites) መታገዝ ይቻላል።

በመሆኑም ሰሞኑን 
#ረመዳን_1442 ዓ.ሂ በአገራችን ያለው የጥሬ ብር ማዕድን አማካይ ዋጋ በግራም ወደ 35 ብር የተጠጋ ነው። ኒሷቡን ለማወቅ ይህን በ595 (የ200 ዲርሀም ክብደት በግራም) እናበዛዋለን፦

35 x 595 = 20,825

👉 የዘንድሮው ረመዳን ኒሷብ ወደ ሀያ ሺህ አካባቢ ነው ማለት ነው።

ስለዚህ ከዚህ ሳይቀንስ የጨረቃ አመት ያስቆጠረ ገንዘብ ያለው ሰው አንድ አርባኛውን (2.5%) ወጪ ያደርጋል።

ረመዳን 20/ 1442
___

ስለ ወረቀት ገንዘብ የዘካህ ህግ አጭር ማብራሪያ ከፈለጉ የስረኛውን ያንብቡ።
====
በዘመናችን የዋጋ ተመንነትን ተክቶ የሚገኘው የገንዘብ ኖትን አነሳስና ታሪካዊ ሂደት፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሊሰጠው የሚችለውን ሸሪዓዊ ብይን የተመለከቱ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል።
ባጭሩ የገንዘብ ኖት አነሳሱ ላይ ለወርቅ ወይም ለብር ባለቤትነትና ለእዳ ማረጋገጫ ሰነድ (ሪሲት) ሆኖ ሲዘዋወር ቆይቷል፤ ሆኖም ይህ ተጭባጭ ተቀይሯል።
የዛሬው የኢኮኖሚው ዓለም ነባራዊ ሂደት በግልፅ እንደሚያሳየው  የወረቀት ገንዘቡን በሚወክለው የወርቅ ወይም የብር መጠን በባንክ የመቀየር መብት በመሻሩና ያለ ተቀማጭ የወርቅ ሽፋን መታተም በመጀመሩ በኖቶቹ እና በወርቁ ወይም በብሩ መካከል የነበረው ህጋዊ ትስስር ቀርቷል። በዚህም መሰረት የእያንዳንዱ አገር ገንዘብ (currency) የግዢ አቅም ከአገሩ የኢኮኖሚ ሀይል ጋር የተዛመደ ሆኗል።
ይህም ማለት የገንዘብ ኖት የሰዎች ዋነኛ መገበያያና የዋጋ ተመን መሆኑ በተዘዋዋሪ ከወርቅና ከብር ጋር ቢያመሳስለውም ከሁለቱ ጋር ያለው የእዳ ትስስር ቀርቶ ራሱን የቻለ የዋጋ ተመን ሆኗል።

ስለሆነም «ኒሷብ» የደረሰ የገንዘብ መጠን ኖሮት አመት ያሳለፈ ሙስሊም ከገንዘቡ 1/40ኛውን (2.5%) ለዘካህ መክፈሉ የግድ ይሆናል።

ታዲያ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት አነስተኛ የገንዘብ መጠን (ኒሷብ) የሚገደብበት መሠረት የወርቅ ኒሷብ ዋጋ ወይስ የብር? የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ ውዝግብ ቢነሳም ብዙሀኑ የዘመናችን ሊቃውንት የመረጡት ሚዛን ደፊ አቋም በወቅቱ ከሁለቱ የኒሷብ ዋጋዎች አነስተኛ በሆነው ላይ እንደሚሆን ነው። ከላይ እንዳሳለፍነው የወረቀት ገንዘብ ራሱን የቻለ የዋጋ ተመን መሆኑ ከሁለቱ ኒሳቦች በአንዱ ላይ ብቻ ሳንወሰን ልክ አብዛኛዎቹ ቀደምት ሊቃውንት የንግድ ዘካህን አስመልክቶ እንደፈረዱት በየትኛውም በኩል አንደኛው የኒሷብ መሰረት ላይ መድረሱን ብቻ ከግምት እንድናስገባ ያደርገናል። ይህ ብዙ ሰዎች ዘንድ ወጪ የሚሆንውን የዘካህ መጠን ስለሚያበዛው ለዘካህ ተቀባዮች ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል።

ለምሳሌ፦
ዘካህ በሚወጣበት ወቅት የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ 2000 የኢት. ብር
#ቢሆን ይህንን በ85 ስናበዛው የወርቅ ኒሷብን ዋጋ ይሰጠናል፦
2000 x 85  = 170,000 ብር ይሆናል፤

የብር (ሲልቨር) ዋጋ ደግሞ በግራም 30 ብር
#ቢሆን ይህንን በ595 ስናበዛው የኒሷቡን ዋጋ ይሠጠናል፦
30 x 595 = 17,850 ይሆናል፤

ይህ ውጤት ከወርቁ የኒሷብ ዋጋ ያንሳል። በመሆኑም የገንዘብ ኖት ዘካህ በብር ዋጋ ላይ የተመሠረተ ይሆናል ማለት ነው።

የወርቁ ወይም የብሩ ጊዜያዊ ዋጋ በተቀየረ ቁጥር የኒሷቡም ዋጋ አብሮ መቀየሩ እንዳይረሳ።

በአሁኑ ጊዜ ያለው ተመን የሚያሳየንም የብር ኒሷብ ዋጋ ከወርቅ ኒሷብ ዋጋ እጅግ እንደሚያንስ ስለሆነ ቢያንስ 595 ግራም ጥሬ ብር የሚገዛ የገንዘብ መጠን ያለው ባለሀብት 1/40ኛውን (2.5%) ወጪ ማድረግ ይጠበቅበታል።



🌐
/channel/tahaahmed9

ይህ ጽሀፍ ከሸይኽ ኢሊያስ አህመድ የትምህርት መድረክ የተገኘ ነው። 👇 ይህን ተከትለው መድረኩን እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል።

/channel/ustazilyas

Читать полностью…
Subscribe to a channel