14074
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
"የወንጀሎችን (የኃጢአትን) እውነታና መጥፎ ውጤታቸውን ማወቅ ከፈለግክ 'አድ-ዳእ ወደ-ደዋእ' (በሽታና መድኃኒቱ) የተሰኘውን መጽሐፍ አንብብ። ስለ ወንጀል ያለህን አመለካከት 180 ዲግሪ ይቀይረዋል፤ እኛ አቅልለን የምናያቸው ወንጀሎች ምን ያህል ከባድ እንደሆኑም ትረዳለህ። አላህ ይቅር ይበለን። እንዲሁም የአላህን ፍትሃዊነትና ቅጣቱን ታውቅበታለህ።"
سهري لتنقيح العلوم ألذ لي *** من وصل غانية وطيب عناق
وتمايلي طربا لحل عويصة *** أشهى وأحلى من مدامة ساقይህ ግጥም፦
የኢማም አሽ-ሻፊዒ (ወይም እንደ አንዳንዶች አባባል የኢማም አዝ-ዘርኑጂ) ግጥሞች የሚመደብ ሲሆን እውቀትን የመገብየት እርካታ ከማንኛውም ዓለማዊ ደስታ እንደሚበልጥ ይገልጻሉ።
ገጣሚው ሌሊቱን ሙሉ ተኝቶ ከማሳለፍ ይልቅ መጽሐፍትን በማገላበጥ እና ዕውቀትን በማጥራት የሚገኘው ድካም፣ ለሰው ልጅ በስሜት ደረጃ ከሚገኝ ከፍተኛ እርካታ (ፍቅር/መተቃቀፍ) የበለጠ ጣፋጭ እንደሆነ ይገልጻል።
ሁለተኛው ስንኝ፡ አንድን እጅግ አስቸጋሪ የሆነ የዒልም እንቆቅልሽ ወይም "አልፈታ" ያለን ጥያቄ ሲፈታ የሚሰማው የደስታ ስሜት፣ ወይን ጠጥቶ (ከመሰከር) በላይ መንፈስን እንደሚያድስ ይናገራል።
ማሳሰቢያ⚠️⚠️**
⛔️ዛሬ ሌሊት 27ኛው ሌሊት ነው፤ እሷም ለይለቱ አልቀድር ፍተኛ ተስፋ የሚጣልባት ሌሊት ናት። ይህች ሌሊት፤
- ከመጨረሻዎቹ አስረት ቀናት ውስጥ ናት፣
- ከቀሩት ሰባት ጎደሎ ያልሆኑ (ተጨማሪ) ሌሊቶች ናት፣
- ዊትር ጎዶሎ ( ኢተጋማሽ) ሌሊት ናት፣
- ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ሌሊት ከፍተኛ ጥረት ያደርጉባት ነበር፣
- ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ለይል ሰላት (ቂያም) በጀመዓ አሰግደደዋቸዋል፣
- ሰሓቦቻቸውን በጀመዓ አሰግደዋቸዋል፣ ያ
- ቂያማቸውን ከዒሻ ጀምሮ እስከ ፈጅር አቅራቢያ ያራዝሙት ነበር፣
- ከሰሓቦች እና ከሰለፎቹ ውስጥ በነዚህ ሌሊት ለይለተ አል ቀድር መሆኗን እንደማያጠራጥሩ ተገልጿል፣
- ከቀደምት ሊቃውንትም የተወሰኑት ይህች ለሊት በትክክል ለይለተ ቀድር እንደሆነች ገልጸዋል፣
- ሌሎቹ ደግሞ ዊትር ሌሊቶች (21፣23፣25፣27፣29) መካከል የምትገኝ ስትሆን በብዛት ለይለተ አል ቀድር በየዓመቱ እንደምትለዋወጥ ተናግረዋል፣ ነገር ግን በብዛት በ27ኛው ሌሊት እንደምትከሰት ጠቅሰዋል፣
- ማስረጃዎቹም ሲሰባሰቡ ይህን አቋም ይደግፋሉ።
እደለ–ቢስ ሰውማ እሷን (ለይለተል ቀድር) ያጣ ነው!
📚የሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሀይሊ (አላህ ይጠብቃቸውና)
ከትዊትር ገፃቸው ከለቀቁት ወደ አማርኛ የተተረጎመ ።
*"اللهم*
*"أنت العالم بأسرائرنا فأصلحها،*
*"وأنت العالم بجوائجنا فاقضها،*
*"وأنت العالم بذنوبنا فاغفرها،*
*"وأنت العالم بعيوبنا فاسترها،*
*"وأنت العالم بكسورنا فاجبرها،*🤲🏻🤎🍂
በትክክለኛ ሰነድ (ሰነዳቸው በታመነ ዑለማዎች) ተረጋግጠው የመጡ ዱዓዎች በውስጣቸው ትልቅ ረድኤትና በረከት አላቸው።
በትላልቅ ፎንቶችና በሚያምር አቀራረብ የተዘጋጁ ከቁርአንና ከሐዲስ የተገኙ ጥቂት መሳጭ ዱዓዎችን ያጠናቀረ ኪታብ እንካችሁ፦
እናንተ በተለይ 27 ለሊት ላይ ተጠቀሟቸው ለምትወዷቸው ወዳጆች ያጋሩ።
🔴 የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
احسنوا توديع رمضان
ረመዳንን አሸኛኘቱን አሳምሩ!
⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ረመዷን 24 /1447 አ/ሂ
http://t.me/kalityhamzamesjid
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በቀን ከሰባ ጊዜ በላይ ተውበት ያደርጉ እንደነበር ተነግሯል። ታዲያ እኛ በሀጢአት ያደፍን ሰዎች! ተውበት ለምንድን ነው የማናደርገው? ይሁንና ምንም እንኳ ትንሽ ቢሆንም ከማንኛውም ኃጢአት ተውበት ለማድረግ ጥረት ብታደርግ፣ ፣ ይህ ነገር ያለ ፍልሚያ በቀላሉ ይሆናል ብለህ ታስባለህን? በእርግጥ ተውበት ለማድረግ እንደቆረጥክ ቢያውቅ አንድ አካል አለ፣ ከብስጭት የተነሳ አእምሮውን ያጣል። እርሱም ለረጅም ጊዜ ባንተ ላይ ኢንቨስት ያደረገ (አካል) ነው፣ አሁን ደግሞ ኢንቨስትመንቱን ሁሉ ሲያጣ ያለ ምንም ተቃውሞ የሚመለከትህ ይመስልሃል? ፈጽሞ አይቻልም። ይህ አካልማነው? ካልከኝ። ሸይጣን ይባላል። በእርግጠኝነት እሱ ጥርጣሬዎችን፣ ጥያቄዎችን እና ተቃውሞዎችን ያቀርብብሃል። እንደ ዝንጀሮ ዘሎ አናትህ ላይ ይወጣል!- ያም ሆነ ይህ አስፈላጊው ሃሳብህን እንድትቀይር እና ተውበት እንዳታደርግ ማድረግ ነው ጥረቱ።
ለምሳሌ፣ ኃጢአቱ ተደጋጋሚ ከሆነ ፦
“ ኃጢአት በተደጋጋሚ ትሠራለህ፣ ከዚያም ተውበት ታደርጋለህ? ከዚያም ወደ ተመሳሳይ ኃጢአት ትመለሳለህ፣ ከዚያም ተውበት ታደርጋለሁ … ይህ ንፍቅና ነው፤ አላህን አታፈረውም? አንተ ለተውበት ብቁ አይደለህም።" ይልሃል። ማሻ አላህ! ሸይጣን ላንተ ምን ያህል አጥብቆ ሲጨነቅ አስተውለሃል!?
ውድ ወንድሜ፣ ውድ እህቴ! ሸይጣን በተመለከተ አንድ አምልጦ የወጣ መረጃ አለኝ። ይኸውም የርሱን ውርደትን የያዘ ከአላህ ጋር የተደረገ ውይይት ነው። ይህ ውርደት ደግሞ ተውበት ለማድረግ ባሰብክ ቁጥር እንዳታደርግ ሲወተውትህ ለርሱ የምትሰጠው በጣም ጠንካራ ምላሽ ይሆንሃል።
ነብዩ (ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም) ከብዙ ዘመናት በፊት ቀደም ሲል በሸይጣን እና በአላህ (ተባረከ ወተዓላ) መካከል ስለተደረገ ውይይት ተርከዋልናል።
ስለሆነም ይህን ውይይት (ላሳውቅህ) ፍቀድልኝ፤ አንተም ይህን ሸይጣን በተመለከተ የመጣውን የውርደት መረጃ አጥብቀህ ይዘህ የሁል ግዜ መርህ ታደርገዋለህ። ኢንሻአላህ!💪
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ኢብሊስ (ሸይጣን) አለ፦ በክብርህ እምላለሁ! ነፍሶቻቸው በሰውነታቸው ውስጥ እስካለች ድረስ ባሮችህን ማሳሳት(መወትወት) አልተውም። አላህ (ተባረከከ ወተዓላ)ም አለ፦ በክብሬና በላቀ ማዕረጌ እምላለሁ! ተውበት እስካደረጉ ድረስ ለእነርሱ መማሬን(ምሕረትን) ማድረጌን አልተውም።"
📍"المستمع للقرآن شريك للقارئ في كل حرف حسنه والحسنه بعشر أمثالها."
📗الشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله
🎙فتاوى نور على الدرب٣٥٠/٢٦
ሼኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁሏህ) እንደገለጹት፡- አድማጭ ከቃሪው (አንባቢ) ጋር በምንዳ ተጋሪ ነው። ስለዚህ ለአድማጭ በእያንዳንዱ ፊደል መልካም ሥራ (ሐሰና) አለው፣ መልካም ሥራም በአሥር እጥፍ ነው። ይህም (በሚከተለው) የአላህ ቃል ተገልጿል፦
{وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ}
*”بالأمسِ كُنا نقول:*
*اهلاً رمضانُ واليوم نقولُ مهلاً رمضانُ، اللهمَّ اغفر لنا ما مضى.. وأصلح لنا ما بقي، واختم لنا رمضانَ وأنتَ راضٍ عنا، واجعلنا ووالدينا من عتقائك من النار*🤲🏻🤎🤎🍂₎
”يا ابن آدم لو عرفت قدر نفسك ما أهنتها بالمعاصي"
Читать полностью…
ሱፍያን አሥ-ሠውሪይ እንዲህ ብለዋል፡-
“ጓደኛህ ዱንያን ቸል እንድትል የሚያደርግህ፣
ከዱንያ ይልቅ አኼራን እንድትከጅል የሚያደርግህ ይሁን።
የዱንያ ሰዎች ስለ ዱንያ እያወሩህ ዲንህን እና ቀልብህን ያበላሹብሃል፣
ሞትን ማስታወስ አብዛ፣
ላለፈው ኃጢአትህ አላህን ምህረት ጠይቅ።”
[ ሒልየቱ– አል-አውሊያ (7/82)]
✍🏻 በነዚ በተባረኩ ለሊቶች በላጩ ዱዓ፡-
«አላሁ ኢነከ ዐፍዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ» የሚለው ነው። ትርጉሙም ፦ አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህና ይቅር ባይን ትወዳለህና ይቅር በለኝ* ማለት ነው።
#ዚክር
«ከጾመኞ ሁሉ በላጩ
አላህን በጾማቸው ወቅት
በብዛት የሚያወሱ(የሚዘክሩ) ናቸው።»
📚ኢብኑል ቀይም (አል ዋቢሉ አስ–ሠይብ / ገጽ 153)
ኢላሂ! ከጾመኞች እንጂ ከረሀብተኞች አትመድበን።
🔔 የማንቂያ ደወል!
የረመዳን ቀናት እየተቆጠሩ ሲያልፉ ምንኛ ይፈጥናሉ!
በኢባዳ ለመትጋት ብርታት እንዲሆነን ይህ የትርፍ ወር የተቆጠሩ ጥቂት ቀናቶች ብቻ መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው። አላህ እንዲህ ይላል።
«أياما معدودات» البقرة 184
«የተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)» አልበቀራህ 184
የረመዳን ወቅት በመልካም ስራ የምንሽቀዳደምበት ወቅት ነው።
ሆኖም የረመዳን 1,2,3..10,15 ቀናት ሲያልፉ በጣም ይፈጥናሉ!!
የመጀመሪያው ግማሽ አልፏል። መዘናጋት በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ የተለመደ ክስተት ቢሆንም፤ መዘናጋታችን በአጨዳ ወቅት ከሆነ ግን ኪሳራው ከባድ ነውና እንጠንቀቅ!!
የተቀሩትን ቀናት በጥሩ ሁኔታ አልፎ ከሆነ አሻሽለን መልካም ስራን እንጨምር፤ በሚገባ ካልጠቀምንበትም ጉድለታችንንም አናሟላ፤ አናካክስ። አላህ ያበርታን!
«የረመዳን ወር ሊሰናበተን ተቃርቧል፤ ከእርሱም ጥቂት እንጅ አልቀረም፡፡ ከእናንተ ውስጥ በረመዳን መልካም ሥራን የሠራ ሰው በዚህ መልካም ሥራ ላይ ይጠናከር፤ ሳይጠቀምበት በዋዛ ያለፈበት ሰው ደግሞ በረመዳን መጨረሻ መልካም ሥራን በመሥራት ረመዷኑን ይፈፅም፡፡ ሥራ የሚታየው(ከግምት የሚገባው) ፍፃሜ ነውና፡፡»
📕ኢብኑ ረጀብ/ ለጣኡፉል መዓሪፍ(386)
*اللهم آتِ نفوسنا تقواها، وزكِّها أنت خير من زكّاها، أنت وليُّها ومولاها* 🤲🏼
ይህ እጅግ ጥልቅ የሆነና የነፍስን ንጽህና የሚለምን ውብ ዱዓ ነው።
ትርጉሙም፦
"ጌታ ሆይ! ለነፍሶቻችን ጥንቃቄን (ተቅዋን) ስጣት፤ አንተ ከሁሉም በላይ አጥሪ ነህና አንጻት (እጠባት)፤ አንተ ረዳቷም ጌታዋም ነህና።" 🤲🏼
عن البراء بن عازب -رضي الله عنهما- قال: قام رجل فقال: يا رسول الله: إن حمدي زين وإن ذمي شين، فقال النبي ﷺ: "ذاك الله عز وجل".
رواه الترمذي وصححه الألباني والوادعي.
ኢብኑ ዑመር እንዲህ ብለዋል “የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከተምር አንድ ሷዕ * ከገብስ አንድ ሷዕ ዘካተል ፊጥር እንዲወጣ በባሪያም ፣ በነፃም ፣ በወንድም በሴትም ፣ በህፃንም በትልቅም በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ አድርገዋል።”
📚(ቡኻሪ 15ዐ3 ሙስሊም
🚫 ማሳሰቢያ፡ (* አንድ ሷዕ አራት እፍኞች ወይም 2.4ዐ ኪግ ማለት ነው)
*اللهم إنا نسألك زيادة في الدين، وبركة في العمر، وصحة في الجسد، وسعة في الرزق، وتوبة قبل الموت، وشهادة عند الموت، ومغفرة بعد الموت، وعفواً عند الحساب، وأماناً من العذاب، ونصيباً من الجنة، وارزقنا النظر الى وجهك الكريم*🤲🏻🤎🍂
Читать полностью…
በላጭ የዱዓ ሰዓታት…
የዱዓ ሰዓታት በዘንጊነት ሊያልፉብን አይገባም፤ ምክንያቱም ዱዓ ኢባዳ (አምልኮ) ነው። በተለይ ጾመኛው አላህ በዲኑ ፅናት እንዲለግሰው እና መልካም ስራዎቹ ተቀባይነትን ለመጠየቅ ዱዓ በጣም ይፈልጋል።
እነዚህን ሦስት ወሳኝ ጊዜያት በቀንህ ተጠቀምባቸው፦
🌇 (ኢፍጣር)፡- ሰአት
መግሪብ ሰዓት ከማንም ትኩረት አጥፊ ነገር ርቀህ ዱዓ አድርገው። ሐዲስ ላይ እንደመጣው፦ «ለጾመኛ የማይመለስ ዱዓ አለው» ተብሏል። እንዲሁም «ጾመኛ እስከያፈጥር(ዱዓው ተቀባይነት አለው።)» ተብሏል።
✨ ስሑር ወቅት፡-
ይህ የልብ ንጽህና እና ምሕረትን የምንጠይቅበት ጊዜ ነው። አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል፦ «በሌሊት መጨረሻ ሰዓቶችም(ስሑር) እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ።» (ዛሪያት፥ 18)
🔉 በአዛን እና በኢቃማ መካከል፡-
ነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «በአዛንና በኢቃማ መካከል የሚደረግ ዱዓ አይመለስም(ተቀባይነት አለው)፤ ስለዚህ ዱዓ አድርጉ።»
አላህ ዱዓችንን ይቀበለን እና የጊዜ በረካን ይስጠን። አሜን።
በጣም የሚያምር እና ልብን የሚነካ ጥያቄዎች… እነዚህ ጥያቄዎች የራስን ነፍስ መመርመርን የሚጠይቁ፣ ልብን ወደ ተውበት እና ወደ አላህ መመለስ የሚጋብዙ ናቸው።
እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች አብረን እንመልከታቸው፡-
«አፈኩለማ ኢሽተሀይተ ኢሽተረይተሁ?» (በተመኘሁ ቁጥር ትገዛለህን?) -
ጃቢር ኢብን አብዱላህ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
«ዑመር ኢብኑል ከጣብ (ረዲየላሁ አንሁ) በእጄ ላይ ፌስታል አንጠልጥዬ አዩኝና፡- "ይህ ምንድን ነው ጃቢር?" አሉኝ።
እኔም፡- "ሥጋን አስፈለገኝና ገዛሁኝ" አልኳቸው።
ዑመርም፡- ትላንት ገዝተህ አልነበረምን?
ጃቢርም፦ " ዛሬም ተመኘሁና ገዛሁት።" አላቸው
እሳቸውም፦
ጃቢር ሆይ!"በተመኘህ ቁጥር ትገዛለህን?"
(ጣፋጮቻችሁን በዱንያ ሕይወታችሁ አሳለፋችሁ፡፡ በእርሷም ተጣቃቀማችሁ፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጹ በነበራችሁት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ»)} [አሕቃፍ:19]
የሚለውን አንቀጽ (አልትፈራም?)" አሉት።»
ይህ የሰው ልጅ ደካማነትን የሚያሳይ ነው። ነፍስ በፍላጎት ጊዜ ትዕግስትን አትማርም። ነገር ግን ነፍስ ትዕግስት የምትማረው እራስህን በምትፋለምበት ጊዜ ነው።
«አፈኩለማ ኸለውተ ዐሰይቱ?»
(ከሰዎች ገለል ብለህ ለብቻ በሆንክ ቁጥር ጌታህን ታምፃለህን?) -
ማንም ሰው ከሰው አይነ ሲሰወር ኃጢአት እንደሚሰራ ሁሉም ያውቃል።( ከአላህ እይታ ባይሰወርም) ነገር ግን እውነተኛ አማኝ የሆነ ሰው እኔ ባላየውም አላህ ያየኛል። ብሎ ያምናል።
«አፈኩለማ ተዒብተ አስተረህተ?»
(በደከምክህ ቁጥር ታርፋለህን?) - ሕይወት ትግል ናት። ነፍስን መዋጋት ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አይቻልም።
«አፈኩለማ ዩሲረ ለከ ተማደይተ?» (በተመቸህ ቁጥር ወሰን ታልፋለህን?) - ምቾት ሰውን ወደ ዘና ማለት እና ወደ ኃጢአት ሊመራው ይችላል።
ከዚያም በጣም አሳዛኝ የሆነውን እውነታ አስታውሰናል?
ኃጢአት ስንሠራ፣ ቁርአን ከእኛ ጋር መሆን ያቆማል፣ የሌሊት ስግደት ይርቃል፣ የልብ መረጋጋት ይጠፋል፣ ኑሮ ይጠበባል፣ በረከት ይወገዳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ በጣም አስፈሪው ነገር ያንን የኃጢአት ቅደም ተከተልን ማየት ትጀምራለህ፦
· መጀመሪያ ከባድ ነው፣
· ከዚያም ይቀላል፣
· ከዚያም ትላመደዋለህ፣
· ከዚያም እየወደድከው ትመጣለህ፣(ሱስ ይሆናል)
· ከዚያም በልብህ ላይ ይታተማል፣
· ከዚያም ሌላ ኃጢአት ማነፍነፍ ትጀምራለህ።
ይህ እንዳይሆንብን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
በመጨረሻም ነፍስህ ወደ ኃጢአት ስትጎተጉትህ፣ በዚህ የቁርኣን አንቀጽ አናግራት፦
«ቁል አዛሊከ ኸይሩን አም ጃንናቱ አል-ኹልዲ አል-ለዚ ውዒ አል-ሙተቁን»
(በላቸው፡ ይህ(በሀጠአት የምታገኘው አፍታዊ ደስታ) ይሻላልን ወይስ አላህ ለሚፈሩት ቃል የተገባው የዘላለም ጀነት?)
📚 [አል ፉርቃን፡15]
ይህ አንቀጽ ለነፍስ ትልቅ ማስተማሪያ ነው። አለማዊ ፍላጎትና የዘላለም ጀነት ሲነጻጸሩ፣ ማንኛውም አእምሮ ያለው ሰው ጀነትን ይመርጣል።
አላህ ሁላችንንም ከኃጢአት ይጠብቀን፣ ተውበታችንን ይቀበለን፣ ልባችንን ያንጻልን፣ ወደ ጀነቱ ያስገባን። አሚን።
يا ربّ.. اجعلنا ممن نالوا شرف العتق، وذاقوا برد العفو، وفازوا برضاك والجنة. اللهم لا تخرجنا من هذا الشهر إلا وقد أصلحت حالنا، وغفرت ذنبنا، وجبرت قلوبنا بفيض كرمك. لعلها المنجية، ولعلها الليلة التي يتغير فيها القدر.
Читать полностью…
25ኛው ሌሊት፦
ልብን (ከቂም ከጥላቻ)ማጥራት ለሊት!
ወደ ሰማይ መዳፎቻችን ከማንሳታችን በፊት፣ በልባችን ውስጥ ያለውን እንመርምር። አንዳችን በአንዳችን ላይ ቂም ይዘናልን? በልባችን ውስጥ መቆራረጥ(ማኩረፍ) ወይም መራራቅ አለን?
እዝነት በእነዚህ ሌሊቶች ይወርዳል፣ ነገር ግን የተጣሉ ወይም የተኮራረፉ ሰዎች እዝነትን ሊከለከሉ ይችላል። በዛሬዋ ሌሊት አላህ ይቅር እንዲለው የሚፈልግ ሰው፣ እሱ ራሱ ለአላህ ባሮች ይቅር ይበል። በሰጁድህ ውስጥ በል፡ 'ጌታዬ ሆይ! ያንተን ፊትህን በመፈለግ ስል የበደሉኝን ሁሉ ይቅር አልኩ፤ አንተም ይቅር በለኝ'።”
ልቦቻችሁን አጥሩ፤ ሰላታችሁ፣ (ዒባዳችሁ)ንጹሕ ይሆናልና። ለይለቱ አል–ቀድር የሰላም ሌሊት ናት፤ ሰላምም የሚሰፍነው በንጹሕ ልቦች ውስጥ ብቻ ነው።
ረመዳን ሲሰናበተን እንዲህ ያሉ ቃላትን ስትሰማ ምን እንደሚሰማህ አስብ::
ረመዳንን በአግባቡ ባለመጠቀምህ የሚሰማህን ቁጭት፣ ጉሮሮህን የሚተናነቅህ ሲቃ …
ረመዳን ገና አላለቀም፤ አሁንም በመጨረሻዎቹ አስርት ወረቃማ ቀናት ውስጥ ነን።
አሁንም ለሰላት፣ ለዱዓ፣ ለንፁህ ተውበት ቀሪ ጊዜ አለ::
እነዚህን ቀናት በአግባቡ ተጠቀምባቸው::
ምናልባት በሱጁድ ውስጥ የምታደርገው ንፁህ ዱዓ እና ተማፅኖ ዕድልህን ለዘላለም ሊለውጠው ይችላልና።
«ቀልብህን በነዚህ ሦስት ስፍራዎች ላይ ፈልገው፦
ቁርአንን በምታደምጥ ጊዜ፣ አላህ የሚወሳበት መድረክ( መጃሊስ ዒልም ) ላይ እና ከሰዎች ገለል ብለህ ለብቻህን በምትሆንበትጊዜ፡፡ ቀልብህን በእነዚህ ስፍራዎች ባታገኘው፤ አላህን ልብን እንዲሰጥህ ለምነው፤ ምክንያቱም አንተ (እውነተኛ) ቀልብ የለህምና።»
✍ኢብኑል ቀዪም/በዳዒኡል ፈዋኢድ (1/149)
▪️ኢብኑል ጀውዚ - አላህ ይዘንላቸው - እንዲህ ብለዋል፡-
*"በወሩ መጨረሻ ላይ ከመጀመሪያ ጊዜ የበለጠ ትጋት መኖር አለበት።
ለሁለት ነገሮች ሲባል፦
*አንደኛው፦-ለዚህ አስር ቀናት ክብር እና ለይለተል ቀድርን ለመፈለግ ሲባል።
*ሁለተኛው ደግሞ፡- ወሩን ለመሰናበት ሌላ የረመዷን ወር ማግኘት አለመገናኘቱን እርግጠኛ አይደለምና።"
📚 [ አተብሲራ ሊኢብሊል ጀውዚይ (2/ 103)]።
«ሌሎች ወራቶች ሁሉ ምትክ ሊኖራቸው ይችላል፤
የረመዳን ወር ግን ምትኩን ከየት ታገኛላችሁ?»
ኢብኑ ረጀብ
📚(ለጣኢፍ አል-መዓሪፍ / ገጽ 263)
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
النفس اللوامة
✨ወቃሽ ነፍስ
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ጎተራ ሼል ዲ ፖ ፈትሕ መስጂድ
🗓 ረመዷን 17/1447 አ/ሂ
"ፈረሶች በውድድር ላይ ሳሉ መጨረሻ ሲቀራርቡ ድልን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ስለዚህ፣ ፈረሶች ከአንተ የበለጠ ብልህ አይሁኑ! ሥራዎች በመጨረሻዎቻቸው ነው የሚገመገሙት።"
- ኢብን አልጃውዚ
ኢማም ኢብኑ አል_ቀዪም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ባሪያው ኃጢኣትን በታዛኝነት(በምትክ) ሲቀይር፣ አላህ በእርሱ ላይ የነበረውን ቅጣት በደኅንነት፣ ውርደትንም በክብር ይቀይራል።»
📚(አድ ዳእ ወደ_ደዋእ፣ ገጽ 73)