sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14074

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

📢 የደርስ መቀጠል ማስታወቂያ!

በተባረከው የረመዳን ወር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩትና በየመሳጂዱ ሲሰጡ የነበሩት ዱሮሶች፤ አላህ ፈቃዱ ከሆነ ከነገ (ረቡዕ) ጀምሮ በነበራቸው ፕሮግራም መሠረት የሚቀጥሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።
የዒልም ጉዟችንን በንቃት እንድንቀጥል አላህ ይርዳን።
>
ትምህርቱን ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!

🌐 t.me/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ታላቅ የዚክር ስጦታ !
"ወደ መኝታህ በምትሄድበት ጊዜ (ከመተኛትሀ በፊት)፦
«

ላ ኢላሀ ኢለላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዓሊዪል ዓዚም፤ ሱብሐነላህ፣ ወልሐምዱሊላህ፣ ወላ ኢላሀ ኢለላህ፣ ወላሁ አክበር።"

>
ያለ ሰው፤ ወንጀሎቹ የባሕር አረፋ ያህል ቢሆኑ እንኳ ይማሩለታል።"

>
የሐዲሡ ደረጃ
📚፦ ሐዲሡ ሶሒሕ (ትክክለኛ) ነው።
>

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በፋቲሃ መታከም (ሩቅያ ማድረግ)
ሸይኽ ሙሐመድ ሳሊሕ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ)እንዲህ ብለዋል፦
> "ሱረቱል ፋቲሃ 'ሩቅያ' (ፈውስ የሚገኝባት ) መሆኗ ከነቢዩ ﷺ ተረጋግጧል። ይህም ማለት በታመመ ሰው ላይ ፈውስን በመፈለግ ትቀራለች። ይህ ደግሞ በተግባር የተሞከረና የተረጋገጠ የሆነ ነገር ነው። በታመመ ሰው ላይ ፋቲሃን መቅራት ለፈውስ በጣም ቅርብ ከሆኑ ሕክምናዎች አንዱ ነው።"
>
ምንጭ፦ ፈታዋ ኑሩን ዓለ አድ-ደርብ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በኢማሙ አሕመድ እና በተማሪያቸው አል-መርሩዚ መካከል በትዳር ዙሪያ  የተደረገ ድንቅ ውይይት!
● [መርሩዚ] እንዲህ አለ፦ አቡ አብደላህ (ኢማም አሕመድን) እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፦ "ነቢዩ ﷺ ሳይጋቡ መቆየትን (ምንኩስናን) ከልክለዋል። የነቢዩን ﷺ ፈለግ የጠላ ሰው እውነት ላይ አይደለም። የነቢዩን ባልደረቦች፣ የሙሃጅሮችንና የአንሷሮችን መንገድ የጠላ ሰው ደግሞ ከዲኑ ውስጥ ምንም ቦታ የለውም።"
* ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «እኔ በሌሎች ሕዝቦች ፊት በእናንተ ብዛት  እፊካከራለሁና(እኩራለሁ።) በብዛት ውለዱ።»
* "ነቢዩ ያዕቆብ (ዐለይሂ ሰላም) በዚያ ሁሉ ሀዘናቸው ውስጥ እንኳ አግብተዋል፣ ልጅም ተወልዶላቸዋል።"
* ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ሴቶች(ሚስቶች) ለእኔ (እንዲወደዱ) ተደርገዋል።»
* የነቢዩ ﷺ ባልደረቦችም ያገቡ ነበር።
● እኔም አልኩ፦ ሰዎች ግን "ገቢያቸንን በሐላል መንገድ የማግኛ መንገዱ ጠቧል።" ይላሉ።
* እሳቸውም ፦ "ነቢዩ ﷺ ምንም ለሌለው ሰው እንኳ  በብረት በቀለበት (መህርነት) ድረዋል።"
* እኔም፦ በቁርኣን ሱራም ቢሆን (ይቻላል አይደል)? አልኩኝ።
እሳቸውም፦ "ይህንን ተወው" አሉ። "ትክክል (ሶሒሕ) አይደለም እንዴ?" አልኳቸው።
* እሳቸው፦ "ተወው አልኩህ! ከአንድ ነገር ስከለክልህ ተከለከል፤ አንድ ወንድ ሊያገባ ይገባል፤ ካለው (ይቀልባታል)፣ ከሌለው ደግሞ ይታገሳል።"አሉኝ።
● እኔም አልኩ፦ "እርስዎ፦ "የምቀልባት ካጣሁ እፈታታለሁ" ይሉኛል። እኔ ግን ስራ አግኝቼ መህሯ አንድ ሺህ ድርሀም ቢሆንብኝስ? እኔ ደግሞ አሁን ላይ ምንም የለኝም።
* ሳቁና እንዲህ አሉ፦ "በአምስት ድርሀም አግባ! ኢብኑ አል-ሙሰየብ (ታላቁ ታቢዒይ) ልጃቸውን በሁለት ድርሀም ድረዋል።"
● እኔም፦ ቤተሰቦቼ በአምስት ድርሀም እንዳገባ አይፈቅዱልኝም አልኳቸው።
* አሉ፦ "አሃ! አሁን የዱንያን ነገር አመጣህብኝ፤ ይህ ሌላ ጉዳይ ነው።"
● እኔም፦ ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም (ታላቁ ዛሂድ) "የቤተሰብ ሐላፊ መሆን እንዴት ያስፈራል?!..." ማለታቸው ይወራል ስላቸው፤
* ንግግሬን ሳልጨርስ ጮኹብኝና እንዲህ አሉ፦ "በጎንዮሽ መንገዶች (ጠቃሚ ባልሆኑ ወሬዎች) ውስጥ ወደቅን። አላህ ዓፊያውን ይስጥህና—ሙሐመድ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው ምን ላይ እንደነበሩ ተመልከት!"
● ቀጠልኩና ለአቡ አብደላህ እንዲህ አልኳቸው፦ -ፉደይል ኢብኑ ዒያድ "አንድ ሰው በልባችን ውስጥ (ትልቅ ቦታ) ይኖራል፤ ነገር ግን በማዕዱ ዙሪያ ሰዎች ሲሰበሰቡ (ቤተሰብ ሲያፈራ) ከልባችን ይወጣል።" ማለታቸው ይወራል?
* አሉ፦ "ከእነዚህ የጎንዮሽ ወሬዎች ተወኝ!አላልኩህም? እውቀት እንዲህ አይቀሰምም! አላህ አውፍ ይበልህና! —ሙሐመድ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው ምን ላይ እንደነበሩ ተመልከት!"( እነሱን ተዋቸው!)
* ከዚያም ቀጠሉና፦ "እነሆ በዘመንህ ያሉ ደጋግ ሰዎች (ሷሊሖች) አግብተው እንጂ አታገኛቸውም።"
📚 ምንጭ፦ አል-ጃሚዕ ሊዑሉሚ አል-ኢማም አሕመድ (10/ 484 - 485)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🌷ሰባሑል ኸይር
> "በአላህ እምላለሁ! ሲሳይህ በባሕር ሥር ባለ ድንጋይ ውስጥ ቢሆን እንኳ፣ አንተ ጋር እስኪደርስ ድረስ አላህ ያወጣዋል።
> እወቅ! የሰው ልጅ ኃይል ሁሉ ቢሰባሰብ እንኳ፣ አንተ ጋር ሊደርስ ከተጻፈልህ ነገር (ሪዝቅ) የሚከልክልህ ምንም ነገር የለም፤ ስለዚህ ተረጋጋ።"
>

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

قال رسول الله ﷺ

من دعا إلى هدى كان

له من الأجر مثل أجور من تبعه

📚[ اخرجه مسلم ]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ረሒመሁላህ) አንድ ሰው ደሃ ቢሆንም እንኳ ለጋብቻ ማበረታታታቸው እና ጋብቻን ከአንዳንድ ዒባዳዎች ማስቀደማቸው፦
● ሷሊህ (ልጃቸው) እንዲህ ይላሉ፦ [ኢማም አሕመድን] ስለ አንድ ከሰርዶ (ሳር) ምንጣፍ እየሰራ ስለሚሸጥ ሰው ጠየቅኳቸው፣ ከሚያገኘው ገቢ (ትርፍ) ለቀን ቀለቡ (ምግቡ) የሚሆን እንጂ ከዛ በላይ አያገኝም። ይህ ሰው ለጋብቻ ቅድሚያ ይስጥን? አልኳቸው፣
አባቴ እንዲህ በማለት መለሱልኝ፦ ለጋብቻ ቅድሚያ ይስጥ። አላህ ሲሳዩን (ሪዝቁን)  ይዞላት ይመጣል።”
● እንዲህም አሉ፦“ ያግባ፣ ከተፈለገም ይበደር። በእጁ ላይ ለሐጅ የሚያደርሰው ሁለት መቶ ድርሃም ቢኖረው፣ ነገር ግን በራሱ ላይ ፈተና (ዝሙት) ከፈራ፣ እንዲያገባና ሐጅን እንዲተው አዘዋለሁ።”
● አቡ ዳውድ(ተማሪያቸው) እንዲህ ይላሉ፦ አቡ ዐብዲላህ [ኢማም አሕመድ] እንዲህ አሉ፦ “እንዲያገባ የሚያዙት ወላጆች ካሉት፣ እንዲያገባ አዘዋለሁ። ወይም ለራሱ ችግር (በፈተና መውደቅን) የሚፈራ ወጣት ከሆነ፣ እንዲያገባ አዘዋለሁ።”
● አል-መርሩዚ እንዲህ አለ፦ አቡ ዐብዲላህ [ኢማም አሕመድ] እንዲህ ሲሉ ሰምቼዋለሁ፦ "ለሴት ከወንድ የተሻለ ነገር የለም፣ ለወንድም ከሴት የተሻለ ነገር የለም።”
ጣዎስም እንዲህ ብሏል፦ “ሴት የወንድ ግማሽ ዲኑ ናት።”
● እንዲህም አሉ፦ አቡ ዐብዲላህ [ኢማም አሕመድ] እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ፦ “ያላገባ ሆኖ መኖር በኢስላም አስተምህሮ ውስጥ በምንም አይነት መንገድ የሚታወቅ ነገር አይደለም። ነቢዩ ﷺ አሥራ አራት ሚስቶችን አግብተዋል፣ ሲሞቱ ዘጠኙን ሚስታቸውን ተለይተው ወደ አኼራ ተሸጋግረዋል።”
• በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ቢሽር ኢቢኑ አል-ሓሪስ አግብቶ ቢሆን ኖሮ፣ ነገሩ ሁሉ በተሟላለት ነበር። ሰዎች ትዳርን ቢተው ኖሮ፤ ጂሃድ አይወጡም ነበር፣ ሐጅ አያደርጉም ነበር፣ ያም አይሆንም ነበር፣ ይህም አይሆንም ነበር።”
• እንዲህም አለ፦ ነቢዩ ﷺ ምንም ነገር ሳይኖራቸው ያነጉ ነበር፣ ምንም ነገር ሳይኖራቸውም ያመሹ ነበር። ከዘጠኝ ሚስቶች ተለይተው ሞተዋል። ትዳርን መርጠዋል፣ በእርሱም ላይ አበረታተዋል።”
📚 አል-ጃሚዕ ሊዑሉሚል ኢማም አሕመድ (10/483)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ደረትህ ላይ ጭንቀ ጥበብ ይልሃልን? ምክንያቱን በማታውቀው ጭንቀት ተወጥረሃል? ዛሬ ጁምዓ ነው፤ ፈጣን ውጤት ያለው ነብያዊ መፍትሔ እሰጥሃለሁ። በነቢዩ ሙሐመድ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ስታወርድ ሦስት ተአምራት ይከሰቱልሃል፦
* ሶለዋትህ ለሳቸው ይቀርባል። ስምህ በሰው ልጆች ሁሉ በላጭ በሆኑት (በነቢዩ) ዘንድ ሲነሳ እስቲ አስበው!
* አላህ በአንተ ላይ 10 ጊዜ ሶለዋት ያወርድልሃል። የአላህ አሥር እዝነቶች በልብህ ውስጥ ያሉትን ቁስሎች ለመፈወስ በአንተ ላይ ይወርዳሉ።
* የዱዓ መክፈቻ ነው። በዱዓህ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ሶለዋትን አድርግ፤ አላህ በመካከላቸው ያለውን ዱዓ ከመቀበል አይመለስም።
ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ጊዜውን ሁሉ ሶለዋት በማድረግ ለሚያሳልፍ ሰው እንዲህ ብለዋል፦ 'ጭንቀትህ ይወገድልሃል፤ ወንጀልህም ይማርልሃል።' ከጭንቀት መወገድና ከወንጀል መማር በላይ ምን ትፈልጋለህ? ቀኑን በሰላም ለመጀመር ዛሬ ለራሳችሁ የማይቋረጥ የሶለዋት ፕሮግራም አድርጉ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«

ከቀኖቻችሁ ሁሉ በላጩ ቀን የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በእኔ ላይ ሶለዋት ማውረድን አብዙ።»

🤍

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የፈጅር ሰላት (صلاة الفجر)

"የፈጅር ሰላት... አላህ ለእርሱ ያለህን ፍቅር የሚፈትንበት ቅጽበት ነው፤ የአልጋህን ሙቀት ትተህ ለጥሪው ምላሽ ስትሰጥ፣ በልብህ ውስጥ በማንም የማይጠፋ ብርሃን ትሸለማለህ።"

"የፈጅር ሰላት፦ ልብህ በፈጣሪው ፊት ለመቆም የሚያገኘው ወርቃማ እድል ነው።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

"በጨለማ ወደ መስጂዶች ለሚሄዱ ሰዎች በቂያማ ቀን ሙሉ ብርሃን እንደሚኖራቸው አብስራቸው።"
(ቲርሚዚና አቡ ዳውድ ዘግበውታል።)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«አላህ ሆይ! ባምጽህ አንተን አቅልዬ ወይም ለትእዛዝህ ግድየለሽ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ያቺ በመጥፎ ነገር በምትወተውተው የነፍስያዬ ድክመት ምክንያት እንጂ። ስለዚህ ማረኝ፣ ወደ አንተም አቅርበኝ። ጌታዬ ሆይ! አንተን ከማመፅ (ከመዓሲያ) ጠብቀኝ አርቀኝም።
አላህ ሆይ! ወንጀሌን ሁሉ፣ ጥቃቅን ሆነ ከባዱ፣ የመጀመሪያውንም ሆነ የመጨረሻውን ማረኝ። ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በድያለሁና ምህረት አድርግልኝ።
አላህ ሆይ! ጥፋቶቼን የሚታበስበትን ንጹሕ (መመለሻ የሌለው) ተውበትን ለግሰኝ።
> «አላህ ሆይ! ጥፋቶቼን የምታብስበትን ንጹሕ ንስሐን ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ! በሰራሁት ስህተት ልክ እና በተሰማኝ ጸጸት ብዛት ምህረትን እለምንሃለሁ፣ ወደ አንተም እመለሳለሁ።»
>

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የቪድዮው መልክት፦
«በቃ!ሙስሐፎቻችንን (ቁርኣናችንን) ዘጋን ማለት ነው?! በቃ ማንበቡን ተውነው?!ቁርኣን የማይቀራባቸው ቤቶች መኖራቸው ትልቅ አደጋ ነው! ሙስሐፉን ሳትከፍት ቀን እንዲያልፍብህ መፍቀድህ ትልቅ አደጋ ነው! "አደጋ" ሲባል ያለማጋነን በትክክለኛው አደጋ!
ምክንያቱም ይህ (ቁርኣን) የላቀው የአላህ ቃል ነውና። በእሱ ተደሰት፣ በእሱም ራስህን ከፍ አድርግ። (ቁርኣኑን) በልብህ የሐፈዝክ (በቃል የሸመደድክ) ብትሆን እንኳ (ሙስሐፉን ተመልክተህ አንብብ)።

ኢማሙ አሕመድ (አላህ ይዘንላቸውና)፤ በቤታቸው ውስጥ በየቀኑ ሙስሐፉን ይገልጡና ያነቡ ነበር።»

(ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ አል አሸ–ሸይኽ ሀፊዘሁሏህ)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የዘዋጅ (የትዳር )ጥቅሞች
ኢማም ኢብኑ ቁዳማ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ትዳር የተወደደ (ሙስተሐብ) ተግባር ሲሆን ብዙ ትርፎችም አሉት። ከጥቅሞቹም መካከል፦"
* ልጅ ማግኘት፦ የትዳር ዋነኛው ዓላማ የሰው ልጅ ዝርያ እንዲቀጥል ማድረግ ነው፤ በዚህም ውስጥ፦
* የሰውን ልጅ ዘር በማስቀጠል፤
* የነቢዩን ﷺ ፍላጎት መፈጸም፤ እርሳቸው ነገ በመልካም ተከታዮቻቸው ብዛት ይኩራራሉና።
*

በመልካም ልጅ ዱዓእ በረካን መፈለግ እንዲሁም ህፃን ልጅ ቢሞት (ለወላጆቹ) አማላጅ መሆኑን መከጀል።

* ከሸይጣን መጠበቂያ፦ የፍላጎትን (የሸህዋን) አደጋ በመከላከል ራስን ከሸይጣን ጥቃት መጠበቅ።
* ለነፍስ እረፍት መስጠት፦
ከትዳር አጋር ጋር በመቀራረብና በመጨዋወት ለነፍስ መጽናኛንና ደስታን ማግኘት።

* ልብን ከቤት አስተዳደር ስራዎች ነፃ ማድረግ፦ እንደ ምግብ ማብሰል፣ ቤት መጥረግ፣ ዕቃ ማጠብና የኑሮ መሰናዶዎችን በማስተካከል ሴት ልጅ ስለምታግዝ
ወንድ ልጅ ጊዜውን ለዕውቀትና ለዒባዳ እንዲያውል ታግዘዋለች። መልካም ሴት በዚህ መልኩ ለዲን ትልቅ ረዳት ናት

፤ እነዚህ የቤት ውስጥ ስራዎች ባይኖሩ ኖሮ ልብ በጭንቀት ይወጠር ነበርና።
* ነፍስን መገላገልና ማለማመድ፦ ለቤተሰብ ሐላፊነትን በመውሰድ፣ በባህሪያቸው ላይ በመታገስ፣ ከእነሱ የሚመጣን ችግር በመቻል፣ እነሱን ወደ ቀጥተኛው የዲን መንገድ በመምራት፣
ለእነሱ ሲባል ሐላል ሲሳይን ለመፈለግ በመድከም እና ልጆችን በመንከባከብ ነፍስን ማለማመድ። እነዚህ ሁሉ ታላቅ ምንዳ ያላቸው ስራዎች ናቸው።
ሐላፊነትን መሸከምና ቤተሰብን ማስተዳደር በአላህ መንገድ ላይ እንደ መታገል (ጂሃድ) ይቆጠራል።
* ከነቢዩ ﷺ ሐዲስ፦ በኢማም ሙስሊም ዘገባ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
> "አንድ ዲናር በአላህ መንገድ (ለጂሃድ) ብታወጣ፣ አንድ ዲናር ባሪያ ነፃ ለማውጣት ብታወጣ፣ አንድ ዲናር ለምስኪን ሰደቃ ብትሰጥ እና አንድ ዲናር በቤተሰቦችህ ላይ ብታወጣ፤ ከነዚህ ሁሉ ትልቁን ምንዳ የሚያስገኘው በቤተሰቦችህ ላይ ያወጣኸው ዲናር ነው።"
>
ምንጭ፦ ሙኽተሰር ሚንሃጅ አል-ቃሲዲን (ገጽ 161 - 162)

#ትዳርን_ማበረታታት
መልካም አዳር!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የዒዳችን መጠናቀቂያ ላይ … ሁልጊዜም ይህንን እናስታውስ..

እውነተኛው በዓላችን (ዒዳችን) በጀነት ውስጥ ይሆናል፤ አላህን በማየትና ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን ጋር በመቀማመጥ የምናሳልፈው። ያኔ ፊቶች በደስታ ያበራሉ፣ ልብሶችም ከሐርና ከዲባጅ የተሰሩ ይሆናሉ። እዚያ አድካሚ ስራ የለም፣ የሚታመምም ሆነ የሚያረጅ አካል የለም፣ የሚያለቅስ ዓይንም ሆነ የመለያየት ስቃይ የለም... አላህ እኔንም እናንተንም፣ እንዲሁም የምንወዳቸውን ሁሉ የጀነት ሰዎች ያድርገን።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አሰላሙ አለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ፤
🌷ሰባሑል ኸይር!
የዕለቱ መልእክት
ከዓብደላህ ኢብኑ አል-ሐሪስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው እንዲህ ብለዋል፦ "

ከአላህ መልክተኛ (ﷺ) በላይ ፈገግታ የሚያበዛ አንድም ሰው አይቼ አላውቅም።"

ዛሬ በዕለት ተዕለት ውሎህ በተለይም ሰዎች ዘንድ መጀመሪያ ስትገናኝ ፈገግታን በተግባር ለመፈፀም ሞክር።
ፈገግታና የፊትህ ብሩህነት በሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ የሚያመጣውን ለውጥና ተፅዕኖ ተመልከት።
በሥነ-ምግባር ከሰው ሁሉ በላጭ የሆኑትን ውድ ነቢይህን (ﷺ) ለመምሰል ጥረት አድርግ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኒካሕ(ጋብቻ )የሸይጣንን ተንኮል ለመመከት ይረዳል።
ኢብን ተይሚያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
○ "ላጤ መሆን የሸይጣንን ተንኮል ለመመከት፣ ዒልምን ለመቅሰም እና አላህን ለመገዛት የበለጠ ያግዛል ተብሎ የሚታሰበው፦

የሸሪዓን ድንጋጌና ተጨባጭ ሁኔታን የሚቃረን ስህተት ነው።

ይልቁንም ላጤ አለመሆን (ማግባት) የሸይጣንን ተንኮል ለመመከት የበለጠ ያግዛል።"

📚መጅሙዕ አል-ፈታዋ (31/ 63)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ፈውስ ለሚፈልግ ሰው
ኢብን አል-ቀዪም አል-ጀውዚያ (አላህ ይዘንላቸውና) "መዳሪጁ ሳሊኪን" በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦
> "እኔ በዚህ ረገድ (በሩቃ) በራሴም ሆነ በሌሎች ላይ አስደናቂ ነገሮችን ሞክሬያለሁ፤ በተለይም መካ (አላህ ያክብራትና) በነበርኩበት ጊዜ። እንቅስቃሴዬን ሊገቱ የሚቃረቡ በጣም አስቸጋሪ ህመሞች ያጋጥሙኝ ነበር፤ በተለይ በጦዋፍ ወቅትና በሌሎችም ጊዜያት። በዚያን ጊዜ ወደ ፋቲሃ ለመቅራት እፈጥንና ህመሙ ባለበት ቦታ ላይ እደባብሰዋለሁ፤ ያኔ ህመሙ ልክ እንደ ጠጠር ተንከባሎ እንደሚወድቅ (ወዲያው እንደሚጠፋ) ሆኖ ይሰማኝ ነበር። ይህንንም ደጋግሜ ሞክሬዋለሁ።
> እንዲሁም ከዘምዘም ውሃ በአንድ (ብርጭቆ) እወስድና ፋቲሃን ደጋግሜ እቀራበት ነበር፤ ከዚያም እጠጣዋለሁ። በዚህም ውስጥ በመድኃኒት የማላገኘውን ዓይነት ጥቅም እና ጥንካሬ አገኝ ነበር። ነገሩ ከዚያም በላይ ታላቅ ነው፤ ሆኖም (ውጤቱ) እንደ እምነት ጥንካሬና እንደ እርግጠኝነት (የቂን) ጥራት ይለያያል። አላህም ረዳታችን ነው።"
>

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

> "አንድ (ሰው እንደ ተራራ የሚገዝፉ ወንጀሎችን ተሸክሞ  የውመል ቂያማ ይመጣል፤ ነገር ግን ምላሱ አላህን በማውሳት (በመዘከሩ) የተነሳ ወንጀሎቹን ሲያፈራርሳቸው (ሲዘርዛቸው) ያገኘዋል።" (ኢብኑ ተይሚያህ)
>  ይህን ዚክር ደጋግመው ይበሉ፦
✨ አስተግፊሩላህ አል-ዐዚም ወአቱቡ ኢለይህ
✨ አስተግፊሩላህ አል-ዐዚም ወአቱቡ ኢለይህ
✨ አስተግፊሩላህ አል-ዐዚም ወአቱቡ ኢለይህ
⤴️ ለሚወዱት ሰው በማጋራት የዚክሩ ተቋዳሽ ያድርጓቸው።
ጥቆማ፦  የአላህን ዚክር ማብዛትና ኢስቲግፋር ማድረግ (ምሕረት መለመን) ምን ያህል ታላላቅ ወንጀሎችን እንኳ ሳይቀር እንደሚያብስ  የታላቁ ዓሊም ኢብኑ ተይሚያህ ምክር ነው። በተለይም በዚህ ዘመን ልብ በጭንቀትና በወንጀል በከበደበት ጊዜ ይህን ማዘውተር ትልቅ እረፍት ይሰጣል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ዑመር ኢብኑ ሳሊህ አል-በግዳዲ እንዲህ ይላሉ፦
"ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበልን 'ቀልብን የሚያለሰልሰው (የሚያራራው) ምንድን ነው?' ብዬ ጠየቅኳቸው። ወደ እኔ ተመለከቱና አንገታቸውን ደፉ፤ ደግመው ተመለከቱኝና ዳግም አንገታቸውን ወደ መሬት አቀረቀሩ፤ ከዚያም እንዲህ አሉ፦ 'ቀልብን የሚለሰልሰው በምንድን ነው? ያልከኝ?

(ቀልብ የሚለሰልሰውማ) ሐላልን በመመገብ ነዋ!'"

> "አላህ ሆይ! ሐላል ሪዝቅን በመፈለግ ላይ እርዳን፣ አግራልንም።"

{اللهم اكفني بحلالك عن حرامك، وأغنني بفضلك عمن سواك} 🤲

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

عَن سُلَيْمَانَ التَّيمِيِّ قَالَ:

«إِنَّ الرَّجُلَ لَيُذنِبُ الذَّنب فيُصبحُ وَعَليهِ مَدْلَتهُ»

سير أعلام النبلاء» (٦ / ٢٠٠)]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የዋጋ መናር!!
ኢብኑ ሙፍሊሕ አል-ሐንበሊ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

​"የሚገርመው ነገር፤ ብዙ ሰዎች ስለ መኖሪያ ቤት መፈራረስ፣ ስለ ሲሳይ (ሪዝቅ) ማነስ፣ ስለ ዘመኑ መክፋትና ስለ ዋጋ መናር ያለቃቅሳሉ (ይረበሻሉ)። ነገር ግን ዲን ከሰዎች መራቁ፣ ሱናዎች መጥፋትና ቢድዓዎች መስፋፋት አልቅሰው አያውቁም። ስለ ድክመታቸውም አያለቅሱም፤ ይህም የሆነው የኢማናቸው መዳከም እና ዱንያ በዓይናቸው ውስጥ ትልቅ ቦታ ስላላት ነው።"

​📚 አል-አዳብ አሽ-ሸሪዒያ (3/240)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

قال رسول الله ﷺ :

« ያ ኡቅባ !
የቆረጠህን ቀጥል፣
የነፈገህን ስጥ፣
የበደለህንም ይቅር በል ። »

(📚 ሶሒሕ አት-ተርጊብ: 2536)

ስለ ሐዲሱ ጥቂት ማብራሪያ ፦
ይህ ታላቅ ሐዲስ የላቀ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሲሆን፣ ሶስት ቁልፍ ነጥቦችን ይዟል፡
* የቆረጠህን ቀጥል፦ ዝምድናን ወይም ሰላምታን ላቋረጠብህ ሰው ቅድሚያውን ወስደህ መድረስ።
* የነፈገህን ስጥ፦ በችግርህ ጊዜ ያልደረሰልህን ወይም የከለከለህን ሰው፣ እሱ ሲቸገር በመርዳት የልብህን ንፅህና ማሳየት።
* የበደለህንም ይቅር በል፦ መበደልህን እያወቅክ ለአላህ ስትል ይቅርታ ማድረግ የጥንካሬ ምልክት ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ከታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም አል-ጀውዚያ (ረሒመሁላህ) ድንቅ መጽሐፍት አንዱ ከሆነው "አል-ፈዋኢድ" (الفوائد) ላይ የተወሰደ እጅግ ጥልቅ የሆነ የሥነ-ልቦና እና የመንፈሳዊ ጥንካሬ ምክር !
> "

ከሰዎች ሁሉ ብልህ (አስተዋይ) ማለት የክፉ ሃሳብን (ወይም ፍላጎትን) ገና በጅምሩ ላይ የሚቆርጥ ሰው ነው።
"
>
ቁልፍ ነጥቦች (ከኢብኑል ቀይም ማብራሪያ ተቀንጭቦ)፦
ኢብኑል ቀይም በዚሁ መጽሐፋቸው ላይ አንድ ወንጀል ወይም መጥፎ ድርጊት እንዴት ደረጃ በደረጃ ወደ ተግባር እንደሚቀየር እንዲህ ያስረዳሉ፦
* አል-ኻጢራ (الخاطرة) - ሃሳብ፦ መጀመሪያ በአእምሮ ውስጥ የሚመጣ ብልጭታ ወይም ሃሳብ ነው።
* አል-ፊክራ (الفكرة) - ማሰላሰል፦ ያንን ሃሳብ ደጋግሞ ማሰብ።
* አሽ-ሸህዋ (الشهوة) - ፍላጎት፦ ማሰላሰሉ ወደ ስሜትና መሻት ይለወጣል።
* አል-ዒራዳ (الإرادة) - ቁርጠኝነት፦ ያንን ስሜት ለመፈጸም ውሳኔ ላይ መድረስ።
* አል-ፊዕል (الفعل) - ተግባር፦ በመጨረሻም ወደ ስራ መግባት።
ለምን ገና በጅምሩ መቁረጥ አስፈለገ?
* ቀላሉ መንገድ፦
መጥፎ ሃሳብን ገና በጅምሩ (በኻጢራ ደረጃ) ማስወገድ በጣም ቀላል ነው። አንዴ አድጎ ወደ ቁርጠኝነት ከደረሰ ግን ለመከላከል እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል።

* የልብ ጥራት፦ መጥፎ ሃሳቦችን ገና ሲመጡ "አዑዙ ቢላህ" በማለት ወይም ወደ ሌላ ጠቃሚ ነገር በመዞር የሚያጠፋ ሰው ልቡን ከዝገትና ከጭንቀት ይጠብቃል።
* የብልህነት መለኪያ፦ ብልህ ሰው እሳቱ ሳይቀጣጠል በጭሱ ጊዜ የሚያጠፋ ነው።
ባጭሩ፦ ውጊያው መጀመር ያለበት በአእምሮ ውስጥ ነው። በሃሳብ ደረጃ ድል ካደረጉት፣ በተግባር ደረጃ ወንጀሉን መከላከል ቀላል ይሆናል።
📚(አል ፈዋኢድ)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

​✨ የፈጅር ሶላት፡ የነፍስ ብርሃን ✨

በዙሪያህ ያለው ዓለም ሁሉ ፀጥ ረጭጭ ባለበትና የሰው ልጆች በከባድ እንቅልፍ በተሸነፉበት ቅፅበት፤ የፈጅር አዛን የዝምታውን ግድግዳ ሰብሮ  (ሐያ ዐለ አስ–ሰላህ) "ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል" እያለ ሲጣራ... ያኔ ነው እውነተኛው የልብ ንቃት የሚጀምረው።

ፈጅርን የሰገደ ሰው ቀን ሙሉ በአላህ ጥበቃ (ዚም’ማህ) ስር ይሆናል። ታዲያ የፈጣሪ ጥበቃ ከሌለ ቀንህ እንዴት ያምራል?

"አላህ ሆይ! የፈጅርን ብርሃን፣ ስክነቱን በረከቱን አትከልክለን።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

(አቡ ሙሳ አል-አሽዐሪ) ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-

​"እኔና መስሩቅ ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ዘንድ ገባንና እንዲህ አልናት፡- 'የምእመናን እናት ሆይ! ከሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች መካከል ሁለት ሰዎች አሉ። አንደኛው ጾም ማፍጠሪያውን ያፈጥናል፣ ሶላቱንም ያፈጥናል (ቶሎ ይሰግዳል)። ሌላኛው ደግሞ ማፍጠሪያውን ያዘገያል፣ ሶላቱንም ያዘገያል።'
​እሷም፡- 'ከሁለቱ ማፍጠሪያውን የሚያፈጥነውና ሶላቱን የሚያፈጥነው ማነው?' አለች። እኛም፡- 'ዐብዱላህ (ማለትም ኢብኑ መስዑድ) ነው' አልናት።
​እሷም፡- 'የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ነበር የሚያደርጉት' አለች።"
📚 (ሙስሊም ዘግበውታል)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

📌 አንተ ወጣት ስማኝማ!

> ወንጀልን መተው ከፈለግክ መጀመሪያ ወደ ወንጀሉ የሚወስደውን በር ዝጋ!"
በወንጀል ላይ የመቀጠልህ ትልቁ ችግር አብዛኛውን ጊዜ ራሱ ወንጀሉ ላይ አይደለም፤ ይልቁንም

ወደ ወንጀሉ በሚያደርሱህ ምክንያቶች ላይ በምታሳየው ቸልተኝነትና መዘናጋት ላይ ነው።

በየጊዜው በዚያው ተመሳሳይ መንገድ፣ በዚያው ድብቅ ሁኔታ ውስጥ ትወድቃለህ።
እነዚህ (ወደ ወንጀል የሚመሩ) ምክንያቶች፦ ከሰዎች ተገልሎ በብቸኝነት ማሳለፍ(ኸልዋህ)፣ ዘመናዊ ስልክ፣ የተወሰኑ ጓደኞች ወይም ደግሞ አዕምሮ ላይ የሚመላለሱ መጥፎ የስሜት ፍላጎቶች(ኸጠራት ረዲኣህ))ሊሆኑ ይችላሉ።
ለወንጀል በሚያጋልጡ ምክንያቶች ተከበህ እስከቆየህ ድረስ ደጋግመህ ትወድቃለህ፤ ከእርሱ መላቀቁም  ይከብድሃል።

የወንጀሎች መንገድ አብዛኛውን ጊዜ ቀላልና ጣፋጭ መርዝ ነው።(ቀልብህን ይገለዋል)
ከማንኛውም ወንጀል ለመላቀቅ የመጀመሪያው መንገድ ይህንን 'ቀላል መንገድ' መዘጋገት ነው፤ በመንገዱ ላይ እንቅፋቶችን አስቀምጥ፣ አጥርም ስራ! 

በዚያ መንገድ ለመጓዝ በሞከርክ ቁጥር እንዳይሳካልህና በፍጥነት እንድትመለስ እንቅፋቶችን ፍጠር።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

​ሰባሑ አል ኸይር❤️
ከእለት ተእለት ስራህና በፊት፤ ዛሬ ልብህ በቁርኣን አንቀጾች ላይ አርፏልን?
በየእለቱ ማለዳ ከአላህ ቃል (ከቁርኣን) ጋር የማይታጠፍ ቀጠሮ ይኑርህ። ያኔ ቀኑ ረጋ ያለ፣ ህይወትህ ቀላል፣ እናም ነገሮችህ ሁሉ ባላሰብከው መንገድ ሲገሩልህ ይሰማሃል።

ማለዳህን በቁርኣን ጀምርቀኑ ይባረክልሃል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በዋትስኣፕ ለመከታተል፦👇
https://whatsapp.com/channel/0029VbC2qVH6hENvXGwN6U0c

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

እያንዳንዱ ሰው ታሞ እስኪተኛ ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግሮች እንዳሉበት ያስባል፤ ልክ በታመመ ጊዜ ግን ጤና ከሁሉም በላይ አስፈላጊ፣ ውድ እና ታላቅ ጸጋ መሆኑን ይረዳል..
ከዚያ በኋላ ጤና ከታላላቅ ጸጋዎች መሆኑን ትረዳለህ፤
በዓፊያ ማልዳህ፣ በዓፊያ መጓዝህ እና ቀኑን ሙሉ በዓፊያ ማሳለፍህ (ትልቅ ስጦታ ነው)።
ከነቢዩ ﷺ ዱዓዎች መካከልም፦
اللَّهُمَّ إِني أسألك العافية في الدنيا والآخرة،اللهم إني أسألك العفو والعافية في ديني ودنياي وأهلي ومالي).*~*.. ✿ً⃟🌷ً⃟✿..
"አላህ ሆይ! በዱንያም በአኺራም ዓፊያን (ጤናንና ሰላምን) እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! በዲኔ፣ በዱንያዬ፣ በቤተሰቤና በገንዘቤ ላይ ይቅርታህንና ዓፊያን እጠይቅሃለሁ" የሚለው ይገኝበታል።
📌 ዛሬ በጤና ተነስተህ መጓዝ መቻልህ ብቻውን ትልቅ "ሀብት" መሆኑን አትዘንጋ። አልሐምዱሊላህ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel