14074
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
የነቢዩን(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሐዲስ መከተል በንፁህ ሸሪዓ ወሰኖች ላይ መቆም ነው። 🕯️
📜 የአላህ መላክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁንና) የዚህ ዘመን ጠማማ ጥሪ አቅራቢዎችን (አሳሳቾችን) ያስጠነቀቁበት ግልጽ የሆነ የነቢይነት ሙዕጂዛ፤ እንዲህ አሉ። «አንድ ሰው በአልጋው ላይ ተደግፎ እያለ፣ ከእኔ ከሆኑት ሐዲሶች አንዱ ተወርቶለት፡ "በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መጽሐፍ (ቁርአን) አለ.." የሚልበት ጊዜ ሊመጣ ተቃርቧል። ንቁ! የአላህ መላክተኛ እርም ያደረጉት ነገር አላህ እርም እንዳደረገው ሁሉ ነው።»
#የነቢዩ_ሱና
ከኃጢአት ለመራቅ ከሚረዱህ ነገሮች አንዱ የአላህን ጸጋዎች ማስታወስ እና ማስተንተን ነው፤ ለመሆኑ የምታምጸው ማንን ነው?
አንተ የምታምጸው ሳትጠይቀው የረዘቀህን ፣ ነውርህን የሸፈነልህን፣ በሰዎች መካከል ያከበረህን እና በቁጥር ስፍር በሌላቸው በርካታ ጸጋዎች የከበበህን አላህን ነው።
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
> "የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትጨርሷትም፤ ሰው በእርግጥ በጣም በደለኛ ከሃዲ ነው፡፡" (ሱረቱ ኢብራሂም: 34)
>
እስቲ አስበው... በምድሩ ላይ ትኖራለህ፣ ከሲሳዩ ትመገባለህ፣ በጸጋዎቹ ውስጥ ትገለባበጣለህ፣ ከዚያም ታምጸዋለህ!
የአላህን ጸጋዎች ባስታወስክ ቁጥር፣ ልብህ እርሱን ለመታዘዝ ያፍራል፤ ይህ ፍርሃት ብቻ ሳይሆን፣ ለአላህ ካለህ ክብርና ሀፍረት የመነጨ ነው። አላህን በረሳህ ጊዜ ካመጽከው ደግሞ፣ ምሕረትን (ኢስቲግፋርን) አብዛ፣ ይቅርታውንና ምሕረቱንም ለምን።
ከቀደምት ደጋግ ሰዎች (ሰለፎች) አንዱ እንዲህ ብሏል፦
> "እጆቼን ወደ ላይ አንስቼ አላህን ስለምንና ዱዓዬን ሲመልስልኝ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዱዓዬን ካልመለሰልኝ ደስታዬ እጅግ የላቀ ይሆናል።"
>
"ለምን?" ተብሎ ሲጠየቅም እንዲህ ሲል መለሰ፦
> "ምክንያቱም እሱ (አላህ) የራሱን ፍላጎት ነው የሰጠኝ እንጂ እኔ የፈለግኩትን አይደለም። በእሱ ፍላጎትና ውሳኔ ላይ ያለኝ እምነት፣ እኔ ለራሴ መልካም ነው ብዬ ካሰብኩት በላይ ነው።"
>
ገባችሁ? አላህን አንድ ነገር ጠይቃችሁት ሳይመልስላችሁ ሲቀር፤ እወቁ፣ ከእናንተ ላይ አንድን መጥፎ ነገር እንዳራቀላችሁ። እሱ ባለው ጥበብና እውቀት፣ እናንተ ለራሳችሁ ያላያችሁትን መልካም ነገር ለእናንተ አይቶላችኋል።
እወቅ! በአላህ እዝነትና እውቀት የምታምን ከሆንክ፣ የደረሰብህ ነገር ሊስትህ እንደማይችልና የሳተህም ነገር ሊደርስብህ እንደማይችል እወቅ።
# ጃሚዑል መሳኢል (جامِعُ المَسَائِلِ)
ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢቢን ዐብዱልሐሊም ኢቢን ዐብዱሰላም ኢብኑ ተይሚያህ
“ነገር ግን ይህ ማለት አላህ በሰማይ ውስጥ ነው፣ ሰማያትም ይከቡታል ወይም ይይዙታል ማለት አይደለም። ይህንንማ ከቀደምት (ሰለፎች) እና ከዑለማኦች መካከል ማንም አላለውም። ይልቁንም አላህ ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፣ ከፍጡራኑ የተለየ (ያለተነካካ) መሆኑን፣ በፍጡራኑ ውስጥ የእሱ ማንነት (ዛቱ) ምንም ነገር እንደሌለ፣ በእሱም ማንነት ውስጥ ከፍጡራኑ ምንም ነገር እንደሌለ ተስማምተዋል።
* ማሊክ ኢቢኑ አነስ እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ በሰማይ ነው፤ እውቀቱ ግን በየቦታው ነው።»
* ለዐብዱላህ ኢቢኑ አል-ሙባረክ፦ «ጌታችንን በምን እናውቀዋለን?» ተብለው ሲጠየቁ፤ «ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ የላቀ፣ ከፍጡራኑ የተለያየ መሆኑን በማወቅ» አሉ።
* አሕመድ ኢቢኑ ሐንበልም፦ ልክ ይህና ይህ (የተባለው) ዓይነት ነው ብለዋል።
* አሽ-ሻፊዒይም እንዲህ ብለዋል፦ «የአቡ በክር ኸሊፋነት አላህ በሰማዩ የወሰነው እውነተኛ ውሳኔ ነው፤ የኡለማኦች ልቦችም በዚህ ላይ ተስማምተዋል።»
* አል-አውዛዒይም እንዲህ ብለዋል፦ «እኛና ታቢዒዮች በብዛት በነበርንበት ጊዜ አላህ ከዐርሹ በላይ መሆኑን እናረጋግጥ ነበር፤ በሱና ላይ በመጡት ባህሪያቱ ሁሉ እናምናለን።»
ስለሆነም አላህ በሰማይ ውስጥ የተከበበ፣ የተያዘ ነው ብሎ የሚያምን፣ ወይም ወደ ዐርሽና ወደ ሌላ ፍጡር ፈላጊ ነው ብሎ የሚያምን፣ ወይም በዐርሹ ላይ ከፍ ማለቱ (እስቲዋእ) ልክ ፍጡር በወንበሩ ላይ እንደሚደላደለው ዓይነት ነው ብሎ የሚያምን ሰው፤ እሱ የተሳሳተ፣ ቢድዓ አራማጅና መሃይም ነው።
(3/198)
ወንድሞቼ ሆይ! ጉቦ(ሙስና) አሁን ላይ መልክና ዓይነቱን ቀይሯል።
* አንዳንድ ጊዜ ስጦታ ይሆናል፣
* ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለ ወለድ የሚሰጥ ብድር (ቀርደን ሀሰን) ይሆናል፣
* አንዳንድ ጊዜ በነፃ መኪና ማስተካከል፣
* ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግብዣ፣
* አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የዋጋ ቅናሽ ይሆናል።
ስለዚህ፣ በዚህ እርግማን ውስጥ እንዳንወድቅ የጉቦን መልክና ዓይነቶች ልናስተውል ይገባል። አላህ ይጠብቀን።
> ለ1447ኛው ሂጅሪያ አ/ ሂ ምርጥ የሐጅ ልዑካን ምደባ ላይ ቀዳሚ ደረጃዎችን በመያዝ፣ በከፍተኛ ሥርዓትና ለሐጃጆቻቸው በማሳየት ረገድ ግሩም ምሳሌ ለሆኑት ሕዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! 🏆
>
ምርጥ የሐጅ ልዑካን (ልኡካን ቡድኖች)
### 💎 የአልማዝ ሽልማት
* 🇲🇾 ማሌዢያ
* 🇪🇹 ኢትዮጵያ
* 🇮🇶 ኢራቅ
### 🥇 የወርቅ ሽልማት
* 🇹🇷 ቱርክ
* 🇰🇲 ኮሞሮስ (ጁዝሩል ቀመር)
* 🇩🇯 ጅቡቲ
### 🥈 የብር ሽልማት
* 🇪🇬 ግብፅ
* 🇴🇲 የኦማን ሱልጣኔት
* 🇲🇦 ሞሮኮ
### 🥉 የነሐስ ሽልማት
* 🇸🇬 ሲንጋፑር
* 🇹🇳 ቱኒዚያ
* 🇩🇿 አልጄሪያ
የሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) ወርቃማ ምክር!
> 🔴 "በዲን ውስጥ ማጥበቅና ወሰን ማለፍም ሆነ፤ ቸልተኝነትና ግድየለሽነት አይፈቀድም። ይልቁኑ በዚህና በዚያ መካከል መካከለኛ (ሚዛናዊ) ሁን።"
> — አሽ–ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን፣ ፈታዋ (9/367)
>
## 📌 ጠቃሚ ምክር!
በአካሉ፣ በንግግሩ፣ በጽሑፉ እና በሁሉም ጉዳዮቹ ላይ ጥንካሬን ለሚሻ ሰው፦
👇👇
ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህን ማውሳት (ዚክር) ለሚያዘወትረው ሰው ጥንካሬን ይሰጠዋል። አልፎ ተርፎም ያ ሰው በዚክር አማካኝነት ያለ ዚክር ሊያደርገው የማይችለውን ከባድ ነገር ሁሉ በቀላሉ ይከውናል።
እኔ ራሴ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን (ረሒመሁላህ) ብርታት በተመለከትኩ ጊዜ በአካሄዳቸው፣ በንግግራቸው፣ በጀግንነታቸውና በጽሑፋቸው ላይ የሚገርም ነገር አይቻለሁ። አንድ ጸሐፊ በአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ሊጽፈው የሚችለውን የኪታብ ዝግጅት እሳቸው በአንድ ቀን ውስጥ ይጽፉት ነበር። የጦር ሠራዊቱም በጦርነት ወቅት የነበራቸውን ታላቅ ጥንካሬና ጀግንነት በተግባር መስክሯል።
●● የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለልጃቸው ፋጢማ እና ለዐሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ወደ መኝታቸው በሚሄዱበት ጊዜ፦
* 33 ጊዜ ‘ሱብሐነላህ’
* 33 ጊዜ ‘አልሐምዱሊላህ’
* 34 ጊዜ አላሁ አክበር ፣ ብለው እንዲያወሱ አስተምረዋቸዋል።
ይህንን ያስተማሯት ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ስንዴ ፈጭቶ ማዘጋጀትና የቤት ውስጥ ሥራ ደክሟት አገልጋይ እንዲሰጧት በጠየቀቻቸው ጊዜ ነበር። ይህንን አስተምረው ማጠቃለያው ላይ፦ '(ይህ ዚክር) ለእነሱ ከአገልጋይ ይበልጥ በላጭ ነው' አሏት።
👈 በመሆኑም ይህንን ዚክር አዘውትሮ ያደረገ ሰው በአካሉ ላይ አገልጋይ ከመፈለግ የሚያብቃቃውን (የሚተካውን) ጥንካሬ ያገኛል ተብሏል።"
> 📚 ምንጭ፦ አል-ዋቢል አስ-ሰዪብ፣ ገጽ (185)
>
### ግንዛቤ ማስተካከያ!
የሰው ልጅ ለሰዎች የመጸወተውና በአላህ መንገድ ላይ የሰጠው ነገር ሁሉ ለአኼራው የሚቀረው እውነተኛው ሀብቱ ሲሆን፣ ለራሱ አስቀርቶ የበላውና የተጠቀመበት ግን አላፊና ጠፊ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
የአላህ መልእክተኛም ﷺ አንድ የበግ ጠቦት አረዱና፤(ዓኢሻን) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፦
(“ከበጓ ላይ ምን የቀረ ነገር አለ?”)
*(እናታችን ዓኢሻም* እንዲህ አሏቸው፦ “ከትከሻዋ በስተቀር ምንም የቀረ ነገር የለም።”
የአላህ መልእክተኛም ﷺ እንዲህ አሉ፦
“ከትከሻዋ በስተቀር ሙሉዋ ቀርታለች እንጂ!”
*[ቲርሚዚ የዘገቡት ሲሆን፣ አልባኒ ሰሒሕ ነው ብለውታል]*
📌 ዙልሒጃ ቀን 10 (የዒድ ቀን)፦
> በተለያዩ ምክንያቶችና በህመም ሳይጓዙ የቀሩ፣ ልባቸው ግን ከመካ ያልተለየ ብዙ ወገኖች አሉ።
يا راحلين إلى البيت العتيق * سرتم جسوما وسرنا نحن أرواح إن أقمنا عن عذر وعن قدر * ومن أقام عن عذر كمن راحا
"እናንተ በአካላችሁ ተጓዛችሁ፣ እኛ ግን በነፍሳችን ተጓዝን፤ በእውነተኛ ምክንያት የቀረ ሰው ግን እንደተጓዘ ይቆጠራል።" አላህ (በኡዝር) የቀሩትን የሑጃጆችን አጅር ይመንዳቸው! 🕊️❤️ #ዙልሒጃ #የዒድ_ቀን
>
📌ዙልሒጃ ቀን 09 (የዐረፋ ቀን)፦
> የዒድ ቀን ምንኛ ታላቅ ቀን ነው! ያ ቀን አላህን ወደማየት ቀን ያሻግረናል። አላህ መጋረጃውን ገልጦ፦ "ባሪያዎቼ ሆይ! ተመልከቱኝ" ይላል። አላህን ከመመልከት የበለጠ ያማረ ምንም ዓይነት ጸጋ የለም። አምላካችን ሆይ! እኛንም ከእነርሱ ወገን አድርገን! 🤲 رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا #ዒድ_ሙባረክ #ዐረፋ
ዙልሒጃ 8(የውሙ ተርዊያህ)
ከሚና ጥሪው(ተልቢያው) ይጀምራል፣
በአረፋም እለት ዱዓዎች ወደ ላይ ይውጣሉ፣
በመቀጠል በሰከነ መንፈስ ወደ ሙዝደሊፋ፣
በጀመራትም የኢማን እርምጃዎች ይፈጸማሉ..
የሐጅ ትዕይንቶች በቅዱሳን ቦታዎች መካከል መዘዋወር ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የልብ ወደ አላህ የመጓዝ ጉዞ እንጂ።
#ሐጅ
#ሐጅ_1447ዓ_ሂ
የአእምሮና የሃሳብ ጥንካሬ የሚገለጠው መርህን ግልጽ በማድረግና ማንነትን ጠብቆ በማስረዳት ላይ እንጂ፣ የሰሚዎችን ስሜት ለመከተልና የአስተሳሰብ ግጭትን ለመሸሽ ሲሉ በማንነት ውስጥ መለዘብ አይደለም።
Читать полностью…
📌ዙልሒጃ ቀን 08፦
> ከወንጀላቸውም ልክ እናታቸው እንደወለደቻቸው ቀን ሆነው ይነጻሉ! ሑጃጆቹ ሙሉ ስነ-ሥርዓቱን በደስታ ያጠናቅቃሉ፤ ፊታቸው በብርሃን ይፈካል፣ ልቦናቸው በደስታ ይሞላል። አላህ የሁሉንም ሐጅና ዱዓእ ተቀብሎ ከእሳት ነፃ ከሆኑት ያድርገን። 🕋 ሰፊ በረከቱ በሁላችንም ላይ ይውረድ። #ሐጅ #ዙልሒጃ
ዐላመቱ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ
### ጥያቄ (ከአድማጭ)፦
> "ጥያቄ አቅራቢው እንዲህ ይላል፦ 'እኔ መልካም ነገርን የምትወድ ነፍስ አለችኝ፤ ነገር ግን ደካማ ናት፣ ከወንጀልና ከጥፋት ፊት መቆም አትችልም። ወንጀልን ባየሁ ቁጥር ከፊቱ እደክማለሁ። ታዲያ ለዚህ የሚሆን፣ የሚመሩኝ መድኃኒት ወይም ፈውስ አለን?'"
>
### የሸይኽ ኢብን ባዝ ምላሽ፦
"አዎ! አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) *'ሰውም ደካማ ሆኖ ተፈጠረ'* ብሏል። ነገር ግን እንድትጠነክር አላህ መሣሪያዎችን ሰጥቶሃል።
ልብህ በእነርሱ እንዲጠነክር ያደረገልህን መሣሪያዎች ሰጥቶሃል፤ እነርሱም፦
* አላህን መታዘዝ፣ * ዚክርን (እርሱን ማውሳትን) ማብዛት፣ * በእርሱ ታላቅነት ላይ ማስተንተን እና በአንተ ላይ ስላለው መብት ማሰብ ናቸው።
አንተ ወደ እርሱ ተመላሽ መሆንህን፣ ተጠያቂ መሆንህንም አስብ፤ *'በጌታህ እምላለሁ! ከሚሠሩት ነገር በሙሉ በእርግጥ እንጠይቃቸዋለን'* ተብሏል።
አንተ በጥፋቶችህ ምክንያት ቅጣት የሚገባህ መሆንህን፣ በታዛዥነትህ ደግሞ ምንዳ (አጅር) የምታገኝ መሆንህን አስብ። ስለዚህ (ነፍስህን) አስታውሳት፤ ስሜትንም አትከተል፤ ከአላህ መንገድ ያሳስትሃልና። ነፍስ በአላህ እዝነት ካልተጠበቀች በስተቀር ሁልጊዜም ወደ መጥፎ ነገር አዛዥ መሆንዋን እወቅ። ስለዚህ ለስሜቷ አትታዘዝላት።
አላህ እንዲህ ብሏል፦
> *'ያ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ፣ ነፍሱንም ከክፉ ስሜቷ የከለከለ፤ በእርግጥ ጀነት እርሷ መጠጊያው(መኖሪያወ) ናት።'*
>
ስለዚህ ነፍስህ ወደ ወንጀል ስትጠራህ፦ ነገሩ ከባድ መሆኑን፣ አላህ ከወንጀል መከልከሉን፣ በአላህ ቁጣና ቅጣት የተዛተበት መሆኑን አስታውሳት፤ (አላህ ካልማረው በስተቀር)። አንተ ደግሞ በዚያው ወንጀል ላይ እያለህ ልትሞት ትችል እንደሆነ፣ ይቅርታ ይደረግልህ ወይም ትቀጣ እንደሆነ አታውቅም።
ስለዚህ ታገላት፣ አስታውሳት፣ ነገሮችን አቅልሎ ከመመልከት (ቸልተኝነት) ተጠንቀቅ። በዚህ ላይ ከተሳካልህ አላህ ያግዝሃል፤ ከዚህችም ነፍስ ክፋት ትድናለህ።"
:
### በአላህ መገለጫ ባህሪያት (ሲፋት) በተመለከተ ትልቅ መርሆ (ቃዒዳህ)
"ማስጠጋቱ (ኢዳፋህ) ከተለያየ፥ የባህሪያቱ ሁኔታ (ከይፊያህ) ይለያያል።"
ይህ ማለት አንድን ባህሪ ወደ አንድ አካል ስናስጠጋ እና ወደ ሌላ አካል ስናስጠጋ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ግልጽ ይሆናል፦
* የአላህ ፊት እና የፍጡር ፊት፦ "የአላህ ፊት" ስንል ወደ አላህ አስጠጋነው፤ "የፍጡር ፊት" ስንል ደግሞ ወደ ፍጡር አስጠጋነው። ማስጠጋቱ ስለተለያየ የአላህ ፊት በምንም መልኩ ከፍጡር ፊት ጋር አይመሳሰልም።
* የአላህ እጅ እና የፍጡር እጅ፦ ማስጠጋቱ የተለያየ ስለሆነ ፍጹም የተለያዩ ናቸው።
* የአላህ (ዐይን) እና የፍጡር አይን፦ በተመሳሳይ መልኩ ማስጠጋቱ ስለተለያየ አይመሳሰሉም።
* የአላህ ከዐርሽ በላይ መሆን (ኢስቲዋእ) እና የፍጡር በሆነ ነሀር ላይ መደላደል፦ ሁለቱም የተለያዩ ናቸው።
ይህንን ይበልጥ ለማስረዳት በዱንያ እና በጀነት መካከል ያለውን ምሳሌ ወስደናል። ለምሳሌ፦ የጀነት የቴምር ዛፍ እና የዱንያ የቴምር ዛፍ ስንል ስማቸው አንድ ቢሆንም፥ አንደኛው ወደ ጀነት ሌላኛው ወደ ዱንያ በመጠጋታቸው ምክንያት ሁነታቸውና ባህሪያቸው ፍጹም የተለያየ ነው። የጀነት ወንዞች እና የዱንያ ወንዞችም እንዲሁ።
> ዋናው መልዕክት (ማጠቃለያ)፦
> "ማስጠጋቱ (ኢዳፋህ) ከተለያየ፥ የባህሪያቱ ሁነታም ይለያያል።" አላህ ለእርሱ የሚገቡ የላቁ እና ምሉዕ ባህሪያት አሉት፤ ፍጡርም ለእርሱ የሚሆኑ ደካማ ባህሪያት አሉት። በመሆኑም የአላህ ባህሪያት ከፍጡራን ባህሪያት ጋር በፍጹም አይመሳሰሉም።
>
ይህ የኢማም ኢብኑል ቀዪም (አላህ ይዘንላቸውና) ጥቅስ የሚያስተምረን መርሳት ለሰው ልጅ ትልቅ እፎይታ እና እምቅ ችሎታ የተሰጠው መለኮታዊ ጸጋ መሆኑን ነው። መርሳት ባይኖር ኖሮ የሰው ልጅ ያለፈውን መጥፎ ትዝታ፣ ህመም፣ ቁጭትና ሀዘን ሁልጊዜም እንደ አዲስ እያሰበ ህይወቱን መምራት አይችልም ነበር። ማለፍና መርሳት መቻላችን ህመማችን እንዲሻርና ወደፊት እንድንቀጥል ይረዳናል።
Читать полностью…
## በ (ሰላት) ላይ የሚታዩ ስድስት የሙናፊቆች (መናፍቃን) ባህሪያት
ኢማም እብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) መናፍቃን ሰላት በሚሰግዱበት ጊዜ የሚታዩባቸውን ስድስት መጥፎ ባህሪያት እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፡
### 1. ለመስገድ በሚነሱበት ጊዜ ስንፍና ማሳየት (الكسل عند القيام إليها)
ሰላትን ለመስገድ መነሳሳት ማጣት፣ መክበድ እና መዘግየት።
አላህ تعالى
በቁርአኑ ላይ እንደገለጻቸው፡
{وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ} (ወደ ሰላትም በቆሙ ጊዜ ሰነፎች
ሆነው ይቆማሉ)።
### 2. ለይዩልኝ (ሪአእ) መስገድ (الرياء ومراءاة الناس)
ሰላትን የሚሰግዱት ወይም አሳምረው የሚያደርጉት ሰዎች እንዲያዩላቸውና እንዲያደንቋቸው ብቻ ነው፤ የአላህን ውዴታ ፈልገው አይደለም።
### 3. ሰላትን ከወቅቱ ማዘግየት (تأخيرها عن وقتها)
ሰላት የመስገጃው ጊዜ አልፎ እስኪቃረብ ድረስ ሁል ጊዜ ማሳደር እና ማዘግየት፤ ለምሳሌ የዐስርን ሰላት ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል (ወደ ዳልቻ ስትቀይር) ማዘግየት።
### 4. ሰላትን ማጣደፍ (نقرها)
በሰላት ውስጥ የመረጋጋት (ጡማእኒናህ) እጥረት ማሳየትና በጣም ማጣደፍ። ነቢዩ ﷺ ይህንን ድርጊት "ቁራ መሬት ላይ እንደሚጭረው" (ንቅረል ጉራብ) በማለት መስለውታል። በዚህ አይነት ስግደት ውስጥ እውቅናም ሆነ ኹሹዕ (ተመስጦ) አይገኝም።
### 5. አላህን ማውሳት (ዚክር) ማነስ (قلة ذكر الله فيها)
ልብ ሳይገኝ (ሳይተኮር)፣ የቁርአን አንቀጾችንና ዚክሮችን ሳይገነዘቡ እንዲሁ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ብቻ ማድረግ።
### 6. የጀማዐ ሰላትን መተው (التخلف عن جماعتها)
ያለ ምንም (ሸሪዐዊ) ምክንያት እና አቅም እያላቸው የጀማዐ ሰላትን በመስጂድ ከመስገድ ወደ ኋላ ማለት።
> ኢማም እብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፡ "እነዚህ በሰላት ውስጥ የሚታዩ ስድስት ባህሪያት የንፍቅና (መናፍቅነት) ምልክቶች ናቸው።"
📚ኪታቡ አስ–ሰላት ገፅ(80)
>
በሱጁዱ አስ– ሰህው (የመርሳት ሱጁድ) አራት አስፈላጊ መርህዎች
የመጀመሪያው መርሆ፡(ቃዒዳህ) በሶላት ውስጥ ዋጅብ የሆኑ ነገሮችን በመርሳት ሳያደርጉ ካለፉ፤ ከማሰላመት በፊት ሱጁድ ይደረጋል።
ሁለተኛው መርህ(ቃዒዳህ)፡ ሩክን የሆኑ ነገሮችን በመርሳት ሳያደርጉ ካለፉ፤ ያን የረሱትን ሩክን አሟልተው ከዚያ ሶላቱን ጨርሰው ከሰላምታ በኋላ ሱጁድ ያደርጋሉ።
ሦስተኛው መርህ(ቃዒዳህ)፡ በመጠራጠር ላይ የተመሰረተ ሱጁድ ሲሆን በዋነኛው በመጠራጠር (በገመትነውን በመመስረት) ከሰላም በኋላ ሱጁድ ይደረጋል። በትንሹ በመመስረት (የተረጋገጠውን አነስተኛ በመመስረት) ከማሰላመት በፊት ሱጁድ ይደረጋል።
አራተኛው መርሆ(ቃዒዳህ)፡ በሶላት ውስጥ ማንኛውም በመርሳት የተነሳ መጨመር ከሆነ፤ ከማሰላመት በኋላ ሱጁድ ይደረጋል።
«ሰደቃ መከራንና በላእን በመመለስ፣ የሰውን እይን (ክፉ ዓይንን) በመከላከል እንዲሁም የምቀኛን ተንኮልና ሸር በማክሸፍ ረገድ አስደናቂ ተፅዕኖ አላት።»Читать полностью…
(በዳኢዑል ፈዋኢድ 2/234)
🛡️ የአማኞች ጋሻ፦ የአላህን ባህሪያት በቃላት ጨዋታ የማደብዘዝ ሴራ!
ሽብር!
### 📌 “እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባ ታላቅ ነጥብ አለ!
💡በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡትን የጌታችንን (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ባህሪያት በሚያጠራጥር ወይም በሚያሳቅቅ ቃል መግለፅ እውነታውን በፍጹም አይቀይረውም!
ኢማም አሕመድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለው ነበር፦
> « ..وَلَا نُزِيلُ عَنْهُ صِفَةً مِنْ صِفَاتِهِ لشَنَاعَةٍ شُنِّعَتْ.. »
> *“የሚፀየፍ ተፀይፎ ስላወገዘ (ብለን) ከባህሪያቱ አንዱንም አንገፍፍም (አናስወግድም)!”*
> 📄 [“አል-ኢባና” ሊ’ብኒ በጣህ (3/326)፤ “ዘም-ሙ’ት-ተእዊል” ሊ’ብኒ ቁዳማህ፣ ገፅ 22]
>
### 🔍 የ“ተዕጢል” (የአላህን ባህሪያት አስተባባዮች) ስልት ምንድን ነው?
በአቀንቃኞቹ ንግግር ላይ *“አላህ ለራሱ ያፀደቃቸውን ባህሪያት አንቀበልም!”* የሚል ቀጥተኛ የማስተባበያ ገለፃ ላይገኝ ይችላል። ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ ለዚህ ዓላማ መንገዱን የሚደለድሉት ባህሪያቱን ያለ አደብ በተለያዩ ፍልስፍናዊ ቅፅላዎች እየጠሩ እውነታውን በማድበስበስ ነው!
*(በሀገራችን ብሂል፦ «ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ‘ጅግራ’ ይሏታል» እንደሚባለው!)*
ባህሪያቱን ለማስተባበልና ሰዎችን ለማሸበር የሚጠቀሙባቸው ስያሜዎች፦
* አዕራድ (أَعْرَاض)፦ እንደ መስማትና ማየት ያሉትን የአላህ ባህሪያት።
* አዕዷእ (أَعْضَاء) ወይም ጀዋሪሕ (جَوَارِح)፦ እንደ ፊትና እጅ ያሉትን ባህሪያት።
* ሐዋዲሥ (حَوَادِث)፦ እንደ ንግግር ያሉ ሲፈልግ የሚፈፅማቸውን አድራጎቶች።
* ተሐይ-ዩዝ (تَحَيُّز)፦ “አስቲዋእ”ን (በዐርሹ ላይ መሆኑን) እና ከፍጥረተ ዓለሙ በላይ መሆኑን።
* አግራድ (أَغْرَاض)፦ ከውሳኔውና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉትን ጥበቦችና ዓላማዎች።
### ⚠️ የማደናገሪያው ጥግ
እነዚህን ቃላትና መሰሎቻቸውን የሚተረጉሙት በመሠረታዊው ቋንቋዊ መልዕክታቸው ሳይሆን፣ በተምታታ ፍልስፍናዊ ይዘታቸው ነው።
በዚህም ሳይበቁ፤ የአላህን ባህሪያት ከማመሳሰል (ተሽቢህ) በፀዳ መልኩ በቁርኣንና በሐዲሥ እንደተገለፁት በቀጥታ የሚቀበሉትን የሐቅ ባለቤቶች (አህሉስ-ሱናህን)፦ *“አላህን በእነዚህ አሸማቃቂ መገለጫዎች ይገልፃሉ!”* እያሉ በቅጥፈት ይወርፋሉ።”
📚 ምንጭ፦ የአማኞች ጋሻ — ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ (ገፅ 93)
*
/channel/sultan_54
ቁርኣንን በተሳሳተ መንገድ መረዳት የሚያስከትለው አደጋ!
ቁርዓንን በትክክል የመረዳትን እጅግ አንገብጋቢ አስፈላጊነት መገንዘብ ግድ ይላል።
ቁርኣንን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ለኡማው (ለህዝበ ሙስሊሙ) መጥፋት፣ መከፋፈል፣ መናቆር፣ እና ከመስመር መውጣት ምክንያት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።
ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር፤ አህሉ-ሱናዎች ቁርዓኣንን በሱና (በነብዩ ሐዲስ) እንደሚተረጉሙ ነው፤ ለዚህም ነው "አህሉ-ሱና" ተብለው የተሰየሙት።
በተለየ ቡድን ስም አልተጠሩም፤ "ሙተከሊሚን" (የከላም/የፍልስፍና ሰዎች)፣ "አሽዓሪያ"፣ "ማቱሪዲያ" ወይም "ሱፊያ" ተብለው አልተሰየሙም። በፍጹም! ከ"ሱና" ውጪ ሌላ ስም የለንም።
قال الإمام مالك رحمه الله: أهل السنة الذين ليس لهم لقب يعرفون به، لا جهمي ولا قدري ولا رافضي."
— [الانتقاء لابن عبد البر، ص 35]
## የአያሙ አት-ትሽሪቅ (ሑጃጆች ሚና ላይ የመቆያ ቀናት) ትርጉምና ደረጃ
ምስጋና ለአላህ ይሁን። የአያሙ አት-ትሽሪቅ ቀናት ማለት አላህ በቁርኣኑ፦ "አላህንም በታወቁት (በተቆጠሩት) ቀናት ውስጥ አውሱት" (አል-በቀራህ፡ 203) በማለት የጠቀሳቸው ቀናት ናቸው። እነሱም ከዕርዱ ቀን (ከዒድ አል-አድሃ) በኋላ ያሉ ሶስት ቀናት ሲሆኑ፤ 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት ናቸው።
ከእነዚህ ቀናት ውስጥ በላጩ መጀመሪያው ቀን (11ኛው ቀን) ነው። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
> "አላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ የላቀው ቀን የዕርዱ (የዒድ) ቀን ነው፣ ከዚያም ‘የቀር’ር’ (ሑጃጆች ሚና ላይ የሚቆዩበት ቀናት) ቀን ነው"
>
እሱም 11ኛው ቀን ነው።
## የእነዚህ ቀናት ትሩፋት እና ተግባራት
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
> "የዐረፋ ቀን፣ የዕርዱ ቀን እና የአያሙ አት-ትሽሪቅ ቀናት ለእኛ ለኢስላም (ህዝቦች) በዓሎቻችን ናቸው፤ እነሱም የመብያና የመጠጫ ቀናት ናቸው።"
>
ስለሆነም በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚከተሉትን ማድረግ ይደነገጋል (ይወደዳል)፦
* አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ)፦ የእስልምናን መገለጫዎች ማሳየት፣ መደሰት እና ሀሴት ማድረግ።
* ዝምድናን መቀጠል፦ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር መዘያየር።
* የተገደበ ተክቢራ (አት-ተክቢር አል-ሙቀየድ)፦ ከግዴታ ሶላቶች በኋላ የሚደረገው ተክቢራ እስከ 13ኛው ቀን የዐስር ሶላት ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል።
* አጠቃላይ ተክቢራ (አት-ተክቢር አል-ሙጥለቅ)፦ በማንኛውም ሰዓት፣ ሁኔታ እና ቦታ ላይ የሚደረገው ተክቢራም እንዲሁ ይቀጥላል።
* የኡድሂያ እንስሳትን ማረድ፦ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የዒድ መሥዋዕት ይታረዳል።
* መጾምን መከልከል፦ በእነዚህ ቀናት መጾም አይፈቀድም፤ ነገር ግን (በሐጅ ላይ ሆኖ) የመሥዋዕት (ሀድይ) እንስሳ ማቅረብ ላልቻለ ሰው ብቻ መጾም ይፈቀድለታል።
ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ለመቃረብ በማሰብ ማረድ (መስዋት ማድረግ) ከገንዘብ ኢባዳዎች ሁሉ በላጩ ነው::
Читать полностью…
#Eid_Aladha1447
🌺 عيدكم مبارك! 🌺
🔶 🌸Eid Mubarak! 🌸 🔶
🌹 ዒድ ሙባረክ! 🌹
🤲تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🤲
🤲ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን🤲
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
@sultan_54
ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል!
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐ «የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)
ያስታውሱ ዛሬ ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን (የውሙ አት–ተርዊያ) ሑጃጆች የሐጅ ስራቸውን የሚጀምሩበት እለት ነው።
የነገው ዘጠነኛው ቀን የውሙ ዓረፋ ነው። ሑጃጆች በዓረፋ ምድር የሚቆሙበት ለነሱም ይሁን ለሌላው ሙስሊም ማህበረ–ሰብ እጅግ ልዩ የዒባዳ ቀን ነው።
በጾም፣ በዚክር በተለይ ተክቢራ እና ዱዓእ እንድንጠቀምበት ልንተዋወስ እና አንዳችን ሌለኛውን ሊያበረታታ ይገባል።
የነገውን ቀን ጾም በተመለከተ ከላይ በጠቀስነው ሀዲስ ላይ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያለፈውን እና የመጪውን አመት ወንጀል ያሰምራል ማለታቸው ይህን እለት በጉጉት እንድነጠብቀው ያደርጋል።
ከጾም ውጪ በዚህ ቀን ልዩ በሆነ መልኩ ልናደርጋቸው የሚወደዱ ነገሮችን በተመለከተ በተከታይ ጽሁፎች ኢንሻ አላህ ለመጠቆም እሞክራለሁ።
ወደ መልካም አመላካች እንደ ሰሪው ምንዳ አለው!!
ለሌሎችም መልእክቱን እናስተላልፍ
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 /channel/tahaahmed9
##"የዓረፋ ቀን በዓል (ዒድ) መሆኑን ያውቃሉን? አዎ!
እሱማ አላህ ዲኑን የሞላበት፣ ጸጋውንም ያጠናቀቀበት ቀን አይደለምን? ይህ የሆነው ደግሞ ከብዙ የተውሂድ አንቀጾች፣ ከታሪኮች፣ ከሕግጋቶችና ከነቢያዊ ሐዲሶች ረጅም ሰንሰለት በኋላ ነው።
ይህ በዓል ለሙስሊሞች ዘንድ እጅግ ታላቅ መሆኑን ማስታወስና ማስተንተን ይገባል። እንዲያውም አንድ አይሁዳዊ (ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ) እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ *‘እኛ የይሁዳ ማኅበረሰቦች ላይ እንዲህ ዓይነት አንቀጽ (አያህ) ወርዶ ቢሆን ኖሮ፣ ያንን ቀን የበዓል ቀን (ዒድ) አድርገን እንይዘው ነበር።’* ዑመርም (ረዲየሏሁ.ዐንሁ) እንዲህ ሲል መለሱለት፦ *‘እኔ ይህች አንቀጽ( ማለትም፦"...ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፤ ለእርናንተም እስልምናን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ..." (አል-ማኢዳህ: 3)
በየትኛው ቀን በነቢዩ (ﷺ) ላይ እንደወረደች ጠንቅቄ አውቃለሁ፤ እሷም የወረደችው በዓረፋ ቀን ነበር።’*"
#ዒድ_ዐረፋ#ዙልሒጃ
ቃላት ፍርድ አላቸው።
በሸሪዓ ሚዛን "ሙስሊም አይደለሁም" የሚሉ ግልጽ ቃላት እንደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ወይም እንደ ምሳሌያዊ አነጋገር አይታዩም። ይልቁንም ቀጥተኛ የእምነት ክህደት መግለጫ ናቸው። አንድ ሙስሊም ከእውነተኛ ማስገደድ ውጭ ይህንን ለማድረግ መብት የለውም።
## 🌟 የዓረፋ ቀን እና የዕርድ ቀን (የዒድ ዕለት) ታላቅነት!
ምስጋና ለአላህ ይሁን። የዓረፋ ቀን በአላህ (ዓዘ ወጀል) ዘንድ እጅግ ታላቅ ቀን ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም) በትክክለኛ ሐዲሳቸው እንዲህ ብለዋል፦
> *“አላህ በዓረፋ ቀን ከእሳት ነፃ የሚያወጣቸውን ያህል ባሮችን (ከእሳት) ነፃ የሚያወጣበት ሌላ ምንም ቀን የለም።”*
>
የአንዳንዶቹ የዓሊሞች አባባል እንደሚያመለክተው፣ አላህ በቁርአኑ “በመስካሪውና በተመሰከረበትም እምላለሁ” (وشاهد ومشهود) ሲል የፈለገበት ‘የተመሰከረበትን ዕለት’ ማለትም የዓረፋን ቀን ነው። እሱ ፀሐይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጩ ቀን ነው። በዚህ ዕለት ከሚደረግ ዱዓእ የበለጠ በአላህ ዘንድ ታላቅ የሆነ የለም። የአላህ መልዕክተኛም ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም))፦ *“ከዱዓእ ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን ዱዓእ ነው”* ብለዋል።
የዓረፋ ቀን ትሩፋትና የአላህን ችሮታ ማግኘት ሑጃጁንም (ሐጅ ላይ ያለውን) ሆነ ሀገር ላይ ያለውን (ሐጅ ያላደረገውን) እኩል ያጠቃልላል። ሑጃጆች በዓረፋ ሜዳ ላይ በመቆም ታላቁን የሐጅ (ሩክን) ማዕዘን ይፈጽማሉ፤ ነቢዩ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም)) *“ሐጅ ማለት ዓረፋ ነው”* እንዳሉት። ሐጅ ያላደረጉት ደግሞ የዓረፋን ቀን በመጾም ወደ አላህ መቃረቢያን ይሻሉ። ይህንንም ጾም የአላህ መልዕክተኛ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም)) እንደተናገሩት፦ ያለፈውን አንድ ዓመትና የሚመጣውን አንድ ዓመት (በድምሩ የሁለት ዓመት) ወንጀል ያስተሰርያል ብለው ከአላህ ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉ።
ስለሆነም እሱ በረከቱ አጠቃላይ፣ ትሩፋቱ ታላቅ፣ ምሕረቱና እዝነቱ የሰፋ፣ ከእሳት ነፃ የመውጫ ቀን ነው። ይህ ቀን ከዱንያ ቀናት ሁሉ በአላህ ሚዛን ዘንድ እጅግ ከባድ ቀን ነው። ወደ ዓረፋ ቀን ከተመለከትክና “በነዚህ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ውስጥ ከዓረፋ ቀን በስተቀር ሌላ ቀን ባይኖር እንኳ፣ የአስሩን ቀናት በላጭነት ከሌላው የዓመቱ ቀናት ሁሉ በላይ ለማስበለጥ በቂ በሆነ ነበር” ብትል እውነት ነው። ታዲያ ከላይ የተጠቀሱት ታላላቅ ትሩፋቶች ሁሉ ተደምረውበትማ እንዴት አይበልጥ?! እነኚህ ቀናት አላህ ሐጅን ያዘዘበትና ሑጃጆች የአምልኮ ሥርዓታቸውን የሚፈጽሙባቸው የታወቁት ቀናት ማጠቃለያ ናቸው። ይህም አላህን ለማውሳትና በነዚህ ቀናት ውስጥ ያሉትን ጥቅሞች ለመታደም የተደነገገ ነው።
በመቀጠልም የአስሩ ቀናት ማሳረጊያ (አሥረኛው ቀን) የሆነው የዕርድ ቀን (يوم النحر) ይመጣል። እሱም በምሥራቅም ሆነ በምዕራብ ያሉ የሙስሊሞች ኡማህ በደስታ የሚሞሉበት ታላቅና የተባረከ የዒድ ቀን ነው። ይህ ቀን በአላህ ዘንድ እጅግ ታላቅ ከሆኑ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። ነቢዩ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)) እንዲህ ብለዋል፦
> *“በአላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ ታላቁ ቀን የዕርድ ቀን (የዒድ ዕለት) ነው።”*
>
ይህ የአላህ መልዕክተኛ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)) የተናገሩት ፍፁም የሆነ ማበላለጥ (تفضيل مطلق) ነው። ይህ ፍፁም ማበላለጥ የዒድ ቀንን በናፍቆት የምትጠብቀው ታላቅ ቀን አድርገህ እንድትይዘው ያደርግሃል። ይህ በታላቁ ጌታህ ዘንድ ከሁሉ የበላይ የሆነ ታላቅ ቀን ከሆነ፣ በአላህ ይሁንብህ! አንተ በዚህ ቀን ምን ልትሠራ ተዘጋጅተሃል?! በአላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ በላጭ በሆነው ቀን ምን ታደርጋለህ?
አላህ በዚህ ቀን ተክቢራን ደንግጎልሃል፣ የዒድ ሰላትን ደንግጎልሃል፣ የምታርደውን ኡድሒያ (ዕርድ) ደንግጎልሃል። ለሙስሊሙ ኡማህ በሙሉ፤ ሑጃጁንም ሆነ ሌላውን፣ አላህን በማክበር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አላህን እንዲያወድሱ፣ ተክቢራ፣ ተህሊልና ተሕሚድ እንዲያደርጉ ደንግጓል።
የሙስሊሙ ኡማህ ሑጃጁም ሆነ በሀገሩ ያለው ሁሉ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንድ ድምፅ ይሰበሰባል። ምድር በሙሉ ለታላቁ ጌታችን በምናደርገው ተክቢራ፣ ተህሊልና ተሕሚድ ትናወጣለች፣ በድምፅም ትሞላለች። በእርግጥም የሙስሊሙ ኡማህ የዚህን ቀን ታላቅነት በአምልኮ ሥርዓቱ፣ በሸሪዓው፣ በዓቂዳውና በባህሉ ላይ ያንጸባርቃል። በዚህም የሙስሊሙ ኡማህ አረብም ሆነ አረብ ያልሆነው፣ ታናሹም ታላቁም፣ ወንዱም ሴቱም ሁሉ በአንድ ሰው ልብ ላይ ሆነው በአንድ ድምፅ እንዲህ ይላሉ፦
> الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله
> الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
> *(አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሀ ኢልለላህ፣ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ)*
>
🚩 @ /channel/sultan_54
የታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ዕንቁ ምክር፦
“ኢማን በልብ ውስጥ የሚገኝ ደስታ፣ ጥፍጥና እና እርካታ አለው።
አንድ ሰው የአምልኮ ተግባራትን በሚፈጽምበት ጊዜ ያንን ጣፋጭና መንፈሳዊ የደስታ ቃና ካላገኘ፣ ኢማኑን አጥቷል ወይም ጎድሏል ማለት ነው!»
📔 አር-ሪሳላህ አት-ተቡኪይያህ (7)*Читать полностью…