14074
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
ሐሰን አል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
> "አንድ ሰው ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ (መማር) ከጀመረ፣ ብዙም ሳይቆይ የዒለሙ ተፅዕኖ (ፍሬ) በሰላቱ፣ በዕርጋታውና በውስጥ ፍርሃቱ (በኹሹኡ)፣ በንግግሩ እንዲሁም በጠቅላላ ባህሪው ላይ መታየቱ አይቀርም ነበር።"
>
📚 ምንጭ ሚን ሀድዪ አስ-ሰለፍ ፊ ጠለቢል ዒልም — ሊል-ዘህራኒ
ኢብን ጀሪር አጥ-ጦበሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ቁርኣንን እያነበበ ፍቺውንና ማብራሪያውን (ተፍሲሩን) በማያውቅ ሰው በእጅጉ እገረማለሁ፤ ለመሆኑ እንዴት በንባቡ ብቻ ሊደሰት (ጣዕሙን ሊያገኝ) ይችላል?!"
"«ጌታህም በእርግጥ ይሰጥሃል፤ ትደሰታለህም።» (ዱሃ፡ 5)
ከላቀውና ከፍ ካለው አላህ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ ለምኑ፤ በባዶ እጃችሁም አይመልሳችሁም። ስለ ኑሯችሁ ተናገሩ፤ ልባችሁ ምን እንደሚመኝም ንገሩት። የመልሱን ብርሃን በአይናችሁ እንደምታዩት ሁሉ አጥብቃችሁ ዱዓ አድርጉ።
እርሱ አላህ ነውና... ይሰማችኋል፣ የልባችሁን ስብራት ይጠግናል፣ ያከብራችኋል፣ ያበለጽገናልም፤ የልብ ስብራት መለስለስንና የደስታን ጣዕም እንድንቀምስም ያደርገናል።❤️
### የጀመዓ ሰላት ደረጃ እና ትሩፋት
2. የመላእክት ዱዓ!
ሁለተኛው ታላቅ ደረጃ— በቡባኻሪ እና ሙስሊም በሰፈረው መሠረት—አንድ ሰው መስጂድ በገባ ጊዜ መላእክት ለእርሱ ዱዓ ያደርጉለታል፦ *'አላህ ሆይ! ይህንን ባሪያህን ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት...'* እያሉ ከሰላት በፊት፣ በሰላት ውስጥና ከሰላት በኋላም ጭምር—እንኳን ለአንድ ሰዓት ለ10 ሰዓታት ያህል ብትቀመጥ እንኳ—በመስገጃህ ላይ እስካለህና ውዱእህ እስካልጠፋ ድረስ መላእክት ዱዓ ማድረጋቸውን አያቋርጡም።
ከቀደሙት የሻፊዒይ መዝሃብ ሊቃውንትና የቡኻሪ ሻሪሕ የሆኑት ኢብኑ በጣል (ረሒመሁላህ) የተናገሩት ውብ ንግግር ምንኛ ያምራል! እንዲህ ብለዋል፦
> *'ወንጀሉ የበዛበት ሰው በማንኛውም ቀን በመስጂዶች ውስጥ መቆየትን ያብዛ። በአንድ ግዴታ ላይ ጉድለት ካጋጠመህ፣ ወይም በትንሽም ሆነ በትልቅ ወንጀል ላይ ከወደቅህ፣ በዚያ ቀን ወደ መስጂድ መገስገስንና እዚያ መቆየትን አዘውትር። ለምን ካልክ? መላእክት ላንተ ዱዓ እንዲያደርጉልህ ዕድሉን ታገኝ ዘንድ ነው።'*
• قال أبو سليمان الداراني -رحمه الله-:
«لو أن الدنيا كلها في لقمة، ثم جاءني أخ لي، لأحببت أن أضعها في فيه».
الأخوّة
### የጀመዓ ሰላት ደረጃ
"የጀመዓ ሰላት! በማንኛውም ቀን—እንኳን ለአንድ ሰላት ይቅርና—ከጀመዓ ሰላት ወደ ኋላ ባልህ ቁጥር፣ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ፣ ክርክርና እንከን የሌለባቸውን አምስት (5) ታላላቅ ትሩፋቶችን፣ ደረጃዎችንና ምንዳዎችን በሶሒሕ ማስረጃዎች አስታውስሃለሁ። ከእነዚህም ውስጥ አራቱ በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገቡ ሲሆን፣ አንዱ ደግሞ ከሁለቱ ሶሒሕ መጻሕፍት ውጪ የተዘገበ ነው።
በማንኛውም ቀን ከጀመዓ ሰላት ወደ ኋላ ባልህ ቁጥር፣ አዛን ሰምተህ መጥፎን አዛዥ የሆነችው ነፍስህ እንድትተኛ ወይም የጀመዓ ሰላትን እንድትተው ስትገፋፋህ፣ በአንድ ሰላት ወይም በአንድ ቀን ውስጥ ልታጣቸው የምትችላቸውን እነዚህን አምስት ታላላቅ ነገሮችና ደረጃዎች አስታውስ።
አንዳንድ ሰዎች ስለ ጀመዓ ሰላት ደረጃ ከአንድ ሐዲስ ወይም ከአንድ ደረጃ ውጪ አያውቁም። እሱም፦ *'የጀመዓ ሰላት ከነጠላ ሰላት በ25 ደረጃ ይበልጣል'* የሚለውን ሲሆን፣ በሌላ ዘገባ ደግሞ *'በ27 ደረጃ ይበልጣል'* የሚል ነው። አሁን ግን አምስቱን ታላላቅ ደረጃዎች ስማ፦
### 1. የእርምጃዎች ምንዳ (አጅር)
የመጀመሪያው ደረጃ፣ መስጂድ ሄዶ በሚሰግድ ሰው የሚገኝና ቤቱ በሚሰግድ ሰው ደግሞ የሚታጣው የእርምጃዎች ምንዳ ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በቡኻሪና ሙስሊም በሰፈረውና ከአቡ ሁረይራ በተዘገበው ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፦
> *'አንድ ባሪያ ውዱእን አሳምሮ አድርጎ ወደ መስጂድ ቢወጣ፣ ከሰላት ውጪ ሌላ ነገር ካላስወጣው፣ አላህ በእያንዳንዱ እርምጃው አንድ ሐሰና (መልካም ሥራ) ይጻፍለታል፣ አንዲት ወንጀልንም ይታበስለታል።'*
>
ከቤትህ ስትወጣ ከመጀመሪያው እርምጃህ ጀምሮ አንድ መልካም ሥራ ይጻፍልሃል፣ አንድ ወንጀልህም ይረግፋል። ሁለተኛው እርምጃህ መልካም ሥራ ነው፣ ሶስተኛውም እንዲሁ፣ እስከ ሰፉ (መስመር) ድረስ። ቤትህ ከመስጂዱ 100 እርምጃ ይርቃል ብንል—በአሁኑ ጊዜ ከ70 ወይም 80 እርምጃ በታች የሚርቅ ሰው የለም—100 እርምጃ ነው ብንል እንኳ 100 መልካም ሥራ ታገኛለህ፣ 100 ወንጀልም ይታበስልሃል። ስትመለስም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው።
አንድ ሰው 'ለመመለሻውም እንደሚታሰብ ምን ማስረጃ አለ?' ቢል፣ አዎ! ሌላ የተለየ ማስረጃ አለን። እሱም በሁለቱ ሶሒሕ መጻሕፍት የተዘገበው የአንሷሪው ሰው ሐዲስ ነው። ከባሕርይው የተነሳ ከእርሱ የበለጠ ከነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መስጂድ የራቀ ቤት ያለው አልነበረም፣ ሆኖም አንድም ሰላት አያመልጠውም ነበር። 'ከቀኑ ሐሩርና ከክረምቱ ቅዝቃዜ የምትጠብቅህ የ (ጋማ ከብት) ብትገዛ ምን አለበት?' ተብሎ በተጠየቀ ጊዜ፣ እርሱም፦ *'እኔ ወደ መስጂድ መሄዴንም ሆነ ወደ ቤተሰቦቼ መመለሴን አላህ ዘንድ ይታሰብልኝ ዘንድ ነው የምፈልገው'* አለ። ንግግሩ ለነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በደረሰ ጊዜ *'አላህ ይህንን ሁሉ ሰብስቦ ሰጥቶሃል'* ብለው እንዲያበስሩት አዘዙ። ስለዚህ ይህ መሄድና መመለስ 200 መልካም ሥራና 200 ወንጀል መታበስ ይሆናል።
በእስልምና ደግሞ አንድ መልካም ሥራ በአንድ ብቻ አይታሰብም። በአስር (10) ነው፤ እርግጠኛ ናችሁ? እራሳችሁን መልሳችሁ ፈትሹ። የአንዳንድ ሰዎች ስህተት መልካም ሥራ በአስር ብቻ ይባዛል ብለው ማሰባቸው ነው። በእስልምና አንድ መልካም ሥራ በአንድ፣ በስምንት ወይም በዘጠኝ የሚባዛበት ሥርዓት የለም። ነገር ግን መልካም ሥራ ከአስር ይጀምርና እስከ 700 ሺህ እጥፍ ድረስ ያድጋል። ለዚህም ማስረጃው በቡኻሪ የተዘገበው ሐዲስ ነው፦ *'የአንድ ባሪያ እስልምና ካማረ፣ አላህ ለእርሱ እያንዳንዱን መልካም ሥራ ከአስር እጥፍ እስከ ሰባት መቶ እጥፍ፣ ከዚያም በላይ በብዙ እጥፍ ይጽፍለታል፤ አላህም ለሻው ሰው ያባዛል።'* የባሪያው እስልምና ማማር፣ ቀጥ ማለቱ፣ እውነተኝነቱና እኽላሱ አላህ ሥራውን እንዲያባዛለት ያደርጋል። ይህ ሰው በአንድ ሪያል ይመጸውታል፣ ያኛውም በአንድ ሪያል ይመጸውታል፤ ነገር ግን ለዚህኛው 10,000 መልካም ሥራ ሲጻፍለት፣ ለሌላኛው ደግሞ 1,000 መልካም ሥራ ሊጻፍለት ይችላል። ይህ የሆነው ከሀሜት በራቀውና ከልብ ፍላጎት በማይናገረው በነቢዩ ንግግር መሠረት ነው።
ስለዚህ እነዚህን 200 እርምጃዎች በአስር ብናባዛቸው 2,000 መልካም ሥራዎች ይሆናሉ። በቀን ስንት ሰላት አለን? አምስት ሰላቶች። የብርና የዲናር ባለቤቶች የት አላችሁ? 2,000 ሲባዛ በአምስት ስንት ይሆናል? 10,000 መልካም ሥራዎች ይጻፉልሃል፣ 10,000 ወንጀሎችም ይታበሱልሃል። በአላህ እምላለሁ! ይህ የተመረጡት ነቢያችሁና የተወደዱት መልእክተኛችሁ ንግግር ነው። ሰላትን ለመተው በታከትክ ቁጥር የእርምጃዎችን ምንዳ አስታውስ። ዛሬውኑ በተግባር ሞክረው፤ ከቤትህ ወጥተህ ዘወትር ወደምትሰግድበት የሰፈርህ መስጂድ ስትሄድ ስንት እርምጃ እንደሆነ ቁጠር፣ ከዚያም በሁለት አባዛው፣ በመቀጠልም በአስር አባዛው፤ በአንድ ሰላት ውስጥ ብቻ ምን ያህል መልካም ሥራ እንደምታጣ ታውቀዋለህ።
በታሪክ እንደተረጋገጠው የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አገልጋይ የነበሩትና ብዙ ሐዲሶችን በመዘገብ ከሚታወቁት አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እርምጃዎቻቸውን ያቀራርቡ ነበር። ታቢዒዮችም 'ለምንድን ነው እንዲህ የምታደርገው?' ብለው በጠየቋቸው ጊዜ፣ እርሳቸውም፦ *'እርምጃዎቼ እንዲበዙልኝ ስል ነው'* ብለው መልሰዋል። ይህ እንግዲህ ሸሪዓው ከሚፈቅዳቸውና ከሚቀበላቸው መልካም ብልሃቶች (ሒየል) በኩል ነው —ምክንያቱም በአንዳንድ ብልሃቶች ባለቤታቸው ላይ ጥፋትን የሚያስከትሉ ሲሆኑ፣ በሸሪዓው የተፈቀዱና በማስረጃ የተደገፉ ብልሃቶች ግን አሉ።
ይቀጥላል…
"በቁርአን ውስጥ ከአላህ ውጭ ያለን አካል መለመንን (እነሱን መማፀን) የሚከለክሉ፣ ድርጊቱንም የሚያወግዙ እና በባለቤቱ ላይ በሽርክ የሚፈርዱ።ከአርባ በላይ አንቀጾችን አግኝቻለሁ፤
**እንዲሁም ከሃያ በላይ የሚልቁ አንቀጾችን አላህን ብቻ መለመንን የሚያዙ፣ በእሱ ላይ የሚያበረታቱ እና አድራጊውን የሚያወድሱ። ሆነው አገኘሁ።”
✍— *ሸይኽ ሷሊህ አስ–ሲንዲ (አላህ ይጠብቃቸው)*
«ለኢብኑል ሙባረክ (አላህ ይዘንላቸውና)፦ “ከዕድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው ቢባሉ ምን ያደርጉ ነበር?” ተብለው ተጠየቁ፤ እሳቸውም፦ “ሰዎችን አስተምር ነበር” ብለው መለሱ።»
ምንጭ: በበይሀቂ (አል-መድኸል [2/45]) የተዘገበ።
ስለ "ዐቂቃህ" ከሀ እስከ ፐ፡ ማወቅ የሚገባዎ አጠቃላይ መመሪያ!
## 1. መግቢያ እና ትርጓሜ
* ዐቂቃህ ማለት ምን ማለት ነው? ለወንድ ወይም ለሴት ልጅ መወለድ ምስጋናን ለመግለጽ ሲባል የሚታረድ ልዩ የ”እርድ” ዓይነት ነው።
* የስያሜው ምስጢር፦ * “ዐቂቃህ” የሚለው ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት፤ የሚታረደው እንሰሳ የምግብ፣ የመጠጥና የአየር ማስገቢያና ማስተላለፊያው (ጉሮሮው) ስለሚቆረጥ ነው።
* በተጨማሪም “ተሚማህ” የሚል ስያሜ አለው፤ ይህም ዐቂቃህ የተደረገለት ልጅ ሥነ-ምግባሩ የተሟላ ይሆናል ከሚል እምነት የተነሳ ነው።
## 2. የ“ዐቂቃህ” ሸሪዓዊ ብይን (ሑክም)
* ዐቂቃህ በሸሪዓዊ ፍርድ “ሱናህ” (የተወደደ) የሚለውን ቦታ ይይዛል።
* ነገር ግን አቅም ያለው ሰው ሳይፈጽመው ቢቀር ይጠላል፤ እንዲያውም “ዋጂብ” (ግዴታ) ነው ያሉ ዑለማዎችም አሉ።
* ዐቂቃን አስመልክቶ ከሰላሳ በላይ ሐዲሶች ተዘግበዋል። ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
> “ልጅ የተወለደለትና ለእርሱ ማረድ (መስዋዕት ማድረግ) የፈለገ ሰው ይፈጽም።” *(አቡ ዳውድ)*
>
* የሐዲሱ ጽንሰ-ሐሳብና ጥቅሞች፦
* ዐቂቃ የተደረገለት ልጅ ደስተኛና ነፃ ይሆናል።
* ወላጅና ኃላፊ የሆኑ ሰዎች ለልጁ ዐቂቃ ካላደረጉ፣ ልጁ በዕለተ-ቂያማህ ለቤተሰቡ አማላጅ (ሸፋዓ) አይሆንም።
* ዐቂቃህ ከልጁ ጋር የማይፋታ እዳ መሆኑን ለመጠቆም በሐዲሱ ላይ *“እያንዳንዱ ህጻን በዐቂቃው የታገተ ነው”* የሚል የአፅንኦት ቃል ተጠቅሷል።
## 3. የእንስሳቱ ዓይነት፣ ዕድሜና የዕርድ ብዛት
### ሀ. ለወንድ እና ለሴት ልጅ የሚታረደው መጠን፡
* ለወንድ ልጅ፦ ሁለት በግ። (ሁለቱ በጎች በአካል መጠናቸውና በዕድሜያቸው ተቀራራቢ ቢሆኑ ተመራጭ ነው) ።
* ለሴት ልጅ፦ አንድ በግ።
> ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)) እንዲህ ብለዋል፦ *“ስለ ወንድ ልጅ እኩል የሆኑ ሁለት በጎች፣ ስለ ሴት ልጅ ደግሞ አንድ በግ ይታረዳል::”* *(አቡ ዳውድ/አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)*
>
### ለ. ለዐቂቃ የሚሆኑ እንስሳትና የዕድሜ መስፈርት፡
ለዐቂቃ የሚሆኑት የቀንድ ከብቶች (የቤት እንስሳት) ሲሆኑ የእድሜ ገደባቸው እንደሚከተለው ነው፦
| የእንስሳው ዓይነት | ሊኖረው የሚገባው አነስተኛ ዕድሜ |
|---|---|
| ግመል | 5 ዓመት የሞላው |
| በሬ / ላም | 2 ዓመት የሞላው |
| ፍየል | 1 ዓመት የሞላው |
| በግ | 6 ወር የሞላው |
## 4. የዐቂቃ ጊዜና ሥነ-ሥርዓት
* የመታረጃው ጊዜ፦ ዋናው ሱናው ህጻኑ በተወለደ በሰባተኛው ቀን ማረድ ነው።
* *ምሳሌ፦* ልጁ እሑድ ከተወለደ ዐቂቃው ቅዳሜ ቀን ይሆናል።
* አስፈላጊ ማሳሰቢያ፦ ዐቂቃ ማለት እርድ የተፈፀመበት ዕለት እንጂ ሥጋው የተበላበት ቀን ማለት አይደለም። (ስለዚህ በሰባተኛው ቀን አርዶ ሥጋውን በሌላ ቀን ማዘጋጀትና መጋበዝ ይቻላል)።
* አስፈላጊ ዚክር፦ በሚታረድበት ጊዜ በልዩ ሁኔታ በአፍ የሚባል የተለየ ዚክር የለም፤ ባለቤቱ “በልቡ ዐቂቃ መሆኑን ነይቶ” “ቢስሚላህ አላሁ አክበር” በማለት ያርዳል።
## 5. የሥጋ ክፍፍልና ማኅበራዊ ጉዳዮች
* የሥጋው አጠቃቀም፦ ለራስ (ለቤተሰብ ብቻ) መመገብ፣ ወይም ጓደኞችንና ዘመዶችን ጠርቶ መጋበዝ፣ አሊያም ለድሆች በሰደቃ መልክ ማከፋፈል ይቻላል።
* ዋና ማሳሰቢያ፦ የበጉን ዋጋ (ክፍያ) ለሌላ ሰው በሰደቃ መልኩ ሰጥቶ “አርድልኝ” ማለት አይፈቀድም። ምክንያቱም ባለቤቱ ራሱ (ወይም ወኪሉ) በእጁ ደም በማፍሰስ ወደ አላህ ሊቃረብ ስለሚገባ ነው።
* ለተጋባዦች ዐቂቃ መሆኑን በግልጽ መናገር ግዴታ ባይሆንም፣ ቢነገራቸው ግን ለልጁ ዱዓእ ሊያደርጉለት ስለሚችሉ የተሻለ ነው። (ነገር ግን ካበላ በኋላ “ዱዓእ አድርጉ” ብሎ መጠየቅ የለበትም) ።
## 6. የተለያዩ ወሳኝ አሕካሞች (ሕግጋት)
* በተለያዩ ቀናት ማረድ፦ ሁለት በግ በአንዴ ማግኘት ያልቻለ ሰው፣ አንዱን ካገኘ ማረድ ይበቃለታል፤ ሁለቱን በጎች በተለያዩ ቀናት ማረድ ይፈቀዳል።
* የእናት ሚና፦ ወላጅ አባት በሕይወት ከሌለ፣ እናት አባትን ወክላ ማረድ ወይም ማሳረድ ትችላለች።
* ካደገ በኋላ ማረድ፦ ልጅ ዐቂቃ ሳይደረግለት ካደገ፣ የአባት ግዴታ/ሱና ቢሆንም እንኳ ልጁ ለራሱ ማረድ ይፈቀድለታል።
* ስለ ቅርጫ፦ ለዐቂቃ በሚታረደው እርድ ላይ ከአንድ በላይ ሰው ሆኖ በቅርጫ መካፈል አይቻልም።
* ስለ አጥንት ስባሪ፦ አጥንት ሳይሰባበር መታረድና መበለት አለበት የሚሉ ከፊል ዓሊሞች አሉ። ይህንንም የሚያደርጉት “የልጁ ዕድል (ዕጣ ፈንታ) እንዳይሰባበር” በሚል መልካም ተስፋና ምኞት ነው። ሆኖም ለዚህ አመለካከት ሰሒሕ (ትክክለኛ) የሆነ መረጃ ማቅረብ አይቻልም።
## ፯. በ“ኡድሒያ” እና በ“ዐቂቃህ” መካከል ያለው ልዩነት
ሁለቱን አጣምሮ በአንድ እርድ መነየት አይቻልም (በአልባኒ ፈትዋ መሠረት)። ዋና ዋና ልዩነቶቻቸውም የሚከተሉት ናቸው፦
1. የሥጋው አዘገጃጀት፦ የዐቂቃ ሥጋ ተቀቅሎ (ተሰርቶ) ማከፋፈል ወይም መጋበዝ ተመራጭ ነው።
2. ስለ አጥንት፦ በዐቂቃ ላይ (በከፊል ዓሊሞች ዘንድ) አጥንት አለመስበር ይወደዳል።
3. ስለ ቅርጫ፦ በኡድሒያ ላይ በግመልና በበሬ ቅርጫ የሚፈቀድ ሲሆን፣ በዐቂቃ ላይ ግን በጋራ መታረድ (ቅርጫ) በፍጹም አይቻልም።
> ማጠቃለያ፦ ይህ ጥናት በተቻለ መጠን ዋና ዋና ነጥቦችን ለማሰባሰብ የተሞከረበት ሲሆን፣ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ ሰፊ ዕውቀት ለማግኘት ሌሎች ተዛማጅ የፊቅህ መጽሐፍትን ማንበብ ይመረጣል።
> ወላሁ አዕለም (አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው)
> * ዝግጅት፦ አቡ ሑዘይፋ ሱልጣን ኸዲር
>
ኢላሂ! እኛ እየሞከርን ነውና ወደፈለግንበት አድርሰን፤
ኃጢአት እንሰራለን እና
እባክህ ማረን፤
እንፈራለንና አማንን ስጠን፤
እንሰናከላለንና ቀና አድርገን።
🖋️ አንዲት ኒቃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት በጀርመን አገር በሚገኝ አንድ የገበያ ማዕከል ውስጥ እየሸመተች ነበር።
የሚያስፈልጋትን ዕቃ ገዝታ ከጨረሰች በኋላ፣ የገዛችበትን ሂሳብ ለመክፈል ወደ መክፈያ ማሽኑ (ካሽየሩ) አመራች።
ከመክፈያ ሳጥኑ በስተጀርባ የተቀመጠችው ሰራተኛ ሂጃብ ያላደረገችና የዓረብ ዝርያ ያላት ሴት ነበረች፤ ኒቃብ የለበሰችውን እህት በንቀት ዓይን ከተመለከተቻት በኋላ፣ የገዛቻቸውን ዕቃዎች በግልጽ በሚታይ ንዴት ጠረጴዛው ላይ እያጋጨች መቁጠር ጀመረች።
ኒቃብ የለበሰችው እህት ግን ምንም ዓይነት ምላሽ ሳትሰጥ በጥንካሬና በዝምታ ተረጋግታ ቀጠለች፤ ይህ ሁኔታ የሰራተኛዋን ንዴት ይባስ አባባሰው።
በመጨረሻም ትንኮሳ በሞላበት ድምፅ እንዲህ አለቻት፦
“እኛ እዚህ ጀርመን ውስጥ በቂ ችግርና ቀውስ አለብን፤ ያንቺ ኒቃብ ደግሞ ከችግሮቹ አንዱ ነው! እኛ እዚህ ያለነው ለንግድ እንጂ ሃይማኖትን ወይም ታሪክን ለማሳየት አይደለም። ሃይማኖትሽን መለማመድ ወይም ኒቃብ መልበስ ከፈለግሽ፣ ወደ ሀገርሽ ተመልሰሽ እዚያ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያለሽ።”
ኒቃብ የለበሰችው እህት የገዛቻቸውን ዕቃዎች ወደ ቦርሳዋ መክተቷን አቆመችና በዝምታ ተመለከተቻት…
ከዚያም ፊቷ ላይ የነበረውን ኒቃብ ገለጥ አደረገችው፤ ሰማያዊ ዓይን ያላት፣ ፀጉረ ወርቅ (ብላንድ) ጀርመናዊት ነበረች።
በመረጋጋትም እንዲህ አለቻት፦
“እኔ አባቴም አያቴም (ስር መሰረቴ) እውነተኛ ጀርመናዊት ነኝ…
ይህ ደግሞ የኔ እስልምና ነው…
ይህችም የኔ ሀገር ናት…
እናንተ ግን ዲናችሁን ሸጣችሁት…
እኛ ደግሞ ገዛነው።”
📚 قال الإمام ابن القيم (رحمه الله) :
((فإن للإيمان فرحة وحلاوة ولذاذة في القلب ، فمن لم يجدها فهو فاقد للإيمان أو ناقصه)).
📔 الرسالة التبوكية (7)
••❥❥✺•✿•✺❥❥••
📚 ኢማም ኢብኑል ቀዪም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
> ኢማን በልብ ውስጥ ደስታ፣ ጣፋጭ ቃና እና እርካታ አለው፤ ይህንን ያላገኘ ሰው ወይ ኢማን የሌለው ወይ ኢማን የጎደለው ነው፤፤))
>
📔 አር-ሪሳላህ አት-ተቡኪያህ (7)
••❥❥✺•✿•✺❥❥••
> አካልህ ቢቆራረጥ እንኳ የጠዋትና የማታ አዝካሮችን አትተው! በፍጹም እንዳትተው።
> ከምሽት ዚክሮች መካከል አንዱን እንኳ ብትል እንኳ አድርገው።
ለምሳሌ፦ 'በስሚላሂለዚ ላ የዱሩ መዓ ኢስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዲ ወላ ፊ አስ–ሰማኢ ወሁወስሰሚኡል ዓሊም' (በስሙ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳውን በአላህ ስም እጀምራለሁ፤ እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው) የሚለውን ዱአ ብቻ ብትል እንኳ የጠዋትና የማታ ዚክርን እንዳደረግክ ይቆጠርልሃል። በምሽትም እንዲሁ።
> የመጨረሻው ደግሞ ከመተኛት በፊት የሚደረጉ ዚክሮች ናቸው። ከመተኛትህ በፊት እነዚህን ማውሻዎች ሳታደርግ በፍጹም እንዳትተኛ።
> አንዲት ዚክር ብቻ እንኳ ብትሆን፤ ለምሳሌ፦ 'አስተግፊሩላሀለዚ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወል ሀዩል ቀዩሙ ወአቱቡ ኢለይህ' (ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን፣ ህያውና ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህ ምህረት እለምነዋለሁ፤ ወደ እርሱም እመለሳለሁ) ብትል ምን እንደሚሆን ታውቃለህ?
> ከጦርነት ሜዳ የሸሸህ እንኳ ብትሆን፣ ወይም የወነጀልከው ወንጀል የዚህችን ዓለም አሸዋ ያህል የበዛ ቢሆን እንኳ አላህ ወንጀሎችህን በሙሉ ይምርሃል።
> እና ይሄ ከባድ ነው? እንግዲያውስ ከአላህ ጋር ኑር!"
>
«አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
"ከሥራም ወደሠሩት እንመጣለን፤ የተበተነም ትቢያ እናደርገዋለን።" *(ሱረቱ አል-ፉርቃን፡ 23)*
ፉደይል የተባሉት ታላቅ ዓሊም ይህንን የቁርዓን አንቀጽ አስመልክተው ሲናገሩ፦
"ከማያስቡትም ከአላህ ዘንድ ለእነሱ ግልጽ ሆነላቸው።" *(ሱረቱ አዝ-ዙመር፡ 47)* እንዲህ አሉ፦ "መልካም ሥራዎችን የሠሩ መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን (በትንሣኤ ቀን) ሲያዩት ወንጀል ሆኖ አገኙት።"
እነዚህ ሥራዎች (በውስጣቸው ለአአሏህ ብቻ ያልጠሩ) ጉድለት ያለባቸው ሥራዎች ናቸው። ለአላህ ብሎ የሚሠራ ይመስላል፤ ነገር ግን በእውነታው ለራሱ ስምና ዝና (ወይም ለሌላ ምድራዊ ጥቅም) ነው የሠራው። ለአላህ ብሎ በተገቢው መንገድ አላጠራውም።
ይህ ሰው (በቂያማ ቀን) ወንጀል እንጂ መልካም ምንዳ አይኖረውም። እሱ ግን መልካም ሥራ የሠራ መስሎት ነበር። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ራሱን በትክክል አያውቅም ነበር።
ራሱን በአግባቡ የሚያውቅና አላህ ከራሱ (ከነፍሱ) ክፋት እንዲጠብቀው የሚለምን ሰው፣ ነፍሱ አታታለውም። ይህ (የተሸወደው) ሰው ግን መልካም ሥራ የሠራ መስሎት ይመጣል፤ ነገር ግን በእውነቱ ለአላህ ብሎ አልሠራም፣ ለራሱ ስሜት ሲል ነው የሠራው። በዚህም ምክንያት የሠራው ሥራ ሁሉ "የተበተነ ትቢያ" (ዋጋ ቢስ) ሆኖ ይቀራል።»
የተከበሩ ዶክተር ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ ጧሊብ በሸሪዓ እና ኢስላማዊ ጥናቶች ክፍል የዶክትሬት (PhD) ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ( Excellent) ከመጀመሪያ ደረጃ ክብር (First-Class Honors) ጋር በማግኘታቸው እንኳን ደስ አሎት እንላለን።አላህ ወደ ቀደሞ ኢማምነታቸው በሰላም ይመልሳቸው ዘንድ እንጠይቀዋለን። Читать полностью…
አላህ ይጠብቃቸው፣ በእሳቸው (ዒልም) ሌሎችን ይጠቅም ዘንድ እመኛለሁ።
> مختارات من كتاب صيد الخاطر
> «ከሰይዱል ኻጢር መጽሐፍ የተመረጡ ጥቅሶች»
> تَقْوَى الداعِيَةِ تَصْنَعُ التَّأْثِير
> «የአንድ ዳዒ አላህን መፍራት (ተቅዋ) በሰዎች ላይ ተፅዕኖን ይፈጥራል።»
> قَالَ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى: وَإِنَّ قُلُوبَ النَّاسِ لَتَعْرِفُ حَالَ الشَّخْصِ وَتُحِبُّهُ، أوْ تَأْبَاهُ وَتَذُمُّهُ، أَوْ تَمْدَحُهُ وَفْقَ مَا يَتَحَقَّقُ بَيْنَهُ وَبَيْنَ اللهِ. (ص 98)
> **«አላህ ይዘንላቸውና (ኢብኑል ጀውዚ) እንዲህ ይላሉ፦“የሰዎች ልቦች የአንድን ሰው (እውነተኛ) ማንነትና ሁኔታ ያውቃሉ። በእሱና በአላህ መካከል ባለው ግንኙነት (በውስጠ ሚስጥሩ) ልክ ወይ ይወዱታል፣ያወድሱታል። ወይም ይጠሉታልና ይነቅፉታል።”
📚ገጽ 98**
ደርሶችን ሼር በማድረግ አግዙኝ።
👇
ከዚህ በመቀጠል በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ አደም ሀፊዘሁሏህ ተቀርተው የተጠናቀቁ ደርሶች pdf ተገጥሞላቸው ከስር ተጭነዋል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ በማሰራጨት አግዙን አሏህ ይቀበለን
👇
ይህን ሸይኽ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው በቋንቋ እና በሀዲስ በተፍሲር መረጃ እያጣቀሱ ሰፊ እና የማያዳግም ማብራርያ መስጠታቸው ነው ።
💫💫💫💫
#አቂዳ 👇
1, "አድ'ዱሩሱል ሙሂማህ | الدروس المهمة"
2, "ኡሱሉ'ሱንናህ | أصول السنة"
3, "ሸርሑ ከሽፊ' ሹቡሀት | شرح كشف الشبهات"
4, "ሸርሑ መሳኢሊል ጃሂሊያህ | شرح مسائل الجاهلية"
5, "ሸርሑ ዐቂደቲ 'ጠሐዊያህ | شرح عقيدة الطحاوية
6, "ሸርሑ ኡሱሊ አስ-ሱና | شرح أصول السنة"
7, "ደዓኢሙ ሚኒሃጂ ኑቡዋህ | دعائم منهاج النبوة"
8, "ሸርሑ ሱንና ሊልበርበሃሪ | شرح السنة للإمام البربهاري"
9, አልዑቡዲያህ / العبودية
10,ሙዘኪራ ዐለል ዐቂደቲል ዋሲጢየህ / مذكرة على العقيدة الواسطية
11,አሠባት_ዐለል_ኢስላም/الثَّباتُ عَلى الإسلامِ
12,አልወጅዝ/ الوجيز في عقدية سلف الصالح
13,ደላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ/ضلال جماعة الأحباش
14,ፈትሁል መጅድ
#ፊቅህ
1, "ሙዘኪራ ፊ አሕካሚ አስ-ሲያም | " مذكرة في أحكام الصيام
#ቀዋኢድ_አልፊቅሂያ 👇
#ኡሱል_አልፊቅህ 👇
#ተርቢያ እና #አደብ👇
#ሀዲስ 👇
1,አልአርበዑነ_ነወዊያህ/الْأَربَعُونَ النَّوَوِيَّة
2,አሉእሉእ_ወልመርጃ/ اللؤلؤل والمرجان
3,ቡሉጉል መራም / بلوغ المرام
4, "ሱነኑ አቢ ዳውድ / سنن أبي داود"
4,ጃሚዑ ቲርሚዚይ
5,ሪያዱ ሷሊሂን
#ሙሰጠላሁል_ሀዲስ 👇
1,ሙስጠለሑል ሐዲሥ/مصطلح الحديث
#ሲራ 👇
1,ኹላሶቱ_ኑሪል_የቂን ጁዝ1-3/خُلاصَةُ نُورِ اليَقِينِ فِي سِيرَةِ سَيِّدِ المُرسَلِينَ
2, "አር'ረሒቁል መኽቱም | الرحيق المختوم
#ነህው 👇
1,መትኑል አጅሩሚየህ/متن الأجرومية
2, "ሙልሐቱል' ኢዕራብ | ملحة اﻹعراب"
3, "ከሽፉ'ኒቃብ | كشف النقاب"
4، "አል'ፈዎኪሁል ጀንያህ | الفواكه الجنية"
5,ሸርሑ ኢብኒ ዐቂል ዐላ አልፊየቲ ኢብኒ ማሊክ/شرح ابن عقيل على ألفية ابن مالك
#ሶርፍ 👇
#አል_ኢምላ 👇
#መንጢቅ👇
#በላጋ👇
#አል_ቁርዐን_ወኡሉሙሁ 👇
1, "ኡሱሉን'ፊ ተፋሲር | أصول في التفسير"
2,ሸርሑ ሙቀዲመቲ ተፍሲር/شرح مقدمة التفسير
3,አል ቀዋዒዱል ሒሳን አል ሙተዐሊቀቲ ቢተፍሲሪል ቁርኣን/القواعد الحِسان المتعلقة بتفسير القرآن
🧳
የነብያት ፋና የአለም ብርሃን የጀነት ስንቅ
🛖
📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል:-
🗞️ በ Telegram~Channel ⤵️
📎 🌴
የቴሌግራም ቻናል
ጀይን👇👇👇
/channel/teaching_of_all_prophets
/channel/teaching_of_all_prophets
✍በአቡ ሀኒፋ ሙሀመድ ሀፊዘሁሏህ የተዘጋጁ
*هما طريقان:*
، *الأوّل : ۞ فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ ۞*
، *الثاني : ۞ نَسُوا اللَّهَ فَنَسِيَهُمْ ۞*
*فاختر لنفسك طريقاً.*🥹
«ጸጋ (ኒዕማ) ከምስጋና ጋር የተያያዘ ነው፤ ምስጋና ደግሞ ከበረከት ጋር የተሳሰረ ነው። ሁለቱም በአንድ ላይ የተቆራኙ ናቸው። በመሆኑም ባሪያው ማመስገንን እስካላቆመ ድረስ፥ ከአላህ የሚገኘው ጭማሪ (በረከት) ከቶ አይቋረጥም።» ዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ
Читать полностью…
🔴 የተለያዩ ነገሮችን በመቀላቀል (ባለመለየት) ምክንያት ብዥታ(ሹብሃ) ይፈጠራል።የዱንያ (የዕለት ተዕለት) ሰላምታ (ለምሳሌ፦ "እንደምን አደርክ/ሽ")፦ ይህ ከልማድና ከማኅበራዊ ግንኙነት የሚመደብ ነው፤ ዓላማው በሰዎች መካከል ፍቅርንና ሰላምን ማስፈን ሲሆን ምንም ዓይነት ዲናዊ(ሀይማኖታዊ) ይዘት ወይም የሌላን ወገን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ማጽደቅ የለበትም።
ከሃይማኖታዊ በዓል ጋር የተያያዘ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦ እዚህ ጋር ነገሩ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ምክንያቱም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ በቀጥታ ከሃይማኖታዊ ሥርዓትና ከባለቤቶቹ እምነት (ዓቂዳ) ጋር የተያያዘ ስለሚሆን ነው። ስለዚህ በ"ማኅበራዊ ሰላምታ" እና "በሃይማኖታዊ በዓል መግለጫ" መካከል ያለው ልዩነት ሰማይና ምድር ነው።
## ተውሂድ እና ስለ ወደፊት እጣ ፈንታ አለመጨናነቅ
ወንድሞቼ ሆይ! ሸይጣን በአማኝ ልብ ውስጥ ፍርሃትን ለመዝራት ትልቅ ዓላማ እና ከፍተኛ ጥረት አለው። ከፈጣሪ (ከአላህ) ውጭ ያለን ነገር የስጋት ስሜትን በአማኝ ልብ ውስጥ ለመትከል ይተጋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ከአላህ ውጭ ያለን አካል ወይም ነገር በፈራ ቁጥር እምነቱ (ኢማኑ) እና ተውሂዱ እየደከመ ይሄዳል።
አንድ አማኝ ከአላህ ውጭ ያለን ነገር መፍራት ከጀመረ፣ ያ (ለሸይጣን) መግቢያ በር ይሆንለታል። ልክ እንደ ሀዘን ሁሉ፤ ሸይጣን የአማኝን ልብ ለማሳዘን ከፍተኛ ፍላጎት አለው። አላህ በቁርአኑ እንደሚለው፦
> *"የሚስጥር ውይይት (የነጃዋ) ከሸይጣን ብቻ ነው፤ እነዚያን ያመኑትን ሊያሳዝን።"*
>
ስለዚህ ሸይጣን አማኞችን ለማሳዘን ይጓጓል።
### የሀዘንና የስጋት ተጽእኖ
ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ‘መዳሪጁ አስ–ሳሊኪን በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦
> *"አላህ ሀዘንን አይወድም። ሀዘን እምነትን ያደክማል። ሸይጣን ግን ሀዘንን ይወዳል። ለምን ቢሉ? ባሪያውን አላህን ከመታዘዝ ስራ ስለሚያስረው፣ ስለሚያዳክመውና ልቡን ስለሚሰብረው ነው። ፍርሃትም ልክ እንደዚሁ ነው።"*
>
ስለዚህ እናንተ ሙእሚኖች ሆይ! ከአላህ ውጭ ያለን ነገር ከመፍራት ተጠንቀቁ። ዛሬ ላይ ሰዎች በጭንቀት፣ በድንጋጤ እና ስለ መጪው እጣፈንታ በመጨነቅ እንዲሁም በሌሉና በማይጨበጡ ምኞቶች/ቅዠቶች ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ። ሊሆኑ ስለሚችሉ ነገሮች ከሚጨነቁት ቅዠቶች በተጨማሪ ማለት ነው።
ነገር ግን እምነት በልብ ውስጥ ሲጠነክር እና ተውሂድ ሲጎለብት፣ ሰው ከአላህ በቀር ማንንም አይፈራም።
### የሕይወት ፈተናዎችን በአዎንታዊ እይታ መመልከት
* በስራ ወይም በንግድ አጋርነት፦ አንድ ሰው ከባልደረባው ወይም ከንግድ አጋሩ ጋር በስራ ጉዳይ ቢኳረፍ፣ ሪዝቁ እንዳበቃለት አድርጎ ማሰብ የለበትም። በአጋሩ ጉዳይ አላህን ይፍራ፤ ነገሩ ቢሳካ አልሐምዱሊላህ፣ ባይሳካ ደግሞ ምናልባትም አላህ ከክፉ ነገር አርቆት ሊሆን ይችላል።
* በትዳር ሕይወት፦ ከባለቤቱ ጋር ቢጣላና ዱንያ የጠበበችበት ቢመስለው፣ ምናልባትም አላህ በእነሱ መለያየት ውስጥ መልካም ነገርን አስቦ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ከመለያየቱ በኋላ የተሻለና የላቀ መስተካከልን ሊያመጣ ፈልጎ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሰው በጭንቀት ውስጥ ራሱን ሊያጋንን አይገባም።
* በበሽታና በፈተና፦ ልጁ ቢታመም ወይም እሱ ራሱ በካንሰርና በመሰሉ ከባድ በሽታዎች ቢያዝ፣ ነገሩ ሁሉ አበቃለት ማለት ነው? አይደለም! አንተ ሙእመን ነህ። የዚህች ዓለም (የዱንያ) ሕይወት የፈተና እና የመሻገሪያ ቤት እንጂ ሌላ አይደለችም።
### በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ መኖር
በአላህ እምላለሁ! በካንሰር እና በመሰሉ በሽታዎች የሚሞት ሰው፣ በድንገተኛ ሞት ከሚሞት ሰው በተወሰነ መልኩ የተሻለ እድል አለው። ምክንያቱም ይህኛው በበሽታው ምክንያት ወንጀሉ ይሰረዝለታል፣ ለእሱ ማስጠንቀቂያ ይሆነዋል፣ ራሱንም እንዲመረምር እድል ይሰጠዋል። በድንገተኛ ሞት የሚሞተው ግን ይህንን የመሰለ እድል አያገኝም።
አላህ እጅግ በጣም አራህማን እና ለባሮቹ ሩህሩህ ነው። ስለዚህ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑራችሁ።
> *"ከነሱም አንዲት ጭፍራ በእርግጥ ነፍሶቻቸው አሳሰቧቸው። በአላህ ላይ ያለ ሀቅ የጃሂሊያን (የመሃይማንን) ጥርጣሬ ይጠረጥራሉ።"*
>
ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! ከአላህ በቀር ሌላን አትፍሩ። መጪውን ጊዜ አትፍሩ፣ ድህነትን አትፍሩ፣ በሽታን አትፍሩ፣ በነፍሳችሁም ሆነ በልጆቻችሁ ላይ አትስጉ። ነገሩ ሁሉ በአላህ እጅ ነው።
ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሕይወታችሁን ብትመረምሩ፣ በአንድ ወቅት ስላመለጣችሁ አዝናችሁበት የነበረ ነገር፣ በኋላ ላይ በእሱ ውስጥ ፈጽሞ ያላሰባችሁት መልካም ነገር እንደነበረበት ትገነዘባላችሁ። በሰዎች ታሪክና ሕይወት ውስጥም ይህንን እናያለን፤ ከስራው የተባረረ ሰው ስራዬ አለቀብኝ ብሎ ሲያስብ፣ አላህ ግን ሰፊና ታላቅ የሲሳይ በር ይከፍትለታል። ሰጪው አላህ ነው፤ ለአንተ የተጻፈልህ ነገር ሳይመጣልህ አይቀርም።
ኢብኑል ቀይም እንዳሉት እወቅ፦
> *"ድህነት ከተጻፈብህ እሱ ላንተ መልካም ነው። ምክንያቱም አንተ ለዱንያ ሳይሆን ለአኼራ የተፈለግክ ልትሆን ትችላለህ። በሽታ ከተጻፈብህም ላንተ መልካም ነው፤ ምክንያቱም አላህ ለአኼራ ፈልጎሃል።"*
>
አላህ በራህመቱ ይሸፍነን፣ እርግጠኝነትን (የቂንን) ይስጠን። ከአላህ ውጭ ሌላን አንፍራ።
ይህ ማለት ግን ሰበብ ማድረስን (መጣርን) መተው ማለት ነውን? ፈጽሞ አይደለም! ዛሬ ላይ እኛ የምንኖረው ሰበብን በማጋነን ቀውስ ውስጥ ነው..ያለነው።
.
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
«በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው፤ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል!»
(ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት)
ዐብላህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለው ነበር "
ማንም ሰው በዲኑ ጉዳይ ላይ ሌላውን በጭፍን አይከተል።”
“ቁርኣንን አንብቡ፤ እርሱ በቂያማ እለት ለባልደረቦቹ (ለሚያነቡትና ለሚተገብሩት) አማላጅ ሆኖ ይመጣልና።”
اللهم إننا نحاول فأوصلنا
وإننا نذنب فآغفرلنا
وإننا نخاف فآمنا، وإننا نتعثر فأقمنا.
የእለቱ መልክት
የአላህ መልክተኛ ﷺ ካሉት በላይ አትጨምር!
የኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ልጅ ዐብዱላህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ «እኔና አባቴ በመስጂድ ውስጥ እያለፍን ነበር፤ በዚህ መሀል አንድ ተራኪ (ቀሳስ) “ሐዲሠ ኑዙልን” (አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ስለመውረዱ የሚገልጸውን ሐዲሥ) ሲያወራ ሰማነው። እንዲህም አለ፦ “የሸዕባን ወር ግማሽ ሌሊት (ኒስፉ ሸዕባን) በሚሆንበት ጊዜ አላህ (ዓዘ ወጀል) ያላንዳች መወገድ (ከቦታው ሳይለቅ)፣ ያላንዳች መዘዋወር፣ ያላንዳች መለዋወጥና ሁኔታው ሳይቀየር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል”።
በዚህ ጊዜ አባቴ (ኢማም አሕመድ) ከንዴት የተነሳ ተንቀጠቀጡ፣ ቀለማቸውም ቢጫ ሆነ (ፊታቸው ተለወጠ)፣ እጄንም ያዙኝ፤ እኔም እስኪረጋጉ ድረስ ያዝኳቸው። ከዚያም፦ “ወደዚህ አስመሳይ (ያለ እውቀት ወደሚዘባርቀው ሰው) ውሰደኝ” አሉ። ልክ እሱ ጋ ሲደርሱ እንዲህ አሉት፦ “አንተ ሰውዬ! የአላህ መልክተኛ ﷺ ከአንተ ይበልጥ ለጌታቸው (ለአላህ) ክብር ተቆርቋሪ ነበሩ፤ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዳሉት ብቻ በል (ከራስህ ፍልስፍና አትጨምር)፤፤” ከዚያም ዘወር ብለው ሄዱ።»
📔 [አል-ኢቅቲሷድ ፊ አል ኢዕቲቃድ — ሊዐብዱል ገኒይ አል-መቅዲሲ (21)]
ዓብደላህ ኢብኑል ሙባረክ እንዲህ ተጠየቁ፦ 'ዑመር ኢብኑ ዐብደልዓዚዝ ይበልጣል ወይስ ሙዓዊያ?' እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ 'ሙዓዊያ ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር በተሳተፈባቸው በአንዳንዶቹ የውጊያ አውደ ግንባሮች ላይ ሳለ ወደ አፍንጫው የገባው አቧራ እንኳ ከዑመር ኢብኑ ዐብደልዐዚዝ ይበልጣል።'"Читать полностью…
(ምንጭ፦ አል-ሁጃ ፊ በያኒል ሙሐጃ [2/377] በአቡ ቃሲም አል-አስበሃኒ የተዘጋጀ)
"ከከሀዲያን እና ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር በአደባባይ ወይም በየቲቪ ቻናሎቹ የሚደረጉ ይፋዊ ክርክሮች፤ ይህ ከሰለፎች የዳዕዋ መንገድ ነውን? ውጤቱስ ምንድን ነው?!
ይህንን በተመለከተ፤ ከሰለፎች (አላህ ይዘንላቸውና) በሰፊው የተነገረውና የታወቀው መንገድ፡ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ፣ እነሱን ከመስማት፣ ከእነሱ ጋር ከመከራከርና ክርክር ከመግጠም መራቅ ነው።
ለዚህም ምክንያቱ፦
* አንደኛ፦ ክርክር ልብን ያደክማል፣ ቂምና በቀልንም ያወርሳል።
* ሁለተኛ፦ ሰሚው (ሰፊው)ማህበረሰብ እውነቱ የትኛው እንደሆነ መለየት ላይችል ይችላል። በተለይም የቢድዓው ባለቤት አቀራረቡ የተዋጣለትና አንደበተ ርቱዕ ከሆነ፣ እንዲሁም የሱናው ባለቤት ደግሞ የማስረዳት አቅሙ ደካማ ከሆነ፤ ይፋዊው ክርክር ለሰፊው ህዝብ ፈተና (ፊተና) መሆን ይጀምራል። ህዝቡም ጥመትን እውነት ነው ብሎ ሊከተል ይችላል።
ስለዚህ ሰለፎች ይከለክሉ የነበሩት ለዚህ ነው።"
"አላህ ይጠብቃችሁና፤ በዚህ ዘመን በሳተላይት የቲቪ ቻናሎች ላይ የሚደረጉ የክርክር መድረኮችን በተመለከተ፦
እነዚህ መድረኮች አብዛኛውን ጊዜ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል። ለምን ቢባል?
* አንደኛ፦ ጥያቄዎችንና ጥርጣሬዎችን (ሹብሃቶችን) ወደማያውቁትና ንፁህ ወደሆኑት የሰፊው ህዝብ ልቦች ውስጥ ያስርጻሉ። አንድ ተራ ሙስሊም በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፣ ከዚህ በፊት ሰምቶት የማያውቀውንና በጭንቅላቱ ውስጥ ጨርሶ ያልነበረን ጥርጣሬ (ሹብሃ) በነዚህ መድረኮች አማካኝነት እንዲሰማ ይደረጋል። ከዚያም ያ ጥርጣሬ ልቡ ውስጥ ይፈጠራል። በክርክሩ ላይ ለቀረበው ጥርጣሬ የተሰጠው ምላሽ በቂ ባይሆን ወይም ግልጽ ባይሆንለትስ?! ያ ሰው ጥርጣሬው ልቡ ውስጥ እንደታተመ ይቀራል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው።
* ሁለተኛ፦ እነዚህ መድረኮች ለቢድዓ ባለቤቶችና ለጠማሞች የራሳቸውን መርዝና ጥመት የሚረጩበት ሰፊ መድረክና ነፃ ማስታወቂያ ይሆኑላቸዋል። መቼም ቢሆን ሊያገኙት የማይችሉትን ሰፊ ህዝብ በእነዚህ ቻናሎች አማካኝነት ያገኛሉ።
ስለዚህ ትክክለኛውና ጥንቃቄ የተሞላበት መንገድ፡ እውነትንና ሱናን በራሱ ጥራቱና ውበቱ ለህዝቡ ማስተማር ነው። የጠማሞችን ጥርጣሬ ግን ስማቸውን ሳያነሱና መድረክ ሳይሰጧቸው፣ እውነቱን ጠንካራ በሆነ መረጃ በማብራራት ማፍረስ ይገባል።"
ሸይኽ ዶ/ር ሳሊህ አስ-ሰንዲ
"የተባሉትን ቃል ለወጡ" — የሲፋት ማዛባት አደገኝነት
"ቁርኣን ላይ ያሉ አሻሚ ነጥቦችን (ሙተሻቢሃትን) በመምዘዝ የሚከራከሯችሁ ሰዎች ወደፊት ይመጣሉ። እናንተ ግን በሱና ሞግቷቸው/ያዟቸው፤ ምክንያቱም የሱና ባለቤቶች የአላህን መጽሐፍ (ቁርኣንን) ይበልጥ አዋቂዎች ናቸውና።"
(ዑመር ኢብኑ አል ኸጧብ)
— ዳሪሚይ የዘገቡት