sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14577

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🌟 ልዩ የዳዕዋ ዝግጅት በነሲሓ መስጂድ

👌እሁድ ዙልቂዕዳ 26/1445 ዓ.
ግንቦት 25/2026 ከ 3፡30 ጀምሮ 18 ማዞሪያ በሚገኘው ነሲሓ መስጂድ


ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

__
🕌 ibnu Masoud islamic Center
t.me/merkezuna

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

«አንድ ሰው  ልጆቹ እሱን አይተው እንዲማሩበት፣ ሴቶችም የእሱን አርአያ እንዲከተሉ፣ እንዳያደርጉትም በቤቱ ውስጥ የሱና ሰላቶችን ቢሰግድ  ብልህነት ነው።

የማይሰገድበት ቤት መቃብር ነው።”

📚ሸርሑ ቡሉጊ አል-መራም / ኢብኑ ዑሰይሚን (3/46]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ሴቶች ነሺዳን እያዜሙ እና ቁርኣን እያነበቡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ብቅ ብቅ ማለት የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል። ይሄ ነገር ደዕዋ ሆነ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ከመውደድ አይካተትም። ይልቁንም ለአመፅ እና ለፈተና የቀረበ ነው።
አጅነቢይ ወንዶች ፊት ቁርኣንን መቅራትና ነሺዳ ማዜም እንዲሁም የሴቶችን ቅላፄን ማስዋብ፤  በቁርኣን የተወገዘው ንግግርን ማለዘብ ውስጥ ይካተታል። ለወንዶችም እነሱን ማዳመጥ ፈተና ነው። ጥቂት የማይባሉ ሴቶች ቻነል ከፍተው ይህን ድርጊታቸውን ደዕዋ ነው ብለው መሞገታቸው ፈተናውን እና  መከራ ያባብሰዋል።
አላሁ ሙስተዓን
اللهم ردنا إلى دينك ردا جميلا.

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🤲 ኢላሂ !
በውዴታቸው ቅን  የሆኑ የዲን ወንድሞችን ለግሰን!

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡-

"ከእስልምና ቀጥሎ ከጥሩ ወንድም በላይ ምንም አይነት በላጭ ነገር አንድ ሰው አልተሰጠም።"

ቁወቱ አል–ቁሉብ - (178/2)

ኢማም አሽ– ሻፊኢይ - አላህ ይዘንላቸውና፡-

“የዲን ወንድሞች ጋር መጓዳኘት የሚያክል ደስታ የለም፣ ወንድሞቻችን መለያየት የሚያክል ሐዘን የለም።

ሹዐቡል ኢማን - (504/6))

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

بكاء الشيخ الشريم

🎙ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ያነባች አይን በፍፁም የጀሀነም እሳትን አላህ አያሳያትም።🎙

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🌴🔊 مادة الفرق والأديان،الروافض 💿🌴


📚 ርዕስ :- ሺዓ(አር– ረዋፊድ)

🎙ማብራሪያ ፦ ኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

🗂 ትምህርቱን ጥራት ባለው (64kbps) የተቀዳ

📀 《ደርሱን ፊ ኡሱሊል ፊረቅ》

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

📢#ደርስ_ይከታተሉ!
በነሲሓ ቲቪ ሲተላለፍ የነበረው በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ የተሰጠውን  አል ዐቂደቱል ዋሲጢያህ ደርስ ወደ ኦዲዮ በመመለስ እና ለመከታተል በሚያመች መልኩ አጠር ባሉ ክፍሎች ተዘጋጅቶ በሳምንት ሁለት ቀናት ሰኞ እና ሐሙስ በዚህ ቻናል ይለቀቃል። ደርሱ ተደራሽነት ይኖረው ዘንድ ሼር ያድርጉ!

📗የኪታቡ ስም ፡
"العقيدة الواسطية"
"አል ዐቂደቱል ዋሲጢያህ" 
(መሰረታዊ የአህሉስ-ሱንና ወልጀመዓን ዐቂዳ የሚያብራራ ኪታብ )

▪️ዘወትር ሰኞ እና ሐሙስ  
⏰ ከቅኑ 10፡00

👤የደርሱ አቅራቢ ፡ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ 
https://www.facebook.com/ustathilyas

t.me/ustazilyas

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አላህ ወፍቃችሁ ሀጅ እና ዑምራ ለምትሄዱ ሰዎች አጭር ግን በጣም ጠቃሚ ምክር አለኝ ።
በተቻላችሁ አቅም ከሶሻል ሚዲያ እና ከሰልፊ ፎቶ እና ቪዲዮ ራቁ ። ቢሊየኖች መካከል ተመርጣችሁ ወደ ጌታችሁ ቤት ተጠርታችሁ በሶሻል ሚዲያ እንቶ ፈንቶ እና በፎቶ ራሳችሁን አትጥመዱ ። ዛሬ ሙስሊሙ ዑማ ብዙ ከባባድ ጉዳዮች አሉበት ። በግላችን ስንት ሃጃ አለብን ። ከዋናው ከንጉሱ ቤት ሂዶ ወደ እሱ ተጥዶ ተዋድቆ ሃጃ እንደ ማውጣት በንቶ ፈንቶ መጠመድ ትልቅ ጉዳት ከባድ ቅጣት ነውና ጥንቃቄ እናድርግ የሚለውን ለማስታወስ ነው ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

⛔️⛔️ሰበር ዜና!



የዘንድሮ የኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የመጀመሪያው በረራ በሰላም መዲና ደርሰዋል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

الشيخ بندر بليلة آية من سورة التوبة
♡:❤️❤️❤️

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

11 ምላሾች
«ሙታንን መጣራት ሰበብ ስለሆነ እንጂ አደራጊው አላህ መሆኑን ስለምናምን ሺርክ አይሆንም!» ለሚሉ…

በሸይኽ ኢልያስ አህመድ
NesihaTv

https://youtu.be/QEm-jU4lytY

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

Telegram፡ /channel/nesihatv

YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCX2E30J71sKpnLQuGr7kt6w

Facebook፡ facebook.com/nesihatv

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaaWvl5CXC3Ic7glOv3U

@nesihatv

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«የጁምዓ እለት አንዲት ሰአት አለች፣ አንድ የአላህ ባርያ ዱዓ አድርጎ ያቺን ሰዓት አይገጠምም፤ አላህ ዱዓውን ቢቀበለው እንጂ።»

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

القارئ الشيخ عبد الله بعيجان

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🕋 ⁩ሐጅ ድኅነት እና ወንጀሎችን ለማስወገድ  አይነተኛ ፈውስ ነው!
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
🔶" በሐጅ እና በዑምራ መካከል ምንም ክፍተት ሳታደርጉ በማከታተል ሐጅና ዑምራን ፈፅሙ።
እሳት የብረት ጉድፎችን  ሙልጭ አድርጎ እንዲሚያሰወግደው ሁሉ እነሱም ድህነትና  ወንጀሎችን ያስወግዳሉ።"
📚【አልባኒ ሰሒህ ብለውታል (1200)】


✿ ✿ ✿ ✿ ✿ ✿

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ: ‐ «እድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው ብትባል ምን ትሰራበት ነበር?» በማለት ተጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «ሰዎችን አስተምር ነበር።» በማለት መለሱ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የሀጅ አፈፃፀም ክፍል አንድ

ሐጅ ለማድረግ ለተነሳችሁ …
የሐጅ እና ዑምራን ድንጋጌዎችን ለመፈፀም ጠቃሚ ደርስ ስለሆነ አድምጡት።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ቁርአን ሓፊዝ ነው!
ግን ኩራተኛ…

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

(إنَّ بين يدَيْها فِتنةً وهرْجًا قالوا: يا رسولَ اللهِ! الفتنةُ قد عرفناها فالهرْجُ ما هو؟ قال: بلسانِ الحبشةِ القتلُ، ويُلقَى بين النَّاسِ التَّناكُرُ فلا يكادُ أحدٌ أن يعرِفَ أحدًا)

إرواه أحمد بن حنبل، في المسند، عن حذيفة بن اليمان، الصفحة أو الرقم:2771، صحيح

(በእርግጥም ከቂያማ በፊት ፈተና እና "ሀርጅ" አለ።" የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኛ ፈተናን አውቀናል፤ ታዲያ "ሀርጅ" ምንድን ነው? አሉ፡- በሐበሾች ቋንቋ ግድያ  ማለት ነው አሉ፤ በሕዝቦችም መካከል አለመተዋወቅ ይጣላል። ማንም ሰው ማንንም አያውቅም።)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሐጅ ለማድረግ ለተነሳችሁ …
የሐጅ እና ዑምራን ድንጋጌዎችን ለመማር የሚረዳ ጠቃሚ አፕሊኬሽን ስለሆነ አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

اللَّهُمَّ إنِّي أسْألُكَ رِضَاكَ وَالجَنَّةَ ، وَأعُوذُ بِكَ مِنْ سَخَطِكَ وَالنَّارِ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የመማር ጌጡ ትህትና ነው
~
መማር ጥሩ ነው። ልብን ሊያሳብጥ ግን አይገባም። አንዳንድ የተማሩ ወንድሞቻችን ግን ከንግግራቸው / ከፅህፈታቸው ውስጥ እብሪት ይንፀባረቃል። የመማር ውበቱ ትህትና ነው። ደግሞም በሆነ ዘርፍ መማር ማለት በሁሉም ዘርፍ ላይ ዳኝነት ያጎናፅፋል ማለት አይደለም። እንዴት ነው በሁሉም ዘርፍ ላይ ዘው ብለው እየገቡ ሂስና ግምገማ የሚሰጠው? አንድ ከፍተኛ አቅም ያለው መካኒክ ሆስፒታል ሲሄድ ተራ ሰው ነው። መኪና ፈታቶ ስለሚገጥም ብቻ ቀዶ ህክምና ይሰጣል ማለት አይደለም። በተማሩት ዘርፍ ላይ የያዙት ትልቅ ስም እያደፋፈራቸው ስህተት ነው መባል እንኳ የሚበዛበት ሃሳብ እየሰነዘሩ ወዳጅ የሚያሳቅቁ ሰዎች አሉ። መሳሳት የትም አለ። ግን አይነት አለው። ከኩራት፣ ከትእቢት፣ ከመታበይ ጋር ሲሆን ያስንቃል።
ብዙ ሙስሊም ምሁራን በህዝበ ሙስሊሙ መሀል ስላለ ጉዳይ ሲያነሱ ለራሳቸው ያላቸውን ከፍ ያለ ግምት በተለያየ መልኩ ሲያንፀባርቁት ይታያሉ። ምናልባት ካልተማረ ህዝብ መሀል የሚገኙ ልዩ ክስተቶች አድርገው ራሳቸውን እያዩ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ ግን የምናቀብጣቸው እኛው ነን። በቅጡ ባልገባቸው ነገር ውስጥ ገብተው ሲያቦኩ "ልክ ነህ ዶክተር!" ፣ "ልክ ኖት ፕሮፌሰር"፣ " የተማረ ይግደለኝ"፣ ... እያሉ በቦታውም ያለ ቦታውም አድናቆት መስፈር ማክበር ሳይሆን ማሽቃበጥ ነው። እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለምናደንቀውም፣ ለራስም፣ ለህዝብም፣ ... ለማንም አይበጅም። ለማንም!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ከሐጅ ድንቃ ድንቅ ማህደር

ዐብዱላህ ኢብኑ ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ ሐጅ ሲያደርጉ ሠላሳ ግመሎች እና ሠላሳ አሽከሮች አብረዋቸው ነበሩ፣ ታዲያ የሚደንቀው! እርሳቸው በእግራቸው እየተጓዙ ለእያንዳንዱ አሽከር አንዳንድ ግመልና ሠላሳ ሺ ዲርሃም ሰጧቸው። አረፋ በደረሱም ግዜ፣ ከባርነትም ነፃ ከአወጧቸው በኋላ ፦ «እኔ ከባርነት ነፃ እንዳወጧኋቸው እኔንም አላህ ከእሳት ነፃ ያወጣኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።» አሉ።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል፦
‹‹ ለሰዎች ብሎ መስራት ሽርክ  ነው፡፡ ለሰዎች ብሎ ስራን መተው ይዩልኝ (ሪያእ) ነው፡፡ ኢኽላስ ማለት ደግሞ ከሁለቱ አላህ ሲያድንህ ነው፡፡››

አል አዝካር ሊነወዊይ (1/33)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ውብ የአገላለፅ ጥበብ እና ጠንከር ያለ ጠቃሚ መልክት ማስተለለፍን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ መፅሀፍ ቁርኣን ብቻ ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

እርሷም ከአስር በኋላ ነች።
አቡ ዳዉድ በዘገቡት

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

📌 በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!! 

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤

ያለንበትን የረጀብ ወር በማስመልከት የሚፈፀሙ የቢድዓ ተግባራት ተበራክተዋል። የረጀብን የመጀመሪያ እለት፣ የመጀመሪያ ጁምዓ፣ አስራ አምስተኛውን እለት እንዲሁም ሀያ ሰባተኛውን ቀን ማክበር ቢድዓ መሆኑን፤ በሌሎች ወሮች  እንደሚፈፀሙት የሰኞና ሀሙስ ወይም አያመልቢድ ፃሞች ካልሆነ ወሩን አስመልክቶ የተደነገገ ልዩ ፆምም ይሁን ሰላት እንደሌለ ገልጫለሁ።   ይህ ማለት ግን ረጀብን ከሌሎች ወራቶች የሚለየው ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም። 

የረጀብ ወር፤ በሱረቱል ተዉባህ ቁጥር 36  ከተጠቆሙት የተከበሩ አራት ወራት (አሽሁሩል ሁሩም) አንዱ  ነው።

አላህ እንዲህ ይላል፤ 

[إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36 

« አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤  በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36

عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم.

ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤ 
ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤ 
ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው።  አላህ ረጀብንም ከእነዚህ  የረከበሩ ወራት  አድርጎታል። 

እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤

1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።  
ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር
ውጊያ አይፈቀድም።

2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ። 

እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው። በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ  በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል። 

ኢባደላህ!

አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል። 
እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው። 

ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው።

ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል።   ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ። 

ሸይጣንን እናሸንፍ!

አላህ ከጥፋት ይጠብቀን..

አሚን!!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ማንንም ለማስደመም ብለህ አታነብ፣ ለራስህ ስትል አንብብ፣ ያኔ በራስህ፣ በዝምታህ፣ በቸልተኝነትህ፣ በምርጫህ ትገረማለህ።

ብዙ ነገሮችን በማለፍ ብቻ ተጠቃሚ እንደምትሆን ይሰማሃል ፣ አጉል ክርክር ብዙውን ጊዜ አለመግባባት ወይም የቅድመ ዝግጅት ውጤት መሆናቸው ይገባሃል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ለ1445 የአሏህ እንግዶች የአሠልጣኞች  ሥልጠና  ተሰጠ።

ሚያዚያ 27፣ 2016 (አዲስ አ በባ) - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት "የዘመነ መስተንግዶ ለአርረሕማን እንግዶች" በሚል መሪ ቃል ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የሐጅ ተጓዦች በጠቅላይ ምክር ቤቱ አዳራሽ የአሠልጣኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ።

ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጠቅላይ  ምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ   አብዱልፈታህ መሐመድ ናስር በዘንድሮ የሐጅ ጉዞ የሑጃጁን ክብር የጠበቀና ከወትሮ የተለየ ለማድረግ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደሚጀምር የተናገሩት ኃላፊው የአላህ እንግዶች በጉዞ ወቅት በሐገር ዉስጥና በሳዑዲ እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ እና እንዲደጋገፉ አሳስበዋል።

ሑጃጁ የበረራ ጊዜውን እንዲያውቅ ምክር ቤቱ የመረጃ መስጪያ ቁጥር 9933 የከፈተ ሲኾን፣ ከምክር ቤቱ ለሑጃጁ ወቅታዊ መረጃ  በEtho Hajj አጭር መልዕክት ማስተላለፊያ  እየላከ በመኾኑ ሑጃጁ እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል።

የሐጅ ጉዞ ቀጥታ ወደ መዲና መኾኑን የተናገሩት ኃላፊዉ ሑጃጁ የሚጓዝበትን የበረራ ቀን እና በመዲና የሚያርፍበትን ሆቴል ከወዲሁ እንዲያውቅ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል።

አብዛኛው የሐገራችን ሑጃጅ ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ በመሆኑ ለሐጅ ሲመዘገቡ በሰጡት የስልክ ቁጥር ሳዑዲ ሆነው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት  እንዲችሉ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ኃላፊው ተናግረዋል።

በዛሬው የአሠልጣኞች ሥልጠና ላይ የተሳተፉት ከመቀሌ፣ ከወራቤ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ እና ከፉሪ የምዝገባ ጣቢያዎች  የተመረጡ ሠልጣኞች ናቸው።
****
ሸዋል 26፣ 1445 ዓ.ሂ.
*​**
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

✨🍃

ሐጅ ከእስልምና ምሰሶዎች አንዱ ነው።
ይህን እውነታ አምኖ፣አቅም ኖሮት ሐጅ ያላደረገ ሰው ታላቅ አደጋ ውስጥ ነው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel