sultan_54 | Unsorted

Telegram-канал sultan_54 - የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

14577

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Subscribe to a channel

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ጥያቄ፡  ወደ ሱጁድ በምንወርድ ጊዜ በጉልበታችን ነው መውረድ ያለብን ወይስ በእጃችን ?

መልስ፡ አንድ ሰው ወደ ሱጁድ እንዴት መውረድ እንዳለበት በተመለከተ በዑለማኦች መካከል ሰፊ ውዝግብ አለ፣ መጀመሪያ እጅ  ወይስ ጉልበት መቅደም የሚገባው በሚለው ሀሳብ ላይ። ሀነፊዮች፣ ሻፊዒዮች እና ኢማሙ አህመድ በአንደኛው ዘገባቸው፤ ሰላት የሚሰግድ ሰው ከእጁ በፊት አስቀድሞ በጉልበቱን መውረድ አለበት የሚለውን ሀሳብ ይደግፋሉ።  ቲርሚዚም ይህ የብዙሃኑ ዑለማዎች አስተያየት እንደሆነ በመናገር በሱነናቸው  (2/57)  እንዲህ ብለዋል፡- "በአብዛኞቹ ሊቃውንት ዘንድ አንድ ሰው ከእጆቹ በፊት በጉልበቱ ወደ ሱጁድ መወረድ እንዳለበት ያምናሉ፣  በሚነሳበት ጊዜ ደግሞ እጆቹን ከጉልበቱ በፊት ማንሳት አለበት፣ ይላሉ። ይህንን ሀሳብ የሚያንፀባርቁ የዋኢል ኢብኑ ሁጅርን ሐዲስ በማስረጃ ያጣቅሳሉ፡- "የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱጁድ ሲያደርጉ፣  ከእጆቻቸው በፊት ጉልበቶቻቸውን አስቀድመው ሲወርዱ አይቻለሁ። ሲነሱ ደግሞ ከጉልበታቸው በፊት እጆቻቸውን አነሱ።"
(አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ አል-ኒሳኢ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አል-ዳረልቁጥኒ ዘግበውታል (1/345)።
መጀመሪያ  ወደ ሱጁድ ሲውረድ ጉልበት ማስቀደም አለበት ብለው ከሚያምኑ ዑለማዎች መካከል ሸይኽ አል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እና ተማሪያቸው ኢብኑል ቀይም ይገኙበታል። ይህንን አመለካከት የሚደግፉ የዘመናችን ሊቃውንት  መካከል ደግሞ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ እና ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ኡሠይሚን ይገኙበታል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ በአል-ፈታዋ (22/449) ላይ ጠቃሚ አስተያየት ሰጥተዋል፦"በሁለቱም መንገድ መስገድ በዑለማዎች ስምምነት መሰረት ሰላቱ ትክክል ነው።( አይበላሽም)ስለዚህም አንድ ሰጋጅ አስቀድሞ መንበርከክ አሊያም በእጆቹ ወደ ሱጁድ መውረድ ይችላል።  በማንኛውም ሁኔታ ሱጁድ ቢያደርግ ሰላቱ ትክክለኛ ነው። ነገር ግን የትኛው ነው የሚሻለው ብለው ተከራከርዋል።"
ስለዚህ ጧሊቡ አል–ዒልም የሆነ ባመነበት እና እሱ ዘንድ ሚዛን ይደፋል የሚለውን አቋም  መተግበር ይኖርበታል፣ ተራው ሙስሊም ደግሞ ያመነበትን ዓሊም ሃሳብ መከተል ይችላል።
ወላሁ አዕለም።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

.
⚠️ ማስታወሻ!

🔘 ዓሹራን ለመፆም ያቀዳችሁ!

🗓 መጪው #ሰኞ ሙሐረም 9ኛው እና #ማክሰኞ ደግሞ ሙሐረም 10ኛው [ዓሹራ] ነው።

የዓሹራ ቀን ፆም በሐዲስ እንደመጣው ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ያሰርዛል።  አሏህ ይወፍቀን።

📨 ሌሎችን በማስታወስ በአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ከዙህድ በላጩ ፥
ዛሂድ መሆንህን መደበቅ ነው።»
ዐብዱላሂ ኢብን ሙባረክ
📚አዙህድ ሊኢብኒ አቢ አዱንያ (61
)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሐጅ ላይ ያለ እውቀት ፈትዋ ይበዛል ተጠንቀቁ!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

الحج تقديس لا تسيس
أتينا الطواف لا لطائفية
أتينا للعرفات لا لرفع شعارات
أتينا لتلبية لا لتأليب

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አንድ ሰው አርባ አመት ሲሞላው፦
”ወደ አኼራ ጎዞህ ተቃርቧልና ስንቅህን አዘጋጅ።˝ ብሎ ከሰማይ☝️ ተጣሪ ይጣራል።

📚ረውደቱ አል ዑቀላእ (52)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

"አያሙ አት–ተሽሪቅ  የመብላት፣ የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናት ናቸው።"
📚(ሙስሊምና ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል)

/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

70 ነቢያት የሰገዱበት የሚና መስጂድ....

🔅ሑጃጆች በሚና ቆይታቸው 5 ወቅት ሰላቶችን በሰዓታቸውና በጀመዓ ሊሰግዱ ይገባል።

🔅ጀመዓውን ወንዶችም ሴቶችም በየማረፊያቸው መስገድ የሚችሉ ከመሆኑም ጋር ወንዶች ከቻሉ... እዛው ሚና ውስጥ የሚገኘው "መስጂደል-ኺፍ" ላይ
ሄደው ቢሰግዱ ይመረጣል።

🔅ነቢዩ ﷺ (መስጂደል-ኺፍ ላይ 70 ነቢያት ሰግደውበታል) ብለዋል።

🔅ጀመዓህ ሰላትን ወደዚህ መስጂድ እየሄዱ መስገድ እንደሚወደድም ሊቃውንት ገልጸዋል።

✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል-መዓድ
/channel/ahmedadem

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አሁን! በዚህ ሌሊት…
ሑጃጆች ሚና ሜዳ ላይ ያድራሉ። ነግቶ ወደ ዓረፋ ሜዳ ሊሄዱ በጉጉት ይጠባበቃሉ። ለነርሱ የዛሬው ፈጅር የተናፈቀ ወዳጅን ለማግኘት፣ በጉጉት የሚጠበቅ ቀጠሮ ነው። ዓረፋ በባሮቹ ደግነት አላህ በመላኢካዎች ላይ የሚፎክርበት ታላቅ መሰብሰቢያ ነው። «ሐጅ ዓረፋ ነው!» እንዳሉት የኛ ተወዳጅ [ﷺ]።
በእርግጥ የዛሬው የሚና አዳር ተወዳጅ ነው። ግዴታ አይደለም!

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም(ረሂመሁላህ) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦
"ያ አባ ኢስሐቅ! ዱዓ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?"
እሳቸውም ፦"ቀልባችሁ በአስር ነገሮች ሞታለች።" አሏቸው።
እነሱም፦"ምን ምንድ ናቸው?" ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦
"(አንደኛ) አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።
(ሁለተኛ) ነቢዩን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፣ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
(ሦስተኛ) ቁርኣንን አነበባችሁት ፣አልሰራችበትም።
(አራተኛ) የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
(አምስተኛ) ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋ ገጠማቹ።
(ስድስተኛ) ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ ሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
(ሰባተኛ) የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
(ስምንተኛ) ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
(ዘጠኝ)ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፣ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
(አስር) ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።

【"ጃሚዑል በያን አልዒልሚ ወፈድሊሂ"(2/12)】

📮/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የዐረፋ ቀን በላጩ ተግባር ዱዓ ነው።
ስለሆነም ለነገው የዐረፋ ቀን ዱዓችን እናዘጋጅ።
ኢማሙ አውዛዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋለ፦
"ሃጃቸውን (ዱዓቸውን) ለዐረፋ ቀን የሚያዘጋጁ ሰዎች ላይ ደርሻለሁ።"
ለዐረፋ ቀን የሚሆን በትላልቅ የተፃፈ ዱዓ ነው አውርደው ይጠቀሙት።
t.me/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
“ከነዚህ አስር ቀናት የበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱባቸው ቀናት የሉም።”

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የሐጅ ምንዳን የሚያስገኙ ተግባራት
(1)
ለወላጆች መልካም መዋል!

አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ጋር መጥቶ ፦"ጅሃድ ማድረግ እፈልጋለሁ ግን አቅሙ የለኝም።" አላቸው። እሳቸውም፦ "ከወላጆችህ አንዱ በህይወት አሉን?" በማለት ጠየቁት።
 እርሱም፡-"አዎ! እናቴ በህይወት አለች።" በማለት መለሰላቸው።
እሳቸውም፦" አላህን በጽድቋ ተገናኘው፡ ይህን ካደረክ ፣ ሐጅ፣ ዑምራ እና የጂሃድ ምንዳን ታገኛለህ።" አሉት።፡
📚አል ሓፊዝ አል ዒራቂይ ሐዲሰን ሐሠን ብለውታል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ወኔ ላይ የተገነባ ወጣት እርሱ ሚዛናዊ እንዳይሆን ከሚያደርጉት ሰበቦች አንዱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ግለተ–ስሜት ነው። አንዳንዴ የሆነ ሀሳብ ሲደግፍ  አንዳንዴም ተጻራሪውን አቋም ሲደግፍ ታገኘዋለህ፣  ለዚህ ሁሉ ትክክለኛ ልጓም እና ግለተ–ስሜትን የሚቆጣጠረው የየሸሪዓ እውቀት እና ጤናማ አዕምሮ ነው።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

حكم من تجاوز الميقات ليحرم من ميقات آخر الشيخ سليمان الرحيلي
የሀገረሩን የኢሕራም ሚቃት አልፎ ከመዲና ሰዎች ሚቃት ዙልሑለይፋ ላይ ኢሕራም ያደረገ ሰው ምንም ችግር የለበትም።
እርድም አይጠበቅበትም።

https://youtube.com/watch?v=0ZWvtofXTXo&si=3NNpya3SVDOUPuo5

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ችክ ብለው ከማይጠይቁት ጋር ሄዱ!

አንድ አቅመ ደካማ ለማኝ አንድን የገጠር ሰው አርዳታ ጠየቀ። ገጠሬውም እኔ ለሌላ ሰው የሚሰጥ ነገር የለኝም፤ ያለውም ለራሴ የምፈልገው ነው ብሎ መለሰለት። ለማኙም፥ “እራሳቸው ችግር አንኳ ቢኖርባቸው ሌሎችን የሚያስቀድሙ የት ገቡ?!” በማለት ጠየቀው፤ ገጠሬውም፥ “ሰውን ችክ ብለው ከማይጠይቁት ጋር ሄዱ!” ብሎ መለሰለት ይባላል።
(ቁርኣን የህይወት ብርሃን)
ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

/channel/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنّ أولى الناسِ بي يومَ القيامةِ أكثرُهم عليَّ صلاةً﴾

“በቂያማ ዕለት ከሰዎች ሁሉ ለኔ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው በኔ ላይ በብዛት ሰለዋት የሚያወርድ ነው።”

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

『ልብ ሲታመም የሚጠቅመውን ነገር ይጠላል፤ የሚጎዳውን ደግሞ ይወዳል።』ኢብኑ ተይሚያ

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ሐጅ ላይ ላላችሁ… በአያመ ተሽሪቅ የመጨረሻው ቀን ልክ ጀመራትን ጨርሳችሁ ከሚና ወደ መካ እንደተመለሳችሁ፤ ከ14ኛው ቀን ጀምሮ ወደ ሃገራችሁ የመመለስ ፍላጎታችሁ ይጨምራል። የሆነ ዒባዳን አጠናቃችሁ ረፍት ላይ ያላችሁ አይነት ስሜት አለው፤ የምትሠሩት ታጣላችሁ።

ዞሮ ዞሮ እንደ አካሄዳችሁ ወረፋ ነው የምትመለሱት ስለተባለ፤ ከወረፋችሁ ቀድማችሁ መምጣት የምትችሉበት ነገር ከሌለ ወረፋችሁ እስኪደርስ ድረስ እንደት ማሳለፍ እንዳለባችሁ ልጠቁማችሁ።

ጥቂት የማይባል ሰው ጀማዓህ ሶላት ራሱ እዛው ሆቴል አካባቢ ባለ መስጅድ ወይም ሆቴል ውስጥ ይሰግዳል እንጂ ሐረም ለመመላለስ ሲዘናጋ ይስተዋላል። እናንተ አላህ መርጧችሁ የተከበረው ቤቱን ዚያራ ወፍቋችሁ ሳለ፤ ሰው እንደት ወደዛ በሄድኩ እያለ እናንተ ከዚያ ለመውጣት አትቸኩሉ። ስለዚህ ወደሃገራችሁ እስከምትመለሱ ድረስ፤ የሥራና የቤተሰብ ጭንቀቱ እንዳለ ቢሆንም ያላችሁን ቆይታ አጣጥሙት።

ፈጅር ላይ ቀደም ብላችሁ ከእንቅልፋችሁ ተነሱና ወደ ሐረም ሂዱ፤ ተሃጁዳችሁንና ዊትራችሁን ሰጋግዳችሁ፣ እዛው ፈርዱን ከሰገዳችሁ በኋላ ጸሐይ እስከምትወጣ ድረስ እዛው እየቀራችሁና ዚክር እያደረጋችሁ በማሳለፍ ሹሩቃችሁን ሰግዳችሁ ወደ ሆቴል በመመለስ ቁርስ ብሉና እስከ ዙህር ተኙ። ዙህር ላይ ምሳ ብሉና ወደ ሐረም በማቅናት ዙህራችሁን ሰግዳችሁ እስከ ዒሻእ እዛው አሳልፉ። በመሃል እንቅልፍ ካለም ከዙህር እስከ ዐስር ባለው የሆነች ያክል አረፍ በሉ። ከዐስር በኋላና ከመጝሪብ በኋላ ሙሐደራዎችና ደርሶች ስለሚኖሩ ዐረብኛ የምትችሉ ዘወር ዘወር ብላችሁ አዳምጡ። በ74 ቁጥር ግራውንድ ላይ ብትገቡም ተመዝገቡና ከጠዋት እስከ ማታ የቁርኣን ሒፍዝና ሐለቃ ስላለ ተሳተፉ። ብዙ አስተማሪ ዶክተሮች አሉ። ከዚያ ዒሻእን ሰግዳችሁ ወደ ሆቴል መጥታችሁ ራት በልታችሁ እስከ ፈጅር ለጥ ማለት ነው።

ከዐስር በኋላና በመሳሰሉት ወቅቶች ሲመቻችሁ ጠዋፍ እያደረጋችሁ፣ ካዕባን በዓይናችሁ ብሌን በቀጥታ በምታዩበት ቦታ ላይ በመሆን እያጣጣማችሁ፣ ቁርኣናችሁን እየቀራችሁ፣ ዚክርና ዱዓችሁን እያደረጋችሁ ብታሳልፉ፤ እመኑኝ ያ ቶሎ ወደ ሃገሬ በገባሁ እያለ መሄጃ ቀኑ የናፈቀው ልባችሁ ጭራሽ ሃሳቡን ቀይሮ መሄጃ ቀኔ ደረሰ እያለ ይጨነቃል።


ሞክሩት'ማ!
ደግሞ አንድ ሰው አንድን ዒባዳህ ሲያጠናቅቅ፤ የዛ ዒባዳው ተቀባይነትና ፍሬ ማፍራቱ የሚታየው ከዚያ በኋላ ባለው ጥንካሬና ድክመቱ ነው።

አላህ ያግዛችሁ፤ ይቀበላችሁም።

||
t.me/MuradTadesse

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

#قالَ: قالَ رَجُلٌ: لَأَتَصَدَّقَنَّ بصَدَقَةٍ، فَخَرَجَ بصَدَقَتِهِ، فَوَضَعَهَا في يَدِ سَارِقٍ، فأصْبَحُوا يَتَحَدَّثُونَ: تُصُدِّقَ علَى سَارِقٍ فَقالَ: اللَّهُمَّ لكَ الحَمْدُ، لَأَتَصَدَّقَنَّ بصَدَقَةٍ، فَخَرَجَ بصَدَقَتِهِ فَوَضَعَهَا في يَدَيْ زَانِيَةٍ، فأصْبَحُوا يَتَحَدَّثُونَ:................الحديث
[صحيح البخاري]

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

قال الله تعالى: ﴿فإذا قضيتم مناسككم فاذكروا الله كذكركم آباءكم أو أشد ذكرا﴾
አላህ አዘወጀለ እንዲህ ብሏል፡-
(የሐጅ ሥርዓቶቻችሁን በፈፀማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከዚያም በላይ ማውሳት አላህን አውሱ።)

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

🔴 ሐጅ መብሩር!
አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሐጅ ምልክቶች አንዱ፤ ሙስሊሙ ከሀጅ በኋላ ያለው ሁኔታ ከሱ በፊት ካለው ሁኔታ የተሻለ መሆኑ ነው።
ይህም በአላህ ቃል ውስጥ የተመሰከረ ነው፡- {እነዚያንም የተመሩትን መመራትን (ሂዳያህ) ሰጣቸው። ፈሪሀንም ( አላህን መፍራትንም) ሰጣቸው።} (ሱረቱ ሙሐመድ፡ 17)
ሐሰን አል-በስሪ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
“ተቀባይነት ያለው ሐጅ ምልክቱ፦ አንድ የሐጅ ተጓዥ ለዱንያ ያለው ግምት ፣ስግብግብነት ቀንሶ ለአኼራ ህይወቱ ክጃሎቱ ጨምሮ መመለሱ ነው።”

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ዙልሂጃ 11 የዒድ ማግስት"የውሙል ቀር" ማለትም ሁጃጆች ሚና ላይ ተረጋግተው የሚቀመጡበት ዕለት ሲሆን ይህንን ቀን አስመልክተው የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
🔖"አላህ ዘንድ ከሁሉም ከቀናቶች በላጩ ቀን የውሙ ነሕር(የዒደል አድሓ ቀን) ነው።በመቀጠልም የውሙል ቀር።" 📚አቡዳዉድ ዘግበውታል አልባኒ ሰሒህ ብለውታል።
🔖አቡ ሙሳ አልዐሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የዒድ ቀን ኹጥባ ሲያደርጉ እንዲህ ብለዋል፦
"ከዐረፋ ቀን በመቀጠል ሦስቱ ቀን የዚክር ቀናት በነዚህ ቀናት የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት አለው።ስለዚህም ክጃሎታችሁን ወደ አላህ ከፍ አድርጉ ።" 📚【ተፍሱሩ አጠበሪይ (4/203—206)】
🔖ዒክሪማ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ብለዋል ፦
"ሰሓቦች በነዚህ አያም ተሽሪቅ ቀናት ይህን ዱዓ ያበዙ ነበር። "ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺራ ሐሰነተን ወቂና አዛበ አንናር።"
📚【ኢብኑ ረጀብ (ለጣኢፍ አልመዓሪፍ)】

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የሴቶች አረፋ በሚል ማረድ በሸሪዓዊ እይታ እንዴት ይታያል?
በሸይክ ኢልያስ አህመድ ፊዘሁሏህ
t.me/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“አላህ ዱዓችሁን እንደሚቀበላችሁ እርግጠኛ ሆናችሁ ዱዓ አድርጉ።
እወቁ!  አላህ ልብ ዝንጉ ሆኖ የሚደረግ ዱዓን አይቀበልም።”



t.me/sultan_54

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

ይህ የሐጅን ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት የሚያብራራ አጭር ጽሁፍ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል–ዑስይሚን ተዘጋጅቶ ወደ አማርኛ ተመልሶ የተሰራጨ ነው።
በአላህ ፍቃድ የየእለቱን የሐጅ ተግባር ከዚህ ቀጥሎ ከፋፍለን እናቀርባለን:–

(ክፍል–1)

የመጀሪያው ቀን ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን የውመ አት–ተርዊያ በመባል የሚታወቀው ነው።
1️⃣ ለሐጅ ኢህራም ወይም ኒያ ማድረግ
በመካ ከተማ እና በዙሪያዎ ያለ ሰው ካለበት ቦታ ታጥቦ፣ (አካሉን) ሽቶ ተቀብቶ፣ የኢህራም ልብሱን ለብሶ እና "ለበይከ ሀጀን፤ ለበይከ አላሁመ ለበይክ፤ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለከ" በማለት ኢህራም(ኒያ) ያደርጋል። ከዚህ ቀን በፊት መካ ያልመጣና ከሚቃት ክልል ውጪ ለሀጅ ወይም ዑምራ የሚመጣ ሰው የሚቃት ክልሉን ያለ ኢህራም(ኒያ) ማለፍ የለበትም።* 2️⃣ *ወደ ሚና መጓዝ*
ወደ ሚና ይጓዛል እዚያም የዘጠነኛው ቀን ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ ይቆያል። የስምንተኛውን ቀን የዙሁርን፣ የዓስርን፣ የመግሪብን እና የዒሻን እንዲሁም የዘጠነኛውን ቀን ፈጅር ሰላቶች በየወቅታቸው እና አራት አራት ረከዓ የሆኑትን የዙህር የዓስርና የዒሻእ ሰላቶች ሁለት ሁለት ረከዓ በማድረግ አሳጥሮ ይሰግዳል።

ይቀጥላል…

ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ
አላህ ያግራልን!

✍️ ጣሀ አህመድ

🌐
/channel/tahaahmed9

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
📚 ቡኻሪና ሙስሊም

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

«ከጌታህም ወደ ኾነች ምሕረትና ስፋቷ ሰማይና ምድር ወደ ሆነችው ጀነት ተቻኮሉ።”

ሞት አይጠብቅምና ፍጠን! ነገ ተውበት እገባለሁ፣ ነገ የንባብ ፕሮግራም አዘጋጅቻለሁ፣ እና የአመጋገብን ስርአት ለመከተል ቃል እገባለሁ። ብለህ…

ድንገት ነገ ይመጣል፣ እናም  ያሰብከውን ምንም ነገር አልተፈፀመም ፣ ሁላችንም ሞት ሩቅ እንደሆነ እናምናለን ፣ ከደቂቃዎች በፊት የሞቱት  እነደኛው እንሞታለን ብለው አላሰቡም። የጥቂት አፍታዎች መዘግየት ሙሉ ህይወትን ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል።

ነገር ነገርን ያነሰዋል እንደሚባለው…

አል-ሰናቢሂ እንዲህ ይላሉ፡-
"እኛ ነብዩን  ለማግኘት ተመኝተን ከየመን ስደተኛ ሆነን  መዲና ስንደርስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ከዚህ አለም በሞት ተለይተውናል።"

አምስት ምሽቶች አርፍደው መገኘታቸው የሰሓባ የሚባለው ታላቅ ክብር አሳጣቸው።

ስለዚህ ፍጠን፣ የአንድ ሰአት መዘግየት ብዙ የጀነትን ፀጋዎች ሊያሳጣህ ይችላል።

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

አንድ ሙስሊም ለሐጅ ወይም ለዑምራ ለመጓዝ ከወሰነ ቤተሰቦቹን እና ጓደኞቹን አላህን እንዲፈሩ መምከር አለበት፣ ሙስሊሙ  የአላህን ትእዛዙን መፈጸም እና የተከለከሉትን ነገሮች መራቅ አለበት።

የተበደረውን እና ዕዳ ያለበትን ይጽፍ ምስክር ሊኖረው ይገባል። ከሀጢአቶች ሁሉ በቅንነት ለመፀፀት መቸኮል አለበት ምክንያቱም አላህ جل جلاله እንዲህ ይላል፡-

"ሁላችሁም አማኞች ሆይ ትድኑ ዘንድ ወደ አላህ ተጸጸቱ (ተውበት አድርጉ)"
[አን-ኑር 24:31]

እውነተኛ ንስሐ ማለት ኃጢአትን መተው፣ ከዚህ በፊት በሠራው ነገር መጸጸት እና ወደ ኃጢአት ላለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ሰዎችን በአካልም ሆነ በገንዘብ የበደለ ወይም ክብራቸውን የሚነካ ነገር ተናግሮ ከሆነ ጥፋቱን ማረም ወይም ከመጓዙ በፊት ይቅርታ እንዲያደርጉለት መጠየቅ አለበት ምክንያቱም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በሀብቱ ወይም በክብሩ ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርም ሆነ ዲርሃም ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ይቅርታ ይጠይቀው። ለርሱ መልካም ሥራ ቢኖረውም ለእሱ ይሰጣል። ከሰራው በደል ጋር ተመዛዛኝ  ሀሰናት ይወሰድበት። ለእሱ ምንም አይነት መልካም ስራ ከሌለው ከባልደረባው መጥፎ ስራ ከፊሉ ተወስዶ ሸክሙ ላይ ይጨመራል።”

ለሐጅ ወይም ለዑምራ ንፁህ ሀብቱ (ማለትም ሀላል የሆነውን እና ከሃላል ምንጭ የሚገኘውን) መጠቀም ይኖርበታል ምክንያቱም ከነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በተዘገበው ሰሒህ ዘገባ ላይ እንዲህ ብለዋል፡- “በእርግጥ አሏህ ንፁህ ነው ከመልካም ነገር (ማለትም ሀላል)በስተቀር ምንም አይቀበልም።"
አቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰው ሐጅ አድርጎ ሐላልና ንጹህ ሲሳይ ይዞ ቢወጣና ቢያስቀምጥ እግሩ በመጓጓዣው ውስጥ  'ለባይክ አላሁመ ለበይክ' ሲል ከሰማይ ጠሪ ይጠራውና፦" ሲሳይህ ​​ሃላል ነው፣ መጓጓዣህም ሃላል ነው፣ ሀጅህም ተቀባይነት ይኖረዋል።"  ኃጢአትህም ይሰረይልሃል።" ይለዋል።
ስንቁ ሀራም ከሆነ ግን፦
ጠሪው ከሰማይ “ስንቅህ ሐራም ነው፤ ገንዘባችሁም ሐራም ነው፤ ሐጅህም ተቀባይነት የለውም።” ይለዋል።

ሁጃጅ የሆኑ ሰዎችን  ምንም ፍላጎት ማሳየት የለበትም፣ እነሱን ከመጠየቅ ይቆጠብ አለበት።
ምክንያቱም ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
“ክብሩን ለማስጠበቅ አላህን እንዲረዳው የሚለምን አላህ ይረዳዋል። እሱን; ከጥቅም ውጪ ሆኖ የአላህን እርዳታ የሚፈልግ ሰው አላህ ራሱን ያዘጋጃል።"
እሳቸውም (የአላህ በረከትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አሉ፡-
“አንድ ሰው በቂያማ ቀን ፊቱ ላይ ቁራጭ ሥጋ  የሌለው ሆኖ እስኪመጣ ድረስ ሰዎችን ይጠይቃል።"

ሐጃጁ ሐጅና ዑምራን በመስራት የአላህንና የኋለኛይቱን ዓለም ውዴታ በመሻት በነዚያ የተቀደሱ ቦታዎች ላይ በንግግርና በተግባር ወደ አላህ መቃረብን መሻት ይኖርበታል። ወደ ሐጅ የመሄድ ፍላጎት ዓለማዊ ጥቅም ወይም  መኩራራት መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም እነዚህ ከዓላማዎች ሁሉ በጣም የሚገዝ ነው። ለመልካም ሥራዎች ውድቅና ተቀባይነት የሌላቸው ምክንያቶች ናቸው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል ትርጉሙ):

" የቅርቢቱን ሕይወትና ብልጭልጭዋን የሚፈልግ ሰው። ለነሱም ሥራቸውን በውስጧ እንሞላቸዋለን። ለነሱም በእርሷ ምንም የሚቀነስ የላቸውም።"

Читать полностью…

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ዘውትር ስርዓት ባለው መልኩ ማንበብ የሰዋስው፣ የቋንቋ ክህሎት እና የፅሁፍ ችሎታን ለማሻሻል ይረዳል።

Читать полностью…
Subscribe to a channel