ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
➪ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦
🌹《አንድ ሙስሊም ከወንድሙ የሚደርሰውን ወሬ በመልካም መተረጎም እየቻለ በመጥፎ ጥርጣሬ ሊያስተናግደው አይገባም።》
ሊቢኒል ሙፍሊሕ 2/47}
📚{አልአዳቡ አሸርዒያህ
#ሑስኑ_ዘን_በወንድሞች_መካከል_ቢሰፍን_ኖሮ_በርካታ_አለመግባባቶች_በከሰሙ_ነበር።
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።»
ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።
تلاوة خاشعة من سورة مريم
#بندر_بليلة
#اكسبلور #
اجر_لي_ولكم
#تلاوة_خاشعة
quran#
#سبحان_الله_وبحمده_سبحان_الله_العظيم
#سبحان_الله_وبحمده_سبحان_الله_العظيم
#اللهم_صل_وسلم_على_نبينا_محمد
#تلاوة_حجازية
ሀሰን ታጁ እና የኸዋሪጆች መመሳሰል!
ሐሰን ታጁ ሰሞኑን የምርጫ ግዜ ስለተቃረበ፣ በመጅሊስና አመራሮች ላይ ከባድ የማጠልሸት ዘመቻ እና ቅስቀሳ አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
እስከ ደሴው የአንድነት እና ሰደቃ ፕሮግራም ላይ አሁን ወሃቢያ እያለ ከሚዘልፋቸው እና ከሚቀጥፍባቸው ሰዎች ጋር ትግሉን ደግፎ ተሳትፎ ሲያደርግ ነበር፣ ይሁንና የኋላ ኋላ መታሰር ስላልፈለገ የወያኔ ተልእኮ ተሰጥቶት መንግስትን ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ሽማግሌ፣አስታራቂ በመመስል ከአቋማቸው እንዲመለሱ ሲወተውታቸው ስላልተቀበሉት፣ በመጅሊስ የስልጣን እርከን ላይ ስላልተሳተፈ በእልህ ከአሕባሽ ጋር ተደምሯል።
ምን ስለከሉት?!
ዲኑን በነፃነት እንዲያረምድ እንቅፋት አልሆኑበት፣ እንደልቡ ሲዛለፍና ሲቀጥፍ አልከሰሱት አላሳሰሩት፣ ይህን ያህል ጥላቻ የሚሰብከው ለምን ይሆን?ከኸዋሪጆች አንዱ ወደ ሐሰን አል-በስሪይ መጥቶ፣ እንዲህ አላቸው፦
“በኸዋሪጆች ላይ ምን ይላሉ?”
ሐሰን አል በስሪይም፦“እነሱ የዱንያ ሰዎች(ጥቅመኞች) ናቸው።” በማለት መለሱ።
ሰውየውም፝ “ይህን ከየት አምጥተው ሊናገሩ ቻሉ? ከእነሱ ውስጥ አንድ ሰው ጦሩ (መሳሪያ ታጥቀው)እስኪስከበረ ድረስ ይጓዛል፣ ከቤተሰቡና ከልጆቹም ተለይቶ ለጂሃድ ይዘምታል!”
ሐሰን አል በስሪይም ፦"እስኪ ንገረኝ አሚርህ ሶላት፣ ዘካ፣ ሐጅ ወይም ዑምራ እንዳትሠራ ይከለክልሃልን?”
ሰውየው አለ፡ “አይ አይከለክለኝም።” በማለት መለሰ።
ሐሰን አልበስሪይም ፣ እርሱ (የምትዋጋው) ለዓለማዊ ጥቅም ብለህ አንተ በርሱ ላይ አመፅ የምታነሳሳወ።” በማለት መለሱለት።
📚البصائر والذخائر، لأبي حيان التوحيدي ت 400ه)
ጀግንነት ሁል ጊዜ በመናገር አይደለም፣ ጥበብም ሁል ጊዜ በዝምታ ውስጥ አይደለችም። አላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ ከጅለው በዒልም ለሚናገሩ እና በጥበብ ዝም የሚሉ ሁሉ የአላህ እዝነት በነርሱ ላይ ይሁን።
✍አሸይኽ ሱለይማን አር–ሩሓይሊ ሐፊዘሁላህ
ከቲውተር ገፃቸው የተወሰደ
الشيخ عبد الودود مقبول حنيف
Читать полностью…أبو بكر الشاطري
نبرة مع الخشوع
"የመልክተኞቹ አለቃ የሆኑት ሰይዲ
ﷺ
ጥሪያቸው ከቁረይሽ፣ ከአይሁድ፣ ከክርስቲያኖች እና ከመናፍቃን "አዛ" (ጥቃት) አላመለጠም። ታዲያ ... የአሕሉ አስ–ሱናህ (የሰለፎች) ጥሪ ከጥቃት ነጻ እንዲሆን ትፈልጋላችሁን?!
በሱና (በነቢዩ ﷺ
መንገድ) ላይ ጸኑ፤ ትዕግስትም አድርጉ።"
— አሽ–ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዑመር ባዝሞል
«ፈተናዎች(ችግሮች) የሚቆዩት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፤ የሰው ልጆች ዕድሜ እንደሚጠናቀቅ ይጠናቀቃሉ።»
ስለዚህ በታጋሽነት ወደ አላህ ተጠጋ! 🌟
ኢብኑል ቀዪም /መዳሪጅ አስ–ሳሊኪን (374)
የተሰበሩ ቀልቦችን ጠግኑ፣ ለሰዎች ስሜት ግምት ይስጡ፣ ከመናገርዎ በፊት ቃላቶቻችሁን ጠንቅቀው ያዘጋጁ፣ በተግባራችሁ ርኅሩኅ ይሁኑ፣ የጋራ አኗኗራችሁን አስቡ፣ ማንንም አትጎዱ፣ ለሰዎች መልካም ቃል ተናገሩ፣ ንጹህና ገርነት ያለው ሕይወት ኑሩ፤ ይህ የነቢያት መንገድ፣ የታላለቆች አኽላቅ ነውና።" 🌸🌺
Читать полностью…أراد الله بعبده خيرًا يسّر لسانه للصلاة على محمد ﷺ.
ابن الجوزي
اللهم صلِّ وسلِّم وبارك على نبينا مُحمّد.🌿
ዒባዳዎች ከባድ አልነበሩም፤
በወንጀሎች የተነሳ ልቦቻችን ተበላሽተዉ እንጂ…
እስቲግፋር እናብዛ...🥀
ከሠለፎቹ መካከል አንዱ አንዲህ ብለዋል፦
«ሰዎች በነገስታት ደጅ ልቅናን ይፈልጋሉ ፥ ነገርግን አላህን በመታዘዝ ውስጥ እንጂ አያገኙትም።»
إغاثة اللهفان (1/٧٨)
«ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ፡፡ በመልካቹም አስጠጋኝ።»
📚ዩሱፍ (101)
/channel/sultan_54
🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ
🎙 خطبة الجمعة
نعمة العافية
✨የ ዓፊያ ዋጋ
🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር
🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ
🗓 ዙልቂእዳ 12/1446 አ/ሂ
ولو كانت الدنيا تدوم لأهلها ..... لكان رسول الله حيا وباقيا
/channel/sultan_54
ነሲሓ ሪሳላ :
🔖 ሸይኽ ሙሀመድ ዓሊ አደም አል’ ኢትዮቢ ( ረህመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ :
" በዚህ ፈትና በበዛበት ዘመን እራሱን ተቆጣጥሮ እውቀትን ለመፈለግ የሚጥር (ወጣት) ከአላህ ወልዮች ይቆጠራል ። "
[📚ፈዋኢድ አል‘ኢልሚያህ
ወዱረሩ ተርበውያ ገፅ–19 ]
🗓 ሀሙስ 30 , 2017
🗓 ዙልቂዕዳ 10 , 1446 ሒ
============
ነሲሓ ቲቪ
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!
📡 Nilesat /11545 / V / 27500
@nesihatv
🔴 ማለዳዎን በዚህ በሚማርክ ቲላዋ ይጀምሩና ቀንዎን ያስውቡ!
تلاوة عاطرة للشيخ علي جابر رحمه الله
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
( عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين من بعدي ...)
”አደራችሁን ሱናዬን አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ከእኔም በኋላ የተመሩ
እና የተቃኑ ምትኮቼ ሱናንም አጥብቃችሁ ያዙ፡፡
ከታዋቂ የአገር ሽማግሌዎችና ምሁራን አንዱ የነበሩት ሀጂ ደርባቸው መሐመድ ዛሬ ከጁምዓ ሰላት በፊት ወደ አኼራ ሄደዋል።
አላህ ይዘንላቸው፤ ስራቸውን ይቀበላቸው ወንጀላቸውንም ይማራቸው። የቀብር ስነስርዓቱ በአላህ ፈቃድ ዛሬ አስር ላይ በኮልፌ መካነ መቃብር የሚፈፀም ይሆናል።
አል ዓፊያ አ/ማ የቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ልጃቸው ሸይኽ አዩብ ደርባቸው፣ ለመላው ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።
ረሒመሁላሁ ረህመተን ዋሲዓህ
وفاة الحاج درباتشو محمد والد استاذ أيوب رحمه الله اليوم قبل الجمعة والدفن وقت العصر إن شاء الله.
رحمه الله رحمة واسعة
إنا لله وإنا اليه راجعون
ቃዲ ሹረይህ እንዲህ ይላሉ፦፡-
«ፊትናዎች በመጡ ጊዜ አትጠይቁ፣ አታውሩም!»
ምንጭ፦ _ሲያር አዕላም ነብላእ
ማለትም ስለእርሷ መረጃ አትጠይቁ፤ ስለ ፊትናው መረጃ ካላችሁም ለማንም አትንገሩ፣ ፊትናውን በማራገብ ወይም በማስፋፋትም አትሳተፉ።
በዚህ ዘመን ይህ ምክር ምንኛ አስፈላጊ ነው!?
አሏህ ሆይ ከይፋም ሆነ ከተደበቀውም! ከክፉ ፊትናዎች ጠብቀን።
በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ይህ ምክር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ያልተረጋገጠ መረጃ ማራመድ ህብረተሰቡን ሊያደናግር ብሎም ግዜውን ያላግባብ ሊያባክን ስለሚችል፣ ይህን የሰለፎችን ንግግር ከግምት ማስገባት አስፈላጊ ነው።
ኢስላማዊ የልጆች አስተዳደግ ዋና ዋና መርሆች**
ኢስላም ለልጆች አስተዳደግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ሃይማኖት ነው። በቁርአን እና በሐዲስ መሠረት፣ ልጆችን በአላህ ፍራቻ፣ በአኽላቅ፣ እና በጥበብ ማዳበር ይገባል። ከኢስላማዊ ተርቢያ ዋናዎቹ መርሆች መካከል፦
### 1.ስለ ተውሒድ (አላህን ብቻ መገዛት) ማስተማር
- በመጀመሪያ ልጆችን ስለ አላህ ብቸኛ ተመላኪነት (ተውሒድ) አስተምሩ።
- "ልጅህ አፍ መፍታት ሲጀምር ለእሱ 'ላ ኢላሀ ኢላ አላህ' (ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም) የሚለውን ቃል ደጋግመህ አሰተምር።"
- በተፈጥሮ ውስጥ የአላህን ምህረት፣ እና በፍጥረታት ውስጥ የአላህን መነሩን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ያሳዩኣቸው።
### 2. የነቢዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ምሳሌ መከተል
- ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ለልጆች የሚያሳዩትን ፍቅር፣ ርኅሩኅነት እና ትምህርት ይከተሉ።
### 3. የስነ ምግባር እሴቶችን ማስተማር
- እውነትን መናገር፣ አክብሮት፣ ምሕረት፣ እና ፍትሕ እንዲያውቁ ያድርጉ።
- "እውነትን ተናገሩ፣ ምንም እንኳን ከራስዎ ጋር ቢሆንም።" (ቡኻሪ ሀዲስ)
- ሀራም ነገሮችን እና ድንጋጌዎችን (ሀላል እና ሀራም) አስረዱኣቸው።
---
### 4. የሰላት እና የቁርአን ትምህርት
- ልጆችን ከህፃንነታቸው ጀምሮ ሰላት፣ ዚክር፣ እና ቁርአን አስተምሩኣቸው።
- "ልጆቻችሁን ሰላትን በሰባት ዓመት ያስተምሩ።" (ሀዲስ)
- ቁርአንን በማንበብ እና ትርጉሙን በማወቅ እንዲያድጉ ያግዙኣቸው።
### 5. ፍቅር እና ቅጣት መለያየት
- ፍቅርን አሳዩ፣ ነገር ግን ስህተት ሲፈፅሙ በጥበብ የሚማሩባቸው ቅጣት ይስጡ።
---
### 6. የቤተሰብ ግንኙነትን ማጠናከር
- ከልጆች ጋር ጊዜ ያሳልፉ፣ የታላለቅ ስብእናዎችን ታሪኮችን ይንገሯቸው፣ በቤተሰብ ውስጥ የሰላም አካባቢ ይፍጠሩ።
- "እናንተ አማኞች ሆይ! ነፍሶቻችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት አድኑ።" (አትሕሪም:6)
### 7. ኢስላማዊ ትምህርት በጥበብ ማዳበር።
- ልጆችን በሥነ-ምግባራዊ ትምህርት ያንፁ።
- "ዕውቀትን መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።" (ሀዲስ)
### 8. የልጅን መብት ማክበር
- ልጆች የሚገባቸውን **ፍትሕ፣ አክብሮት፣ይስጡ።
“አላህ ለባሪያው መልካምን በሻ ጊዜ ፣ አንደበቱን በነቢዩ አለይሂ ሰሏት ወሰላም በማውረድ ላይ ያገረዋል።”
(ኢብኑል ጀውዚ)
ሰለዋት እናብዛ ጁምዓም አይደል?!
خشوع وبكاء شديد للشيخ الشربم
Читать полностью…«ዱዓእን ያዘወተረ፣ የንጉሱን በር ማንኳኳትን ሙጥኝ ያለ... ለእርሱ ይከፈትለታል!»
አቡደርዳእ/ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ
➪ስራህን በአግባቡ ሳትሰራ ቀርተህ አለቃህ ለብቻህ እፈልግሃለሁ ሲልህ ምን ያህል ያስፈራል፣ያስደነግጣል! አይደል?!
☞︎︎︎የአለቃዎች አለቃ ረቡል ዓለሚን ዘንድ የቂያማ ዕለት ለብቻህ ሲያናግርህስ…
𝐓𝐞:http://t.me/sultan_54
وكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا
"ሁሉም፤ በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነዉ ወደርሱ መጪዎች ናቸዉ"
【መርየም፤95】
ጌታችን ሆይ!
እዘንልን፣ወንጀላችንን ደብቅልን፣ይቅርታም አድርግልን።
ዩሱፍም ወንድሞቹ( እርሱ ቢሰርቅም ከዚህ በፊት ወንድሙም ሰርቆ ነበር) ባሉ ጊዜ በውስጡ ዋጥ አድርጎ ያዘ ቅጥፈታቸውን ይፋ አላደረገም(አልተጋፈጣቸውም)**
(ዩሱፍ :77)
በእርግጥም! አንዳንዴ መወቃቀሰ ልቦችን ያጠራል፣ ቁስሎችን ያፅዳል፣ ቁስል ከመሰፋትዎ በፊት ፍቱን ፈውስ ነው።
ግን ሁሉም ሁኔታዎች ለመወቃቀስ የማይመቹ ሊሆኑ ይችላሉ።
አንዳንዴ ሁሉን ነገር ብትረዳም እንዳልተረዳህ በመምሰል ማሳለፍ አለብህ!
ሁሉን ነገር ባየህም ጊዜ እንዳላየህ ሆነህ ማለፍ አለብህ!
አፍታዊ ሽንፈት ቢመስለህም እንኳ!
አንዳንዴ አውቆ እንዳላወቀ ማለፍን ተለማምድ።
የታላላቅ ስብእና ባለቤት፤ አጋጣሚውን ሁሉ ተጠቅሞ ሰዎችን ልክልካቸውን ከመናገር ይልቅ ሰዎችን ማግባባት የተሻለ መሆኑን ይገነዘባሉ።
ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም በውስጣቸው ያለውን ቅሬታ አምቀው ይዘው፤ ልክልካቸውን በመናገር እውነታውን አላፍረጠረጡትም፣ ምክንያቱም አውቆ ማለፍ ከትላልቅ ስብእናዎች አንዱ ስለሆነ ነው!
ኢማም አህመድ እንዲህ ይሉ ነበር፡
"ከሰዎች ጋር ጤናማ መስተጋብር ለመመስረት ዘጠኝ አስርተኛ በመተላለፍ ውስጥ ነው።"
ኢማም ሻፊዒ ደግሞ፡ "ብልሃተኛው ጠቢብ ምንም እንኳ የተረዳ ቢመስልም የሚተላለፍ ነው።" ይላሉ።
አክሠም ኢብን ሰይፊ እንዲህ ይላሉ፦"አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ባለው አኗኗር ጠበቅበቅ ያለ፣ ከሰዎች በፍጥነት ይለያያል፣ ፈታ ያለ ሰው ግን ከሰዎች ጋር ይቀራረባል፣ ደስታም በመተላለፍ ውስጥ ነው።"
ኢብኑ አል ቀዪም እንዲህ ይላሉ፡ "ከኩሩ(ከላቁ) ባህሪያት አንዱ የሰዎችን ጥፋቶች መተላለፍ ነው!"
📕- አድሃም ሸርቃዊ || ረሳኢሉን ሚነል ቁርኣን 🤍🤍