techtalkethio | Unsorted

Telegram-канал techtalkethio - Tech Talk Ethio

-

Subscribe to a channel

Tech Talk Ethio

🕹PYTHON ለመማር ሚጠቅሙ መንገዶች


❇️ Python ከ high-level programming language ሚመደብ አንዱ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ ነው ።

❇️ It was founded in 1991 by developer Guido Van Rossum.


▶️ Learn Python Basics

╰┈➤ Syntax
╰┈➤ Variables
╰┈➤ Operators
╰┈➤ Loop
╰┈➤ Condition
╰┈➤ Function

▶️ Python Intermediate Level

╰┈➤ Object Oriented Programming
╰┈➤ Data Structures
╰┈➤ File Handling
╰┈➤ Error and Exception Handling
╰┈➤ Custom Exception

▶️ Python Advanced Level

╰┈➤ Working with modules
╰┈➤ Decorators
╰┈➤ Lambda Functions
╰┈➤ Comprehension
╰┈➤ SQLite Database
╰┈➤ API

▶️ Learn about Git/Github

╰┈➤ Version Control System
╰┈➤ Code Management
╰┈➤ Understanding Git/GitHub
╰┈➤ Preparing Github Repositories
╰┈➤ Uploading Projects on Github

▶️ Do some Python Projects

╰┈➤ Calender
╰┈➤ Alarm Clock with GUI
╰┈➤ Web Scrapper
╰┈➤ Bacon Desktop Apps
╰┈➤ Python Snake Game


❇️ ብዙ ተማሪዎችና Developer'ኦች አሁን ላይ ምርጫቸው እያደረጉት ነው (ማርኬቱም ከፍ ብሏል 😉)

#Share
@techtalkethio

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለአምስት ሚሊዮን ያህል አፍሪካዊያን በሳተላይት ኢንተርኔት ሊያቅርብ ማቀዱን አስታወቀ።

⚡️ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለአምስት ሚሊዮን ያህል አፍሪካዊያን በሳተላይት ኢንተርኔት ሊያቅርብ ማቀዱን በዋሽንግተን እየተካሄደ ባለው የአሜሪካና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ይፋ አድርጓል።

⚡️ኩባንያው ለግብጽ፣ ሴኔጋልና አንጎላ አንዳንድ አካባቢዎች አሁኑኑ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርና ለናይጀሪያና ኮንጎ ደሞ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥረቱን እንደሚገፋበት ገልጧል። ሆኖም ለአፍሪካ አገራት የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽፋን አለመኖር እንቅፋት እንደሆነ ኩባንያው መግለጡን የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

Share @techtalkethio

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

📲Ip Webcam

💢ይሄን 👆 አፕ በመጠቀም ስልክዎን ልክ እንደ security camera ማድረግ ይችላሉ።

✔️የሚጠቀመው #WiFi_hotspot ሲሆን እናንተ #Hotspot አብርታችሁ ሌሎቹ እንደ #ካሜራ የሚጠቀሙባቸው ስልኮች📲 connect ያደርጋሉ።

✔️4 ስልኮች📱 ድረስ እንደ #ካሜራ መጠቀም ያስችላል።

✔️በስልክዎ ካሜራዎቹን📸 Zoom, Record, Capture, Turn Off, On ማድረግ ይችላሉ።

✔️ሰርቨሩን ሲያስጅምሩት በ kb size የሆነች ፋይል እዛው ላይ ዳውንሎድ ያደርጋሉ።

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

ኢትዮ ቴሌኮም ከዛሬ ጀምሮ በአጠቃላይ ጥቅል አገልግሎት ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ጥቅል ሳይገዙ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞችም ከ20 እስከ 30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉንም ገልጧል።

ከሶስት እስከ አስር ደቂቃ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ከመደበኛው ታሪፍ የ20 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ትናንት የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ከአስር ደቂቃ በላይ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ደግሞ የ30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ተደርጓል ብለዋል።
(ኢዜአ)

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

🍡 ከጎግል መረጃ የመፈለጊያ #ጠቃሚ ስልቶች ልጠቁማችሁ

🍢የዘወትር የመረጃ መፈለጊያ የሆነው የጎግል ፍለጋችን ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ ስልቶችን ልንጠቁማችሁ ወደናል።

1⃣. ትክክለኛውን ቃል ለመፈለግ ቃሉን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት ለምሳሌ፡- “Android” በማለት ጎግል ብናደርግ ከዚሁ ጉዳይ ጋር ብቻ የተገናኙ መረጃዎችን በሰፊው እናገኛለን።

2⃣. ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ለመፈለግ

በቅርጽም ሆነ በይዘት ተቀራራቢነት ያላቸውን ድረ ገጾች ለማግኘት ወይም እንደ እከሌ አይነቱን ድረ ገጽ ፈልግልኝ ለማለት related: የሚለውን አስቀድመን የድረ ገጹን አድራሻ እናስከትላለን፤

ለምሳሌ፡- ጎግልን related:amazon.com ብለን ብንጠይቀው ከአማዞን ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ድረ ገጾች ውጤት ይሰጠናል።

3⃣. ጎግል የምንፈልገውን ብቻ እንዲፈልግልን ደግሞ ከቃላቱ በፊት የሰረዝ ምልክትን መጠቀም አለብን።

ይህም በተለይ በርካታ ትርጉም ያላቸውን ነገሮች ስንፈልግ የማንፈልገውን ለይቶ በቀላሉ የምንፈልገውን ጉዳይ ማግኘት ያስችላል።

ለምሳሌ፡- terminator –movie ብለን ብንፈልግ የፍለጋ ውጤታችን ቴርሚኔተር ላይ ብቻ ያተኮረ እና ተርሚኔተር ስለተባለው ፊልም ፈጽሞ ያላካተተ ይሆናል።

4⃣. ድረ ገጾች ስለ አንድ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የሰሩትን በቀላሉ ለመፈለግ

አንድ ደረ ገጽ ስለሆነ ነገር ከዚህ በፊት የሰራቸውን ለመመልከት የምፈልገውን ቃል ከጻፍን በኃላ ክፍት ቦታ ሰጥተን site: ብለን በመጻፍ የምንጎበኘውን ድረ ገጽ አድራሻ በማስከተል መፈለግ፤

ለምሳሌ፡- barrack obama. Site: bbc.com ብለን ብንፈልግ ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን በተመለከተ በድረ ገጹ ላይ ያወጣቸውን ዘገባዎች ለመመልከት እንችላለን።

5⃣. ትርጓሜዎችን ለመፈለግ

የፊደላትን ትርጓሜ ለማወቅ እና ተመሳሳይ ፍቺዎችን ለመፈለግ define: አስቀድመን ቃሉን መጻፍና መፈለግ የተሻለ ውጤት ያስገኝልናል።

ለምሳሌ፡- define:injera ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ሰለ እንጀራ ዘርዘር ያለ መረጃ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ያለውን ትርጓሜ በስፋት ማግኘት እንችላለን።

በዚህ መንገድ የአንዳንድ ቃላትን ሰያሜ መነሻ እና ትርጉም ለማግኘትም ቀላል ነው።

6⃣. የተለያዩ የፋይል አይነቶችን ለማሰስ

ጎግል የፒዲኤፍ አልያም ፓወር ፖይንት ውጤቶችን እንዲሰጠን ለመጠየቅ የሚከተለውን አማራጭ እንጠቀማለን።

ለምሳሌ፡- “Scientific Journalism” filetype:pdf

7⃣. አዲስ የሆኑ እና ትኩረት የሳቡ አለማቀፍ ጉዳዮችን ለማግኘት

ከምንፈልገው ርዕሰ ጉዳይ በፊት የሃሽታግ ምልክትን ማስቀደም፤ ለምሳሌ #action2017 ብለን በመፈለግ በርካታ መረጃዎችን ማግኘት ያስችላል።

8⃣. በጎግል ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም

ጎግል ትራንዝሌት ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ዘርዘር ያሉ ጽሁፎችንም ለመተርጎም ያስችላል።

ለምሳሌ፡- hello የሚለውን ቃል ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ለመተርጎም translate english to french hello በማለት ጎግል ላይ መፈለግ እንችላለን።

9⃣. የረሳናቸውን ፊደላት ለማስታወስ

ጎግል የዘነጋናቸውን ቃላት እንዲያስታውሰን ኤስትሪክስን (*) መጠቀም እንችላለን። ኤስትሪክስን መጠቀም በተለይ የረሳናቸውን የዘፈን ግጥሞች ለማስታወስ ይረዳል።

ለምሳሌ፡- “Come * right now * me” የሚለውም የዘፈን ግጥም ጉግል ብናደርግ “Come Together” የሚል ርዕስ ያለውን የቢትልስ ሙዚቃ ግጥም ውጤቶች ይሰጠናል።

🔟. የአየር ሁኔታ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ዌዘር የሚለውን ቃል ከከተሞቹ አስቀድመን መፈለግ

ለምሳሌ:- weather Adiss ababa #techtalkethio

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

ዋይ ፍይ መስበርያ 6version deres yeseral

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

#tech_life_hacks

How to change your phone from 3G to 4G

⚠️Your phone must be #rooted

➡️Install root explorer

➡️Search for a file called 'persist.radio.lteon'

➡️Open that file and change it from 'false' to 'true' save

➡️Reboot your phone.
You will be able to see "LTE/wcdma/gsm (auto connect)" in network mode.

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።


🧑‍💻👩‍💻👨‍💻 #SHARE 👨‍💻👩‍💻🧑‍💻
@techtalkethio

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

Best websites for Academic Research
1. https://www.researchgate.net/search
2. https://scholar.google.com/
3. https://books.google.com/
4. https://www.ieee.org/
5. https://www.jstor.org/
6. https://www.science.gov/
7. https://www.sciencedirect.com/
8. https://www.base-search.net /

Share @techtalkethio

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

ሰላም ሰዎች በቅርብ በአዲስ ይዘት እንመጣለን Share አድርጉ

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

የስልካችሁ እስክሪን ከናንተውጭ እዳይሰራ ማረጊያ ነው።

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

✳️ሰላም Guys ዛሬ ልታውቋቸው እና ልትጠነቀቁዋቸው የሚገቡ ነገሮችን እናያለን።

💠ክፍል 1 (Part 1)

🔻Malware ማለት ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ሲሆን ዓላማው ኮምፒውተር ላይ ያሉ ፋይሎችን መስረቅ ፤ ማጥፋትጨ ፤ ማስተካከል ወይም ሲስተሞች እንዳይሰሩ ወይም የሚሰሩትን ስራዎችን ማደናቀፍ ነው። Malware ማለት ኮምፒውተሮች ወይም ሲስተሞች የቀን ተቀን ስራዎቻቸውን መስራት እንዳይችሉ የሚያደናቅፉ ጎጂ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡

🔻እንደዚህ ዓይነት ጎጂ ፕሮግራሞች እኛ በተለምዶ ቫይረስ እንላቸዋለን፡፡ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም Malware ሲባል አንድ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን እንደ ፕሮግራሞቹ ዓላማ የተለያዩ ዓይነት ፕሮግራሞችን የያዘ ነው፡፡ ቫይረስ ከፕሮግራሞቹ መካከል አንዱ ነው፡፡

🔻Malware ኪሚባሉት ፕሮግራሞች መካከል የተወሰኑትን ልጥቀስላችሁ።

➜1ኛ፦ Virus

🔻Virus ማለት የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆን እራሱን ኮምፒውተራችን ላይ ባሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ለምሳሌ ሚዚቃዎች ፤ ቪዲዮዎች ላይ በማጣበቅ ኮምፒውተራችን ላይ ይቀመጣል፡፡ እራሱን ያባዛል፡፡ ኢንተርኔት ኔትዎርክ ሲያገኝ በኔትዎርኩ አማክኝነት ከኮምፒውተር ወደ ኮሚፐውተር ይሰራጫል፡፡
ቫይረስ የተላያዩ ጉዳቶችን ያደርሳል፡፡ ለምሳሌ ፦

◈የኮምውተራችን ቡት ሴክተር ስራ ያዘባል ( Infects boot sector)

◈የኮምውተራችን ሲስተም ፕሮግራሞች ስራቸውን እንዳይሰሩ ያደናቅፋል (Infects system programs)

◈የምንጠቀማቸው የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይበክላል( Infects ordinary programs)
⚠️Join & share

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

ሁሌ chat ማረግ ሊደብሮት ይችላል ዛሬ ለናንተ ምርጥ የgame bot ይዤ መጥቻለው

🎮 TELEGRAM GAMES LIST 🎮

➊. @gamee (34 gameዎች)
➋. @gamebot (3 gameዎች)
➌. @ludeiBot (4 gameዎች)
➍. @GamesHDBot (2 gameዎች)
➎. @awesomebot (3 gameዎች)
➏. @brugamebot (6 gameዎች)
➐. @DontDieBot (1 game)
➑. @MicroGamesbot (1 game)
➒. @LazyGamesBot (1 game)
➓. @keepieuppie_bot (1 game)
11. @lonagamebot (1 game)
12. @foxgamebot (1 game)
13. @LHGamesBot (1 game)
14. @dotspuzzle_bot (1 game)
15. @Sean_Bot (1 game)
16. @GameLotus_bot (2 gameዎች)
17. @WiMi5Bot (2 gameዎች)
18. @ForaGamesBot (1 game)
19. @GameMatrisBot (3 gameዎች)

Читать полностью…

Tech Talk Ethio

✅ኦርጂናልና ፌክ ሚሞሪ እንዴት በቀላሉ መለየት ይቻላል???

1⃣. ኦርጂናል #ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት #ፎርማት ማድረግ ነው።

☑️ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል👍 ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ ያሳያቹና ይቋረጣል‼️

2⃣.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ💻 ወይም በስልኮ📲 ወደ ሚሞሪው ፋይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል።

☑️ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፋይል ወደገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት⏰ ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 ደቂቃ+ ሊወስድ ይችላል ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ😡 ነው ማለት ነው።

3⃣. የሚሞሪው ፋይል የመያዝ አቅም

☑️ለምሳሌ 8GB ሚሞሪ ቢኖርዎት #Original ከሆነ ቢያንስ 7.4GB ይሆናል። ስለዚህ 7.4GB የሚሆን ፋይል ይላኩበት በትክክል ከተቀበለ #አስተማማኝ👍 ነው።

4⃣. ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት SD insight የተባለ አፕ ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን አፑን ከታች አስቀምጥላችኋለው።

☑️ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕ ስንከፍተው #ስለ_ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል👍 ነው ማለት ነው ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም አይነት መረጃ አያሳየንም❌ ይህ ማለት ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው ስለዚህ የማይታወቅ😡 ሚሞሪ ነው ማለት ነው፡፡


# @techtalkethio comment 👉 @lijsami19

Читать полностью…
Subscribe to a channel