terakiapp | Unsorted

Telegram-канал terakiapp - ተራኪ | Teraki App

7909

https://linktr.ee/terakiapp ⬇️Google Play | ጉግል ፕሌስቶር - bit.ly/3CTALq3 ⬇️App Store | አፕ ስቶር - https://apple.co/3AVp0i3 Telegram - https://t.me/terakiapp ☎️ አብረውን መስራት ለሚፈለጉ ደራሲያን፣ ተራኪዎች እና ፖድካስተሮች በ +251904641111 | +251904649999 ይደውሉልን።

Subscribe to a channel

ተራኪ | Teraki App

🆓▶️በነፃ ያድምጡ!!

🌟በ 20 ደቂቃ ብቻ አድምጣችሁ የምትጨርሷቸው የመጽሃፍ ትረካዎችን “ቅልብጭ” በሚባለው የመጽሃፍ መደባችን ስር በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ።

ተራኪ መተግበሪያን ከአፕ ስቶር ወይም ከጉግል ፕሌይ ስቶር ያግኙ
➡️Google Play | ጉግል ፕሌስቶር - bit.ly/3CTALq3
➡️App Store | አፕ ስቶር - https://apple.co/3AVp0i3

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🛸ዳሎጵያ - ሳይንሳዊ ልብወለድ

"ይህ መፅሀፍ ሳይንስን ከመንፈሳዊነት ጋር ያጣመረ ስራ ነው… ዳኝነቱ ለአንባቢ ይሁን!... ነገር ግን አንድ ነገር ልበል… በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1990 ዓ.ም ላይ
አንድ ሰው "ወደፊት ምን መሆን ትፈልጋለህ?" የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ… እኔም "ጠፈርተኛ" ብዬ መለስኩለት… ያው ጠያቂ መልሶ "ፊዚክስና ሂሳብ ላይ እንዴት ነህ?" ሲል ጠየቀኝ… "ጎበዝ አይደለሁም" አልኩት… እንደገና "ጥሩ የሆንክበት የትምህርት አይነት ምንድነው?" አለኝ… "ባዮሎጂ" በማለት ስመልስ… "በቃ ጠፈርተኛነቱን ተወውና ሀኪም ለመሆን በርትተህ ተማር" ብሎ የግል ሀሳቡን ሰነዘረልኝ… እኔ ግን ቅር ቅር አለኝ… በህይወት ዘመኔ አራት ነገር ለመሆን ፈልጌ አንዱም አልተሳካልኝም… ቄስ
(ሰባኪ)፣ ፓይለት፣ ጠፈርተኛና አስተዳዳሪ (ባለስልጣን) የመሆን ምኞት ነበረኝ… የትኛውም ምርጫ አልሆነልኝም… ነገር ግን ከሃያ ሁለት አመት በኋላ ሳላስበው በዚህ
መፅሀፍ ውስጥ እነዚህን አራቱንም የሙያ ዘርፎች ለራሴ ተወንኩባቸው… ደራሲ መሆን ለካ እንዲህ የልብ ያደርሳል!… እንዴት እንደረካሁ!!!... ተመስገን አምላኬ!!!"

- የደራሲው መልዕክት

📝 ሲሳይ መኳንንት
🎤ተራኪ - ናኦድ ባዬ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/SZDg

#ዳሎጵያ #ልብወለድ #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🏠✝️በእኔ ቤት

ይህ ድርሰት በኢትዮጵያ አርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ዉስጥ ያለውን እምቅ የእዉቀት ሀብት ሲያሳይ እግረ መንገዱን በጥቂቶች የሚከናወኑ አስተዳደራዊ እና ስነ ምግባራዊ ብልሽቶች የፈተና ምንጭ መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳ ሥራ ነው፡፡ ትረካውን ካደመጡ በኋላ በልቦለዱ ውስጥ የታመቁት ሀሳቦች አደባባይ ወጥተው ለውይይት መነሻ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡

📝 በ በረከት ዘላለም
🎤ተራኪ - እስጢፋኖስ ግርማ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/R5dL

#በእኔቤት #ልብወለድ #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

✝️ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለደመራ በዓል እና ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! ✝️

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🌼አበባየሁሽ ለምለም! አበባየሁሽ ለምለም! 🌼

ከብረው ይቆዩ ከብረው! አዲሱን ዓመት በልጽገው፣ ወግ መዓረግ አይተዉ፣ ነገሮች ለእርሶ ተሳክተው፣ ወሰን የለሽ እድሎች ወደ ቤቶ ገብተው፣ ከብረው ይቆዩ ከብረው!🥂

2️⃣🔠1️⃣7️⃣ በፍቅር፣💖 በሳቅ እና ስፍር ቁጥር በሌላቸው የደስታ ጊዜያት የተሞላ ዓመት ይሁንልን። 🍾

መልካም አዲስ ዓመት ከተራኪ!

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

እንተዋወቅ 👋

አፍሪ ፖድካስት ተጀመረ ⭐️

አፍሪ ፖድካስት ለሰራተኞች፣ ለቀጣሪዎች እና ለስራ ፈላጊዎች ጠቃሚ መወያያ እርሶችን በማንሳት እና እንግዶች በመጋበዝ የሚያቀርባቸው ፕሮግራሞች ይኖራሉ። በየጊዜው የሚለዋወጠውን የስራ ዓለም ፣ ስለሙያ እድገት እና ስለ የግል ስብዕና እድገት እንዲሁም ስለስኬት ታሪኮች እና የባለሙያ ምክር ለማስቃኘት ተዘጋጅቷል።

🔥 ለመመልከት🔗 https://www.youtube.com/watch?v=ddXyAb5iKkU&t=210s

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

💰💼 ድለላ እኮ የተከበረ ሙያ ነው!!

ድለላ ወይም የኮሚሽን ስራ በብዙዎች ዘንድ አሉታዊ ስም ሲሰጠው ይስተዋላል። ይህ 'የድለላ ሞያ ጥበብ' የተሰኘው መጽሃፍ 'ደላላ ማለት ምን ማለት ነው?' ከሚለው ጀምሮ ፤ የድለላ አይነቶች፣ ባህሪያት እና መርሆች ፤ እስከ ስለኮሚሽን አጠያየቅ (የድካም ዋጋ አከፋፈል) ዘዴዎች ሰፋ አርጎ ያወጋናል።

ይህ መጽሐፍ "ሥራ የለም” ለሚሉ ለበርካቶች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይታመንበታል። ስለሆነም ተረካውን በማድመጥ ዘርፈ ብዙ በሆነው የድለላ ሞያ ይሳተፉ፡፡ ለህብረተሰቡም የሰመረ አገልግሎት ይስጡ፡፡ ሀገርንም ይጥቀሙ፡፡

✒️ ወንድሙ ማናዬ

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/P3zm

#የድለላ_ሞያ_ጥበብ #ቢዝነስ #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🆕🎙መልመጃ ፖድካስት
ከ ቤዛዊት እሸቱ ጋር

በጣም ብዙ ጊዜ ሰዎች ምን ይቆጫቹሀል ሲባሉ ዮኒቨርስቲ ያባከንኩት ጊዜ ፣በመማር የጨረስኩት፣ ሞያውን ሳልፈልግ መማሬ፣ትምህርቱን የተማርኩትን ያህል ስራው ላይ አልጠቀመኝም ሲሉ እሰማለሁ ። አንዳንድ ሰዎችም በተቃራኒው እንኳን ተማርኩ እዛ ያሳለፍኩት ጊዜ በምንም አይተመንም  የሚያስብሉ ትዝታዎች አሉ ይላሉ...እነዚህን ሀሳቦች ዋና ጉዳይ አድርገን ከተለያየ ሞያ ከመጡ እንግዶች ጋር ልናወራ ነው 💜

ቅዳሜ ከሰኔ 22 - ከ11 ሰአት ጀምሮ ወደ እናንተ በYOUTUBE እና ተራኪ አፕ ላይ ይደርሳል ።

Subscribe እያረጋቹ ቆዮንማ
▶️YOUTUBE: https://youtu.be/SlNTbNNHxiQ?feature=shared

#መልመጃ #Melmeja #Podcast

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

ወደ 'ራስ - አጫጭር ተረኮች 🎧

ይህ ወደ 'ራስ የተሰኘ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ መጽሐፍ በቴክኒክና ይዘት አጠቃቀሙ ለሥነ- ጽሑፋችን እንግዳ ከሚባሉት ሥራዎች የሚመደብ ነው። መጽሐፉ አጫጭር የሚባሉ ተረኮችን ቢይዝም በገጸ ባህርያቱ ተያያዥነት ወጥ ልቦለድም ነው ማለት ይቻላል።

ተረኮቹ በዋናነት ስለ ሕይወት የሚበሰለሰሉ፣ ራሳቸውን በመፈለግ የተጠመዱ፣ አብዝተው የሚጠይቁና በመፈለግ የተጠመዱ በርካታ ገጸ ባህርያትን ይዘዋል። መጽሐፉን ያነበብ ሰውም በመጨረሻ የሚደርሰው ራሱ ላይ ሲሆን ራሱን ወደ መፈተሽና ወደ መጠየቅም ይመለሳል።

✒️ በ ናትናኤል ዳኛው


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/keTh

#ወደራስ #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችን ነው።

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ Sana ፖድካስት ክፍል

ሴትና አስተርጓሚነት

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
በዚህ ክፍል የአለም ሴቶች ቀን በማስመልከት ፤ ስለ ሴት አስተርጓሚዎች እና ቻይነኝ ቋንቋ ዝምድና በጥቂቱ በማንሳት ፤ ቀጥሎም በስራ አጋጣሚ ያጋጠመኝን ገጠመኝ ፥ ጥያቄ መልክ አቅርቢያለው ፤ ተጋበዙልኝ ።
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ReformedHub #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ ነፃነት ፖድካስት ክፍል

Technology እያበሰለን? ነው እያደቀቀን?

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
In this episode of Netsanet Podcast, the hosts explore the impact of technology on personal growth. They discuss whether technology is aging Gen Z faster and its implications. The concept of the Quarter-Life Crisis is explored through personal stories, addressing challenges and growth. The phenomenon of Information Hoarding is examined, questioning the effective use of readily available knowledge. The podcast concludes by reflecting on the accelerated maturation process in today's world, influenced by societal expectations and technological advancements. Tune in for a concise yet captivating discussion on the intersection of technology and personal growth.
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ነፃነት #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧 አዲስ ፖድካስት - Sana Podcast
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
Sana podcast mainly tell stories about chinese language translators and career path experience.

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧 በ አዲሱ የ አሳብ ፖድካስት ክፍል

ራስን መጠራጠር/self doubt

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
On the 40th of our this week assab podcast we will be discussing the different aspects of self doubt how it affects our lives and how it can influence us psychologically. We will be talking about the remedies for self doubt how to over come it and so much more . Tune in to the conversation
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#አሳብ #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ ነፃነት ፖድካስት ክፍል

Saving in Ethiopia

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
እንኳን ወደ የነፃነት ፖድካስት ክፍል በሰላም መጣችሁ! በነፃነት ክፍላችን ስለ ፋይናንስ ስለ ቁጠባ፣ እና ስለ ወጪ ያለንን እውቀት ለማዳበር የሚረዱንን ወሳኝ ጥያቄዎችን በማንሳት መልስ የሚሆኑ መፍትሄዎችን ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ነፃነት #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

💌ያልተላከው ደብዳቤ
እና ሌሎች አጫጭር ልብወለዶች

ይህ ድርሰት በ2017 ዓ.ም. ተጽፎ ለአንባበያን የበቃ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ ሲሆን 'ሳይመረጥ የቀረው ለእናቶቸ የተላከው ደብዳቤ' ፣ 'የቱ ናት ኢትዮጵያ የቱን እንበላት' ፣ 'ይጣራል አድዋ' ፣ 'የጋራ ጡት አባይ' እና 'የመከነው ህልም' የተሰኙ የተለያዩ አጫጭር ልብወለዶች እና የጉዞ ማስታወሻዎችን የየዘ፣ ለማድመጥ የሚማርክ ትረካ ነው።

📝 በ ትክክል ገና

▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/T3vU

#በእኔቤት #ልብወለድ #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙ቪንቴጅ ፖድካስት - ክፍል 57

በዚህ ሳምንት የቪንቴጅ ፖድካስት 57ኛው ክፍል በማህበራዊ ሚዲያዎች የምታውቋት Sasu (@withsasu) ጋር ቆይታ አድርገዋል። ስለቲክቶክ፣ ፌሚኒዝም፣ ዴቲንግ እና ሌሎችም ነገሮች አውግተዋል። እንደምትወዱት ተስፋ እናደርጋለን።


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://youtu.be/sjzCqY1qwBw?si=yeVCXGotdKCneu9p


#ቪንቴጅ_ፖድካስት #Podcast

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

⭐️ሶባሐል ኸይር! - እስላማዊ የመጽሃፍ ትረካ 🕋

የዚህ መጽሐፍ መግቢያ እንዲህ የሚል ሊሆን ቻለ ...
“የምትናገሩትም ሆነ የምትጽፉት ነገር ታሪካችሁ ነው፤ ከዕድሜያችሁ በላይ ምድር ላይ ሊቆይ ይችላልና በጥንቃቄ ፃፉ፣ ተናገሩም፡፡'' ተብሏል፡፡
መጽሐፉ በዋናነት ሰዎች ከፈጣሪያቸው አላህ ሱ.ወ. አንፃር መልካም ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ (ተፋኡል እንዲኖራቸው)፣ በዱንያ ሕይወታቸው እንዲበረቱና ተስፋ እንዳይቆርጡ፣ ዱንያንም በብልሃትና በጥንካሬ እንዲሻገሩ ሀሳብ ይሠጣል፣ መንገድ ይጠቁማል፡፡ በየትኛዉም ከባድ የዱንያ ማዕበል ዉስጥ ብትሆኑ ፊትለፊታችሁ ብሩህ ነው አብሽሩ አትፍሩ ይላል፡፡ ወዳጆቼ ... ምክሩና ምልከታው ከናንተም በላይ ለኔ ያስፈልጋል፡፡ እኔን ፀሐፊዉን፤ እናንተን አንባቢዎችንም ተጠቃሚዎች ያድርገን፡፡

📝 በ ሙሐመድ ሰዒድ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/nseZ

#ሶባሐልኸይር #እስላማዊ #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎁በአዲስ ዓመት አዲስ ገጸ-በረከት ከተራኪ!

አሁን በተራኪ የመጽሐፍትን በስጦታ መስጠት ይችላሉ! አዲሱን የተራኪ መተግበሪያ በማደስ/በመጫን፤ የመጽሐፍት ትረካን በቀላሉ ለጓደኞችዎ እና ለቤተሰብዎ በስጦታ ማበርከት ይችላሉ። በቀላሉ ሊሰጡት ወደሚፈልጉት መጽሐፍ ገጽ በመሄድ እና 'የስጦታ ምልክቱን' ይጫኑ! 🎁

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

⭐️Freelancer ስራ ፈላጊ ነው - ከ ዮናስ ሞህ ጋር | AFRI PODCAST EPISODE 04 🎙

ዮናስ ሞህ፣ ልምድ ያለው ነፃ አውጪ፣ ዲጂታል ገበያተኛ፣ የይዘት ፈጣሪ እና የ Khlix መስራች በአፍሪ ፖድካስት ላይ።

የፍሪላንስ ንግድዎን እንዴት እንደሚጀምሩ እና እንደሚያሳድጉ፣ ደንበኞችን ማግኘት፣ ፋይናንስዎን ማስተዳደር፣ የስራ-ህይወት ሚዛን መጠበቅ እና ኤጀንሲን ስለመገንባት ተግባራዊ ምክሮችን ያግኙ። የፍሪላንስ ጀማሪም ሆንክ የስራ ለውጥ እያሰባችሁ ከሆነ ይህ ክፍል ለእርስዎ ነው!!!

🔥 ለመመልከት🔗https://www.youtube.com/watch?v=RELhnhrhlRc

#AfriPodcast

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙በመልመጃ ፖድካስት ክፍል 3 ቤዛዊት ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በህግ ምሩቅ ከሆነው ሰመረ ካሳዬ (ሰመረ ባሪያው) ጋር ቆይታን አድርገዋል።

በቆይታቸው ሰመረ በህግ ትምህርት ላይ እያለ ከገጠመው መልካም ቆይታ አንስቶ ሲወጣ ስላለው ከባድ ጉዳዮች በግልጽ አስቀምጧል ።ስራው ላይ በስፋት ያልተሰማራበትን ምክንያት ጨምሮ፣ ስለ ሶሻል ሚድያ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ማህበረሰባችን በስፋት አንስተዋል!

በYOUTUBE እና ተራኪ አፕ ላይ ያገኙታል ፤ እንዳያመልጣቹ!

▶️https://www.youtube.com/watch?v=enUymN6Ck4s&t=302s

#መልመጃ #melmeja #podcast

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🚨ሰኔ 30 ደርሷል! Promo Code 'Sene30'3️⃣0️⃣🔣🛍

እኛ ደግሞ የክረምቱ ጊዜ መቃረቡን ተከትሎ ፤ የተለያዩ ሙሉ እና አጥረው የተዘጋጁ የመጽሃፍ ትረካዎችን በ 30% ቅናሽ ፕሮሞ ኮድ 'Sene30' በመጠቀም ማድመጥ እንደሚችሉ ስናበስር በደስታ ነው!
እስከ ሰኔ 30 ብቻ! 🎁

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

📣 🎧 መቆያ
የወጎች እና አጭር ልቦለዶች ስብስብ 🎧

ከመጽሃፉ ትረካ የተወሰደ

🗣️ከዕለታት አንድ ቀን እንደማንኛውም ሰነፍ ክርስትያን ከመጽሃፍ ቅዱስ አንዲት መስመር ላነብ፣ ቅዱሱን መጽሃፍ ከመኝታ ክፍሌ መጽሃፍ
መደርደርያ ላይ አነሳሁ።

አቧራውን አራግፌ ወደ መኝታዬ ተጠጋሁ፤ የአባታችን ሆይ ፀሎቴን የማስከትልባት ጥቅስ ፍለጋ፡፡ ከመተኛቴ በፊት ጥቁር እና አዲስ የሆነችውን የፈጣሪ ድርሳን ከፈትኳት። ምን እንደመራኝ እንጃ(በመንፈስ ታግዤ ይሆን?) የወንዳወንዱ ዔሳው እና የያዕቆብ ታሪክ ላይ አረፍኩ(ኦሪት ዘፍጥረት)፡፡ ልብወለድ እንደሚያነብ ሰው በዔሳው ጉዳይ ላይ ብዙ ተጠመድኩ፤ ቁመናው ሳበኝ። አኗኗሩንወደድኩ፤ እሱ አደን ሲወጣ ቤት የምጠብቀው ሚስቱ ብሆን ስል ተመኘሁ።🗣️

✒️ እናኑ ግርማ መልካ (አርክቴክት)


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/kNkY

#መቆያ #ወጎች #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

ምንሽሮ - አጫጭር ተረኮች 🎧

ምንሽሮ ስለ ካድሬዎች ምን ትላለች? 🧐
..ከሙያ አንጻር ጎበዝ የሚባል ካድሬ አለቃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዳየሁትከሆነ ካድሬዎች በብዛት ገምጫጫ ናቸው፡፡ እንኳን ቀልድ ነገርም በቅጡ አይገባቸውም፡፡ ብዙ ጊዜ ለተመደቡበት ተቋም የሙያ መስክ ባዳ ናቸው። ስለዚህም በሥራ ዙሪያ ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ለመግባባት ይከብዳል፡፡ ሰው አያቀርቡም፤ የሚናቁ ይመስላቸዋል፡፡ ጨዋታ እና ቀልድ አይወዱም፤ ክብራቸው እና ተፈሪነታቸው የሚቀንስ ይመስላቸዋል፡፡ የሰው ችግር አይረዱም፤ የሚፈልጉት ነገር መፈጸሙ ብቻ ነው የሚያረካቸው፡፡ ሕዝብ የሚጠቀምበት ጥቂት ሥራ ሳይሆን ሹመት የሚያገኙበት የውሸት ሪፖርት ይወዳሉ፡፡ እራሳቸውን ችለው ውሳኔ አይሰጡም፤ ጉዳዩን ሁሉም ገብቶ እንዲያቦካው ይፈልጋሉ፡፡ ለሥራው ኃላፊነት አይወስዱም፤ የጭንቅ ቀን ሲመጣ ባለሙያዎቻቸውን አጋፍጠው ዞር ከማለት አይመለሱም፡፡

✒️ በ እመቤት ተሾመ ከበደ


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/6omc

#ምንሽሮ #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🌙ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ ዓልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዒድ ሙባረክ! 🤲

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ Reformed Hub ፖድካስት ክፍል

Biblical concept of Music - ሙዚቃ በመፅሐፍ ቅዱስ አውድ

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
We spoke about the general concept of music. WHO is The originator? WHO is The giver? WHO The receiver? What are the categories? And etc we answered other questions like this!
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ReformedHub #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ Halak Podcast By AASTU ECSF ክፍል

Biblical Wisdom for Everyday Life Part 1

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
በዛሬው የሃላቅ ዝግጅታችን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን አንዳንድ መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆች እና ምክሮችን ከወንድማችን ፓስተር ሰለሞን ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንደትከታተሉ እንጋብዛቿለን። ይህ ፖድካስት የተዘጋጀው በAASTU ECSF Counseling Team ነው፣ ፖድካስትዎን በሚያዳምጡባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ ፖድካስተ‍ኣችንን ማግኘት ይችላሉ።
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#Halak #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ ምስባክ ዘዘወትር ፣ ዘሰንበት ወዘበዓላት ዐበይት ፖድካስት ክፍል

ዘየካቲት ፴ ወመጋቢት ፩

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
ቅዳሜ የካቲት 30 ተረከቦተ ርእሱ ለዮሐንስ መጥምቅ
እሑድ መጋቢት 1 ዘዐቢይ ፆም ዘዘወረደ
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ምስባክ_ዘዘወትር_ዘሰንበት_ወዘበዓላት_ዐበይት #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ MERI  ፖድካስት ክፍል

ሩጫ Disciplined አድርጎኛል

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
Welcome መሪወች to Episode 1 of our podcast with ሻለቃ Haile Gebresilassie! We're thrilled to present a captivating conversation with the legendary ሻለቃ Haile Gebresilassie as he shares his stor
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#MERI #ፖድካስት

Читать полностью…

ተራኪ | Teraki App

🎙🎧በ አዲሱ የ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች በፍኖተ ሕይወት 2015 ፖድካስት ክፍል

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት) በመምህር ዮሐንስ ጌታቸው

━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
"ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል"
━━━━♬♫♪◖(●。●)◗♪♫♬━━━━
#ኦርቶዶክሳዊ_ትምህርቶች_በፍኖተ_ሕይወት #ፖድካስት

Читать полностью…
Subscribe to a channel