በደንብ ልብ እንበል……‼
ትኩረት እናድርግ………‼
_________________________________
قال ﺍﺑﻦ ﺣﺠﺮ ﺍﻟﻌﺴﻘﻼﻧﻲ رحمه الله
لا يمنعنّك سوء ظنك بنفسك، وكثرة ذنوبك أن تدعو ربك فإنه أجاب دعاء إبليس
حين قال "رب فأنظرني إلى يوم يبعثون"
"قال إنك من المنظرين"
[[Ibn Hajar Al-Asqalani]]
★]>ኢብኑ ሐጀር አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ፡–
በነፍስህ ያለው መጥፎ ግምትና የወንጀልህ ብዛት ጌታህን ከመለመን እንዳይከለክልህ}
ኢብሊንስ እንኳ በለመነው ጊዜ እሺ ብሎታል እንዲህ ሲለው
{ጌታዬ ሆይ እስከ መቀስቀሻው ቀን አቆየኝ} ሲል
{ አንተ ከዘውታሪዎች ነህ አለው}
{فتح الباري: [١٦٨/١١]}
እናስተውል……‼
ኢብሊስ =>የዘግናኝ ስራ ባለቤት አሏህን እጂግ በጣም ያመፀ ከመሆኑ ጋር እዚህ ቦታ ላይ ግን አላህ ለጥበቡ የለመነው ነገር ሰጥቶታል።
★‼……ታድያ እኛ ቀንና ማታ ለጌታችን ሱጁድ እያደረግን ሙስሊም ሆነን እንዴት ከጌታችን ተስፋ ትቆርጣለን‼??
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
#ያንች_አይደለም_
🌺
በየመንገዱ ሁሉ ስታልፊ አንችን ትክዝ፣ፍዝዝ ብሎ ያየሽ ሁሉ ያንች አይደለም ።
🌸በሚድያው ሁሉ #ሰለፊዋን ወዳጅ #የሷነኝ #ሀላሌን_ወዳጅ እያለ
የሚለልፈው ሁላቸው ያንች አይደሉም ።
🥀በተለያዩ ሚድያዎች እየገባ
#ሀይ_እንዴት_ነሽ የሚልሽ
ሁሉ ያንች አይደለም ።
🌹ኧረ እንደውም ልትርቂው ይገባል ።
በውስጥ መስመር እየገባ
#እወድሻለሁ #አፈቅርሻለሁ #እያለ የሚፅፍልሽ ሁሉ ያንች አይደለም።
💐እንደውም አንችን አላህ
ተከልከይ ባለብሽ ቦታ
ለማስወደቅ ንግግሮችን እያስጌጠልሽ ነው ።
🌺ስለዚህ አንቺ የኔ ነው
ብለሽ ያሰብሽው ሳይሆን
አላህ ያንች ነው ያለው ይሆናል
🌼#ግን_ታውቂያለሽ_ውዷ_ሰለፍይ
አንች እንትናን እወደዋለሁ ስለዚህ
የኔ ማድረግ አለብኝ ብለሽ #ብተለፊ #ብትደክሚ ያንች አታዳደርጊውም ።
አላህ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጅ ።
#ስለዚህ_ሱኒዋ
ካንች የሚጠበቀው ምርጥ የአላህ ባሪያ
እና በሰለፎች መንገድ ላይ እየተጓዝሽ እውቀትን ፈልጊ።
💐ብቻ አንች በዲንሽ ጠንክሪ በዱዓ በርች ላንች ይሆናል ያለው ለቅፅበት አይቆይም ይመጣል ።
✍ወንድምሽ አቡያሲር(ሙሀመድ_ሰኢድ)
T.me/sefinetunuh
#ፈትዋ_ቁ_0⃣6⃣4⃣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📮የኔጥያቄ ለያንዳንዳችን አድሰይጣን አብሮን አለተባለ ታዲያ አያተል ኩርሲ ብቀራም አይለየንም ማለት ነዉ
❓❓❓❓❓❓❓❓❓
📮ምግብ የጀመረ ወንድ ህፆንልጅ ሽንት ይነጅሳል ዉሀ ይረጭበታል
ወይስ ይታጠባል
🅾🅾🅾🅾🅾🅾🅾🅾🅾
📮አንድሰዉ በየቀኑ
ይሳሳታል አለምንም ምህረት
ይጠይቃል ይህሰው
እስከሚሞት በዚህ
ከቀጠለ እስከመጨረሻዉ
አየተማረ ይቀጥላል ማለትነዉ❓
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ_አል-ኬሚሲይ
🥀➖➖➖➖➖➖➖➖➖🥀
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
#ሰውን_ሳይሆን_መረጃን_ተከተል።
#መረጃ_በዞረበት_ዙር።
የሱና ሰዎች ከሌሎች ሰዎች የለያቸው በምግግራቸው ሁሉ ያከ መረጃ አያወሩም ።
ምንም እንኳ ሀገራቸው ቢለያይም ነገር ግን
ንግግራቸው ፈፅሞ አይጋጭም ።
እንደውም አንድ ሩቅ ሀገር የሆነ የሱና ኡስታዝ
የተናገናገረው እዚህ ላለው የሱና ሰው ንግግር ያጥናክራል ።
የዚህ ሁሉ ምክንያት
#ንግግራቸው_በቁርአን_እና_በሀዲስ_መረጃ_በማድረግ_የተደገፈ_ነው።
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
✍@abuyasirseid
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
T.me/sefinetunuh
T.me/sefinetunuh
ፈሱብሃን አሏህ እንዴት የፈጠረውን አዛኙን ቸሩን_ተንከባካቢውን ....አሏህን ትቶ ምንም ማይጠቅሙትን ማይጎዱትን ነገራቶች እንዴት አእምሮ ያለው ሰው ያመልካል??
قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُم مِّن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِي الظُّلُمَاتُ وَالنُّورُ ۗ أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ ۚ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
«የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «አላህ ነው» በል፡፡ «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በእነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን» በል፤ «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡✍️
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
(🌹ጀነት🌹)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🌹ጀነት የምትጠራባቸዉ በቁርአን ዉስጥ የተጠቀሱ የተለያዩ ስያሜዎች አሏት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ከነዚህም ውስጥ ፦
👇👇👇👇👇👇
1. ዳሩስ' ሰላም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
2. ዳሩል ኹልድ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
3. ዳሩል ሙቃመህ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
4. ጀነቱል መእዋ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
5. ጀነቱል አድን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
6. አልሀየዋን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
7. አልፊርደውስ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
8. ጀነቱን' ነኢም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
9. አልመቃሙል አሚን
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
〰〰〰〰〰〰〰〰
ጀነት የነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ሰዎች ሀገር ::
የነዚያ አላህን ብቻ አጥሪዎች ፍፁም ታዛዦች የሆኑ ባሮች
መስፈሪያ ናት::
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
👌 ጀነት የነዚያ ጌታቸዉን የሚጠነቀቁ ቃል ኪዳን ሲገቡ የአላህን ኪዳን የሚያሟሉ በንብረታቸውና በህይወታቸው በአላህ መንገድ የሚታገሉ ሰዎች መዘዉተሪያ አገር ነች ::
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
👌ጀነተ የነዚያ ከስህተታቸዉ ተመላሾችና፣ ቅን ታዛዦች፣ አመስጋኞች፣ ጿሚዎች ፣ ለአላህ አጎንባሾችና ሰጋጆች በበጎ ስራ አዛዦች ከክፉ ከልካዬች የሆኑ ዉድ የአላህ ባሪያዎች ዘላለማዊ የድሎት ስፍራ ነች ::
ጀነት ጀነት ጀነት ስሟ ራሱ እንዴት ይማርካል🌹🌹 ሱብሀነከ ረቢ💎
🌹አላህ ጀነትን ይወፈቀን🌹
አሏህ ጀነትን ወራሾች ያድርገን
አሏህ መልካም የሱ ታዛዥ ምርጥ ባሪያዎቹ ያድርገን ያረብብብ🌹🌹🌹
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
/channel/tewihd
ግብዣዬ ከላሙሏህ🌹💎 የልብ እርጋታ የመንፈስ ደስታ ሚሰጠው ከላሙሏህ ብቻ ነው ወሏህ 🌹🌹💎💎
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
ሕይወት ቀጥላለች _ዱንያ አሁንም አለች_እኛም ስላለን እንተነፍሳለን ።
ልክ በአሁን ሰዓት _የዱንያ ሀሳብ ሚያብሰለስለው አለ _የጌታዉን ዉዴታ በመሻት ደግሞ ጥረት ሚያደርግ አለ።
ቁጭ ብሎ ፌቡ ላይ ተጥዶ እዚህ ሰዓት የደረሰ_አለ_በዱዓ_ሥም ጫት ላይ ቁጭ ብሎ ንጋትን አሻግሮ የሚያይ አለ።
በዉድቅት ሌሊት ከሚቀሰቅስ ሀሳብ ጌታዬ ይጠብቀን_ከሚያባንን ጭንቀት አላህ ነጃ ይበለን ፡፡
በማይረባ_ነገር_ጊዜን_ከማጥፋትና ዕድሜን ከማቃጠል ይሰትረን፡፡
መሰተር_ማለት_ከወንጀል_ብቻ_አይደለም👉የሰው እጅ ከማየት ጌታዬ ይሰትረን!!
እናም እያላችኋለሁ ህይወት ሁሌም ትቀጥላለች ቴክኖሎጂ ረቀቀ ፈሳድ በዛ በወንጀል ታጠርን _አዎ ወንጀላችን በዝቷል_ ልባችን ደርቆ አኼራን ከማስተወስ ዘንግተናል ......... ስንቶቻችን ይሆን ከነገሮች ይልቅ ወንጀላችን አስፈርቶን ለወንጀላችን ምህረትን መጠየቅና እንባን ለጌታችን ምናነባው እ?
መልሱን ለእናንተ ተውኩትኝ !!
በርግጥም “አምስቱ ሶላቶች በመካከላቸው የተሠሩትን ወንጀሎች ያብሳሉ፡፡” ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡
አልሐምዱ ሊላህ!
إِنَّ السَّاعَةَ آتِيَةٌ أَكَادُ أُخْفِيهَا لِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍ بِمَا تَسْعَىٰ
«ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪናት፡፡ ልደብቃት እቃረባለሁ፡፡ ነፍስ ሁሉ በምትሠራው ነገር ትመነዳ ዘንድ (መጭ ናት)፡፡
ይገርመኛል ...
የኔ ነገር አብዝቶ ይገርመኛል …
የትም ዞሬ ዞሬ ፤ የትም ጠፍቼ ቆይቼ መጥቼ አላህ ሆይ ማረኝ ስለው አለማፈሬ ይገርመኛል።
ገረመኝ ...
የቱን ያህል ባጠፋም ከጉያህ መውጣት አለመቻሌ ለኔ ለራሴ ገረመኝ፤
አህህ
አንተ ጌታዬ እኔ ባርያህ በመሆኔ እንዴት ዕድለኛ ነኝ !!....
ያ ረብ
' ረሕማን' የሚለዉን ሥምህን አስታወስኩኝና እዝነተህ ትዝ አለኝ፤
ከሰፊው ረሕመትህ ቦታ ካጣሁማ ሞቼ ትቢያ ሆኜ መቅረትን ተመኘሁ፡፡
𝑚𝑒𝑑𝑖 🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
📩 نَصِيْحَةٌ مُوْجَزَةٌ لِمُشْرِفِيْ القَنَوَاتِ
📱አጭር ምክሮች ለቻናል ባለቤቶች
🎙 አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
/channel/abu_reyyis_arreyyis/1947
ውዷ እህቴ የምን መዘናጋት ነው ?
ተነሽ ለአኼራችን ምን ይዘናል እህቴ???
ምን ይዘን ነው ከሰይፍ የሳለውን የሲራጥን ድልድይ የምናልፈው???
ምን ይዘን ነው ከበታቹ ጀሀነም ከላይ የሲራጥ ድልደይን የምናልፈው?? በየት ነው ጀነት መግቢያችን ያ አላህ ተነሽ እህቴ ተማሪ ዲንሽን !!!!!
°ጥፍጥናን ቁራጩ ሞት የማይቀር ነው!!
ታዳ ምን ይዘን ነው የምንሄደው??
ነቃ በይ ውዷ እህቴ ሰአት አለሽ ተማሪ!!
ጅህልና ጨለማ ነው !!
ጅህልና ያሳፍራል!!
ጅህልና ያስንቃል !!
ጅህልና የበታች ያደርጋል !!
ጅህልና ሞትን እዳታስታውሽ ያደርግሻል!!
ጅህልና የአዛኙ ጌታሽን ትዕዛዝ እንዳትጠብቂ ያደርግሻል !!
ብዙዙዙዙዙ.......
እናም💎🌹
ጀግናዬ ንቂ ተማሪ ተማሪ ጋሊቲ💎!!
ተምሳሌቶችሽን እወቂ
አትፍሪ ( ا ) ብለሽ ጀምሪ!!
አሊፍ ብለሽ መጀመርሽ የበላይነትሽን እንጂ የበታችነትሽን አይገልፀውም ማንም ከእናቱ ሆድ ውስጥ ተምሮ የወጣ የለም ።።
ከማንም አታንሽም ተማሪ ታታሪ ጀግና ሁኚ 🌹🌹🌹🌹
አሏህ ጠቃሚ እውቀትን ይስጠን ያረብ🌹
በኢኽላስም ያስውበን!!
በሰለፎቻችን መንሃጅ ያኑረን መጨረሻችንንም ያሳምርልን💎🌹
𝓶𝓮𝓭𝓲🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
አኽዋቲ _ወ _አኽዋኒ👇
👉 አደራችሁን መጥፎ ሐሳብ መርዝ ነው። ደካማ መሆን ሞት ነው። ስንፍና ውርደት ነው። የሐሳብ ራእይ መለዋወጥ ወይንም በአንድ አቋም ላይ አለመፅናት መጥፎ ነገር ያስገባል።
ከእንደዚህ ከመሆን እንጠንቀቅ ፏ ያች ቀን ትሁንላቹህ🌹🌹🌹
𝑚𝑒𝑑𝑖🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
ወንድሜ ሆይ በጧቱ ያነቃህ ዘንድ እቺን ምርጥ ምግብ ጋበዝኩህ አሉ !!
ኦው ማራኪ ጣዕም እኮ ነው ያላት ሳህ ??
ቀጣይ ደግሞ ከዚህች የተሻለ ትጋበዛለክ ለዛሬ እሄ ብቻ ይበቃል!!
ደግሞ አትቆጣ ሁሌ ጣፋጭና አልጫ ነገር ይሰለቻል ብዬ በማሰብ እኮ ነው !!!
ወደ ቁም ነገሩ እንግባማ ¡¡
/////////// ወንድሜ |||
፣⤵️ #ቲኒሽ_ልበልህማ_ወንድምዬ:—⤵️
ከአምሳያዬ (ከሴት ልጅ) ለእህቴ ባልተናነሰ ያንተም የወንድሜ ነገር ያ ሳስበኛል።
እናማ አንተ በተፈጥሮህ (ብዙ ጊዜ) እርጋታ ይታይብሃል፣
እዚሁ ሚድያ ላይ መታዘብ ይቻላል፣ ወንድሞች ቁጥቦች ናችሁ።
በተለይ ትንሽ ወደ ሸሪዓው እውነተኛን መጠጋት ጠጋ ያላችሁትን ማለት ነው።
ለዚህ፦⤵️
☞ቶሎ አትወድቅም፣ ከወደቅክም ቶሎ አትነሳም ❗️
☞ፈጥነክ ልብህን አትከፍትም፣ ከከፈትክ ደግሞ ከነመስኮቱ ነው የምትከፍተው❗️
☞ቶሎ አታነባም፣ ካነባህ ግን
ከደም ያልተናነሰ አሳማሚ እንባ ነው የሚወጣህ❗️
☞ፈጥነህ አታምንም፣ ካመንክ ታዲያ እላፊ ታምናለህ❗️
ይህ ብዙ ግዜ በወንድ ልጅ ላይ የሚስተዋል ባህሪ ነው።
በቃ #ወንድ_ልጅ ረጋ ያለ ነገር ነው;
ሲፅፍ፣ ሲናገር፣ ሲስቅ፣ ሲተዋወቅ፣,,,,,,, ብቻ በአብዛኛው ሁኔታ!!
ወንድ ከሴት የበለጠ ቀዝቃዛ መሰለኝ… አይደል ወንድሞቼ?
ይህን ስላችሁ
(ቅልብልብ ወንድ ቸኳላ ኢማነቢስ በአልባሌ አሞራ ጮሌዎች በሰው ሂወት መጫወት ሱስ የሆነባቸው የሉም ማለት አይደለም አሉ አላፎች )።
እናማ አኺ:—
ያቺ ላንተ ያላት ወሏህ ያንተው ነች‼️
አሏህ በህይወትህ ውስጥ "ትዳርን ወስኖልህ ከሆነ" በቃ ልጅቱ(ሚስትህ) ላንተ ተፅፋልህሃለች። ‘
#ቀለሙም_ደርቋል !!!‘
➣ካንተ ሚጠበቀው "ዱዓዕ" እና "ሰብር“ ብቻ ነው‼️
ታግሰህ ጠብቃት!!!
➣ለምን ይቺም ያቺም ታምርሃለች❓❓
ለምን ከፋኢዛም ከፌሩዛም ትነካካለህ❓❓
ለምንድነው ከአሚራም ከሰሚራም ጋር ይምትጀናጀነው❓❓
"ሰበብ ላደርስ ብዬ ነ………ው" ብለህ ብቻ እንዳታስቀኝ‼️
#ወንድሜ! እስኪ ተመከር❗️
ይቺን ልጅ ልብህ ለጋብቻ ካልፈቀዳት ተዋት‼️
አዎ ተ„„„„„ዋ„„„„„ት!!!
ላንተ ባትሆን ለሌላው ወንድምህ ትሆናለችና ልቧን አትስለባት በአሏህ‼️
በቃ ተዋት ያንተ ልታደርጋት ካልፈለግክ‼️
ውድ ወንድሜ!
ወንድ ልጅ #አይኑን ሲያምን ሴት ግን #ጆሮዋን ታምናለች ይባላል።
ሴት በወሬ (በዝና) ብቻ ትወዳለች ነው አሰንግዲህ።
ወንድ ደግሞ እስኪያይ ይጠብቃል…
ያ ማለት ግን ያየሃት ሁላ ያንተ ነች ማለት አይደለም።
ብዙ ሴቶችን በቀረብክና ባወራህ ቁጥር ወሏሂ ላንተ ለራስህ
ጥሩ አይሆንም ወላዋይ ትሆናለክ በወላዋይነትህም ትግዳለህ።
➣በስነልቦናህ ላይ አሉታዊ ተፅኖ
ያሳድራልና ተጠንቀቅ።
ብዙ ብዙ ነገር‼️
ለሴት ልጅ ያለህ አመለካከት ይበላሻል፣ ሴትን መናቅ ይመጣል፣
ሴቱን በሙሉ ባንድ አይን ማየት ትጀምራለህ!!
ብዙ ሴቶች "ውይይይይ ወንዶ………ች!!! እነሱን
ሰብስቦ ነበር። እርርርርሪ""""ኡኡኡኡ" ምናምን እያሉ የሚያማርሩት
ለምን ይመስልካል⁉️
➣የሆነ በቃ በወንድ ልጅ ላይ ጥናታዊ
ፅሁፍ የሚያዘጋጁ ይመስል ከሀሰንም ከሁሴንም ከጀሚልም ከጀማልም ሲያወሩ ይከርሙና
መጨረሻ ላይ " #ዉይ_ወንድ ! " ለማለት ይበቃሉ።
አደጋ አለው‼️
ዉሎ ሲያድር ባንተነትህ ላይ ቀላል የማይባል ችግር ይፈጥራል ሴቶችን አብዝተህ ባወራህ ልክ!!
#የሷ ችግር የለውም ትንሽ አለቃቅሳ ወይም ሞልጫህ ይወጣላታል።
ዛሬ ሺ ግዜ ብትወድህ ነገ "ለማቀፍ በቂ
ጥንካሬ ያለው ክንድ" ካጋጠማት አይደለም አንተን እራሷን ትረሳለች‼️‼️
➣ነገ ባንድ ጣሪያ ስር ከሱ ጋር ስትሆን ያ ሁ………ሉ የእንባ እና የቃላት ፏፏቴ ደርቆ ጉዳዩዋ ሁሉ ይሄኛው ሰው ይሆናልና የሷ
ብዙም አይቸግርም!!!
ይልቅ አንተ ለራስህ አስብ።❗️
ማር አንደበት ያላት ሴት ብታጋጥምህ ማሯን እያልክ ከመርዟ ጋር አትተሻሽ‼️
ሰምተሃል¡🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah✍️
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ مَنْ أَحْسَنَ عَمَلًا
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እኛ ሥራን ያሳመረን ሰው ምንዳ አናጠፋም፡፡
🍁ሱረቱል ካህፍ🍁
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
/channel/tewihd
✋ የነፍሱ ጉዳይ ለሚያስጨንቀውና ነፍሱ ለጥፋት እንዳትዳረግ ለሚሰጋ ብቻ!
❍ ታላቁ የዘመናችን ዓሊም ኢማም ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
《 የነፍሱ ጉዳይ የሚያስጨንቀውና ነፍሱ ለጥፋት ትዳረጋለች ብሎ የሰጋ ሰው ፝እራሱንና ሌሎችን ይጠቅም ዘንድ ሸሪዓዊ ዕውቀቶች እና የዕውቀት ማዕዶች ላይ ትጉህ መሆን አለበት።》
መጅሙዐል ፈታዋ(8/77)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
ሂስድ ( ቅናት ) (ምቀኝነት)
ሂስድ ➬ በሰው ልጅና በጂኒዎች ላይ ብቻ የሚገኝ በሽታ ነው ።
===
ሂስድ ➬ የአላህን ወሳኔ በመቃወም የሌሎችን እድገትና ስኬት ማየት ካለመፈለግ ከልብ ውስጥ የሚመነጭ ጥላቻ ወለድ በሽታ ነው ።
===
ሂሰድ ➬ በባህሪው በፍጥነት እየተሰፋፋ የሚሄድ አደገኛና አቃጣይ በሽታ ነው ።
===
ሂስድ ➬ ያለበት ሰው የሚፈለገውን ነገር ሁሉ አላህ ቢሰጠውም አይደሰትም ። የእሱ ደስታው የሌሎችን ማጣትና ውድቀት ሲመለከት ብቻ ነው።
===
ሂስድ ➬ ውጤቱ የበሽተኛውን መልካም ስራዎችን ማቃጠል ( ማበላሸት ) ነው ።
#መፍትሄው ሁሌም በኑሮ ፣ በጤና ....ከእኛ በታች ያሉትን በማየትና አላህ በሰጠን በመደሰት ብሎም አላህን በማመስገን ብቻ ነው!!
➹ ቅን እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና➹
አሏህ ውስጣችንን ((ከሂስድና ከንፍቅና)) ያፅዳልን!!
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
አደምን አለይሂ ሰላም
#አላህ ምን አለው
#ሰይጣንስ ምን አለው
#እኛንስ ወዴት ነው ሚጠራን #ክፍል 4
ብናዳምጠው ተጠቃሚ
እንሆናለን ቆየት ካሉ ሙሀደራዎች
ይ
ቀ
ጥ
ላ
ል
Share Share ➘➘➘
/channel/AbuFewzanAselefy/934
ክፍል አንድን ለማግኘት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
/channel/AbuFewzanAselefy/913
ክፍል ሁለትን ለማግኘት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
/channel/AbuFewzanAselefy/918
ክፍል ሶስትን ለማግኘት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷
/channel/AbuFewzanAselefy/921
ለጎረቤትህ መልካም ሰው ሁን አኺ,,,,,,,,,!!!!
እንዴት?? በምን አይነት መልካም ልሁን እያልከኝ ነው ወይ??
ከሆነም ና ቲንሽ ላካፍልህ 👇
👉የጎረቤትህን ሐቅ ጠብቅ...
የሚያስከፋውን ንግግርም ሆነ ስራ ራቅ...
👉ስለማይመለከትህ ነገር አትጠይቀው...
👉ነውሮቹን አትከታተል አትሰልል...ካንተ የደበቀውን ነገር አትይበት...!!
👉እንዳትሰማው የሚፈልገውን ነገር አትስማበት...ከሚስቱና ከሴት ልጆቹ አይንህን ሰበር አድርግ...!!
👉ከምትበላውና ከምትጠጣው አጋራው...ሲያስከፋህ ቻለው ታገሰው...!!
👉መከራ ሲደርስበት አጽናናው...
ሲታመም ጠይቀው...ሲሞት ቅበረው...
👉በአጠቃላይ ለራስህ የምትወደውን አይነት ስብእና አሳየው።
👉ይህንን ካደረግክ ጥሩ ጎረቤት ትሆናለህ የጎሮበትንም ሀቅ ተወጣህ ማለት ነው ።(طيب )✍️
medi🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
ውዷ እህቴ ሀገር ካለው ባልሽጋር እንደት ነሽ ?
ውዴ እዛ ያለውን ባልሽን የምትጠይው የምትንቂው ከሆነ
♻️በተለይ እዚህ አገር መተሽ ተቀይረሽ በድንሽም ሆነ ባስተሳሰብሽም በከለርሽም ተቀይረሽ ይሆናል ነገር ግን አንቺ ተቀይረሽ እዛ ያለውን ባልሽን የምትንቂ ያለምንም ነገር የድን እውቀት ስለሌለው ውበቱ ጥቁርቁር ስላለ አስተሳሰቡ ያው የዱሮው ስለሆነ የምትጠይው ከሆነ ተሳስተሻልና ዙረሽ ራስሽን ፈትሺ
↪️ ዙረሽ ድሮ የነበራችሁን ፍቅር በመካከላችሁ የነበረውን መተዛዘን ዞርር ብለሽ አስታውሺ
↪️የድን እውቀት ከሌለው እንድማር ገፋፊው ምከሪው ፊትሽን ኮሶ አስመስለሽ ከምትሸሽው ባወቅሽው እውቀት ጥሪው
ለከለሩ መቀየር ከሆነ የምትንቂው የምትጠይው ያለበትን ቦታውን ልፋቱን አስታውሺ
↪️ መክረሽው አስመክረሽው ድርቅ እንኳን ካለ የመለየት ጉዳይ እንኳን ቢፈጠር በክብሩላይ ሳትጨፍሪ ልቡን ሳትሰብሪ ቀስ ብለሽ ውልቅ በይ።
↪️ሀቢበቲ የሰው ቀልብ መስበር የሰው ሞራል መንካትን የምያክል በደል የለም በደል እንደግርሳት ያቃጥላል መቼም ከሆድ አይጠፋም በተለይ በሚወድሽ ሰው ላይ ከሆነ ከባድ ነው !!
↪️አሁን ላይ ጠልተሽው አመናጭቀሽው እየወደደሽ ገፍተሽው ቢለቅሽና የምትመኝውን አይነት ባል ብታገቢ እመኝኝ በሰፈርሽው ቁና መሰፈርሽ አይቀርም !!!!
↪️አሏሁ አዘው ጀል በተከበረው ቃሉ እንድህ ይላል <. ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسِ
.ይኽችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን
copy ነች
ውድ እህቶቼዋ አደራችሁን በትዳራችሁ ጉዳይ ጥንቃቄ አድርጉ !!
ለሁሉም ነገር አስተዋይና ብስል ሁኑ በላይ ባሉት ምክሮች ተግብሩ ዘላችሁ ፍታኝ እንዳትሉ ኢንተቢሁ 🌹🌹🌹💎💎💎
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
ፈገግ በሉ ወዳጆቼ !!!
➪➪➪➪➪➪➪➪
ስለ አህባሽ አስቂኝ ፍልስፍና አብዱላህ አልሀረሪ ጨረቃ ላይ ታይተዋል ስለሚለው ቅጥፈታቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች
በነገራችን ላይ አዚህ እኛው ሀገር ሸዋሮቢት መጥተው እንዲህ ብለው ቀጥፈዋል። "እኛ በሸዋሮቢት መውሊድ ስናከብር አላህ የሚለው ቃል በሰማይ ተፃፈ" ብለው እርፍ አሉት
ስለ ሌሎችም ቅጥፈታቸው ስሙና
ተገረሙ በዛውም ፈገግ በሉ
🎙 በኡስታዝ ሳዳት ከማል አቡ መርየም
/channel/AbuImranAselefy/2283
/channel/AbuImranAselefy/2283
/channel/AbuImranAselefy/2283
💎🌹ጀግናዬ💎🌹
ጣፋጭ ነገሮችን ሁሉ ቀምሰሽ ይሆናል !
.......እንደ ጤንነት በጣም ጣፋጭ ግን የለም!!
መራራንም ሁሉ ቀምሰሽ ይሆናል !!
.......ሰው እንደ መለመን,, በጣም የሚመር ነገር ግን የለም!!
ድንጋይና ብረትንም ተሸክመሽ ሞክረሽው ይሆናል!!
.....እንደ እዳ, በጣም የሚከብድ ነገር ግን የለም!!
ስለሌለሽ~ አልሞትሽም
ስላለሽም ~ለዘላለም አትኖሪም!!
የሚያኖርሽ /የሚያኖረን አንድ አሏህ ይመስገን!!
ቀን ያስጎነብሳል አሏህ ግን ያነሳል!!
ቀንሽን 'ና ሌሊትሽን ፈጣሪን በማመስገን ጀምሪ ስለተደረገልሽ
ብቻ አይደለም ስላጣሽውም ነገር ጭምር እንጂ የምታመሰግኚው ምክኒያቱም ጌታችን አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ላንቺ የሚጠቅመውን ያውቃልና ።
ስለ ድህነትሽ አመስግኚ💎
ስለ መራብሽና ስለ መናቅሽም አመስግኚ💎
ስለ መታረዝሽና ስለ መገፋትሽም አመስግኚ 💎
አዎ ምን አልባትም ባልጠበቅሽው ሰው ልብሽ ተሰብሮ ይሆናል አመስግኚ። ለምን መሰለሽ አሏህ ላንቺ ስላላለው እና ላንቺ ኸይር ስላልሆነ አሏህ የተሻለውን ሊሰጥሽ አራቀልሽ ታዲያ አልሃምዱሊላህ አትይምን እህቴ!!
ባጠቃላይ ውዴ፦ አመስጋኝና ተብቃቂ እንስት ሁኚ 💎💎
#ልክ ነሽ እህቴ #ምስጋና__ታሪክን__ይቀይራልና
እሄው እኔም እላለሁ አልሀምዱሊላሂ ረቢል አለሚን🌹🌹✍️
𝑚𝑒𝑑𝑖🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
💢አለባበስህ ሱናውን የጠበቀ ይሁን❕
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔺ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚት በታች ሚያስረዝሙ ወንዶች ቅጣት
🔺ልብሳቸው የሚያስረዝሙ ሰዎች የሚያመጧቸው ማምታቻዎች
🔺አቡ በክር ሲዲቅ ልብሱ ያስረዝም ነበር ለሚሉ ሰዎች የተሰጠ መልስ
🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
#ፎቶ__ፎቶ ነው!
የነጭ ሆነ የአረብ ሆነ የሀበሻ ሆነ!
በሂጃብ በኒቃብ ተሸፈነ + የተገላለጠ ሆነ + በጥምጣም ሆነ በቶብ ፎቶ ፎቶ ነው!
☞ ተዘቀዘቀም + ቀለም ተሰመረበትም ፎቶ ፎቶ ነው!
ልዩነቱ መሸፈኑና መገለጡ + መዘቅዘቁና ቀለም መቀባቱ ነው!
አዘለም አቀፈም ያው ተሸከመ ነው!
ከፎቶ ነቱ አይቀየርም!
አወ
👉አንዳንድ እህትና ወንድሞች የፎቶን ክልከላ!
ለተገለጡት ብቻ እንደሆነ አስመስለውታል!
👉 ሂጃብ + ኒቃብ ለብሶ ፎቶ
ቶብ/ ጀለብያ + ጥምጣም ……………… ለብሶ ፎቶ ነው!
👉 ቆይ ለእነርሱ ለብቻው የተወረደ ፎቶ ሀላል ነው ያለ ሀድስ አለ እንዴ??
ካለ መረጃውን አንጡ!
👉 የሚታወቀው ፎቶ ክልክል እንደሆነ ነው!
ለዚህም
👉 ስለ ፎቶ ክልክልነት ብዙ ተብለናል!
ከተባልነውም መካከል ጥቂቶቹ እነዚህን ይመስላሉ!
١ 👈 #عن ابن عباس رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم :- قال
كل مصور في النار يجعل له
بكل صورة صورها نفساً فتعذبه في جهنم،
👉 ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል:-
ሁሉም ፎቶ አንሽ የእሳት ነው!
ሲቀርፀው በነበረበት ፎቶ ሁሉ ነፍስ ተደርጎበት በዚያ እሳት ውስጥ ይቀጣል!
(رواه مسلم)
٢ 👈 #عن عبدالله بن مسعود رضي الله عنه قال:-
سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم :-
يقول إن أشدّ الناس عذاباً عند الله يوم القيامة المصورون،
👉 አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየአሏሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ!
የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ!
👉 ከሰዎች መካከል ቅጣት የሚበዛባቸው ፎቶ አንሽዎች ናቸው!
[رواه البخاري (٥٩٥٠) ومسلم (٢١٠٩)]
٣ 👈 #نهى صلى الله عليه وسلم:-
عن الصور في البيت، ونهى الرجل أن يصنع ذلك،
👉 ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ፎቶ ቤት ውስጥ እንዳይገባ ብለው ከልክለዋል!
👉 ሰዎቹንም ፎቶ እንዳይሰሩ ከልክለዋል!!
[ السلسلة الصحيحة (٨٠٩/١)]
👉 አያችሁ አይደል?
እሄ በትንሹ ነው ከዚህ በላይ መጨመር ይቻል ነበር ፅሁፉ እንዳይረዝም ስለተፈለገ ነው!
👉 እህቴ ሆይ!
አንች ተሸፍነሽ በየ ሚድያው ፎቶሽን እያንከራተትሽ!
የተገለጠችዋን ፎቶ ስታይ ለማውገዝ ከመቸኮልሽ በፊት!
አንች ከምትነሽው ፎቶ ተቆጠቢ!
👉 ስለተሸፈንሽ ሀላል አይምሰለሽ!
የተከለከለ እየተዳፈርሽ ነው!
የሱና ወንድሞችሽንም እየፈተንሽ ነው!
አወ 👉 ከተገለጠችው በላይ በተሸፈነችው እንስት ይፈተናሉ!
የተፈተኑም አሉ!
እናም እህቴ አላህን ፍሪ!
ክልክልን አትዳፈሪ!
ወንዶችንም አትፈትኒ!
👉 የምታስተላልፊው መልዕክት ካለ ከፎቶ ውጭ ባለ ነገር ማስተላለፍ ይቻላል!
የግድ ፎቶ ካልሆ ያለ የለም!
👉 ሌላኛዋ ደግሞ!
አንችም አላህን ፍሪ!
የሰዎች ፎቶ ስለሆነ ሀላል አይምሰልሽ!
👉 በመዘቅዘቅና በቀለም መቀባት ከሚዲያ ሚድያ የምታሯሩጭው ክልክል የሆነ ፎቶ ነው አላህን ፈርተሽ ተቆጠቢ!
ካለ ፎቶ መልዕክቱን ብቻ አስተላልፊ!!
ወንድም!
👉 አንተም አላህን ፍራ!
በጥምጣም + በቶብ/በጀለብያ ስለሆነ የተነሳኸው ሀላል አይምሰልህ! ክልክል ነው!
👉 #አንተኛው ወንድም ደግሞ!
እባክህን ደዩስ አትሁን የራስህ አልበቃህ ብሎ የልጂና የሚስትህን በየሚድያው አትለጥፍ!
እንዲሁም ☞ ሰለጠን እንዳሉት ኩፋሮች/ኢስላምን የማያውቁ ሴቶች በየ ሚድያው + በየ ቲቪው ለምናምን ማስታወቂያነት እንደሚጠቀሙባቸው!
👉አንተም ሚስትህን የምናምን ማስታወቂ አታድርጋት!
ደዩስ አትሁን!
የግድ በእርሷ ካልተዋወቀ አይሸጥም አትበል!
ገባየ ርዚቅ ነው! የርዚቅህን ታገኛለህ!
👉 በሚስትህ አስማምተህ ከምታገኘው በላይ!
እናም አላህን ፍራ!
በሚስትህም + በልጂህም አላህ እንዳይጠይቅህ ተጠንቀቅ!
So… …………… አላህን ፍሩ + እንፍራ!
ክልክልን የሆነን አንዳፈር!!
እላለሁ!
ወላሁ ተዓላ አዕለም!!
/channel/sadatkemalman
✨✨✨የፈጅር ሶላት ትሩፋቶች✨✨✨
🔻 ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው”
ብለዋል፡፡ [ሙስሊም]
🔻ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ
ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን
በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡
ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ
እንደቆመ ነው” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
🔻ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ
እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡
[ቡኻሪና ሙስሊም]
🔻 ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች
የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን
አብስራቸው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570]
🔻 ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ
ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡
በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም
እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡
ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን
በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
“እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው
የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
🔻ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ
የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ
የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ
እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!”
ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403]
🔻ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ
የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት
የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ
ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
🔻ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ
ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
“ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም
ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች
ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ
ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና
ሙስሊም]
🔻ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን
የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት
ጌታችሁን ታያላችሁ፡፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡
ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት
ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
🔻ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ
ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
⁉️ተጠንቀቅ⁉️
⁉️ የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት
መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!!
[ቡኻሪና ሙስሊም]
⁉️የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን
መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው
ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ
ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ
ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]
⁉️የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ
የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ
ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ
ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ
እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡
[ቡኻሪና ሙስሊም]
⁉️ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ
ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው
ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን
ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ
እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም
እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም
ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ
የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው
ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡
🔔ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህእንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡
💫በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ
ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
💫 ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር
ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ
የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ
ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
💫ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ
ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ
ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም
እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ
የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
💫ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት
ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ
ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
💫 በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ
ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡
መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ
አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት
ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ
የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ
እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡
💫በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡
የተወሰደ
/channel/ibnukedir
"ዱዓእ" ማለት፡- የምትፈልገውን ነገር ሊሰጥህ፣ የምትመኘውን ነገር ሊያሳካልህ፣ ከምትጠላውና ከምትፈራው ነገር ሊጠብቅህ እንደሚችል አምነህ ለዚህ አካል የምታቀርበው ተማጽኖና ልመና ማለት ነው፡፡
አንድ ሙስሊም ዱዓእ አደረገ ማለት፡- የሚፈልገውን ነገር ከአላህ ለማግኘት፣ ከሚፈራው ነገር በአላህ ለመጥጠበቅ ጌታውን አላህን አጥብቆ ለመነ፣ ተማጸነ ማለት ነው፡፡ "ዱዓእ" ልብ ከምላስ ጋር በመጣመር ከሚፈጸሙ የዒባዳ ዘርፎች ውስጥ የሚመደብና ተቀዳሚ ተግባርም ነው፡፡
ዱዓእ በዱዓነቱ ብቻ ለባለቤቱ አጅር ያስገኛል፡፡ ሶላት የሰገደ በሶላቱ፣ ዘካት ያወጣ በዘካው፣ ሶደቃህ ያወጣ በሶደቃው አጅር እንደሚያገኘው፤ እጁን ወደ ላይ አንስቶ ያ አላህ! ያ ረቢ! የሚል ጌታውን የሚማጸን ባርያም የዱዓውን ምላሽ ወዲያው ቢያገኝ፤ ወይም ምላሹ ቢዘገይም በዱዓው ብቻ አጅርን ያገኛል፡፡ ምክንያቱም ዱዓእ ዒባዳህ (አምልኮ) ነውና!፡፡
🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
🌹ኦኽቲ_ከገባሽ_ስሚኝ_ልንገርሽ💎
ከቤት ውጭ የዱቄት መኣት ተለቅልቀሽ ምትወጪውና በየሚዲያው ላይ ፎቶ እየተነሳሽ ምትፖስችዋ ራስሽን ምታረክሽዋ ልታይ ልታይ ባይዋ እህቴ በጣም ስለምታሳዝኒኝ እስኪ በአቅሜ የሆነች ነገርን ላስታውስሽ ፈለኩ ዛሬ !!! ከኔ ጋ ነሽ ኣ ? አዎና መሆንም አለበት 🌹
👉 እናም ምን መሰለሽ ኦኽቲ ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ውስጥሽን(ስብእናሽን)
አይቶ ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው።
#ለምን ነገርሽኝ እንዳትይኝ??? ምክንያቱም ያው እንዳልኩሽ ከላይ ስለምታሳዝኒኝ አስብልሻለዋ!!!
👉 ወንዶች ሲባሉ ኢላ ማረሒመ ረቢ የፈለጉትን ነገር እስኪያገኙ ድረስ ሴትን ልጅ ንግስት ማድረግ ይችሉበታል ።
👉 ከልቡ ያፈቀረ ሰው ግን ተብታባ ነው። ውሸትን ለመግለፅ እንኳን አንደበት የለውም።
👉ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ ተማርኮና እጅ ሰጥቶ የቀድሞ ማንነቱን ወዲያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ሌት ተቀን አንችን በምናቡ ሲያወጣ እና ሲያወርድ ፣ ☞ያንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ ፣ ሀላል ሚስቱ ሆነሽ ከሱ ብዙ ልጆችን ወልዳቹ ከዚያም አልፎ ጀነትም ላይ የሱ ሚስት እንድትሆኚለት ሚመኘው ሚስኪኑ የአሏህ ባሪያ ☞ከሰው በላይ የነበረው ላንቺ ፍቅር ሲል መቀመቅ ሲወርድ ፡ ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። ያኔ ላንቺ ተራ ሰው ይመስልሻል።
👉እናም ፍቅርሽን ሳይሆን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና በዝሙት ዳግም ብትፈጠሪ እንኳን ዳግመኛ የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ እንዳይሽር እንዳይድን አርገሽ ትሰብሪዋለሽ።
👉እሱም ለዘላለም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ ቁርጡን አውቆ ይቀመጣል።
👉አንቺ ግን ሳታውቂው ከፍቅር ፊልሞች ላይ ባየው አማላይ ቃላቶች ወይም ከፊክሽን መፅሀፎች ላይ በሸመደደው የሽንገላ ቃላቶች ያታለለሽ ሰው ግን ከአንድ ለሊት መኝታ በኋላ ለአይኑ እንኳን ይጠየፍሻል።
አየሽ ኣ ውርደት??
👉 አስበሽዋል አንደኛ የፈጠረሽን አዛኙን አሏህን አመፅሽው _ክብረ ንፅህናሽን አጣሽ_ ውብ የሆንሽዋ ፅጌሬዳ አበባ በዚህ አታላይ ሰው እንደቀላል ነገር ረገፍሽ/ ተቀጠፍሽ!!!
እኔምልሽ ግን እህቴ ውብ የሆነች አበባን ቆርጠሽ ብትጠያት ዳግም ታብባለች ወይ ??እ ትደርቃለች እንጂ!!!
አንቺኮ ከውቧ አበባ በላይ ነሽ _ድንቅ ፉጥር እኮ ነሽ ውዴ እንዴት በቀላሉ ዱርዬ በቃላት ጋጋታው ሊቀጥፍሽ ይችላል ???
እኔምልሽ ኦኽቲ 👉 አሁንም (boyfriend) ከሚባል አፀያፊ 'ና ቆሻሻ ነገር አለሽበት እንዴ እ?? ግን እንዴት ? አይ መሆንማ የለበትም !!!
እርግጠኛ ነኝ ከእንዲህ አይነቱ እርኩስ ቆሻሻ ነገርማ ወደ ጌታሽ ተመልሰሽ ትክክለኛ ተውበት አድርገሽ ከጌታሽ ያለሽን ግንኙነት እያስዋብሽ እንደሁ ተስፋ አለኝ🌹
እናም ጀግናዬ 👉በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ ሰው ያሻውን ፈፅሞ ሲያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እንኳን ዋጋ አይሰጥሽም ፡ ከጥፍሩ ቆሻሻ እኩል እንኳን አይቆጥርሽም !!
👉እናም እህቴ ለዚህ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ።99 ነጥብ።
እባክሽን ፎቶ እየተነሳሽ በሚዲያው ሁሉ ራስሽን አታርክሽ ከቤት ስትወጪም አትዝረክረኪ በሂጃብሽ ተውበሽ ውጪ !!
እህቴ ከጌታሽ ዘንድ ምርጥ የአሏህ ባሪያ መሆን ከፈለግሽ ከዝሙት'ና ከተለያዩ ማዕሲያዎች ራቂ !!!
በቃ የእስካሁኑ ሁሉ አለፈ አይደል አልሞትሽም ጊዜም አለሽ ኢርጂዒ ኢለሏህ💎
ውዷዬ ሁሌም ሚያከብርሽን እና ሁሌም ንግስ አድርጎ ሚያኖርሽን የህይወት አጋርሽን ከመመኘትሽ በፊት አንቺ ቁጥብ ሆኚ (ክብረ _ ንፅህናሽን ጠብቂ)!!
(ቁጥብነትሽ)_ (ክብረ_ ንፅህናሽ) ደግሞ ሁሌም የተረጋጋሽ _ሁሌም አስተዋይ_ የመልካም ስነምግባርሽን _የአይን_አፋርነትሽን ወ.ዘ.ተ.... ሚገልፅልሽ ነውና ክብርሽን ጠብቂ !!!
ጓደኛ ምረጪ ወደ ጌታሽ ሚያቃርቡሽን_ ዲንሽን ትማሪ ዘንድ ሚገፋፉሽን_ በሂጃብሽ ትዋቢ ዘንድ ሚያግዙሽን _ከሙንከራት ነገራቶች በሙሉ እንድትርቂ ሚያግዙሽን 💎
አዎ ኦኽቲ ያለፈው አልፏል አሁን ንቂ ዲንሽን ተማሪ ለሌሎች እህቶችሽ ገና አርአያ መሆን ምትችይ ውብ ድንቅዬ እንስት ነሽ 🌹 ነቃ በይ ጊዜው አረፈደም 💎 እንማር ያወቅነውን አንኩራራበት ለሌሎች እናካፍል طيب 🌹
መካሪም አይደለሁም _አዋቂም አይደለሁም ገና ያንቺው ቢጤ እውቀትንም ሆነ ምክርን ምፈልግ ነኝ !!!
ሁሌም ከትላንት ዛሬያችንን ከዛሬ ነጋችንን ለማስዋብ እንጣር 🌹
እናም " ውጫዊ ውበት ቀልብን ይስባል"
"ውስጣዊ ማንነት ግን ልብን ያስገዛል"
𝑚𝑒𝑑𝑖🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
/channel/tewihd
ልብና \\\ ሸክላ
ልብና ሸክላን የሚያመሳስላቸው ነገር አላቸዉ ሁለቱም እንክብካቤን ይሻሉ በጥንቃቄ ከያዝናቸዉ ሳይበላሹ ሁሌም ይኖራሉ፡፡
ሳንከባከባቸዉ ከወደቁ ግን ይጎዳሉ የሰበራሉ ፡፡
ምናልባት ልንጠግናቸዉ እንችል ይሆናል ቢሆንም ግን አንደ በፊቱ ልንመልሰዉ አንችልም !!✍️
medi 🖋
/channel/medi_bint_seid_umu_hibetullah
🌱ፎቶ እና ሙሽሪት !!!
ፎቶ መነሳቱን ስልጣኔ አርገን
በሄድንበት ቦታ መቅረፅ አበዛን
ሴቷ ተኳኩላ ሊፕስቲክ ተቀብታ
መነሳቱን ያዘች ባገኘችው ቦታ
ደግሞ የሚገርመው የነሙሽሪት
እንዳልሆነ ሁና ሰርጌነው በማለት
ጠባብ ቤሎ ለብሳ ፊቷን በመቀባት
እጅ እግሯን አስውባ መጣች ወደ ወንዶች
አምረሻል ሙሽሪት ብለው እንዲያደንቋት
ሚዜወቿን ሰብስባ ፎቶ ለመነሳት
ቁማ ተንበርክካ ተነሳች በአይነት
ወንዶች እየገቡም ተነሱ አብረዋት
እንዲህ ተቀባብተሽ ለአጅ ነቢ መታየት
ፎቶ ከወንድ ጋር ተቃቅፈሽ መነሳት
ጠባብ ልብስ ለብሰሽ ለወንዶች መታየት
ዱንያ አኼራሽን ያበላሻል ቢሏት
አለች ዝም በሉኝ የዛሬን ልደሰት
ሙዚቃም ክፈቱ ሰርጌ ደምቆ ልሙት
ብላ ተናገረች ሀያዕዋ ርቋት
ሸይጧን ማንነቷን እንድትረሳ አድርጓት
ከሙዚቃው ገብታ ዳንሱንም ጀመረች
አንዴ ከባሏጋር አንዴከሴቶችጋር መጨፈር ጀመረች
በዚች አጭር ጊዜ ብዙ ወንጀል ሰራች
ሰርጌ ለቅሶ ይመስላል ብላ ስላሰበች
እንዲህ ተኳኩለሽ የተነሳሽው
በሁሉም እጅ ገባ አንች ሳታስቢው
ውዱ ወንድምሽን እንቅልፍ ነሳሽው
ወንጀል ላይ ለምውደቅ አንች ሰበብ ሆንሽው
እህቴ አድምጭኝ እስኪ ከሰማሽ
ስሜት አሸንፎሽ ሱናን ቸላ ያልሽ
ፎቶ ይፈቀዳል ለአንዳንድ ነገር ሲሉሽ
በአገኘሽው ቦታ መቼ ተነሽ አሉሽ
ለትምህርት መረጃ እንዲሁም ለፓስፖርት
በጣም አስፈላጊ ቁም ነገር ለሆኑት
የዛሬን ልደሰት ብለሽ በማሰብሽ
ስንቱን ወንጀል ሰርተሽ ከጌታሽ ተጣላሽ
በይ አሁንም ይብቃሽ እስቲግፋር አድርጊ
ለሰራሽው ወንጀል ይቅርታ ጠይቂ
በረሱሉ ሱና ቀጥ ብለሽ ዝለቂ
ቁርአንን ሀዲስን አድርጊው መመሪያሽ
ዘመን አመጣሹን መከተሉ ይብቃሽ
ሂጃብሽን ልበሽ አላህ እንዲወድሽ
ተገላልጦ መሄድ በይ አሁንም ይብቃሽ
የዛሬን ልደሰት ማለቱ ይቅርብሽ
ቁርአንን አንብቢ ኢልምንም ተማሪ
ከስሜትሽ ወጥተሽ በእውቀት እንድትሰሪ
ጓደኛም ምረጭ ምርጥ ተቀማማጭ
ለዲን ተቆርቋሪ ስታጠፊ ገሳጭ
በረሱሉ ሱና ታንፃ ያደገች
ለዘመን አመጣሽ ያልተንበረከከች
የረሱሉን ሱና አጥብቃ የያዘች
ለአላህ እጅ ሰጥታ በሂጃብ የፀናች
ለሽርክ ለቢድዓ ጠላቱ የሆነች
ሱናን ለማስፋፋት ቆርጣ የተነሳች
ይችን ሰው ውደጃት ምርጥ የአላህ ባሪያ ናት
መሰሎቿ ይብዙ አላህ ይጠብቃት
ጓደኛ ካልመረጥሽ ለዲን ተቆርቋሪ
አንችም እንደሷ ነሽ የምትሆኝ ከሳሪ
ስታጠፊ አትመክርሽ ይልቅ ማበራታት
ለዲኗ አትጨነቅ ስሜት አሸንፏት
አላማ ያረገች ተደስታ ኑራ ተደስታ መሞት
ሀራም ይሁን ሀላል ምንም ጭንቅ የላት
የሷ ፍላጎቷ ለጊዜው መደሰት
ይች አትጠቅምሽም በቶሎው ራቂያት
ሞት መጥቶ ሳይወስድሽ ሳታደርጊ ተውበት
ስራሽ ተበላሽቶ ሳትቆሚ ከአላህ ፊት
አሁኑ ሰው ምረጭ መንገድ አመላካች
ለአላህ እጅ ሰጥታ የወሰነች መሞት
የፎቶ ጉዳቱ በጣም የከፋ ነው
ዱንያን አኼራን የሚያበላሽ ነው
አደራሽ እህቴ ፈጣሪሽን ፍሪው
ከወንጀል ርቀሽ እሱኑ ተገዥው
ለጊዜያዊ ደስታ የአኼራ ቤትሽን ምነው ዘነጋሽው
በሱና ቀጥ በይ ከወንጀል ርቀሽ
በጀነተል ፊርደውስ እንዲሆን መኗሪያሽ።
✍ በወንድም አህመድ ሀጅ
📚✍ኢብኑ ተይሚያህ የሱና መድረሳ የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦
/channel/slaveOfAllahsua
📮የፌስቡክ ገፃችንን ጆይን ያድርጉ፦
https://m.facebook.com/Sualih-Ibnu-Muhammed-ሷሊህ-ኢብኑ-ሙሃመድ-1600253226970961/?refid=11&ref=opera_speed_dial&__xts__%5B0%5D=11.%7B%22event%22%3A%22visit_page_tab%22%2C%22user_id%22%3A100009332698134%2C%22page_id%22%3A1600253226970961%7D
👍👍↖️👍👍↖️👍👍↖️👍
🌴ለጎደኞቻችን ሼር እናድርግ✍
ከሊቃውንት አንደበት
📗
ኢማሙ ሻፊዒይ(ረሂመሁላህ)
«ከእናንተ በዕውቀት ከሚበልጣችሁ ሰው እውቀትን ተማሩ። በዕውቀት የምትበልጧቸውን ደግሞ አስተምሩ።
ይህን አደረጋችሁ ማለት ያላወቃችሁትን ዕውቀት ቀሰማችሁ ፣ ያወቃችሁትን ዕውቀት ደግሞ ሸመደዳችሁ ማለት ነው።»
{አልሙቀፋ አልከቢር 5/226}
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd