♻️📌የጁምዓ ቀን ማስታወሻዎች
የጁሙአ ቀን ደረጃ ( ابن القيم)
➛🔘ኢብኑል ቀይም አል ጀዉዚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
⓵« የጁምዓ ቀን ተመላላሽ ባዕል ነው አይሁዳንና ነሷራን ለመቃረንና በዚህ ቀን የተለዩ በሆኑ ኢባዳዎች ላይ እንዲጠነክር ሲባል ብቻውን መፆም ሀራም ይሆናል።
⓶«የጁምአ ቀን በጀነት አሏህ ለጀነት ሰወች ግልፅ የሚሆንበት ቀን ነው።
قال تعالي
አሏህ እንዲህ አለ፦
ﻭَﻟَﺪَﻳْﻨَﺎ ﻣَﺰِﻳﺪٌ
ከኛ ጋ ጭማሬ አለ
ﻗﺎﻝ ﺃﻧﺲ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ
አነስ ረዲየሏሁ አንሁ ይህን አንቀፅ በተመለከተ እንዲህ አለ፦
ﻳﺘﺠﻠﻰ ﻟﻬﻢ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺟﻤﻌﺔ
(በየ ጁምአ ቀን ለጀነት ሰወች አሏህ ይገለጠላቸዋል)
⓷« የጁምዓህ ቀን ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ነው።
قال ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ وعلى آله وصحبه وسلم
ﺧﻴﺮ ﻳﻮﻡ ﻃﻠﻌﺖ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺸﻤﺲ ﻳﻮﻡ
ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ [ ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ]
የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
ፀሀይ የወጣችበት ከሆነ ቀን ሁሉ በላጩ ቀን ማለት የጁምአህ ቀን ነው።
📚[[ሙስሊም ዘግበውታል]]
⓸«በጁምአህ ቀን ዉስጥ አሏህ ተለምኖባት የማይመልስባት ሰአት አለች።
ﻗﺎﻝ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ وعلى آله وصحبه وسلم
ﻓﻴﻪ ﺳﺎﻋﺔ ﻻ ﻳﻮﺍﻓﻘﻬﺎ ﻋﺒﺪ ﻣﺴﻠﻢ
ﻭﻫﻮ ﻗﺎﺋﻢ ﻳُﺼﻠﻲ ﻳﺴﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺷﻴﺌﺎً ﺇﻻ
ﺃﻋﻄﺎﻩ ﺇﻳﺎﻩ
[ ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ﻭﻣﺴﻠﻢ]
የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንዲህ ብለዋል፦
በጁምአህ ቀን ውስጥ የሆነች ግዜ አለች አንድ ሙስሊም የሆነ ባሪያ ቁሞ እየሰገደ እና አሏህን እየለመነ አያገኛትም የለመነውን ነገር አሏህ ቢሰጠው እንጂ።
📚[[ቡኻሪና መስሊም ዘግበውታል]]
⓹«የጁምአህ ቀን ትንሳኤ ቀን የምትቆምበት ቀን ነው።
قال ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ﻭﻻ ﺗﻘﻮﻡ ﺍﻟﺴﺎﻋﺔ ﺇﻻ ﻓﻲ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ
[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ]
መልእክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
ትንሳኤ ቀን ጁምአህ ቀን እንጂ አትቆምም።
📚[[ሙስሊም ዘግበውታል]]
⓺«የጁምአህ ቀን ወንጀሎች የሚታበሱበት ቀን ነው።
⓻«በጁምአህ ቀን የሞተ ሰው መጨረሻው ያማረ መሆኑን ያሳያል።
قال ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ﻣﻦ ﻣﺎﺕ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﺃﻭ ﻟﻴﻠﺔ
ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﻭُﻗِﻲَ ﻓﺘﻨﺔ ﺍﻟﻘﺒﺮ
[ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ]
የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
የጁምአህ ቀን ወይም ለሊት የሞተ ሰው ከቀብር ፈተና ተጠበቀ ።
📚[[ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል]]
⓵«የጁምአህ ቀን ሰደቃ ከሌላው ቀን ሰደቃ እጅግ በጣም ምንዳዉ ይደራረባል።
ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ
ﻭﺷﺎﻫﺪﺕُ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺇﺫﺍ ﺧﺮﺝ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﻳﺄﺧﺬ
ﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﻓﻲ ﺍﻟﺒﻴﺖ ﺧﺒﺰ ﺃﻭ ﻏﻴﺮﻩ ﻓﻴﺘﺼﺪﻕﺑﻪ
ﻓﻲ ﻃﺮﻳﻘﻪ ﺳﺮﺍً
ኢብኑል ቀይም አሏህ ይዘንላቸውና ኢብኑ ተይምያ ወደ ጁምአህ ሲወጡ እቤት ያገኙትን ዳቦም ሆነ ሌላ ነገር ይይዙና በመንገዳቸው በሚስጥር ሲሶድቁት ተጥጃለሁ ይላሉ።
አሏህ በጁምዓህ ቀን ከሚጠቀሙ የአሏህ ባሮች ያድርገን።"
➬➬➬
🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹
@tewihd
قال ابن رجب رحمه الله :
" وأفضل الأعمال خشية الله في السر والعلن "
📕 فتح الباري [٦٣/٤]
_ኢብኑ ረጀብ_ [አሏህ ይዘንለት] እንድህ አለ፦
"ከስራዎች በላጩ በሚስጥርም በይፋም አሏህን መፍራት ነው።"
📕ፈትሁል ባሪ (4/63)
👇👇👇
@tewihd
ኢማሙ አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይሉሃል:-
«ስለ ተውሒድ ስትናገር የሽርክ ሰዎች ይቃወሙሃል።
ስለ ሱና ስታወራ የቢድዓ ሰዎች ይቃወሙሃል።
ስለ ማስረጃና ማረጋገጫ ስትናገር የመዝሃብ ጭፍን ተከታዮች; ሱፍዮች እና መሃይማን ይቃወሙሃል።
ስለ በመልካም ነገር (ሙስሊም) መሪዎችን ስለመታዘዝ፣ ለነርሱ ዱዓ ስለማድረግ፣ እነርሱን ስለመምከር፣ እና ስለ አህለል ሱንናህ ዓቂዳ ስትናገር ኸዋሪጆች እና ሌሎች አፈንጋጭ ቡድንተኞች ይቃወሙሃል።
ስለኢስላም እና በእለት ተእለት ኑራችን (ኢስላምን) ስለመተግበር ስትናገር ሴኩላሪስቶች፣ ሊበራሊስቶች (ፀረ–እምነት ቡድኖች) እና እነሱን የመሳሰሉ ዲናችንን ከእለት ተእለት ኑራችን መለየት የሚፈልጉት ይቃወሙሃል።
አህለል ሱንናህ እጅጉን ባይተዋሮች (እንግዶች) ናቸው። እነዚያ (የጥመት) ቡድኖች በእኛ (በአህለል ሱናዎች) ላይ በሚቻላቸው ሁሉ ጦርነት አውጀዋል። በድምፅ በሚታይ፣ በፅህፈት ጦርነት አውጀውብናል። ቤተሰብና ጓደኛ ሁሉ ሳይቀር በዚህ እንግዳ ላይ ጦርነትን አውጀዋል።ሆኖም ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ ግን በዚህ ባይተዋርነታችን ደስተኞች ነን። እንኮራበታለንም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባይተዋሮችን አወድሰዋቸዋልና።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: –
“ ኢስላም እንግዳ ሆኖ ጀምሯል። እንደ ጅማሮውም እንግዳ ሆኖ ይመለሳል። ለእንግዶቹ ‘ጡባ’ (ጀነት ውስጥ የምትገኝ ዛፍ ወይንም መልካም ነገር) አለቻቸው።”
“እነርሱ (እንግዶቹ) እነማን ናቸው?” ተብለው በተጠየቁም ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምም: “ሰዎች በተበላሹ ጊዜ (እራሳቸውን እና ሌሎችንም) አስተካካዮች ናቸው።” ብለው መለሱ።» [ሲልሲላህ አስሰሒሐህ 1273]
👇👇👇
@tewihd
“ሱናህ” ማለት ምን ማለት ነው?
“ሱናህ” ማለት ብዙሃኑ ህዝብ ዘንድ ያለው ፍቺው ቢሰሩት አጅር
የሚያስገኝ ቢተውት ግን የማያስቀጣ የዒባዳ አይነት የሚል
ነው፡፡ ይሄ ግን ዘግይቶ የመጣ ፊቅሃዊ ፍቺ ነው፡፡ በተለያዩ
የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሦች ላይ የሚገኘውን
“ሱናህ” የሚል ቃል በዚህ መልኩ ከፈታነው ስህተት ላይ
እንወድቃለን፡፡ ለምሳሌ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
“በርግጥም ከናንተ በፊት ያሉትን ሰዎች ፈለጎች ( # ሱናዎች )
ትከተላላችሁ” ሲሉ ሶሐቦች “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው
(ትከተላላችሁ) የምትለን?” ሲሉ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ፡፡
ልብ ይበሉ በዚህ ሐዲሥ ላይ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
የአይሁድና የክርስቲያኖችን ጥፉ አካሄድ “ሱናህ” ሲሉ
ጠርተውታል፡፡ ይሄ እንግዲህ የሱናህ ቋንቋዊ ፍቺ እንደሆነ
ያሳየናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የትኛውም አካሄድ ወይም ፈለግ
ሱናህ ይባላል ማለት ነው በቋንቋ ደረጃ፡፡
የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አጠቃላይ አስተምሮም “ሱናህ”
ይባላል፡፡ ይህን ግልፅ ከሚያደርጉልን ማስረጃዎች አንዱን
እንመልከት፡
ሶስት ሰዎች ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚስቶች ዘንድ
አንዷጋ ይሄዱና ስለ እሳቸው ዒባዳህ ይጠይቃሉ፡፡ ሲነገራቸው
ጊዜ ቀለል አድርገው አዩት፡፡ ከዚያ ግን “እኛንና እሳቸውን ምን
አገናኘን? እሳቸው እኮ ያለፈውም የሚመጣውም ወንጀላቸውን
ይቅር ተብሎላቸዋል” ይላሉ፡፡ ከዚያም አንዱ “እኔ ከዚህ በኋላ
ሌሊቱን ሁልጊዜ እሰግዳለሁ (አልተኛም)” አለ፡፡ ሌላው “እኔ
አመቱን ሙሉ እፆማለሁ አላፈጥርም” አለ፡፡ ሌላው “እኔ ሴቶችን
አገላለሁ (አልቀርብም)፡፡ በጭራሽ አላገባም” አለ፡፡ ከዚያ ነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደነሱ በመሄድ “እናንተ ናችሁ እንዲህ
እንዲህ ያላችሁት? ወላሂ እኔ ከናንተ በላይ አላህን ፈሪ እና
የምጠነቀቀው ነኝ፡፡ ይሁን እንጂ እኔ እፆማለሁ አፈጥራለሁ፡፡
(ሌሊቱንም) እሰግዳለሁ እተኛለሁ፡፡ ሴቶችንም አገባለሁ፡፡
# ከሱናዬ_የዞረ_ከኔ_አይደለም !!” አሉ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)
ይስተዋል!! በዚህ ሐዲሥ ላይ “ሱናህ” ተብሎ የተገለፀው ትርፍ
ዒባዳህ ለማለት አይደለም፡፡ ምክኒያቱም “ግዴታ ያልሆነን ዒባዳ
የተወ ከኔ አይደለም” አይሉምና ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
ይልቁንም እያሉ ያሉት ከኔ ፈለግ ያፈነገጠ ከኔ አይደለም ነው፡፡
ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ “ሱናህ የሚለው
ቃል በቋንቋ ደረጃ መንገድ ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ
መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የነበሩበትን ቅን
መመሪያና ብርሃን የሚያጠቃልል ነው- ግዴታም ይሁን ትርፍ
ዒባዳህ፡፡ አሁን ያለው ሙያዊ ፍቺ ግን ግዴታ ያልሆነውን የነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፍኖት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን
በአንዳንድ ሐዲሦች ላይ የመጣው ሱናህ የሚለው ቃል በዚህ
ሙያዊ ፍቺ ሊተረጎም አይገባውም፡፡ ለምሳሌ መልእክተኛው
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱናየን አደራችሁን” ማለታቸው እና
“ከሱናዬ የዞረ ከኔ አይደለም” ማለታቸው እንደምሳሌ መውሰድ
ይቻላል፡፡” (ተሕዚሩ አስሳጂድ፡ 44)
ይህንን ግንዛቤ ከሚያጠናክሩልን የዑለማእ ንግግሮች ውስጥ
አንድ ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡
1. “ # ሱናህ ማለት የኑሕ መርከብ ነች፡፡ የተሳፈረባት
ይተርፋል፡፡ ከሷ ወደ ኋላ የቀረ ግን ይሰምጣል፡፡” አልኢማም
ማሊክ ረሒመሁላህ፡፡ ያስተውሉ!! አልኢማም ማሊክ በዚህ
ንግግራቸው ላይ እያነሱ ያለው ስለ ትርፍ ዒባዳህ ሳይሆን
አጠቃላይ ስለነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምሮ ነው፡፡
በሚገባ ያጢኑት፡፡
2. “ኢስላም ማለት #ሱናህ እንደሆነ እና ሱና ማለትም ኢስላም
እንደሆነ እወቁ፡፡ አንዱ ያለ ሌላው ፀንቶ አይቆምም፡፡”
አልኢማም አልበርበሃሪ ረሒመሁላህ፡፡ ረጋ ብለው ይመልከቱት፡፡
3. “ቢድዐህ ከልዩነት ጋር የተቆራኘች ናት፡፡ ልክ #ሱናህ
ከመሰባሰብ ጋር የተቆራኘች እንደሆነችው፡፡ የ #ሱናህ እና
የጀማዐህ ሰዎች ይባላል፡፡ ልክ የቢድዐህ እና የልዩነት ሰዎች
እንደሚባለው፡፡” ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ፡፡
በነዚህ የዑለማእ ንግግሮች ውስጥ “ሱናህ” የሚለው ቃል
በጥቅሉ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አካሄድ እንጂ ትርፍ
ዒባዳህ ማለት እንዳልሆነ እጅግ ሲበዛ ግልፅ ነው፡፡ ህዝባችን
ዘንድ በሰፊው የሚታወቀው የሱናህ ፍቺ ግን ትርፍ ዒባዳህ
ማለት እንደሆነ አሳልፈናል፡፡ ከዚህ ፍቺ በትይዩ ያለው ግዴታ
ዒባዳህ ነው፡፡
የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አካሄድና መንገድ “ሱናህ”
ብለን ስንጠራ ግን ከቢድዐ ትይዩ ያለውን ነው፡፡ ሰዎች ግን
በሰፊው የሚያውቁት ዘግይቶ የመጣውን ፊቅሃዊ ፍቺውን ስለሆነ
በዚህ ላይ ግንዛቤ የመሙላት ስራ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡
ያለበለዚያ ለነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሦች እና
ለቀደምት ዑለማዎች ንግግሮች የተዛባ ፍቺ እንድንሰጥ
ያደርገናል፡፡ ይሄ ደግሞ አደገኛ ነገር ነው፡፡ በጥቅሉ “ሱናህ”
ማለት የተፈጠርንበትን አላማ ማለትም አምልኮትን እንዴት
መፈፀም እንዳለብን የሚያሳይ ነብያዊ የአፈፃፀም መመሪያ
ወይም “ማኑዋል” ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ አተናተንም “ሱናህ”
ማለት ትርፉንም ግዴታውንም ዒባዳ የሚያጠቃልል ነው፡፡
እንዳውም ከግዴታ ዒባዳዎችም ባለፈ መሰረታዊ የዐቂዳህ
ርእሰ-ጉዳዮችን ሁሉ የሚያቅፍ ነው- “ሱናህ”፡፡ ለዚህም ነው
ታላላቅ ቀደምቶች ትክክለኛውን የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም አስተምሮ ግልፅ ያደረጉባቸውን እና ጠማማ
አስተሳሰቦችን ያጋለጡባቸውን ኪታቦቻቸውን “አስሱናህ” እያሉ
መጥራታቸው፡፡ ለምሳሌ፡-
1. “አስሱናህ” የዐብዱላህ ኢብኒ አልኢማም አሕመድ ኪታብ
2. “አስሱናህ” የአልኢማም አልበገዊ ኪታብ
3. “ሸርሑ አስሱናህ” የአልኢማም አልበርበሃሪ ኪታብ
4. “ኡሱሉ አስሱናህ” የአልኢማም አሕመድ እና ሌሎችም
ከዚህ በመነሳት ያልተበከለውን የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
አስተምህሮት የሚከተለውን ሰው “ሱኒ” ስንለው አጠቃላይ
ስብስቡን ደግሞ “አህሉስሱናህ” እንላለን፡፡ ይሄ ስያሜ ከጥንት
ሰለፎች ዘንድ ጀምሮ የሚታወቅ እንጂ መጤ ነገር አይደለም፡፡
ወላሁ አዕለም
✍ (ኢብኑ ሙነወር)
~~~~~~~~~~~
/channel/tewihd
የተዘነጉ #ሱናዎች
ንፅህናው በተረጋገጠ ጫማ ሰላትን መስገድ።
,
አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ ተጠየቀ « ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እስከነጫማቸው ይሰግዱ ነበርን? »
አነስም « አዎን ይሰግዱ ነበር።»
ቡኻሪ
👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
⭕ الإمام أبوبكر الباقلاني والنصارى ⭕
التقى الإمام أبو بكر الباقلاني صاحب (إعجاز القرآن) -رحمه الله- وكان مشهورًا بالمناظرة وقوة الحجّة؛ التقى راهبًا نصرانيًّا.
አቡ በክር አልባቅላኒይ ይህ ሰው ትልቅ ዓሊም ከመሆኑም ባሻገር ክርክር ላይ ሚስተካከለው የለም የሚባልለት ሰው ነው ።
እናላችሁ የሆነ ቀን ይህ ሰው ከአንድ ቄስ ጋር ይገናኙ'ና
⬅ فقال النصراني: أنتم المسلمون عندكم عنصرية؟!
ቄሱ፦"እናንተ ሙስሊሞች ከባድ የሆነ ወገንተኝነት ይታይባችኋል"
⭕ قال الباقلاني: وما ذاك؟!
አቡ በክር፦"እንዴት?"
⬅ قال النصراني: تبيحون لأنفسكم زواج الكتابية -اليهودية أو النصرانية- ولا تبيحون لغيركم الزواج ببناتكم!!
ቄሱ፦ "ምክንያቱም እናንተ ለራሳችሁ ክርስትያን ሴቶችን እና የአይሁድ ሴቶችን ታገባላችሁ፤ ነገር ግን የናንተን ሴቶች ለማንም አሳልፋችሁ አትሰጡም፤ ሀራም ትላላችሁ።"
⭕ قال له الإمام: نحن نتزوج اليهودية لأننا آمنا بموسى، ونتزوج النصرانية لأننا آمنا بعيسى، وأنتم متى ما آمنتم بمحمد زوجناكم بناتنا.
አቡ በክር፦ "አሃ! እኛ እኮ ክርስቲያን ሴቶችን ምናገባው በዒሳ ስለምናምን ነው።
የአይሁድ ሴቶችን ምናገባው ደግሞ በሙሳ ስለምናምን ነው፤ እናንተም በሙሀመድ ካመናችሁ ሴቶቻችንን እንድርላችኋለን።"
💥 فبهت الذي كفر!!
✹•━━━━━━•✹
كان أبو بكر الباقلاني -رحمه الله تعالى- من كبار علماء عصره، فاختاره ملك العراق وأرسله في عام ٣٧١ للهجرة لمناظرة النصارى في القسطنطينية.
አቡ በክር በሂጅራ አቆጣጠር በ371 ላይ ከነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዑለማኦች ይመደብ ስለነበር የግዜው የነበረው የዒራቅ ገዢ አቡ በክርን ወደ ቆስጠንጢንያ በግዜው የሮም ዋና ከተማ ለክርክር ላከው።
عندما سمع ملك الروم بقدوم أبي بكر الباقلاني أمر حاشيته أن يُقَصّروا من طول الباب بحيث يضطر الباقلاني عند الدخول إلى خفض رأسه وجسده كهيئة الركوع فيذلّ أمام ملك الروم وحاشيته!!
የሮሙ ንጉስ የአቡ በክርን መድረስ በሰማ ግዜ ለወታደሮቹ የቤተመንግስቱን በር እንዲያሳጥሩት'ና፤ አቡ በክር ሲገባ አጎብድዶ እንዲጋባ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ባዘዛቸው መሰረት ወደ ቤተ መንግስ እሚገባ ሰው ሁሉ ዝቅ ብሎ እንዲገባ በሩን አሳጠሩት።
💥لما حضر الباقلاني عرف الحيلة، فأدار جسمه إلى الخلف وركع ثم دخل من الباب وهو يمشي للوراء جاعلًا قفاه لملك الروم بدلًا من وجهه!!
አቡ በክርም ቤተ መንግስት ደርሶ ሊገባ ሲል በሩ አጥሮ ተመለከተ'ና የተሸረበውን ሴራ በመረዳት ፊቱን አዞሮ፤ ወደ ኋላ በማጎብደድ ለንጉሱ ፊት ቂጡን ሰጥቶ ገባ።
💥هنا علم الملك أنه إمام داهية!!
ይህን ግዜ ንጉሱ የአቡ በክርን ከባድነት ተገነዘበ።
دخل الباقلاني فحياهم ولم يسلم عليهم (لنهي الرسول -صلى الله عليه وسلم- عن ابتداء أهل الكتاب بالتسليم).
አቡ በክር ከገባ በኋላ ከንጉሱ ዙርያ የተሰለፉትን ቄሶችን ሲያይ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ አይነት ነገር አላቸው [ሸሪዓው ሰላምታን ግን አላቀረበም ለምን አህለል ኪታብ ስለነበሩ]።
⭕ ثم التفت إلى الراهب الأكبر وقال له: كيف حالكم وكيف الأهل والأولاد؟
ከዝያም ወደ ዋናው ቄሳቸው ዞር ብሎ፦ "እንዴት ነህ? ቤተሰብ ልጆች እንዴን ናቸው?" አለው።
⬅ غضب ملك الروم وقال: ألم تعلم بأن رهباننا لا يتزوّجون ولا ينجبون الأطفال؟!
ይህን ሲሰማ ንጉሱ እጅግ በመቆጣት "ቄሳችንን እንደማይጋቡ እና እንደማይዋለዱ እያወቅክ እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቃለህ?" አለው።
⭕ فقال أبو بكر: الله أكبر!! تُنَزّهون رهبانكم عن الزواج والإنجاب، ثم تتهمون ربكم بأنه تزوج مريم وأنجب عيسى؟!
አቡ በክርም፦ "አላሁ አክበር !
ቄሶቻችሁን ልጅ ከመውለድ እና ሚስት ከማግባት እያጥራራችሁ ለአላህ ግን የመርየም ልጅ የሆነውን ዒሳን ልጁ ነው በማለት ትቀጥፋላችሁ" አለው።
⬅ فزاد غضب الملك، ثم قال الملك -بكل وقاحة-: فما قولك فيما فعلت عائشة؟!
የንጉሱ ንዴት እየጨመረ በንቀት ተውጦ፦ "ዓኢሻ ስለፈፀመችው ቅጥፈት ምን ትላለህ" አለው።
⭕ قال أبو بكر: إن كانت عائشة -رضي الله عنها- قد اتهمت (اتهمها المنافقون) فإن مريم قد أتهمت أيضًا (اتهمها اليهود) وكلتاهما طاهرة، ولكن عائشة تزوجت ولم تنجب، أمّا مريم فقد أنجبت بلا زواج!!
አቡ በክርም፦ "ዓኢሻ ባልሰራችው ያወሩባት ሙናፊቆች ናቸው።
መርየምም ባልሰራችው ያወሩባት የሁዶች ናቸው፤ ሁለቱም ግን ንፁሃን ናቸው።
☞ መርየም ደግሞ ትዳር አልያዘችም ፤ ግን ወልዳለች። ታዲያ ማን ናት እስቲ ከሁለቱ ለጭፍን ወቀሳ ቅርብ የሆነችው።
⁉ فأيهما تكون أولى بالتهمة الباطلة وحاشاهما -رضي الله عنهما-؟!
☞ እውነት እናውራ ካልን ዓኢሻ ትዳር ይዛለች ግን በውሸት ቢቀጠፍባትም አልወለደችም።
ሁለቱም ንፁሃን እንስቶች
ናቸው" አለ።
💥 فجن جنون الملك!
⬅ قال الملك: هل كان نبيكم يغزو؟!
ንጉሱ ብስጭቱ ጨመረ እና፦ "ነብያችሁ ለጦርነት ይዘምት ነበር?" አለው።
⭕ قال أبو بكر: نعم.
አቡ በክርም፦ "አዎን" አለ።
⬅ قال الملك: فهل كان يقاتل في المقدمة؟!
ንጉሱም፦ "በጦርነት ሰዐት ፊት ለፊት ገብቶ ይጋፈጥ ነበር?" አለው።
⭕ قال أبو بكر: نعم.
አቡ በክርም፦ "አዎን" አለው።
⬅ قال الملك: فهل كان ينتصر؟!
ንጉሱም፦ "ድልን ይቀዳጅ ነበር?" አለው።
⭕ قال أبو بكر: نعم.
አቡ በክርም፦ "አዎን" አለው።
⬅ قال الملك: فهل كان يُهزَم؟!
ንጉሱም፦ "ይሸነፍስ ነበር?" አለው።
⭕ قال أبو بكر: نعم.
አቡ በክርም፦ "አዎን" አለው።
⬅ قال الملك: عجيب! نبيٌّ ويُهزّم؟!
ንጉሱም፦ "ይገርማል! ነቢይ ይሸነፋል እንዴ?" አለ።
⭕ فقال أبو بكر: أإله ويُصلَب؟!
አቡ በክርም፦ "ይገርማል!
ጌታ ይሰቀላል እንዴ?" ብሎ ክርክሩን አሳመረለት።
💥 فَبُهِتَ الذي كفر!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
ለሱብሒ ሶላት መነሳት ለከበደው
ሙእሚን ከመልካም ሥራ አይደክምም፣ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስም አይሰለችምም፡፡ በተለይ
ከዒባዳ፡፡ የአምልኮ ተግባራት የተደነገጉት ለርሱ ለራሱ ጥቅም መሆኑን ያውቃልና፡፡
ስለሆነም ከአንዱ ሶላት ሲወጣ ሌላኛውን ይናፍቃል፡፡ ዒሻ ላይ ሆኖ ስለ ሱብሒ ያስባል፡፡
ሙስሊሞች እንደየእምነታቸው የጥንካሬ ደረጃም ለሶላቱ የሚሰጡት ግምት ይለያያል፡፡
ወዲህ ለሶላት የሚጓጉ እንዳሉ ሁሉ ወዲያ ደግሞ የሶላት የሚከብዳቸው ይኖራሉ፡፡ በተለይ
የሱብሒ ሶላት፡፡ በዚህም የተነሳ በጣም አሳልፈው ከነጋ በኋላ የሚሰግዱ ያሉ ሲሆን፤
ጭራሹኑ የማይሰግዱም አሉ፡፡
የሱብሒ ሶላት መነሳት ከከበደን እነኚህን ነገሮች እናስታውስ -
1- የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሙናፊቅ የሚከብዱ ሁለት ሶላቶች የዒሻ እና የሱብሒ
ሶላቶች ናቸው ብለዋልና ከሙናፊቅ ባህሪ ይጠንቀቅ፡፡
2- ሰዎች የሱብሒን እና የዒሻን ሶላት ትሩፋት ቢያውቁ በእንፉቅቅም ቢሆን ሄደው በሰገዱ
ነበር፡፡ ብለዋልና ትሩፋቷን እናስብ፡፡
3- ከሱብሒ ሶላት በፊት የምትሰገድ የሱንና ከዚህች ዓለም እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ
በላጭ ናትና ታላቅ ነገር አያምልጠን፡፡
4- የሱብሒን ሶላት በጀመዓ የሰገደ ቀኑን በአላህ ዋስትናና ከለላ ሥር ይኖረዋል ብለዋልና
የአላህ ከለላና ጥበቃ አይለፈን፡፡
5- አላህ ሆይ ከሕዝቦች ማለዳቸውን ባርክላቸው ብለዋልና በረከቱን እንሻማ፡፡
6- የሱብሒ ሰዓት የአላህ መላእክት የሚጣዱበት ነውና በሰዓቱን ንቁ እንሁን፡፡
7- የሱብሒን ሶላት የሰገደ ቀኑን ሙሉ ንቁ ሆኖ በጥሩ ስሜትና በደስ ይውላል፡፡
8- ከጣፋጭ እንቅልፍ ተነስቶ ሱብሒን መስገድ መቻል በነፍሲያ ላይ ትልቅ የመወዳጀት
ምልክት ነው፡፡
9- ሱብሒን ተነስቶ መስገድ መቻል አላህን ከራስ አብልጦ የመውደድ ምልክት ነው፡፡
10- ሱብሒን ተነስቶ መስገድ መቻል ሸይጣንን ድል ማድረግ ነው፡፡
11- የሱብሒ ሶላት እንደሌሎች የተቀሩት የግዴት ሶላቶች ሁሉ ግዴታ ናት፡፡
ለሱብሒ ሶላት ለመነሳት የሚያግዙ ነገሮች
1- አምሽቶ አለመተኛት፣
2- አላህን መፍራት፣
3- ዉዱእ ላይ ሆኖ መተኛት፣
4- ለመነሳት ኒያ አድርጎ መተኛት፣
5- ቀኑን በመልካም ሥራ ማሳለፍ፣
6- አላህ ምህረት መለመን፣
7- አላህን አብዝቶ ማውሳት፣
8- ከኃጢኣት መራቅ፣
ኢማሙ ሻፊዕ (ረህመቱላሂ አለይሂ) እንዲህም ብለዋል፡-
أجمع العلماء على أن من استبانت له سنة النبي صلى الله عليه وسلم لم يحل له أن يدعها لقول أحد ا"
አንድ ሰው የመልዕተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም ሱና ግልፅ ከተደረገለት ቡሃላ ለሌሎች ንግግር ሲል መተዉ እንደማይፈድለት ኡለሞች በጋራ ተስማምተውበታል ብለዋል፡፡
(ኢብኑል ቀይም ኢላም አል ሙወቂን(2/361)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
አል-አላመቱ ኢብኑ ቁዳማህ አት-ተዋቢይነ በሚለው ኪታቡ ከአብዱልዋሂድ ኢብኑ ዘይድ (የሚከተለውን አስገራሚ ታሪክ አስተላልፏል አብረን እንከታተለው)
አብዱልዋሂድ ኢብኑ ዘይድ እንዲህ ይላአሉ:-
"በአንዴት ሰፊና ላይ (እየተጓዝን ነበር) ንፋስ ወደ የብስ ጣለችን (እዚያም) አረፍን
ወዳው ጣኦዎትን የሚያመልክ ሰው አየን እና ወደሱም በማቅናት አንተ ሰው ሆይ ማንን ነው የምታመልከው? ብለን አልነው።
እሱም ወደ ጣኦዎቱ አመላከተን
ይህ የሚመለክ አምላክ አይደለም አልነው
(ታዲያ) እናንተ ማንን ነው የምታመልኩት? (ሲል ጠየቀን)
አላህን ነው የምናመልከው አልነው።
አላህ ማነው? (ሲል ጠየቀን)
(አላህ ብሎ ማለት በዛቱ) ከአርሹ በላይ ስልጣኑ በምድር ላይ በህያው እና በሙታን ላይ ፍርዶ የሆነ ነው አልነው።
በሱ(በአላህ መኖር) እንዴት አወቃችሁ? አለን
ይህ ንጉስ፣ታላቅ እና የተላቀ የሆነው(አላህ) ቸር የሆነን መልእክተኛን ላከልን እና በዚህ(በሱ መኖር) ነገርን አልነው።
መልእክተኛው ምን ሰራ? አለን
መልእክቱን አደረሰ ከዚያም አላህ ገደለው አልነው።
ከናንተ ጋር ምልክት ትቷልን? አለን
(እኛም) አዎ አልነው
እሱም (መልእክተኛው) ምን ትቷል? አለን
(እኛም) ከእኛ ዘንድ ንጉስ ከሆነ(ጌታው የወረደ) ቁራአንን ትቷል አልነው።
ንጉስ የሆነውን(ጌታችሁን) ቁራአን አሳዩኝ የንጉሱች መፃሀፍ ያማረች ልትሆን ይገባታል አለ
ሙስሀፍን(ቁራአንን) አመጣንለት
እሄን በጣም የሚያውቀው ማነው? (ሲል ጠየቀ)
ከቁራአን የሆነን ምእራፍ አነበብንለት (የጀመርነውን የቁራአን) ምእራፍ እስከምን ጨርስ ድረስ እሱ እያለቀሰ እኛም ከመቅራት አልተወገድንም እንቀራለን እሱም ያለቅሳል
ለዚህ የንግግር ባልተቤት ላይታመፅ ይገባል አለ እና ከዚያም ሰለመ የእስልምና ህግጋቶችን እና ከቁራአን ምእራፎችን አስተማርነው ከኛም ጋር በሰፊናይቷ ላይ አሳፈርነው።
በሄድን እና በእኛም ላይ ለይሉ ጨልሞ ሁላችንም የምኝታ ቦታችንን በያዝን ግዜ
እናንተ ሰዎች ሆይ ይሄ ያመላከታችሁኝ ጌታ ለይሉ በጨለመ ግዜ ይተኛልን? አለን
አንተ የአላህ ባሪያ እሱ ሂያው፣ትልቅ እና በራሱ ተቋቋሚ የሆነ ጌታ ነው አይታኛም አልነው።
ምንኛ የጠፋችሁ ባሮች ናችሁ ጌታችሁ ሳይተኛ እናንተ ትተኛላችሁን አለን እና ከዚያም ትቶን አምልኮውን ተየያዘው
ሀገራችን በደረስን ግዜ ለባልደረባየ ብየ አልኩት ይህ ሰው ወደእስልምና አድስ የገባ እና ሀገሩም እሩቅ ነው (አልኩት እና) ዲርሀምን ሰበሰብንለት እና ሰጠነው።
ይህ ምንድን ነው? አለ
ለጉዳይህ የምታጠፋው ይሆንሀል አልነው
ላኢላሀኢለላህ! እኔ በባህር ደሴት ላይ በውስጡ ጣኦዎት ሳመልክ ያላስቸገረኝን አሁን እሱን (አላህን)ካወቅኩት በኋላ ያስቸግረኛልን?! አለ
ከዚያም ለራሱ ስራን መስራት ያዘ ከዚያም በኋላ እስከሞተ ድረስ ትልቅ ሷሊህ ሆነ
ምንጭ [አተዋቢን ሊብኒ ቁዳማህ ገፅ 179]
ወንድማችን ኢብኑ ሙሀመድዘይን
👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
ሸይኽ ኢስላም ኢብኑል ቀይም
(رحمه الله)
እንዲህ ይላሉ
👉 ከታናሹም ይሁን
ከሚጠላውም ሰው ይሁን
ከጠላቱም ይሁን
👉 ሀቅ 👈
መጥቶለት ለዚህ ሀቅ ከመጎተት የተኩራራ የሆነ ሰው
ኩራቱ የላቀ በሆነው الله ላይ ነው የሚሆነው
ምክንያቱም الله ራሱ ሀቅ ነውና
فإن الله هو الحق
👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
"ታላቅ ዲናዊ ኮርስ በጎንደር ከተማ"
የፊታችን ጁሙዓ የካቲት 12 / 2013 ከሰዓት በኋላ ጅማሮውን አድርጎ አስከ እሁድ የካቲት 14/2013 ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ የሚቆይ የሶስት ቀናት ኮርስ በጎንደር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ኮርሱን የሚሰጡት ፡- ታዋቂው ዓሊም ሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ያሲን (አል`ለተምይ) - ሃፊዞሁሏህ - ይሆናሉ፡፡
ኮርሱ ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ጀሚል ዘይኑ - ረሂመሁሏህ - “አቂደቱል ኢስላምያ ሚነልኪታቢ ወስ'ሱናህ” በሚል ርዕስ ባዘጋጁት አጨር የጥያቄና መልስ ኪታብ ዙሪያ ይሆናል፡፡
ኮርሱ የሚካሄደው ፡- “በመስጅድ አስ'ሱናህ”
አድራሻ፡- ቀበሌ 10 ብሪጋታ መውረጃ ጎን
ማሳሰቢያ ፡- - በዚህ ኮርስ ወንዶችም ሴቶችም መሳተፍ ይችላሉ፡፡
#ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በዝግጅቱ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉና ለምትችሉ ሁሉ ይህ ታላቅ አጋጣሚ እንዳያልፋችሁ
ኮርሱ እንዳያመልጣችሁ አደራ! አደራ! አደራ!
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
/channel/alateriqilhaq
كن على بصيرة
قَٱلَ الإِمَام مَالِك"رَحِمَه اللّٰه"
«إِذَا رَأَيتَ قَسَاوَة فِي قَلبك، وَوهناً فِي بَدَنك، وَحِرمَاناً فِي الرِّزق، فَاعلَم أَنكَ تَكَلَّمت فِيمَا لا يُعنِيك»
[ فَيض القَدِير || ٢٨٦/۱ ]
ኢማም ማሊክ አሏህ ይዘንለት እንድህ አለ፦
«ልብህ ላይ ድርቅናን ካገኘህ ፤ ሰውነትህ ከደከመ ፤ ሪዝቅህን ከተነፈግክ ፤ እወቅ በማይመለከትህ ነገር ውስጥ ገብተህ ዘባርቀሃል (አቡክተሃል)»
ፈይዱል ቀዲር 1/286
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
☑️ በነብዩ ላይ ሰለዋት ስታወርድ ሰይድና የሚል አትጨምርاللهم صل على سيدنا محمد
ማለት ትክክል አይደለም። ከሱናነቱ ይልቅ ለቢድአ የቀረበ ነው። ሰይድና ብለህ አትጨምር። ሶሀባዎች ለመልእክተኛው ባንተ ላይ ሰለዋት እንዴት እናውርድ ብለው ሲጠይቁ اللهم صل على محمد በሉ ነው ያላቸው።
ከኢብኑ ኡሰይሚን ንግግር የተወሰደ
#የመልካም ~ #ሴት ~#ፀባይ ~#መገለጫ:
ሀቢቡና ሙሐመድ ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
አልነግራችሁምን?? የጀነት ሴት ስለሆነችው: -
ፍቅር ሰጭ እና ፣ ወላድ የሆነች በተቆጣችበትና መጥፎ በተደረገባት ወይም ባለቤቷ በተቆጣ ጊዜ ይሄ እጄ እኮ በእጅክ ነው አንዲትን መኳል እንኳን ቢሆን አልኳልም አንተ ከእኔ የወደድክ እስክትሆን ድረስ የምትል ነች ።ሷሂህ በሆነ ሰነድ መልካም ሚስት ድምጿን ከባሏ ድምፅ ከፍ አታደርግም ቀንድ እንዳላት ፍየልም አትዋጋም ይልቁንም ባሏ በተቆጣ ጊዜ እርሱን ለማባበል ትሮጣለች።
እያንዳንዳችን ስነምግባራችንን ልናርም እና ስነምግባራችን ልናስተካክል ይገባል ከመሣደብ ሠዎችን ከመገላመጥ ሠዎችን ከማዋረድ እና ዝቅ ከማድረግ የሠዎችን ስም ከማጥፋት እንደዚሁም ከሠዎች ጋር ከመጣላት እና ሠዎችን አዛ ከማድረግ ሁሉ ልንታቀብ ይገባል እውን የነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ተከታይ ከሆንን ማለት ነው ። ነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) አይታወቁም ነበር በህዝቦቻቸው መካከል ታማኙ በመባል እንጂ አይታወቁም ። ዛሬ ስንት እና ስንት ሙስሊሞች አሉ የነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ሙሀባ ሊገለን ነው ብለው የሚናገሩ ሠዎች ነበዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) እንወዳለን ሠሀባዎችን ሠለፎችን እንወዳለን ብለው ነገር ግን አታላይ ሆነው እናያቸዋለን የሚሠርቁ ሆነው እናያቸዋለን የሚያጭበረብሩ ሆነው እናያቸዋለን የሚሠርቁ ሆነው እናያቸዋለን የሚዋሹ ሆነው እናያቸዋለን የአላህ መልክተኛ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ወዳጅ የሆነ ሠው አሚን ነው ታማኝ ነው ማለት ነው ። ለምንድን ነው በታማኝነት የታወቁት ነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ምክንያቱም ነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ታማኝነታቸውን ስለተመለቱ ነው ስላወቁ እና ስላዩት ነው ። በንግግራቸው የማይዋሹ መሆኑን ንፁህ መሆናቸውን ስላረጋገጡ ለነብዩ (ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ይህንን ምስክርነት የሠጡት ማለት ነው ። ታዲያ እኛ ዛሬ በምላሣችን ከምናረገው ዳእዋ ይልቅ ተግባሮቻችን ዳእዋ ሊያደርጉ ይገባል እንደዚሁም አህላቃችን ዳእዋ ሊያደርግ ይገባል ታማኝነታችን ደእዋ ሊያደርግ ይገባል ። ልብሣችን ያምራል ቁመናችን ያምራል ሠላታችን ያምራል ነገር ግን በምላሣችን የምንዋሽ ከሆነ በአካላታችን የምናታልል በተግባራችን የምናታልል የምናጭበረብር ከሆነ አደጋው የከፋ መሆኑን ልናውቅ ይገባል ማለት ነው ።
/channel/kunselefyAleljadaAselefymenhaji/299
« ንግግር እውነት ከሌለበት መልካምነት የለውም። የሚዋሽ ሰው ጥመት ውስጥ ይገባል። ጥመት ውስጥ ደግሞ የገባ ይጠፋል። ከሶስት ነገሮች የተጠበቀ በርግጥ ይድናል ፦ ሰግብግብነት፣ የደመነፍስ ሰሜትና ቁጣ»
[ ዑመር ኢብኑ አል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ ]
ዐብዱላህ ኢብኒ መስዑድ እንዳወሩትና ቡኻሪና ሙስሊም (ረዲየላሁ ዐንሁም አጅመዒን) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሶሓቦችን ትውልድ እና እነርሱን ተክተው የሚመጡ ሁለት ትውልዶች ማለትም ታቢዒዮችን እንዲህ በሚል ንግግር ያላቸውን ደረጃ ተናግረዋል . .
خَيرُ النَّاسِ قَرنِي ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم
« መልካም ሰዎች ማለት እኔ ያለሁበት ትውልድ ነው። ከዚያም እነርሱን የሚከተሉት። ከዚያም እነርሱን የሚከተሉት። »
እነዚህ ናቸው «አስሰለፍ አስሷሊሕ» የሚባሉት ቀደምት አበው ደጋግ ፃድቃን ትውልዶች !!!
@Tewihd
“በሀሰት መናገር እና ሐቅን ከመግለፅ መለጎም ከተጋቡ
የሚወለደው ሐቅን አለማወቅና ፍጡርን ማጥመም እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡”
ኢብኑልቀይም ረሒመሁላህ (አስሰዋዒቁል ሙርሰላህ፡ 1/315)
فضيلة الشيخ محمد ولي الحبشي رحمه الله راحمتا واسعة
https://youtu.be/mpke7HSG1BI
በዘመናችን ሱፊይና ሰለፊይ እያላችሁ ኣትከፋፍሉን እኛ አንድ ነን በማለት በጭፍንና በግብስብስ ለሚጓዙ ሁሉ መፍትሄና አቋም ማስተካከያ የሚሆን
ታላቅና እጅግ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት በታላቁና የሐገራችን ዑለማዎች አንጋፋ በሆኑት በሼይኽ ሙሐመድ ወሌ (ረሂመሁሏህ) ተዘጋጅቶ የቀረበ ትምህርት በመሆኑ ሙስሊሞች ባጠቃላይ ልንማረውና ራሳችንን ልናስተካክልበት ይገባል
/channel/tewihd
يقول شيخ الإسلام ابن تيمية :
الاستعانة بالله والتوكل عليه واللجوء إليه والدعاء له هي التي تقوّي العبد وتيسر عليه أموره ولهذا قال بعض السلف: من سره أن يكون أقوى الناس فليتوكل على الله.
[مجموع الفتاوى 10/32]
«አንድን ባሪያ ጠንካራ የሚያደርጉት እና ነገራቶቹንም የሚያገሩለት (ነገራት) ፡ በአሏህ መታገዝ ፣በእርሱም ላይ መመካት፣ ወደ እርሱም መሸሽ እና እርሱንም መጣራት(ዱዓእ ማድረግ) ናቸው ፤ለዚህም ነው አንዳንድ ሰለፎች ፡ "ከሰዎች ሁሉ በላይ ጠንካራ መሆን የፈለገ ሰው ፡ በአሏህ ላይ ይመካ!" ያሉት። »
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
ቆንጆ ፋኢዳ ብዙ ሙስሊሞች የተዘናጉበት ነገር !!
قال الشيخ العلامة صالح الفوزان - حفظه الله تعالى -:
"تعليق عبارات (ما شاء الله) وغيرها على السيارات لا يجوز"
انظر : شرح المنتقى 24-06-1437هـ
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ይላሉ፦ መኪና ላይ ‹‹ማሻ አላህ›› (ይህን የመሳሰሉትን አዝካሮችን) ብሎ መፃፍ ወይም ማንጠልጠል አይቻልም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
🔷 የኹጥባ ዱዓ ላይ እጅን ማንሳት 🔹
🕰 ፈትዋ ቁጥር : 282
📮 #ጥያቄ↶
⭕️ የጁሙዓ ኹጥባ ላይ በሚደረገው ዱኣ ላይ እጅን #ማንሳት እንዴት ይታያል⁉️
✅ #መልስ↶
☑️ በመሰረቱ በዱዓ ወቅት እጅን በደረት ትክክል ወደ ላይ ከፍ ማድረግ #የተደነገገና ዱዓውም #ተቀባይነት ይኖረው ዘንዳ ሰበብ ከሆኑ ነገራቶች መካከል አንዱ ነው። ለዚህም ነብዪ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፣ "አሏህ የሚያፍርና ቸር ነው ፣ ባሪያው #እጁን ወደ እርሱ ከፍ ሲያደርግ ባዷቸውን እንዳይመልስበት ያፍራል።" አቡ ዳውድ (3556)
☑️ ሆኖም እጅን ማንሳት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ #ያልተደነገገበት ሁኔታ ላይ እጅን ማንሳት የተከለከለና #ቢድዓ ይሆናል። ከነዚህ ከተከለከሉ ሁኔታዎች መካከል በሶላት መጀመሪያ ላይ የሚገኘው #የመክፈቻ ዱዓ ላይ ፣ በሁለት ሱጁዶች #መካከል ፣ በተሸሁድ ዱዓ ላይ እና #በጁሙዓ ኹጥባ ላይ (ለኢማሙም ለመእሙሙም) ናቸው።
☑️ በተለይ የጁሙዓ ኹጥባውን በተመለከተ ነብዩ - ﷺ - በኹጥባቸው ላይ #በጠቋሚ ጣታቸው ከመጠቆም ውጭ እጃቸውን #አንስተዋልም ሆነ አዳማጩም እጁን እንዲያነሳ #አዘዋል የሚል የለም። #ሶሀቦችም ይህን በሚያደርጉ አካላት ላይ አውግዘዋል።
•┈┈•◈◉❒✒❒◉◈•┈┈•
🗂 #ምንጭ↶
📘ፈታዊ አርካኒል ኢስላም ለኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 392
◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈
قال الإمام عبد الله بْنُ الْمُبَارَكِ رحمه الله
رأيت الذنـوب تميت القلوب .. .. وقد يورث الـذل إدمانها
وترك الذنـوب حياة القلوب .. .. وخير لنفسك عصــيانها
وهل أفسد الدين إلا الملوك .. .. وأحـبار سـوء ورهبانها
ሲሕር (ድግምት ) እና አደገኝነቱ
من أتى عرافاً فسأله عن شيء لم تقبل له صلاة أربعين ليلة
“አዋቂነኝ ባይ ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ አንድን ነገር የጠየቀው ሰው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።” ብለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላ ሰሂህ ሐዲሥም እንደተገለፀው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
من أتى كاهناً فصدقه فقد كفر بما أنزل على محمد
“ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የሚለውን ያመነ ሰው በሙሐመድ ላይ በወረደው ነገር ክዷል።”
የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህንኑ ከልክለዋል – እንዲህ በማለት፡-
ليس منا من تطير أو تطير له أو تكهن أو تكهن له أو سحر أو سحر له
“ገድ ያየ ወይም የታየለት፣ የጠነቆለ ወይም የተጠነቆለለት፣ ድግምት የሠራ ወይም የተሠራለት ከኛ አይደለም።” (ጦበራኒ ዘግበውታል።)
ጆይን
👇👇👇
@tewihd
قال الإمام الأوزاعي رحمه الله : « عليك بآثار من سلف وإن رفضك الناس ، وإيّاك وآراء الرجال وإن زخرفوها لك بالقول ؛ فإن الأمر ينجلي - حين ينجلي - وأنت على طريق ...
“አደራህን!የቀደምቶችን ፋና አጥብቀህ ያዝ! ሰዎች ጀርባቸውን ቢሰጡህም! ከሰዎች አስተያየት ተጠንቀቅ!በቃላት ቢያሸበርቁልህም እንኳ፣ አንተ ቀጥ ያለው መንገድ ላይ ከሆንክ ነገሩ በሒደት ይገለጣል።”
👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd
ሸይኹል ኢሰላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብሏል ፦
تُحرس السنّةُ بالحق والصدق
لا تحرس بكذبٍ ولا ظُلم ..!
« ሱናህ በሀቅ እና እውነተኝነት እንጂ በውሸትም በበደልም አይደለም የምትጠበቀው»
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd