tewihd | Unsorted

Telegram-канал tewihd - አስ–ሱናህ 🇵🇸

-

﴿وَلا تَلبِسُوا الحَقَّ بِالباطِلِ وَتَكتُمُوا الحَقَّ وَأَنتُم تَعلَمونَ﴾ البقرة ٤٢ “እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡” አልበቀራ 42

Subscribe to a channel

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ተኩላው እና ግመሉ
~
አንድ ተኩላ ከወንዝ ውሃ የሚጠጣውን ግመል ከወንዙ ዳር ቆሞ እንዲህ ሲል ጠየቀው
« ለመሆኑ የወንዙ ስምጠት ምን ያህል ነው?»

ግመሉም « እስከ ጉልበት ድረስ ያሰምጣል» ሲል መለሰለት።

ይህንን ምላሽ ተኩላው ሰማና ዘሎ ወንዙ ውስጥ ሲገባ የወንዙ ውሃ ሙሉ ሰውነቱን ሸፈነው።
እንደምንም ጭንቅላቱን ከውሃው ለማውጣት ጥረት አደርገና ከብዙ ጥረቶች በኋላ በመጨረሻ ወንዙ ዳር ከነበረው ቋጥኝ ላይ ወጣ

ቋጥኙ ላይ ወጥቶ ከተረጋጋና ጥቂት ትንፋሾችን ከሰበሰበ በኋላ ግመሉ ፊት ላይ ጩህት በተሞላበት ድምፅ «ውሃው እስከ ጉልበት ነው ሚያስጥመው አላልከኝም?!» አለው

ግመሉም « አዎ! ውሃው እስከ እኔ ጉልበት ነው ሚያሰጥመው...» ሲል መለሰለት።

ከታሪኩ ስንማር...

‛ አንድን አካል በሆነ የህይወት ጉዳዮች ላይ ስታማክር እርሱ ሚመልስልህ አይቶ በጠቀመው ተሞክሮ ላይ ነው። ይህ ተሞክሮ ደግሞ በአብዝሃኛው ጊዜ ለሱ ብቻ የሚስማማ ነው። ካንተ ጋር የማይስማማ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የሌላን ሰው ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ በህይወትህ ላይ ተግባራዊ አታድርግ ልትሰጥም ትችላለህና።
👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🔉▫️ ٱللَّهُ لَطِيفٌۢ بِعِبَادِهِۦ
አላህ በባሮቹ ሩህሩህ ነው፡፡  ▫️🔉(ሹራ 19)
ቃሪእ፦ ሙሀመድ አሉሀይዲን

ሼር ሼር ሼር
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

◾️ሁሌም መንገደኛ ነን‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖

ኢብኑል ጀውዝይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

✅ መዘውተሪያችን እስኪረጋገጥና የጉዞዋችን መጨረሻ (ፍፃሜ) እስኪያገኝ ድረስ፦ በስድስት ጉዞዎች ውስጥ ሆነን እንጓዛለን።

↪️ የመጀመርያው ጉዞ
👉ከጭቃ የሆነው የመጀመርያ (የአባታችን ኣደም) አፈጣጠር ላይ የነበረ ጉዞ ነው

↪️ ሁለተኛው ጉዞ
👉(ከአባታችን) ጀርባ ወደ (እናታችን) ማህፀን የነበረው ጉዞ ነው።

↪️ ሶስተኛው ጉዞ
👉ከእናታችን ማህፀን ወደዚህ ምድር (ዱንያ) የተደረገው ጉዞ ነው።

↪️ አራተኛው ጉዞ
👉ከምድር ወደ ቀብር የምናደርገው ጉዞ ነው

↪️ አምስተኛው ጉዞ
👉ከቀብር ወደ ሂሳብ መተሳሰቢያ ቦታ (ወደ መውቂፍ) የሚደረግ ጉዞ ነው

↪️ ስድስተኛው ጉዞ
👉ሂሳብ ከሚደረግበት ቦታ ወደ ዘላለም መኖርያ የሚደረግ ጉዞ ነው።

✅ ይህ የዘልአለም መኖሪያች ወይ ጀነት ወይ ጀሀነም አንዱ ነው።

✅ እስካሁን የጉዞዋችን ግማሽ አጠናቀናል። ነገር ግን ከባባድ ጉዞዎች ከፊት ለፊት ይጠብቁናል።

بحر الدموع (٤٦/١)
.👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ንግግሮችን መናገርና በተግባር እነሡን መከወን እጅጉኑ ይለያያል። ስለ ትዕግስት እናወራ ይሆናል፤ ትዕግስት የሚያስፈልጋቸው ክስተቶች ሲገጥሙን ግን የትዕግስትን ባዶ ስም እንጂ ትዕግስትን አላወቅነውም። ህመም ላይ ያሉ ሰዎችን ስለ ቀዷእ እና ቀደር እውነታ በማብራራት አፅናንተናቸው ይሆናል። በኛ ላይ እውነታው ሲጋረጥብን እና ከእነሱ ያነሰ ህመም ሲገጥመን ግን የመከርንው ሁሉ በተግባር ሌላ መሆኑን እንረዳለን።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

. ╭•════─═•❗•═─════•╮
. የሴቶች መስተካከል የዑማው
.
. ╰•════─═•❗•═─════•╯

🔄 የእህቶቻችን ነገር ከ-ኃሊት ታሪክ ስንነሳ።

መልክተኛው ከመላካቸው በፊት የሴት ልጅ ማንነት ለመግለጽ ብንደክም ብንለፋ የነበረው ክስተት ለመዘርዘር የሚያስችል ልብ የለንም።

በሴት ልጅ ላይ የደረሰው ግፍ ሁሉ [ በጃሒሊያ ዘመን ሴቶች ከእነ ሒወታቸው ይቀበሩ ነበር]ብለን በድፍኑ ማለፍ እንጂ[" ሴት የወንድ ልጅ ባርያ ነበረች በገዛ ንብረትዋ እንኳን የመብት ሽርፍራፊ የማትካፈል የበታችና የተረገጠች ነበረች"]

የቱ ጽፌ የቱ ልተወው ብቻ { አለም በሰው ልጅ በመጥፎ ድርጊት ብሎ ካስተናገዳቸው ድርጊት ውሰጥ  ይቅርና በእንስሳት ታሪክ እንኳን ተሰምቶ በውል  የማይታወቅ ከእነሒወትዋ ትቀበር ነበር።}   
 
وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَت ْبِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ

በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
በምን ወንጀል እንደ ተገደለች

 ከዚህ በላይ ብዕራችን አንደበታችን ተጣጥረው ለመግለጽ ቢሞክሩ እጃችን እርደው አንደበታችን ተንተባትቦ ማቋረጣችን አይቀሬ ነው።

እንዲህ ነበሩ ሴቶች በጃሒሊያ ተረግጣ ተደብድባ ከ ቆሻሻ እንኳን ያነሰች ነበረች ቆሻሽ ጥጋ ጥጉ ይጣላል እስዋ ትቀበር ነበር ከነ ሂወትዋ! አባት ሴት ልጅ ተረግዞ ይሆን እያለ ጭንቅላቱ እስኪፈነዳ ይጨነቅ ነበር! ተወለደልህ ተብሎ ሲነገረው ፊቱ ይከስል ነበር ! እንዲ የረከሱ ነበሩ  ሴቶች በጃሒሊያ!።

የአላህ መልክተኛ አላህ ልኮቸው ጃሒሊያ እንዲወድም ተጋፍጠው የሴት ልጅ ክብር ነጻነትዋ እንዲጠበቅላት አወጁ ቁራዐን ያ የጨለማው ዘመን ተወግዶ የሰው ልጅ ከባርነት ቀንበር ወጥቶ የነጻነት ሜዳ ላይ እራሱ እንዲያስገኝ አደረገ

الر ۚ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ النَّاسَ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِ رَبِّهِمْ إِلَىٰ صِرَاطِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ
 
[አሊፍ ላም ራ] ይህ ቁርአን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወዳንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው፡፡

[ጃሒሊያን ያላወቅ እስልምና ሊረዳ አይችልም]ዑመር ኢብኑ ኸጣብ
ዛሬ ሒጃብን ልበሽ እስልምናሽ እውቂ እየተባለ የዚህ ሁሉ ጥሪ አመርቂ ውጤት ያልተገኘው

 1ኛ ዑመር እንዳለው ጃሒልያ ባለማወቃቸው።

 2ተኛ ዘመናዊነት እየተባለ ከምዕራባዊያን በኮንትሮባንድ የመጡ አጓጉል ዲን የሚያስረሱ የምናውቃቸው ጉዳዬች ናቸው።

👉እስቲ እንመልከት :-
ከጃሒሊያን በቅርብ የነበረችው ጃሒልያን የምታውቅ ምራዕባዊነት የማታውቀው በምናብዋም ያልመጣ አዒሻ እንዴት ነበረች ለእስላም ምን አበረከተች ?

እድሜዋ መልክተኛው ወደ አኼራ ሲሄዱ 18 ነበር።

የአንቺ እድሜ ስንት ነው ?!

እውቀትዋ ምጥቁ ከሚባሉ ሴት ወደር ታጥቶላት በጥቅሉ ከወንድም ከሴትም በሚል ውድድር ውስጥ የደረጃዎች ባለቤት ሆናለች። አንቺስ እድሜሽ እና እውቀትሽ የት እና የት ነው ?! እ?

አዒሻ በ18 አመትዋ የእውቀትዋ ምጥቀት በሌሎች በአዋቂዎች ተመስክሮላታል [ የአይሻ እወቅት ተሰብስቦ የነቢያችን ሚስቶች እንዲሁም በዱንያ ያሉ ሴቶች ሁሉ እውቀት ጋር ቢወዳደር የአዒሻ ይበልጥ ነበር ] ኢማም ዙህሪይ ብለዋል።

ምንኛ ታላቅ ሴት ነበረች እውቀት ያተለቃት የልጅ አዋቂዋ አይሻ
 {እውቀት መፈለግ በሙስሊም ወንድ እና ሴት ላይ ግዴታ ነው} ይህንን ተንተርሳ ከወንድ ጎን ቆማ እውቀት ትሸምት ነበር ምንም ሳያግዳት አብረቅራቂው ዱንያ ሳይሸነግላት እራስዋ በእውቀት ተወስወጭፋ ለአኼራዋ ብቻ ሳይሆን ዱንያ ላይ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ሰርታ አለፈች።

ሁሌ ምሳሌ በሴቶች ስናቀርብ አይሻ ሳይጠቀሱ ከማይታለፉ ሆናለች።

👉አንቺ ምን አበረከትሽ ?????

የአንቺው አርያነት በምን ላይ ነው? በዶድራንት ?በፌስቡክ ወሬ ? 50 ጊዜ እየተኲኳልሽ መስታወስ አጠገብ መጣድ? የብፌ እቃዎች ስም ዝርዝር መሓፈዝ ? ብፌ ውስጥ ያልገቡ ዘመናዊ ብጭርቆ ጉዳይ አሳሰበሽ?  [ የሀይድ እና የኒፋስ አህካም እንኳን የማስቀራት ችሎታ የሌለሽ !!] ኧረ የት ነሽ ?!

እራስሽ ሸውደሽ ሊሆን ይችላል ጅልባብ ለብሻለሁ ኒቃብ ለብሼያለሁ ! እያልሽ አትፎግሪ ሀያዐ ተራቁተሽ ኒቃብ ምን ሊሰራ ?! ጥብቅነትሽ  ሳትጠብቂ ዲነኛ ለመምሰል መሞከር ምን የሚሉት የዋህነት ነው ?!

ይልቅ የምናይብሽ የትም የማያደርሱ የማይጠቅሙ የሚጎዱሽ ድርጊት እርግፍ አርገሽ ተያቸው "የፈለገ ብትለፊለት በለፋሽ ቁጥር መጥፎ ባህሪሽ ቢያጎሉ እንጂ ለምንም የማይበጁሽ ጉዳዬች ተዪ ይቅርብሽ በFacebook ከምታተራምሺ የሰለፊያ ሴቶች ተመሳሌት ታሪክ በማጥናት ተጠመጂ ይብቃሽ።

የድሮ ዑለሞች በእነሱ ዘመን ሴቶች እውቀታቸው ላይ ብቻ ያተኩሩ ስለነበር "በእውነተኝነት የተመሰከረላት ሴት እንጂ በውሸት የምናውቃት ሴት የለችም"እስከማለት ደርሰዋል።

ሰለፎቹ እንዲ ነበሩ  ምን ያደርጋል በዚህ ዘመን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነብን 1140 አመት በሙሉ ለእራስዋ ተርፋ ለብዙዎች እውቀት ያካፈለችው አይሻና መሰሎችዋ ስናስታውስ የዛሬዎቹ ከምዕራባዊን ተመሳጥረው ዑማው ለመግደል በኢስላም ላይ ያሴሩ ይመስላሉ!ሁለመናቸው መምሰል! ሴቶች የነገ እናቶች ናቸው።

እናቶች የልጆች አስተማሪ ናቸው። ዛሬ ያልተማረችው ያልተላበሰችው ሀያዐ ነገ ለልጆችዋ ሳሎንዋ  ሆና የማስተማር ችሎታ ከየት አምጥታ ልታስተምር ነው?! እየታየ ያለው ተጨባጭስ የልጆቻቸው እንኳን ማስተማር የሚችሉበት እውቀት የሌላቸው ስናይ  እናዝናለን!!!

  ትላንትና እያስታወስን የልብ ልብ ይሰማንና የዛሬዋ ሴት ሁኔታ ስናይ ልብ ይነሳናል !!

የድሮ ጀግና ሰለፊያ ሴቶች አይነት ትውልድ እህቶች ፈልገን ማጣታችን እምባ ይተናነቀናል።
 

እህቶቻችን! :-
አቋማችሁ  በኢማንና በኢልም ምን አክል ጸንቶዋል ?

በመልክተኛው ብሩህ ጎዳና ላይ ላይ ከሚጓዙ ከማይወላወሉት የሆናችሁ ስንቶቻችሁ ናችሁ ?

ብናውቃችሁም! አላህ የሃዐያ ካባ ያልብሳችሁ እውነተኛ አማኝ ሴት ያድርጋችሁ።

አሏሁመ አሚን
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFTIVIfw_hxjlqArBA

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

#ልቤ ሆይ! አላህ ይዘንልሽ እንኳን አንቺን እራሱንም መጥቀም በማይችል ፍጡር ፍቅር ትዋልያለሽ፣ አላህ ይዘንልሽና እወቂ አንቺ የአላህ መሆንሽን አምነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሽ።

"ከአላህ ጋር ሰላም ነሽ፣ ከአላህ ጋር ትደሰቻለሽ እፎይታ ሰላም በፍቅር ውስጥ ትኖሪያለሽ።

يَهْدِي بِهِ اللَّهُ مَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَهُ سُبُلَ السَّلَامِ وَيُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِهِ وَيَهْدِيهِمْ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል፡፡ በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፡፡ ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል፡፡

#ልቤ ሆይ! ለጌታሽ ፍላጎት ለውዴታው ኑሪ አላህም ችሮታው ሰፊ እዝነቱ ብዙው ነውና።

وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْرِي نَفْسَهُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ رَءُوفٌ بِالْعِبَادِ

ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ነፍሱን የሚሸጥ ሰው አልለ፡፡ አላህም ለባሮቹ በጣም ርኅሩህ ነው፡፡


"ከአላህ ጋር ፍርሃት የለም፣ ከአላህ ጋር ፍፁም ሀዘን ትከዛ የለም ፣ ወደ አላህ ተቃረቢ እርጋታን ታገኛለሽ።


الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

"ልቡን ለአላህ የሰጠና ወደ እርሱም የተጠጋ ፍርሃት ፍፁም የለበትም፦


وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ መጠጊያም በአላህ በቃ፡፡


فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ አንተ ግልጽ በኾነው እውነት ላይ ነህና፡፡


ልቤ ሆይ! መጠጊያሽን ምረጭና ጥግሽን ያዥ!
👇👇👇👇👇
@eross_eross
@Eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

بسم الله الرحمن الرحيم

ቢስሚላሂ ብዬ       ልጀምር በስሙ
እንጠቀም ዘንዳ     ፀጥ ብላችሁ ስሙ

መስማት ብቻ ሳይኾን  ከማዳመጥ ጋራ
የሰማነው አውቀን    በደንብ እንድንሰራ

አዘገየሁ እንጂ    አብሽር አልረሳሁም
አሁን ልበላችሁ     አሰላሙ ዐለይኩም



ምልክቶች በዙ       ዘመኑ ያስፈራል
ዱንያ ጨላለመች    ያበቃች ይመስላል

ደጋጎች አለቁ      አላህ ወሰዳቸው
የቀሩትም ጭምር    በመሄድ ላይ ናቸው

ዑለሞች ቀን በቀን    ሁሉም በየተራ
ተጉዘው አለቁ      ሄዱ ወደ አኼራ

ቂያማ ሲቃረብ    ዑለሞች ያልቃሉ
ሰዎች በጅህልና    ባህር ይዋኛሉ

ይህ ነው ያለንበት    ተጨባጭ ሁኔታ
ዑለሞች ሲሄዱ      ጅህልና በረታ

መሪውም ተመሪው   ሁሉንም ታውሮ
አለማችን ሆነ      የጨለማ ኑሮ

የብስና ባህሩ     በፊትና ተሞልቷል
ምልክቶች በዙ    ዘመኑ ያስፈራል

የፀሀይ ጨረቃ    ግርዶች መደጋገም
የሌሊቱን አልፎ    የቀኑ መጨለም

የበሽታ ብዛት    የወረርሽኝ ክፋት
የኑሮ መወደድ   የዝናቡ መጥፋት

የመሬት መንቀጥቀጥ   ወይም መንሸራተት
አንዳንዴ መደርመስ     ሳይታሰብ ድንገት

ባህር ሞልቶ ፈሶ     ጎርፍ ተጥለቀለቀ
በዚህ ሰበብ ብቻ    ስንት ሰው አለቀ

የእርስ በርስ ውጊያ   ዋጋ ቢስ ጦርነት
ስንቱን ተጭፍጭፎ   ስንቱን አለቀበት

ድንገተኛ አደጋ        በክረምት በበጋ
መብዛታቸውን ሲያይ   ልቤ ፈራ ሰጋ

ይህን ሁሉ ክስተት   ሲታይ በምድር ላይ
ምልክቶች በዙ   ዘመኑ ያስፈራል

የሴቶች መራቆት    እርቃናቸው መውጣት
የወንዶች መጀዘብ     ቅናታቸው መጥፋት

ኸምር እንደ ውሃ     ሲሸጥ በየ ሱቁ
እፍረት አይሰማቸው   አይሸማቀቁ

ዝሙት እንደ ሀላል  ሰዎች መሃል ሲታይ
ምልክቱ በዝቷል    ዘመኑ ያስፈራል

ውሸታሞች ታማኝ    ታማኞች አታላይ
እውነት አጎብድዳ     ውሸት ሲሆን ከላይ

ጃሂል ቂላቂሎች         ተቀምጠው ስልጣን ላይ
ፈላጭ ቆራጭ ሆነው   በሁሉንም ጉዳይ

የልጆች እምቢታ     ለወላጆቻቸው
የወላጅ ዝምታ      ሲያምፅ ልጃቸው

በነብዩ ትንቢት     ሁሉንም ተወስቷል
ምልክቶች በዙ       ዘመኑ ያስፈራል

ኮከቦች ሳይረግፉ  ሰማይ ሳትፈራርስ
ምድር ተቀይራ    ዳግም ሳትታደስ

ከከሳሪ ኾነን        ነገ ከመፀፀት
እንሽሽ ወደ አላህ    እናብዛ ተውበት

ሰላትና ሰላም    ይውረድ በሙሐመድ
በተከተላቸው    ሱናቸው በመውደድ
             
👇👇👇       👇👇👇
  @tewihd @tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🎁ከስለፎቻችን ጠቃሚ ንግግሮች

➡️ በአንድ ወቅት አንድ ሰው ስለዱንያና ስለ አኺራ ታላቁ ታቢዒይ ሀሰነል በስሪ ዘንድ በመምጣት ጠየቃቸው።እንዲህ ሲሉም መለሱለት፦
"ስለ ዱንያና ስለ አኺራ ጠይቀኸኛል።የዱንያና የአኺራ ምሳሌ ልክ እንደ ምሥራቅ እና ምዕራብ ነው።ወደ አንደኛው በቀረብክ ቁጥር ከሌላኛው ትርቃለህ። ... "
👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሁላችንም በዚች ዱንያ ላይ እንግዶች ነን፤
እንግዳ ደግሞ ከመሄድ ቅሮት የለውም።
መልካም የኾነን ነገር አስቀርተን እንሂድ!!
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሁላችንም በዚች ዱንያ ላይ እንግዶች ነን፤
እንግዳ ደግሞ ከመሄድ ቅሮት የለውም።
መልካም የኾነን ነገር አስቀርተን እንሂድ!!
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

☝️ከአድማጮች ጋብዝልኝ ተብዬ ነው።

ጀዛኩሙላህ ኸይር

ሼር ሼር ሼር
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ወዳጅህ ማለት ማን ነው
‏️قال الحافظ النووي - رحِمَهُ اللّٰه -:

وصديق الإنسان ومُحبّهُ هو مَن سعى
في عِمارة آخرته وإن أدى ذلك إلى
نقص في دُنياهُ، وعدوهُ مَن يسعى
في ذهاب أو نقص آخرته وإن حصل
بِسببِ ذلك صورة نفع في دُنياه.

📝شرح صحيح مسلم
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ተሳተፉ  إن شاء الله ትጠቀማላችሁ።

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

✍#በቀን #ሶስት #ፍሬ #ቴምር #በመመገብ #የሚያገኙት #6 #ጥቅሞች
1 #ብርታት #ለማግኘት

🔵 ሰውነት ሲዳከም እና ስራንመከናወን ሲሳነው ይህን ፍሬ በመመገብ ብርታትን
መላበስ ይቻላል።

2 #ለተስተካከለ #ስርአት #ምግብ

🔵 በውስጡ የሚሟሙ አሰሮችን የያዘው ይህ ፍሬ አላስፈላጊ የሆድ መነፋትን በማስወገድ የተስተካከለ የስርአት ምግብ መንሸራሸርን ይፈጥራል። ከዚህ ባለፈም ለሰውነት ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን በማዘጋጀት ሊከሰት የሚችልን የተቅማጥ እና ተያያዥ ችግሮችን መከላከል ያስችላል።

3 #ለበሽታ #የመከላከል #አቅምና #ለአጥንት #ጥንካሬ

🔵 ካንሰርን ጨምሮ በርካታ በሽታዎቸን መዋጋት የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው። ይህ ደግሞ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን በእጅጉ ለማሳደግ ይረዳል። ከዚህ ባለፈም የአጥንት መልፈስፈስን በማስወገድ ጤናማ እና ጠንካራ አጥንት እንዲኖርዎት ያግዛል፤ ይህ ደግሞ በተለይም እድሜ ሲገፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

4 #የብረት #መጠንን #ለመመጠን

🔵 የደም ማነስ በሽታ የብዙ ሰዎች ችግርና አስከፊም ነው፤ ለዚህ ደግሞ በብረት የበለጸገው ይህ ፍሬ እጅጉን ይመረጣል።በሰውነት ውስጥ ያለውን የብረት መጠን ማመጣጠንና በሽታውን ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረትም ያግዛል።

5 #ለጤናማ #ልብ

🔵 በውስጡ ያለው ከፍተኛ የፖታሺየም መጠን ድንገተኛ የልብ ስርአት መዛባትን በመከላከል ጤናማ የልብ ስርአት እንዲኖር ያግዛል። ከዚህ ባለፈም ለልብ ህመም መንስኤ እንደሆነ የሚነገረውን የኮሌስትሮል መብዛትን መከላከል መቻሉም ትልቁ ጠቀሜታው ነው።ለዚህ እንዲረዳ ደግሞ ይህን ፍሬ ማታ በንጹህ ውሃ መዘፍዘፍ እና ጠዋታ ሲነቁ በባዶ ሆድ መመገብ ነው፤ ይህ ለጤናማ ልብ እጅጉን ይረዳልና ይጠቀሙበት።

6 #አለርጅን #ለመከላከል
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

📌♻️ልቦና በህይወትና በሞት ደረጃ ከሆነ ልቦችን በሶስት ከፍለን መመልከት እንችላለን።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
1📌♻️.ሰላማዊ የሆነች ቀልብ፣ በማንኛውም መልኩ ሰላማዊ የሆነችና ሽርክ የሌለባት ቀልብ ነች።ይልቁንም በመውደድ ፣በፍላጎት፣በመመካት፣ተፀፅታ በመመለስ፣በመዋደቅ፣በመፍራትና በተስፋ አሏህን ጥርት አድርጋ ታመልካለች።

    👉 ከወደደች ለአሏህ ብላ ትወዳለች፣ከጠላች ደግሞ ለአሏህ ብላ ትጠላለች፣ከሰጠች ለአሏህ ብላ ትሰጣለች ፣ከከለከለች ደግሞ ለአሏህ ብላ ትከለክላለች።ለማንኛውም ነገሯ ዳኛዋ በረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የወረደው ህግ ነው።በአቂዳም በንግግርም በተግባርም ከአሏህ ህግ ውጭ ሌላን አታስቀድምም።

2.📌♻️የሞተች ቀልብ፣ምንም ህይወት የሌላት ነች፣ጌታዋን አታውቅም፣አትገዛም ትዕዛዙን አታከብርም ፣አላህ የሚወደውን አትሰራም፣ ይልቁንም የአላህ ቁጣ እና ጥላቻ ቢኖርበት እንኳ ከስሜቷ ጋር ነው የምትንቀሳቀሰው፣ ፍርሀቷም፣ ተስፋዋም፣ ውዴታዋም፣ ጥላቻዋም፣ማላቋም፣ ማዋረዷም፣ ከአሏህ ውጭ ነው።ስትወድም ስትጠላም ስትሰጥም ስትከለክልም ለስሜቷ ነው። ስሜቷና የዱንያ ፍላጎቷ ኢማሟ(መሪዋ)፣ ማሀይምነት  ሹፏሯ፣ ዝንጋቴ መርከቧ ነው።

3📌♻️.ህይወትና በሽታ የተቀላቀለባት ቀልብ፣ ይህች ቀልብ ሁለት ገፅታዎች ያሏት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ አንድኛው ገፅታ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው ገፅታ ያሸንፋታል።እርሷ ከሁለቱ ወደ አሸነፈው ትሆናለች።በውሥጧ የአላህ ውዴታ፣ኢማን፣ ኢኽላስ እና ተወኩል አላት።ይህ የህይወት ገፅታዋ ነው።ስሜት ፣ ምቀኝነት ፣ ኩራት ፣በራስ መደነቅ እና የበላይነትን መፈለግ የጥፋትና የክስረት ገፅታዋ ነው።

👉@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ወንድሜ!
ትልትል(የተቦጫጨቀ) ሱሪ ፋሽን ነው ብለህ ለብሰህ፤ሶላት ለመስገድ ተሸማቀህ ሸሚዝህንና ጃኬትህን አውልቀህ ጉልበትህ ላይ ከማሰር፤ ትግል የሌለው እና ማያስነውረውን ኢስላማዊ አለባበስ ልበስ:: ኢስላማዊ አለባበሶች አያሳፍሩም አትፈር! ሊያሳፍርህ የሚገባው ጌታህ ያዘዘህን አምልኮ ከመስራት የሚከለክልህን ወይም እርሱ ዘንድ ለመቆም እንቅፋት የሚሆንብህን ነገር መተግበርህ ነው::
👇👇ሼር
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ በትንሳኤ እለት የማንኛውም ባሪያ እግሮች ከአራት ነገሮች ሳይጠየቅ (ከሒሳብ ቦታ) አይንቀሳቀሱም።

1ኛ ስለእድሜው በምን እንዳሳለፈው፣

2ኛ ስለወጣትነቱ በምን እንዳጠፋው፣

3ኛ ስለገንዘቡ ከየት እንዳመጣው እና በምን እንዳጠፋው፣

4ኛ ስለእውቀቱም ምን እንደሰራበት። ]

📚ጦበራኒ ዘግበውታል።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ብስራት ለሴት እህቶቻችን👇
☘ قال رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
የአላህ መልእክተኛﷺ አሉ👇
"إذا صلت المرأة خمسها
ሴት ልጅ 5 ወቅት ሶላቶችን ከሰገደች

وصامت شهرها
(የረመዷን) ወሯንም ከፆመች
و حصنت فرجها
ብልቷንም (ከሐራም) ከጠበቀች
و أطاعت زوجها
ባሏንም ከታዘዘች
قيل لها : ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت
."(የውሙል ቂያማ)በፈለግሽው በየትኛውም የጀነት በሮች ግቢ ትባላለች"

صححه الألباني
صحيح الجامع ٦٦٠
ሐዲሱን አልባኒ ሶሒሑል ጃሚዕ ላይ ሶሒሕ አድርገውታል።

نسأل الله التوفيق في العمل



@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የኢብኑ ከሢርን አልቢዳያ ወንኒሃያ እያነበብኩ ሳለሁ በጣም የሚገርም ታሪክ አጋጠመኝና ላካፍላችሁ ወደድኩ።
ያኔ በደጉ ዘመን ነው። ደጋጎች የበዙበት ዘመን ቢያከትምም የነዚያን አበው ፋና የተከተሉ ድንቃድንቅ ፍጡሮች የነበሩበት ዘመን።
አሕመድ ብኑ መህዲይ ብኒ ሩስቱም (317 ሂ.) ይባላሉ። ታላቅ ዓቢድና ዛሂድ ነበሩ። በዒልም ፍለጋ ላይ 300 ሺህ ዲርሃም ያወጡ ቆራጥ ናቸው።
በአንድ ምሽት የሆነች ሴት መጥታ እንዲህ አለቻቸው:
"ፈተና ደርሶብኛል። በዝሙት ላይ ተገድጃለሁ። (ተደፍሬያለሁ።) በዚህም ሳቢያ አርግዣለሁ። ታዲያ አንተን እንደ ሽፋን ተጠቅሜያለሁ። አንተ ባሌ እንደሆንክ፣ ያረገዝኩትም ካንተ እንደሆነ  አስወርቻለሁ። እባክህን ሸፍነኝ፣ አላህ ይሸፍንህና። እባክህን አታጋልጠኝ!!"

አሕመድ ጉዳዩን ከማጋለጥ ዝም አሉ። ጊዜው ደረሰና ሴትዮዋ ወንድ ልጅ ወለደች። የአካባቢው ሰዎችና የመስጂዳቸው ኢማም እየመጡ የእንኳን ደስ ያለህ መልእክት ለአሕመድ አደረሷቸው። እሳቸውም ልክ ልጅ እንደተወለደለት ሰው መደሰታቸውን አንፀባረቁ። በሁለት ዲናር ጣፋጭ ነገር አስገዝተው ላኩላት። በየወሩ ቀለብ የሚቆርጡ አስመስለው ሁለት ሁለት ዲናር በኢማሙ በኩል ይልኩላታል። "ሰላምታ አድርስልኝ። እሄው እኔና እሷን የሆነ ጉዳይ ለያይቶን ነው" ይሉታል።
በዚህ ሁኔታ ሁለት አመት አለፈ። አሁን ግን አንድ ነገር ተከሰተ። ልጁ ሞተ። ሰዎች እየመጡ ተእዚያ ደረሷቸው። ልክ ሰው ልጁን ሲያጣ እንደሚሰማው ሐዘንና ጭንቀት ተሰምቷቸው ለሰዎች ታዩ። ከዚያስ ምን ተከሰተ?

ሴትዮዋ ሲላክላት የነበረውን ዲናር ሰብስባ ይዛ መጥታ "አላህ ይሸፍንህ። በመልካምም ይመንዳህ። ስትልከው የነበረው ገንዘብ ይሄውና" አለቻቸው።
"ምን ነካሽ? እኔ ስልክ የነበረው ልጁን በማሰብ ነበር። ውሰጅና ለፈለግሺው አውይው" አሏት።
[አልቢዳያ ወንኒሃያ: 11/163]


@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

በቁርዓን የተቀናበረው ግጥም ቀረበላችሁ እያዝናና የሚያስተምር ነው።
👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🌼 ቫለንታይንስ ደይ
(የፍቅረኛሞች) ቀንን ማክበር
በሸሪዓ እይታ!

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻧﺤﻤﺪﻩ ﻭﻧﺴﺘﻌﻴﻨﻪ ﻭﻧﺴﺘﻐﻔﺮﻩ، ﻭ ﻧﻌﻮﺫ ﺑﺎﻟﻠﻪ ﻣﻦ ﺷﺮﻭﺭ ﺃﻧﻔﺴﻨﺎ ﻭﻣﻦ ﺳﻴﺌﺎﺕ ﺃﻋﻤﺎﻟﻨﺎ، ﻣﻦ ﻳﻬﺪﻩ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻼ ﻣﻀﻞ ﻟﻪ ﻭ ﺃﺷﻬﺪ ﺃﻥ ﻻ ﺍﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻻ ﺷﺮﻳﻚ ﻟﻪ ﻭﺃﺷﻬﺪ ﺃﻥ ﻣﺤﻤﺪ ﻋﺒﺪﻩ ﻭﺭﺳﻮﻟﻪ .

ብዙዎቻችችን እንደምናውቀው (በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር 2ኛው ወር) February "የፍቅር ወር" በመባል መከበር ከጀመረ ረጅም ዘመናትን አስቆጥሯል:: "የቅዱስ ቫለንታይን" ቀን በመባልም ይታወቃል::

ዛሬ ላይም የምናየው የበዓሉ ስርአት የጥንት ሮማኖችን እና የክርስትያኖችን ባህል ቅሪት ይዞ እናገኛለን::

ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር ደግሞ ለሙስሊሞች ይህንን በዓል ማክበር ክልክል ይሆናል።

1 በመጀመሪያ ይህ በዓል በሸሪዓ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለው የፈጠራ ተግባር ነው:: በሸሪዓ መሰረት የሌለውን ተግባር መፈጸም ደግሞ በሀይማኖታችን የተወገዘ ክልክል ነው:: በመሆኑም ይህ በዓል እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ ዓንሀ) ካስተላለፈችው ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ተከታዩን ተናግረዋል፦

‹‹በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)››

[ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።]

ማለትም ውድቅ ተግባር በመሆኑ ወደ ሰሪው አካል ተመላሽ ይሆናል።

2 ይህ በዓል መሰረቱ ሙስሊም ካልሆኑ አካላት ነው። ስለዚህም በዚህ ተግባር መሳተፍ ለእነርሱ እውቅና መስጠት ስራቸውን አድናቂ መሆን እንዲሁም በሚያደርጉት ተግባርም ላይ መተባበር እና ከነርሱ ጋር መመሳሰል ነው። ይህን ተግባር መፈጸም ደግሞ የመልዕክተኛው ﷺ ትዕዛዝ ለመዳፈርና ወደዛቱበት ቀይ መስመር ውስጥ ለመግባት ይዳረጋል። ከከሃዲያን ጋር መመሳሰልን እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፦

‹‹ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡››

[አቡ ዳውድ ዘግበውታል]

3 በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ሸሪዓ የከለከላቸው ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናሉ ከብዙ በጥቂቱ ፓርቲዎች ይዘጋጃሉ ፣ ሙዚቃዎች ፣ የተለያዩ የብልግና ተግባራት ፣ ስርአት አጥነት እንዲሁም ልቅ የሆነ የወንዶችና የሴቶች መቀላቀል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

እነዚህ ተግባራት ደግሞ ሸሪዓ አምርሮ የሚቃወማቸው መጥፎ ተግባራት ናቸው። በመሆኑም ስለ ራሱ የሚጨነቅ ማንኛውም ሰው ከነዚህ ስርአት አጥነት ከሚስተዋልባቸው ዋልጌነት ከተንሰራፋባቸው መጥፎ ተግባራት ራሱን ሊቆጥብ ይገባል።

4 ይህ ተግባር የሰዎችን አዕምሮና ልብ በውሸት ነገሮች ቢዚ እንዲሆን የሚያደርግ እንዲሁም ከነዛ ምርጥ እና መልካም ጻድቅ የነበሩ አርአያ ትውልዶችን ፋናን የሚጻረር በመሆኑ ዛሬም ላይ ቢሆን ከዚህ በዓል ጋር ተያያዢነት ያላቸውን ልማዳዊ ተግባር መፈጸም ክልክል ይሆናል::

ማለትም ምግቦች፣ መጠጦች ፣ ልብሶች እንዲሁም የስጦታ ልውውጦችን እና መሰል ተገባራትን ያጠቃልላል።

ሙስሊሞች ሆይ!

በሀይማኖታችን ልንኮራ ይገባል። ደካማዎችና የጮሃን ሁሉ ተከታይ መሆን የለብንም።

ማሳሰቢያ!

በዚህ በዓልም ይሁን በሌሎች ክልክል በሆኑ በዓላት ላይ በማንኛውም መንገድ እነርሱን መተባበር ለሙስሊሞች የተከለከለ ነው። ምግብና መጠጥ የስጦታ እቃዎች በመግዛት ፣ በመሸጥ ፣ በማዘጋጀት ፣ በማከፋፈል ፣ በማስተዋወቅ እንዲሁም በሌሎች ማንኛውም መንገዶች መርዳት ክልክል ነው።

ምክንያቱም እንዚህ ሁሉ በመጥፎ ተግባራት አንዱ ለሌላው ደጋፊ እንደሆኑ ይቆጠራሉና ነው። የአላህና የመልዕክተኛውን ህግ ለመጣስና ለመተላለፍ ተባባሪ መሆን አይገባ አላህ እንዲህ ብሏል፦

ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ :
‏«ﻭَﺗَﻌَﺎﻭَﻧُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺒِﺮِّ ﻭَﺍﻟﺘَّﻘْﻮَﻯ ﻭَﻻ ﺗَﻌَﺎﻭَﻧُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻹﺛﻢ ﻭَﺍﻟْﻌُﺪْﻭَﺍﻥِ ﻭَﺍﺗَّﻘُﻮﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺷَﺪِﻳﺪُ ﺍﻟْﻌِﻘَﺎﺏِ ‏»
ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ ﻣﻦ ﺍﻵﻳﺔ 2

«በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡»

[አል ማዒዳ :2]

በመሆኑ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን ከዚህና መሰል በሸሪዓ መሰረት ከሌላቸው ተግባራት በመቆጠብ የራሳችንንም ክብር እንዲሁም በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ያለንን ብቸኛ አንጡራ ሀብታችን የሆነውን ዲናችንን ከብክለት ልንጠብቅ ይገባል።

የመዕልክተኛውን ﷺ ሱናህ አጥብቀን በመከተል የከሃዲያንን መንገድ ልንርቅ ይገባናል፡፡ ሙስሊሞችን በጠቅላላ ከውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ከሆኑ መጥፎ ተግባራት እንዲጠብቀንና በእምታችን ላይ ጽናት እና ብርታት እንዲሰጠን አላህን እለምነዋለሁ።

ማስታወሻ!

ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት የቫለንታይንስ (የፍቅረኛሞች) ቀን ማክበርን አስመልክቶ የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ስለዚህ በዓል ተጠይቀው የሰጡትን ፈትዋዎች መሰረት አድርጌ ሲሆን ። የመልእክት መደጋገም እንዳይኖርና ለንባብ አሰልቺ እንዳይሆን ፍሬ ነጥቦችን አሳጥሬ ለማውጣት ሞክርያለሁ።

ባለማወቅም ይሁን በመዘንጋት የተሳሳቱ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን ማረሚያና መገሰጫ እንዲሆን ጌታዬን በመልካም ስሞቹና በሙሉ ባህሪዎቹ እማጸነዋለሁ።

ﻭﺃﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﺃﻥ ﻳُﻮﻓﻘﻨﻲ ﻭﺟَﻤِﻴﻊَ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦَ ﻟِﻤﺎ ﻳﺤﺒﻪ ﻭﻳﺮﺿﻰ .

ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺃﻋﻠﻢ ﻭﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋﻠﻰ ﻧﺒﻴﻨﺎ
ﻣﺤﻤﺪ !
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🌹መልካም ቁርስ☕️🍞🌹

☕️ዛሬ አዲስ ቀን ነው አላህ በድጋሚ የመኖር እድል ሰጠን ። ለተሰጠን ህይወት አምላካችንን እያመሰገንን ላስቀየሙን ለበደሉን ሰዎች ከልባችን ይቅርታ እናድርግ ምክንያቱም ይቺ ዛሬ የተሰጠችን ትልቅ ህይወት ደግመን ላናገኛት እንችላለን ሁሉንም በይቅርታ እንለፍ ህይወት አጭር ናትና ለቂም ቦታ አንስጥ ውስጣችን ሰላምን ያገኛል ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀምበት። አላህን ከማስቆጣትም እንቆጠብ!!√√

አቦ መልካም ቀን ለሁላችሁም ተመኘው
✔️®ahmi

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ከሸይኽ አልፈውዛን ጋር ፈገግ ይበሉ!

አንዱ ጥያቄ ጠያቂ እንዲህ ስል ጠይቋል ፈዲለቱ ሸይኽ ፦

"ዒሳ (አለይሂ ሰላም) ከአርባ አመቱ በፊት ነብይ ሆኗል የሚል ነገር በሐዲስ የተገለፀ ነገር አለን?"

=> ሸይኽ ፈውዛን፦ "አላሁ አዕለም" በማለት መለሱ ።

ጠያቂው ቀጠለ "በመጨረሻ ዘመን ወደ ምድር እንደሚወርድ ተነግሯል፣ እናም ሚስት አግብቶ ይወልዳልን?

=> ሸይኽ ፈውዛን፦ "ጊዜው ላይ ስንደርስ አይተን እንነግራችኋለን" አሉ ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦

"አንዱ ከታቢዒዮች አንዱን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦
"ኢብሊስ ሚስት እና ልጆች አሉትን?"
ታቢዕዩም፦
" አይ! ይህን ሰርግ እነኳ አልተካፈልኩም"
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

📗الكتاب: الأذكار
✏الكاتب: الإمام #النووي
يقول العلماء عن هذا الكتاب
بع الدار واشتر الأذكار
لما فيه حيث جمع الإمام كل الأذكار فيه وهو أفضل الكتب في باب الأذكار

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሰው ስትበድል ደፋር
ይቅርታ ለመጠየቅ ሰነፍ አትሁን

ሰውዬውን በድፍረት እንደ በደልከው ሁሉ

በድፍረት ይቅርታ ጠይቀው

ካልሆነ ነጌ ተ
ዋርደህ ሀቁን ትመልሳለህ
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሞትን መመኘት

ከጃቢር በተወራው ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" ሞትን አትመኙ፤ ከሞት በኋላ ያለው ክስተት እኮ በጣም ብርቱ ነው። ከደስታዎች(እድለኝነት) ውስጥ የአንድ ባሪያ እድሜ ረዝሞ አሏህ ወደ እርሱ መመለስን ሲገጥመው ነው። [አህመድ]

ሞትን መመኘት በብዙ ሁኔታዎች ሚከሰት ሲሆን ከነዚህም፦

- አንድ ባሪያን ዱንያዊ ችግሮች ሲገጥሙት

በዚህ ሁኔታ ላይ ሞትን መመኘት ይከለከላል።
ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦ " አንዳችሁ በደረሰበት መከራ(ችግር) ምክንያት ሞትን እንዳይመኝ። (ሞትን) ማሰቡ ቅሮት ከሌለው እንኳ እንዲህ ይበል ጌታዬ ሆይ! በህይወት መኖሬ ለእኔ መልካም ከሆነ በህይወት አኑረኝ፤ መሞት ለእኔ መልካም ከሆነ አሙተኝ። [ቡኻሪ እና ሙስሊም]
አንድ ሰው በሚደርስበት መከራ ሞትን የሚመኘው ይህ ያጋጠመውን ችግር በሞት መገላገል ፈልጎ ነው። እዚህ ከገጠመው መከራ የከፋ ፈተና ከሞት በኋላ ያጋጥመው እንደሆነ ግን አያውቅም።ችግሮችን ፈርቶ ምን አልባትም አሳማሚውን እሳት እየተመኘ ይሆናልና በዚህ ምክንያት በሚደርሱ ችግሮች ሞትን መመኘት የተከለከለ ይሆናል ።

- በዲኑ(ሃይማኖቱ) ላይ እሚደርሰውን ፈተና ፈርቶ ሞትን መመኘት

የዚህን ጊዜ ሞትን መመኘት ይቻላል።ሶሃቦች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የኢስላም መሪዎች ዲናቸው ላይ ፈተና እንዳይደርስባቸው በመፍራት ሞትን ተመኝተዋል። ዱዓም አድርገዋል።
" በህዝቦች ላይ ፈተናን መጣል የፈለግክ እነደሆን ተፈታኞች ከመሆን ጠብቀህ ወዳንተው ውሰደን" [ቲርሚዚይ]

- ሸሂድ የመሆን አጋጣሚዎች ሲከሰቱ

የሸሂድነትን እድል ለመጎናፀፍ ሞትን መመኘት እንዲሁ ይቻላል። ሶሃቦች ጂሃድ ሲከሰት በጂሃድ ላይ ተሳትፈው ሸሂድ ለመሆን መጠያቃቸውን እሚገልፁ በርካታ መረጃዎች አሉ።

- በስራው የሚተማመን አካል አሏህን ለመገናኘት በሚኖረው ጉጉት የሚያሳድረው የሞት ምኞት

ይህንንም ተግባር በርካታ ቀደምቶች አድርገውታል(ጌታቸውን መገናኘት ፈልገው ሞትን ተመኝተዋል)። አቡ ደርዳእ እንዲህ ይላል፦
" ወደ ጌታዬ ካለኝ ጉጉት ሞትን እመኛለሁ።"
ይህ የሚቻል መሆኑን የአሏህ ቃል ያመላክታል፦
«የመጨረሻይቱ አገር (ገነት) አላህ ዘንድ ከሰው ሁሉ ሌላ የተለየች ስትኾን ለእናንተ ብቻ እንደኾነች እውነተኞች ከኾናችሁ ሞትን ተመኙ» በላቸው፡፡[አልበቀራህ 94]

በሃዲስም ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ያንተን ፊት በማየት መርካትን እለምንሃለው፤ ወደ አንተ መገናኘትንም ምጓጓ (አድርገኝ)፤...) [አህመድ ዘግቦታል]

- ከተጠቀሡት ውጪ ባሉ ሁኔታዎች ሞትን መመኘት

የእውቀት ባለቤቶች ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ ባሉ ሁኔታዎች ሞትን መመኘትን አስመልክቶ የተለያየ ሃሳብ ሲኖራቸው ከፊሎች ይጠላል ሲሉ፤ ሌለኞቹ ይወደዳል ብለዋል።

ከልካዮቹ መረጃ ብለው የጠቀሱት ከላይ የጠቀስነውን የጃቢር ሃዲስ እና ሌሎች ከልካይ ሃዲሶችን ጠቅሰዋል። በጃቢር ሃዲስ ላይ ሞትን መመኘት የተከለከለው በሁለት ምክንያቶች ነው።

አንደኛው፦ ዱንያ ላይ ሲኖር ከሞተ በኋላ በሚገጥሙት ነገሮች ምንም ቃል የተገባለት ነገር ሳይኖር አዳዲስ ከባባድ ክስተቶችን ከሞተ በኋላ ይመለከታል። መላእክቶችን መመልከት፣ የሠራውን መልካም እና መጥፎ ስራዎች እና የጀነት ወይም የእሳት ብስራትን ያያል። ይህ ታዲያ (ሞትን እንዳንመኝ ከሚዳርጉ)የሞት መከራ፣ ሃያልነት እና አስፈሪነት ውስጥ ሚጠቀስ ነው።

ሃዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ጀናዛን (ሬሳ) የተሸከሟት ጊዜ መልካም ከሆነች አፍጥኑኝ..አፍጥኑኝ ትላለች። ከዛ ውጪ ከሆነች ወይ ጥፋቴ! ወዴት ነው እምትወስዷት? ትላለች። የሠው ልጅ ሲቀር ሁሉም ነገር ድምጿን ይሠማል። የሠው ልጅ ቢሠማት በድንጋጤ ይወድቅ ነበር።[ቡኻሪይ]

ሁለተኛው፦ የሙእሚን እድሜ ለመልካም እንጂ አይጨምርም። ከእድለኝነቱ ምልክቶች ውስጥም እድሜው ረዝሞ አሏህ ወደ እርሱ መመለስን የገጠመው ነው። ካለፉ ወንጀሎቹ ተመላሽ የሆነ ፣ መልካምን በመስራት ላይ ጥረት የሚያደርግ ሰው ሞትን ቢመኝ መልካም ስራው እንዲቋረጥ እየተመኘ ነው። በዚህ ገለፃ ብዙ ሶሂህ ሃዲሶች የተዘገቡ ሲሆን ከነዚህም፦ " አንዳችሁ ሞትን እንዳይመኝ መልካም ሰሪ ከሆነ (መልካምን) ይሰራል(ይጨምራል) ፤ መጥፎ ሰሪ ከሆነ ወደ አሏህ በመመለስ እርሱን የሚያስወድድ ስራ ይሰራልና።" [ቡኻሪይ]

#በኢማን መስፈርቶች ላይ ቋሚ የሆነ አማኝ በእድሜው መጨመር መልካም እንጂ ሌላን አይጨምርም። በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ አማኝ ህይወት ለእርሱ ከሞት የተሻለች ናት። የነብዩﷺ ዱዓ ላይ " አሏህ ሆይ ! ህይወት(መኖሬን) መልካምን ምጨምርበት አድርግልኝ፤ ሞትን ከሁሉም መጥፎ ነገር መገላገያ አድርግልኝ። ይሉ ነበር [ሙስሊም]

በሌላ ዘገባም ጥሩ ሰው ማን ነው? ተብለው ሲጠየቁም "እድሜው ረዝሞ መልካም ሠሪው ነው። መጥፎ ሰውስ ማን ነው? ሲባሉ "እድሜው ረዝሞ ስራው የተበላሸ(የከፋ)።"ብለዋል [ቲርሚዚይ]

[ሙለኸስ ለጣኢፉል መዓሪፍ 118-120]

ለተሣተፋችሁም🏅🏆 ሰጥቻቹኋለሁ።
# ሹክረን!!
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

~
«ያልተሳካ ጋብቻ ምንጩ ቁንጅናን የመረጠ ወንድና 'የባንክ ቼክን ያስቀደመች እንስት እመሆናቸው ላይ ነው
👇👇👇👇👇
@eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

አንተ አዎ አንተ ራስህ!! ወደድክም ጠላህም ትሞታለህ ባይሆን ግን ካፊር ሙሽሪክ ሙናፊቅ ሆነህ ሞተህ ሁለት ሞት እንዳትሞት !!

የሞት ሞት ማለት በሽርክ በክህደት ከአላህ ውጭ እየለመኑ ከአላህ ውጭ ላለ እያረዱ እየተሳሉ -----መሞት ነው።

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

#بــــــسم الله الرحمن الرحيم

#አምልኮን ለተመላኪው ብቻ ለይቶ መስጠት፡፡ አላህ ለእርሱ ፊት ብቻ ጥርት የተደረገን ስራ እንጂ አይቀበልም፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
   وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ     البينة: 5
‹‹የአላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት... እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡›› (አል በይነህ 5)
         أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ الزمر: ٣
‹‹ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡›› (ዙመር 3)
       قُلِ اللَّهَ أَعْبُدُ مُخْلِصًا لَّهُ دِينِي الزمر: ١٤
{•አላህን «ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እግገዛዋለሁ» በል፡፡ (ዙመር 14)

#መልዕክተኛውን ተከታይ መሆን፡፡ አላህ ማንኛውም ስራ የመልዕክተኛውን መመሪያ ያልተስማማ ከሆነ አይቀበልም፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا      الحشر: ٧
‹‹መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገርا ተከልከሉ፡፡›› (አል ሀሽር7)
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجً مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا النساء: ٦٥
‹‹በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡››(አል ኒሳዕ 65)

#ነብዩም ስለላሁ አለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል
#በዚህ ዲናችን ውሰጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ነው፡፡››(ቡኻሪና ሙስሊም) ዘግበውታል
'
#ለአላህ ብቻ በመለየት ያልተሰራና ትክክለኛ ያልሆነ ስራ ትርጉም የለውም፡፡
  #ፉደይል ኢብኑ #ዒያድ የሚከተለውን አንቀጽ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፡፡
لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا هود: ٧
‹‹የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ ዘንድ (ፈጠራቸው) (ሁድ 7)

‹‹ይበልጥ የጠራና የተስተካከለ አባ አሊይ ሆይ! ይበልጥ የጠራና የተስተካከለ የሚሆነው እንዴት ነው? በመባል ሲጠየቁ እንዲህ በማለት መለሱ #ማንኛውም ስራ ተቀባይነት የጠራ ሆኖ የተስተካከለ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

እንዲሁም የተስተካከለ ሆኖ #የጠራ ካልሆነ  አይኖረውም፡፡ የጠራ የሚሆነው #ለአላህ ብቻ የሚሰራ ሲሆን የተስተካከለ የሚሆነው ደግሞ የነቢዩን  መመሪያ የተከተለ ሲሆን ነው››
'
እነዚህን ሁለት መስፈርቶች አካተው ከያዙ አንቀፆች ውሰጥ የሚከተለው በአል ከህፍ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ የተወሳው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡
قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ َلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ ً
أَحَدًا    الكهف: ١١٠
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ (አል ካህፍ 11ዐ)

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍂በወንጀሏ መብዛት ምክንያት ወደ ዲን (ወደ አላህ) ለመመለስ ለከበዳት ነፍሰ ሁሉ ከአሏህ የተሰጠን መልካም ተስፋ!!!
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
🍂አዝ-ዙመር፣53📚


۞ قُلْ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ أَسْرَفُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا۟ مِن رَّحْمَةِ ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ
🍂አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ:-
«ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታየ እምላለሁ፣ ወንጀልን ባትሰሩ ኖሮ
አሏህ እናንተን ያስወግድና ሌሎችን ህዝቦች ያመጣ ነበር።
(እነሱም ወንጀልን ይፈፅሙና) ማረን ይሉታል እርሱም ይምራቸዋል»።

እዝነትህ ከቁጣህ የሚቀድም የሆንከው ጌታችን ሆይ በነፍሶቻችን ላይ ድንበርን አልፈናል፣ ያንተን መሀሪነትን የሚያሽንፍ ወንጀል የለምና ምህረትህን ፈልገን ወደ አንተው  መጥተናል አምላካችን ሆይ! ማረን እዘንልን!!
ቁም (7:187)
☞አያመሰግኑም (2:243)
☞ አያምኑም (11:17)
☞ አመፀኞች ናቸው (5:59)
☞ ይስታሉ (6:111)
☞ እውነቱን አያውቁም (21:24)
☞ እንቢተኞች ናቸው (21:24)
☞ አይሰሙም (8:21)
ስለዚህም አላህ እንዳለው ከጥቂቶቹ ሁን !
⭐️ ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው )) (34:13)

⭐️ ጥቂቶች እንጂ ከርሱ ጋር አላመኑም )) (11:40)

⭐️ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ ፤ ከፊተኞቹ ብዙ
ጭፍሮች ናቸው ፤ ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው)) (56:12-14)

✔️ኢብነል ቀዪም ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ:-
‹‹ #የሃቅ #መንገድን #ያዝ ፤ አብረውህ ባሉት ጥቂት ሰዎች ቁጥር
ማነስ ብቸኝነት አይሰማክ ፤ የውሸትን መንገድ ተጠንቀቅ ፤ ጠፊ
በሆነው ብዛት አትታለል››
____
👏 #አላህ #ከጥቂቶቹ #ባሪያዎቹ # ያድርገን  አሚን!!!!!!!!!

የሰብር አንቀፆች ምንኛ ያምራሉ...
﴿ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮِﻳﻦَ ﴾
ታጋሾችን(ሰብረኞችን) አበስራቸው።
﴿ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮِﻳﻦَ ﴾
አለህ ታጋሾችን ይወዳቸዋል
﴿ ﻭَﺍﺻْﺒِﺮْ ﻭَﻣَﺎ ﺻَﺒْﺮُﻙَ ﺇِﻟَّﺎ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ۚ﴾
ታገስ የመታገስህ ምንዳ ከአለህ እንጂ ከሌላ አይደለም
﴿ ﻭَﺟَﺰَﺍﻫُﻢْ ﺑِﻤَﺎ ﺻَﺒَﺮُﻭﺍ ﺟَﻨَّﺔً ﻭَﺣَﺮِﻳﺮًﺍ ﴾
በመታገሳቸው ጀነትንና የሃር ልብስ መነዳቸው
﴿ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢْ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ ﴾
ታጋሾች ምንዳቸውን ያለ ልኬት ነው የሚያገኙት።
"አለህ የማይፈትነኝ ሳይወደኝ ቀርቶ የታጋሾችን ምንዳ ልያሳጣኝ ፈልጎ ይሆን?"(ከአባቶቻችን ንግግር)
ከሰብር ውጪ ይህ ሁሉ ምንዳ የሚገኝበት ምን አለ?
@tewihd

Читать полностью…
Subscribe to a channel