tewihd | Unsorted

Telegram-канал tewihd - አስ–ሱናህ 🇵🇸

-

﴿وَلا تَلبِسُوا الحَقَّ بِالباطِلِ وَتَكتُمُوا الحَقَّ وَأَنتُم تَعلَمونَ﴾ البقرة ٤٢ “እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡” አልበቀራ 42

Subscribe to a channel

አስ–ሱናህ 🇵🇸

"…ወራችሁ(ረመዳን) መጎደሉን ተያይዞታል።
እናንተ ደግሞ መልካም ስራችሁን ጨመርመር አድርጉ።"
(ኢብኑ ረጀብ/ለጣኢፉ አልመዓሪፍ /262)👇👇
Te»@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🚪ፆም🚪

🗓 ክፍል ስድስት (6)

↪ ካለፈው የቀጠለ…

🗒 የፆም መጀመሪያ እና ማብቂያን በተመለከተ ፦

አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ምግብና መጠጥ አስከ ጎህ ድረስ ፈቅዷል። ሰሑርን መብላት የተወደደ መሆኑ ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች መካከል:–

፨ ቡኻሪና ሙስሊም ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገቡት ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም፦

  "ስሑርን ተመገቡ ምክንያቱም ሰሑር በረካ (በረከት) አለውና" ብለዋል።

 ሰሑርን መመገብ ተወዳጅ መሆኑ ብዙ ዘገባዎች መጥተዋል።

» ውሃን በመጎንጨት እንኳ ቢሆን

» ሰሑርን ጎህ ግልፅ አስኪል ድረስ ማቆየቱ ተወዳጅ ነው።

✅ ጎህ ከመውጣቱ በፊት አንድ ሰው ጀናባ (ከሕጋዊ ባለቤቱ ጾታዊ ግንኙነት ወይም በህልም የፍትወት ፈሳሽ ቢያፈስ) ሆኖ ቢነሳ ወይም የሴት ልጅ ከወር አበባ ወይም ከወሊድ ደም ብትፀዳ ቅድሚያ ሰሑር መብላት ይኖርባቸዋል።  ጾምን ይጾማሉ።  መታጠቡን ጎህ እስኪወጣ ድረስ ማቆየት ይችላሉ።

❎ አንዳንድ ሰዎች ሌሊቱን ቁጭ ብለው ስለሚያመሹ ሰሑርን ቀደም ብለው በልተው ሱብሒ ሳይደርስ ቀድመው ይተኛሉ። እነዚህ ሰዎች ብዙ ስህተቶችን ፈጽመዋል።

ከነዚህም:–

1ኛ· ቀድመው ጾም መጀመራቸው
2ኛ· አላህ ግዴታ ያደረገባቸውን ሱብሒ ሰላትን በጀማዓ ባለመስገድ አላህን ማመጻቸው
 3ኛ· ሱብሒን ከወቅቱ አሳልፈው ጸሐይ ከወጣች በኋላ ሊሰግዱም ይችላሉ። ይህ ደግሞ ከታላላቅ ወንጀሎች እና ሀጢአቶች ነው። ሰላት ከወቅቱ ማቆየትን በተመለከተ አላህ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ይላል ፦

"ወዮላቸው ለሰጋጆች ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡"
(አልማዑን 4–5)

፠ ግዴታዊ ጾም ከሆነ በሌሊት ኒያ (ቁርጠኛ ሐሳብ) ማድረግ ግዴታ ነው።

፠  በሌሊት እጾማለሁ ብሎ ነይቶ ነገርግን ለሰሑር ሳይነሳ ቢነጋበት ምንም ችግር የለውም ጾሙንም ሊቀጥል ይችላል። ጾሙ በአላህ ፈቃድ ትክክል ይሆናል።

[አልሙለኸስ አልፊቅህ –
ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን (194)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🔘((ትግስተኞቹ (ታጋሾቹ) ምንዳቸውን የሚሠጡት ያለ ስፍር ቁጥር ነው።))
✍🏻 ሐፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
۞ ሶብር በሦስት ይከፈላል።
(❶) በኢባዳ ላይ መታገስ፤
(❷) ከሀራም መታገስ እና
(❸) አሳማሚ ከሆኑ የአላህ ውሳኔዎች መታገስ።
❍ ሦስቱንም የሰብር አይነቶች ጾም በሚባለው የአምልኮት አይነት ውስጥ ታቅፈው ይገኛሉ።
ምክንያቱም ጾም ውስጥ ፦
👉 በአላህ ትእዛዝ (ጾም) መታገስ፤
👉ፆመኛ ላይ ሐራም የተደረጉ ስሜቶች መታገስ፤
👉ጾመኛ በመጾሙ የተነሳ ጾሙ ረሐብ፤ ጥማት እና በነፍሱ እና በአካሉ ድክመት ያስከትልበታል ሆኖም እነዚህን ስቀይና ሕመም በመታገስ ይወጠዋል።
📍ይህ ህመምና ስቃይ መልካም ስራን ከመስራት የመነጨ በመሆኑ ግለሰቡ በዚህ ተግባሩ ከፍ ያለ ምንዳ ያገኝበታል።"
📘【ለጧኢፉ አልመዓሪፍ (1/150)
👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

⛔️አንድ ሰው አሰጋጁ (ኢማሙ) ለሩኩዕ ተክቢራ እስኪያደርግ ሆን ብሎ ጠብቆ ከዚያም ተክቢራ አድርጎ ሰላት ውስጥ መግባት ተገቢ ተግባር አይደለም።
ይኸኛው(የመጀመሪያው) ረከዓ ተቀባይነት አለው ወይም የለውም? የሚለው ጉዳይ ላይ ለጊዜው ፍርድ ከመስጠት እታቀባለሁ ። ምክያቱም ሆን ብሎ መዘግየቱ ፋቲሓን መቅራት እንዳይችል አድርጎታል። ፋቲሓ መቅራት ደግሞ የሰላት ማዕዘን ነው። ከኢማም ፣ ተከትሎ ከሚሰግድ(መእሙም) ሆነ ለብቻው ከሚሰግድ የፋቲሓ ግዴታነት አይነሳም። ኢማሙ ሩኩዕ እስኪያደርግ ሆን ብሎ ጠብቆ ከዚያም ከተቀመጠበት ተነስቶ ሩኩዕ ማድረጉ ያለምንም ጥርጥር ስሕተት እና ሰላቱን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ነው። በትንሹ እንኳ የመጀመሪያው ረከዓ አላገኘም የሚል ፍርድ ያሰጠዋል።"
📚መጅሙዕ አልፈታዋ… (13/10)
#share👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሱረቱል ካፍ በሸህ ሱደይስ
የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል:–

(የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል)

ፏ ያለ ዱአችን ተቀባይነት ያለው ጁመዓ ይሁንልን🌹🌹

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሸይኽ ኢብነ ባዝ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:–

"ለአንድ ሙእሚን ይህንን የተከበረና ታላቅ ወር
በሚችላቸው በላጭ በሆኑ መልካም ስራዎች
በማጠናቀቅ ላይ ሊበረታና ሊጓጔ ይገባዋል።"

حديث المساء(227)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🗓 ክፍል አራት (4)

🗒 የረመዳን ፆም ግዴታ ስለመሆኑና ጊዜው

✍🏼 ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~

🗒የረመዳን ወር ጾም ግዴታ የሚሆነው:–

1· ሙስሊም በሆነ ሰው ላይ፣
2· ለአቅመ አዳም/ ሄዋን የደረሰ/ች
3· አቅም/ችሎታ ያለው/ት

 በከሀዲ ላይ ግዴታ አይሆንም ቢጾምም ተቀባይነት አይኖረውም። በጾም ጊዜ ቢሰልም ቀሪውን ሰዓት ይጾማል።

» ከሐዲ በነበረበት ጊዜ ያለፈውን ጾም እንዲጾም ግዴታ አይሆንበትም።

» በህጻን ልጅ ላይም መጾም ግዴታ አይሆንበትም።

» እንዲሁም በእብድ ሰው ላይ ግዴታ አይሆንበትም ምክንያቱም ቁርጠኛ የሆነ ዉሳኔ ( ኒያ) ስለሌለው።

» በሽተኛ/ህመም ያለበት እና መንገደኛ በሆኑ ሰዎች ላይ መጾም ግዴታ የለባቸውም። ነገርግን በሽተኛው ከበሽታው ሲድን እና መንገደኛው ወደ አገሩ ሲመለስ ያለፋባቸውን ጾም መተካት (ቀዷእ ማውጣት) ይኖርባቸዋል።

አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል:–

"…ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት፡፡…"

🖱 ጾም ግዴታ የሚሆንባቸው:–

1· መንገደኛ በሆነ እና መንገደኛ ባልሆኑ
2· ጤነኛ እና በሽተኛ
3· ንጹሀን፣ በወር አበባ እና በወሊድ ደም ላይ ያሉ
4· ራሱን በሳተ ሰው ላይ

👆ከላይ በተጠቀሱ ሰዎች ላይ መጾም ግዴታ የተደረገ መሆኑን ማመን እና ሁኔታዎች ሲመቻቹ መተግበር ይኖርባቸዋል።

🗒የአጿጿሙም ሁኔታ:–

» ወዲያው በጊዜው በመጾም (አዳአን) ወይም
» በሌላ ጊዜ በመተካት (ቀዷእ በማውጣት) ሊጾሙ ይችላሉ።

ከእዚህም መካከል:–

፠ ወዲያው በጊዜው መጾም (አዳአን) እንዳለባቸው የሚታዘዙ አሉ ።

እነሱም:– 

1· ጤነኛ እና
2· መንገደኛ/ ጉዞ ላይ ያልሆነ

👉 በሌላ ጊዜ በመተካት (ቀዷእ ማውጣት) ብቻ ያለባቸው:–

1· በወር አበባ ላይ ያለች ሴት

2· በወሊድ ደም ላይ ያለች

3· በሽተኛ ሆኖ መጾም የማይችል ነገርግን ሲድን መተካት የሚችል  ከሁለቱ አንዱ ምርጫ የሚሰጠው:–

፠ መንገደኛ እና በሽተኛ ሆነው እየከበዳቸው ሊጾሙ የሚችሉ ከሆኑ እራሳቸውን ጉዳት ላይ በማይጥል ሁኔታ ምርጫ አላቸው።

፠  አንድ ሰው በምክንያት (ዑዝር) ያፈጠረና ከዛ በኋላ አ ንዳይጾም ያገደው ምክንያት በጾም መሐል (ቀን ክፍለ–ጊዜ ላይ) ቢነሳ ወይም ቢወገድ:–
ለምሳሌ:–

1· መንገደኛ በቀን ክፍለ ጊዜ ቢመለስ
2· በወር አበባ ወይም በወሊድ ደም ላይ ያሉ ቢጠሩ
3· ከሀዲ የሆነ ሰው ቢሰልም
4· እብድ ጤነኛ ቢሆን
5· ህጻን ለአቅመ አዳም ቢደርስ

👆እነዚህ ሁሉ በቀረው ቀን ላይ ከመብላት ይታቀቡና በሌላ ቀን መተካት ይጠበቅባቸዋል። 

እንዲሁም የረመዳን ወር መግባቱ ቀን ላይ ከታወቀ በኋላ ሙስሊሞች በቀሪው ሰዓት መታቀብ እና ረመዳን ከወጣ በኋላ ያንን ያፈጠሩበትን ቀን መተካት (ቀዷእ ማውጣት) ይኖርባቸዋል።

📙ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ (192–193)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🚪ፆም🚪

ክፍል ሁለት 2

🗒የረመዳን ወር ጾም መደንገግን ጥበብ:–

ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ፦

1· ነፍስን ከተለያዩ መጥፎ፣ ቆሻሻና የዘቀጡ ባህሪያትን ለማጽዳትና ለማንጻት

2· በሰው ልጅ አካል ውስጥ የሸይጣን መሄጃ መንገዶችን ያጠባል። ምክንያቱም ሸይጣን በደም ስር ውስጥ እንደደም ይንቀሳቀሳልና… የሰው ልጅ ምግብን ሲመገብ እንዲሁም ሲጠጣ ስሜቱ ይጨምራል፣ ለአምልኮ ያለው ፍላጐት ይቀንሳል ነገርግን ጾም ሲጾም በተቃራኒው ይሆናል።

3· ለዚህች ቅርብ ዓለም እና ለስሜቱ ያለው ፍላጎት እንዲቀንስ ፤ ለመጪው አለም በመልካም ነገርና በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጅ።

4· ለድሆች እንዲራራ እና እንዲያዝን፤ በሚያጋጥማቸው ረሃብና ችግር እንዲሰማውና የችግራቸው ተካፋይ መሆንን ዋነኛ የጾም ጥበቦች ናቸው።

🗞በሸሪዓ ጾም ማለት:–

ከምግብ፣ ከመጠጥ እና ከግብረስጋ ግንኙነት አምልኮን ታሳቢ በማድረግ ከእውነተኛው ጎህ እሰከ ፀሀይ ጥልቀት ድረስ መቆጠብ ማለት ነው።

እንደዚሁም ከተለያዩ አሉባልታ እና አፀያፊ ነገሮችን ራስን መጠበቅና ማቀብንም ያካትታል።

ምንጭ:–
አልሙለኸስ አልፊቅህ (1/374)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

#ፈታዋ_ረመዳኒያ
❗️"አንድ ሰው ያለ ምንም ኡዝር ያለበትን ጾም ቀዳ ሳያወጣ ሌላኛው ረመዳን ከገባበት ወንጀል አለበት ሆኖም (ተውበት ከማድረግ ጋር) ቀዳ ማውጣት ይኖርበታል ። ሚዛን በሚደፋው አቋም መሰረት ሚስኪን ማብላት አይጠበቀበትም።"
📚【ፈታዋ ኡሰይሚን (ቅፅ 19/ገጽ 385)】
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍃 መሳጭ ቲላዋ 🍃

🎙 በሸይኽ ናስር አል ቂጣሚ
👇👇👇
@eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

በዚህ የረመዳን ወር ወደ ኋላ መቅረት ዋጋ ያስከፍላል።
ገብቶ ሲወጣ ፈጣን ነውና መዘናጋት አያስፈልግም።
ምጥቀት ያሻል…
ወሩን በመልካም ስራ ለማጠናቀቅ ወኔ ያስፈልጋል…
"(የረመዳን ቀናት) የሚቆጠሩ ቀናት ናቸው።"
"(በመልካም ስራ) ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ።"
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም
በአንድ ወቅት "ሐሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? በማለት ባልደረቦቻቸውን ጠየቁ።
"አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ። የሚል መላሽ ሠጧቸው። እንዲህ አሉ፦
«ሐሜት ማለት ስለ አንድ ወንድምህ እርሱ የሚጠላውን ነገር ማውሳት ነው።» እርሱ ላይ የምለው ነገር በእውነትም ከርሱ ላይ ያለበት ቢሆንስ? የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። «የምትለው ነገር በርሱ ላይ ካለ አምተኸዋል፤ ከሌለበት ደግሞ የሌለበትን ነገር ለጥፈህበታል(ቀጥፈህበታል)።» አሉት።
(ሙስሊም ዘግበውታል)

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

እንዴት ቆያችሁ ቤተሰቦች....?!


ተራዊህ እንዴት ነበር?!

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

☪ረመዷን ላይ ለቁርኣን ምን ያክል ጊዜ እየሰጠን ነው? ቢያንስ በወር አንዴ ለማኽተም በቀን ምን ያህል ገጾችን እየቀራን ነው? ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ!! ቁጭ ስንል ስልካችንን ከፍተን ሌላ አልባሌ ነገር ከምናይ ወይም ጌም ከምንጫወት ቁርኣንን በመቅራት እንጠመድ!! ባረከሏሁ ፊኩም።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🔻ስንት እና ስንቶች እየተመኙት ያላገኙትን ትልቅ እድል አላህ አጋጥሞሃልና ሳትሰለች አላህን በማምለክ ጊዜህን ተጠቅመህ ኣሳልፈው።
⬇️⬇️⬇️
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

መከራና ችግር ለምን እንጠላለን??

ደስታ ከመከራ ውስጥ ይወለዳል
የተኮረኮመ በድሎት ካደገው በላይ ጥንካሬ ይኖረዋል።

★ ህፃን ልጅ በመቆም የሚፀናው ብዙ ወድቆ ከተነሳ ቦኋላ ነው።

★ ተርበው የበሉት ምግብ ይጣፍጣል።

🔻ተጠምተው የጠጡት ውሃ ይጥማል።
🔻ላብን አንጠፍጥፈው ያገኙት ገንዘብ ያረካል።
⚜ ወድቀው ተነስተው ተቸግረው ያገኙት ነገር በረከት አለው።
⚜ችግርን በመጥፎ ጎኑ ብቻ አናስብ።
★የጨለማ ጥቁረቱ ብቻ አንመልከት።
አላህ እንዲህ ይላል
ከችግር ቦኋላ በእርግጥ ምቾት አለ
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሰላተ ተራዊሕ ላይ ዱኣ ማብዛት እንዴት ይታያል?
አንዳንድ የመስጂድ ኢማሞች ረመዳን ውስጥ ሰላተ ተራዊህ ላይ ዱዓ ሲያስረዝሙ አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ያሳጥራሉ።የትኛው ነው ትክክለኛ አካሄድ ?
መልስ፦"በዚህ ላይ ትክክለኛው አካሄድ በጣም አለማሰጠርና ከልክ በላይ አለማስረዘም ነው።
ሰዎች ላይ እንዲከበድ የሚያደርግ ከልክ በላይ ማስረዘም ተከልክሏል።
የአላህ መልክተኛ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል ሕዝቦቹ ላይ በጣም ማስረዘሙ ሲደርሳቸው እንደዛን ቀን ሲገስፁ ወይም ሲመክሩ ተቆጥተው አያውቁም።
ለሙዐዝም እንዲህ አሉት፦"አንተ ሙዑዝ ሆይ!ሰዎችን (በዲናቸው)ተፈታታኝ ነህን?
በዚህ ላይ ሰላማዊው አካሄድ ከሐዲስ የመጡትን ዱኣዎች ላይ መገታት ይኖርበታል።ትንሽ ቢጨምር ግን ችግር የለውም።
ቁኑት ማስረዘም ሰዎችን የሚያዳክምና የሚከብድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።በተለይ በተለይ አቅመ ደካሞችን ።
አንዳንድ ሰው ለበኋላ ብሎ ያዘገየው ስራ ይኖረዋል፣ ኢማሙ ተራዊህን እሰካልጨረሰ ማቋረጥ አይወድም፣ይህ ከመሆኑ ጋር ከሱ ጋር መቀጠልም ይከብደዋል።
ስለዚህም ወንድሞቼ የመስጂድ ኢማሞች የምመክረው መሀከለኛ ቁኑት ያደርጉ ዘንድ ነው።እንደዚሁም ተራ የሆኑ ሰዎች (ከአሊም ምድብ የወጡ ሰዎች) ዱዓ ዋጂብ ነው ብለው እንደይገምቱ አንዳንዴ መተው ያስፈልጋል።
【አሸይኽ ዑሰይሚን】
#share👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

… ከጎንህ ያለችው ሚስትህ የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት
… ደስተኛ ያልሆንክበት ልጅህ መውለድ የማይችሉ ሁሉ የሚመኙት ነው
… ጠባቧ ቤትህ የጎዳና ልጆች ምኞት ነው
… በገንዘብ የማይተመነው ጤናህ የበሽተኞች ሁሉ ምኞት ነው
… በነፃነት መንቀሳቀስህ እስር ቤት ሆነው የሚሰቃዩ ምኞት ነው
ታዲያ ጌታህን አታመሰግንም

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ምርጥና ያማረ ጁመዓ እንዲሆንልን ተመኘሁ ‼️

وإنّ الهمومَ لتُكْفى ، والذنوبَ لتُغْفر .. بكثرة
‏الصَّلاةِ على النَّبيِّ ﷺ .. فهل من مُصَلٍّ عليه ؟

‏ٰ
‏اللهــمّ صلِّ وَسَلّم وَبَارِك على نبيِّنا مُحَمّد
‏اللهــمّ صلِّ وَسَلّم وَبَارِك على نبيِّنا مُحَمّد

✨🤲🏻@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ረመዳን 9 🌙

የቁርአን ጁዞ 🍂09🍂
عبدالولي الأركاني
ዓብዱልወሊይ አል አርካኒይ
منصور الزهراني
መንሡር አልዛህራኒይ
👇👇👇👇👇
@eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሸይኽ ኢብነ ባዝ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:–

"ለአንድ ሙእሚን ይህንን የተከበረና ታላቅ ወር
በሚችላቸው በላጭ በሆኑ መልካም ስራዎች
በማጠናቀቅ ላይ ሊበረታና ሊጓጔ ይገባዋል።"

حديث المساء(227)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🗒ከፆም ጋር ተያያዥነት ያላቸው
አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦች

1.ፆመኛ ትጥበትን ግዴታ የሚያደርግ (ጀናባ) ላይ ሆኖ ፆምን ማቀድ (መነየት) ከዚያም ጐህ ከቀደደ በኋላ መታጠብ ይፈቀድለታል፡፡

2.በረመዳን ወር በወሊድ እና በወር አበባ ደም ላይ ያሉ ጐህ ከመቅደዱ በፊት ከደሙ ከጠሩ ከዚያ በኋላ ቢታጠቡም እንኳ መፆም ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ 

3.ፆመኛ ጥርሱን መነቀል፣ ቁስሉን መታከም እና በዓይኑ ወይም በጆሮው በኩል የሚወሰዱ በጠብታ መልክ የተዘጋጁ መድሃኒቶችን መጠቀም ይፈቀድለታል፡፡ ይህንን በማድረጉም ጐሮሮው ውሰጥ የጠብታው ጣዕም ቢታወቀው እንኳ ፆሙ አይበላሽም፡፡

4.በቀኑ መጀመሪያም ይሁን መጨረሻ ክፍለ ጊዜ መፋቂያን መጠቀም ፆመኛ ላልሆኑ ሰዎች ሱና እንደሆነው ሁሉ ለፆመኛም የተወደደና የተፈቀደ ነው፡፡

5.ፆመኛ ከከፍተኛ ሙቀትና የውሃ ጥም ራሱን ለማ ስታገስ ውሃ በራሱ ላይ ማፍሰስም ይሁን መታጠብ እንዲሁም የአየር ማቀዝቀዣ መሣሪያዎችን መጠቀም ይፈቀድለታል::

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል »»»
__
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🚪ፆም 🚪

🗓 ክፍል አንድ (1)

🗒የረመዳን ፆም ግዴታ ስለመሆኑ

ሼኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:~

▶ የረመዳን ወር መፆም ከእስልምና ማዕዘናት እና አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ካደረጋቸው መካከል አንዱ ሲሆን ለዚህም ማስረጃ በቁርአን፣ በሐዲስ እና በዑለማኦች ስምምነት የተረጋገጠ ነው።

📔ከቁርአን:–

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡»

እስከ፦

(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡

አልበቀራህ 182–184

📔በሐዲስ:–

ዓብደላህ ኢብኑ ዑመር ነቢዩ –ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም– እንዲህ ብለዋል፦

«እስልምና በአምስት ምሶሶ ተገንብቷል…

1· ከአላህ በስተቀር በእውነት ሊገዙት የሚገባ አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድ –ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም– የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣

2· ሰላትን ማቋቋም

3· ዘካህ – ግዴታዊ ምፅዋት– መስጠት

4· የረመዳን ወር መጾም

5· አቅሙ ከቻለ ሐጅ ማድረግ

( ቡኻሪ ዘግበውታል። )

📚ምንጭ:–
[አልሙለኸስ አልፊቅህ (1/373)]
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ጾመኛ ማን ነው?

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ~

ጾመኛ ማለት: – 

※ አካሎቹን ከሀጢአት የጸዱ፤
※ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤
※ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።

ℹ ጾመኛ ከተናገረ:–

 ※ ጾሙን በማይጎዳ 
※ ስራ ከሰራ ጾሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል።

🔵 ጾመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው።

🔵 ከጾመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመትን እና በደልን ሁሉ ሰላም ይሆናል።

👆ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ጾም ማለት …

⛔ ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ጾም አይባልም።

✅ ጾም ማለት አካላትን ከሀጢአት እና ሆድን ከምግብና መጠጥ በመታቀብ መጾም ነወ።

🗒 ምግብና መጠጥ ጾምን እንደሚያጠፋ ሁሉ ሀጢአትም የጾምን ምንዳ ያጠፋል፣ ውጤቱን ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ጾም እንዳልጾመ ተደርጎ ይታሰባል።

ምንጭ: – አልዋቢሉ አሶይብ (31–32)
አድራሻችን ፡-@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የተከበሩት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና የተራዊህ ሶላትን አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል:- " አንድ ሰው የተራዊህ ሶላትን ወደ ጉዳዩ ሳይሄድ ከኢማሙ ጋር አብሮ የጨረሰ ሌሊቱን ሙሉ ቆሞ እንዳደረ ይቆጠርላታል።"

ቲርሚዚ እንደዘገቡት
ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሸይክ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና ከላይ ያለውን ሀዲስ በማጣቀስ " ፍራሽክ ላይ ተኝተህም ቢሆን አላህ ለሊቱን ሙሉ ለሶላት እንደቆምክ አድርጎ ይፅፍልሀል" ብለዋል።
ስንቶቻችን ነን ይህ ሚስጥር የገባን ???
አላህ ያሳካልን

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

(( إِذَا جَاءَ رَمَضَانُ فُتِحَتْ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ ))

▪️عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : (( إِذَا جَاءَ رَمَضَانُ فُتِحَتْ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ ))

📚 صحيح البخاري - رقم : (1898)

▪️وعَنْهُ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : (( إِذَا دَخَلَ شَهْرُ رَمَضَانَ، فُتِّحَتْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ))

📚 صحيح البخاري - رقم : (1899)

👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

▪️ሰሑር ላይ ኢስቲግፋር እናድርግ

🔻አሏሁ - ተዓላ - የመተቆችን(እሱን የሚፈሩ ባሪያዎችን) ባህሪይ ሲገልፅ እንዲህ ይላል ፦
{ وَبِالْأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ }

[| በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ |] (አዝዛሪያት ፥ 18). በተለይም በዚህ በረመዷን ወቅት ሱሑርን ለመብላት ስለምንነሳ በዛውም ኢስቲግፋር ማድረግን መርሳት የለብንም። አላህ ይወፍቀን ፤ ወንጀላችንንም ይማርልን።
👇👇👇
ጆይን፦@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ከፆመኞች ሁሉ በላጮቹ አላህን ማስተዋስን
(ዚክርን)በፆማቸው ያበዙ ናቸው።
#ኢብኑልቀይም
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

▪️ትኩረት ይሰጠው

🔻ጾመኛ ሆነን ዉዱእ እያደረግን ውሃን ወደአፍንጫችን በምንስብበት ሰአት በጣም ከመሳብ እንጠነቀቅ።
°
🔻ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ስላሉ ነው ፦ [ (ዉዱእ ላይ) ውሃን ወደአፍንጫህ በምትስብ ሰአት በደንብ አድርገህ ሳብ ፤ ጾመኛ የሆንክ ጊዜ ሲቀር። ] (አቡዳውድ ፥ 142 / ቲርሚዚይ ፥ 38 ላይ የዘገቡት እና ሸይኽ አልባኒ አልሚሽካት ፥ 405 ላይ ሶሒህ ያሉት ሐዲስ ነው።

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : (( تَسَحَّرُوا ولوْ بِجَرْعَةٍ مِنْ ماءٍ ))

👈🏽 صححه الألباني في
📚 صحيح الجامع - رقم : (2945)
👉@tewihd

Читать полностью…
Subscribe to a channel