✍ሟርተኛ ብቻ አትሁን‼
✍"ጊዜው ፈጠነ፣ ረመዷን ሊያልቅ ነው፣ ሳንጠቀምበት አመለጠን፣ ፣፣፣፣፣" እያልክ ብቻ እያሟረትክና እየቃዠክ ጊዜህንና ራስህን አታባክን።
🔹በእርግጥም
መስራት ያለብን ሳንሰራ፣ መስገድ ያልብንን ሳንሰግድ፣ መቅራት ያለብን ሳንቀራ፣ መድረስ ያለብን ሳንደርስ ረመዷን ሊሰናበተን እያኮበኮበ ነው።
👈🏿"ረመዷን ሊገባ ስንት ቀን ቀረው?" ስንል እንዳልነበርነው ይኸው ደርሶልን መጠቀም ሳንችል ሊያመልጠን "ረመዷን ሊያልቅ ስንት ቀን ቀረው?" ለማለት በቅተናል።
👌አንድ ነገር ግን አለ
👇🏾
👉🏿"ከሄደው የሚመጣው ይበልጣል"
✍በተቀሩት የረመዷን በላጭ በሆኑ ቀናቶች ያሳመርን እንደ ሆነ አላህ ያለፉን ቀናቶቻችንም ጭምር አሳምሮ ይመነዳናል።
👌ለየት ባለ መልኩ ደግሞ ከፊታችን እየጠበቁን ያሉት "አሽረል አዋሂር" በመባል የሚታወቁ ብርቅዬ የመጨረሻ አስርቱ ቀናቶች ናቸው።
👆
👉በእነዚህ ቀናቶች ውስጥ ደግሞ "ለይለቱል ቀድር" የሚባል ከ1000 ወር ወይንም ከ83 አመት የሚበልጥ የሆነ ሌሊት አለባቸው።
ስለዚህ የትኛውንም አኼራን የሚፈልግ የሆነ ሙስሊም ከዚች ሰዐት ጀምሮ ለየት ያለ ጥረትና ትግል ሊያደርግ ይገባዋል።
✍ልብ በል
=>ለቀሪው የህይወት ዘመንህ የመጀመሪያው ቀን ዛሬ ነው‼
ዛሬውኑ ጀምረህ ወደ አላህ ተቀጣጭተህ ቀሪው ህይወትህ ከአላህ ጋ ብሩህ እና ስኬታማ አድርገው።
#shere
👇👇👇
@tewihd
🌙የለይለተል ቀድር ትርጉም
🔻ለይለተል ቀደር ሁለት ትርጉሞች አሏት።
1ኛው ፡ የክብር እና ደረጃ ያላት ሌሊት ማለት ሲሆን
2ኛው ፡ ትርጉሟ ደግሞ የመወሰኛዋ ሌሊት ነው። ይህም የተባለችው በሷ ውስጥ በአመቱ የሚከሰተውን ክስተት በሙሉ የሚወሰንባት ሌሊት ስለሆነች ነው።
👇👇👇
@tewihd
🌙የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት
🌙የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ልዩ የሆኑ ትርፉቶች እና መለያዎች አሏቸው። ከነሱ ውስጥ ፦ ነብዩ - ﷺ - ከሌላው ቀን በበለጠ መልኩ በዒባዳ ላይ ይጠናከሩ ነበር። አዒሻ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች ፦ | ነብዩ - ﷺ - በሌላ ጊዜያት በዒባዳ ላይ ትግል የማያደርጉትን ያክል በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ በዒባዳ ላይ ትግል ያደርጉ ነበር። ① | በሌላ ዘገባም ላይ ሽርጣቸውን ያጠብቁና ሌሊቱን በዒባዳ ያሳልፉ እንደነበረ እንዲሁም ቤተሰባቸውን ይቀሰቅሱ እንደነበረ ተነግሯል። ②
°
👉ሌሊቱንም በተለያዩ ወደ አላህ የሚያቃርቡ የሆኑ የአምልኮ ዘርፎች ለምሳሌ ቁርአንን በመቅራት፣ ሶላት በመስገድ ፣ ዚክር በማብዛት ያሳልፉት ነበር። ከሌላው ጊዜ ጥረት የሚያደርጉትም እነዚህ ቀናቶች ልዩ ትሩፋት ስላላቸው እና ለይለተል ቀድርንም ፍለጋ ነበር።
°
👉ሌላው ልዩ ትሩፋት እንዳለው የሚይመላክተው ቤተሰቦቻቸውን መቀስቀሳቸው ነው። ምክንያቱም በዒባዳ ላይ ተጠናክረው ከሚገኘው በረካ እና አጅር ተካፋይ እንዲሆኑ ማለት ነው። በመሆኑም እነዚህን ቀናቶች በዒባዳ ማሳለፍ ይገባናል ያገኘነውን እድል መጠቀም ያስፈልጋል። አንድ ሙእሚን እና አእምሮ ያለው ሰው እነዚህን እድሎች በሱም ላይ ይሁን በቤተሰቦቹ ላይ ሊያሳልፍ አይገባውም።
____
①.(ሙስሊም ፥ 1175)
②.(ቡኻሪ ፥ 2024 / ሙስሊም ፥ 1174
ምንጭ ፡ ከመጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን ኪታብ ላይ የወሰድኩት
➖➖➖➖➖➖➖➖
ጆይን ፦ @tewihd
▪️ትኩረት ይሰጠው ~ የለሊቱ የመጨረሻ ሲሶ
👉የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል ፦ [ አላህ - ሱብሓነሁወተዓላ - የሌሊቱ ሲሶ(1/3)ኛ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል ከዛም ይላል ፦ ማንነው የሚለምነኝ እሺ የምለው ፤ ማንነው የሚጠይቀኝ የጠየቀውን የምሰጠው ፤ ማንነው መሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው። ] (ቡኻሪ ፥ 1145)
°
🔻ይህን ሐዲስ በብዛት ስንጠቀምበት የምንስተዋለው የጥመት አንጃዎች 'አሏሁ - ተዓላ - አይወጣም አይወርድም' ስለሚሉ እንደሚወርድ መልስ ለመስጠት ነው። ነገር ግን ከዛ ባለፈ ሌላ ትልቅ ቁምነገርን ይዟል እሱም ሁለተኛው ሀረግ ላይ ነው ፦ "ማንነው የሚለምነኝ እሺ የምለው ፤ ማንነው የሚጠይቀኝ የጠየቀውን የምሰጠው ፤ ማንነው መሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው። " እያለን ነውና ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ ሰአት ላይ ተነሰትን እጃችንን ወደአላህ መዘርጋትን አንርሳ!!
👇👇👇
@tewihd
▪️ከፈጅር በፊት ከሐይድ ጠርታ ሳትታጠብ ፈጅር ቢወጣ
ጥያቄ ፡
ሐይድ ያለባት ሴት ከፈጅር በፊት ጠርታ ነገር ግን ከፈጅር በኋላ ብትታጠብ ፃሟ ትክክል ነውን?
°
መልስ ፡
👉ፈጅር ከመውጣቱ በፊት መጥራቷን እርግጠኛ ከሆነች ፆሟ ትክክል ነው። ዋናው ነገር መጥራቷን ማረጋገጧ ነው ፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሴቶች የጠራች ይመስላታል ግን አልጠራችም። ለዚህም ነው ሴቶች ወደአዒሻ - ረዲየሏሁዐንሃ - ጋር ጥጥን ይዘው የሚመጡትና የመጥራት ምልክቱን ለሷ የሚያሳዩዋት የነበረው።
°
👉ሴት ልጅ መጥራቷን እርግጠኛ እስክትሆን ድረስ መጠባበቅ ይኖርባታል። ከጠራች ፈጅር ከወጣ በኋላ ብትታጠብም ጾምን መነየት ትችላለች። ነገር ግን እዚህም ጋር ሶላትን ልትጠባበቅ ይገባታል ፤ ቶሎ ታጥባ የፈጅርን ሶላት በወቅቱ እንድትሰግድ ማለት ነው።
°
👉ጀናባ ሆኗ ነገር ግን የታጠበችው ፈጅር ከወጣ በኋላ የሆነች ሴትም የሚሰጣት ብይን ልክ እንደሐይደኛዋ ሴት ዓይነት ብይን ነው ፤ ጾሟ ትክክል ነው። ይህም ልክ ወንዱ ጾመኛ እያለ ጀናባ ሆኖ የታጠበው ግን ፈጅር ከወጣ በኋላ ቢሆን በዚህ ላይ ችግር እንደሌለው ማለት ነው። ምክንያቱም ነብዩ -ﷺ- ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግንኙነት አድርገው ጀናባ ላይ ሆነው ፈጅር ያገኛቸውና ጾማቸውን ቀጥለው ከፈጅር በኋላ እንደሚታጠቡ በሐዲስ① ስለተረጋገጠ ነው።^^
_
①. ሸይኹ ለመጥቀስ የፈለጉት (ቡኻሪ ፥ 1926 እና ሙስሊም ፥ 1159) ውስጥ የተዘገቡ ሐዲሶችን ነው።
__
ሼይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አልዑሰይሚን
📕ምንጭ ፦ [ "ፈታዋ አርካኒልኢስላም ወልዓቂዳህ" ፥ ገጽ 608 - 609)
👇👇👇
@tewihd
|> ፆመኛ ገላውን መታጠብ ይችላል። እራሱን ለማቀዝቀዝም እንዲሁ ቢታጠብ ፆሙን አያበላሽበትም።
ነብዩ ﷺ ፆመኛ ሆነው በፀሐይ ምክንያት ወይም የውሃ ጥም ሲሰማቸው ራሳቸው ላይ ውሃን ያፈሡ ነበር። [አቡዳውድ 2365] አልባኒ ሶሂህ ብለውታል
👇👇👇
@tewihd
ከረመዷን ሐዲሶች
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ የረመዷንን ወር በአላህ አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አገኛለው ብሎ የፆመ ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎች ይማሩለታል። (ቡኻሪ ፥ 37 / ሙስሊም ፥ 759)
👇👇👇
@tewihd
ነስር ጾምን ያስፈጥራልን?
^^ ነስር ብዙ ቢሆንም እንኳ ፆምን አያስፈጥርም። ምክንያቱም ለባለቤቱ ያለምርጫው ነው የሚፈሰውና። ^^
ሼይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አልዑሰይሚን
ምንጭ ፦ ፈታዋ አርካኒልኢስላም ወልዐቂዳህ ፥ ገጽ 612
@tewihd
▪️ትኩረት ይሰጠው
👉ጾመኛ ሆነን ዉዱእ እያደረግን ውሃን ወደአፍንጫችን በምንስብበት ሰአት በጣም ከመሳብ እንጠነቀቅ።
°
👉ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ስላሉ ነው ፦ [ (ዉዱእ ላይ) ውሃን ወደአፍንጫህ በምትስብ ሰአት በደንብ አድርገህ ሳብ ፤ ጾመኛ የሆንክ ጊዜ ሲቀር። ] (አቡዳውድ ፥ 142 / ቲርሚዚይ ፥ 38 ላይ የዘገቡት እና ሸይኽ አልባኒ አልሚሽካት ፥ 405 ላይ ሶሒህ ያሉት ሐዲስ ነው።)
__👇👇
@tewihd
🏝 አስደናቂው የሰልማነል ፋሪሲ 🏝
. የህይወት ታሪክ ክፍል~ሁለት
📚እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ:-
📚 አብደሏህ ኢብኑ አባስ ሰልማነል ፋሪሲ ታሪኩን እንዲህ ሲል ነገረኝ ብሎ ይጀምራል።
💫 እኔ ፋርሳዊ ነኝ አስበሃን ከምትባል የኢራን ከተማ (ጀይ) ተብላ ከምትጠራ መንደር ነዋሪዎች ነበርኩኝ።
👉አባቴም የመንደሩዋ ትልቅ ሰው ነበር እኔም አባቴ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ የተወደድኩኝ ነበርኩኝ።
◉አባቴ እኔን በጣም ከመውደዱ የተነሳ እኔ ከቤት ወጥቼ አንድ ነገር እንዳልሆንበት ስለሚፈራ እቤት ውስጥ ብቻ እንድቀመጥ አሰረኝ።
◉ልክ ልጃ ገረድ የሆኑ ሴቶች ከቤት እንደማይወጡት ሁሉ እኔንም አባቴ ከቤት እንዳልወጣ አደረገኝ ። አባቴም እሳትን ያመልክ ስለ ነበር እኔም የአባቴን እምነት በመከተል ያንን እሳት አመልክ ነበር።
◉እሳትን በማምለክም በጣም ብዙ ጊዜ ቆይቻለሁ።
◉ያንን የምናመልከውን እሳት እንዳይጠፋ እቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ። ለአባቴም የእርሻ ስራ የሚያሰራበት ትልቅ የሆነ የእርሻ ቦታ ነበረው።
◉ሁሌም እየሄደ እርሻውን ይከታተል ነበር።
◉ከእለታት አንድ ቀን ግን አባቴ የሆነ ግንባታን በማስገንባት ወደ እርሻው ቦታ መሄድ ሳይችል በመቅረቱ :-
👉ልጄ ሆይ ዛሬ ወደ እርሻው ቦታ እኔ መሄድ ሰላልቻልኩኝ አንተ ሂድና ተመልከት አለኝ።ከሄድኩም በኋላ ምን መስራት እንዳለብኝ ነግሮኝ ወደ እርሻችን ቦታ መሄድ ጀመርኩኝ።
◉እየሄድኩኝ ሳለሁ ግን የሆነ የቤተክርስቲያን ድምፅ ሰማሁኝ በሰማሁት ድምፅ በጣም ስለተማረኩኝ ወደ ስፍራው ተጠጋሁ ቦታው ላይ ስደርስ ሰዎች ስግደትን እያከናወኑ ነበር።ነገር ግን እኔ ከቤት ወጥቼ ስለ ማላውቅ ስለ ሰዎች እምነት መለያየት አላውቅም ነበር።
👉ወደ ቤተክርስቲያኑም በር ላይ ደርሼ ወደ ውስጥ ገባሁኝ ። ከገባሁ በኋላ ደግሞ የተመለከትኩት ነገር በጣም አስገረመኝ።
◉ስግደታቸውም በጣም አስደሰተኝ ልቤም ወደዚህ እምነት አዘነበለ ወደድኩትም ለእራሴም ይህ ሐይማኖት እኔና ቤተሰቦቼ ከምንከተለው ሐይማኖት የተሻለ ነው አልኩኝ።
◉ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስም እዚያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ቆይቼ ወደ ቤት ልሄድ ስል የእዚህ ሐይማኖታቹ መነሻው ከየት ነው ብዬ ጠየኳቸው ? እነሱም(ሶሪያ) እንደሆነ ነግረውኝ ከእዚያም ወደ አባቴ ቤት ተመለስኩኝ አባቴ ግን ከእርሻው ቦታ ቶሎ ስላልተመለስኩኝ እኔን እየፈለገኝ ነበርና እኔም እቤት ስደርስ አባቴ ልጄ ምን ሆነህ ነው ለምንድነው ወደ እርሻው ቦታ ያልሄድከው አለኝ? አባቴ እኔ ወደ እርሻችን ቦታ እየሄድኩኝ ሳለሁ መንገድ ላይ በጣም የሚማርክ ድምፅ ሰማሁኝ በሰማሁት ድምፅ በጣም ተማርኬ ወደ እርሻችን ቦታ ሳልሄድ እስከ አሁን ቆየሁኝ አልኩት ።
👉አባቴም ልጄ ሆይ አሁን አንተ የተመለከትከው ሐይማኖት ላይ ምንም መልካም ነገር የለውም አለኝ። አባቴ ለሚያመልከው እምነት ወገንተኝነት ያዘው።
◉ልጄ አንተ ያለህበት አያት ቅድመ አያቶችህ የነበሩበት እምነት አሁን እዚያ ከተመለከትከው እምነት የተሻለ ነው አለኝ።
👉እኔም አልኩት አባቴ በፍፁም አይሻልም የእነሱ እምነት ከእኛ እምነት የተሻለ ነው አልኩት ያን ጊዜ አባቴ ፈራኝና ሁለት እግሮቼን በሰንሰለት አስሮ ከቤት እንዳልወጣ አደረገኝ ።
◉እኔ ግን የቤት እስረኛ ብሆንም ባየሁት የእውነት ጭላንጭል ልቤ ስለተማረከ እስረኛ ሆኜ መቀመጥ ግን አልቻልኩም።
👉ወደ ክርስቲያኖች ዘንድ መልዕክተኛን ላኩኝ የሶሪያ ነጋዴዎች እናንተ ዘንድ ከመጡ አሳውቁኝ አልኳቸው።
◉ከጊዜያት በኋላ የሶሪያ ነጋዴዎች እንደመጡ መልዕክት ልከው ነገሩኝ።
◉ለመልዕክተኛውም አልኩት ነጋዴዎቹ የሚሸጡትን ሸጠው የሚገዙትን ገዝተው ጨርሰው ወደ ሀገራቸው መመለስን ሲፈልጉ አሳውቁኝ አልኳቸው።
◉ነጋዴዎቹም ጨርሰው ሊመለሱ እንደሆነ አሳወቁኝ ያኔ እግሮቼ ላይ የታሰረውን የብረት ሰንሰለት አውልቄ ጣልኩት ከቤተሰቦቼ ተደብቄ ከእነዚያ ነጋዴዎች ጋር ተገናኝቼ ወደ ሶሪያ ጉዞ ጀመርን።
◉ልክ ሶሪያ እንደደረስን ለነጋዴዎቹ አልኳቸው እዚህ ሀገር ላይ በክርስትና ሐይማኖት ላይ ከሁሉም በእውቀት የሚሻለው ማነው ብዬ ጠየኳቸው ?
👉እነሱም እዚህ ቤተክርሲቲያኑዋ ውሰጥ ያሉት ጳጳስ ናቸው አሉኝ።
◉ወደ ጳጳሱም ሄጄ አባቴ ሆይ እኔ ይህንን የክርስትና ሐይማኖት ወድጄዋለሁ እኔ ከእርሶ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ እኔ እዚሁ ቤተክርስቲያን እርሶንም እያገለገልኩኝ ከእርሶም ሐይማኖቱን ልማር ከእርሶም ጋር ልፀልይ ብዬ ጠየኳቸው? እሳቸውም ፍቃደኝነታቸውን ገልፀውልኝ ገባሁኝ የተወሰኑ ጊዜያቶችንም አብረን ቆየን።
◉ነገር ግን........
ክፍል ሶስት ይቀጥላል።
ቀጣይ ትምህሮቶች ለመከታተል
👌 group join በማድረግ ለሁሉም ወዳጅ ዘመድ ያስተላልፉ።
🖥የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
/channel/Islam_lslamm
ቻናል ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
@tewihd
▪️ተራዊሕ እና leyil ላይ አንዘናጋ
👉በረመዷን የሌሊት ሶላትን መስገድ ትልቅ የሆነ ትሩፋት አለው። ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ የረመዷንን ወር በአላህ አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አገኛለው ብሎ በመስገድ የቆመ ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎች ይማሩለታል ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ)
°
👉የረመዷንን ወር መቆም የመጀመሪያውን ሌሊትም የመጨረሻውንም ሌሊት ያካትታል። በመሆኑም ተራዊሕን መስገድ ረመዷንን ከመቆም ውስጥ ነው። ስለዚህም እነዚህን በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ማሳለፍ የለብንም።
__👇👇
@tewihd
🔔 የማንቂያ ደወል!
የረመዳን ቀናት እየተቆጠሩ ሲያልፉ ምንኛ ይፈጥናሉ!
ከረመዳን 1,2,3..12 ቀናት ሲያልፉ በጣም ይፈጥናሉ!!
የረመዳን ወቅት በመልካም ስራ የምንሽቀዳደምበት ወቅት ነው።
መዘናጋት በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ የተለመደ ክስተት ቢሆንም፤ መዘናጋታችን በአጨዳ ወቅት ከሆነ ግን ኪሳራው ከባድ ነውና እንጠንቀቅ!!
በጥሩ ሁኔታ አልፎ ከሆነ አሻሽለን መልካም ስራን እንጨምር፤ በሚገባ ካልጠቀምንበትም ጉድለታችንንም አናሟላ፤ አናካክስ!
በኢባዳ ለመትጋት ብርታቱ እንዲሆነን ይህ የትርፍ ወር የተቆጠሩ ጥቂት ቀናቶች ብቻ መሆኑን አንርሳ!
«أياما معدودات» البقرة 184
«የተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)» አልበቀራህ 184
___👇👇
@tewihd
❪ለአሏህ እንዴት አድርገህ ነው ሃጃህን (ጉዳይህን) ምትጠይቀው❫
❪جاءتْ أمُّ سُلَيْمٍ إلى النبي ﷺ ، فقالت : يا رسول الله، عَلِّمْنِي كلماتٍ أَدْعُو بِهِنَّ، قال: تُسَبِّحينَ اللَّهَ عز وجل عَشْرًا، وَتَحْمَدِينَهُ عَشْرًا، وَتُكَبِّرِينَهُ عَشْرًا، ثمَّ سَلِي حاجتكِ، فإِنَّهُ يقول: قَدْ فَعَلْتُ، قَدْ فَعَلْتُ
ኡሙ ሱለይም ወደ ነብዩ ﷺ መጣችና እንዲህ አለቻቸው « እርሶ የአሏህ መልእክተኛ አሏህን የምለምንበትን ቃላቶችን አስተምረኝ አለቻቸው» እርሳቸውም «ሱብሃነሏህ አስር ግዜ ፣ አልሐምዱሊሃ አስር ግዜ አሏሁ አክበር አስር ግዜ ትያለሽ ከዚያም ጉዳይሽን ጠይቂው የዛኔ አሏህ «ተቀብያለው ተቀብያለው ይላል» አሏት።
📁 صححه الألباني في صحيح الترغيب (1566)
📲 @tewihd
ቁርአንን ይዞ ሶላተ ተራዊህን መስገድ እንዴት ይታያል ?
አሏህ በቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል፦
[ٰ وَقُومُوا۟ لِلَّهِ قَٰنِتِينَ ]
[ፈሪዎች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ]
ሶላት ላይ ጥቅም የሌላት እንቅስቃሴ ባጠቃላይ ተቀባይነት የላትም ፡ ሱንና እያመለጣቸው መሆኑን ባለማወቅ አንዳንድ ሰጋጆች ቁርዐንን ሶላት ለይ ይከፍታሉ ፡ ከነዚህም ሱንናዎች ውስጥ ወደ ሱጁድ ቦታ መመልከት ፣ እጅን ደረት ላይ ማድረግ እነዚህና የመሳሰሉትን ሱንናዎች ቁርአንን በማስገባትና በማስወጣት እራሳቸውን በመወጠር ያልፏቸዋል፡ ከፊሎችም ስልካቸውን በማውጣት የቁኑትን ዱአ የሚቀዱም አሉ፡ እንዲሁም አስፈላጊ ያልሆነ እንቅስቃሴ ሶላት ላይ ይህ ባጠቃላይ አሏህ ቁርዐኑ ላይ ያዘዘውን ይቃረናሉ፡፡
#በብዙ ጎኖች ሲታይ ቁርአንን ይዞ በሶላተ ተራዊህ ላይ መከታተል ሱናን ተከትሎ የመጣ አይደለም ፡ ከነዚህም ውስጥ ብናይ
-እጅን ደረት ላይ ከማስቀመጥ ይከለክላል
-የሱጁድ ማድረጊያ ቦታን ከማየት ይከለክላል
-ቁርዐኑን በማስቀመጥና በማንሳት እንቅስቃሴ ኹሹዕን ይቀንሳል
-ሰጋጆችንም በእንቅስቃሴ ማጨናነቅ
-የአይን እንቅስቃሴ በማንበብ ላይ ብቻ እንድናደርግ ያደርጋል
ስለዚህ ሶላታችንን በምንሰግድበት ጊዜ ከእንቅስቃሴዎች ተቆጥበን መስገድ ይኖርብናል ፡፡
📚 ዛዱ ሷኢም (55-56)
👇👇👇
@Tewihd
▪️የለይለተል ቀድር ትሩፋቶች
🌙ለይለተል ቀድር ብዙ ትሩፋቶች አሏት። ከነሱም ውስጥ ፦
1.ለሰዎች ልጆች መመሪያ የሆነውን እና በዱንያም ይሁን በአኺራቸው እድለኝነት የሚያገኙበት የሆነው ቁርአን የወረደበት ሌሊት ነው። ①
°
2.መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ሆነች ምን አሳወቀህ? በማለት በጥያቄ መልክ መምጣቱ ያላትን ትልቅ ደረጃ ያመላክታል።
°
3.እሷም ከአንድሺ ወር በላጭ ናት። ይህም ማለት በሷ ውስጥ የሚሰራ ዒባዳ ከአንድሺ ወር በላይ የሚሰራ ዒባዳ ትበልጣለች።
°
4.መላኢካዎቹ እንደዚሁም "ሩሕ" ጂብሪል በጌታቸው ትእዛዝ ይወርዳሉ። እነሱ ደግሞ መልካም ነገርን ፣ በረካን እና እዝነትን እንጂ ይዘው አይወርዱም።
°
5.እሷም ሰላም ነች። ይህም የሆነው በዛች ሌሊት ውስጥ ባሪያው በሚሰራው መልካም ስራ ምክንያት አላህ ከእሳት እና ከቅጣት ነፃ የሚያወጣቸው ሰዎች ብዙ ስለሚሆኑ ነው። ጊዜዋም ፈጅር እስከሚወጣ ድረስ ነው።
°
6.አሏሁ - ተዓላ - እሷን ብቻ አስመልክቶ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የሚቀራ አንድ ሙሉ ምዕራፍ አውርዷል።
°
7.ከትሩፋቶቿ ውስጥ ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ለይለተል ቀድርን በአላህ አምኖ እንዲሁም ምንዳውን ከአላህ ፈልጎ የቆመ ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎቹ ይማሩለታል። ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ ፤ ቡኻሪ ፥ 2017/ ሙስሊም ፥ 1169)
_
①." በጥቅሉ ሲታይ የቁርአን አወራረድ ሁኔታ ሁለት አይነት ነው። አንደኛው አወራረድ ሙሉው በአንድ ጊዜ በለይለተል ቀድር ላይ መውረዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ በ23አመት ውስጥ መውረዱ ነው። "
_👇👇👇
@tewihd
ኢዕቲካፍ
|> ኢዕቲካፍ ማለት በቋንቋ ደረጃ፦ በአንድ መልካም ወይም መጥፎ ነገር ላይ መዘውተር እና ነፍስን በእርሱ ላይ መገደብ ማለት ነው።
|> እንደ ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ፦ አንድ ሰው በተነጠለ (መስፈርቱን በጠበቀ መልኩ) ወደ አሏህ መቃረብን ፈልጎ መስጂድ ላይ የሚያደርገው ማዘውተር "ዒዕቲካፍ" ይባላል።
ዒዕቲካፍ ብይኑ ሱንናህ ነው። ይህ ድርጊት ከረመዷን የመጨረሻ አስርቱ ቀናቶች ላይ ለይለተል ቀድር በመኖሯ ምክንያት ይበልጥ የጠነከረ ሱንናህ ይሆናል።
|> የዒዕቲካፍ የጊዜ ገደብ
አንድ ሰው ዒዕቲካፍን አደርጋለሁ ብሎ የተሣለ ከሆነ በተሣለበት ጊዜ መፈፀም ይኖርበታል። ከዛ ውጪ ባለው በተፈቀደው 'ልቅ' በሆነው የዒዕቲካፍ ድርጊት እስከዚህ ጊዜ የሚባል የጊዜ ገደብ የለውም። ሰለሆነም መስጂድ ላይ የተወሰነ ጊዜያትንም ቢያዘወትር ኢዕቲካፍ ይሰኛል።
|> የዒዕቲካፍ ማዕዘናት
- ኒያህ
- መስጂድ ውስጥ መዘውተር
- ዒዕቲካፍ አድራጊው መገኘት
- ዒዕቲካፍ የሚደረግበት ቦታ(መስጂድ) መሆን አለባቸው።
|> ዒዕቲካፍ ለማድረግ ፆመኛ መሆን መስፈርት ነውን?
በዚህ ነጥብ ላይ የእውቀት ባለቤቶች ልዩነት ሲኖራቸው ከፊሎች ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት አይሆንም ሲሉ ሌለኞቹ ደግሞ ፆምን መስፈርት አድርገዋል።
- ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ አንሁ
" በጃሂሊያ ዘመን በለሊቱ ክፍል መስጂደል ሃረም ላይ ዒዕቲካፍን ሊያደርግ ተስሎ ነብዩ ﷺ "ስለትህን ሙላ" ብለውታል። ቡኻሪይ እና ሙስሊም
-ይህንን ሃዲስ በመያዝ ፆም በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ስለማይኖር ዒዕቲካፍ ለሚባለው ድርጊት ፆም እንደመስፈርት አይወሰድም ብለዋል።
-ነብዩﷺ አስርቱን የመጀመሪያ የሸዋል ቀናቶች ዒዕቲካፍ አድርገው ነበር።[ቡኻሪ እና ሙስሊም]
ከነዚህ አስርት ቀናቶች መካከል አንዱ ዒድ ሲሆን በዒድ ፆም መፆም የተከለከለ ነው። ስለሆነም ይህ ሃዲስም የሚያመላክተው ለዒዕቲካፍ ፆም መስፈርት አለመሆኑ ነው። ብለዋል።
-ሌለኞቹ፦ ዓዒሻ አሏህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ ብላለች "ዒዕቲካፍ ለሚያደርግ አካል ሱንናው ፆመኛ መሆኑ ነው።" [አቡዳውድ]
-አንድ ሶሃብይ "ሱንናው እንዲህ ነው..." ካለ ይህ ንግግሩ ወደ ነብዩﷺ የተጠጋ ንግግር(የነብዩ ንግግር) ተደርጎ ይወሰዳል። ብለዋል።
-ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላል፦ አሏህ ዒዕቲካፍን ከፆም ጋር አቆራኝቶ እንጂ አልጠቀሰም፤ ነብዩም ከፆም ጋር እንጂ አልፈፀሙትም።
[ዛዱል መዓድ 2/87]
ቃዲ ዒያድ እንዲህ ይላል፦ "ይህ ንግግር የአብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤት ንግግር ሲሆን፤ አመዛኙና ትክክለኛውም እርሱ ነው።"[ነስቡራያህ 2/489] ሲል ፆም ለዒዕቲካፍ መስፈርት መሆኑን አመዝኗል።
ይህን አቋም ኢብን ተይሚያህ፣ ጀሷስ[አህካሙል ቁርዓን1/245] እና ኢብን ዓብድል ሐዲይ ያመዘኑት አቋም ነው።
-ነብዩ የሸዋል የመጀመሪያ አስርት ቀናቶችን ዒዕቲካፍ አድርገዋል ለሚለው የሠጡት ምላሽ
ኢብን ዓብድል ሐዲይ እንዲህ ብለዋል፦
" ነብዩﷺ ያደረጉት ዒዕቲካፍ የመጀመሪያው የፊጥር ቀን (የዒድ ቀን) መሆኑን በግልፅ አልተጠቀሰም(ግልፅ አይደለም)። በሁለተኛው ቀን ሊሆንም ይችላል ዒዕቲካፍ ያደረጉት። እንደውም ይህ ነው ግልፅ ሆኖ ሚታየው።"
[ነስቡ ራያህ2/489]
|> የዒዕቲካፍ ቦታ
አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦
[እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው፡፡]
ዒዕቲካፍ የሚደረግበት መስጂድ የጀመዓ ሶላት የሚደረግበት መስጂድ መሆኑ የተሻለ እና በላጭ ነው። ከፊሎች እንደ መስፈርት ጠቅሰውታል።
ኢብን ቁዳማህ እንዲህ ይላል፦
" ይህ እንደመስፈርት የተቀመጠው የጀመዓ ሶላት ዋጂብ(ግዴታ) በመሆኗ ነው። አንድ ሰው በጀመዓ ማይሰገድበት መስጂድ ዒዕቲካፍ በማድረጉ ሁለት ነገሮችን ያጣል፤ አንደኛው ግድ የሆነችውን የጀመዓ ሶላት መተው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መቆጠብ እየቻለ ካለበት መስጂድ ጀመዓ ሶላት ወደ ሚሰገድበት መስጂድ በመውጣት ዒዕቲካፍ ካደረገበት ቦታ መውጣትን ሊደጋግም ነው። ይህ ደግሞ ኢዕቲካፍን ያፈርሳል።"
[አል መጝኒ 3/187]
|> ኢዕቲካፍ አድራጊ መቼ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው(መስጂድ) ይገባል? መቼስ ኢዕቲካፉን ጨርሶ ይወጣል?
- አብዝሃኛዎቹ የእውቀት ባለቤቶች ኢዕቲካፍ አድራጊ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው የሚገባው ሃያኛው ቀን ፀሃይ ስትጠልቅ (የሃያ አንደኛው ለሊት መጀመሪያ ላይ) ነው። ከኢዕቲካፉ ቦታ የሚወጣው ደግሞ የመጨረሻው የረመዷን ቀን ፀሃይ ከጠለቀች በኋላ ነው። ብለዋል።
ሌለኞቹ ደግሞ፦
- ሃያ አንደኛው ንጋት ላይ ከፈጅር በኋላ ወደ ኢዕቲካፍ ማድረጊያው ገብቶ የዒድ ንጋት ላይ ከኢዕቲካፍ ማድረጊያው ይወጣል። ብለዋል።
|> ኢዕቲካፍ አድራጊን የሚነጥሉ ስራዎች
የኢዕቲካፍ ዋና አላማው ነፍስን ወደ አሏህ በሚያቃርቡ ስራዎች ማሰር እና ማጠር ሲሆን፤ ኢዕቲካፍ በሚያደርግበት መስጂድ ውስጥ ባሉ መልካም ስራዎች[ሶላት፣ ዚክር፣ ቂርአት..] ሊሣተፍ ይገባል። ሌሎች የእውቀት ባለቤች ከመስጂድ ውጪ ያሉ አምልኮዎችን መስራት [የታመመን መጠየቅ፣ የሟችን ሬሳ መሸኘት ..] እንደሚችል ጠቁመዋል።
|> ኢዕቲካፍ አድራጊ ሊፈፅማቸው የተቻሉ ድርጊቶች
- ኢዕቲካፍ አድራጊ ለመፀዳዳት(ሽንት ቤት) መሄድ፣ የሚመገበውን ምግብ ሚያመጣለት ከሌለም ለማምጣት መውጣት ይችላል።
- ውዱእ ለማድረግ እና ገላን ለመታጠብ መውጣት
- ፀጉሩን ማበጠርም ሆነ መላጨት፣ ጥፍሩን መቁረጥ
- የተቻለ ከሆነ ለብቻው የሆነን ቦታ መስጂድ ውስጥ ማዘጋጀት
- ያለ እርሱ ሊከወኑ ማይችሉ ግድ የሆኑ የግዢ ወይም የሽያጭ ግብይቶችን መፈፀም
- ኢማም አን ነወዊይ እንዲህ ይላሉ፦ " ኢዕቲካፍ አድራጊ ማግባትም ሆነ ሌላን መዳር ይችላል።
- ሽቶ መቀባት
- በአስገዳጅ ሁኔታ ለምስክርነት ከተፈለገ ከኢእቲካፉ ቦታ መውጣት
- ልጅ የምታጠባ እናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። ሃይድ ላይ ያለችም እንዲሁ(በነጥቡ ላይ የሃሣብ ልዩነት ያለው ቢሆንም) ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች።
|> ኢዕቲካፍን የሚያፈርሱ ተግባሮች
- 'አውቆ' ግንኙነት ማድረግ
- ረስቶ ከሆነ ኢዕቲካፉ አይበላሽም። ምንም የለበትም።
- የዘር ፈሳሽን ማውጣት
- ኢዕቲካፉን ለማቋረጥ ቁርጥ የሆነ ኒያን ማስገኘት...
👇👇👇
@tewihd
የምሽት አዝካር
ﺃﻣﺴﻴﻨﺎ ﻭﺃﻣﺴﻰ ﺍﻟﻤﻠﻚ ﻟﻠﻪ ﻭﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻻ ﺷﺮﻳﻚ ﻟﻪ. ﻟﻪ ﺍﻟﻤﻠﻚ ﻭﺍﻟﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻭﻫﻮ ﻋﻠﻰ ﻛﻞ ﺷﻲﺀ ﻗﺪﻳﺮ. ﺭﺏ ﺃﺳﺎﻟﻚ ﺧﻴﺮ ﻣﺎ ﻓﻲ ﻫﺬﻩ ﺍﻟﻠﻴﻠﺔ ﻭﺧﻴﺮ ﻣﺎ ﺑﻌﺪﻫﺎ. ﻭﺃﻋﻮﺫ ﺑﻚ ﻣﻦ ﺷﺮ ﻫﺬﻩ ﺍﻟﻠﻴﻠﺔ ﻭﺷﺮ ﻣﺎ ﺑﻌﺪﻫﺎ . ﺭﺏ ﺃﻋﻮﺫ ﺑﻚ ﻣﻦ ﺍﻟﻜﺴﻞ ﻭﺳﻮﺀ ﺍﻟﻜﺒﺮ . ﺭﺏ ﺃﻋﻮﺫ ﺑﻚ ﻣﻦ ﻋﺬﺍﺏ ﻓﻲ ﺍﻟﻨﺎﺭ. ﻭﻋﺬﺍﺏ ﻓﻲ ﺍﻟﻘﺒﺮ. ﻭﺇﺫﺍ ﺃﺻﺒﺢ ﻗﺎﻝ ﺫﻟﻚ ﺃﻳﻀﺎ ”: ﺃﺻﺒﺤﻨﺎ ﻭﺃﺻﺒﺢ ﺍﻟﻤﻠﻚ ﻟﻠﻪ ”
ትርጉም ⇩
“ምሽት ላይ ለመድረስ በቅተናል፡፡በዚህ ሰዓት ሉአላዊነት የለዓማት ጌታ የሆነው የአላህ ነው፡፡ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፤ አጋር የለውም፡፡ ሉአላዊነት የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ጌታዬ ሆይ! የዚህን ምሽትና (የቀኑን) መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ምሽትና ከቀጣዩ (ከቀኑ) ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ከስንፍናና መጥፎ ከሆነ እርጅና (ከመጃጀት) በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ! ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
share & Join @tewihd
🏝 አስደናቂው የሰልማነል ፋሪሲ 🏝
. የህይወት ታሪክ ክፍል~አራት
📚እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ:-
🕳 ነገር ግን እርሶም የሞት አፋፍ ላይ ደርሰዋል እርሶስ ወደ ማነው አደራ የሚሉኝ ምንድን ነው የሚመክሩኝ ብዬ ጠየኳቸው።?
💫 ልጄ ሆይ በጌታዬ እምላለሁ አሁን በእዚህ ዘመን እኔና ባልደረቦቼ በነበርንበት ሐይማኖት ላይ አለ ብዬ እሱ ጋር ሂድ የምልህ አንድም ሰው አላውቅም። ነገር ግን አንተ ነብይ የሚላክበት ዘመን ላይ ቀርበሃል ያ የሚላከውም ነብይ በኢብራሂም( አብረሃም)መንገድ ላይ ነው የሚላከው።
🎁 ግን ይህ ነብይ የሚወጣው ከአረብ ምድር ነው ይህም ነብይ የትውልድ ሀገሩን ትቶ ይሰደዳል ያቺም የሚሰደድባት ምድር ሁለት ጥቋቁር ድንጋዮችና ሁለት ኮረብታማ ቦታዎች ያሉባት በኮረብታዎቹም መካከል የቴምር ዛፎች የሚበዙባት የሆነች ከተማ ናት ። በዚህም ነብይ ላይ የነብይነት ምልክቶች አሉበት። ምልክቶቹም ከማንም የሚደበቁ አይደሉም ። ሁሉም ሰው ያውቃቸዋል ከምልክቶቹም አንዱ ስጦታ የተሰጠውን ይበላል ። ዘካ (ምፅዋት) ግን አይበላም።
📜 ሌላኛው ምልክቱ በሁለት ትከሻዎቹ መካከል የነብይነት ማህተም አለ አንተ ወደዚያች ከተማ መሄድ ከቻልክ ሂድና እሱን ተገናኘው ። እኔ የምመክርህ ይህንን ነው ብለው ምክራቸውን አስተላለፋልኝ።
🕳 እኚህ ታላቅ ሰው ከሞቱ በኋላ አሙሪያ (የቦታ ስም)ላይ ፈጣሪዬ ያሻውን ያህል ጊዜ እንደቆየሁኝ (ከልብ) ከሚባል ጎሳ የሆኑ ነጋዴዎች ወደ አሙሪያ (የቦታ ስም) ምድር መጡ። ከእነሱም ጋር ተገናኘሁና እንዲህ አልኩዋቸው። እባካችሁ ከቻላቹ ከእናንተ ጋር ወደ አረብ ምድር ብትወስዱኝ እኔ ደግሞ የተወሰኑ ከብቶች አሉኝ እነሱን እሰጣቹኋለሁ አልኳቸው።
👉እነሱም በሀሳቤ ተስማምተው ወደ አረብ ምድር አብሬያቸው ጉዞ ጀመርን። ነገር ግን እየተጓዝን ሳለ ዋዲል ቁራ (የሚባል አከባቢ) ስንደርስ ግን ቃላቸውን አጠፉብኝና ለአንድ አይሁዳዊ ሰው ባሪያ(አገልጋይ) አድርገው ሸጡኝ ። ነገር ግን ዋዲል ቁራ የብዙ ቴምሮች ባለቤት መሆኑዋን ስመለከታት ያቺ ባልደረባዬ የነገረኝ ሀገር ትሆን እንዴ ብዬ ገመትኩኝ።
🔴 ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ግን አልቻልኩም። እኔን የገዛኝ ሰው ዘንድ ባለሁበት መዲና ከምትባል ሀገር በኑ ቁረይዟ (ከሚባል ጎሳ) የአለቃዬ የአጎቱ ልጅ መጣ ። አለቃዬም ለአጎቱ ልጅ ሸጠኝ እሱም መዲና (የቦታ ስም) ተብላ ወደ ምትጠራ ከተማ ይዞኝ ሄደ ልክ መዲና ከተማ ደርሰን ከተማዋን ስመለከታት ያ አስተማሪዬ ነግሮኝ የነበረችዋ ሀገር እሷ መሆኑዋን አወቅኩኝ። ብዙም ሳልቆይ ያ አስተማሪዬ ይወጣል ያለኝ ነብይ ከመካ መውጣታቸውን ሰማሁኝ ።
🕋 መካ ላይም የተወሰኑ አመታቶችን ቆዩ። እኔ ለአለቃዬ ስራን በመስራት ስለምወጠር ብዙም ወሬዎችን አልሰማም ነበር።
💫ከእለታት አንድ ቀን ግን እኔ የቴምር ዛፍ ላይ ሆኜ ስራ እየሰራሁ ሳለሁ አለቃዬ ደግሞ ከቴምሩ ዛፍ ስር ተቀምጦ ሳለ አንድ የአጎቱ ልጅ መጣ። አጎቴ ሆይ በኑ ቀይለ (አንሳሮችን) ፈጣሪ ይጋደላቸው ዛሬ እኮ እነሱ ቁባ ላይ ስብሰባ ላይ ናቸው። ከመካከላቸውም አንድ ከመካ የመጣ ሰው አለ ያንንም ሰው ነብይ ነው ብለው ይሞግታሉ። ብሎ ሲነግረው ሳዳምጥ በአለቃዬ ላይ የምወድቅ ያህል ተንቀጠቀጥኩኝ።
🌲በፍጥነት ከዛፉ ላይ ወርጄ ለሰውዬው ምንድን ነው ያልከው ስለ ምንድን ነው የምታወራው ብዬ ስጠይቀው? አለቃዬ ከተቀመጠበት በፍጥነት በመነሳት አንተ ይህን ሰው የት ታውቀዋለክ? ሂድ አርፈህ ስራህን ስራ ብሎ በጥፊ መታኝ።
💫እኔም አይ ዝም ብዬ ነው እንደው ነገሩን ለማረጋገጥ ያህል ነው ብዬ ወደ ስራዬ ተመለስኩኝ።
. ክፍል አምስት ይቀጥላል።
┈┈┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈┈┈
ቀጣይ ትምህሮቶች ለመከታተል ከስር የተቀመጡ አስፈንጣሪዎች ይጫኑ።
👌 ግሩፖች join በማድረግ ለሁሉም ወዳጅ ዘመድ ያስተላልፉ።
🖥የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
@Islam_lslamm
channel
👇🏾👇🏾👇🏾
@tewihd
አስደናቂው የሰልማነል ፋሪሲ
. የህይወት ታሪክ ክፍል~ሶስት
📚እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ:-
👉ነገር ግን ጳጳሱ ጥሩ ሰው አልነበሩም ሰዎችን ለድሆች ምፅዋትን እንዲያደርጉ ያዙዋቸው ነበር ። ያንን ምፅዋት እሳቸው ዘንድ ካመጡት በኋላ ግን ለራሳቸው ያስቀሩት ነበር ።ለማንም አይሰጡትም የሚመጣውንም ምፅዋት እያጠራቀሙ ሰባት እንስራ ሙሉ ወርቅና ብርን ሰበሰቡ የዚህን ሰው ክፋት በጣም ጠላሁት ነገር ግን ይህ ሰው ብዙም ሳይቆይ ሞተ።
👉🎟 ክርስቲያኖች እሱን ለመቅበር ተሰባሰቡ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲህ አልኩዋቸው፦
🎟 ይህ ጳጳስ በጣም ክፉ ሰው ነበር ገፅታውን እንደምታዩት አይደለም እናንተን በምፅዋት ያዛችኋል እናንተ ሰብስባችሁ ስታመጡለት እሱ ግን ለእራሱ ያጠራቅመዋል እንጂ ለድሆች አይሰጠውም ነበር ብዬ
ነገርኳቸው ።
👉 አንተ እንዴት አወቅክ ምን አሳወቀህ አሉኝ ?በቃ ካላመናቹ ኑ ወደ ማከማቻው ላሳያቹ ብዬ ቦታውን አሳየሁዋቸው ሰባት እንስራ የወርቅና የብር ማዕድን ከማከማቻው ውስጥ አገኙ ።
ከእዚያም በኋላ በጣም ተበሳጩ። ይህን ሰውማ ምድር ላይ አንቀብረውም ብለው ከሞተ በኋላ በድንጋይ ወገሩት።
👉 ከእዚያ በኋላ ሌላ ጻጻስን ፈልገው አመጡ ነገር ግን እንደሳቸው አይነት ጥሩ ሰው ከእዚያ በፊት ተገናኝቼ አላውቅም።
👉 ለገንዘብ የማይንገበገቡና ከሞት በኋላ ስላለው ህይወታቸው ደግሞ የሚጨነቁ ቀንና ሌሊት ፀሎትን የሚያዘወትሩ ሰው ነበሩ። ከእሳቸው በፊት ማንንም ወድጄው የማላውቀውን ውዴታን ወደድኩዋቸው። ከእሳቸው ጋርም ረጅም አመታትን ቆየሁኝ።
ከእዚያ ሊሞቱ ሲሉ እንዲህ ስል ጠየኳቸው።
አባቴ ሆይ እኔ ከእርሶ ጋር ረጅም አመታትን ቆይቻለሁ በጣም ወድጄዎታለሁ ነገር ግን የፈጣሪ ትዕዛዝ ሆኖ ሞት አፈፍ ላይ ደርሰዋል ታድያ ወደ ማን ጋር ሄጄ እውቀትን እንድቀስም ነው የምትመክሩኝ አልኳቸው እሳቸውም እንዲህ አሉኝ፦
👉ልጄ ሆይ እኔ በዚህ ዘመን በክርስትና ሐይማኖት ላይ እውቀት አለው የምለው አንድም ሰው የለም።
🛎 ሰዎች እኮ ጠፍተዋል እምነታቸውን ቀይረዋል የነበሩበትን እምነት ትተውታል አንድ የማውቀው ሰው ግን አለ ያም ሰው (መውሲል )የሚባል ሀገር ነው የሚገኘው።
💫 እኔ እሱን ነው የማውቀው እሱ በሐይማኖቱ ላይ ነው ያለው እሱ ሐይማኖቱን አልቀየረም እሱ ጋር ሂድ እሱ ዘንድ ይሻልሃል ብለውኝ ከእዚህ አለም በሞት ተሰናበቱ የቀብር ስነ-ስራአታቸው እንዳለቀ እኔም መውሲል ወደ ተባለው ሀገር ጉዞ አቀናሁኝ ።
👉መውሲል ደርሼ ጳጳሱንም አገኘሁዋቸውና እንዲህ ስል ጠየኳቸው፦ አባቴ ሆይ ሶሪያ ላይ የሚገኙት ጳጳስ
ወደ እርሶ ጋር መጥቼ እንድማር አደራ ብለውኝ ነበር እርሶም ሐይማኖቶትን እንዳልቀየሩና እሳቸው በነበሩበት ሐይማኖት ላይ እንደሆኑ ነግረውኝ ነው አልኳዋቸውእሳቸውም እሺ ብለው ተቀበሉኝ ።
💫 ከእሳቸውም ጋር የተወሰነ ጊዜን ቆየሁኝ በጣም መልካም ሰው ሆነውም አገኘሁዋቸው ነገር ግን እሳቸውም ብዙም ሳይቆዩ ሞት አፋፍ ላይ ደረሱ።
💫 ከእዚያም አልኳቸው ባልደረባዎት ወደ እርሶ ልከውኝ ነበር ታድያ እርሶስ ወደ ማን ነው የሚልኩኝ አልኳቸው።
👉 እሳቸውም እንዲህ አሉኝ፦ ልጄ ሆይ እኔ በእዚህ ዘመን ላይ እኔና ባልደረቦቼ በነበርንበት ሐይማኖት ላይ ያለን ሰው አላውቅም አሉኝ።
👉 ግን (ነሲቢን) የሚባል ሀገር ላይ አንድ ጳጳስ አለ ከእሱ ውጪ ሌላን አላውቅም እሱ ጋር እንድትሄድ አደራ እልሃለሁኝ አሉኝ። እኔም ( ነሲቢን) ወደ ተባለው ሀገር ጉዞ አደረኩኝ ። ነሲቢን ደርሼ ጳጳሱን አገኘሁዋቸው ማን እንደላከኝና ለምን እንደመጣሁ ነገርኳዋቸው እሳቸውም ተቀበሉኝ እሳቸውንም ልክ እንደ ጓደኞቻቸው በጥሩ ሁኔታ አገኘሁዋቸው።
👉በጣም ጥሩ ሰው ነበሩ ከእሳቸውም ጋር ጥሩ ጊዜንም አሳለፍኩኝ ። ነገር ግን ብዙም ሳንቆይ ሞት መጣባቸው ሞት አፋፍ ላይ ሲደርሱም እንዲህ ብዬ ጠየኳቸው ፦
👉 አባቴ ሆይ አንዱ ጳጳስ ወደ ሌላው ሌላው ወደ ሌላው እየላኩኝ እርሶ ጋር ደርሻለሁኝ እርሶስ ወደ ማን እንድሄድ ነው የሚመክሩኝ ብዬ ጠየኳቸው።
እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱልኝ፦
👉 ልጄ ሆይ በእዚህ ዘመን በእኛ ሐይማኖት ላይ አለ የምለው አንድም ሰው የለም ነገር ግን[አሙሪያ]የምትባል ሀገር ላይ አንድ ባልደረባችን አለ።
እሱ በእኛ ሐይማኖት ላይ ነው ያለው ከፈለክ ወደ እሱ ሂድ ብለው መከሩኝ ። እሳቸውም ሞተው ከተቀበሩ በኋላ እኔም ጉዞ ወደ አሙሪያ ጀመርኩኝ።
👉 አሙሪያ ደርሼ ጳጳሱንም አገኘሁዋቸው ከየት እንደመጣሁና ለምን እነደመጣሁ ማን እንደላከኝ ታሪኬን አጫወትኳቸው እሳቸውም በጥሩ ሁኔታ ተቀበሉኝ እሳቸውንም ልክ በጓደኞቻቸው እምነት ላይ ሆነው አገኘሁዋቸው።
ከእሳቸውም ጋር የተወሰኑ አመታቶችንም ቆየሁኝ ነገር ግን ሐይማኖቴንም እየተማርኩኝ ጎን ለጎን ስራ መስራትን ጀመርኩኝ።
👉 የተወሰኑ ከብት በግና ፍየሎችንም አፈራሁኝ ከእዚያ የፈጣሪ ትእዛዝ ሆነና ጳጳሱ የሞት አፋፍ ላይ ደረሱ።
👉💫 ከእዚያም በኋላ እንዲህ ብዬ ጠየኳቸው አባቴ ሆይ አንዱ ጳጳስ ወደ ሌላው ሌላውም ወደ ሌላው እየላኩኝ እርሶ ጋር ደርሼ ነበር።
👉 ነገር ግን እርሶም የሞት አፋፍ ላይ ደርሰዋል እርሶስ ወደ ማነው አደራ የሚሉኝ ምንድን ነው የሚመክሩኝ ብዬ ጠየኳቸው።?
. ክፍል አራት ይቀጥላል።
ቀጣይ ትምህሮቶች ለመከታተል ከስር የተቀመጡ አስፈንጣሪዎች ይጫኑ።
ግሩፖች join በማድረግ ለሁሉም ወዳጅ ዘመድ ያስተላልፉ።
የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
/channel/Islam_lslamm
channel
👇👇👇
@tewihd
▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ
🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
👇_👇👇
@tewhid
▪️ካሰብንበት ቀላል ነው
👉በግሌ በረመዷን ቁርአንን በሶስት ቀን ውስጥ የሚያኸትም ሰው አውቃለሁ። ያውም ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብሎ የሚውል ሳይሆን ስራ እያለበት ሁኔታዎችን እያመቻቸ እየቀራ ማለት ነው። ሌላም ከዚህ ባነሰ ቀን ውስጥ የሚቀራ ይኖራል።
°
👉ሰለፎቹ በረመዷን ቁርአንን በሶስት ቀን አኸተሙ ፣ በአንድ ለሊት አኸተሙ ሲባል ብዙ አይግረመን ለማለት ነው። እኛም ካሰብንበት ቀላል ነው ፤ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ላይ የምናጠፋውን ጊዜ ቀንሰን ብንቀራ እንዲሁም ታክሲ ላይ ስንሄድ ፣ በስራ መሀል ትንሽ ክፍተት ስናገኝ ጊዜያችንን በአግባቡ ተጠቅመን ብንቀራ ብዙ ጊዜ ማኽተም እንችላለን።
👇👇👇
@tewihd
▪️በፆም ወቅት አክታን መዋጥ
🔻^^"ወደ አፉ ካልደረሰች አታስፈጥርም ፤ ወደ አፉ ከደረሰች እና ካወጣት ግን ዑለማዎች ሁለት አባባል አላቸው።
1.ታስፈጥራለች ያሉ አሉ። ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር አስጠግተዋት ማለት ነው።
2.አታስፈጥርም ያሉ አሉ። ከምራቅ ጋር አስጠግተዋት ማለት ነው።
°
🔻ለማንኛውም አንድ ሰው አኽታ መዋጥን መተው ይኖርበታል። ከጉሮሮው ስር ወደ አፉ ለመጎተት መሞከር የለበትም። ነገር ግን ፆመኛ ቢሆንም ባይሆንም ወደ አፉ ከደረሰች ያውጣት። ታስፈጥራለች ለማለት ግን ማስረጃ ያስፈልጋል። "^^
________________
👤ሼይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አልዑሰይሚን
📕ምንጭ ፦ ["መጅሙዓል ፈታዋ"(19/355)
➖➖➖➖➖
➖➖➖➖➖
📣ጆይን ፦ @tewihd
🏝 አስደናቂው የሰልማነል ፋሪሲ 🏝
. የሂወት ታሪክ ክፍል~አንድ
📚እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ:-
📚 ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ከአብደላህ ኢብኑ መስዑድ ረዲያሏሁ ዐንሁ በተላለፈው ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
📚 «ما من نبي بعثه الله في أمة قبلي إلا كان له من أمته حواريون وأصحاب، يأخذون بسنته ويقتدون بأمره، ثم إنها تخلف من بعدهم خلوف يقولون ما لا يفعلون، ويفعلون ما لا يؤمرون، فمن جاهدهم بيده؛ فهو مؤمن، ومن جاهدهم بلسانه؛ فهو مؤمن، ومن جاهدهم بقلبه؛ فهو مؤمن، وليس وراء ذلك من الإيمان حبة خردل».
📚 “የእርሱን ፈለግ የሚይዙና ትዕዛዙን የሚከተሉ ረዳቶች እና ባልደረቦችን ከህዝቦቹ አድርጎለት እንጂ አሏህ አንድንም ነብይ ከእኔ በፊት አልላከም፤ ከእዚያም ከእነሱ በኋላ የማይሰሩትን የሚናገሩ ያልታዘዙትን የሚሰሩ ይተካሉ ፡፡ (እነኚህን) ሰዎች በእጁ የታገላቸው ሙእሚን(አማኝ) ነው፤ በምላሱም የታገላቸው ሙእሚን ነው፤ ከእዚህ በኋላ የሰናፍጭ ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን(እምነት) የለም”
👉💫 አላህ በተለያዩ የቁርአን አንቀፆች ነቢዩም ﷺ በብዙ የሃዲስ ጥቅሶች ባልደረቦቻቸውን ያወድሷቸዋል ። ለእኛም ሞዴል የተደረጉ ለእሰልምናም ትልልቅ ጀብዶችን የሰሩ ትልልቅ መሰዋአቶችንም የከፈሉ በሁሉም ነገራቸው አሰተማሪ የሆኑ ባህሪያቸውና ሰነ_ምግባራቸውና ስብዕናቸው ሁሉ ከእነሱ በኋላ ለሚመጣው ትውልድ ትምህርትና ትልቅ ተምሳሌትም ነው። ከእነዚያ ከነቢዩ ሙሀመድ ﷺባልደረቦች ውስጥ
እሰልምና ላይ ትልቅ የሆነ ትውስታ ካላቸውና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው በእውቀትም በሌሎችም ባማሩ ስነ-ምግባሮች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ውሰጥ አንዱ ስለሆነው የነቢዩ ﷺ ባልደረባ ሰልማነል ፉሪሲ ረዲየላሁ ዐንሁ የሂወት ታሪክ ዛሬ ላወጋቹ ወድጃለሁ ::
◉ ሰልማነል ፋሪሲ ማለት:- የትውልድ ሀገሩ ድሮ ፓርሺያ አሁን ኢራን ተብላ ከምትጠራው ሀገር ነበር።
ከሰልማነል ፋሪሲ አሰደናቂ ታሪኮች ውስጥ በዕድሜ ጠገብትነቱ ይጠቀሳል አንድ መቶ ሃያ(120)ዓመታት በሂወት እንደኖረ የታሪክ ሙሁራን ይጠቅሳሉ ።
ሰልማነል ፋሪሲ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሀገሩ ሲነሳ እሳት አምላኪ ከነበሩ ሰዎች መንደር ውስጥ የወጣ ታላቅ ሰው ነበር ።
ከሃገሩም የወጣበት ምክንያት እውነትን ፍለጋ ነበር። እውነትንም ፍለጋ ከሀገር ወደ ሀገር መሰደድ እና ከፍተኛ እንግልትም ደርሶበት ነበር ።ይህም ሲሆን ግን እውነትን ከመፈለግ በፍፁም አልታከተም ነበር ።እውነትን ለማግኘት ከነበረው ትልቅ የሆነ ሞራልና ጠንካራ የሆነ ወኔ ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ሁሉ ትልቅ የሆነ ተምሳሌት ነው ።ጣፋጭ የሆነው የሰልማን ታሪክ እንደቀጠለ ነው።
◉ ሰልማነል ፋሪሲ ከነብዩ ባልደረቦች ውሰጥ በግንባር ቀደምትነት ይወሳል ::
ከእዚህ በፊት ሰለነበሩት መፅሃፍቶች እውቀት የነበረውና በእስልምናም ላይ ትልቅ አዋቂ የሆነ ሰው ነው :: ከሰልማን ባልደረቦች ከነበሩት ውሰጥ ሙአዝ ኢብኑ ጀበል ረዲያሏሁ ዐንሁ የተባለው ሶሃባ ነብዩﷺ እሰልምናን እንዲያሰተምር ወደ የመን ከላኩዋቸው ሳሃባዎች ውሰጥ አንዱ ነው። ሙአዝም ረዲያሏሁ ዐንሁ ሊሞት ሲል ባልደረቦቹ ሙአዝ ሆይ እሰቲ ምከረን ኑዛዜን ስጠን አሉት እሱም እንዲህ ሲል ምክሩን ጀመረላቸው [[ እውቀትና ዕምነት እቦታቸው ላይ ናቸው የፈለጋቸውማ ያገኛቸዋል የፈለጋቸው ይደርስባቸዋል እውነታን የፈለገ እውቀትን የፈለገ ያገኘዋል አያጣውም ብሎ ከመከራቸው በኃላ እውቀትን ከእነዚህ አራት ሰዎች ታማሩ ብሎ አብዷላህ ኢብኑ መሰኡድን አቡ ደርዳን አብደላ ኢብኑ ሰላምን ሰልማነል ፋሪሲን ረዲየላሁ ዐንሁማ ጠቅሶ ከእነዚህ እውቀትን ተማሩ ብሎ ኑዛዜውን አሰተላለፈላቸው]]]
◉ ሰልማን እስልምናን የተቀበለው ነቢዩ ﷺ ከመካ ወደ መዲና ከተሰደዱ በኃላ ነው።
◉ ሰልማን የነቢዩን መላክ እሳቸው ከመላካቸው በፊት ያውቅ ነበር ።
ከእዚያ በፊት የነበሩት የመፃሃፍት አዋቂዎች አንብበው በነገሩት መሰረት ሰለሚመጣው ነብይ እነሱ ዘንድ የነበረውን ትንቢት ነግረውት ስለነበር በጉጉት ይጠባበቅ ነበር።
👉💫ከተነገረው ትንቢት ውሰጥ ይህ ነቢይ ከየት እንደሚወጣና ምን አይነት የነብይነት ምልክት እንዳለው በቂ መረጃ ሰለነበረው ይህንን ምልክት ይዞ ይጠባበቅ ጀመር።
◉ ነገር ግን ከብዙ እንግልትና ችግር በኃላ አላህ አመቻችቶለት በስተመጨረሻ ላይ ሲያስበው ወደ ነበረው ቦታ አደረሰው የሚመኘውንም ነገር አገኘ።
◉ ነገር ግን እውነትን ለመፈለግ ትልቅ የሆነ ትግልን ያደረገ ትልቅ የሆነ መሰዋአትንም የከፈለ ታሪካዊ ጀብድንም የፈፀመ ለሌሎችም እውነትን ለሚፈልጉ ሰዎች በሙሉ ተምሳሌት የሚሆን ታላቅ ሰው ነው።
◉ ታሪኩንም ለመዳሰስ የተፈለገው ከእርሱ ሂወት ትምህርትን እንድንወሰድና እኛም እውነትን በመፈለግ ላይ መታከት እንደሌለብን እንድንረዳ ነው።
◉ ነብዩም ﷺ ሰልማንን እስልምናን ከተቀበለ በኋላ የሂወት ታሪኩን ሲነግራቸው እስቲ ቁምና ለባልደረቦችህ ንገራቸው አሉት።
ይህም ሌሎች ሰዎች ከሰልማን ቁም ነገርን እንዲማሩ ፈልገው ነው።
◉ ሰልማን እስልምናን ከተቀበለ በኃላ እስልምናን ተምሮ ትልቅ አሰተማሪም ለመሆን በቅቷል ።
በእስልምና ታሪክ ከተደረጉ ጦርነቶች ውሰጥ የበድርና የእሁድን ጦርነቶች በባርነት(አገልጋይ) ምክንያት ሳይካፈል ቢቀርም ከዚያ በኋላ የነበሩ ጦርነቶችን ግን ሙሉ በሙሉ ተሳትፎዋል።
በኡመር ኢብኑል ኸጣብ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘመን (መዳኢን) በተባለ ሀገርም አሰተዳዳሪ ሆኖ አገልግሏል ።
ከነቢዩም ﷺ መሞት በኃላ እስልምና ሲስፋፋ ትልቅ አስተዋፆ አደርጎዋል። የሞተውም በኡስማን ኢብኑ አፋን ረዲየላሁ ዐንሁ መንግሰት ዘመን 33ኛው ወይም 36ኛው ዓ .ሂጅራ ነው በሚል የታሪክ ሙሁራን ዘግበዋል።
ሰልማን ታሪኩንም አብዱላህ ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ለተባለው ባልደረባው እንዲህ ሲል ነግሮታል።
እኛም ከእሱ የተላለፈውን ዘገባ መጠነኛ በሆነ ዳሰሳ ለማየት ወደናል።
ታሪኩ ረጅም ቢሆንም ከፋፍለን ለማየት እንሞክራለን።
◉ የሰልማ የሂወት ታሪክ ጅማሬ እንደሚከተለው ነው።
◉ ኢማሙ አህመድ የተባሉት የኢስላም ሊቅ ሙስነድ በሚባለው ኪታባቸው(መፆሐፋቸው) ላይ ዘግበውታል።
◉ አብደላህ ኢብኑ አባስ ሰልማነል ፋሪሲ ረዲየላሁ ዐንሁማ ታሪኩን እንዲህ ሲል ነገረኝ ብሎ ይጀምራል።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
ቀጣይ ትምህሮቶች ለመከታተል
ግሩፖች join በማድረግ ለሁሉም ወዳጅ ዘመድ ያስተላልፉ።
🖥የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
/channel/Islam_lslamm
ቻናል ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
@tewihd
▪️ቁርአንን እናኽትም
🔻ያጀመዓ! ቁርአን በወረደበት በዚህ ታላቅ ወር እንደምንም ብለን አንዴ እንኳን ማኽተም ካቃተን በቁማችን ሞተናል!!
_👇👇👇
@tewihd
*ጥያቄ ተራዊህን በተመለከተ*
__________
ጠያቂ ሰውየው የዒሻ ሶሏት እየተሰገደ ሳለ መስጂድ ደረሰ፡፡
_ነገር ግን እየተሰገደ ያለው ተራዊህ መሆኑን ጠርጥሮ ለብቻው ዒሻ መስገድ ጀመረ ።_
*እንደተሳሳተ በተገነዘበ ጊዜ ምን ማድረግ ይኖርበታል!?*
መልስ 👇
*የጀመረውን ሶሏት አቋርጦ ከኢማሙ ጋር ሶሏቱን መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ላይ ሶሏትን በጀመዐ መስገድ ግዴታ ነውና!!*
[[ 📚 اللجنة الدائمة ]]
👇👇👇
@tewihd
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም(ረሂመሁላህ) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦
"ያ አባ ኢስሐቁ! ዱዓ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?"
እሳቸውም ፦"ቀልባችሁ በአስር ነገሮች ሞታለች።" አሏቸው።
እነሱም፦"ምን ምንድ ናቸው?" ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦
"(አንደኛ) አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።
(ሁለተኛ) ነቢዩን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፣ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
(ሦስተኛ) ቁርኣንን አነበባችሁት ፣አልሰራችበትም።
(አራተኛ) የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
(አምስተኛ) ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋ ገጠማቹ።
(ስድስተኛ) ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ ሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
(ሰባተኛ) የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
(ስምንተኛ) ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
(ዘጠኝ)ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፣ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
(አስር) ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
【"ጃሚዑል በያን አልዒልሚ ወፈድሊሂ"(2/12)
👇👇👇
📮@tewihd