tewihd | Unsorted

Telegram-канал tewihd - አስ–ሱናህ 🇵🇸

-

﴿وَلا تَلبِسُوا الحَقَّ بِالباطِلِ وَتَكتُمُوا الحَقَّ وَأَنتُم تَعلَمونَ﴾ البقرة ٤٢ “እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡” አልበቀራ 42

Subscribe to a channel

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የቱንም ያክል ብትሰበር ምንም ማለት አይደለም
ሁሌም ቢሆን ካቆምክበት መጀመር... ከዚያም ከመጀመሪያው የተሻልክ መሆን ትችላለህ
@eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🕋ሰላትን በተገቢው መልኩ ያለመስገድ
ምክንያቶች: 

እነዚህ ምክንያቶች ብዙ ናቸው:  አሳሳቢ እንዲሁም ትልቅ ከሚባለው ምክንያቶች:
🛑 ስሜትንት መከተል ሰለዚህም ነው الله  ስሜትን መከተልን ሰላትን ከማጥፋት ጋር አቆራኝቶ የጠቀሰው ።
{فخلف من بعدهم خلف أضاعوا الصلاة وتبعوا الشهوات فسوف يلقون غيا★ إلا من تاب وآمن} ..
ከእነሱም በኃላ ሰላትን ያጓደሉ( የተው) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ የጀሃነምንም ሸለቆ በርግጥ ያገኛሉ።

  🛑 የዚህን ሰላት እውነታ አለመረዳት: አሳሳቢነቷን አለማወቅ: ጥቅሟን አለማወቅ: ትሩፋቷን አለማወቅ: ምንዳዋን አለማወቅ: الله ዘንድ ያላትን ደረጃ አለማወቅ: ሌሎችም ምክንያቶች አሉ።

🛑 ሰላት ላይ ቸልተኛ ከሚያደርጉ ምክንያቶች:  አብዘሃኛው ሰጋጅ ሚሰግደው እንደ አካል ስራ ብቻ ነው የአካል እንቅስቃሴ የልብ ስራ የሌለበት:  እነሱ ዘንድ መተናነስ መፍራት አላህ ፊት መዋረድ ሚባል ነገር የለም: የሚሉትንም አያስተውሉም የሚሰሩትንም እንደዛው:  ስለዚህ ከሰላት ምንም ሳይጠቀሙ ይወጣሉ ። ለልቦቻቸውም ብርሃን ሚባል ነገር አያገኙም: እምነታቸውም ላይ ጭማሬ አያገኙም:  ከመጥፎ እንዲሁም ከተጠሉ ነገራቶችም መራቅ አይችሉም ።

✳️ ይህ ሁሉ የሆነው እነሱ ሚሰግዱት የአካል ሰላት እንጂ የነፍስ ሰላት ስላልሆነች ነው።  ለዚህች ሰላት ሚገባትን ሃቅ ቢሰጧት:  የፈሩ ሆነው ልባቸውን ሰብስበው:  ወደ الله ተመልሰው እንዲሁ በሱ ፊት መቆማቸውን እያሰቡ ቢሰግዱ እቺን ሰላት ይወዷት ነበር ልባቸውም  ወደ እሷ የተንጠለጠለ ይሆን ነበር ። ለዚህም ነው  ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሰላት የአይን መርጊያዬ ተደረገች ያሉት


لشيخ العلامة محمد صالح لعثيمين.

📚المصدر فتاوى نور لى الدرب لشريط (72)

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ዜሮ ነው ውጤቱ!

ቢያለቅስ ቢጮህ በእንብርክክ ቢሄድ
ቢድህ ቢሰባበር ለዘልዓለም ቢሰግድ

በአንድ እግሩ ቢቆም ድንጋይ ተሸክሞ
ላፍታ ባያፈጥር ቢልፈሰፈስ ደግሞ

ተውሒድን ዘንግቶ በአላህ ካጋራ
ቀብር ቆሌ ጅኒ አድባሩን ከጠራ

ከአላህ ውጭ ያለ ላይጠቅም ላይጎዳ
ላይሰጥ ላይከለክል ላያግዝ ላይረዳ

ሰው አምላኩን ትቶ ሌላን ከተጣራ
ዒባዳው ከንቱ ነው ጩሄቱ ኪሳራ

ፈጣሪና ፊጡር ላይገናኝ ነገር ነገር
አላህን ከወሊይ ከሸይኽ ማወዳደር
ዜሮ ነው ውጤቱ የዓቂዳ ችግር

👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሰባት አውዳሚ ወንጀሎች ...

بسم الله الرحمن الرحيم

ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ፦ « ሰባት አጥፊ ወንጀሎችን ራቁ !!! » "አል-ሙቢቃት" ማለት "አል-ሙህሊካት" ማለት ነው።

ምንድናቸው ? እነሱ ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸው እንዲህ አሉ ፦

👉 በአላህ ላይ ማጋራት !

👉 ድግምት

👉 ድግምትን ከሽርክ ጋር አቆራኙት‼️
ምክንያቱም ከሽርክ ስለሚመደብ ነው።

👉 አላህ እርም ያደረገውን ነፍስ ያለ አግባብ መግደል።

👉 አራጣ መብላት‼️

👉 የቲምን ገንዘብ መብላት‼️

👉 በጦር ግምባር ላይ ወደ ኋላ መመለስ።

👉 "አሳማሪ" "ከብልግና ዝንጉ የሆኑ" እንዲሁም አማኝ የሆኑ ዕንስቶችን በብልግና ማነወር‼️ ማለትም ፦ በዝሙት ማነወር ማለት ነው።

... እነዚህ ከትላልቅ ወንጀሎች ውስጥ ሰባቱ ናቸው። ትላልቅ ወንጀሎች ብዙ ናቸው።

👉 ወላጆችን ማመፅ ከትላልቅ ወንጀል ነው‼️

👉 ዝምድናን መቁረጥ ከትላልቅ ወንጀል ነው‼️

👉 ዕውቀትን መደበቅ ከትላልቅ ወንጀል ነው‼️

👉 መራገምና መሳደብ ከትላልቅ ወንጀል ነው‼️

👉 መንገድ መቁረጥ (ሽፍታነት) ከትላልቅ ወንጀል ነው‼️

ከዚህ ውጪም ብዙ የሚቆጠሩ አሉ።


ሰማሓቱ ሸይኽ ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላ ቢን ባዝ

ኢስማኤል ወርቁ …
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ከ"ሼጣን" ተጠንቀቁ ‼️

አስተዋይ ቆራጥ የሆነ ሰው ይህን ግልፅ የሆነ ጠላት ይጠነቀቃል።

👉 የሰው ልጅ አባት የሆነው "አደም" ከሱ የተሻለ እንደሆነ ያውቃል !!!

👉 የሰው ልጅ እናትም እነደዛው ነች !!!

👉 የአንተ እናት "ሐዋ " ትልቅ ትሩፋት አላት !!!

👉 ይህ ከመሆኑም ጋር "ሐዋ "ና
" አደም " ከሴጣን ተንኮል አልዳኑም !!!

👉 አንተም ተጠንቀቅ‼️እኔ... እኔ... አትበል !!!

👉 በነፍስክ አትደነቅ‼️የአላህን ጠላት ተጠንቀቅ‼️

👉 የአላህን ጠላት ተጠንቀቅ‼️

👉 በእርግጥም ወጥመዱና ገመዱ ውስጥ (ጥሎካል‼️) ከአንተ በላጩ ማነው ?

👉 እስከ መጨረሻው ሁሌም ሁሌም በሌሊትክም በቀንም ከዚህ ጠላት ተጠንቀቅ‼️

👉 ትድን ዘነድ ይከጀላልና (ወደ አላህ) የተዋረድክ ሁን !!!!!

👉 አላህን ቅናቻና መገጠምን ጠይቅ !!!

👉 ከ"ሼጣን" ሸሪዓዊ በሆነ መጠበቂያ በአላህ ተጠበቅ።

👉 አላህን ማውሳት አብዛ !!!

❤ وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ الرَّحْمَٰنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِينٌ

👉 (( " ከአልረሕማን ግሣጼ (ከቁርኣን) የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእርሱ
ቁራኛ ነው፡፡ " ))

(አል-ዙኽሩፍ (36))

👉 አላህን ከማውሳት መዘናጋት ለሴጣን መሾም ምክንያት ነው !!!

👉 አላህን ማውሳትን ማብዛት ሰላም ለመሆን ምክንያት ነው !!!

(ታላቁ ኢማም ሸይኽ ኢብን ባዝ)
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🔺አላህ እኮ መልካም እንጂ ሌላን አይቀበልም!
~~~~
#ገራሚ_ታሪክ
አስመዒ የሚባለው ምሁር አንዲትን ሴት  በጭንቅላቷ ላይ ሮማንን ክፍት በሆነ ዕቃ ውስጥ አድርጋ ተሸክማ ስትሄድ ያያል
የሆነ ሰው ይመጣና ከዚህች ሴት ላይ አንድ ሮማን እሷ ሳታውቅ ይሰርቅባታል ከዚያም ይህ ግለሰብ መንገዱን ይቀጥላል
ይህን ክስተት ያየውም አስመዒ ይህንን ግለሰብ መከታተል ጀመረ
በኋላ ላይም  ሰራቂው ግለሰብ በመንገድ ላይ አንድ ሚስኪን ያገኝ እና የሰረቀውን ሮማን ለሚስኪኑ ይሰጠዋል

በዚህ ጊዜ አስመዒም ወደግለሰቡ ይመጣና ትገርማለህ! ከሴትየዋ ስትሰርቅ የራበህ መስሎኝ ነበር ከሷ ሰርቀህ ለሚስኪን ትሰጣለህ? ነገረ ስራህ በጣም ይገርማል! አለው
ሰውየውም እኔማ ከጌታዬ ጋር እየተገበያየሁኝ ነው አለው

አስመዒም በመቃወም እንዴት ነው ባክህ ከጌታህ ጋር የምትገበያየሁ? አለው
ሰውየውም ስሰርቃት አንዲት ወንጀል ብቻ ይፃፍብኛል ለሚስኪን ሰደቃ ሳደርገው ደግሞ 10 ሀሰናት ይፃፍልኛል ስለዚህ አንዱ ባንዱ ይጠፋፋና እኔ ጋር 9 ሀሰናት ይቀራል ማለት ነው
ለዚያም ነው እኔ ከጌታዬ ጋር እየተገበያየሁኝ ነው ያልኩህ አለው!

አስመዒም አላህ ይዘንለትና ለዚህ ሰው እንዲህ አለው
ስትሰርቃት አንዲት ወንጀል ይፃፍብሃል ሰደቃ ስታደርጋት ግን አላህ ካንተ ይህን ሰደቃ ምንም አይቀበልህም ምክንያቱም አላህ እኮ መልካም ነው መልካምን እንጂ ሌላን አይቀበልም.....አንተ ልክ የተነጀሰን ልብስ በሽንት እንደሚያጥብ ሰው ነህ አለው!!!

ሱብሃነሏህ! ዛሬ ላይ ልክ እንደዚህ ግለሰብ ለራሱ እና ለሌላው ሰው ያለ ዕውቀት ፈትዋ የሚሰጥ ምንኛ በዛ

አላህ ስሜትን ከመከተል ነጃ ይበለን!!
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍁ኢብኑል ቀይም رحمه الله እንዲህ አለ፦

ዱንያን ያፈቀረ ሰው ዱንያ በሰውየው ላይ ያላትን ደረጃ ትመለከታለች ከዛም አገልጋይዋ ፣ባሪያዋ ታደርገዋለች ታዋርደዋለችም ። እሷን ችላ ያለን አካል ደግሞ አልቃ(ከፍ) አድርጋ ትመለከተዋለች ፣ትካድመዋለች ፣ትተናነስለታለችም።


አልፈዋኢድ
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

አል-ኢማም አል-አልባኒይ በዚህ ዘመን አህለ-ል-ኪታብ የሚባሉ ሴቶችን ማግባት ጥሩ አለመሆኑን በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍂የዛሬው ቲላዋ 2

🍃Tilawa Of The Day🍃

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

سوالي اكرمكم الله هو هل يجوز للمرأة ان تلبس ملابس زوجها لما تكون في المنزل معه.


الشيخ #صالح_الفوزان حفظه الله
💡المصدر(: 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
ጥያቄ፦ አላህ ያክብራቹና አንዲት ሴት ቤቷ ውስጥ ስትሆን የባሏን ልብስ መልበስ ይቻልላታል?

መልስ፦ ለሴት ልጅ በወንድ መመሳሰል አይቻልላትም በቤቷም ውስጥ ይሁን ከቤቷም ውጪ በልብስም ይሁን በሌላ ወንድን ብቻ በሚመለከቱ ጉዳዮችም ጭምር።
ነብዩ() ከወንድ ጋር የሚመሳሰሉ ሴቶችን እንዲሁም ከሴት ጋር የሚመሳሰሉ ወንዶችን ተራግመዋል።

ሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

💫ሱፍያን አሰውሪይ እንዲህ አለ፦

  🤝 አንድ ወንድምክን ለአላህ ብለህ ከወደድከው: ነፍስህንም ገንዘብህንም ለግሰው:  አደራ አደራ ከጭቅጭቅና ከክርክር: በዚህ ምክንያት በዳይ፣ አታላይና ወንጀለኛ ልትሆን ትችላለክ።
በሁሉም ቦታ ላይ ትእግስት ይኑርክ
ትግስት ወደ መልካም ይጎትታል
መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት።

ሂልየቱል አውሊያእ

👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

➧አያሙ-ተሽሪቅ መፆም አይቻልም

▫ከዙልሒጃህ 11 እስከ 13 ድረስ ያሉት የተሸሪቅ ቀናት በመባል የሚታወቁት ቀናቶች ዒዳችን ስለሆኑ መፆም አይቻልም።  ረሱል -ﷺ- እንዲህ ይላሉ ፦ [ (ሶስቱ) የተሽሪቅ ቀናቶች የመብላት የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናቶች ናቸው። ] (ሙስሊም ፥ 1141). በነዚህ ቀናቶች መፆም የተፈቀደው ሐጅ ላይ ቃሪን ወይም ሙተመቲዕ ሆኖ የሀድይ እርድ ያላገኘ ሰው ብቻ ነው እና ጥንቃቄ እናድርግ።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ጌታችን አላህ سبحانه وتعالى በቀኑ ክፍለ ጊዜ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ የሚወርድበት ዕለትና ባሪያዎቹንም ከሌላው ጊዜ በተለየ ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ዕለት ስለሆነ እኛንም ዘሮቻችንም አላህ ከ ጀ ሐነ ም እሳት ነፃ እንድለን የምንማጸንበት ልዩ ቀን ነው !
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

#ወንድሜ ሆይ የአረፋ ቀን (ዘጠነኛው) ቀን በጣም የላቀ ቀን ነው!
#የዱኒያ የአኼራ ሀጃህን ምትጠይቅበት የሆነን ዱዓዕ አዘጋጅ! ከሰዎች (ተገለል) ብቻህን ሁን! አልቅስ! ጌታዬ ብለህ በዕርግጠኝነት ላይ ሆነክ ተማፀነው
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

` ታላቁ ሶሃብይ አብደሏህ ኢብን  መስኡድ

ስሙ አብደሏህ ኢብን መስኡድ ኢብን ጛፊል ኢብን ሃቢብ አል ሁዘሊይ ሲሆን ወደ ኢስላም ቀድመው ከገቡት ስድስተኛው ነው። ሁለት ሒጅራዎችን አድርጓል። የበድር፣ የኡሁድ፣ የኸንደቅን  ዘመቻዎች እና በይዓቱ ሪድዋንንም ተሳትፏል። ከነብዩﷺ ጋር ብዙ ክስተቶችን የተካፈለ ሲሆን ፤ ከነብዩﷺ 848 ሃዲሶችንም አስተላልፏል።

- አብደሏህ ኢብን መስኡድ ከረሡልﷺ ጋር ሁሌም ተጣማሪ ነበር። ነብዩﷺ ዘንድ በመግባት እርሳቸውን ያገለግል ነበር። የነብዩን የጫማ፣ የመፋቂያ እና ሌሎች ነገሮችን በማሰናዳት ያገለግላቸው ነበር።
ኢብን መስዑድ ነብዩﷺ ዘንድ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሶሃቦች መካከል አንዱ ነበር። ነብዩﷺ ከእለታት አንድ ቀን ጉዞን እየተጓዙ ሳለ ኢብን መስኡድ ውብ በሆነ (ግልፅ በሆነ መልኩ) ቁርዓን ሲቀራ አደመጡትና " ቁርዓንን ልክ እንደወረደ መቅራትን የፈለገ የኢብን መስዑድን አይነት አቀራር ይቅራ።" አሉ።
ነብዩﷺ ኢብን መስኡድን ዛፍ ላይ ወጥቶ ዛፉ ላይ ካለው ነገር እንዲያመጣላቸው ባዙዘዙት ጊዜ በባቶቹ ቅጥነት ሶሃቦች ሲስቁ ምን አሳቃችሁ? በአብዱሏህ እግር ነውን ምትስቁት? የአብደሏህ እግር የቂያማህ እለት ከኡሁድ ተራራ በላይ ትመዝናለች። ሲሉ ተቿቸው።
አብደሏህ ኢብን መስዑድ ቁርዓን ሲቀራ ውብ ድምፅ ነበረው። የቁርዓን እና የተፍሲሩን(ፍቺ) ጭምር ጥልቅ እውቀት ነበረው።ኢብኑ መስኡድ
" አንዲት ሱራ(ምዕራፍ) የት እንደወረደች እና አንዲት አያ(አንቀፅ) ለምን እንደወረደች አውቃለሁ።" ይል ነበር።

አብደሏህ ኢብን መስኡድ በ32ኛው ወይም በ33ኛው አመተ ሒጅራ መዲና ላይ ሞቷል። በበቂዕ የሙስሊሞች መቃብር ተቀብሯል። ኡስማን ኢብኑ ዓፋን፣ ዙበይር ኢብኑል ዓዋም እና ሌሎች ሶሃቦች ሶላተል ጀናዛን ሰግደውበታል።
እድሜውም ስልሳዎቹ አካባቢ እንደነበር የታሪክ ምሁራን ጠቅሰዋል።

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

👉 አስመዒ (رحمه الله)

አስመዒ አንዲትን ሴት ሮማን በእቃ አድርጋ  ጭንቅላቷ ላይ ተሸክማ ያያል :  አንድ ሰውዬ ደግሞ  ተደብቆ ወደ እዚች ሴት ይጠጋና ሳታየው አንድ ሮማን ይወስድባታል።

🫴አስመዒም ይህን ሰው ተከታተለው ሰውየውም ባንድ ሚስኪን በኩል አለፋና ለዛ ሚስኪን ሮማኑን ሰጠው

አስመዒም በጣም ትገርማለክ  ተርበክ የሰረቅክ መስሎኝ ነበር አንተ ግን ሰርቀክ ለሚስኪን ሰደቃ ታደርጋለክ ይህ በጣም ያስገርማል።
  ሰውየውም እንዲህ አለ እንዳዛ አይደለም ነገሩ እኔ ከጌታዬ ጋር  እየተገበያየው ነው አለው።

አስመዒም ንግግሩን ውድቅ በማድረግ ከጌታህ ጋር ትገበያያለክ? 

ሰውየውም: –ስርቆት ፈፀምኩኝ አንድ ወንጀል ተፃፈብኝ
እሷንም ሰደቃ አደረኩኝ አስር ምንዳ ተፃፈልኝ ጌታዬ ዘንድ ዘጠኝ ምንዳ ይቀረኛል ስለዚህ እኔ ከጌታዬ ጋር እየተገበያየሁኝ ነው።

አስመዒም እንዲህ አለው:  ሰርቀክ አንድ ወንጀል ተፃፈብክ የሰረቅካትን ደግሞ መፀወትክ አላህ ደግሞ ይህን አይቀበልክም ለምን ከተባለ አላህ መልካም ነው መልካምን ነገር እንጂ አይቀበልም ። አንተ ማለት የተነጀሰን ልብስ በሽንት እንደሚያጥብ ሰው ቢጤ ነክ አለው።

👌አሁን ባለንበት ዘመን የዚህ ሰውዬ አምሳያ ስንትና ስንት ነው ያለው: ለነፍሱ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ያለ እውቀት  ፈትዋ የሚሰጥ

ሀቅን ይዣለው ብሎ በመገመት በባጢል  ሚከራከር ፣ለነፍሱ ሀራም የሆነን ነገር  ሀላል ለማድረግ ሚሞክር

ሌላው በጣም በግልፅ ሚታየው ሰርቆ አጭበርብሮ በሰደቃ ለማለፍ ሚሞክር ይህ በጣም በዝቷል በተለይ ባለንበት ሀገር ላይ

نسأ الله السلامة والعافية

      للإشتراك في القناة اضغط هنا👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍁ነብዩ ﷺሰላዋት ማውረድ ያለው ጥቅም

አንደኛ፦ የአላህን ትእዛዝ መቀበልን ያሳያል  አላህ እንዲህ ስላለ ፦አላህና መላእክቱ በነብዩ ላይ የአክብሮት ሰላዋትን ያወርዳሉ 
እናንተ ያመናችሁ  ሆይ! በሱ ላይ የአክብሮት ሰለዋትን አውርዱ።
የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።

💫ሁለተኛ ፦የአንድ ባሪያን ደረጃ በጀነት ውስጥ  ከፍ እንዲል ታደርጋለች

  አነስ ባስተላለፈው ሐዲስ ነብዩ እንዲህ አሉ፦ በእኔ ላይ አንዲት ሰለዋትን ያወረደ አላሁ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል፣ከሱ ላይ አስር ወንጀሎቹ  ይራገፋሉ፣  ደረጃው በአስር  ከፍ ይላል።

ኢማም አነሳኢ ዘግቦታል
ሸይኽ አልባኒ ትክክል( ሰሒህ ብለውታል)።


@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ወንድምህ በስንት ትሸጠዋለህ⁉️

ሁለት ሰዎች ፊት ለፊት እየተያዩ ይጨዋወታሉ። አንደኛው ጠየቀ;

“ወንድምህ በስንት ሸጥከው❓"
ሲለው
“በዘጠና (90) ስህተት” አለው
“በጣም እርካሽ ነው የሸጥከው‼️” አለው።

አትገረምም❓
ወንድሙን 89 ስህተት ሁሉ ሲሳሳት (ሲያጠፋ) “ይቅር” ብሎ አልፎት ዘጠና ስህተት በሰራበት ጊዜ ተለያየው።

ከየትኛው ትገረማለህ⁉️
👉 89 ስህተት አልፎ በ90 ስህተት የተሰናበተው ወይንስ
👉በ90 ስህተት መለያየት “አሳንሰሃል (በእርካሽ ሽጠሃል)” ባለው❓❓

አሁን ወደራስህ ተመልከት❗
ስንት ወንድሞች ነበሩህ❓ በስንት ስህተት ነው የተለያየሃቸው❓ አሁን ላይ ካሉህ ወንድሞችህ ያለህ አኗኗር ምን ይመስላል❓ ምን ያክል ስህተቶች አይተህ ታልፋለህ❓ ይህ የሁላችንም የቤት ስራ ነው‼️
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ሙሳ ለህዝቦቹ ኑዛዜን ሲያስተላልፍ እንዲህ አለ ፦
ህዝቦቼ ሆይ! ችግራችሁን እንዲያነሳላችሁ፣ ምትፈልጉትን መልካም ነገር እንዲችራችሁ እገዛን ከአሏህ ጠይቁ። ባላችሁበት የችግር ሁኔታም ትዕግስት አድርጉ። ምድርን እንደፈለጉ እንዲውስኑባት ምድር  የፊርዓውንና የሌላም አይደለችም። ምድር የአሏህ ብቻ ናት። እርሱ በፍላጎቱ በምድር ላይ  ሰዎችን ይተካል። ያገኛቸው ፈተና እና ችግር ቢያገኛቸው እንኳ በምድር ላይ መልካም ፍፃሜው ለእነዛ የእርሱን ትዕዛዝ ተግባራዊ ለሚያደርጉ እና ክልከላውን ለራቁ አማኞች ነው።

ከኢስራኢል ልጆች የሆኑት የሙሳ ህዝቦችም ለሙሳ እንዲህ አሉ ፦
አንተ ሙሳ ሆይ! አንተ ከመምጣትህ በፊትም ከመጣህ በኋላም ልጆቻችንን በመግደል እና ሴቶቻችንን በማገድ በፊርአውን እጅ ብዙ ተሰቃየን።

ሙሳም ሲመክራቸው እንዲህ አላቸው ፦
ጌታችሁ ጠላታችሁ ፊርዓውን እና ህዝቦቹን ሊያጠፋ፣ ከእነርሱ በኋላም በምድር ላይ ሊያመቻችላችሁ እርግጥ ነው። ከዚህ ክስተት በኋላ የምትሰሩትን (ክህድት ወይስ ምስጋና) ሊመለከትም ነው።
[ተፍሲር አል ሙኽተሶር]
- ሱረቱል አዕራፍ 168-169 -

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

እኔ ስሞት...
1. ከእኔ ጋር የሚዛመዱ ሁሉንም ነገሮች ሰርዝ ❲ፎቶዎች፣ ቻቶች፣ ቪዲዮዎች❳
2. የኔን ፎቶዎች ወይም መልዕክቶች ለማንም አታጋራ።
3. የኔን ሶሻል ሚድያ ❲ፌስቡክ፣ ቴሌግራም...ወዘተ❳ ሪፖርት በማድረግ አዘጋ።
4. የኔን የሞተ አካል፣ ከሞቴ ጋር የሚገናኝ ማንኛውንም ነገር በፍፁም ፎቶ አታንሳ።
5. አስቤውም ሆነ ሳላስበው ከጎዳውህ ይቅር በለኝ።
6. ለሞተችው ነፍሴ ብዙ ዱዓ አድርግላት።
7. የኔ ወዳጅ ማንኛውም ገንዘብን የተመለከተ ቅሬታ ካለህ በቅንነት ቤተሰቤን ተገናኝና ጠይቅ...ጨርስ።
እባክህ በፍፁም ሌላ ነገር አትንካ... አታስቸግር።
ሞት ወደእኛ መች እንደሚመጣ አናውቅም። በማንኛውም ሰአት እና ጊዜ ከፊቱ ልንቆም እንችላለንና።
ሞት ወደ እኛ ሲመጣ ምንም ማሳወቂያ መልዕክት አይልክምና።
በቃ ይህው ነው መልዕክቴ።

አላህ ረጅምን እድሜ ይስጠን።
ራስህን ጠብቅ፣ በደስታ በጤና ኑር።
👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ኢስላም ማለት ሱናህ ነው ሱናም ኢስላምነው::
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ዓብደላህ ኢብን አልሙባረክ
እንዲህ አለ፦

👉የቢድዓ ሰው በቀን ሰላሳ ጊዜ እንኳን ፊቱን ቢቀባ ፊቱ ላይ ጨለማ አለ።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ከሁሉም በፊት ተውሒድ

ቅድሚያ ለተውሒድ

ሸይኽ ሷሊሂ አልፈውዛን ሀፊዘሁሏህ
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

🍂የዛሬው ቲላዋ🍂

🍃Tilawa Of The Day🍃

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ወደ ፊትና ሚጣሩ ዱአቶችን ራቅ!!"
📌قال العلامة صالح الفوزان -حفظه الله-:
" الله نهانا عن الجلوس مع القوم الظالمين ، ومن أظلم الظالمين دعاة الفتنة ، لا تجلس معهم ، لا تستمع لهم ،
لا تقل أنا أعرف ولا يمكن لهم أن يخدعوني ، لا لا تُزكِّ نفسك يا أخي "
📚شرح كتاب الفتن والحوادث ص٧٨

@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

የሚያረገርግ ቤት፣ የሚያፈስ ጣሪያ፣ የሚነቃነቅ ምሰሶ የሚፀናው በተውሒድ ነው፡፡ የፈጠረንን ጌታ አላህን አንድ አድርጎ በማምለክ፡፡
ከአላህ ዉጭ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ፣ ሀሳብ የምንጥልበት ማንኛውም ነገር ሁሉ ጣኦት ነው፡፡ ሌላን አካል ከሱ ማስቀደም ክህደት ነው፡፡

አላህ እኔን ፍሩ፣ እኔን ተገዙ … ሲለን ከሱ ዉጭ ያለውን ሁሉ ከሕይወታችን እንድናስወጣ ነው፡፡ በኔ ተማመኑ፣ በኔ ተመኩ ሲለንም በሌሎች ላይ ያለንን መመካት ሊያስጥለን ነው፡፡

እናም ወዳጆቼ! ሁለመናችን በአምላካችን ብቻ ይዘወር፡፡ ዉስጣችንን ፈጣሪያችን ብቻ ይንገስበት፡፡ ቤታችንን ከአላህ ዉጭ ማንም አይኑርበት፡፡ በሱና ለርሱ ብቻ መኖር ትልቅ ክብር ነውና፡፡

@Eross_eross

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته،
🌙  ዒድ ሙባረክ🌙

🌙تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
وعيد مبارك
🌙እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አል_አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️
        

🌠🌠🌠🌠🌠
🌠
🌠🌠🌠🌠🌠
🌠
🌠🌠🌠🌠🌠
    
🌠🌠🌠🌠🌠
           🌠
           🌠
           🌠
🌠🌠🌠🌠🌠

🌠🌠🌠🌠🌠
     🌠                 🌠
     🌠                    🌠
     🌠                       🌠
     🌠                     🌠
     🌠                 🌠
🌠🌠🌠🌠🌠

  MUBAREK
በተለየዩ ቋንቋ በመልዕክት ማስተላለፍ ይቻላል @bdi_07 👈
እኛም መልሰን ለእናንተው እንደርሳለን ።
👇👇👇
@tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

ﷲ أكبر والقلوبُ تكبّرُ
كُل العظامِ أمامَ ربّي تصغرُ!

ሀያላን ሁሉ ከፊቱ ሲቀርቡ የሚያንሱ የሆነው የሀያሎች ሀያል፤ የትልቆች ታላቅ፤ የንጉሶች ንጉስ የሆነው አላህ እልቅና ይገባው‼️


አላሁ አክበር  አላሁ አክበር  አላሁ አክበር…

@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

➟ምርጥ ሚስት ማለት...!

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ رحــــمــــه الــــلــــه ሲናገሩ፦

መልካም ሚስት ለባሏ መልካምነቷ የቀጠለ ሲሆን የብዙ አመት የደስታው መሠረት ትሆናለች። ይህች ሴት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ሲል የተናገሩላት ናት፦

⇝ይህች አለም ጊዜያዊ መቆያ ናት! ከውስጧ ምርጡ ነገር አማኝ ሚስት ናት። ወደርሷ ስትመለከት የምትወዳት የሆነች (ሚስት)።

⇝ትዕዛዝህን ወዲያውኑ የምትፈጽም እና ከሷ በራቅክ ወቅትም በራሷና በገንዘብህ አንተን የምትጠብቅህ ናት። ይህንንም አስመልክቶ በአንድ ወቅት ሙሀጅሮች የአላህ መልዕክተኛን ﷺ ምን አይነት ሀብት መፈለግ እንዳለባቸው በጠየቋቸው ወቅት እንዲህ መልሰውላቸዋል።

⇝አንደኛችሁ (እነዚህን)ይፈለግ!

⇝አላህን የሚያስታውስበት ምላስ
⇝አላህን አመስጋኝ ልብ እና
⇝በመጭው አለም ጉዳዩ እሱን የምታግዘው አማኝ ሚስት
ቲርሚዚ ዘግበውታል

⇝ምናልባት ላንተ ይህች መልካም እንስት ፍቅርና መዋደድን ቁርአን እንደሚለው ትሰጥህ ይሆናል። ነገር ግን ካንተ መለየቷ ከሞት በበለጠ ህመሟ ነው። ከዚያም አልፎ ገንዘቧን ሁሉ ነገሯን ከማጣቷ በላይ ያንተ ማጣት ለሷ ስቃይ ነው። ምርጥ ሚስት ማለት እሷ ናት።
መጅሙዕ አል ፈታዋ (35/299)
👇👇👇
@Tewihd

Читать полностью…

አስ–ሱናህ 🇵🇸

*አላህ ዘንድ ከሰዎች ተወዳጁ ማነው? ከስራዎችስ ይበልጥ ተወዳጁ የትኛው ነው?*

ዓብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት አንድ ግለሰብ ወደ መልእክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጣና አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ ዘንድ ተወዳጁ ሰው ማነው? ከስራዎችስ የበለጠ ተወዳጁ የትኛው ነው? አላቸው:: እሳቸውም:- “አላህ ዘንድ ተወዳጁ ሰው ለሰዎች የተሻለ ጥቅም የሚሰጥ ሰው ነው:: አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሆነው ስራ ደግሞ ሙስሊምን ማስደሰት ወይም ጭንቀቱን ማስወገድ አልያም እዳውን መክፈል ወይም ከሱ ላይ ረሀብን ማባረር ነው:: ” አሉ:: በማስከተልም “በዚህ መስጂድ ውስጥ ( መስጂድ-አነበዊ ለማለት ነው) አንድ ወር በኢዕቲካፍ ከማሳልፍ የወንድሜን አንዳች ጉዳይ ለማስፈፀም መንቀሳቀሴን እመርጣለሁ:: ቁጣውን የተቆጣጠረ አላህ ገመናውን (ዓውረቱን) ይደብቅለታል:: ቁጭቱን መወጣት እየቻለ ከመወጣት የተቆጠበ አላህ የቂያማ እለት ልቡን በተስፋ ይሞላለታል:: የወንድሙ ጉዳይ እስኪመቻችለት (እስኪፈፀም) ከወንድሙ ጋር የተንቀሳቀሰ እግሮች በሲራጥ ላይ በሚንሸራተቱበት (የቂያማ እለት) አላህ እግሮቹን እንዲፀኑ ያደርግለታል:: ኮምጣጤ ማርን እንደሚያበላሸው ሁሉ መጥፎ ስነ-ምግባርም ስራን ያበላሻል::” አሉ:: ጠበራኒ ዘግበውታል::
👇👇👇
/channel/tewihd

Читать полностью…
Subscribe to a channel