አንዳንዴ ደግሞ እንዲህ ይሆናል👇
ስጦታህ ከፍ ሊል ሙሲባህ ይበረታል‼️
ነብዩላህ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላት ወሰላም
በፈተናው መጀመሪያ ላይ ፈረጅ ቢመጣለት ኖሮ፤
በመጨረሻ የሀገሩ ንጉስ ሆኖ አያነጋም ነበር።
👉ወንድሞቹ ጉድጓድ ውስጥ ጥለውት፣
👉ባሪያ ተደርጎ ተሽጦ፣
👉በባርነት አገልግሎ፣
👉በበደል ታስሮ፣
ይህንን ሁሉ ሙሲባ በሰብር ከተሻገረ በኋላ የበዳዮቹ ሁሉ የበላይ ሆኖ በንግስና አነጋ።
🖊️አንተንም አንዳንዴ የተሻለና ከፍ ያለ ስጦታ ይሰጥህ ዘንዳ ሙሲባዎች ሊበዙብህና ሊከብዱህ ይችላሉ።
🌱{فَصَبْرٌ جَمِيلٌ}
🖊️በአቡ ነዲራ
🫵👉@tewihd
👉እውነት ሸህየህያ حفظه الله ዑስማንን رضي الله عنة ሙብተዲዕ ነው ይላልን ❓
👉እውነት ሸህ የህያ حفظه اللهየመልክተኛው ﷺ ንግግር ያለመረጃ ተቀባይነት የለውም ይላልን ❓
👉ሸህ የህያ በዚ መስአላ ዙርያ ምንድነው ያለው⁉️
👉ኡለማዎች በዚ ዙርያ ምንድነው ያሉት ❓
👉ሀዳድይ ሀጁሪይ ለሚሉት አላዋቂዎች የተላለፈ ጥያቄ
👉በዚ መስአላ የሰለፍዮች አቋምስ ምንድነው⁉️
እዲሁም የመሀበርተኞች አላዋቂነት ሰምተው ይታዘቡ
@tewihd
በሁለት ሶላቶች መካከል ቦታ መቀየር …
#ﺗﻐﻴﻴﺮ_ﺍﻟﻤﻜﺎن_بين_الصلاتين !
بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم.
እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
በአላህ ስም እጀምራለሁ።
سُئِل ﺍﻟﺸﻴﺦ / إﺑﻦ ﻋﺜﻴﻤﻴﻦ
- رحمه الله تعالىٰ :
ﻫﻞ ﻭﺭﺩ ﺩﻟﻴﻞ علىٰ ﺗﻐﻴﻴﺮ ﺍﻟﻤﻜﺎﻥ ﻷﺩﺍﺀ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺑﻌﺪ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻔﺮﻳﻀﺔ ؟
ጥያቄ ፦
"ከፈርድ" (ግዴታ) ሶላት በኋላ "ሱና" ለመስገድ ቦታን መቀየር መረጃ መጥቶበታልን❓
ﻧﻌﻢ ! ﻭﺭﺩ في ﺣﺪﻳﺚ ﻣﻌﺎﻭﻳﺔ ﺭضي ﺍلله ﻋﻨﻪ ﺃﻧﻪ ﻗﺎﻝ :
" ﺇﻥ ﺍلنبي ﷺ ﺃﻣﺮﻧﺎ ﺃﻥ ﻻ ﺗﻮﺻﻞ ﺻﻼﺓ ﺑﺼﻼﺓ ، حتىٰ ﻧﺘﻜﻠﻢ ، ﺃﻭ ﻧﺨﺮﺝ " .
📝 ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ
ﻓﺄﺧﺬ ﻣﻦ ﻫﺬﺍ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﻌﻠﻢ ﺃﻧﻪ ! ينبغي ﺍﻟﻔﺼﻞ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﻔﺮﺽ ﻭﺳﻨﺘﻪ ، ﺇﻣﺎ ﺑﻜﻼﻡ ، ﺃﻭ ﺑﺎﻧﺘﻘﺎﻝ ﻋﻦ ﻣﻜﺎﻧﻪ .
ﻋﻦ ﺍلأَﺯْﺭَﻕُ ﺑْﻦُ ﻗَﻴْﺲٍ ﺃﻥ ﺭجلاً صلَّىٰ ﻣﻊ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ﺛﻢ ﻗﺎﻡ ﻟﻴﺸﻔﻊ ! ﻓﻮﺛﺐ ﻋﻤﺮ رضي الله عنه ﻓﺄﺧﺬ ﺑﻤﻨﻜﺒﻪ ﻓﻬﺰﻩ ﺛﻢ ﻗﺎﻝ :
( ﺍﺟﻠﺲ ! ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻢ ﻳﻬﻠﻚ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﻜﺘﺎﺏ ، ﺇﻻ ﺃﻧﻪ ﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﺑﻴﻦ ﺻﻼﺗﻬﻢ ﻓﺼﻞ ؛
ﻓﺮﻓﻊ ﺍلنبي ﷺ ﻓﻘﺎﻝ : " ﺃﺻﺎﺏ ﺍلله ﺑﻚ ﻳﺎ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﺨﻄﺎﺏ " .
📝 رواه أبو داود وصححه الألباني
📍ويكفي في الفصل بينهما الإستغفار ! ولو ثلاثا …
❗لعل هذا الحكم ! يهم المرأة أكثر ، لأن مصلاها واحد في البيت ، فتصلي الفريضة ثم تقوم وتصلي السنة ، ولا تفصل بينهما بكلام أو حركة أو انتقال .
‼ فالخلاصة !
من صلىٰ الفريضة ، عليه أن يفصل بينها وبين صلاة النافلة ، بكلام أو إستغفار أو تسبيح أو حركة أو إنتقال .
🎙 فتاوىٰ إبن عثيمين 861
ــــــ ✵✵ ــــــ ✵✵ــــــــــــ ✵✵ ــــــ
መልስ ፦
አዎ ! ሙዓዊያ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የተናገረው በሆነ "ሐዲስ" ውስጥ መጥቷል።
(( " ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)
አንድን ሶላት ከሌላ ሶላት ጋር እስከ ምንናገር ወይም እስከ ምንወጣ ድረስ እንዳናገናኝ (እንዳናያይዝ)
አዘውናል። " ))
【ሙስሊም ዘግቦታል】
የዕውቀት ባለቤቶች (ዑለማዎች)
ከዚህ "ሐዲስ" በመያዝ በግዴታና በሱና
ሶላት መሀል ክፍተት ማድረግ ይገባል አሉ።
እሱም ፦ በንግግር ወይም ቦታን
በመሸጋገር (በመቀየር) ማለት ነው።
ከአዝረቅ ቢን ቀይስ (በተያዘ "ሐዲስ")
አንድ ሰውዬ (( " ከነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ጋር አብሮ ሰገደ ፤ ከዚያም (ሌላ ሶላት በማጣመር ለመስገድ ተነስቶ ቆመ ፤ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ትከሻውን በመያዝ ጎትቶ አሰቀመጠው ፤
በማስከተለም እንዲህ አለው ፦
" ተቀመጥ ! የመፅሓፍት ባለቤቶችን እኮ አላጠፋቸውም ፤ በሁለት ሶላታቸው መሀል ክፍተት ባለማድረጋቸው ነው
እንጂ … "
ነብዩም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም )
ቀና አሉና አሉ ፦ " አንተ የኸጣብ ልጅ (ዑመር) ሆይ ! በእርግጥም አላህ
(ያልከውን) ገጥሞሃል አሉት።
【አቡ ዳውድ ዘግቦታል ፤ ኢማሙ አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል】
👉 በሁለት ሶላቶች መሀል ሦስት ጊዜም
ቢሆን " ኢስቲግፋር" በማድረግ ክፍተት ለመፍጠር በቂ ነው።
ይህ "ሑክም" በአብዛኛው ሴት ልጅን ያሳስባል ! ምክንያቱም በቤት ውስጥ መስገጃዋ ቦታ አንድ ነው ፤ ግዴታ ሶላቷን ትሰግዳለች ከዚያም ተነስታ ሱናዋን ትሰግዳለች ፤ በመካከላቸው በንግግር ወይም በእንቅስቃሴ ወይም ከቦታው በመሸጋገር (በመቀየር) ክፍተት አታደርግም !
የጉዳዩ ጭብጥ !!
ግዴታ ሶላትን የሰገደ የሆነ ሰው በርሱ ላይ ማድረግ ያለበት (በግዴታና በሱና) ሶላት መሀል በንግግር ወይም
" በኢስቲግፋር " ወይም " በተስቢሕ "
ወይም በእንቅስቃሴ ወይም ከቦታው በመሸጋገር (በመቀየር) ክፍተት ማድረግ ነው !!!
【ፈታዋ ኢብን ዑሰይሚን (861)】
ታላቁ ኢማም መሐመድ ሷሊሕ
አል–ዑሰይሚን
ኢስማኤል ወርቁ…
👇👇👇
@tewihd
☞ እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ???? ☜
አጂብ የሆነ ታሪክ
አንድ ወጣት በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ ይወድና ለጋብቻ ያጫታል ከተጫጩ በዃላ ግን ግልፅ በሆነ አረፍተነገር እናቱን እንደማትወዳት እና አብራቸው መኖር እንደማትፈልግ ትነግረዋለች ።
እሱን ብትወደውም እናቱን ግን ልትወድለት አልቻለችም እናቱም
በእድሜ የገፉ ስለነበሩ ልጂቷ ልጂቷ ብዙ ታስቸግራቸው ጀመር።
ከዛም ልጅ እንደማያገባትና እንደሚለቃት አስረግጦ ሲነግራት ልጂቱ ልጁን ስለምትወደው ደነገጠች እንደምታስተካክልና እናቱን እንደምታከብር እንዲያገባት ተማፀነችው።
ልጁም ካስተካከልሽ ብሎ እሽ አላት ከዛም የሰርጋቸው ቀን ደረሰ ምሽቱ ላይ ሠዎች በተሰበሰቡበት መሐል እናቱ ተጋባዥ እንግዶችን ለማስተናገድ በደስታ ሽር ጉድ ሲሉ
*ሙሽሪት በንዴት ይህቼን አሮጊት እናትክን ወዳ በልልኝ አታሳየኝ ከቻልክ እንደውም ሽጣት አለችው*
ልጁም ፈገግ ብሎ ተነሳና ሰዎች ከተሰበሰቡት መሐል
*"እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ "ለ 3 ጊዜ በተከታታይ ማለት ጀመረ*
እናቱም ከልጃቸው አንደበት የሰሙትን ማመን አቃታቸው ማዘንና ማልቀስ ጀመሩ እንግዶቹን በጣም ተገረሙ አዘኑ ከዛም ሙሽራው ወደ ሙሽሪት ዘወር አለና
*"አየሽ እናቴን ማነም ሊገዛት አልቻለም
ለምን እንደሆነ ታቂያለሽ? ምክንያቱም እናት ውድ ነች እናቴ ከምንም በላይ ውድ ነች ዋጋ አይተምናትም እኔ ግን
እናቴን እገዛታለው አንችን ደግሞ ሺጨሻለው
* ፈትቸሻለው በማለት የሰርጉ ቀን ቀለበቱን ከፊቷ ላይ በመወርወር ትቶላት እናቱን ይዞ ሲወጣ ወዲያው ከእንግዶቹ አንዱ ተከተለውና እንዲክ አለው "
*ለሴት ለልጄ ከአንተ የተሻለ ጥሩ ልጅ
አላገኝም ፍቃደኛ ከሆንክ ልጄን ልዳርልክ*
ብሎት ልጁን ይዞ ወደ ቤቱ ወሰደው ልጁም የዛን ሰው ልጅ ሲመለከታት እጅግ ውብና አደበኛ ነበረች አገባትም ለባሏም ሆነ ለባሏ እናት ፍቅሯን ያለ ገደብ ትሰጣቸውና ትንከባከባቸው ጀመር።
የወለደቻት እናቷ እስክትመስላት ድረስ
የሚጠበቅባትን ሁሉ መወጣት ጀመረች።
መልካምና ደስተኛ የሆነ ህይወት ይኖሩ ጀመር።
*አንድን ነገር ለ አሏህ ብሎ የተወ አሏህ የተሻለውን ይወፍቀዋል*
እህቴ ከታሪኩ ብዙ ቁምነገሮችን ተማሪበት፣ ለጓደኞችሽም አጋሪው
@tewihd
وااااا أسفاه على شبابنا..
👆👆👆👆👆👆
🔵በጣም ያሳዝናል الله ሙስሊም አድርጎ ፈጥሮህ እያለ ዲንህን ጠንቅቀህ አለማወቅህ الله ያሳውቀን
والله المستعان
@tewihd
"ምስጋና"
:
ንፉግነት እጃችን ዘንድ ተጣብቶ፤ ውሸት ምላሳችን ላይ ተመርጎ፤ ምቀኝነት ልባችን ውስጥ ተሰግስጎ፤ አረመኔነት በሀሳባችን እየዋኘ፤ አይናችን በቁስ እንዲመዝን ተገድዶ፤ ክርፋት ነፍሲያችን ላይ ተሰፍቶ፤ መልካምነት እንደ አድማስ ጥግ ርቆ ...... አለን።
የመፈጠርን አላማ ስተን ፈነጨን። ቁሳዊነታችን ልኩን አጣ።የወንድምን ቁስል ከማከም ይልቅ እንጨት እየሰደዱ ማደማማቱን ተያያዝን። ሂሳብ ይሉት ጭንቅ ከፊታችን መኖሩን ዘነጋን።ቀብር ይሉት ሀገር አፉን ከፍቶ የሚጠብቀን አልመሰልንም። ሲራጥ ይሉት ድልድይ ስለመኖሩ ከነጭራሹ እንደረሳን ...... አለን።
ቢሆንም አልሃምዱሊላህ አሁን አለን!
አዛኝና መሀሪው ጌታችንን እንዲምረን የምንጠይቅበት ሰዐት ይሆናል! ማን ያውቃል ነገ ስለመገኘታችን? ማንም!
አላህ ሆይ ዛሬን እስትንፋሳችንን ስለቀጠልክልን እልፍ ምስጋና ይገባህ!
👇👇👇👇
@eross_eross
ስለፆም አሳሳቢ ነጥቦች...!!!
👉👉👉 በታላቁ ዐሊም አል-ሙሓዲስ "አል-ፈቂህ" "አል-ዋሊድ" (ሸይኽ አሕመድ ቢን የሕያ አነጅሚ)
بسم الله الرحمن الرحيم
قال شيخنا العلامة المحدث الفقيه الوالد الشيخ أحمد بن يحيى النجمي
1- أحسن ما قيل في تعريف الصيام: إمساك المسلم العاقل أو المسلمة العاقلة الخالية من الحيض والنفاس عن الطعام والشراب والشهوة الجنسية من طلوع الفجر الثاني إلى غروب الشمس بنية التعبد.
1. ባማረ ሁኔታ ፆምን የሚገልፀው አባባል ፦
👉 ሙስሊም ፣ አይምሮው ጤናማ የሆነ ሰው እንዲሁም ሴት አማኝ አይምሮዋ ጤናማ የሆነችና ከወር አበባ ደምና ከወሊድ ደም ነፃ የሆነች እንዲሁም ከምግብ ፣ ከመጠጥ ፣ ከፆታዊ ዝንባሌ ከሁለተኛው "ፈጅር" ወቅት አንስቶ (አላህን) ለማምለክ በሚል "ኒያ" ፀሐይ እስከ እስቀሚጠልቅ ድረስ ፆም በመፆም (መቆጠብ) ማለት ነው።
(في مسائل الصيام من كتاب
" تأسيس الأحكام ")
… ኢስማኤል ወርቁ …
/channel/amr_nahy1
✍የሰብር አንቀፆች ምንኛ ያምራሉ...
﴿ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ﴾
ታጋሾችን(ሰብረኞችን) አበስራቸው።
﴿وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ﴾
አለህ ታጋሾችን ይወዳቸዋል
﴿وَاصْبِرْ وَمَا صَبْرُكَ إِلَّا بِاللَّهِ ۚ﴾
ታገስ የመታገስህ ምንዳ ከአለህ እንጂ ከሌላ አይደለም
﴿ وَجَزَاهُمْ بِمَا صَبَرُوا جَنَّةً وَحَرِيرًا﴾
በመታገሳቸው ጀነትንና የሃር ልብስ መነዳቸው
﴿إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُمْ بِغَيْرِ حِسَابٍ﴾
ታጋሾች ምንዳቸውን ያለ ልኬት ነው የሚያገኙት።
"አለህ የማይፈትነኝ ሳይወደኝ ቀርቶ የታጋሾችን ምንዳ ልያሳጣኝ ፈልጎ ይሆን?"(ከአባቶቻችን ንግግር)
-------------
ከሰብር ውጪ ይህ ሁሉ ምንዳ የሚገኝበት ምን አለ?
👇👇👇👇
/channel/tewihd
ወላሂ በጣም ያስለቀሰኝን ፈታዎ አዳምጡትማ""
"አየ የበተሰብ ነገር""አየየ ነፍሴ"በጣም ከባድ ነው،،
""ሶላት ቀላል አደለም ወላህ""ባልተቤትህ ስላተ ትመስክረልህህህ""
⁉️""ባሌ"ሲፈልግ ይሰግዳለ""ሲፈልግ"አይሰግድም""ለሱ"የሚሰራ መልካም ስራ ይበቃልን""⁉️
✅ሸይኹ""አይበቃም"አይጠቅመውም"አላህ ይዘንለትም"አይባልም"""""
👇👇
@tewihd
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ቢን ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
«ነፍሲያችን እና ወንድሞቻችንን የምንመክርበት ነገር፣ አላህን በመፍራት ላይና በደጋግ ቀደምቶች መንገድ በመጣበቅ፣ እንዲሁም ከቢድዓና ከሙብተዲዓዎች መጠንቀቅን፣ ትክክለኛውን ዓቂዳንና የሚቃረነውን በማስተማር ላይ ትኩረት መስጠትን፣ እንዲሁም በዓቂዳቸውና በእውቀታቸው ታማኝ ከሆኑ ዓሊሞች (እውቀት) መያዝን ነው።
ከነዚያ እውነትን በባጢል ከሚያደባልቁና እውነትን የሚያውቁት ከመሆናቸውም ጋር የሚደብቁ ከሆኑ መጥፎ ሰባኪ (ዳዒዎች) መጠንቀቅን!፣ አልያም ከነዚያ እውነትን እነሱ የማያውቁት ሆነው ሳለ ከሚሞግቱ መሀይማን መጠንቀቅን ነው የምንመክረው። ምክንያቱም እነሱ ከሚያሳምሩት የበለጠ አበላሾች ናቸው!።» [አል አጅዊበቱል ሙፊዳ ዐን አስኢለት አልመናሂጅ አልጀዲዳ 257–258]
@tewihd
ቁጭ ብለህ ምንም አታመጣም
ጊዜ ያስረጀሀል እንጂ አይቀይርህም
ምትቀየረው አንተው እራስህ ነህና ተነስ
{ وَمَنۡ أَرَادَ ٱلۡـَٔاخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعۡیَهَا
[سُورَةُ الإِسۡرَاءِ: ١٩]
አኼራን የፈለገ ለሷም መስራት ያለበትን የሰራ ....
{ فَإِذَا قُضِیَتِ ٱلصَّلَوٰةُ فَٱنتَشِرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ وَٱبۡتَغُوا۟ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَٱذۡكُرُوا۟ ٱللَّهَ كَثِیرࣰا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ }
[سُورَةُ الجُمُعَةِ: ١٠]
ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡
abduselam
@tewihd
✍ችግር ባጋጠመህ ጊዜ ሰዎች ፊታቸውን ቢያዞሩብህ እንኳን አላህ ከነ ችግርህ ብቻህን አይተውህም፡፡ እና አንተም ስታዝን ሲቸግርህ ብቻ ሳይሆን ስትደሰትም ከአላህ ጋር ሁን!
@tewihd
🚨 ለኢስላም ምን አበረከትን? 🚨
📮በሚል ርዕስ ሁሉም ሙስሊም ሊያዳምጠው የሚገባ ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።
🎙 በኡስታዝ አቡ ዒክሪማ ዓብዱረዛቅ ግርግቦ አላህ ይጠብቀው።
📅 እሁድ 13/01/2016E.C 📅
🕌 በአንዋር መስጂድ {አዲስ አበባ}
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 /channel/Al_Furqan_Islamic_Studio/13527
♡ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
📲 « አሪፍ አፕሊኬሽን »
• በታላቁ ሸይኽ (አብደላህ አል-ዒርያኒ) ቀለም ስለ ታላቁ የረመዷን ወር በጥያቄና-መልስ መልኩ ተፅፎ የቀረበው...
🎤 በኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሙሀመድ
ሰዒድ አስተማሪነት ተቀርቶ የተጠናቀቀው...
📚« مجالس شهر رمضان » የተሰኘው ኪታብ...
✓ በአፕሊኬሽን መልኩ ባማረ ሁኔታ ከpdf ጋር ተሰርቶ ለስራ በቅቷል።
↪️ የኡስታዝን ቻናል ለማግኘት ⤵️⤵️
🔗 /channel/Abu_Muhammed_MuhammedSed
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 /channel/mesjidalsunnah/12217
የፊርዓውን ታሪክ በውሃ አብቅቷል
የቃሩን ታሪክ በምድር መደርመስ አብቅቷል ።
የኑምሩድ ታሪክ በትንኝ ተጠናቋል።
የአብርሃ ታሪክ በድንጋይ አበቃ።
የጭፍራዎቹ ታሪክ በንፋስ አብቅቷል።
የአታቱርክ ታሪክ በቀይ ጉንዳኖች አብቅቷል።
የሂትለር ታሪክ እራሱን በማጥፋት ተጠናቀቀ።
አላህ የውሸት ታሪኮችን በጣም ቀላል በሆኑ ነገሮች እንዲያከትሙ ያደርጋቸዋል።
አላህ ቢፈቅድ (የአይሁድ ልጆች) ታሪካቸውን በቅርቡ እንመለከታለን።
[ قناة الفوائد العلمية] 👆منقول
@tewihd
ኢስላም ሱብሂ
አብድረህማን ሙስኢድ
ሚንሻሪ አፋሲ
የነዚህ ቃሪዎች አቀራር ወደ ሙዚቃ ስለሚሄድ አታዳምጡ !
✍️فتاوى : - ⬇️
▪️سائل يقول:-
ما حال قراءة إسلام صبحي؟
👇👇👇
@tewihd
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
☝️አሏህ ሰባቱን ይስጠን!
ኢንሻ አላህ...
✓ ከአላህ እገዛውን እየጠየቅን, ከዚህ በኋላ ጥያቄዎችን (ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ) ቀጣይነት ያለውና በደሩሪ ሀጃ ምክንያት እንጂ መልቀቅ ያለማቆም ስራ እንሰራለን!
"ቻናሉ ይጠቅማቸዋል" ለምትሏቸው ሰዎች ሼር በማድረግ ወደ ኸይር ነገር አመላክቷቸው።
والله مجزيكم به!
➣ ቻናሉን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ ↴↴↴
@tewihd
💬 ለአስተያየት ↴
@eross_11
🔴ጀለቢያ በመልበስ እና ኢማማ በመጠምጠም እጅ ከፍንጅ ተይዘሃል'' እያለ ነው።
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የደረሰበት ትልቅ ግኝትi
👇👇👇
@tewihd
አዋጅ‼️ ማንም ሰው በዲኑ ጉዳይ ሌላውን በጭፍን አይከተል። እንዲያ የሚያደርግ ከሆነ ሰውየው ሲያምን ያምናል፣ ሰውየው ሲከፍር ይከፍራል። አብዱላህ ኢብኑ መስኡድ ረዲየላሁ አንሁ አለ
አጥ-ጦበራኒ: 9/152
👇👇
@tewihd
⭕️ቀብር ላይ ስም መፃፍ
⭕️هل يجوز أن تكتب في قبر الميت اسمه
الشيخ عبد الحميد الحجوري
👇👇👇
@tewihd
ታገስ!
አውሮፕላን ውስጥ ሆነህ አንድ የሚያበሳጭ ነገር ቢገጥምህ "ወራጅ አለ!" አትልም እኮ ብስጭትህን ዋጥ አርገህ መሬት እስክታርፍ ትታገሳለህ። አሁን የሚገጥሙህን ፈታኝ ነገሮች በትዕግስት ማሳለፍ ከቻልክ የጊዜ ሚዛን ላንተ ማዳላቱ አይቀርም፤ ታገስ ወዳጄ!
copy @eross_eross
(አባቱም) አለ ልጄ ሆይ !ህልምህን ለማንም አታውራ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብካልና ሰይጣን ለሰው ግልፅ ጠላት ነውና ።( ዩሱፍ : 5)
ፀጋህን ለሁሉም አትናገር ሁሉም ሰው ላንተ ወዳጅ አይደለምና ለሁሉም ምቹ የሆነ የተከፈተ መፅሀፍ አትሁን❗️❗️
👇👇
@tewihd
ውሎህን በዚህ ፈካ አርገው
አስባቹሁታል ግን ሰው ከዚህ የበለጠ እርካታ ሚሰጠው ስላገኘ ይሁን እራሱን በሙዚቃ በነሺዳ በመንዙማ ውስጥ ሚደበቀው!
👇👇👇
@tewihd
▫️¦¦ وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ¦¦▫️
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ "(ኢስራዕ፣32)
▪️ الشاب : يوسف_أبكر
ወጣት:- ዩሱፍ አበከር
▫️ 🏠مدينة : جدة 239
•|| قنــاة تلاوات خاشعة
@tewihd
ሼር ሼር ሼር
ፎቶ__ፎቶ ነው!
የነጭ ሆነ የአረብ ሆነ የሀበሻ ሆነ!
በሂጃብ በኒቃብ ተሸፈነ + የተገላለጠ ሆነ + በጥምጣም ሆነ በቶብ ፎቶ ፎቶ ነው!
☞ ተዘቀዘቀም + ቀለም ተሰመረበትም ፎቶ ፎቶ ነው!
ልዩነቱ መሸፈኑና መገለጡ + መዘቅዘቁና ቀለም መቀባቱ ነው!
አዘለም አቀፈም ያው ተሸከመ ነው!
ከፎቶ ነቱ አይቀየርም!
አወ
👉አንዳንድ እህትና ወንድሞች የፎቶን ክልከላ!
ለተገለጡት ብቻ እንደሆነ አስመስለውታል!
👉 ሂጃብ + ኒቃብ ለብሶ ፎቶ
ቶብ/ ጀለብያ + ጥምጣም ……………… ለብሶ ፎቶ ነው!
👉 ቆይ ለእነርሱ ለብቻው የተወረደ ፎቶ ሀላል ነው ያለ ሀድስ አለ እንዴ??
ካለ መረጃውን አንጡ!
👉 የሚታወቀው ፎቶ ክልክል እንደሆነ ነው!
ለዚህም
👉 ስለ ፎቶ ክልክልነት ብዙ ተብለናል!
ከተባልነውም መካከል ጥቂቶቹ እነዚህን ይመስላሉ!
١ 👈 #عن ابن عباس رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم :- قال
كل مصور في النار يجعل له
بكل صورة صورها نفساً فتعذبه في جهنم،
👉 ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል:-
ሁሉም ፎቶ አንሽ የእሳት ነው!
ሲቀርፀው በነበረበት ፎቶ ሁሉ ነፍስ ተደርጎበት በዚያ እሳት ውስጥ ይቀጣል!
(رواه مسلم)
٢ 👈 #عن عبدالله بن مسعود رضي الله عنه قال:-
سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم :-
يقول إن أشدّ الناس عذاباً عند الله يوم القيامة المصورون،
👉 አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየአሏሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ!
የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ!
👉 ከሰዎች መካከል ቅጣት የሚበዛባቸው ፎቶ አንሽዎች ናቸው!
[رواه البخاري (٥٩٥٠) ومسلم (٢١٠٩)]
٣ 👈 #نهى صلى الله عليه وسلم:-
عن الصور في البيت، ونهى الرجل أن يصنع ذلك،
👉 ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ፎቶ ቤት ውስጥ እንዳይገባ ብለው ከልክለዋል!
👉 ሰዎቹንም ፎቶ እንዳይሰሩ ከልክለዋል!!
[ السلسلة الصحيحة (٨٠٩/١)]
👉 አያችሁ አይደል?
እሄ በትንሹ ነው ከዚህ በላይ መጨመር ይቻል ነበር ፅሁፉ እንዳይረዝም ስለተፈለገ ነው!
👉 እህቴ ሆይ!
አንች ተሸፍነሽ በየ ሚድያው ፎቶሽን እያንከራተትሽ!
የተገለጠችዋን ፎቶ ስታይ ለማውገዝ ከመቸኮልሽ በፊት!
አንች ከምትነሽው ፎቶ ተቆጠቢ!
👉 ስለተሸፈንሽ ሀላል አይምሰለሽ!
የተከለከለ እየተዳፈርሽ ነው!
የሱና ወንድሞችሽንም እየፈተንሽ ነው!
አው 👉 ከተገለጠችው በላይ በተሸፈነችው እንስት ይፈተናሉ!
የተፈተኑም አሉ!
እናም እህቴ አላህን ፍሪ!
ክልክልን አትዳፈሪ!
ወንዶችንም አትፈትኒ!
👉 የምታስተላልፊው መልዕክት ካለ ከፎቶ ውጭ ባለ ነገር ማስተላለፍ ይቻላል!
የግድ ፎቶ ካልሆ ያለ የለም!
👉 ሌላኛዋ ደግሞ!
አንችም አላህን ፍሪ!
የሰዎች ፎቶ ስለሆነ ሀላል አይምሰልሽ!
👉 በመዘቅዘቅና በቀለም መቀባት ከሚዲያ ሚድያ የምታሯሩጭው ክልክል የሆነ ፎቶ ነው አላህን ፈርተሽ ተቆጠቢ!
ካለ ፎቶ መልዕክቱን ብቻ አስተላልፊ!!
ወንድም!
👉 አንተም አላህን ፍራ!
በጥምጣም + በቶብ/በጀለብያ ስለሆነ የተነሳኸው ሀላል አይምሰልህ! ክልክል ነው!
👉 #አንተኛው ወንድም ደግሞ!
እባክህን ደዩስ አትሁን የራስህ አልበቃህ ብሎ የልጂና የሚስትህን በየሚድያው አትለጥፍ!
እንዲሁም ☞ ሰለጠን እንዳሉት ኩፋሮች/ኢስላምን የማያውቁ ሴቶች በየ ሚድያው + በየ ቲቪው ለምናምን ማስታወቂያነት እንደሚጠቀሙባቸው!
👉አንተም ሚስትህን የምናምን ማስታወቂ አታድርጋት!
ደዩስ አትሁን!
የግድ በእርሷ ካልተዋወቀ አይሸጥም አትበል!
ገበያ ሪዚቅ ነው! የርዚቅህን ታገኛለህ!
👉 በሚስትህ አስማምተህ ከምታገኘው በላይ!
እናም አላህን ፍራ!
በሚስትህም + በልጂህም አላህ እንዳይጠይቅህ ተጠንቀቅ!
So… …………… አላህን ፍሩ + እንፍራ!
ክልክልን የሆነን አንዳፈር!!
እላለሁ!
ወላሁ ተዓላ አዕለም!!
/channel/fewaedabibekr
copy_shear
ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👇👇
@tewihd
➡አደራህን አደራህን !!በወንጀለኛ ላይ አትኩራ።
➡በበጎ ስራህ የበላይነት አይሰማህ!!!
➡የሰዎችን ስሜት አትጉዳ!!!
➡ሁሉም ሰው የአቅሙን ይሰራልና።
ማን ተቀባይነት እንደሚያገኝ
የሚያውቀው 👉አላህ ብቻና ብቻ ነዉ
👇👇👇
@tewihd
በዚህች በጠፊዋ ዐለም ዱንያ ውስጥ ያሉ ነገራቶች ባጠቃላይ ወይ ትተዋቸዋለህ ወይ ይተውኳል።
አሏህ ሲቀር ወደ እርሱ ስትዞር የሚቸርክ ሲሆን ከእርሱ መንገድ ስትርቅ ደግሞ ወደ እርሱ መንገድ የሚጠራህ ነው
👇👇
@tewihd