🫵አንተ የሰራከውን ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሰዎችንም ወንጀል ትሸከማለክ።
መቼ❓
ለዚህ ቁርኣን መልስ ይሰጥካል አላህ እንዲህ አለ ፦
وَلَيَحْمِلُنَّ أَثْقَالَهُمْ وَأَثْقَالًا مَّعَ أَثْقَالِهِمْ وَلَيُسْـَٔلُنَّ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ عَمَّا كَانُوا۟ يَفْتَرُونَ
ሸክሞቻቸውንና ከሸክሞቻቸው ጋር (ሌሎች) ሸክሞችንም በእርግጥ ይሸከማሉ፡፡ በትንሣኤም ቀን ይቀጥፉት ከነበሩት በእርግጥ ይጠየቃሉ፡፡
ይህ ማለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ የምታሰራጨው: ዘፈን ፣ቪዲዮ ብቻ ምናለፋክ አንተ የላካቸውን መጥፎ ነገሮች ሰዎች ከፈፀሙት የነዚህን ሰዎች ወንጀል ትሸከማለክ።
አላህ ባንተ ምክንያት ዘፈን በሰሙ ሰዎች ይተሳሰብካል።
ባንተ ምክንያት መጥፎ ነገር ባዩ ሰዎች ወንጀል አንተን ይተሳሰብካል።
👉ወንጀሌ ይብቃኝ አትልም🤚
ስለዚህ ተጠንቀቅ ወንድሜ ❗️
✍AbuEkrima
@tewihd
ወላሂ በጣም ያስለቀሰኝን ፈታዎ አዳምጡትማ""
"አየ የበተሰብ ነገር""አየየ ነፍሴ"በጣም ከባድ ነው،،
""ሶላት ቀላል አደለም ወላህ""ባልተቤትህ ስላተ ትመስክረልህህህ""
⁉️""ባሌ"ሲፈልግ ይሰግዳለ""ሲፈልግ"አይሰግድም""ለሱ"የሚሰራ መልካም ስራ ይበቃልን""⁉️
✅ሸይኹ""አይበቃም"አይጠቅመውም"አላህ ይዘንለትም"አይባልም"""""
👇👇👇
@tewihd
አንድ ሺ ኢማሙል አልባኒ እና አንድ ሺ ኢብን ባዝ ያስፈልጉናል‼
(ኢማም ሙቅቢል አል ዋዲዒይ)
✍🏾 قال العلامة مقبل الوادعي رحمه الله :
«إن المجتمع الذي نعيش فيه محتاجٌ إلى تربية، ومحتاج إلى ألفِ شخصٍ مثلِ الشيخ ابن باز وألفِ شخص مثلِ الشيخ الألباني يُرَبُّونهم على العلم الصحيح وعلى التوحيد وعلى الدعوة إلى الله بِرِفْقٍ ولِين»
📚 (تحفة المجيب: ٢٨٤)
📌 «የምንኖርበት ማህበረሰብ ጥሩ ተርቢያ (አስተዳደግ) ያስፈልገዋል፤ በትክክለኛ እውቀት፣ በተውሒድና ወደ አላህ በሚያቀርቡት ደዕዋ ላይ በርህራሄና ለዛባ በሆነ መንገድ ተርቢያ የሚያደርጉ (የሚያንፁ) አንድ ሺ የሸይኽ ኢብኑ ባዝ አምሳያና አንድ ሺ የሸይኽ አልባኒ አምሳያ ያስፈልገዋል።»
(ቱሕፈቱል ሙጂብ: 284)
👇👇👇
@tewihd
የቤት ወጪ ማውጣትህ ኪሳራ አይደለም
🌴قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى:
*طلبُ الحلال ، والنفقة على العيال ؛ بابٌ عظيم لا يعدِلُه شيﺀٌ مِن أعمال البرِّ . انتهى
📚 الإيمان الأوسط ٦٠٩
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " دِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، وَدِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ فِي رَقَبَةٍ، وَدِينَارٌ تَصَدَّقْتَ بِهِ عَلَى مِسْكِينٍ، وَدِينَارٌ أَنْفَقْتَهُ عَلَى أَهْلِكَ، أَعْظَمُهَا أَجْرًا ؛ الَّذِي أَنْفَقْتَهُ عَلَى أَهْلِكَ ". رواه مسلم
@tewihd
⭕️👉🏼ምንኛ ያማረ ድምፅ ነው الله ይጠብቅህ ።
⭕️👉🏼በአሁን ሳዓት ሀበሻ ላይ የሚገኙት የሸይኽ አቡ ሰለማ ሱለይማን አል_ዒማድ ልጅ ነው ሁለቱም አላህ ይጠብቃቸው።
👇👇👇
@tewihd
እዋጅ!! አዋጅ!! አዋጅ!!👇👇👇
እኛ ሙስሊሞች መመሪያችን ቁርእን እና ሀዲስ ነው። ከዛ ውጭ ያለ ማንም ይሁን ማን አሊም ሆነ ጃሂል፣ ተማሪ ሆነ አስተማሪ ንግግሩ ወይም አስተምህሮቱ ቁርአን እና ሀዲስን ከገጠመ እንቀበለዋለን ካልገጠመ ደግሞ አርቀን ካጥር ውጭ እንጥለዋልን ምክንያቱም ዲናችን ለሀቅ እንጂ ለማንም ወገንታዊ እንዳንሆን ነው የሚያስተምረን።
وعن ابن عباس قال: ما أحد من الناس إلا يؤخذ من قوله ويدع غير النبي صلى الله عليه وسلم. والله أعلم .
ታላቁ ሱሀብይ አብደላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ ይላል '' ማንም እካል ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ውጭ ንግግሩ ይያዛል
ይተዋልም" ማለትም የማንም አካል ንግግር ተቀባይነቱም ሆነ ተምላሽነቱ የሚለካው በሀቅ ወይም በመረጃ ጋር በመግጠሙ እንጅ ሀቅ ወይም ትክክለኛው መንገድ በሰዎች እይለካም።
@tewihd
ሸይኽ ሙቅቢል አል ዋዲዒይ እንዲህ ይላሉ 👇
አሁን ያሉ የሙስሊም መንግስታቶች ኢስራኤልን ተዋግተው ፊሊጤንን ይከፍታሉ ተብሎ አይከጀልም ምክንያቱም እነሱ የአሜሪካ ቅጠረኞች ናቸውና
ፊሊስጤን ዙሪያ ያሉ መንግስታቶችም የኤስራኤል ዘበኞች ናቸው ።
👇👇👇
እኔ የምለው ይህ እንዲህ ከሆነ የመጀመሪያው ቂብላችን ማነው የሚያስመልሰው ⁉️
የመጀመሪያው ቂብላችን አስመልሳለሁ ብሎ የሚታገለው በኤስራኤል ቦንብ የሚጋየው ፋሲቅም ይሁን ሙብተዲእ ሙስሊም እስከሆነ ድረስ ባናግዘውም ወይም ዱአ ባናደርግለትም ጂሀዱን እንደ ወንጀል መቁጠሩ እንዴት ታዩታላቹህ ❓
ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል
إن الله ليؤيد هذا الدين بالرجل الفاجر
አላህ ከፈለገ ዲኑን አመፀኛ በሆነ ሰውም ይረዳል ።
ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል 👇
فكم من مُقاتلٍ، وكم من مجاهدٍ، وكم من يرائي نفع الله به في الإسلام، وهو ليس من أهل الخير، وهذا الواقع شاهد بذلك.
አላህ እንዲህ ይላል
{ الۤمۤ (١) غُلِبَتِ ٱلرُّومُ (٢) فِیۤ أَدۡنَى ٱلۡأَرۡضِ وَهُم مِّنۢ بَعۡدِ غَلَبِهِمۡ سَیَغۡلِبُونَ (٣) فِی بِضۡعِ سِنِینَۗ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡرُ مِن قَبۡلُ وَمِنۢ بَعۡدُۚ وَیَوۡمَىِٕذࣲ یَفۡرَحُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ (٤) }
[سُورَةُ الرُّومِ: ١-٤]
በሩሞችና በፋርሳውያን መሀል በነበረው ጦርነት
ሩሞች ሲያሸንፉ ሰሀቦች ተደስተዋሉ
በሩሞቹ ድል ሰሀቦች የተደሰቱት ሩሞች ሙስሊሞች ሆነው አይደለም ካፊሮች ነበሩ
ግን አህለል ኪታቦች ነበሩ ፉርሶች ደሞ ጣኦት አምላኪ ሙሽሪኮች ነበሩ ሙሽሪኮቹ ከሚያሸንፉ አህለል ኪታቦቹ ማሸነፋቸው ስለሚሻል ሰሀቦች በሩሞች ድል ተደሰቱ
👇👇👇
@eross_eross
የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ሚዛናዊነት
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : هذا وأنا في سعة صدر لمن يخالفني؛ فإنه وإن تعدى حدود الله في بتكفير أو تفسيق أو افتراء أو عصبية جاهلية ؛ فأنا لا أتعدى حدود الله فيه بل أضبط ما أقوله وأفعله وأزنه بميزان العدل وأجعله مؤتما بالكتاب الذي أنزله الله وجعله هدى للناس حاكما فيما اختلفوا فيه قال الله تعالى"
📚 مجموع الفتاوى (245/3)
"እኔ በሃሳብ ለሚለየኝ አካል ሆደ ሰፊ ነኝ። ከኢስላም በማስወጣት ወይም በማውገዝ ወይም በኔ ላይ በመቅጠፍ ወይም ደግሞ የመሃይማን ወገንተኝነት በማንፀባረቅ ድንበር ቢያልፍብኝም እኔ በሱ ላይ ድንበር አላልፍበትም። ይልቁንም የምናገረውንም ሆነ የምፈፅመውን እቆጣጠራለሁ። በፍትህ ሚዛንን እመዝናሁ።
(ንግግሬንም) አላህ ባወረደውና ለሰዎች መቅኛና በሚለያቲሸርት ጉዳይ ላይ ዳኛ ባደረገው መጽሐፍ (ቁርኣን) የሚመራ አደርጋለሁ።"
【መጅመዕ አልፈታዋ 3/245】
@tewihd
ቆም በል!
ለእየንዳንዷ ወንጀል አኺራ ላይ ቅጣት እንዳላት ሁሉ ዱንያ ላይም መራራ ቅጣት አላት።
‹‹እስካሁን ለፈፀምኩት መች ተቀጠሁ?›› ካልክ ተከተለኝ።
-የዱዓ እርካትህን እና ተቀባይነትን አልተነጠቅህም?
-ቁርአንን ሳትቀራ ሂጃብ ተደርጎብህ ቀናትን አላስቆጠርክም?
-ለይል ሰላት ሳትቆም በርካታ ሌሊቶች አላለፉም?
-ዚክር ከማድረግ ምላሶችህ ላይ ሂጃብ አልሆነም?
-በገንዘብ እና በክብር ፍላጎት እንድትኳትን ናላህን አላዞረብህም?
-ዒባዳዎችን መፈፀም እንደተራራ ገዝፈውብህ እንድታያቸው አላደረገብህም?
-ውሸት፣ ሀሜት እና ተራ ወሬዎችን በምላስህ እንዲቀልልህ አላደረገምን
@tewihd
ማንን ትመስላለህ?~~~~~~~~~~~~
ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለም "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው" ብለዋል። [አቡ ዳውድ ዘግበውታል።]
እኔ እምልህ ወንድሜ! አንተ ማንን ትመስላለህ? አለባበስህ፣ አነጋገርህ፣ የፀጉር አቆራረጥህ፣ ሁኔታህ፣ … የማንን ይመስላል? ውሎህ ከማን ጋር ነው? የማንን በአል ታደምቃለህ? ሙስሊም መሆንህን ሰው በቀላሉ አይቶ ይለይሀል ወይ? ለ"አሰ፞ላሙ ዐለይኩም" ትመቻለህ ወይ? "ደግሞ ለ‘አሰ፞ላሙ ዐለይኩም’ የሚመችና የማይመች አይነት ሙስሊም አለንዴ?!" አልከኝ?! እንዴታ! ሙስሊምነትህ ለአላፊ አግዳሚ ሙስሊም ካልታወቀ የሰፈርህ ልጅ ካልሆነ በስተቀር ማን "አሰ፞ላሙ ዐለይኩም" ይልሀል?!
ወንድሜ! የተግባር ሙስሊም ሁን። ሙስሊሞችን ምሰል። መልካም ሰዎችን ምሰል። በካፊር አትመሳሰል። ጋጠ ወጦችን፣ ፍንዳታዎችን፣ ዘልዛላዎችን አትምሰል። የርካሽ ፋሺኖች ማራገፊያ፣ የቆሻሻ አስተሳሰቦች መድፊያ አትሁን። እራስህን ሁን።
👇👇👇
@tewihd
👉 አኽላቃችን ሲታይ ገና ነን እኮ ❗️
👉 ዘመኑ የመተጋገዝ ሳይሆን የመጠቃቀም ሆኗል
👌 ሁሉም የራሱን መስለሀ ነው የሚፈልገው
ነፍሴ ነፍሴ ባይ በዝቷል
👇 ብዙዎች የሚፈልጉት
➤ መርዳት ሳይሆን መረዳት
➤ ማገዝ ሳይሆን መታገዝ
➤ መጥቀም ሳይሆን መጠቀም
➤ መስጠት ሳይሆን መሰጠት
➤ ማክበር ሳይሆን መከበር
➤ መስማት ሳይሆን መሰማት
➤ ነው ነው ነው
👌 አንድ ሰው ብድር ጠይቆህ ብትከለክለው አንተ በተራህ ተቸግረህ ብድር ጠይቀሀው ሚከለክልህ ጊዜ ሊመጣ ይናፍቀዋል
👌 ታሞ ካልጠየቅከው መታመምህን ይጠብቃል
➤ ቁጭ ብሎ ውድቀትህን ይጠባበቃል
➤ ሀሰድ ምቀኝነት የተባለው እኮ ይሄው ነው
በቁርአን
፡ وَيُؤْثِرُونَ عَلَى أَنْفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ
ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ
የተባሉ አይነት ሰዎች አሉ ይሁን በዚ ዘመን ❓
✍ አቡ መርየም
👉@tewihd
كتاب ــــــ مجالس شهر رمضان
تأليف ــــ ابو عبد الرحمن عبدالله بن احمد الارياني
👌 ስለ ረመዳን ወር የተፃፈ ኪታብ ነው
@tewihd
➡️ ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" ከአካላችን እንቅስቃሴ ሁሉ ቀላሉ የምላስ እንቅስቃሴ ነው በአንድ ሰው ላይ በጣም ጎጂው እሱ ነው "
አል ጀዋቡል ካፊ ገፅ ( 281 )
👇👇👇
@tewihd
#ፈታዋ_ረመዳኒያ
❗️"አንድ ሰው ያለ ምንም ኡዝር ያለበትን ጾም ቀዳ ሳያወጣ ሌላኛው ረመዳን ከገባበት ወንጀል አለበት ሆኖም (ተውበት ከማድረግ ጋር) ቀዳ ማውጣት ይኖርበታል ። ሚዛን በሚደፋው አቋም መሰረት ሚስኪን ማብላት አይጠበቀበትም።"
📚【ፈታዋ ኡሰይሚን (ቅፅ 19/ገጽ 385)】
👇👇👇
@tewihd
የጥበበኛው ሉቅማን ምክሮች
#ልጃቸውን እንዲህ በማለት ምክር ሰጡት፦
#ዱንያ (ምድራዊ ህይወት) እንደ ጥልቅ ባህር ነች በሷም ብዙዎች ሰምጠዋል፡፡ስለዚህ በሷ ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለክ ጀልባህን የአላህ ፍራቻ መቅዘፊያህን ኢማን መንገድህን ደግሞ በአላህ ላይ መመካት አድርግ፡፡»
ልጄ ሆይ!
ከፈሪሃ አላህ ሰዎች ጋር ሁሌም ተጎዳኝ እነርሱ በሚሰሩት ስራ ተካፋይ ትሆናለህና በተጨማሪም የአላህ ልዩ ፀጋ በነርሱ ላይ ሲወርድ አንተም ከድርሻው ታገኛለህና ከመጥፎ ሰዎች ጋር አትጎዳኝ ከነርሱ የሚገኝ መልካም ነገር የለምና፡፡ይልቅስ የአላህ ቅጣት በወረደችባቸው ጊዜ አንተም ከቅጣቱ ተካፋይ ከመሆን በቀር፡፡
ልጄ ሆይ!!
#ዘወትር አቀማመጥህ ከኡለማዎች ጋር ይሁን እነዚህ ብልሆች የሚናገሩትን ከልብህ አድምጥ፣ ከአላህ መልካም ምንዳ በተስፋ ስትጠብቅ ቅጣቱንም በመፍራት ይሁን፣ ዘወትር ጌታህን ከሀጢያትህ ይምርህ ዘንድ ጠይቅ፡፡»
ልጄ ሆይ!!
#ከሀሰት ጨርሶ ራቅ ሀሰት ጠላትን እንጂ ወዳጅን፣ ጥላቻን እንጂ ፍቅርን አያፀናም፡፡ በቀብር ስነ ስርዓት ላይ ዘወትር ተገኝ የነገን ሞት ያስታውስሃልና፡፡ ከድግስና ከጭፈራ ቦታ ራቅ ድግስ ከንቱ አለማዊ ደስታን እንድትናፍቅ ያደርግሃል አላህ ዘንድ ስትቀርብ ይዘኸው የምትሄደውን ስራ ያዘናጋሀል፡፡ ያለመጠን አትመገብ፡፡»
ልጄ ሆይ!!
#እጅጉን ጣፋጭ አትሁን ሰዎች ይበሉሃል ፣ እጅግም መራራ አትሁን አንቅረው ይተፉሃል፡፡ ሌት እንደ ዶሮ ንቃት ይኑርህ፣ ለተውበት ዛሬ ነገ አትበል ሞት አዘናግቶ ይወስድሃልና፡፡ ከጅላጅሎች አትጎዳኝ አይረቤ ንግግሩንም አትከታተል፡፡ ከብልህ ሰዎች ጋር ፀብ አትፍጠር ካንተ ከሸሹ ከዕውቀታቸው ተጠቃሚ አትሆንምና፡፡»
ልጄ ሆይ!!
#አላህን ከሚፈራ ካልሆነ ሰው ጋር አትመገብ ምንጊዜም ኡለማዎችን አማክር፡፡ ከዕዳ ሽሽ ዕዳ የቀን ውርደት የማታ ፀፀት ናት፡፡ ከአላህ ራህመት ተስፋ አትቁረጥ ተስፋህ ያለ ቅጥ ደንድኖ ለሃጢያት እንዳያበቃህም ተጠንቀቅ፡፡ አላህን ፍራ ፍርሃት ግን ከእርሱ እዝነትና ተስፋን አስቆራጭ አይሁን
@tewihd
ተነስተሀል!!
አዎ ዛሬ ሌላ ቀን ነው።በረጅሙ ተንፍስ,አላህን አመስግን,ዛሬ የመጀመሪያ አዲስ ቀን ነው።ወንድሜ አደራህን በትናንት ሽርፍራፊዎች ዛሬህን እንዳትጀምረው።
ዛሬ ከእቅዶችህ ውስጥ አንዱ ግቡ የሚመታበት ቀን ነው።
@eross_eross
:
📚ተውሂድ የሁሉም ነብያት ተልዕኮ
አላህ በተለየዩ ዘመናት በርካታ ነቢያትን ልኳል፡፡ እነዚህ ነብያት ለተላኩላቸው ሕዝቦች ያስተምሩ የነበረው የአላህን ብቸኛ አምላክነት የሚገልፀውን (ተውሂድ አል ኡሉሂያ) የተውሂድ ክፍል እንደነበረ ቅዱስ ቁርአን ይነግረናል፡፡
وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اُعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ... النحل: ٣٦ط
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡›› (አል ነህል 36)
በሱረቱል አንቢያ ውስጥም አላህ (ሱ.ወ) ወደየህዝቦቻቸው ስለላካቸው መልዕክተኞች ለነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፅላቸው እንዲህ ይላል፡-
وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلاَّ نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لا إِلَهَ إِلاَّ أَنَا فَاعْبُدُونِ... الأنبياء: ٢٥
‹‹ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡›› (አል አንቢያ 25)
በየዘመናቱ ወደ ሕዝቦቻቸው የተላኩ ነቢያት በአቂዳ ዙሪያ ጠንከር ያለ የፀና አቋምና እምነት እንዲኖራቸው ነበር፡፡ ሕዝባቸውን ያስተምሩና ይመክሩ፣ ያስጠነቅቁና ይዘክሩ የነበረው፡፡
@tewihd
የሚበጅህን ምረጥ
~~
ዑመር ኢብኑል ኸጧ፞ብ ረዲየላ፞ሁ ዐዘንሁ እንዲህ ይላሉ:–
"ከታገስክ የምትመነዳ ሆነህ የአላህ ውሳኔ ይፈፀማል።
ተስፋ የምትቆርጥ ከሆንክ ወንጀለኛ ሆነህ የአላህ ውሳኔ ይፈፀማል።"
~
[ተሕቂቁ ዙ፞ኑን ቢ አኽባሪ ጧ፞ዑን፣ መርዒ ኢብኑ ዩሱፍ: 4/126]
👇👇👇
@tewihd
#ተውሒድ
⚙ተውሂድ የአንድነት ምንጭ ነው።
⚙ተውሂድ የዱኒያም የአኬራም የደስታ ምንጭ ነው።
⚙ተውሂድ ነብያት የተላኩበት አላማ ነው
⚙ተውሂድ የሰው ልጅም አጋንንት የተፈጠሩበት አላማ ነው።
⚙ተውሂድ የሸፍአ ዋስትና ነው።
⚙ተውሂድ በቁርዐን የመጀመሪያ ትዕዛዝ ነው።
⚙ተውሂድ ከጭንቀት ከትካዜ የሚያላቅቀን የደስታ ምንጭ ነው።
⚙ ተውሂድ ከጀሀነም መዳኛ ሰበብ ነው።
⚙ተውሂድ የጀነት ቁልፍ ነው።
⚙ተውሂድ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዳዕዋቸውን የጀመሩበት
የጨረሱበት ነው።
⚙ተውሂድ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተደበደቡለት ምክንያት ነው።
⚙ተውሂድ ነብዩላሂ ኢብራሂም አለይሂ ሰላም) እሳት ውስጥ የተወረወሩበት
ምክንያት ነው።
⚙ተውሂድ የእኛ የመፈጠር ምክንያት ነው እና ህብረተሰቡውን በተውሂድ
እናንፅ!!!
👉 @tewihd
ከተግባር ሁሉ በላጩ.....
ነብያችን (صلى الله عليه وسلم) ከሶሀቦች ጋር በተሰበሰቡበት አንድ ሰው፦
"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!ከሁሉም የተሻለው ተግባር የቱ ነው?" ሲል ይጠይቃቸዋል።
እርሳቸውም፦ "ዕውቀት" ሲሉ ይመልሱለታል። ከዚያም "ምን አይነት ዕውቀት?" ሲል መልሶ ይጠይቃቸዋል።
እርሳቸውም ሲመልሱ፦ "ስለአላህ የሚኖር ዕውቀት" ይላሉ።
እነርሱም፦ "ስለተግባር ስንጠይቅዎ እርሶ ስለዕውቀት ነው የሚነግሩን" ይሏቸዋል።
ነብያችንም (صلى الله عليه وسلم) "ስለ አላህ ባለን እውቀት ላይ ተመስርቶ የተሰራ ትንሽ ስራ አትራፊ ነው። በአላህ ላይ ባለን እውቀት ያልተመሰረቱ ብዙ ተግባራት ትርጉም አይኖራቸውም።" ሲሉ መለሱ።
ጆይን👇
/channel/tewihd
‹‹ኡስታዝ እኔ ተቸግርያለሁ፤ የሴት ነገር ከአቅሜ በላይ ሁኗል። በየጎዳናው እነሱን ማየት ሱስ ሁኖብኛል ና እንደው ምን ተሻለኝ? ›› ይላል አንድ ጎረምሳ ከኡስታዙ ፊት ሁኖ።
በትዝብት እየተመለከቱት አንድ በወተት እስከአፉ የተሞላ ብርጭቆ ሰጥተውት፦‹‹ይችን ይዘህ በጎዳናው በኩል ዙረህ ና፤ ምናልባት ከወተቱ ጠብ ቢል እንኳ ከኋላህ ሁኖ ሚኮረኩምህን መድቤብኃለሁ›› አሉት።
ጎረምሳው ወተቱን ይዞ በጥንቃቄ ጉዞውን ጀመረ፤ ምንም ሳይደፋበትም ጎዳናውን ዙሮ ሼኩ ዘንድ ደረሰ።
‹‹አሁን ስንት ልጃገረዶችን አየህ ጎዳናው ላይ›› አሉት ሸይኩ።
‹‹ኧረ ምንም አላየሁም! ከኋላዬ ኮርኳሚ መድበውብኝ እንዴት ነው ወተቱን ትቼ ሴት እማየው›› ብሎ መለሰላቸው።
‹‹የሙእሚን ባህሪም አላህን በመፍራት ላይ ይህን ያህል ነው በጥንቃቄ ሊሞላ ሚገባው። ›› ብለው በጥበብ አለንጋ ከመስመር አስገቡት።
Copy
@tewihd