tfanos | Unsorted

Telegram-канал tfanos - Tesfaab Teshome

2111

ለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ። ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍

Subscribe to a channel

Tesfaab Teshome

"እንደ ኢየሱስ ...."
* * *

በእለተ ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን1976 አ.ም፥ ቁመተ መለሎው ወታደር ፥ የኩባ ጦር አካዳሚ ምሩቁ፥ የአይየር ሃይሉ ኮማንዶ፥ ምክትል መቶ አለቃ ላቀው በዛብህ ለምልምል ወታደሮች ትምህርት ሊሰጥ ተሰይሟል። እጩ ወታደሮች በግማሽ ክብ ሰርተው ምክትል መቶ አለቃውን በተመስጦ ይከታተሉታል።

መልከ-ቀናው ወታደር "ዛሬ ስለ እጅ ቦንብ አስተምራችኋለሁ" ካለ በኋላ ቦንቡን አወጥቶ "ይህ የቦንቡ ዋና አካል ነው..." እያለ ማብራሪያ መስጠት ጀመረ። ጥቂት ሲያስተምር ከቆየ በኋላ ግን የተለየ ነገር አደረገ።

ድንገት በታላቅ ድምፅ "ዞር በሉ፥ ዞር በሉ፥ ዞር በሉ" እያለ መጮህ ጀመረ። ከምልምሎች መካከል ጥቂቶቹ አንዳች ተውኔት የሚያዩ መሰሉ። ሌሎቹ ነገሩን እንደ ቀልድ ቆጠሩት። ከፊሎቹ ደግሞ የሰልጣኞቹን ስነ ልቦና ለመለካት እየተደረገ እንዳለ ማስፈራሪያ አሰቡ።

ከ1972- 1975 ወደ ኩባ አቅንቶ ውትድርናን የተማረው፥ የደብረዘይቱ አየር ሃይል ወታደሩ፥ ባለ ሉጫ ፀጉሩ አሰልጣኝ ፥ ቁመተ ለግላጋው ኮማንዶ ፥ ምክትል መቶ አለቃ ላቀው በዛብህ በሃይለኛ ድምፅ እና በተሸበረ መንፈስ ሆኖ "ዞር በሉ" እያለ የማጓራቱን ሰበብ በአግባቡ የተረዳ አልነበረም።

ምክትል መቶ አለቃው ፥ በቀኝ እጁ ቀለበቱ የተነቀለለትን ቦንብ ይዞ በግራ እጁ 'ከዚህ አከባቢ ሽሹ' የሚል ምልክት እየሳየ በከፍተኛ ድምፅ "ዞር በሉ" ሲል ምልምሎች ነገሩን እንደ ቀልድ ስለተመለከቱ በህብረት ሳቁ።

ምክትል መቶ አለቃው ግን "እባካችሁ ዞር በሉ፥ በሆዳችሁ ተኙ" አለ። ድምፁ የጭንቀት ነበር።
እርሱ በእጁ ሞት ጨብጧል። በሴኮንዶች እድሜ የምልምሎቹን ህይወት የመታደግ ሃላፊነት አለበት። ከርሱ ሊማሩ የተሰበሰቡትን ህይወት ከአደጋ የመጠበቅ ወታደራዊ ግዴታ ወድቆበታል።
ምልምል ወታደሮች ከሞት ጋር እንደተጋፈጡ አያውቁም። ከጥቂት ሴኮንድ በኋላ እዛ ስፍራ ጅምላ ጨራሽ ሞት ይከሰታል። ይህ ከመሆኑ በፊት በጭንቀት ሆኖ "ዞር በሉ" ብሎ ተማፀነ።

ምክትል መቶ አለቃው "ዞር በሉ" ብሎ ከጮኸ በኋላ ፊቱን አዞሮ ጀርባውን ለሰልጣኞች ሰጠ። በእጁ የጨበጠውን ቦንብ ሆዱ ላይ አጣብቆ ተኮራመተ። በዛች ቅፅበት ታላቅ ፍንዳታ ሆነ። ሰልጣኝ ወታደሮች በየአቅጣጫው ሮጡ።
የወታደሮቹ አሰልጣኝ ስጋ እና ደም ሜዳው ላይ ተበታተነ። በደም የተጨማለቀ ቱታው ተበጣጠሰ።

ምክትል መቶ አለቃው ምልምሎች ላይ አንዳች ጉዳት እንዲደርስ ስላልወደደ እራሱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የነርሱን ህይወት አደነ።

ያኔ ፥ በአሰልጣኛቸው መስዋዕትነት ህይወታቸው ከተረፉ ሰዎች መካከል አንዱ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ሲሆን "የማይፃፍ ገድል" በሚለው መፅሐፉ የአሰልጣኛቸውን የጀብዱ መስዋዕትነት 'እንደ ኢየሱስ' በማለት በዝርዝር ፅፎታል።


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

በቦክስ ውድድር ህይወታቸውን ያጡ ቡጠኞች
* * *

በቦክስ ውድድር ወቅት ጉዳቶችን መመልከት የተለመደ ሊሆን ቢችልም አንዳንድ አጋጣሚዎች ግን እጅግ ዘግናኝ ይሆናሉ። አስፈሪ ጉዳቶች፥ ሲከፋ ደግሞ የህይወት መቀጠፍ ይከሰታል።

ከቡጢ ተፋላሚዎች መካከል እድል የከዳቸው ጥቂት ቦክሰኞች ግዳይ ሊጥሉ በገቡበት ሪንግ ወድቀው በዛው ቀርተዋል፥ ላይመለሱ አንቀላፍተዋል፥ እስከወዲያኛው አሸልበዋል።
ለቦክስ ግጥሚያ ወደ ሪንግ ገብተው ሞት ከጎበኛቸው መካከል ጥቂቶችን እንተዋወቅ።

1፥ ፍራንኪ ካምቤል

ጣሊያን- አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቡጠኛ ሲሆን ካደረጋቸው 40 የፕሮፌሽናል ግጥሚያ መካከል በ33ቱ ድልን የተቀናጀ ጀግና ነው!
በፈረንጆች አቆጣጠር፥ ነሐሴ 25 ቀን 1930 ላይ ቀን ከዳው። በሳንፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማክስ ቤየር ጋር ያደረገው ፍልሚያ የሞቱ ሰበብ ሆነ።
ፍራንኪ ካምቤል ሪንጉ ዙሪያ ወዳለው ገመድ ሲያመራ፥ ባየር በቀኝ እጁ ከባድ ቡጢ ባላጋራው ጭንቅላት አከባቢ አሳረፈ።
ቀጥሎ በተከታታይ ብርቱ ጡጫ ያስተናገደ ሲሆን ድብደባው ለከፋ ጉዳት ዳረገው።
የተፋላሚው ምት የበረታበት ካምቤል ወደቀ፥ ቀጥሎ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም ሃክሞች ነብሱን አልታደጉትም። በጭንቅላቱ ውስጥ በፈሰሰ ደም የተነሳ እስከወዲያኛው አሸለበ!

2፥ ፓትሪክ ዴይ

ከዩናይትድ ስቴትስ የተገኘ ቡጠኛ ነው።
ለርሱ እና ለቤተሰቡ ጥቁር በሆነች እለት የሐገሩ ልጅ ከሆነው ቻርልስ ኮንዌል ጋር ሊፋለም ወደ ሪንጉ ገባ። በሪንጉ ውስጥ ሶስት ጊዜ ወድቀ።
የ27 አመቱ ፓትሪክ ዴይ ነገሩ ሲከብደው ምልክት ሰጠ። ሁኔታው ያልጣማቸው ዳኛ ውድድሩን አስቆሙ።
ከዚህ በኋላ ቦክሰኛውን አጣድፈው ወደ ሆስፒታል ወሰዱት። እርሱ ግን ያልተለመደ አይነት መንቀጥቀጥ እና መንዘፍዘፍ ውስጥ ገባ። ሃኪሞች ሊረዱት እየተሯሯጡ ሳለም ራሱን ሙሉ ለሙሉ ሳተ።
ዶክተሮች የተፈራውን አደጋ ለማስቀረት ተረባረቡ፥ የአንጎል ቀዶ ጥገናም አደረጉለት።
ነገር ግን ህይወቱ ልትተርፍ አልቻለችም። ከ አራት ቀናት በኋላ ቦክሰኛው ሞተ።

3፥ ዴቪድ "ዴቪ" ኤስ ሙር

ከ1953 እስከ 1963 በፕሮፌሽናልነት የተፎካከረ ቡጠኛ ነው። ሐገሩ ዩናይትድ ስቴትስ ናት። በቦክስ ህይወቱ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
በአንድ የውድድር ወቅት ከሹገር ራሞስ ጋር ሊፋለም ወደ ሜዳ ገባ። በዛ የውድድር ወቅት ዴቪ ሙር ተገፍትሮ ሲንገታገት የሪንጉ ገመድ አንገቱን አገኘው።
ዳኛው ውድድሩን ከማስቆሙ በፊት ህመሙን ተቋሞ ውድድሩን ቀጠለ፥ አንዳች እክል እንዳልገጠመው ሰው ሆነ ተቧቀሰ።
እንደ አለመታደል ሆነና ከውድድሩ በኋላ ኮማ ወስጥ ገባ። ለ75 ሰአታት ያህል ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ ህይወቱ አልፈች።

4፥ ጄምስ ሙሬይ

ከወደ ስኮትላንድ የሆነው ቦክሰኛ ጄምስ መሬይ በመፋለም ሳለ ህይወቱን ያጣ ሰው ነው።
1995 ወርሃ ጥቅምት ላይ ከ Drew Docherty ለመቧቀስ ተገናኙ።
በቡጢ ውድድሩ መካከል ግን ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ፥ Murray ወደቀ።
በኋላ ላይ ሲጠራ የአንጎል ደም መፍሰስ እንደገጠመው ተረጋገጠ። በዚህም የተነሳ ላይመለስ አንቀላፋ

5፥ ኤድ ሳንደርስ

ከባድ ሚዛን ተወዳዳሪ ነው።
በታኅሣሥ 1964 ዊሊ ጀምስን ገጠመ። ይሄ የመጨረሻ መጋጠሙ ነበር።
ሳንደርደስ በውድድሩ ወቅት የድካም ስሜት ማሳየት የጀመረ ሲሆን ቀላል ጥቃቶችንም መቋቋም ተሳነው። ቀጥሎም ንቃተ ህሊናውን በማጣት ራሱን ስቶ ተዘረረ። እስከ ቀዶ ጥገና የደረሰ የህክምና ርብርብ ቢደረግም ማገግም ሳይችል ቀረ፥ ነብሱ ከስጋው ተለየች።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሰምንኛውን የአትሌቲክስ ውዝግብ ለመዳኘት ቀላሉ መንገድ ሰአት መመልከት ነው።

አቴሌትክስ የአደባባይ ውድድር ነው፥ ለመዳኘት ግልፅ ነው።

የፌደሬሽኑ ውሳኔ አግባብ መሆን አለመሆኑን ለመመዘን ያስመዘገቡትን 'ምርጥ ሰአት' መመልከት በቂ ነው።

ሌላው ክርክር ወንዝ የሚያሻግር አይመስለኝም

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ደርግ ከወደቀ በኋላ የሽግግር መንግስት ቻርተር ሲዘጋጅ ከአርቃቂዎቹ መካከል ኢሳያስ አፈወርቂ ነበረበት። ከሌንጮ ለታ እና ከመለስ ዜናዊጋ በመሆን ተሳትፎ አድርጓል።

'ኢሳያስ ምን አግብቶት እዚህ ውስጥ ገባ?' የሚል ጥያቄ የሚጠይቅ ካለ ሌንጮ መልስ አለው።

በቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ የተፃፈው ፊልስምና (6) መፅሐፍ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል።
ፖለቲከኛው ሌንጮ ቃል በቃል "ኢሳያስ አለቃችን ነበረ፥ የሚያዘንን እናደርጋለን፥ ከሱ ቃል አንወጣም" ብሏል።

(ኢሱ ጭሱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መፈትፈት ይወዳል

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

''አለምን ያመሱት ሰባቱ እህትማማቾች"
* * *

የነገሩ ስር የሚጀምረው በፈረንጆች የዘመን ቀመር 1928 ነሐሴ 28 ነው። በሐገረ ስኮትላንድ ደጋማ ስፍራ ነዳጅን መቆጣጠር ግቡ ያደረገ ፥ ገመናውን እንዳይታወቅ የተጠነቀቀ ሚስጥራዊ ጉዞ ተጀመረ።

ዜግነታቸው ሆላንዳዊ፥ አሜሪካዊ እና እንግሊዛዊ የሆኑ ሰዎች በሚስጥር ቀጠሮ ተገናኙ፤ በመገናኘታቸውም የአለምን ነዳጅ ስለመቆጣጠር እቅድ አበጁ።

በስብሰባው ከተገኙት መካከል ሆላንዳዊው ሄንሪ ዴተርዲንግ 'የነዳጁ ናፖሊዮን' የሚል ተቀፅላ ያገኘ ነው። ይህ ሰው እና ወዳጆቹ በጋራ በመሆን ድርጅትን መሰረቱ፥ ስያሜውንም 'ሮያል ደች ሼል' አሉት።

ከወደ አሜሪካ የሆነው ዋልተር ሲ ቴግል ስታንዳርድ ኦይል ኩባንያን ወክሏል። የነዳጅ ጉድጓዶች፥ ማጓጓዝ፥ ማጣራት እና ማከፋፈሉን በቁጥጥሩ ያውላል።
እንግሊዛዊው ሰር ጆን ካድማን ደግሞ የአንግሎ-ፋርስ የነዳጅ ኩባንያ ዳይሬክተር ነው

አልጀዚራ በአንድ ወቅት በሰራው ሰፋ ያለ ዘገባ እንዳተተው ከሆነ እኚህ ግለሰቦች በሚስጥር ተገናኝተው ከተማከሩ በኋላ የአለምን ነዳጅ በቁጥጥራቸው ለማስገባት ተነሱ፥ ይሄንም ለማሳካት ጦርነትን ፈጠሩ፥ ሴራ ጎነጎኑ።

በወቅቱ የመኪና ኢንዱስትሪ እድገቱ እጅግ ፈጣን ነበር፤ የአቶሞቢል ዘርፉ ገንዘብ በገፍ የምንቀሳቀስበት መሆን ጀምሯል። በዚህ የተነሳ ፕላኔታችን የነዳጅ ፍላጎቷ ከፍ አለ። ነዳጅም የረብጣ ዶላሮች መዘወሪያ ሆነ።

ያኔ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በሚስጥር ከተገናኙ በኋላ 'የነዳጅ ዘርፉ ላይ ዋነኛ አትራፊ ለመሆን የምናደርገውን ፍልሚያ እናቆምና አብረን እንስራ፥ የአለምን ነዳጅ እንቀራመት፥ ያለከልካይ ተባብረን ሃብት እናጋብስ' ተባባሉ፤ በዚህም ተስማሙ።
በስምነታቸው መሰረት ፥ የምርት ቀጠናዎችን፣ የትራንስፖርት ወጪዎችን የሽያጭ ዋጋዎችን ወዘተ.. ይጋራሉ። ይህን ዋና አላማ በማድረግ የአለምን ሀብት የመቆጣጠር እርምጃ ጀመሩ።

ሶስቱ ሰዎች ስራቸውን 'ሀ' ብሎ እንደጀመሩ እቅዶቻቸውን የሚጋሩ ፥ ሃሳባቸውን የወደዱ ሌሎች አራት ሰዎች ተጨመሩ። ቁጥራቸውም ሰባት ደረሰ፥ ነገሩ የሰባት ኩባኒያዎች ውል ሆነ። እኚህም ''ሰባቱ እህትማማቾች'' ተባሉ።
እንግዲህ ነገሩ 'የሳባቱ እህትማማቾች ሚስጥራዊ ስምምነት' ነው።

በፈረንጆቹ አቆጣጠር፥ ነሐሴ 28 ቀን 1928 አ.ም የመጀመሪያውን ስብሰባ ካከሄዱ በኋላ በብርቱ አቀዱ፥ ጠንክረው ሰሩ፥ ታትረው ሴራ ጎነጎኑ።

እጃቸውን ወደ ፖለቲካ ሰፈር መስደድ ጀመሩ፥ ፖለቲከኞችን ለጥቅማቸው በሚመች መንገድ ዘወሯቸው። በሐገረ ኢራን እና በሳውዲ አረቢያ ፖለቲካ ዘው ብለው በመግባት ለሚፈልጉት ወገን ድጋፍን ቸሩ።
ኢራን እና ኢራቅ ወደ ሞቀ ጦርነት ሲገቡ ትርፍ ለማጋበስ በማሰብ ወደ ጦርነቱ ቀጠና አሰላለፋቸውን አሳምረው ገቡ፥ ሁለቱ ሐገራት ደም ሲፋሰሱ እነርሱ የፈለጉትን የገንዘብ ጥቅም አገኙ። በሁለቱ ሐገራትን መፋለም ዶላር አተሙ!

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1960 ዎቹ አከባቢ ላይ 'ሰባቱ እህትማማቾች' የተባሉቱ እኚህ አካላት በሸረቡት ሴራ እየታገዙ 85 በመቶ የሚሆነውን የአለም የነዳጅ ክምችት እስከመቆጣጠር ደረሱ።

አሁን አለም ላይ ያላቸው የነዳጅ ቁጥጥር ከቀደመው ዘመን አንፃር የቀነሰ በመሆኑ አዲስ የትኩረት አቅጣጫ ቀይሰዋል። አልጄዚራ እንደሚለው ከሆነ ደግሞ የአደን ትኩረታቸው አህጉራችን አፍሪካ ሆናለች።

ሚሊዮኖች ከተቀጠፉት እና አመታትን ከተሻገረው፥ በመጨረሻም ደቡብ ሱዳንን በመነጠል ከተቋጨው የሱዳን እርስ በእርስ ጦርት ጀርባ በሱዳን ያለውን ድፍድፍ ነዳጅ መቆጣጠር የፈለጉቱ 'የሰባቱ እትማማቾች' እጅ አለ።

'ሰባቱ እህትማማቾች' ሰዎች አይደሉም፥ በሰዎች የተፈጠሩ ኩባያዎች እንጂ።
እኒህ ኩባኒያዎች በመጣመር በአንድ ዘመን የአለምን ነዳጅ ተቆጣጣሪ ለመሆን በቅተዋል። ከፖለቲካዊ ቀውሶች ጀርባ በመሰለፍ፥ በጦርነቶች በመሳተፍ፥ ሴራ በመጎንጎን ሃብትን አከባብተዋል።
ዛሬ ላይ በነዳጅ ላይ የሚያሳርፉት ተፅዕኖ የቀደመውን አይነት ባይሆንም ፥ የሃይል ሚዛን ቢቀየርም፥ ጉልበታቸው ልል አልሆነም።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ብዙ ጊዜ 'ኢትዮጵያ አትፈርስም' ሲባል እንሰማለን። ይሄን  ከዜጎች እስከ ፖለቲከኛ፥ ከአክቲቪስት እስከ ሃይማኖት አባት ይሄን ደጋግመው ይናገራሉ። ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው። በዛሬው አጀንዳ እንዳስሰዋለን
👇

https://youtu.be/8J-BdSEsLnU

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ልደቱ ብዙ ጊዜ ከፊታችን አደጋ እየመጣ እንዳለ ተናግሯል፥ አስፈሪ ነገሮችን ደጋግሞ ተንብዮ ያውቃል።

ቀጥሎ ስለሚመጣው አደጋ ሲያስጠነቅቅ እንደሟርተኛ ይቆጠር ነበር። በዚህ መሓል 'እኔ ሟርተኛ ሳልሆን የፖለቲካ ነብይ ነኝ' ለማለት አይዳዳውም። ሁሌም "እኔ የተናገርኩት ስህተት ሆኖ የናንተ ተስፋ ትክክል ቢሆን እመኛለሁ፥ ትንቢቴ ተሳክቶ ሐገር ችግር ላይ ገብታ ከማይ ግምቴ ከሽፎ የተሳሳተ ፖለቲከኛ ተብዬ ብፈረጅ እና ህዝብ ቢጠላኝ እመርጣለሁ" ይል ነበር።

ያኔ የተናገራቸውን የሚያደምጥ አልነበረም፥ 'ባይሳኩ ይሻላል' ያላቸው ትንቢቶቹ አንድ በአንድ አካል ለብሰዋል።

ቀጥሎስ? አድማጭ ያገኛል ወይስ የቀደመው ስህተት ይደገማል ?

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ከዚህ በፊት የፃፍኩትን ፅሁፍ ድጋሚ ላጋራችሁ አሰብኩ 👇

በዘመነ ደርግ ከኢህአፓ ጎራ በመሆን ከመንግስቱ ሃይለማርያም መንግስት በተቃራኒ ቆሞ የነበረው አንዳርጋቸው ፅጌ ኢህአፓ ሲፈራርስ ለስደት ከተዳረጉት መኻከል ነበር። ህወሃት መራሹ ጦር ድል ቀንቶት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር አንዳርጋቸው ፅጌ ከሐገረ እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለመሆን ቻለ።

አንዳርጋቸውን "ተው ወያኔ ከሚመራው መንግስት ጋር አትተባበር" ብለው የመከሩት ነበሩ። እርሱ ግን ምክራቸውን ቸል አለው።

"ወያኔ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከነበረው ዘረኛ አስተሳሰብ ወጥቷል፥ ኢህአድግም ሐገርን ወደተሻለ አቅጣጫ ይመራል" ብሎ ተስፋ አድርጎ እንደነበር በመፅሐፉ አስፍሯል። በግልፅ ቋንቋ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢህአድግን ስልጣን የተቀበለው መለስ ዜናዊን እና ፓርቲውን በማመን ነበር።
('ታሪክ ራሱን ይደግማል' እንደሚባለው ሁሉ ከሰላሳ አመት በፊት አቶ መለስ ዜናዊ እና ፓርቲያቸው ሐገር እንደሚያሻግሩ አምኖ ስልጣን የተረከበው አንዳርጋቸው ፅጌ ከአመታት በኋላ ዶክተር አብይን እና ፓርቲያቸውን ለውጥ እንደሚያመጡ አምኖ ሲደግፋቸው ከርሟል)

በእርግጥ በዘመነ ወያኔ ከነመለስ ዜናዊ ጋር እንዲሰለፍ ያስቻለው እምነት ብቻ አልነበረም። ይልቅ ስሜት ነበር።

አንዳርጋቸው ፅጌ 'ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ' በሚለው መፅሐፉ ቀጣዩን አስፍሯል

"መንግስቱ ሃይለማርያም እና ግብረአበሮቹ ከስልጣን ተወግደው፥ ወንድሞቼንና ጓደኞቼን ካሰቃዩበት፥ የስንቱን ሃገር ወዳድ ደም ካፈሰሱበት ቤተመንግሥት እራሴን ሳገኘው የተሰማኝን የሚያሰክር ስሜት አስታውሳለሁ"

ፅሁፉ በግልፅ እንዲሚናገረው ከምክኒያታዊ ፖለቲካ በተጨማሪ ስሜታዊ ሁኔታ አቋቋሙ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። ለደርግ የነበረው ጥላቻ ወደ ኢህአዴግ ገፍትሮታል።

ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ስልጣን የያዘ ሰሞን እነ አንዳርጋቸው ፅጌ በቀደመው የመንግስቱ መኖሪያ ስብሰባ ተቀምጠው ነበር። መለስ ዜናዊ ነጠላ ጫማ ተጫምቶ የወታደር ኮፊያ በአናቱ አድርጎ እየሳቀ ወደ ተሰብሳቢዎች ተቀላቀለ። "ሰዎች" አለ መለስ ዜናዊ በፈገግታ "የመንጌን ባርኔጣ አግኝቻለሁ" አላቸው ጭንቅላቱ ላይ ወደ ደፋው የወታደር ኮፊያ እያመላከተ።

ሌላኛው ተሰብሳቢ ኮሌኔል ኤፍሬም ነው። በመለስ ዜናዊ የተፈጠረውን የጨዋታ ድባብ ተከትሎ ኮሌኔሉም ማውራት ቀጠለ። "በመንግስቱ ሃይለማርያም አልጋ ላይ ነበር ያደርኩት፥ ለሊቱን አልጋው አቃዠኝ" አላቸው። እነ አንዳርጋቸው በደስታ እንደ ልጅ ይስቃሉ።

እንደ ጉድ ይፈሩ የነበሩ የደርግ ሹማምንት ተወግደው አንዳርጋቸው በቅርብ የሚያውቃቸው ሰዎች ዋና ባለስልጣናት መሆናቸው ሳያንስ ጨዋታቸው ስሜት የተሞላበት ነበር። ተጭሶ ካለቀ የሲጋራ ቁራጭ ትምባሆ እየፈረፈሩ በደብተር ወረቀት በመጠቅለል ያጨሳሉ። ደግሞም በደርግ ባለስልጣናት ላይ ያላግጣሉ።

ለደርጎች ጥላቻ አድሮበት የነበረው አንዳርጋቸው ፅጌ "ይሄን አይቼ ብሞትም አይቆጨኝም ነበር" እስኪል ድረስ በስሜት ተነከረ።

ከአመታት በኋላ ከኢህአዴግ በተፃራሪ የቆመው አንዳርጋቸው ከቀደመው ሹመቱ ጋር በተያያዘ "የወቅቱ ስሜት" የማዘናጋት ድርሻ እነደነበረው አውስቷል።

ማጣቀሻ መፅሐፍ፥ አንዳርጋቸው ፅጌ "ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ"

(ይህን ፅሁፍ ከወራት በፊት ፖስቸው የነበረ ነው

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ብዙ ጊዜ 'ነብያት ነን' ብለው የሚመጡ የሐገራችን ሰዎች ጤንነት የምር ያሳስበኛል። ነገሩን እንደአትራፊ ቢዝነስ ቆጥረው የመጡ ነጋዴዎችን ማለቴ አይደለም። የምር እራሳቸውን እንደነብይ ስለሚቆጥሩቱ ነው የማወራው።

"አምላክ በራዕይ ተገልጦልኝ እንዲህ እና እንዲያ አለኝ" ይላሉ። የሚያወሩትን እንደ ባለአእምሮ ከመዘንን ተራ ነገር ይሆናል፥ አማካይ ንቃት ካለው ሰው ግንዛቤ በታች ነው። ከምንም በላይ 'እናምንበታለን' ከሚሉት ሃይማኖት ዶክትሪን ይላተማሉ።

እኚህ ሰዎች እየዋሹ አይመስለኝም። የምር አንዳች ነገር ተገልጦላቸዋል ብዬ እገምታለሁ። ነገር ግን የተገለጠ ሁሉ አምላክ ነው ማለትም አይደለም።

በአንዳች አይነት የአእምሮ መናጋት ፥ በመንፈስ ቀውስ ፥ የስነልቦና መዘባረቅ ውስጥ የገቡ ይመስለኛል።

እናም የምር 'አምላክ ተገለጠልን' እያሉ የሚዘባርቁ ሰዎች የአእምሮ መታወክ ውስጥ እንደ ገቡ በመጠርጠር ህክምና እንዲያገኙ መተባበር አስፈላጊ ነው። በተለይ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ወደ ሕክምና በመውሰድ ሊረዷቸው ይገባል።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ዛሬ ስለ አሰብ እንነጋገራለንተ

ኢኮኖሚያዊ ፖፑቲካዊ እና ታሪካዊ ጉዳዮችን ለማንሳት ሞክሬያሁ።

ለሌሎች ብታጋሩ እወዳለሁ

https://youtu.be/ZLnk8CIPxlc

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ንዴቴ ሲለቀኝ ይሄን ፖስት አጠፋው ይሆናል

አሁን ወደቤቴ ስጓዝ ሁለት ወጣቶች ገጠሙኝ፥ ሌቦች መሆናቸው ነው።
ቤቴ ለአስፓልት ቅርብ ነው፥ አከባቢዬ የደህንነት ስጋት የለውም። ያለ ምንም ስጋት እያዘገምኩ አንዱ አስቆመኝ። በዚህ መሓል ጓደኛው ደረቴ ላይ አሪፍ ቡጢ አሳረፈ። ተንገዳግጄ ወደቅሁ።

ከጀርባዬ ድንጋይ ነበር፥ እድለኛ ሆኜ ድንጋዩ አላገኘኝም።
መኪና ሲመጣ ሮጡ።

ምንም የከፋ ጉዳት አልደረሰብኝም። ጉልበተኝችን ትግል የምገጥም አይነት ጅ ል አይደለሁም። የያዝኩትን ቢጠይቁኝ ሰጥቻቸው በሰላም ልሄድ የምችል ነኝ።

ወደኋላ ስወድቅ ድንጋዩ ቢያገኘኝ አልተርፍም ነበር። እንደ እድል ሆኖ ተረፍኩ፥ ደግሞ አልተሰረቅኩም።

ድንገት መኪና ሲመጣ ልጆቹ የሸሹ ቢሆንም ነገሩ የምር አበሳጭቶኛል

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

የአነቃቂ ተናጋሪዎች አደንዛዥ ገፅታ

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ከሞተ ሰው ጋር ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎች"

አንዳንድ ነገሮች ለማሰብ እንኳ የሚፈትኑ ቅዠታዊ ቢመስሉም ሰዎች ደፍረው ያደርጉታል።
በሬሳ ፍቅር መለከፍ ፥ ከበድን ጋር መዋሰብ ፥ ከሙት ጋር ፆታዊ ግኑኝነት መከወን ሊሆን የማይችል መስሎ ቢታይም፤ ይሄን ማድረግ የሚያስደስታቸው ፥ ከህያዋን ይልቅ ከሙታን ጋር ወሲብ መፈፀም የሚያረካቸው ሰዎች አሉ። አዎ እንዲህ አይነት ሰዎች አሉ!
በእርግጥ የሰው አእምሮ ነገር ግራ አጋቢ ነው!

ነገርየው ኔክሮፊሊያ የሚል መጠሪያ አለው።
የቃሉ መገኛ ከወደ ግሪክ ነው። ፊሊዮስ የሚለው የግሪክ ቃል መሳብ ወይም ፍቅር የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፥ nekros ማለት ደግሞ ሙት አካል እንደማለት ነው። የሁለቱ ጥምር ቃላት ውጤት የሆነው ኔክሮፊሊያ በሙት አካል መሳብ የሚል ትርጉምን ይሰጣል።
የዚህ ሰላባ የሆኑ ሰዎች ወደ ሙት አካል ይሳባሉ። መሳባቸው ደግሞ ወሲባዊ ፥ ምኞታቸውም ፆታዊ መገናኘት ነው።

ይህ ከበድን ጋር ወሲብ የመፈፀም ዝንባሌ ዘመን አመጣሽ አይደለም። ድሮ ከበዙ መቶ አመታት በፊትም የነበረ ግራ አጋቢ ድርጊት ነው።በግሪክ አፈ ታሪክ፥ በተለያዩ ማህበረሰቦች ጥንታዊ ባህል፥ በግሪኮ-ሮማን ዘመን፥ በመካከለኛው ዘመን እና በዘመናዊው አለም ይህ ዝንባሌ ያላቸው ፥ ከሙታን የሚዋሰቡ ሰዎች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

የዚህ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ፥በተለያየ ወቅት አስከሬኖች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ሲፈፅሙ ተይዘዋል፥ ከሬሳ ጋር ለመዋሰብ ሲሉ መቃብር ጠባቂዎችን ማጥቃታቸው ተሰንዷል። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ከሬሳ ጋር ወሲብ የመፈፀም ፍላጎታቸውን ለማርካት ሲሉ መቃብሮችን ቆፍረው አስከሬን ሬሳ እስከመስረቅ ደርሰዋል።

እጅግ አስደንጋጩ ነገር በዚህ ዝንባሌ የተነሳ የንፁሃን ህይወት መቀጠፉ ነው። ከአስክሬን ጋር መዋሰብ የሚፈልጉና አስክሬን ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች ንፁሃንን በመግደል ከሬሳቸው ጋር ፆታዊ ግኑኝነት እስከመፈፀም ደርሰዋል። በምዕራባዊው አለም በተሰነዱ መረጃዎች መሰረት ፥ ጥቂት የማይባሉ ተጎጂዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ከተደረገ በኋላ የፆታ ግንኙነት ተፈፅሞባቸዋል።

ከህያዋን ይልቅ ከሙታን መዋሳብ ባስ ሲልም በህወት ያሉትን ገድሎ ፆታዊ ግኑኝነት መፈፀም ግራ አጋቢ ድርጊት መሆኑ እሙን ቢሆንም ፥የነገሪየውን ሰበብ በተመለከተ የጠራ ነገር ማስቀመጥ አዳጋች ነው።
ዛሬም ድረስ 'ኒክሮፊሊያ' የተባለው ግራ አጋቢ ችግር መምጫ ሰበቡን በአግባቡ ተረድቻለሁ ያለ የለም። ዛሬም ለምርመራ ክፍት ነው።

ነገሩን እንቋጨው።

ከሞተ አካል ጋር መዋሰብ መፈለግ ያልተመደ ዝንባሌ መሆኑ ግልፅ ነው። እንዲህ ያለ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች በግርድፉ በሶስት መደብ ሊመደቡ ይችላሉ

ሀ፥ እዚህ ምድብ ያሉት ገዳይ ናቸው። ከሞተ አካል ጋር የሚደረግ ወሲብ እርካታ ስለሚሰጣቸው በህይወት ያለ ሰው በመግደል ከሬሳው ጋር ወሲብ ይፈፅማሉ። የግድያቸው ብቸኛ ሰበብ ለወሲብ ዓላማ አስከሬን ማግኘት ነው።

ለ፥ በህይወት ያለ ለመግደል አይደፍሩም። ነገር ግን ከሙታን መዋሰብን ይወዳሉ። የሞተ ሰውን ሲያገኙ ለወሲብ ደስታ ይጠቀሙበታል። ለወሲብ አላማ በእጃቸው ህያዋንን መግደልን ባይደፍሩም አስከሬንን ይዋሰባሉ።

ሐ፥ እኒህ ምናባቸውን ብቻ የሚጠቀሙ ናቸው። በሃሳባቸው ከሬሳ ጋር ይገናኛሉ፥ ሙትን በመወሰብ ምኞት ይቃጠላሉ፥ ከበድን ጋር ፆታዊ ግኑኝነት ስለመፈፀም ደጋግሞ ያስባሉ። ነገር ግን ድርጊታቸውን አካል አያለብሱትም። ከመመኘት በዘለለ በተግባር አያደርጉትም።

(በእርግጥ የሰው አእምር ግራ አጋቢ ነው !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አነቃቂ ንግግር እናደርጋለን ባዮች በዝተዋል። እነዚሁ አነቃቂ ነን ባዮች መንግስታዊ መዋቅርንም ጭምር ተቆጣጥረዋል። የንግግሮቻቸው ማጠንጠኛ የሆነው የስህበት ሕግ ጎጂ መልክን ዛሬ በ #አጀንዳ እንዳስሳለን።

👇

https://youtu.be/AVEXO7R6Blg

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

https://vm.tiktok.com/ZM2tfPQjP/

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ልደቱ አያሌው ወያኔ ነው"
* * *

ልደቱን 'ወያኔ' ማለት የተለመደ ፍረጃ ነው፥ ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑ ሰዎች በህወሓት ተላላኪነት ይፈርጁታል። 'እርሱ ለህወሓት ስስ ልብ አለው' ይላሉ። አንዳንዶች ለዚህ የሚያቀርቡት ሰበብ የሞኝ ይመስላል። 'ዝምባለችሁ አሉባልታችንን እመኑ' ነው ነገረ ስራቸው።

በሐቅ ሚዛን ቆመን ልደቱ ላይ የሚቀርበውን ክስ ብንመዝን ከርሱ ይልቅ ለወያኔ የማቀርቡት ከሳሾቹ ናቸው።

ፖለቲካ የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው። ልደቱ የህወሓትን አስተሳሰብ በሞገተበት ልክ የሞገተ ሌላ ሰው ማግኘት ከባድ ነው።
አስረጅ እንጥቀስ!

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የሰራው ሕገ-መንግስት ከፓርቲው አስተሳሰብ ማሳያዎች መካከል ነው። 'ሕግ የሕግ አውጪው አስተሳሰብ፥ አላማ ፥ ፍላጎት ወዘተ መለኪያ ነው' ቢባል ስህተት አይደለም።
ልደቱ የሕገመንግስቱን ህፀፆች በስፋት አብራቷል፥ ሕገመንግስቱን ተችቷል። "ስጦታ ከእስር ቤት" በሚለው መፅሐፉ አማራጭ ሕገ-መንግሥት ፅፏል።

'ልደቱ የሕወሓት ተላላኪ ነው' ብለው ከሚወነጅሉት መካከል ጥቂት ያልሆኑቱ የሕገመንግስቱ አፍቃሪ ናቸው። 'ሕወሓት አበጀው' የሚሉትን ሕግ እያፈቀሩ 'ሕጉ አይበጅም' ባዩን ተላላኪ ይሉታል።

አንዳንዶች በዘመነ-ኢህአዴግ የተተገበረውን የብሔር ፌደራሊዝም ይወዱታል ፥ ጠበቃም ይቆሙለታል። ልደቱ ግን 'ብሔር መር ፌደራሊዝም አውዳሚ' እንደሆነ ከማመን በዘለለ አማራጭ ሃሳብ ይዞ ቀርቧል። (ጂኦግራፊ ፥ ቋንቋ ፥ ታሪክ ፥ ለአስተዳደር አመቺነት ከግምት የገቡበት ፌደራሊዝም ይተግበር ባይ ነው)
የብሔር ፌደራሊዝም እያፈቀሩ ፥ ይህን የሚቃወመውን ልደቱን 'ወያኔ ነው' ማለት ያስተዛዝባል።

ሕወሓት መሬትና ብሔርን ያጋባች ፓርቲ ናት። ልደቱ ግን በተቃራኒው መሬትን ከብሔር ነጥሎ ይመለከታል። "አዲስ አበባ ወይም ወልቃይት ፥ መተከል አሊያም ወለጋ .... የብሔር ባለቤትነት ሊኖራቸው አይገባም። መሬትም ቢሆን የግለሰቦች የግል ሐብት እንጂ የመንግስት ንብረት አይደለም" ይላል ልደቱ።
ጥቂት የማይባሉ ፖለቲከኞች ፥ መሬትን ከብሔር ይሰፋሉ፣ ደግሞም 'መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችል ንብረት መሆን የለበትም' ይላሉ።
አስገራሚው ነገር መሬትን በተመለከተ ባላቸው አቋም ከሕወሓት ጋር ተስማምተው ሲያበቁ ፥ ይህን የሚቃወመውን ልደቱን ግን 'በሕወሓትነት' ይፈርጁታል።

ልደቱ ፥ የፖለቲካ አስተሳሰቡ ግልፅ ነው። እሱ የሊብራል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ አራማጅ ነው። በምንም ሰበብ ከግራ ፖለቲካ ጎራ ከሆነው ሕወሓት ጋር አንድ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን ልክ እንደ ህወሃት የግራ ፖለቲካ ካምፕ የሆኑ ሰዎች የሊብራሊዝም አቀንቃኙን 'ወያኔ' ይሉታል።

ልደቱ የካፒታሊዝም ደጋፊ ነው። "ገበያው ነፃ ይሁን" ይላል። በሕወሓት ወገን ደግሞ ገበያው ላይ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ይበረታታል።
ኢኮኖሚን በተመለከተ ከህወሓት ጋር አንድ አይነት ምልከታ ያላቸው ልደቱን 'ወያኔ' ሲሉት እናያለን።

ልደቱ በታሪክ አረዳድም ቢሆን ከሕወሓት ይለያል። ልደቱን በሕወሓትነት ከሚፈርጁት መካከል ጥቂት ያልሆኑት የህወሓትን የታሪክ መረዳት ይጋራሉ።

አንድ ሰው የህወሓትን የፖለቲካ አስተሳሰብ ማመን መብቱ ነው፤ አይከለከልም። ነገር ግን ልደቱን በሕወሓትነት ከሚከሱት መካከል ብዙዎች በአስተሳሰባቸው ለህወሓት የቀረቡ ሆነው ሳለ ፥በእውቀት እና በምክንያት የህወሓትን አስተሳሰብ የሞገተውን ሰው 'የወያኔ ተላላኪ' ይሉታል።

ይህ ለትዝብት ይደርጋል።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሻሸመኔ ተትልቁ መስጂድ ሳምንታዊ ውይይት ይደረግ ነበር። በየሳምንቱ ከBicola Nas ጋር በመገኘት በርዕሰ ጉዳዮች የራሴን ሃሳብ አካፍላለሁ።
በውይይቶቹ በተገኘሁባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ አንድ ነገር እጠነቀቃለሁ፥ የእምነቱን እሴት ላለመጣስ። ይሄ ቀላሉ ሃላፊት ነው።

የኦርቶዶክስ ተቋማትን በጎበኘሁባቸው አጋጣሚዎች እሴት ላለመጣስ እጠነቀቃለሁ። ጫማ በሚወለቅ ቦታ አወልቃለሁ፥ ከማይመለከተኝ ስፍራ ገለል እላለሁ። ይሄ ቀላል ሃላፊነት ነው።

በ Mish'A-el ጋባዥነት የይህዋ አምላክ ምስክሮችን አመታዊ ስብሰባዎች በተካፈልኩባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ እሴቶቻቸውን ላለመጣስ እሞክራለሁ፥ ይህ ቀላል ሃላፊነት ነው።

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ እንደ አንዳች ገድል የሚነገሩ አይደለ። አንድና አንድ ሁለት ነው የማለት ያህል ተራ እውቀት ናቸው። አሳፋሪው ነገር ፥ ይሄን የማያውቁ መደዴ ሰዎች ብዙ ናቸው።

የሌላን እሴት ማክበር የስነምግባር ሀሁ ነው። የሌላውን ክብር በመዳፈር የሚሰበክ ሃይማኖት የለም። ኦርቶዶክስን በማስቆጣት ኢየሱስን ማክበር አይቻልም።

ግለሰብን ትሁት ያላደረገ እምነት የውሸት ነው። ሌላውን ለማስቆጣት ሰበብ የሚሆን ሃይማኖታዊ መረዳት ከንቱ ነው።

ልጆች ሳለን ፥ በቃለህይወት ቤተክርስቲያን ስንማር ቸርቻችን ላይ ድንጋይ የሚወረውሩ ስዶች ነበሩ። አድጌ ስለ ነርሱ ሳስብ ሃፍረት ይሰማኛል። "እንዴት ያሉ ጋጠወጦች ነበሩ?" እላለሁ።

ዛሬም ነገሩ ተመሳሳይ ነው።

ህፃን ያይደለች ሴት ፥ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅጥር በመገኘት አማኙን የሚያስቆጣ ድርጊት ስታደርግ ስመለከት "ጤና አላት ይሆን?" እላለሁ።

የሌላውን እሴት ማክበር ኳንተም ፊዝክስ አይደለም። ይሄን ማድረግ የማይችል ሰው ያሳፍራል።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ክቡርነትዎ፥ አንድ ሲደመር አንድ ሦስት ነው ማለትዎ ስህተት ስለሆነ ቢያርሙት ሸጋ ነው"

"አንዳንዶች መተቸት ይወዳሉ፥ ነገር ግን ውሾች ቢጮሁም ግመሎች ይቀጥላሉ"

"ክብርነትዎ ፀሐይ በምዕራብ ትወጣለች ማለትዎ ስህተት ስለሆነ ይታረም"

"አንዳንድ ሰዎች መተቸት ይወዳሉ፥ ነገር ግን ውሾች ቢጮሁም ግመሎች ይቀጥላሉ"

"ክቡርነትዎ ስንዴ ዘርተን ጤፍ እናጭዳለን ማለትዎ ስህተት ነው ይታረም"

"አንዳንዶች መተቸት ይወዳሉ፥ ነገር ግን ውሾች ቢጮሁም ግመሎች ይቀጥላሉ"

"ክቡርነትዎ ደሃን በማሳደድ ድህነት የሚጠፋ አይደለም"

"አንዳንዶች መተቸት ይወዳሉ፥ ነገር ግን ውሾች ቢጮሁም ግመሎች ይቀጥላሉ"

"ክቡርነትዎ ሁሉንም ነገር መተቸት መውደድ አያስመስሉት ፥ የውሻና ግመልን ተረት አለቦታ መተረት ስህተት ስለሆነ ይታረሙ"

"አንዳንዶች መተች ይወዳሉ፥ ነገር ግን ውሾች ቢጮሁም ግመሎች ይቀጥላሉ"

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

የአእምሮ ህክምና ለፖለቲከኞች
* * *

ትላንት ኢያስፕድ ተስፋዬ እና ሞገስ ዘውዱ ያደረጉትን ውይይት ስመለከት አንዲት ሃሳብ ቀልቤን ሳበች። እያስፕድ "የአእምሮ ህመም መድሃኒት የሚወስዱ ፖለቲከኞች አውቃለሁ" አለ። ይህች ነጥብ ቀልቤን ወስደዋለች።

ነገረ ስራቸው የወፈፌ የሆኑ ሰዎች ፖለቲካውን ሲዘውሩት መመለከቱ ተለምዷል ፥ ከፖለቲካው ሰፈር ዋና ሰዎች መካከል ጥቂት የማይባሉቱ የአእምሯቸው ጤንነት አጠያያቂ ነው። ከተናጋ አእምሮ ጤነኛ ሃሳብ መጠበቅ ጥቁር ወተትን የመመኘት ያህል ነው። ፖለቲከኞች መንፈሳቸው የታወከ፥ አእምሯቸው የታመመ ፥ ስነልቦናቸው የተናጋ በሆኑ ቁጥር ጣጣው ለህዝብ ይተርፋል።

ከጥንት ጀምሮ የሐገራችን ፖለቲካ መጠላለፍ የሞላበት ነው። ብዙ ሴራ እና የከፋ መጎዳዳት የፖለቲካችን ዋነኛ መልክ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ውስጥ 27 በመቶ የሚያህለው ዜጋ ለአእምሮ ጤና ችግር የተጋለጠ እንደሆነ ይነገራል። ቁጥሩ አወዛጋቢ ቢሆንም በኛ ሐገር ለአዕምሮ ጤና መናጋት አጋላጭ የሆኑ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ከግምት ስናስገባ፥ የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለአእምሮ ጤና ቀውስ የተጋለጡ መሆናቸውን መጠርጠር እንችላለን።

በርካታ ዜጎች የአእምሮ ጤና እክል ተጋላጭ መሆናቸውን ካመንን በኋላ ከነርሱ መካከል ፖለቲከኞች እንደሚኖሩበት ብንገምት ስህተት አንሆንም።

ፖለቲካችን ሞት አምራች ነው!

በልጅ እያሱና በተፈሪ መኮንን መካከል የነበረው ሽኩቻ የሰገሌን ጦርነት አስከትሏል። መንግስቱ ነዋይና ገርማሜ ነዋይ የሃይለስላሴን መንግስት ለመለወጥ ያደረጉት ሙከራ ታላላቆችን ቀጥፏል። ደርግ ወደ ስልጣን ኮርቻ ሲወጣ ወደሞት የተነዱ ነበሩ። መኢሶን ፥ ኢህአፓ እና ደርግ መጠላለፋቸው ለትውልድ ተርፏል። ቀይ ሽብር አንድ ትውልድ በልቷል። ጓድ መንግስቱን ከመንበር ለማውረድ በ1981 በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት የተነሳ ታላላቅ የጦር መሪዎች ላይመለሱ አንቀላፍተዋል። ህወሃት 17 አመት በፈጀ የትጥቅ ትግል ወደ ስልጣን ስትመጣ ብዙ ዋጋ ተከፍሏል። በምርጫ 97 ለውጥን የጠበቁ የጥይት ሲሳይ ሆነዋል። ኢህአዴግን ለመለወጥ በተደረገ አመፅ የሞቱ ጥቂት አይደሉም። ፖለቲካችን ዛሬም ሞትን ያመርታል!

የሰቆቃ ታሪክ ሲደጋገም ለአእምሮ መታወክ ይዳርጋል።

እንደህዝብ ሰቆቃ በተደጋጋሚ ጎብኝቶናል። ጦርነት እና ረሃብ ብዙ ነገሮችን አናግቶብናል።
መጠላለፍ የማይለየው ፖለቲካም የቀውስ ምክኒያት ነው። በተወሳሰበ ሴራ ያለፉ ፖለቲከኞች ስነልቦናዊ ሁኔታቸው እንዴት ባለ መንገድ ሊታወክ እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ ነው።

አግባብነት የጎደለው ተጠራጣሪነት እና በመጠራጠር የተነሳ ሌሎችን ለማጥቃት መፈለግ ፥ ራስን ዝቅ አድርጎ ማሰብ ወይም ያለ አግባብ ራስን ከፍ ማድረግ ፥ ግጭትን አብዝቶ መውደድ ፥ ካጋኙት ሁሉ መላተም፥ ተቃራኒዎችን በጠላትነት መፈረጅ.. ወዘተ ስነልቦናዊ ጤና የማጣት ምልክት ነው።

ምን እያወራሁ ነው?

የእኛ ሐገር ፖለቲካ የፖለቲከኞችን ስብእና የመስለብ፥ ለአእምሮ እና ስነልቦናዊ ቀውስ የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው።

ከ 360 በላይ የአእምሮ ጤና እክል አይነቶች እንዳሉና የአእምሮ ጤና ችግርን በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ መሆኑን ከግምት ማስገባትም አግባብ ይኖረዋል።
ደግሞም ለአእምሮ ጤና ችግር የተጋለጡ ፖለቲከኞች ሲኖሩ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ አይከብድም።

ምን በጀን?

በረጅም ጊዜ እቅድ የአእምሮ ጤና ጉዳይ ለፖለቲካ ተሳትፎ አንድ መመዘኛ የሚሆንበት እቅድ ቢነደፍስ? ይህ እንደ ቅንጦት ይታሰብ ይሆን?


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

'አማራ በትግራዩ ጦርነት'
* * *

በቁጥር ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትግራዩ ጦርነት ዋና አክተሮች የአማራ ኤሊት ይመስላቸዋል፥ ወይንም አስመስለው ያቀርባሉ።
የትግራዩ ጦርነት ተዋናዮችን ማንነት በብሔር መመደብ ፥ በነገድ ኮታ መስጠቱ አስፈላጊ ባይሆንም አማራን ለሚወቅሱቱ አግባባዊ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።

ከልደቱ አያሌው እስከ ኢንጂነር ይልቃል ፥ ከቴዎድሮስ አስፋ ወሰን እስከ ያየሰው ሽመልስ ጦርነቱን ተቃውመዋል፤ የኤርትራን ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል፣ ለህዝቡ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። እውነት ለመናገር የትግራዩን ጦርነት ያወገዙ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ብዙ ነው። ምናልባት ከጦርነቱ አውጋዦች መሓከል ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው።
ይሄን እውነት ቸል ብሎ አማራን መኮነን ጥፋት ነው።

ምናልባት 'ብዙ አማራዎች ጦርነቱን ደግፈዋል' የሚል ክርክር ይመጣ ይሆናል፤ ይህ ከፊል እውነት ነው። ጦርነቱን የደገፉት ከአማራ የተወለዱት ብቻ አይደሉም። ከሁሉም ብሔር የተውጣጡ ሰዎች ለጦርነቱ ድጋፍ ሰጥተዋል፥ ዘመቻውን መርተዋል። ጦርነቱ ላይ በፕሮፖጋንዳ ፥ በፖለቲካ አመራር ፥ በጦር ተሳትፎ የነበራቸውን የሌላውን ብሔር ተወላጆች በብዛት መቁጠር ይቻላል።

አለማዬ ፥ ጦርነቱን በብሔር ኮታ መከፋፈል አይደለም። ነገር ግን አግባብነት በጎደለው እና ከአውድ በወጣ መንገድ አማራን መውቀስ ህዝብን ለጥቃት የሚያመቻች በትር ማቀበል እንዳይሆን ማሰብ ያስፈልጋል !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

አንዳርጋቸው ፅጌ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ "ኢሳያስን እና ዶክተር አብይን ያገናኘሁት ብቸኛው ሰው ነኝ" ብሏል።
እንግዲህ አንዳርጋቸው እንደተናገረው ከሆነ ሻቢያ እና ብልፅግና መካከል ድልድይ በመፍጠሩ የተሳተፈ ሌላ አካል የለም። ዋነኛው እና ብቸኛው ሰው አንዳርጋቸው ነው።

ኢሳያስ አፈወርቂ እጁን ወደ ኢትዮጵያ ከሰደደ በኋላ ብዙ ጥፋት ሰርቷል። ያ ጥፋት እንዲሰራ መንገድ የጠረገው ሰው ቀጥሎ ምን ይፈጥር ይሆን?

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"እብድ ነኝ" ፥ የአንዳርጋቸው ፅጌ ድራማ
* * *

በዘመነ ደርግ መሰረተ ትምህርትን እንዲያስተምሩ ከተመረጡ ወጣቶች መካከል አንዱ አንዳርጋቸው ፅጌ ነበር። አንዳርጋቸው ለሰፊው ህዝብ መሰረተ ትምህርት እንዲያስተምር ቢመደብም ደስታ አጣ፥ ከዘመቻው ለማምለጥ ወጠነ።

በወቅቱ ወጣት የነበረው አንዳርጋቸው ያኔ የኢህአፓ አባል ብቻ ሳይሆን ዋና አመራሮችን ከቦታ ቦታ የሚውስድ ሹፌራቸው ጭምር ነበር። እናም 'ከዘመቻው አምልጬ የኢህአፓን ስራ ልከውን' ብሎ ወጠነ፥ ውጥኑም እንዲሰምር ድራማን ፈጠረ።

ከእለታት በአንዱ እንዲህ ሆነ። ለሊት ነው፥ አብዛኛው ሰው እንቅልፍ ላይ ሳለ ያልተኙቱ ተተራመሱ። በኡኡታ እንቅልፍ ላይ ያሉትን አነቁ፥ ጠባቂዎች ተጣድፈው ወደ ስፍራው ደረሱ።

የመተራመሱ ሰበብ አንዳርጋቸው ነበር። ጨርቅ ቀዶ ራሱን ሰቆሎ ሊገድል ሲል ደረሱበትና አተረፉት። ግራ መጋባትና ውክቢያ በቤቱ ተፈጠረ።
'ምን ነክቶት ሊሞት አሰበ' ተብሎ ሲጠየቅ ከወዳጆቹ "አልፎ አልፎ የሚነሳ የአእምሮ ህመም አለበት፥ ይህን ያደረገው እብደቱ ተቀስቅሶ ነው" የሚል መልስ ተሰጠ።
የነገሩን ልክነት ለማጥራት ወደ ምርመራ ክፍል ተወሰደ። በምርመራ ቦታ አንዳርጋቸው ግድግዳው ላይ እያፈጠጠ መዛበረቅ ጀመረ። ለሚቀርብለት ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ ሁሉ አራምባና ቆቦ ሆነ። ይሄኔ መርማሪዎች 'ይህ ወጣት የአእምሮ መታወክ አለበት' ብለው ደመደሙ። አብሯቸው ቢቆይ ድንገት ህይወቱን በገዛ እጁ ሊያጠፋ እንደሚችል ጠረጠሩ። ስለዚህ ያላቸው አማራጭ እሱን ማሰናበት ሆነ።

አንዳርጋቸው ፅጌ ያኔ እንደ እብድ ሆኖ የታየው ድራማ ሲሰራ ነበር። ከዛ የማምለጫ እቅድ ማዘጋጀት ሲጀምር አልፎ አልፎ የሚነሳ 'የአእምሮ መታወክ' እንዳለበት ውስጥ ውስጡን አስወራ። ቀጥሎ ገመድ ይዞ ራሱን ሊገድል እንዳሰበ አስመስሎ ተወነ። ይሃኔ እብደቱን ያመኑቱ በድንጋጤ በገጠር ያለውን ዘመቻ አቋርጥ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ወሰኑ።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ጀዋር መሐመድ "የመደመርን ኳልኩሌተር ሰርቼዋለሁ" ብሎ በተናገረ ማግስት ደማሪው አብይ ጀርባ ሰጠው፥ ሳይቆይ ጀዋር ወደ ዘብጢያ ወረደ።
አሁን ጀዋር 'ኳልኬተሩን ሰራሁት' ብሎ በኩራት እንዳልተናገረ ከሚዳያ ገሸሽ ብሎ ዝምታን መርጧል።

አንዳርጋቸው ፅጌ ''የለውጡን ሮድማፕ ሰርቼዋለሁ'' ብሎ በአደባባይ መናገሩ ተረስቶ ከለውጡ መሪ ተኳርፏል። የለውጥ ሮድ ማፕ አዘጋጅቻለሁ ባዩ አንዳርጋቸው ዛሬ ከለውጡ ተጣልቶ ሐገር ጥሎ መኮብለሉ ተሰምቷል።

ለማ መገርሳ "እኔን እና አብይ ከሞት በቀር የሚለየን የለም" ብሎ የነበረ ቢሆንም ሞት ከመምጣቱ በፊት ተለያይተዋል።

ገዱ አንዳርጋቸው ካወዳደሰው ለውጥ ሰፈር ተገፍትሮ ጥግ ይዟል።

የለውጡ 'ዋና ሰዎች' መስለው ይታዩ የነበሩቱ አንድ በአንድ በመንገድ ተንጠባጥበዋል።

ቀጥሎስ ?

ጊዜ ጌታ !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሁሉም አከባቢ የፀጥታ ስጋት አለ። የደህንነት ስጋቱን የሚያባብሰው ደግሞ የመንግስት የፀጥታ መዋቅር ነው።

በየአከባቢው አንዳች መኣት የተፈጠረ ይመስል የስጋትን ድባብ ይፈጥራሉ፥ ትራንስፖርት ያግዳሉ፥ መንገደኞችን በሚያውክ መንገድ ይፈትሻሉ፥ እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ ይጥላሉ፥ ወዘተ።

ሽብር ስነ ልቦናዊ ነው።

ዮቫል ሃራሬ 'አሸባሪዎች ዋነኛ አላማቸው ፍርሃትን መፍጠር ነው፥ በእውነተኛው አለም የሌላቸውን ግዝፈት በሰዎች ምናብ ከፈጠሩ በኋላ በሰዎች ላይ በሚሰፍር ስጋት ተመርኩዞ መንግስትን ጫና ውስጥ ይከታሉ' ይላል።

ከሃራሬ የተሻለ ምሳሌ እንዋስ፥

አንድ ዝንብ ግዙፍ መኖሪያን ማወክ አይችልም። ነገር ግን ያ ዝንብ የበሬ ጆሮ ላይ ቢገባ በሬው ተደናብሮ ሙሉ ቤቱን ያውካል። አሸባሪዎችም በዚህ መንገድ የመንግስትን መዋቅር ተጠቅመው ስጋትን ይፈጥራሉ፥ ግዙፍ ጭራቅ መስለው ይታያሉ።

በየአከባቢው ድንገት አስጨናቂ ጥበቃ መፍጠር አንዳች ስጋት እንዳለ በዘወርዋራ መናገር ነው። እግዶችን ማብዛት 'አደጋ ጣይ በዙሪያችሁ አለ' የሚል መልእክት ማስተላለፍ ነው።

የፀጥታ መዋቅር ሰዎች ከፍተኛ መተራመስ ሲፈጥሩ፥ ዜጎችን ሲያዋክቡ ወዘተ ለሌሎች ፕሮፖጋንዳ እየሰሩ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል።

መንግስት የዜጎችን ፀጥታ መጠበቅ ግዴታው ቢሆንም በዚህ ነገር ደጋግሞ ነጥብ ጥሏል። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዴ አላስፈላጊ መተራመስ በመፍጠር ዜጎች ደህንነት እንዳይሰማቸው ያደርጋል።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

https://vm.tiktok.com/ZM2vowh5Y/

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ከታሪኩ የማይማር ስህተቱን እንደ እንስሳ ሲደጋግም ይኖራል"

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ከሞተ ሰው ጋር ወሲብ የሚፈፅሙ ሰዎች"

አንዳንድ ነገሮች ለማሰብ እንኳ የሚፈትኑ ቅዠታዊ ቢመስሉም ሰዎች ደፍረው ያደርጉታል።
በሬሳ ፍቅር መለከፍ ፥ ከበድን ጋር መዋሰብ ፥ ከሙት ጋር ፆታዊ ግኑኝነት መከወን ሊሆን የማይችል መስሎ ቢታይም፤ ይሄን ማድረግ የሚያስደስታቸው ፥ ከህያዋን ይልቅ ከሙታን ጋር ወሲብ መፈፀም የሚያረካቸው ሰዎች አሉ። አዎ እንዲህ አይነት ሰዎች አሉ!
በእርግጥ የሰው አእምሮ ነገር ግራ አጋቢ ነው!

ነገርየው ኔክሮፊሊያ የሚል መጠሪያ አለው።
የቃሉ መገኛ ከወደ ግሪክ ነው። ፊሊዮስ የሚለው የግሪክ ቃል መሳብ ወይም ፍቅር የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፥ nekros ማለት ደግሞ ሙት አካል እንደማለት ነው። የሁለቱ ጥምር ቃላት ውጤት የሆነው ኔክሮፊሊያ በሙት አካል መሳብ የሚል ትርጉምን ይሰጣል።
የዚህ ሰላባ የሆኑ ሰዎች ወደ ሙት አካል ይሳባሉ። መሳባቸው ደግሞ ወሲባዊ ፥ ምኞታቸውም ፆታዊ መገናኘት ነው።

ይህ ከበድን ጋር ወሲብ የመፈፀም ዝንባሌ ዘመን አመጣሽ አይደለም። ድሮ ከበዙ መቶ አመታት በፊትም የነበረ ግራ አጋቢ ድርጊት ነው።በግሪክ አፈ ታሪክ፥ በተለያዩ ማህበረሰቦች ጥንታዊ ባህል፥ በግሪኮ-ሮማን ዘመን፥ በመካከለኛው ዘመን እና በዘመናዊው አለም ይህ ዝንባሌ ያላቸው ፥ ከሙታን የሚዋሰቡ ሰዎች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

የዚህ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ፥በተለያየ ወቅት አስከሬኖች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ሲፈፅሙ ተይዘዋል፥ ከሬሳ ጋር ለመዋሰብ ሲሉ መቃብር ጠባቂዎችን ማጥቃታቸው ተሰንዷል። ጥቂት የማይባሉት ደግሞ ከሬሳ ጋር ወሲብ የመፈፀም ፍላጎታቸውን ለማርካት ሲሉ መቃብሮችን ቆፍረው አስከሬን ሬሳ እስከመስረቅ ደርሰዋል።

እጅግ አስደንጋጩ ነገር በዚህ ዝንባሌ የተነሳ የንፁሃን ህይወት መቀጠፉ ነው። ከአስክሬን ጋር መዋሰብ የሚፈልጉና አስክሬን ማግኘት ያልቻሉ ሰዎች ንፁሃንን በመግደል ከሬሳቸው ጋር ፆታዊ ግኑኝነት እስከመፈፀም ደርሰዋል። በምዕራባዊው አለም በተሰነዱ መረጃዎች መሰረት ፥ ጥቂት የማይባሉ ተጎጂዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ከተደረገ በኋላ የፆታ ግንኙነት ተፈፅሞባቸዋል።

ከህያዋን ይልቅ ከሙታን መዋሳብ ባስ ሲልም በህወት ያሉትን ገድሎ ፆታዊ ግኑኝነት መፈፀም ግራ አጋቢ ድርጊት መሆኑ እሙን ቢሆንም ፥የነገሪየውን ሰበብ በተመለከተ የጠራ ነገር ማስቀመጥ አዳጋች ነው።
ዛሬም ድረስ 'ኒክሮፊሊያ' የተባለው ግራ አጋቢ ችግር መምጫ ሰበቡን በአግባቡ ተረድቻለሁ ያለ የለም። ዛሬም ለምርመራ ክፍት ነው።

ነገሩን እንቋጨው።

ከሞተ አካል ጋር መዋሰብ መፈለግ ያልተመደ ዝንባሌ መሆኑ ግልፅ ነው። እንዲህ ያለ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች በግርድፉ በሶስት መደብ ሊመደቡ ይችላሉ

ሀ፥ እዚህ ምድብ ያሉት ገዳይ ናቸው። ከሞተ አካል ጋር የሚደረግ ወሲብ እርካታ ስለሚሰጣቸው በህይወት ያለ ሰው በመግደል ከሬሳው ጋር ወሲብ ይፈፅማሉ። የግድያቸው ብቸኛ ሰበብ ለወሲብ ዓላማ አስከሬን ማግኘት ነው።

ለ፥ በህይወት ያለ ለመግደል አይደፍሩም። ነገር ግን ከሙታን መዋሰብን ይወዳሉ። የሞተ ሰውን ሲያገኙ ለወሲብ ደስታ ይጠቀሙበታል። ለወሲብ አላማ በእጃቸው ህያዋንን መግደልን ባይደፍሩም አስከሬንን ይዋሰባሉ።

ሐ፥ እኒህ ምናባቸውን ብቻ የሚጠቀሙ ናቸው። በሃሳባቸው ከሬሳ ጋር ይገናኛሉ፥ ሙትን በመወሰብ ምኞት ይቃጠላሉ፥ ከበድን ጋር ፆታዊ ግኑኝነት ስለመፈፀም ደጋግሞ ያስባሉ። ነገር ግን ድርጊታቸውን አካል አያለብሱትም። ከመመኘት በዘለለ በተግባር አያደርጉትም።

(በእርግጥ የሰው አእምር ግራ አጋቢ ነው !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

የአማራ ነገር

በምርጫ 97 ወቅት አራት ፓርቲዎች ኢህአድግን ለመጣል ግንበር ፈጠሩ። 'ቅንጅት ነን' ብለው ራሳቸውን ለህዝብ አስተዋወቁ።
በሐገራችን ፖለቲካ ጉልህ አሻራ ያኖረው ቅንጅት የምስረታ ሰሞን መስራቾቹ በአማራ ጉዳይ ተከራክረዋል።
"ቅንጅቱን ማን ይምራው?" የሚለው ጥያቄ ለቅንጅት ሰዎች ትልቅ ራስ ምታት ነበር። እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆነ ሰው 'መሪ መሆን የለበትም' የሚል ጠንካራ ክርክር ነበር።

ኋላ ላይ ኢንጅነር ሃይሉ ሻውል አመራር መሆናቸው የነገሩን ጭብጥ አይለውጠውም። መሪ ከመሾማቸው በፊት 'ከአማራ ብሔር የተወለደ ፓርቲያችንን እንዲመራ ባንመርጥ ይሻላል' ብለው ተሟግተዋል። የዚህ ሰበባቸው አማራን ጠልተው ሳይሆን የፖለቲካውን ማህበረሰብ ፈርተው ነው። አማራ መሪ ከተደረገ 'አሃዳዊ ፥ የብሔሮች ጠላት፥ ትምክህተኛ' ወዘተ የሚል ዘመቻ ተከፍቶ በተለያዩ ብሔሮች ዘንድ እንጠላለን የሚል ፍርሃት ነበረባቸው።

(ይኸን አሳዛኝ እውነት ልደቱ አያሌው 'የአረም እርሻ' በሚለው መፅሐፉ፥ ብርሓኑ ነጋ 'የነፃነት ጎህ ሲቀድ' በሚለው መፅሐፉ አስፍረውታል)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የቆመበት መሰረት ያስደነግጣል። ስለ ብዝሃነት ተደጋግሞ ይነገራል። ነገር ግን የህብረብሔራዊነት ማሳያ አማራን ማግለል፥ የፌደራሊስትነት ምልክት አማራን መግፋት፥ የዴሞክራሲና እኩልነት ማረጋገጫው የአሃዳዊነት ተረክ ሆኗል። ምንም አይነት የፖለቲካ አቋም ያለው አማራ ፖለቲከኛ ከፍ ባለ ጥርጣሬ ይታያል። ፌደራሊስት ቢሆን እንኳ በአሃዳዊነት እና ጨፍላቂነት ይፈረጃል።

ዘውግ ዘለል እና አንድነት ተኮር ፖለቲካ ማራመድ የአማራ አጀንዳ እንደማስፈፀም ይቆጠራል። በተለይ ዘውግ ዘለል ፖለቲካ አራማጁ አማራ ከሆነ በጭምብላምነት ይፈረጃል።

ተቋማትን ለአማራ እንዳይመቹ ማድረግ አግባብ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው።

1993 ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን እንዲመሩ እጩ ከቀረቡ ሰዎች መካከል ከአማራ ብሔር የተወለዱት ስማቸው እንዲሰረዝ መደረጉን ብርሃኑ ደቦጭ 'የድንቁ*ርና ጌቶች' በሚለው መፅሐፉ አስፍሯል። ለዚህ ሰበቡ "አማራ እስከዛሬ መርቷል፥ ይበቃዋል" የሚል ነው።

መሪነት መስፈርቱ ብቃት ሲሆን አግባብነት አለው። ነገር ግን አጥንት ቆጥሮ ከመንበር ማግለል አስደንጋጭ ህመም ነው።

አማራን ከፖለቲካ መንበር መገፍተርን እንደ አግባብ የሚቆጥሩ ጥቂት አይደሉም። ለዚህ የሚያቀርቡት ምክኒያት "አማራ ድሮ ስልጣን ነበረው" የሚል ግራ የሆነ ሰበብ ነው።

አማራ እንዲገፋ የሚያደርጉ አሳተዛዛቢ ትርክቶች ሚዲያውን ተቆጣጥረዋል፥ ዝነኛ ሰዎች ጭምር በአማራ ላይ መሳለቅ ፌደራሊዝም ይመስላቸዋል፥ ስለ አማራ መገፋት መናገር ጭምብላምነት የሚመስላቸው እልፍ ናቸው።

በዚህ ሁሉ መሓል ንፁሃን ወደ ሞት ይነዳሉ።

(በእውነት አማራ ያሳዝናል!


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"የመድመቅ ሕግ"

መጉላትን ስትፈልግ፥
ሕዝብ መድመቅ ሲሻ ፥መደብዘዝን ምረጥ
ሁሉም ላውራ ካለ ፥ሳትታክት አድምጥ
ሐገር መንጋ ሲሆን ፥በድፍረት ተነጠል
'ከፍ ልበል' የሚል ፥
ያለልክ ሲበዛ ፥ ግድ የለም ዝቅ በል፤

ሁል ጊዜም አስተውል

አእላፋ ሲራኮቱ ፥ ገሸሽ ማለት ልመድ
በራስህ ጎደና ፥ ብቻህን ተራመድ

ግፊያ የሌለበት፥
የእምነትህ መንገድ ፥ ላንተ ይበቃሃል
ደግሞ ሰው ጎርፍ ነው፥
ፈለግህን ስትይዝ ፥ 'ልከተል' ይልሃል!

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ከመጥፎ ዜና እንጀምር ፥ አሁን ገበያው ላይ ካሉ ስራዎች መካከል ጥቀት የማይባሉት በአጭር ጊዜ ከገበያ ይወገዳሉ። ዛሬ የሚፈለጉ የሚመስሉ ሞያዎች ነገ የማይፈለጉ ይሆናሉ፥ ባለሞያዎችም ይገፈተራሉ።

የቀደመውን መጥፎ ዜና የሚያካክስ ጥሩ ዜና አለ፥ ዛሬ ገበያ ላይ የሌሉ የስራ መስኮች ነገ ወደ ገበያ ይመጣሉ። አዳዲስ የስራ በሮች በስፋት ይከፈታሉ።

ትላንት 'ሹፍርና' የሚባል ሞያ ገበያው ላይ አለነበረም። የመኪና መፈጠር ለሹፌሮች አዲስ የስራ በርን ከፈላቸው። ነገ ሹፍርና ከገበያው ሊወገድ ይችላል። ቴክኖልጂ ሾፌሮችን ይተካል።

አለም የምትለዋወጥበት ፍጥነት አስገራሚ ነው። ልጆች ሳለን ኢንጂነሮች በቀላሉ ስራ ያገኙ ነበር። ምህንድስና ገናና ስም ነበረው። ወደ ወጣትነት ስንሸጋር ግን ነገሩ ተገልብጦ ጠበቀን። ኢንጂነሪንግ የተማሩ እኮዮቻችን ስራ አልባ ሆነው ተገኙ፥ ሞያውም ማሽሟጠጫ ሆነ።
እዚህጋ የትምህርት ስርኣቱን ብልሽት መውቀስ አግባብ ነው። ደግሞም ትላንት ይፈለግ የነበረው ዛሬ ሳይፈለግ መቅረቱ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ሊሆን ይገባል።

በአያቶቻችን ዘመን ለውጥ አዝጋሚ ነበር። ዛሬ ግን በአይን ቅፅበት እድሜ ነገሮች ይፈራረቃሉ።

ከሁለት መቶ አመት በፊት የነበረ ወታደር ለአመታት የጦር ስርኣትን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ትግበራ ቢገባ ተግዳሮት አይገጥመውም። የተማረውን አካል ለማልበስ እድል አለው። አያቶቻችኝ ከቀደምቶቻቸው የተማሩትን ግብርና ደግመው መተግበር ይችላሉ።
ከ500 አመት በፊት በኖሩ ሰዎች መካከል እና ከነሱ መቶ አመት በኋላ በመጡ ሰዎች መካከል የሰፋ ልዩነት የለም።

ድሮ ፥ አንድ ሰው የተማረውን ሊተገብር እድል አለው። ግብርና አሊያም የጦር ስርኣት ግንባታ ወይም ሌላ ሞያ የተማረ ሰው ያንኑ ይተገብረዋል።

ዛሬ ነገር ተለውጧል። አንድን ጉዳይ ተምረን ሳንጨርስ ጉዳዩ ያረጃል። ከአምስት አመት በፊት የነበረ ቴክኖሎጂ ዛሬ አሮጌ ይሆናል።
በወጣትነት የተከማቸን እውቀት እስከ ጉልምስና እየመነዘሩ መኖር አይቻልም። በየለቱ አዳዲስ ነገር ይፈጠራል። የትላንቱ እውቀት ዛሬ በሌላ ይተካል። የቀደመው በአግባቡ አገልግሎት ሳይሰጥ አርጅቶ በሌላ ይለወጣል።

በቀደመው ዘመን አንድን ነገር በአግባቡ ተምሮ ማገባደድ ጥሩ ነበር። ዛሬ ግን አንድ ጊዜ መማር አይበቃም። በየለቱ እንዳዲስ የማይማር ራሱን አፍርሶ የማይሰራ ዘመኑን አይዋጅም።

ፈጣን በሆነው የእውቀት እና የመረጃ ማዕበል በፍጥነት መማር ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል። የያዙትን እየለቀቁ ሌላ መጨበጥም የዚህ ዘመን መልክ ነው።

ቴክኖሎጂ ገበያው ላይ ያሉ የስራ መስኮችን ከገበያው እየገፈረ ነው። በዚህ የተየሳ ስራ አጥነት ይፈጠራል። ይህ ግን የሳንቲሙ አንድ ገፅ ነው። የሳንቲሙ ሌላው ገፅ ቴክኖሎጂ አዳድስ እድሎችን መፍጠሩ ነው።

ይህን ዘመን የሚገልፅ ቃል ቢፈለግ 'ለውጥ' የሚለው ዋነኛው ገላጭ ቃል ነው።
እኛ በለውጥ ማዕበል ውስጥ ነን። ይህ የለውጥ ማዕበል በረከትም መርገምም ነው።

ለውጥን ለመግራት ፥ ዘመንን ለመዋጀት ሁነኛው መሳሪያ ሳይደክሙ መማር ፥ ሳይታክቱ ራስን ማሻሻል ነው።

በዩቫል ኖህ ሃራሬ ምክር እንቋጭ

ሃራሬ እንዲህ ያለውን ዘመን ለመዋጀት "ተግባቦት ፥ ተባባሪነት፥ የፈጠራ ክህሎት" ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው ይላል።

እኚህን ክህሎቶች ለማዳበር መትጋት ሸጋ አይደለም ?

@Tfanos

Читать полностью…
Subscribe to a channel