tfanos | Unsorted

Telegram-канал tfanos - Tesfaab Teshome

2111

ለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ። ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍

Subscribe to a channel

Tesfaab Teshome

በአንድ እንቅፋት ሦስቴ
* * *

"ስራ ፈታቻለሁ"
"ስራ ከምትፈታ እየታገልክም ብትሰራ አይሻልም ነበር?"
"የግል ችግር ገጥሞኛል"
"ምን ገጠመህ?"
"የ17 አመት ወንድም እንዳለኝ ነግሬሽ አውቃለሁ?"
"አላስታውስም"
"የ17 አመት ወንድም አለኝ"
"ምን ሆነ?"
"ዘመቷል"
"መዝመት ማለት?.... ወደ ጦርነቱ?"

ጮኸች። በሆቴሉ የነበሩ ሌሎች ሰዎች በሙዚቃውና በግል ወሬያቸው ተይዘው ባይሆን ድንጋጤ ያዘለ ድምፀቷ ያስደነግጣቸው ነበር። ወንድሜ እንደዘመተ የሰማኹ ቀን 'ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው?' ብዬ እንደተደናበርኩ እሷም ተደናበረች

"አዎ። ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው"
"ቤተሰብ እንዴት ፈቀደ?"
"በቤተሰብ ፈቃድ አይደለም"
"ታፍሶ ነው?"
"አልታፈሰም። ስለ ጦርነቱ እንደ አቅሙ መረጃ ይሰበስብ ነበር። ነሸጠውና ተመዘገበ። ነገር ግን ወደ ስልጠና ከገባ በኋላ ስልክ አግኝቶ ደውሎልኝ እንደፈራ ነገረኝ"
"እኔን" ደረቷን ደቃች
"እኔን" ደረት መድቃቱን ደገመች

"እሱ ከሄደ በኋላ እናቴ ደህና አይደለችም። 'አዳዲሶቹ ጥይት ማብረጃ ይሆናሉ' ሲባል ሰምታለች። ወንድሜ ፈንጂ አምካኝ አልያም ጥይት ማብረጃ ሆኖ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሞተ እርግጠኛ ናት"

"የኔ እናት" ደረት መድቃቱን ሰለሰች

"አይኗን ማየቱ ያስጨንቃል፥ ምግብ በመከራ ነው የምትበላው፥ለሊት ትቃዣለች"

"እኔ ልሰቃይላት" እንባዋ ተዘረገፈ

"መሄድ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ። እኔ የሱን እጥፍ እድሜ ኖሬያለሁ፥ 35 አመቴ ነው። ከሱ በተሻለ ህይወትን አጣጥሜያለሁ። እርሱ ግን ልጅ ነው"
"አንተስ ምን በወጣህ?"
"ከሱ በተሻለ ኖሬያለሁኝ"
"ገና በ 35?"
"ከ 17 አይሻልም? እሱ እኮ ምንም አልኖረም"

እንባዋ የመናገር ፍላጎትቴን አናረው። ለቅሶዋ በእናቴ ፊት የምሸሽገውን የታፈነ ስሜቴን እንድዘረግፍ ምክኒያት ሆነኝ።
"በጦርነት የሞተ ወንድም እንዳለኝ ነግሬሻለሁ?"
"አልነገርከኝም"
"የሁለት አመት ታላቅ ወንድሜ በባድመ ጦርነት ወቅት 'ጠላት የአገራችንን ድንበር ሊደፍር አይገባም' ብሎ ከሻቢያ ጋር ለመፋለም ሄዶ መስዋዕት ሆነ። ታምኚኛለሽ መሞቱን መርዶ ተነገረን እንጂ ሬሳውን የመቅበር እድል አላገኘንም"

"እኔን" ሌላ ደረት መድቃት

"ታናሽ ወንድሜ ደግሞ በ 97 ነው የሞተው"
"እንዴ....?"
"ተባራሪ ጥይት ነው የበላለው። ከምርጫ ጋር በተያያዘ ጉዳይ አገር ስትታመስ ከመንግሥት ወታደር ለተቃዋሚዎች የተተኮሰች ጥይት ወንድሜን በላችው"

"ምን ጉድ ነው?" እንባ የተቀላቀለበት ደረት መድቃት ያጀበው ንግግር

"ምን የሚሉት መኣት ነው? እንዴት ያለ መራራ እድል ነው?" ስታለቅስ አብሬያት አለቀስኩ።

"እናቴ ግማሽ አእምሮዋን አጥተዋለች"
"ለእኔ ያድርገው" እንባና ደረት መድቃት አልተለያትም

"ተስፋ ቆርጫለሁ። አዲስ ህይወት የማልሞክረው፥ እንደ ህፃን ከእናቴ ቤት መውጣትን የምፈራው 'ለማን ትቼያት እሄዳለሁ?' በሚል ስጋት ነው። አራት ወንዶችን ወልዳ ሁለቱ የጥይት ሲሳይ የሆኑባት እናቴ ስለምታሳዝነኝ ከአጠገቧ መራቅ ያስጨንቀኛል"

ወደ ጡቷ ስር ስትሸጉጠኝ ትኩስ እንባዋ በአንገቴ ስር ፈሰሰ። ሴተኛ አዳሪነት የሸፈነው ባህሪዋ በእንባዋ ተገለጠ። በርግጥ ርህራሄዋ እና የማድመጥ ብቃቷ ዘወትር እንዳስደነቀኝ ነው!.... ያላት መልካም ነገር ሁሉ በሴተኛ አዳሪነቷ የተከለለ ቢሆንም እሷን አለመውደድ ፈተና ነው።

"ጠብቀኝ" ከእቅፏ አስወጥታኝ ፊቷን ጠራረገች
"የት ልትሄጂ?"
"መውጫ ከፍዬ ልምጣ"
"አላድርም"
"ታድራለህ"
"ብር የለኝም"
"በነፃ ነው"
ምላሼን ሳትጠብቅ መቀመጫዋን እየወዘወዘች ተራመደች።

@Tfanos
@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ማንም ሲሆን ቢሳደብ መናደድ አያስፈልግም"

"አይ ስድብ መታገስ ይከብዳል"

"ለምን? ይሄማ ልክ አይደለም፥ በቃ ስድብን ከምንም አለመቁጠር ነው"

"አንቺ ምን አይነት ደደብ ነሽ? የማይመስል ነገር አትዘባርቂ፥ ደነዝ"

"ባለጌ ፥ በቅንነት ስመክርህ ትሳደባለህ? ደንቆሮ"

"ይቅርታ እህት፥ ላናድድሽ ፈልጌ አይደለም። 'የቱም ስድብ አያናድድም' ስላልሽ ነው የሰደብኩሽ"

"ዝም በል፥ጋጠወጥ"

"አትቆጪ ምክርሽን ትተገብሪው እንደሆን ልፈትንሽ ነበር የሰደብኩሽ፥ ግን ተናደድሽ"

"ዝም በል"

"እረ ተረጋጊ"

"አልረጋጋም፥ ሰድበኸኝ እንዴት እረጋጋለሁ?"

"ለስድብ መናደድ አያስፈልግም አላልሽም?"

"ብልስ ? አንተ አትናደድ አልኩ እንጂ እኔ አልናደድም ከልኩ?"

@Tfanos
@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ከጋፋት እስከ መቅደላ
* * *

ቴዎድሮስ ያሰሩትን 8 ሺ ኪሎግራም የሚመዝን መድፍ ከተሰራበት ስፍራ እስከ መቅደላ ያስወሰዱበት መንገድ ድራማዊ ነው። ነገሩ ትኩረት የተነፈገው ቢሆንም አግራሞትን የሚፈጥር እና ሰባት ወራት ግድም የፈጀ ነበር።

ንጉስ ቴዎድሮስ ከእለታት በአንዱ "መድፍ ስሩልኝ" የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ለፈረንጆች አስተላለፉ። ትዕዛዙ 'እምቢ' ሊሉት የማይችሉት ከአለት የጠጠረ ነበርና የንጉሱን ፈቃድ ለመፈፀም ሩጫ ተጀመረ።

አላማው ብረት ማቅለጥ የሆነ ግዙፍ ምድጃ ከተዘጋጀ በኋለ ብረት ቀለጦ የእሳት ፈሳሽም ሆነ። ብረት ቀልጦ የተዘጋጀው የእሳት ፈሳሽ ለሞዴልነት ወደ ተዘጋጀው ጉድጓድ እንዲፈስ ተደረገ፤ የማፍሰስ ሂደቱ 20 ደቂቃ የወሰደ ነበር።

በዚህ መንገድ የተጀመረው የመድፍ ስራ ከተገባደደ በኋላ በስራው ለተሰማሩ አውሮፓውያን የክብር ቀሚስ ፥ በብር እና በወርቅ ያጌጠ ፈረስ እና በቅሎ በተጨማሪም ለእያንዳንዳቸው 1 ሺ ብር በሽልማት ተሰጠ።

መድፉ ከጋፋት እስከመቅደላ የሄደበት መንገድ በብዙ የሚያስገርም ፥ ትኩረትን የሚሰርቅ ነበር።
አስቀድሞ መድፉን ለማጓጓዝ አላማ የሚውሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ጋሪዎች ተሰሩ፥የጋሪዎቹ ብዛት 14 ነበር።

መድፉ ግዙፍ ነው፥ ግዙፍ ሲባል ለግነት ያህል ሳይሆን ክበደቱ 80 ኩንታል ወይንም 8 ሺ ኪሎግራም የሚመዝን ነው።
ግዙፉን ቁስ ከጋፋት ወደ መቅደላ ማጓጓዙ መስከረም 21 ፥1860 አ.ም ተጀመረ።
ከጋፋት እስከ መቅደላ ያለው ርቀት 320 ኪሎ ሜትር ነው፥ ደግሞ ስፍራው መንገድ አልተበጀለትም።
የቴዎድሮስ ሰራዊት ከፊሉ ከፊት እየቀደመ መንገድ ሲሰራ ቀሪዎቹ መድፉን በማጓጓዝ ተግባር ይሰማራሉ።

መድፉን መቅደላ ለማድረስ የሚረዳ መጎተቻ በጥንቃቄ ተዘጋጅቷል። በዳገት ላይ ወደኋላ እንዳይንሸራተት ደግሞ ማገጃ ተሰርቷል።
800 ጋሪ ጎታች ሰዎች ተልእኮውን በድል ለመፈፀም ተመድበዋል። በመጎተቻው ከፊት ከሚጎትቱት በተጨማሪ ከኋላ የሚገፉ ሰዎቸ አሉ።

ይህ ሁሉ ዝግጅት ቢደረግም ጉዞው ደህንነቱ የተጠበቀ አልነበረም፥ መንገዱ ሽፍቶች ነበሩበት።
ሽፍቶች መሳናክል እንዳይፈጥሩ ሲባል ከሽፍቶች እየተፋለሙ መንገድ የሚያስለቅቁ ተዋጊዎች ተዘጋጁ።

ጥሻውን እየመነጠሩ መንገድ ማዘጋጀት ፥ ከሽፍታ እየተፋለሙ የደህንነት ስጋት ማስወገዱ ጉዞውን አዝጋሚ በማድረጉ የተነሳ ፥ በቀን የሚደረገው አማካይ ጉዞ ከ3 -4 ኪሎሜትር ብቻ ነበር

እመው "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ የስንቅ እጥረት ተከሰተ። ይሄኔ ቆፍጣናው ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ በመንገድ ወዳለ ሰብል በማቅናት እሸት በመብላት ለሰራዊታቸው 'ያደረግኩትን አድርጉ' የሚል ተግባራዊ መልእክትን አሰተላለፉ።
ቴዎድሮስ በጉዞ ወቅት አረአያ ሆነዋል። ዳገታማ ቦታዎች ላይ ቀልጠፍ ብሎ በመንገድ ስራ ይሰማራሉ፥ ጥሻ ይመነጥራሉ፥ አፈር ይደለድላሉ፥ ድንጋይ ይፈነቅላሉ።

6 ወር ተኩል ከፈጀ አድካሚ ጉዞ በኋላ መድፉ ከመቅደላ ግርጌ ደረሰ።
ከዚህ በኋላ ከቀደመው የላቀ ጥንቃቄ የታከለበት ስራ ተጀመረ። ወደ መቅደላ አምባ የሚያደርስ መንገድ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ጥንቃቄ ተሰራ።

መድፉ ከመቅደላ ግርጌ እየተጎተተ ሽቅብ መውጣት ሲጀመር ብርቱ ስጋት ነበር። በመጨረሻው ሰኣት መጎተቻው ተበጥሶ አደጋ እንዳይደርስ እና የተለፋው ሁሉ ከንቱ እንዳይቀር ተፈርቷል!

ከሰራዊቱ መሃል ከፊሉ 8 ሺ ኪሎ ጎራም የሚመዝነውን ግዙፍ መድፍ ይጎትታል፥ የተቀሩቱ ደግሞ ከኋላ ይገፉታል። ይሄን የሚያደርጉት በህብረት ድምፅ በማውጣት ስለሆነ የንጉሱን ድምፅ የሚሰማ የለም። ቴዎድሮስ መልእክት ማስተላለፍ ሲፈልጉ እጃቸውን ብድግ ያደርጉታል፥ ያኔ ሁሉም ፀጥ ይላል።

አድካሚ የነበረው የመድፍ ጉዞ ሰባት ወራት የተጠጋ ግዜን ፈጅቶ ከጋፋት ተነስቶ መቅደላ ደረሰ። ያኔ ንጉሱ ቦረቁ

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ስለሐገራችን ሙስሊሞች
* * *

የትላንት ሙስሊሞች፦ ጀጎልን አነፁ፥ አሚሮቹ ሐረርን አቅንተው የከተማ መንግስትን አቆሙ።
የሙስሊሙ ኡማ አሻራ ቀላል አልነበረም። የጊቤ መንግስታት ላይ ባለድርሻ ናቸው፥ የጂማን መልክ አበጃጅተዋል፥ ደግሞም የአዳል ሱልጣኔትና የፈጣጋር ታሪክ የነሱ ነው።

በእውነት ሚዛን ታሪክን ከለካን ፥ሙስሊም አባቶች ኢትዮጵያን ገንብተዋል።
ከአፋር እስከ ሱማሌ፥ ከወሎ እስከ ባሌ፥ ከምስራቅ እስከምራብ ፥ ከሰሜን እስከደቡብ ህያው ማህተም አኑረዋል።

ዛሬ ጥቂት ሙስሊሞች ላይ የምወቅስባቸው ነገር አለ። አባቶቻቸው ባቀኑት ሐገር ባለቤትነት አይሰማቸውም፥ አንዳንዶቹ በማይረባ ነገር ጭምር "እዬዬ" ማለት ቁም ነገር ይመስላቸዋል፥ 'የኢትዮጵያ ሙስሊም ታሪክ' ሲባል የአፄዎቹ ነገር ብቻ ትዝ ይላቸዋል። ደጋግመው "ኹለተኛ ዜጋ አታድርጉን" ይላሉ።

በእርግጥ ትላንት መሰደድ እና ባይተዋርነት ነበር። ለዲናቸው የታመኑቱ በቦሮ ሜዳ እንደ እንስሳ ታርደው ደማቸው ኩሬ ሰርቷል፥ በደልን አስተናግደዋል።

ታሪክ ግን የመገፋቱ ብቻ አይደለም።

የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሙስሊም አባቶች ጉልህ ሚና ነበራቸው። የኢትዮጲያ ትላንት ቢመረመር ፥ አከባቢዎች ቢቃኙ ያለ ሙስሊሙ ታሪክ የሐገሪቱ ታሪክ ሙሉ አይሆንም።

ጀግል የጎደለበት፥ ኢማሙ የሌለበት ፥ አዳል የተረሳበት ፥ ሼህ ጦሏህ የማይዘከርበት ፥ ቢላል የማይታወስበት ታሪክ ሙሉ አይደለም። ያለ ጥርጥር ትላንታችን የሙስሊሙ ማህበረሰብ በጎ አሻራ የታተመበት ነው።

ይህን ሐቅ መረዳትና ማክበር የሁሉም ሃላፊነት ቢሆንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሚና የማይተካ ነው።

ነገር ግን ጥቂት ያልሆኑቱ ለታሪካችው ተገቢውን ክብር የነፈጉ ሰነፎች ሲሆኑ ይታያል።

ምን እያልኩ ነው?

የሙስሊሙ ኡማ 'የኢትዮጵያ ሙስሊሞች' ታሪክን ሲዘክር መገፋትና መከራው ላይ ብቻ ማተኮር ስህተት ነው። ይህ ባይተዋርነትን ሊፈጥር ይቻላል።
ደማቁን እና ያልተነገረውን የሐገር ገንቢነት ታሪክ በኩራት እና በልበ ሙሉነት ማውሳት መዘንጋት የለበትም !


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ስለ ዶክተር ደረጀ ከበደ
* * *

ደረጀን በመዝሙሮቹ አለመውደድ ፈተና ነው። እርሱ ያለ ጥርጥር ታላቅ ዘማሪ ነው፥ ይሄን መካድ አይቻልም።
ደረጀ ፖለቲካ ላይ የሚሰጣቸው ሃሳቦች ግን ግራ አጋቢ ናቸው።
'አገልጋዮች በፖለቲካ ጉዳይ አንደበታቸው የተሸበበ ይሁን' የምል አይነት አይደለሁም፥ ፖለቲካ ቀመስ ሃሳብ ለመሰንዘር ነፃነት እና መብት አላቸው ባይ ነኝ።

ደረጀ የአማራ ህዝብ በማንነቱ ጥቃት ሲሰነዘርበት በግልፅ ማውገዙ ፥ ከህዝብ ጎን መቆሙ እና መንግስትን መተቸቱ እጅግ አግባብ የሆነ ቢሆንም ተደጋጋሚ አስተዛዛቢ ጥፋቶችን ፈፅሟል።

የኦሮሞን ህዝብ በግልፅ ለማነወር ሞክሯል። የሚያነበው መፅሐፍ ቅዱስ እና የሚያመልከው እግዚአብሔር ህዝብን ማንቋሸሽን እንደማይወድ መዘንጋት አልነበረበትም።

የአማራ ህዝብ በማንነቱ የተሰነዘረበት ጥቃት ሃጢያትም ወንጀልም ነው። ከ60ዎቹ ዘመን ጀምሮ አማራን ለጥቃት የሚያመቻች ትርክት ሲፈበረክ ነበር። ይህ ሊወገዝ የሚገባ ነውር ነው።

አማራ ላይ ጥላቻ መንዛት ነውር የመሆኑን ያህል ኦሮሞ ላይ ጥላቻ መንዛት ነውር ነው። "ዶክተር ደረጀ አጥፍቷል" ሲባል ነገሩን እንደ አማራ ጠልነት አድርጎ መፈረጅ ግራ አጋቢ ነው። 'ይህ ህዝብ በደል አይድረስበት ያኛው ህዝብ ግን ይበደል' ማለት ኢ-ኢፍትሃዊነት ነው።

"ኦሮሞን ሱሪ መታጠቅ አሰለጠንነው" የሚል ምናብ ወለድ ተረት እያወሩ እንዲሁም ህዝቡን በተደጋጋሚ እያንቋሸሹ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ እና እንደ ፍትህ ጠበቃ ለመታየት መሞከር የሚያስቅ ቀልድ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።

አማራ ላይ ጥላቻ መንዛት ነውር የመሆኑን ያህል ኦሮሞ ላይም ጥላቻ መንዛት ነውር ነው። ዶክተር ደረጀ ከበደ እና አድናቂዎቹ ይሄ ሊዘነጋቸው አይገባም !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ቡዳ ነኝ"
(እውነተኛ ታሪክ)
* * *

ያኔ እድሜዬ 10 አልተሻገርምና ዝርዝር ነገር ለመረዳት አልችልም፤ ነገር ግን እያንዳንዱን ነገር ዛሬም ድረስ አስታውሳለሁ።
እሷ የሰፈራችን ተስተካካይ አልባ ቆንጆ ነች። የቆዳዋ ጥራት እና የመልኳ ማማር ሊዘነጋኝ አይችልም።

በየሳምንቱ ማክሰኞ ሻሸመኔ ሸዋበር ቃለህይወት ቤተክርስቲያን የፓስተር ጌቱ ዱሬሳን አገልግሎት ለመካፈል አብረን እንሄዳለን። ያኔ ብዙ ታወራኝ ነበር።

ባለትዳር ናት፥ ከእኩዮቿ የማትቀራረብ ባይተዋር ባለትዳር። ሁሌም ከትምህርት ቤት መልስ እሷ ዘንድ ሄጄ የሆዷን ትነግረኛለች።

"ዛሬ ህፃን ልጅ ታሞ ትፊበት ተባልኩ" አለችኝ።
ነገሩ ስላልገባኝ "ምንድነው የምትተፊው?" አልኳት
"ምራቅ ነው የምተፋው" እየሳቀችብኝ
"ለምን?"
"ልጁን በቡዳ በልተሻል ብለውኝ..." እንባ ንግግሯን እንዳገደ አስታውሳለሁ።
"ልጃችንን በቡዳ በልተሻል ብለውኝ ተፋሁላቸው፥ የሰፈሩ ሰዎች ተሰብስቦ ተሳለቁብኝ፥ ግልምጫቸው እና ስድባቸው ሳያንሰኝ በጥፊ ተመታሁ" አለችኝ እያለቀሰች።

ያኔ 10 አመቴ ነው። እንዲህ ያለ ነገር ለኔ ልታማክረኝ አይገባትም ነበር። ነገር ግን እኩዮቿ ያገለሏት ባይተዋር ስለሆነች ከኔ በቀር የሆዷን የምትነግረው አልነበራትም።

"ልጅ የሌለኝ ባሌ ልጅ ስለማይፈልግ ነው፥ 'ቡዳ አግብተሃል' ሲሉት ሊፈታኝ ፈለገ፥ ሰበብ እየፈጠረ በየለቱ እንደ አህያ ይደበድበኛል። በአጠና ሲደበድበኝ ብጮህ የሚደርስልኝም የለም። ስለዚህ ዱላውን እቀበላለሁ። የግዴን ነው የምኖረው" አለችኝ በእንባ።

አድጌም ጭምር የቡዳ ነገር ይከነክነኛል። የዛሬ 7 አመት አከባቢ በቁም ነገር ስለ ቡዳ አያቴን ጠይቄው ነበር። ብዙ አፈታሪክ ነገረኝ። "ያወራህልኝ አይተሃል ወይም ያየ ሰው ታውቃለህ?" ብዬ ስጠይቀው 'ከመስማት በዘለለ ማናችንም አይተን አናውቅም' ነበር መልሱ።

'ቡዳ የሆኑ ሰዎች ጅብ ይጋልባሉ፥ ሬሳ ከመቃብር አውጥተው ይበላሉ፥ ሙታንን ለጉልበት ብዝበዛ ይጠቀማሉ' ወዘተ ሲባል እንሰማለን። ለዚህ ሁሉ ማረጋገጫ ቢጠየቅ 'ሰማን' እንጂ አየን የሚል የለም።

ወደ ቀደመ ነገሬ እንመለስ

አንድ እለት ከትምህርት ቤት ስመለስ በር ላይ ጠብቃኝ ። "ምሳ እንደበላህ ቶሎ ና" አለች፥ ያለችኝን አደረኩ።

"ልሄድ ነው" አለችኝ
"የት" አልኳት
"የት እንደምሄድ አላውቅም'' ነበር መልሷ፥ ምላሿ በእንባ የታጀበ ነበር።
ደስታ ከረሜላ ስጦታ ከሰጠችኝ በኋላ "130 ብር አለኝ፥ ይኸ ብር እስከወሰደኝ እሄዳለሁ" አለችኝ።

"ግራ እጄ እቃ በደንብ አይዝም። 'ቡዳ ናት' ያሉ ሰዎች በድብደባ ብዛት የሰበሩት እጄ በደንብ ስላልተጠገነ ከባድ እቃ መያዝ ይቸግራል። በባሌ ድብደባ የተነሳ ወገቤን ያመኛል፥ ይሄ የሆነው ቡዳ ተብዬ ነው፤ እናቴን 'ቡዳ ናት' ብለው ደብድበዋት በተአምር ከሞት ብትተርፍም ያልጋ ቁራኛ ናት። እኔም በልጅነቴ ተሰቃየሁ"

እያለቀሰች ስታወራ ግራ ገብቶኝ አብሬያት አለቀስኩ።

"ሴት ነኝ፥ ሰውነቴን ሸጬ እኖራለሁ" አለችኝ።
'ሰውነት መሸጥ' የሚለውን ንግግር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ከሷ ነው። ነገሩ ስለገረመኝ በአእምሮዬ ቢታተምም ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም። 'ሴተኛ አዳሪ እሆናለሁ' እያለችኝ እንደነበር የገባኝ አድጌ ነው።

"ቡዳ" የሚል ተቀፅላን ሸሽታ "ሸር*ሙጣ" መባልን መምረጧን ያወቅኩት ቆይቼ ነው።

"ስታድግ እንዳትረሳኝ፥ አንድ ቀን አገኝሃለሁ፥ ተስፋአብ ባለውለታዬ ስለሆንክ አልረሳህም" ብለኝ ሁለት ደስታ ከረሜላዎች ሰጠችኝ።

በማግስቱ መጥፋቷ ተሰማ፥ ሰፈርተኛው ሃሴት አደረገ።


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርማሉ
* * *

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ጴንጤዎች 'ፀበል አያድንም' ይላሉ ነገር ግን ከበሽታቸው ለመፈወስ ከእዩ ጩፋ ዘይት በ1ሺ ብር ይገዛሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ሙስሊሞች 'ሰሜኖቹ ክርስቲያናዊ መንግስት ለማቋቋም ስለሞከሩ ሊወገዙ ይገባል' ይላሉ። በተቃራኒው በጅማ እና በሃረር ተቋቁሞ የነበረውን እስላማዊ መንግስት ያሞግሳሉ። (ለኔ ሲሆን መብት ላንተ ሲሆን ጥፋት የሚል ሎጂክ

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ኦርቶዶክሶች 'ጴንጤዎች በመዝሙር ይጨፍራሉ' ይላሉ። ነገር ግን በንግስ ቀን ይሰክራሉ፥ ይጨፍራሉ፥ ይዘሙታሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ኤቲስቶች 'አለምን እግዚአብሔር ፈጠረ' የሚለው ተረት ነው ይላሉ። በተቃራኒው 'አለም ከአንዲት ቅንጣት ተፈጠረች' የሚለውን ያምናሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ አማኞች 'ኹለት የፍልስፍና መፅሐፍ አንብባችሁ አምላክ የለም አትበሉ' ይላሉ። በተቃራኒው አንዱን የሃይማኖታቸውን መፅሐፍ በቅጡ ሳያነቡ አምላክ አለ ማለታቸውን ይረሳሉ


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ብዙ ችግሮች አሉብን። ከችግሮቻችን መሰረቶች መካከል አንዱ ለሳይንስ ተገቢውን ክብር መንፈግ ይመስለኛል።

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ተጨባጭ ያልሆነ ሃሳብ ሲያሰራጩ ያለበቂ ማስረጃ ተቀባይነት ያገኛሉ። ፖለቲካው በሳይንስ በመደገፍ ፈንታ በአሉባልታ ይነዳል፥ ታሪክ በማስረጃ መሰረት መቆም ሲገባው በስሜት ላይ ይታከካል።

'አብሳላት' የምትባል እንስት ቲክቶክ ሰፈር ገናለች። የዝናዋ ሰበብ ከህክምና ሳይንስ ጋር ግብግብ መገጠሟ ነው። "ዶክተሮች በዚህ እና በዚያ ጉዳይ የሚሰጡት ማብራሪያ ስህትት ነው" ትላለች በድፍረት። የድፍረት ንግግሯ በበቂ አስረጅ ሲደገፍ ግን አይታይም።

ህክምናን ያህል እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግን ጉዳይ በዘፈቀደ መተንተን ምን አይነት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል አልገመቸችም፥ ወይም ግድ አይሰጣም።

'ሃክሞች ሪሰርች ስሩ' የሚል ምክር መስጠት ብትወድም እሷ ግን ከህክምና በተቃራኒ ለመራመድ የሰራችውን ሪሰርች አላሳየችንም። ነገሯ ድፍረት ወለድ ነው።

'ባህላዊ መድሃኒት አይሰራም ፥ ሳይንሳዊ ህክምና ፍፁም ነው' የሚል ድርቅና የለብኝም። ነገር ግን በዘፈቀደ የሚሰራጭ ወሬ ውጤቱ አደጋ ሊሆን ይችላል።

ሙያን እና ባለሞያን በተገቢ አግባብ ማክበር ጠቃሚ ነው።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሰዎች ሰላም ሳሉ ከሚናገሩት በላይ በቁጣቸው ወቅት የሚናገሩትን አምናለሁ።

ተበሳጭተው ብሔር ከተሳደቡ፥ በቀጣቸው ወቅት አንድን ሃይማኖት ካንቋሸሹ ፥ ስሜታዊ ሲሆኑ ግለሰብን በቡድን ከፈረጁ በፍፁም ላምናቸው እቸገራለሁ።

"ስለተቆጣው እንጂ ያ የኔ ማንነት አይደለም ገለመሌ" ቢሉ እንኳን አላምናቸው።

በደህና ወቅት የተሸሸገ ማንነት በቁጣ ወቅት ይገለጣል

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"ክብርነትዎ ርቦናል"

"እናንተ ቢርባችሁም ኢትዮጵያ ጠግባለች"

"ክብርነትዎ ጠኔ ሊገለን ነው"

"እኔ ጠግባችኋል ካልኩ ጠግባችኋል፥ እመኑ"

"ክብርነትዎ በረሃብ ብዛት ሞታችን ቀርቧል"

"እናንተ መጥገባችሁን ብትጠራጠሩም አለም መጥገባችሁን መስክሯል"


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ስለ ትግራይ ጦርነት
* * *

ከታሪኩ የማይማር ስህተቱን እየደጋገመ ይኖራል። ጥፋትን ከማስወገጃ መንገዶች አንዱ ከቀደመው በቂ ትምህርት መውሰድ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ በበቂ ሁኔታ መመርመር ይቀድማል።

ደም አፋሳሽ ስለነበረው የሰሜኑ ጦርነት ግባቸው ትምህርት የሆኑ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል።

ሁለት ጥያቄ እናንሳ

ሀ፥ ሴኮ ቱሬ 'መከላከያ ላይ መብረቃዊ እርምጃ ወሰድን' ባለበት ንግግር በቂ ማብራሪያ የሚያሻ ነገር ተናግሮ ነበር። በዛ ንግግር ትግራይ ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሆነ በቂ መረጃ ህወሃት እንዳገኘ እና ራስን ለመከላከል ሲባል ሳይጠቁ እንደቀደሙ ተናግሯል።

መንግስት 'ሰሜን እዝ ተጠቃብኝ' ሲል ህወሃት ደግሞ 'ጥቃት ሊሰነዘርብን ሲል ቀድመን መብረቃዊ እርምጃ ወሰድን' ይላል።
ሁለቱንም የማመን ግዴታ የለብንም። ነገር ግን ፍትህ እና ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር በጉዳዩ ላይ በቂ ምርመራ ሊሰራ ያስፈልጋል።
መንግስት ለጥቃት ሲዘጋጅ ህወሃት ቀደመ ወይስ ህወሃት ቀድሞ አጠቃ? አሳማኝ ማስረጃ መቅረብ አለበት


ለ፥ መንግስት 'ሰሜን እዝ ላይ ድንግተኛ ጥቃት ተሰነዘረ፥ መከላከያ በተኛበት ከጀርባው ተወጋ' ብሏል።
ሐገር ጠባቂ ሃይል 'በተኛበት ተወጋ' የሚለው ነገር ላይ ትችት መሰንዘር ይቻላል።
ነገር ግን መሰረታዊ ጥያቄ እናንሳ፥ መከላከያ ላይ የተባለው ጥቃት ሲሰነዘር ደህንነት ቢሮ ምን ሲሰራ ነበር? የደህንነት ተቋም ሐገር ሉአላዊነት ላይ የሚሰነዘርን ጥቃት ቀድሞ በመገንዘብ እንዲከሽፍ የሚያደርግ ሐላፊነት አለበት።

አንድ እዝ እንዲህ ያለ ጥቃት ሲሰነዘርት የደህንነት ተቋም ቀድሞ አለመድረሱ ጥያቄ አያስነሳም? ነገሩ ሴራ ነው? ወይስ የደህንነት ባለሞያዎች እንዝልህላልነት?

ለጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ማበጀት ለብዙ ነገር ይጠቅማል

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ኤቲስትነትን እንደ አዋቂነት ጥግ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም።

ኤቲስት ማለት በፈጣሪ መኖር የማያምን እንጂ ሳይንቲስት አይደለም።

አለማመን የተለየ ጥበብ ወይም እውቀት አይደለም፥ አያመፃድቅም።
አለማመን፥ የአማኝን መብት የመድፈጠጥ ስልጣንንም አይሰጥም። (ኤቲስት በመሆናቸው ብቻ አማኝ ላይ የመሳለቅ መብት ያላቸው የሚመስላቸው ጥቂት አይደሉም።

በአጭሩ ፥ ኤቲስነትን ከልህቀት እና ከልቅነት ጋር ማስተሳሰር ጥፋት ነው !

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

አንድ ሰው አንድን ብሔር (ኦሮሞን) በጭካኔ የሚፈርጅ ነገር ፖሰቶ ኮሜንት ልመለከት ገባሁ። ከኮማቾች መሓል ምን ያህሉ ያወግዙታል የሚለውን ለማየት ነበር አገባቤ።

ከአንድ ኮሜንት በቀር ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ የብሔሩን አባላት በጅምላ ይሳደባሉ።

የፖስቱ ሰበብ አንድ ወንጀል ነው። ወንጀሉን የብሔሩ አባላት ተፈራርመው አልፈፀሙትም። ለምን ይወቀሱበታል?

በግለሰብ ጥፋት ቡድን አይሰደብም ብሎ መናገር ይደክማል። አንድና አንድ ሁለት እንደሆነ ለኮሌጅ ተማሪ ማስተማር ያስፈልጋል ? እንዴት ለአቅመ ማገናዘብ የደረሰ ሰው እንዲህ ያለ ጥፋት ይሰራል?

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ፓስተር ታምራት በወንጌላዊያን አማኞች (ጴንጤ) ማህበረሰብ ዘንድ በእኩል የሚወደድ አባት ነው።
ከልጅ እስከ አዛውንት የሚወዳቸው 14 የመዝሙር አልበም ሰርቷል፥ በመላው አለም ተዘዋውሮ ወንጌል ሰብኳል፥ መፅሐፍ ፅፏል፥ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በአመራርነት አገልግሏል።

ታሜን የማይወድ ማን አለ?

ፓስተር ታምራት ፥ የሐገችን ፖለቲካ ሲተራመስ እና ንፁሃን ሲቀጠፉ ሃዘኑን እና ርህራሄውን በተለያየ አግባብ የገለፀ ቢሆንም ሰሞኑን ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል።

ሀ፥ መንግስት የሐገርን ሰላም ማስጠበቅ ግዴታው መሆኑን በመገንዘብ በጀርባ አጎንብሶም ቢሆን ሰላምን ያምጣ፥ የፖለቲካ ጥያቄ ካላቸው አካላት ጋር ይደራደር፥ ለፖለቲካ ጥያቄ ጥይት አይተኩስ ብሏል።

ለ፥ ሲኖዶስ፥ አብያተ ክርስቲያናት ፥ መጅሊስ ፥ ካውንስል ... የሚመሩ የሃይማኖት አባቶች ሐገር ለማደን ሃላፊነታቸውን ይወጡ፥ ለማስታረቅ ይንቀሳቀሱ ያለ ሲሆን የሐይማኖት ተቋማትን የበታች አመራሮች ሳይሆን ዋነኛ መሪዎች ወክለው ለማስታረቅ ይንቀሳቀሱ ብሏል። ይህም ማለት ኦርቶዶክስን በቀጥታ አቡነ ማቲያስ ጴንጤን ፓስተር ፃዲቁ ሙስሊሙን ሃጂ ቱፋ በቀጥታ ወክለው እርቅ የማውረድን ስራ የሙሉ ጊዜ ተግባር አድርገው ይከውኑ እንደማለት ነው።

ሐ፥ የሲቭክ ማህበራት ፥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ዛሬ ነገ ሳይሉ ሐገርን ለማዳን ይስሩ ብሏል።

መ፥ መገናኛ ብዙሃን ደም ከሚያቀባ አዘጋገብ እንዲታቀቡ ጠይቋል።

ሠ፥ አሁን ባለው ሁኔታ በመሳሪያ የፖለቲካ ችግርን ለመፍታት ቢሞከር ምንም መፍትሄ የማይገኝ ሲሆን፥ በሆነ ተአምር መንግስት ወይም ሌላ ሃይል ቢያሸንፍ እንኳ ቀውስ ይቀጥላል። ስለሆነም መፍትሄው ሁሉን አቀፍ ውይይት መሆኑን አሳስቧል።

ፓስተር ታምራት የ 20 ደቂቃ ንግግር ያደረገ ሲሆን ሃሳቡን እንደ ሁልግዜውም በትህትና እና በእውነተኛ ቅንነት አቅርቧል።

ፓስተር ታሜ ❤

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ማነው ፃዲቅ ሰው......
* * *

'ህወሃትን ያጠፋል' የተባለው ጦርነት የትግራይን ህዝብ በልቷል። ሕገ የማስከበሩ ዘመቻ ታዳጊዎችን ቀጥፏል፥ 'ጁንታውን ያከስማል' ተብሎ የታሰበው ከበባ የህዝብ ሞት ሰበብ ሆኗል።

ከዚህ በደል ነፃ የሆነ ማን ነው?

"ሁሉም ትግሬ አንድ ነው?" ብሎ ጥፋትን ያስተባበረ ስንት አለ?
"ለውጥ" የተባለው ግራ ገብ ነገር ከመምጣቱ በፊት (ከ2008 ጀምሮ) በመላው ሐገሪቱ አመፅ ሲቀጣጠል "ሐጎስ" የሚባል ምናባዊ ገፀባህርይ በመፍጠር 'ሐብትህን የዘረፈው ሐጎስ ነው' እያለ ሲቀሰቅስ የነበረ ፖለቲከኛ "በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በጥፋት አልተባበርኩም" የማለት መብት የለውም። ሞክኒያቱም ያኔ የዘራው ጥላቻ ፍሬ አፍርቷልና!

በአንድ ወቅት 'ከትግሬ ጋር ቡና አትጠጡ' እስከማለት የደረሱ ሁሉ የጥፋቱ አካል ናቸው።

ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ መንግስት "ሸኔን ላጠፋላችሁ ነው" ብሎ በከፈተው ዘመቻ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ወደሞት ተነድተዋል፥ ሰብአዊ መብት ተደፍጥጧል።
ሚዲያው በኦነግ ሸኔ ስም ጥይት ስለበላቸው የኦሮሞ ወጣቶች ደንታ የለወውም።
ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ መሰረታዊ አገልግሎት የተነፈገ የክልሉ ነዋሪ መከራ ሲጋፈጥ፥ በአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ ስም ሲረገጥ ተመልክቶ ርህራሄን ያሳየ ስንት ነው?

ከዚህ ጥፋት ነፃ የሆነ ስንቱ ነው?

ነገሩ ንፁሃንን የሚቀጥፍ ጥፋት የሚያዋልድ እንደሆነ ከማሰብ ይልቅ አንዳችን አውሬ ለማስወገድ የሚደረግ የፅድቅ ዘመቻ ተደርጎ እንዲታሰብ የወደደ ስንቱ ነው?
ጥቂት የማይባል ኤሊት ፥ ዘመቻውን እንዳልተፈጠረ ሊክድ አልወደደም?
"ሁለም ኦሮሞ ያው ነው" እያለ ጥላቻ የነዛ ስንት ነው?

አማራ ላይ ለአመታት ሳይቋረጥ የቀጠለው የጥፋት ዘመቻ እንዲሳካ መሰረት የጣለ ስንት ነው?

ለዘመናት 'አማራ ጨቋኝ' የሚል ቅስቀሳ መሰራቱ ሳያንስ ፥ ህዝቡ የሚያነሳውን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ 'የአሃዳዊያን ጩኸት' ብሎ የተሳለቀ ስንቱ ነው?

ስለህዝቦች መብት ከሚያወሩ አማራዎች ይልቅ የሌሎችን ስህተት በማጉላት 'ሁሉም ያው ናቸው' በማለት ህዝቡ ለጥፋት ተላልፎ እንዲሰጥ አልተቀሰቀሰም?
በሰሜኑ ጦርነት ከተሰሩ ስህተቶች መካከል 'በአማራ ኤሊቶች' ተሰሩ የሚባሉ ጥፋቶችን ብቻ በማጉላት ህዝቡን ለዛሬ ጥቃት ያመቻቸ ስንቱ ነው?

በፖለቲካችን መንደር ተቆጥሮ የማያልቅ ስህተት አለ፥ ስህተት አልባ ተደርገው የሚሳሉ ጥቂት የማይባሉ ሊህቃን የጥፋት በትርን ደጋግሞ አዋጥተዋል።


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሲዳስሰኝ
* * *

ኢየሱስ ከተራራ እየወረደ ሳለ ተመልክቼው ወደርሱ ዘንድ ፈጥኜ ሄድኩ። ከአለት ይልቅ የሚጠነክር ፍርሃት እየታገለኝ "ጌታ ሆይ ብትወድ አንፃኝ" አልኩት፡፡ በፊቱ ተንበርክኬ "ብትወድ አንፃኝ" አልኩት፡፡

ለምፃም ነኝ፡፡ በማህበረሰባችን የኖረ እምነት መሠረት ለምፅ የእርግማን ምልክት ፥ የሃጢያት ማህተም ነው። እኔ እና ቢጤዎቼ እንደሌሎች አይሁዳዊያን ወደ ምኩራብ የመግባት እድል የለንም፡፡ በእስራኤል ምድር ያለ ሁሉ ፥ ከዳን እስከቤርሳበህ የተሰማራው ህዝብ በሞላ የተረገምን መሆናችንን ያውቃል፥ ወገኖቻችን እንኳን አብዝተው ይፀየፉናል፡፡

በእጁ ሊነካን የሚወድ ማን አለ? ማንም የለም! እኛን በእጅ መንካት ያረክስ አይደል? እንኪያስ መርከስን የሚወድ ማን አለ? ለምፃም የሆንነውን እኛን በእጁ ነክቶ ላለመርከስ መጠንቀቅ ምን ይደንቃል?

የገዛ ዘመዶቻችን "ለምፃም ስላላደረከኝ አመሰግንሃለሁ" እያሉ ያህዌን እንደሚያመሰግኑ ማሰብ ምንኛ ልብ ያደማል?
የገዛ እናቴ እንኳን ከኔ ጋር አካላዊ ንክኪን ላለማድረግ ትጠነቀቃለችና ዳቦ የምታቀብለኝ በረጅም እንጨት ነው፡፡

እንደ ቆሻሻ ከከተማ ውጭ መጣል በእሺታ የምንቀበለው እጣ ፈንታችን ነው። "ለምን ይሄ ይሆናል?" ብሎ የሚሞግት አይኖርም፡፡
እኔና ቢጤዎቼ ብንገፋ ወይም ብንጣል ፥ ብንናቅ አሊያም ብንዋረድ 'አሜን' ብለን እንቀበላለን። የተረገምንና እርኩሳን እንደሆንን አምነናልና በኛ የተነሳ ሌላው እንዳይረክስ በፈቃዳችን እንተባበራለን።

አንዳንዴ "እኔም እንደሌሎች ወደ ምኩራብ የመግባት እድልን ባገኝ" ብዬ ተመኝቼ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ከለምፃምነቴ የተነሳ ይህ ሊሆን እንደማይችል ሳስብ ልቤ ይሰበራል፡፡
አንዳንድ ጊዜ እናቴ እንድታቅፈኝ እመኛለሁ፡፡ ዳሩ ግን ከንቱ ምኞት ነው።

ለምፅ የነጠቀኝን እያሰብኩ ሞትን አልናፈቅኩም?
* * *

ዛሬ ኢየሱስ ከተራራ ሲወርድ ተመልክቼ "ብትወድ አንፃኝ" ብዬ እግሮቹ ስር ተደፋሁ፡፡ ምናልባት ፍቃዱ ሆኖ ቢያነፃኝና እኔም ከሰዎች እኩል ብሆን ብዬ ተመኘው፡፡ ኢየሱስ ግን ዳሰሰኝ፡፡
እኔን መንካት ጸያፍ እንደሆነ እያወቀ ዳሰሰኝ፡፡

በነካኝ ቅፅበት ሠውነቴን አንዳች ነገር ሲወረኝ ታወቀኝ፡፡ ህልም ውስጥ ያለው ነበር የመሠለኝ፥ ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ ለምፅ አልባ የሆነ ሰው ሳይፀየፍ ሲነካኝ በቅዠት ያየሁ መሰለኝ። መዳሳሱ ገርሞኝ አይኔን ከድኜ ከፈትኩ ። ቅዠት አልነበረም፥ እውን ነው።

ኢየሱስን በእንባ በተሞሉ አይኖቼ አየሁት፡፡ አይኖች ርህራሄ ተሞልተዋል፥ ከአይኖቹ ብርሃን ፍቅር ይረጫል ፊቱ ላይ ትህትና ረቧል።

"ጌታ ሆይ አንተ ትሁት ነህ፡፡ እኔን መንካት ፀያፍ እና የሚያረክስ መሆኑን እያወቅህ ልትነካኝ ፈቀድህ። አንተ ልትዳስሰኝ ከወደድክ ባልነፃ እንኳን ግድ የለኝም፥ እንደማትፀየፈኝ ካወቅኩ በኋላ ባልፈወስ እንኳ ግድ የለኝም" ልለው ፈለግኩ። ነገር ግን ልቤ በፍስሃ ብዛት እንደ እምቦሳ ስትዘል ስለነበር ቃል ማውጣት ተሳነኝ።

ከለምፃምነት ከመንፃት በላይ በርሱ መዳሰስ ይበልጣል፡፡ አልተፀየፈኝም፥ አልናቀኝም፥ አላገለለኝም፡፡
"ንፁህ ሆኖ ሳለ እኔን ለምፃሙን ዳሰሰኝ" ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል?

እርሱ የሚጤስ የጧፍ ክር ይጠፋ ዘንድ የማይፈቅድ ፥ የተቀጠቀጠው ሸንበቆ ሲሰበር የማይወድ ነው፡፡

ትህትናው እንዴት ያለ ነው?

* * *
"ዳሰሱኝ የውዴ እጆቹ
ጎበኙኝ መልካም አይኖቹ
ተዳሰስኩ ተፈውሻለሁ
ጌታዬን አከብረዋለሁ"

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

አሁን ቅርብ ሰአት "ፈረሰኛ" የሚባለው የዶሮ አካል ለወንድ መሰጠቱን ፆታዊ መድሎ የሚያስመስል ፖስት አየሁ። እንግዲህ ነገሩ የመብት ትግል መሆኑ ነው

ከኖረ ልማድ ጋር ፀብ መግጠም እና የመብት ትግል እንደሚለያዩ ማብራራት አልፈልግም፥ "የሴቶች መብት ታጋዮች" ፀጉር መሰንጠቅ ትተው እውነተኛው ችግር ላይ እንዲያተኩሩ ማሳሰብም አልሻም፥ ይልቅ ስለፈረሰኛ የተነሳውን ስሌት ተከትዬ የወንዶች መብት እንዲከበር እጠይቃለሁ

ሐገር በሴት መወከሏ ወንዶች ላይ የተቃጣ የፆታ ጥቃት ስለሆነ ወንዶች መብታችንን ልናስከብር ይገባል 🤝

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ሆቴላችን በኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት ላይ በምርጥ የሆቴል አገልግሎት ዘርፍ ዕጩ በመሆን ቀርቧል
እርስዎም ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት ለጃሎ ሆቴልና ለሻሸመኔ ከተማ ድምፅ እንዲሰጡ በአክብሮት እንጋብዛለን!
https://www.oromiatourismweek.org/oromia-tourism-week-public-vote/
ጃሎ ሆቴል ሻሸመኔ

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

'ገደልነት መላ'
* * *

ግዙፋን ዝሆኖች፣
በፍቅር ሲላፉ ፥ በፀብ ሲፋለሙ
በመጣላት ፍልሚያ፣
በመዋደድ ልፍያ፣
የማያገባቸው ፥ ድኩማን ወደሙ፤

ደግሞ በዚህ መሓል፣
ብልህ ገደል ሆኖ ፥ ቀጣፊን ይቀጥፋል
አክሳሚ አስወግዶ፥ ደካማን ያተርፋል!

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

መንግስት ገንዘባችን ለተጫዋቾች አይስጥብን !
* * *

ለእግር ኳሰኞች ውድ ገንዘብ መከፈሉ በራሱ ችግር አይደለም። እግር ኳስ ቢሊዮን ዶላሮቹን የሚያንቀሳቅስ ግዙፍ ዘርፍ ነው፥ በርካታ ተጫዋቾች ሚሊዮኖችን በየአመቱ ያፍሳሉ።

"የኛ ሐገር ተጫዋች ከዶክተር በላይ ይከፈለዋል" ብሎ ማልቀስ ልክ ላይሆን ይቻላል። በሌላውም አለም ስፖርተኞች ከሌሎች ብዙ ሞያተኞች የላቀ ገንዘብ ያገኛሉ።

የኛ ሐገር ችግር የገንዘቡ ምንጭ ነው።
የሐገራችን ክለቦች በመንግሥት በጀት የምንቀሳቀሱ ናቸው። ዜጎች ከከፈሉት ግብር ተወስዶ ለኳሰኞች በየአመቱ ብዙ ሚሊየኖች መከፈሉ ጥፋት ነው።

እግር ኳሱ በራሱ ገቢ መፍጠር ቢችል ኖሮ ለተጫዋች 600 ሺ በወር መክፈሉ ጥፋት አይሆንም ነበር። መንግስት ከዜጎች ታክስ ሰብስቦ ሲያበቃ ፥ ለዜጎች መሰረታዊ ፍላጎትን በማማላት ፈንታ ፥ ሆስፒታል በመገንባት ምትክ፥ ለስፖርተኞች ረብጣ ገንዘብ ሲከሰክስ መመልከት ያስተዛዝባል።

የመምህር ደሞዝ ለማሻሻል በጀት የሌለው መንግስት ፥ ለተጫዎች መቶ ሺዎች ለመክፈል በጀት ሲኖረው ግራ ይገባል።

የአውሮፓ ክለቦች ለተጫዋቾች ሚሊዮን ዶላሮችን የሚከፍሉት ከመንግሥት ካዝና ወስደው ፥ ከህዝብ ሃብት አቀናንሰው አይደለም። እግርኳሳቸው በራሱ ካመጣው ሃብት ላይ ለስፖርተኞቻቸው ይከፍላሉ እንጂ ዜጎች የከፈሉትን የግብር ገንዘብ አይራጩበትም።

መንግስት ከዜጎች የሚያገኘውን ታክስ ሰላም ለማስፈን ፥ ድንበር ለመጠበቅ ፥ መሰረተ ልማት ለማሟላት ያውል። እግርኳሱ እራሱን በራሱ ያስተዳደር፥ እራሱን ይሸጥና ገቢ ያግኝ።
የሐገራችን እግርሷስና ክለቦች ራሳቸው ሃብት ፈጥረው ሲያበቁ ለተጫዋች መቶ ሚሊዮን ድረስ እንኳ በወር ቢከፍሉ ችግር የለውም።
ነገር ግን መንግስት ከዜጎች የሰበሰበውን ግብር ትርፍን ማምጣት ላልቻለው እግር ኳስ አይከስክስ

በታክስ የተሰበሰበ ገንዘብ የዜጎች ሐብት ነው! የዜጎች ሃብት አይባክን

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

በጃንሆይ ጊዜ ትውልዱ ዴሞክራሲ ጠየቀ፥ የነመንግስቱ ሃይለማርያም ቡድን መስከረም 2 ቀን 1967 'የህዝብ ጥያቄ መለስኩ' አለ። ከዛ በኋላ ንጉሱን ዴሞክራሲ የጠየቀው ትውልድ ንጉስ የለሽ፥ ዴሞክራሲ አልባ ሆነ።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

በሐገራችን ሰለምናዊ ስርወ መንግስት እስከ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመን መቆየቱ ይታወቃል። ሰለሞናዊ የተባለው ስርወ መንግስት ግንዱን ከንጉስ ሰለሞን እና ከንግስተ ሳባ የሚያስተሳስር ነው።

'ሰለሞን እና ሳባ ወሲብ ፈፅመው ቀዳማይ ሚኒሊክ የሚባል ልጅ ወለዱ፥ ሰለሞናዊው ስርወመንግስትም የዛ ተቀጥያ ነው' ሲባል መስማት የተለመደ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያየ አጋጣሚ ጥያቄ ተሰንዝሮ የነበረ ቢሆንም አሳማኝ መልስ ሲሰጥ አልገጠመኝም።

የምር ሰለሞን እና ንግስተ ሳባ ፆታዊ ግኑኝነት ፈፅመው ልጅ ለመውለዳቸው ተጨባጭ ማስረጃ አለ? ይሄን ተንተርሶ ሺ ጥያቄዎች መሰንዘር ይቻላል።
ታሪክ በማስረጃ ሊደረጅ ስለሚገባ ይሄን መጠየቅ ጥፋት አይደለም።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ግለሰብን "አንተ" በማለት ፈንታ "እናንተ" ማለት በጣም ደባሪ ነገር ነው። እንዲህ አይነት ነገር መታገስ አልችልም።

'እናንተ' ብሎ ፈረጆ ከሚነሱት መካከል ጥቂት ያልሆኑት የሚጠሉት ቡድን (ሃይማኖት ወይም ብሔር) እንዳለ በግሌ ታዝቤያለሁ። 'እናንተ' ብሎ ፈረጆ መንደርደር አንድም ግለሰቡን ከሚጠሉት ጎራ ለመደመር እንዲመች ጥርጊያ ማበጃጀት ነው።

ብሔርተኝነት አንዱ ባህሪው ጎራ መለየቱ ነው። እኛ እና እነሱ የሚል ጎራ አለው። 'ከኛ ወገን አሊያም ከተቃራያችን ጎራ ነህ' የሚል ፍረጃ አለ። ግለሰብን 'እናንተ' ብሎ ማለትም አንድም የብሔርተኝነት ውልድ ነው

ግለሰብ አእምሮ አለው፥ ያስባል ፥ ስለራሱ ሃላፊነት ይወስዳል። አንድን ግለሰብ ግለሰብነቱን ክዶ ቡድን ማድረግ ግለሰቡን ማዋረድ ነው። ለቡድናቸው አእምሯቸውን የሚያከራዩ ሰዎች አሉ። አቋም ለመያዝ በራስ አእምሮ በመገምገም ፈንታ የብሔራቸው አባላት የያዙትን አቋም እንደወረደ ይቀበላሉ። ይሄ ራስን ማክሰም ነው።
"እናንተ" የሚለው ፍረጃ በሌላ ቃል 'አእምሮህን ለሆነ ቡድን ያከራየህ፥ በራስህ የማታስብ መንጋ ነህ፥ አቋምህ ያንተ ሳይሆን የሌሎች መንጋ አሳዳሪዎች ነው' እንደማለትም ነው። በዚህ የተነሳ 'እናንተ' ማለትን እንደ አዋራጅ ንግግር እቆጥረዋለሁ።

@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

አስፈሪው የአፍሪካ እድል ፈንታ
(Repost)
* * *

መጀመሪያ ላይ የባሪያ ፍንገላ ዘመን ነበር። የላቀ አቅም ያደረጁት ደካሞችን ፈነገሉ፥ ገበያ ወስደው እንደ ሸቀጥ ቸረቸሯቸው፥ ሰው እንደቁስ ነግደው ገንዘብ አገኙ፥ በዚህም ኪሳቸውን አደለቡ። የተሻለ ምቾት ለማግኘት መደላድል ሰሩ።

የባሪያ ንግድ ዘመን አለፈና የቀኝ ግዛት ዘመን መጣ። አፍሪካውያን ከትላንታቸው ተምረው የተሻለ አቅምን አለገነቡምና ተገዥ ሆኑ። ሃይል ያደረጁቱ ፥ አቅም የገነቡቱ፥ ጀርመን ላይ ተሰባስበው ዶለቱ። ከስብሰባቸው ማግስት ደካማዎችን በቀኝ ግዛት ለመግዛት ተሳማሩ፥ በለስ ቀንቷቸው ተቀራመቷቸው።

ሃብታሙ አለባቸው የቀኝ ግዛት ዘመንን 'የካፒታል ልዩነት ዘመን' ይለዋል።

በቀኝ ግዛት ዘመን ካፒታል ያለው ካፒታል አልባውን በዘበዘ! ባለጠጋው ድሃውን ገዛ። አቅመደካማው ለጉልበተኛው ተንበረከከ።

ያ ዘመን አለፈ

ዘመናችን ሌላ መልክ ይዟል። ሳይንስ እና ተክኖሎጂ በህዝቦች መካከል ያለውን ልዩነት በእጅጉ አስፍቶታል። የተፈተነ እውቀት ከስልጡን ፖለቲካ ጋር እየተጋገዙ አገራትን በአቅም እያራራቁ ነው።

ምን እያወራሁ ነው?

ነገ ከትላንት የከፋ ይሆናል! ይህ ሟርት አይደለም! በእርግጠኝነት ነገ ከትላንት የከፋ ይሆናል።

የትላንት ተገዢነታችን መንስኤ የአቅም ልዩነት ነበር። ዛሬ ላይ የአቅም ልዩነታችን ከትላንት ይልቅ የሰፋ እና የከፋ ሆኗል።

አፍሪካ ነገዋ ያስፈራል። የባሪያ ፍንገላው ዘመን አልፎ የቀኝ ግዛት ዘመን እንደመጣው ሁሉ ሌላ መራራ ቀን መምጣቱ የማይቀር ይመስላል።

ያሳዝናል !!!

@Tfanos
@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

'መገኖ አፊኒ'
(እነሱ አማርኛ አይችሉም)
* * *
ማስገንዘቢያ ፥ ይህን ፅሁፍ በፖለቲካ አውድ እንዳትገነዘቡት እና በተሳሳተ መንገድ እንዳትተረጉሙት ማሳሰብ ይኖርብኛል።
*

ያአሳ ለገሰ ይባላል። በዘመነ ደርግ ለወታደራዊ ግዳጅ ከታፈሱ ወጣቶች መካከል ነው። እርሱ አፍ ከፈታበት ሲዳምኛ ቋንቋ በቀር አይናገርም፥ አይሰማም።
ያአሳ፥ የምልምሎች ስልጠና የተጀመረ ሰሞን ከሌሎች ጓዶቹጋ በመሆን ቱታውን ሊያጥብ ወደ ወንዝ ወረደ። ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን አምባጓሮ ተነሳ፥ ከአንድ ምልምልጋ ፀብ ተፈጠረ። የፀቡ መነሾ ፥ የጥሉ ሰበብ ቱታ ነው።
የምልምሎቹ ቱታ አንድ አይነት በመሆኑ ምክኒያት ልዩ ምልክት ካልተደረገበት በቀር ባለቤቱን መለየት አይቻልም።

"ይህ ቱታ የኔ ነው" ብሎ ለተነሳው ምልምል ያአሳ ማብራሪያ መስጠት ተሳነው። በቋንቋ አለመቻሉ ምክኒያት ማስረዳት ስላቃተው በቁጣ ተሞላ፥ በንዴት ብዛት ለፀብ ተጋበዘ፤ ቡጢ ተሰናዘሩ፥ ተቧቀሱ ፥ ተደባደቡ።

ሌሎች ምልምሎች ፀቡን ከገላገሉ በኋላ ወደ የፊናቸው የተሰማሩ ቢሆንም ቅጣት አልቀረላቸውም። የወታደር ድስፕልን በመጣስ ተቀጡ።

ቅጣቱ ስፖርታዊ ነው። ያአሳ፥ "አኮቦኩብ" ሲባል እንደታዘዘው ሊያደርግ ሞከረ፤ "ሩጥ" ሲባል ግን ተነስቶ ቆመ፥ ቀጥሎ "ፑሽአፕ ስራ" ቢባልም በቆመበት ተገትሮ ቀረ።
እሱ አማርኛ አይችልም። ቀጪው ምን እያዘዘው እንደሆነ በአግባቡ አልተረዳም፥ ሁኔታውን የተገነዘበ አልነበረም። ምልምሉ ወታደር ቋንቋ እንደማይችል በወቅቱ ምልምል ወታደር የነበረው በድሉ ዋቅጂራ ለቀጪው ለማስረዳት ቢሞክርም ጆሮ ተነፈገ።

ያአሳ ቋንቋ ባለመቻሉ ግራ ተጋብቶ መቆሙን እንደንቀት የቆጠረው አስር አለቃ በጫማ ጥፊ መታው፥ያአሳ ተዘረረ። ይኼኔ የሞተ ስለመሳላቸው መደናገጥ ተፈጠረ። መቺውም የገደለው መስሎት ተደናበረ። ምልምሉ ለደቂቃዎች ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ ነቃ።

ከዚህ በኋላ ያአሳ ባይተዋር ሆነ። ከጓዶቹ ጋር ለመቀላቀል አይፈልግም፥ ወንዝ ወርዶ ልብሱን አያጥብም፥ በብርቱ ዝምታ ብቻውን ማሳለፍን መረጠ። ምን እንደሚያስብ አይታወቅም። ከስልጠና ውጭ ያለውን ጊዜ ኹሉ በብርቱ ዝምታ ብቻውን ያሳልፋል....

አንድ ቀን 'ያአሳ ጠፋ' ተባለ። የት እንደሄደ ሳይታወቅ ድንገት ተሰወረ። ከመጥፋቱ አንድ ቀን ቀድም ብሎ ለበድሉ ዋቅጅራ 'መገኖ አፊኒ' ብሎ ነበር። (መገኖ አፊኒ ፈጣሪ ያውቃል ማለት ነው....)
* * *

ያያ ቡትሎ ከጋሙኛ በቀር የማይናገር ምልምል ወታደር ነው። ሌላ ጋሙኛ ተናጋሪ ጓደኛ የነበረው ቢሆንም የወንዙ ልጅና የቋንቋ ተጋሪ ጓደኛው ሞቷልና ባይተዋር ነው።

አንድ የልምምድ እለት ለያያ መጥፎ ቀን ነበረች።
እጩ ወታደሮች የጦር መሳሪያ ልምምድ ሊያደርጉ ተሰማሩ።
በልምምድ ስፍራው ያያ ቡቱሎ ያልተጠበቀ ነገር አደረ፥ ስህተት ሰራ። በደረቱ ወደፊት ይሳባል፥ በደረት መሳብ የሚያቀናው ወደ አደጋ ስፍራ ነው፥ ወደሞት ቀጠና! ነገሩ ያልጣመው ሰው ያያ እንዲመለስ ጥሪ ቢያደረግለትም የተባለውን ስላልተረዳ ምላሽ አልሰጠም።

በደረት መሳብ ጥቂት እንደተጓዘ አስፈሪው አደጋ ተፈጠረ፥ የተጠመደ ፈንጂ አገኘው፥ ያያ ቡቱሎን እሳት በላው። ለልምምድ ባቀናበት ስፍራ ወደ አመድነት ተለወጠ።
*

ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ 'የማይፃፍ ገድል' የሚል የእውነተኛ ታሪኮች ስብስብ መፅሐፉ አለው። በመፅሐፉ 'እነሱ አማርኛ አይችሉም' በሚል ርዕሰ በአይኑ የተመለከተውን ያሰፈረ ሲሆን የያያ ቡትሎ እና የያአሳ ለገሰ ታሪክ በዚህ በዚህ ፅሁፉ ተካቷል።


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

ፌደራሊዝም Vs አሃዳዊነት
* * *

ፌደራሊዝም እና አሃዳዊ የፖለቲካ ስርኣትን በተመለከተ የሚሰጡ ትርጉሞች እና ትንታኔዎች የምር ያስቃሉ።

አንዳንዶች ፌደራሊዝም ማለት "ጎሰኝነትን ማስዋብ" ይመስላቸዋል። ጥቂት የማይባሉቱ ደግሞ ከኦርቶዶክስ እና ከአማራ በተፃራሪ መቆም ያስመስሉታል። ከፊሎቹ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ፀብ መግጠም ያደርጋታል።

ፌደራሊዝም በአጭሩ፥ አንድ ሐገር በሁለት የመንግስት እርከኖች የሚተዳደርበት ስርዓት ነው።
የበላይ የሆነ ብሄራዊ መንግስት በውስጡ ላቀፋቸው ግዛቶች ሰፋ ያለ አስተዳደራዊ ሀላፊነት እና ነፃነት ይሰጣል።
ግዛቶቹ የግድ በብሔር መዋቀር አይጠበቅባቸውም።

በሐገራችን፥ አሃዳዊነት (unitary state) እጅግ በተሳሳተ መንገድ የሚተረጎም ነው። ራሳቸውን "ፌደራሊስት" ብለው የሚሰይስሙ አካላት "አሃዳዊነት ማለት አንድ ብሔር፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንድ ቋንቋ ማለት ነው" ይሉናል። በሚያስቅ ሁኔታ "ሚነሊክ አሃዳዊ ነው" ይሉናል። የቀደመ ታሪክን ማውሳት የአሃዳዊነት መገለጫ ይመስላቸዋል። አንዳንድ ወፈፌዎች ደግሞ አማራ እና ኦርቶዶክስ መሆን አሃዳዊ መሆን መስሎ ይሰማቸዋል።

በአጭሩ አሃዳዊነት ማለት፥ ከፌዴራል መንግሥት ስርኣት በተቃራኒ የሆነ ነው። በዚህ ስርኣት ፥ አብዛኛው ወይም ሁሉም የአስተዳደር ሥልጣን በማዕከላዊ መንግሥት እጅ ይሆናል። እንደ ፌደራሊዝም በአንድ ሐገር ሁለት መንግስት ስርኣት አይሆንም። ስልጣን በማዕከል ይከማቻል።

ቋንቋ ፥ ሐይማኖት፥ የብሔር መብት ከዴሞክራሲ ይቀዳል።

ለፅንሰ ሃሳቦች የተሳሳተ ብያኔ እየሰጡ ፖለቲካ መስራት ከንቱ ነገር ነው። ከስህተት የሚወለድ ስህተት ነው!


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

የነ ገቢሳ ትግል፥ የዘመናት የኦሮሞ ጥያቄ.....
* * *

ገቢሳ ሙለታ እድሜው የገፋ አይነስውር ነው። መተዳደሪያው በየጠጅ ቤቱ በሚያቀርበው እንግርጉሮ የሚገኝ ሽልማት ነበር።
በዘመነ ኢህአዴግ ፥ 'ኦህዴድ አመታዊ በአል ሊያከብር ስለሆነ ተገኝተህ አንጎራጉር' በሚል ከሹማምንት የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ወለጋ አቀና።

በፕሮግራሙ ማሲንቆውን እየገዘገዘ በኢህአዴግ የተገደለውን የኦሮሞ ታጋይ ሹርሹራን አወዳደሰ፥ የሟቹን ታጋይ ጀግንነት በግጥሞቹ መሰከረ።
ሹርሹራ ላይ ቃታ የሳበው የኦህዴድ ሰው መሆኑ ይነገር ነበር።

ከዝግጅቱ በኋላ የኦህዴድ ባለስልጣን ተቆጣ፥ አይነስውሩ ድምፃዊ ላይ ደነፋ። የኦህዴዱ ሰው "የምታወዳድሰው ኦነግ የለም፥ ያለነው እኛ ኦህዴዶች ነን፥ ይልቅ ኦነግ ሞቷል ብለህ ዝፈን" ብሎ አዘዘ። ገቢሳ ግን ትዕዛዙን ሊቀበል አልፈቀደም።
"ትሞታለህ" የሚል ዛቻ ቢመጣም "ብትገድሉኝ አይነ ስውር ገደላችሁ ትባላላችሁ" በማለት ፀና።

ከለውጡ በፊት እንደ ገቢሳ ያሉ ኦሮሞዎች ተደጋጋሚ መገፍተር ደርሶባቸዋል። በኦነግነት እየተፈረጁ የተሳደዱ፥ የታሰሩ፥ የተረሸኑ፥ ደግሞም መድረሻቸው የት እንደሆነ ያልታወቁ ኦሮሞዎች አሉ። 'የማረሚያ ቤቶች ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል' ተብሎ እስኪቀለድ ድረስ የኦሮሞ ወጣቶች ወደ እስር ተግዘዋል፥ ታጉረዋል።

የቄሮ ትግል መነሻ ሰበብ አለው። 'መብቴን አትንፈጉት የሚለውን ወገናችንን በኦነግነት አትፈረጁት' በማለታቸው መስዋዕትነት የከፈሉ ብዙ ናቸው። በደብረዘይት ኢሬቻን ለማክበር ተሰባስበው እንደወጡ የቀሩቱ ይረሳሉ?

ስማቸው ያልታወቀ፥ የከፈሉት ዋጋ ያልተነገረ ብዙ ኦሮሞዎች እንደወጡ ቀርተዋል።

የኦህዴድ ሰዎች የገዛ ወገኖቻቸውን ሲገርፉ ከከረሙ በኋላ የህዝብን ትግል ነጥቀው መንበራቸውን አደላደሉ። ሃጢያትን ሁሉ ለህወሓት አደሉ። ቅንጣት ታህል ሳያፍሩ "የትግርኛ ተናጋሪዎች ነበሩ ህዝብ የሚያሰቃዩት" በማለት አስነገሩ።

ትላንት የኦሮሞ ህዝብ ያነሳውን የመብት ጥያቄ በመታከክ ትርፍን ያጋበሱ የፖለቲካ ነጋዴዎች አሉ።
ዛሬ በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች በጦርነት ስለሚሞተው ኦሮሞ የሚያወራ የለም፥ የኦሮሞ ህዝብ ስቃይ መረሳቱ ሳያንስ ህዝቡ በድሎት እንደሚኖር የሚያምኑ አሉ።

"በእንቅርት ላይ" እንደሚባለው ሁሉ ፥ ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑ መደዴዎች 'ስርኣቱ የኛ ነው፥ በኦሮሞነታችን ያሻንን እናደርጋለን' ብለው በአደባባይ ይናገራሉ።
ትላንት የኦሮሞ ወጣት በየእስር ቤቱ ለሰቆቃ ሲደረግ ፥ ተግድለው ሬሳቸው ለአውሬ ሲጣል ኦሮሞነታቸውን ሸሽገው የነበሩ ጥቅመኞች ዛሬ "ኦሮሞነቴን እወቁልኝ" ብለው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ይሄ ሳያንስ ሌላውን ማህበረሰብ በነውረኛ ቃል በመሳደብ ማንነታቸውን ለማፅናት ይታትራሉ።

ሌላውን በማንቋሸሽ ኦሮሞነት አይገለፀም፥ ይሄ 'ሰፉ' ነው። ነገር ግን ነውር እና የህዝብ እሴት ምንነትን የማያውቁ በመሆናቸው ከብልግናቸው ሊታቀቡ አይችሉም።

ሀብታሙ አለባቸው "ህንፍሽፍሽ" የሚል መፅሐፍ አለው። 'ድዱዕ' የምትባል የመፅሐፉ ገፀባህርይ ለዛሬ ትምህርት የሚሆን ጥያቄ ታነሳለች።
"ሰው በህወሓት የተነሳ መላውን ተጋሩ ለምን በጥርጣሬ ያየናል? የህወሃት ሹማምንት በሰረቁ ሌሎቻችን ምን አግብቶን እንወቀስ?" ትላለች። የሃብታሙ መፅሐፍ ለድዱዕ ጥያቄ መልስ አለው።
"አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አንድን ማህበረሰብ በተለየ ሁኔታ እወክለዋለሁ ብሎ ወደ ስልጣን ከወጣ በኋላ የፓርቲውን ድርጊት የህዝብ አድርጎ የሚቆጥሩ ብዙሃን ይፈጠራሉ" ይላል።

የሃብታሙ ሎጂክ ዛሬም ይሰራል።

በእርግጥ በኦህዴድ ጥፋት የኦሮሞ ህዝብ መወቀስ ባይኖርበትም ጥቂት በማይባሉ ሰዎች አእምሮ ውስጥ ህዝብና ፓርቲን አንድ የሚያደርግ ደመነፍስ ይፈጠራል፥ ይህም በሂደት ዋጋ ያስከፍላል።

የኦሮሞ ህዝብ በዘመናት መካከል የሚታወቁ የፖለቲካ ጥያቄዎች አሉት። ጥያቄዎችን በግልፅ ከገመገምን ዛሬም አልተመለሱም።
የህዝብን የዘመናት ጥያቄ በመታከክ መንበር የያዙቱ ህዝቡ ላይ መከራን ፈጥረዋል።

ወላጋ ፥ በተማሩ ሰዎቹ እና በተፈጥሮ ሃብቱ ከመታወቁ ይልቅ በስጋት ቀጠናነቱ እንዲታወቅ አድርገዋል። አንጋፋውን ቦረና በረሃቡ ግዜ ረስተውታል። የራስተ ፈሪያን መዳረሻዋን ሻሸመኔ በሰው ሰቃይነት እንዲትታወቅ አድርገዋል።

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ መልካም እሴቶቹ ሁሉ እንዲዘነጉ እና በስጋትነት እንዲፈረጁ ታትረዋል።

ለአመታት የኦሮሞ ወጣት አጥንቱን የከሰከሰው፥ ደሙን ያፈሰሰው እንዲህ ያለ ነገር እንዲፈጠር አይለም።

ደመ ከልብ ሆኖ በቀሩ ኦሮሞዎች ስም ጥቅምን ያጋበሱ ሆዳሞች በየአደባባዩ "ኦሮሞዎች ተረኞች ነን፥ የወደድነውን እናደርጋለን" እያሉ ሲመፃደቁ ነገራቸው ምን እንደሚያስከትል እንኳ መገመት አይችሉም።

ትላንት ኦሮሞ የታገለው ፥ የታሰረው እና የሞተው እንዲህ ያለ ብልግና እንዲፈጠር አይደለም።

እረፉ!


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

በቀለኛ አስተሳሰብ ያላቸው ፥ ይቅር ባይ መሆን የማይፈልጉ ሰዎች ቢያንስ በአደባባይ ስለሃይማኖት ባያወሩ ደስ ይለኛል። ቂመኛ ሆኖ ስለፈጣሪ የሚያወራ ሰው ግብዝ ነው!

ከብሔራቸው አጥር የማይወጡ ጭፍኖች ፥ ለሌላው ወገን ጥላቻ ያላቸው ፥ እያንዱንዱን ጉዳይ በዘር መነፅር የሚመዝኑ፥ ለሌላው ሃጢያት ያሉትን ለነሱ ነገድ ሲሆን እንደ ፅድቅ የሚመለከቱ ዘረኞች በአደባባይ ስለሃይማኖት ባይወሩ ሸጋ ይመስለኛል።
ጭፍን ብሔርተኛ ሆኖ ስለፈጣሪ የሚያወራ ሰው ግብዝ ነው !

ሁሉም ሃይማኖት መሰረታዊ አስተምህሮ አለው። አማኝ በተቻለ መጠን ለእምነቱ እሴት የሚታመን ቢሆን መልካም ነው።

በግልፅ የሃይማኖትን እሴት የሚፃረር ፥ ከእምነቱ ትምህርት ተቃራኒ የሆነ ሰው እንደ ሃይማኖተኛ ሆኖ ድራማ የሚሰራው ማንን ለማታለል ነው? ራሱን ይሸውዳል ወይስ ተመካቹን ይሸውዳል? ወይስ 'አምነዋለሁ' የሚለውን ፈጣሪ ለማታለል እየሞከረ ነው ?


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

"አባታችን የማይረባ ሰው ነው። በሱ ዘመን ኑሮ ርካሽ ነበር፥ አሁን 20 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ቤት ያኔ ሰባት ሚሊዮን ብቻ ነበር ዋጋው። ጤፍ 10 ሺ ብር ብቻ ነበር። ቅንጡ መኪና በ20 ሚሊዮን ብር ብቻ ይገዛ ነበር፥ የትም ሲንዘላዘል ባያባክን ኖሮ ዛሬ እኛ ሃብታም እንሆን ነበር"

ከላይ ያለው ሃሳብ፥ ለወደፊቱ ልጄ ለጓደኞቹ ከሚያማኝ የተወሰደ ነው።

ልጄ ሆይ፥ በኛ ዘመን አንተ እንደምትገምተው ኑሮ ርካሽ አልነበረም።
ልጄ ሆይ ፥ ባንተ ዘመን አንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋው አንድ ማዳበሪያ ሙሉ ብር መሆኑን ተመልክተህ 'በአባቴ ዘመን ኑሮ ርካሽ ነበር፥ ጤፍ 10 ሺ ብር ብቻ ነበር' ብለህ አታስብ።

በኔም፥ በአያቴም ፥ በምንጅላቴም ዘመን ኑሮ ውድ ነበር።
በአባቴ ዘመን ጤፍ መቶ ብር ቢሆንም አባቴ መጎዣው አልነበረም። እኔም በዘመኔ መግዛት አልችም። አንተም እንደኔ ነህ።

ልጄ ሆይ፥ ለወደፊቱ ልጅህ ባንተ ዘመን ኩንታል ጤፍ ዋጋው ማዳበሪያ ሙሉ ገንዘብ መሆኑን አራክሶ ያወራል። ምክኒያቱም ከታሪክ እንደተማርነው ከዘመን ዘመን ኑሮ ይበልጥ ይከፋልና !


@Tfanos

Читать полностью…

Tesfaab Teshome

የፖለቲካ ሀሁ

ዲሞክራሲ ማለት ከብዙ በመወለድ መንበር ማግኘት ሳይሆን በብዙ በመመረጥ ስልጣን መያዝ ነው።

@Tfanos

Читать полностью…
Subscribe to a channel