#የአውሮፓ_የአመቱ_ምርጥ_ለማን_ይገባል?
🇪🇸 ፔፕ ጋርዲዮላ (የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ)
🇮🇹 ማንቺኒ (የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ)
🇩🇪 ቶማስ ቱኼል (የቸልሲ አሰልጣኝ)
- ኢትዮጵያ ከአዘጋጇ ካሜሩን ጋር ተደልድላለች
ምድብ A
🇨🇲 ካሜሮን
🇧🇫 ቡርኪናፋሶ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ
✅ የመጀመሪያ ጫወታችንን ጥር በገባ በመጀመሪያው ቀን እናደርጋለን።
📆 ጥር 01-2014 🇪🇹 ኢትዮጵያ 🆚 ኬፕ ቨርዴ 🇨🇻
📆 ጥር 05-2014 🇨🇲 ካሜሮን 🆚 ኢትዮጵያ 🇪🇹
📆 ጥር 09-2014 🇧🇫 ቡርኪናፋሶ 🆚 ኢትዮጵያ 🇪🇹
📌 ተጠናቀቀ| ኖርዊች 0-3 ሊቨርፑል
✅ ሞሐመድ ሳላህ 1 ጎልና 2 Assist አድርጎ የጫወታው ኮከብ ሲባል ጆታ እና ፈርሚንሆ ደግሞ ሌሎቹን ጎሎች አክለዋል
⚽ ሪከርድ:- በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ በ5 ተከታታይ ሲዝን በመክፈቻ ጫወታ ጎል ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ ሆኗል።
17-18 🆚 ዋትፎርድ ላይ ⚽️
18-19 🆚 ዌስትሃም ላይ ⚽️
19-20 🆚 ኖርዊች ላይ ⚽️
20-21 🆚 ሊድስ ላይ ⚽️⚽️⚽️
21-22 🆚 ኖርዊች ላይ ⚽️
✅ ሞሐመድ ሳላህ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከተቀላቀለ ከ2017/18 ሲዝን በኋላ 35 ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ሲሆን በዚህ ግዜያት የሚበለጠው በዴብሬይን ብቻ ነው (50)
✅ ሞሐመድ ሳላህ በፕሪምየር ሊጉ የመክፈቻ ጫወታ 10 ጎሎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ከዋይኒ ሮኒ ቀጥሎ ሁለተኛው ምርጥ ስኬታማ ተጫዋች ሆኗል።
⚽️ 8 ጎል 5 assist ሮኒ
⚽️ 7 ጎል 3 assist ሳላህ
✅ በሊቨርፑል ቤት በፕሪምየር ሊጉ በአነስተኛ ጫወታ 10 ጎል በማስቆጠር
🏟 በ13 ጫወታ ዳንኤል ስተሬጅ እና ሞሐመድ ሳላህ
🏟 በ18 ጫወታ ፎውለር እና ፈርናንዶ ቶሬስ
🏟 በ20 ጫወታ ዲዮጎ ዦታ
✅ በምሽቱ ጫወታ ፈርሚንሆ ያስቆጠራት ሁለተኛዋ ጎል በሊቨርፑል ታሪክ በሊግ ውድድር 8,000ኛ ጎል ሆኖ ተመዝግቧል
✍ Yisma Mo
#BREAKING
✅ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በስሙ የታተመ አንድ ሚልየን ማልያ ለመሸጥ አነስተኛ ግዜ የፈጀበት ተጫዋች ሆኗል።
✅ ገናኮ አንድም ደቂቃ አልተጫወተም ፣ አንድም ጎል አላስቆጠረም ምን ጉድ ነው?
☞ መረጃው የስካይ ስፖርት ነው
#የአርሰናል_ደጋፊ_ሆነህ
✅ በመክፈቻ ጫወታ በአዲስ አዳጊ ክለብ ተሸንፈህ
✅ ቀጣዩ ተጋጣሚህ የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ቸልሲ ሲሆንብህ
✅ 3ኛው ጫወታህም የጋርዲዮላው ሲቲ መሆኑን ስታውቅ
#ተገረሙ 🙆♂
✅ ሊል ያለፈው አመት የፍሬንች ሊግ 1 ሻምፒዮን ነው። እና?
✅ እናማ ምን መሰላችሁ አሁን ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሙሉ ተጫዋቾች አመታዊ ደሞዛቸው ተደምሮ ፒኤስጂ ለሊዮኔል ሜሲ ብቻ የሚከፍለው ላይ አይደርስም።
✅ የሊል ትልቁ ተከፋይ ፖርቹጋላዊው አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝ ሲሆን በሳምንት £50,000 ብቻ ይከፈለዋል። የሜሲ ሳምንታዊ ደሞዝ እኮ £675,000 ነው።
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ያግኙ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
#የእንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ_የመጀመሪያ_ሳምንት_ጫወታዎች
✅ አርሰናል አዲስ አዳጊው ብሬንትፎርድን ዛሬ ምሽት ይገጥማል
✅ ነገ ቀን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ሊድስን ያስተናግዳል
✅ ቅዳሜ በለንደን ደርቢ ቸልሲ ክሪስታል ፓላስን ይጋብዛል
✅ ቅዳሜ ምሽት ላይ ሊቨርፑልም ኖርዊችን ይገጥማል
✅ የአምናው ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ በሳምንቱ ታላቅ ጫወታ ከሜዳው ውጪ እሑድ ምሽት ላይ ቶተንሃምን ይገጥማል።
✅ የ2021/22 ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ጫወታዎች ሙሉ ፕሮግራም በኢትዮዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከታች በምስሉ ላይ ይገኛል።
───────────────────────────
#እግር_ኳስ_The_Beautiful_Game በልዩነት በጥራት
───────────────────────────
✅ ይህቺ የ119ኛ ደቂቃ ቅያሪ ነበረች የአውሮፓ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ወደ ብሪጅ የወሰደው። በትክክለኛው ሰዓት ትክክለኛ የተጫዋች ቅያሪ ። 2 የመለያ ምት አዳነ ቸልሲም ሻምፒዮን ሆነ
👏👏👏 #ኬፓ_አሪዛባላጋ 👏👏👏
✅ የፒኤስጂ ተጫዋች በታሪክ ባሎንዶር አሸንፎ አያውቅም
✅ ፒኤስጂ ቤት ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አይታወቅም
✅ በፒኤስጂ ማልያ የፊፋ የአለም ምርጥ የተባለም የለም
✅ በፒኤስጂ ታሪክ የወርቅ ጫማ ያሸነፈ ተጫዋች አይታወቅም
✅ በፒኤስጂ ቤት Best Playmaker የተሸለመ የለም
📌 አሁን እነዚህን ሁሉ ክብሮች ይዞ ሊዮኔል ሜሲ መጥቶላቸዋል። ፒኤስጂ በዘመነ ሊዮኔል ሜሲ ፓሪስ ላይ ገና ካሁኑ ትልቅ ገፅታቸው ሆኗል።
✅ ሊዮኔል ሜሲ በፒኤስጂ ቤት በይፋ 30 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ክለቡ አረጋግጧል
ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና 3⃣0⃣ ቁጥር ማልያ አድርጎ
👕 33 ጫወታ ተጫወተ
⚽️ 8 ጎል አስቆጠረ
🅰️ 3 ለጎል አመቻቸ
#ፖሪስ_እንግዳዋን_ናፍቃለች
✅ ሊዮኔል ሜሲ ገና ከባርሴሎና አልተነሳም የፒኤስጂ ደጋፊዎች ግን የፓሪስ ኤርፖርትን አጥለቅልቀውታል።
✅ የአለም ምርጡን ተጫዋች ፓሪስ ላይ ላይ ማየት ናፍቋቸዋል። ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፒኤስጂ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከሰዓታት ባነሰ ግዜ ውስጥ ይደርሳል ተብሏል።
✅ አሁን ፓሪስ ላይ ያለው የፖሊሶች የደህንነት ጥበቃ የታላቅ ሀገር መሪን ለመቀበል እንጂ ለእግር ኳስ ተጫዋች አይመስልም።
✅ ምስጋና ለላሊጋ አስተዳዳሪዎች ይሁንና ሊዮ ለፓሪሶች ከእግር ኳስ ተጫዋች በላይ ትልቅ ብራንዳቸውም ስለሚሆን ንጉሳቸውን በጉጉት እየጠበቁት ነው
#የቶኪዮ_ኦሎምፒክ_በአሜሪካ_የበላይነት_ተጠናቋል
🇺🇸 626 አትሌቶችን በ28 የተለያዩ የስፖርት አይነቶች ያሳተፈችው ሀገረ አሜሪካ 39 ወርቅ ፣ 41 ብር እና 33 ነሐስ በድምሩ 113 ሜዳልያ አግኝታ ቻይና እና አዘጋጇ ጃፓንን አስከትላ የቶኪዮ 2020 የሜዳልያ ሰንጠረዡን በአንደኝነት አጠናቃለች።
✅ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከአለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን ጎረቤታችን ኬንያ ከአህጉራችን ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች
#SHARE ይደረግ
#ኬንያዊው_ኢሊዩድ_ኪፕቾጌ_የማራቶን_አሸናፊ_ሆኗል
✅ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለሊቱን በተደረገው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ኪፕቾጌ አሸንፎ ከ40 አመት በኋላ በኦሎምፒክ መድረክ ለተከታታይ የወርቅ ሜዳልያ ያገኘ አትሌት ሆኗል።
🇯🇵 2:08:38 ቶኪዮ
🇧🇷 2:08:44 ሪዮ
✅ 3 አትሌቶች ብቻ በኦሎምፒክ ታሪክ በማራቶን በተከታታይ ማሸነፍ ችለዋል
📅 1960 እና 1964 አበበ ቢቂላ
📅 1976 እና 1980 ዋልድማር ሲዬርፒንስኪ
📅 2016 እና 2020 ኢሊዩድ ኪፕቾጌ
✅ ሀገራችንን በቶኪዮ ማራቶን የወከሉት ሹራ ቂጣታ: ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ውድድራቸውን የአየር ንብረቱን መቋቋም አቅቷቸው አቋርጠው ወጥተዋል።
✅ ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በኦሎምፒክ ታሪክ 4 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል
🥉 2004 አቴንስ 5,000 ሜትር ነሐስ
🥈 2008 ቤጂንግ 5,000 ሜትር ነሐስ
🥇 2016 ሪዮ በማራቶን ወርቅ
🥇 2020 ቶኪዮ በማራቶን ወርቅ
✅ በአንድ ኦሎምፒክ ከኬንያ ውጪ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ የሆነ ሀገር የለም። ጎረቤታችን ኬንያ ግን ለዛውም በሁለት ተከታታይ ኦሎምፒክ ይህን ማሳካት ችለዋል (2016 ሪዮ ላይ 2020 ቶኪዮ ላይ)
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
#ምጥን_እግር_ኳሳዊ_መረጃዎች
✅ ሜሲ ነገ በካምፕ ኑ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
✅ የቸልሲ እና የሉካኩ ዳግም ጋብቻ የማይቀር ነው
✅ ፒኤስጂ የፓሪሱን Eiffel Tower ለማክሰኞ ተኮናትሯል
✅ አርሰናል የሊዮኑን ኮከብ ለማግኘት እየጣረ ነው
✅ ሊዮኔል ሜሲ ከፒኤስጂ በአመት €35+ ሚልየን ያገኛል
✅ አልቬስና ብራዚል የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ሆነዋል
✅ ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን በሰፊ ጎል አሸንፏል
📌 ከባርሴሎና ጋር መለያየቱ ይፋ የሆነው የ6 ግዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ነገ በግዙፉ ካምፕ ኑ ስታድየም ተገኝቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።
📌 ቸልሲ ተመጫዋቹ ሉካኩን ዳግም ስታምፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ጣጣውን ጨርሶ እየተጠባበቀ ይገኛል። የለንደኑ ክለብ ለዝውውሩ €115 ሚልየን ለኢንተር የሚከፍል ሲሆን ሉካኩም በአመት €12 ሚልየን ደሞዝ በሚያስገኝለት የግል ጥቅማ ጥቅም ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በርካታ ምንጮች እየዘገቡ ነው
📌 ሊዮኔል ሜሲ ማረፊያው ፓሪስ መሆኑ እውን ነው በአመት €35+ ሚልየን በሚያስገኝለት ክፍያ እስከ 2023 እንዲሁም ለተጨማሪ አንድ አመት በሚያቆየው ቅድመ ስምምነት ድርድራቸውን የፓሪሱ ክለብ እና የሜሲ ወኪል የሆኑት ወላጅ አባቱ ጋር መጨረሳቸው ተሰምቷል።
📌 ፒኤስጂ ታላቁን የፓሪስ ማማ Eiffel Tower ለፊታችን ማክሰኞ እንደተኮናተረ መረጃዎች እየወጡ ነው። የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ለመጨረሻ ግዜ ይህን ያደረገው ኔይማርን የአለማችን የዝውውር ሪከርድ ሰብሮ የግሉ ካደረገ በኋላ በብርሃን በተንቆጠቆጡ ማብራቶች እንኳን ደህና መጣህ ለማለት ተጠቅመውበት ነበር። በተመሳሳይም የሊዮኔል ሜሲን ይፋዊ አቀባበል ማክሰኞ ለማድረግ አስበው ነው ተብሏል።
📌 ከመደበኛው ደቂቃ ወደ ጭማሪ ሰዓት ያመራውና በቶኪዮ ኦሎምፒክ የወንዶች እግር ኳስ ፍፃሜ ብራዚል ስፔንን 2ለ1 አሸንፋ ለሁለት ተከታታይ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘት ስትችል በ38 አመቱ ሀገሩን እየመራ ለድል ያበቃው ዳንኤል አልቬስም በተጫዋችነት ዘመኑ 43ኛ ሻምፒዮንነቱን አሳክቷል።
📌 ፕሪምየር ሉግ ከመጀመሩ በፊት የመጨረሻ የአቋም መፈተሻ ጫወታውን ያደረገው ማንችስተር ዩናይትድ በራፋ ቤኒቴዝ የሚመራው ኤቨርተንን 4ለ0 ሲያሸንፍ ጎሎቹን ግሪንውድ ፣ ሃሪ ማጓየር ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝና ዲዮጎ ዳሎት አስቆጥረዋል።
📌 አርሰናል የሊዮኑን የ23 አመት ኮከብ Houssem Aouar ለማስፈረም ከፈረንሳይ ክለብ ጋር ንግግር ጀምሯል። የሌስተሩ ማዲሰንን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ የነበሩት መድፈኞቹ የማይሳካ ከሆነ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት £25 ሚልየን የሚያወጣው የሊዮኑን ኮከብ የግላቸው ለማድረግ እየጣሩ ነው።
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
#ሲፋን_ሐሰን_ሁለተኛ_ወርቋን_አገኘች
✅ ሲፋን ሐሰን የምትገርም ነች ወርቁን በላች
✅ ለተሰንበት ግደይ ሶስተኛ ሆና የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች
📌 አንደኛ እና 2ኛ የወጡት በትውልድ ኢትዮጵያዊ ናቸው
✅ አሁን በተጠናቀቀው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች የ10000 ሜትር ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን አንደኛ ሆና የወርቅ ሜዳልያ ለኔዘርላንድ አስገኝታለች።
🥇ሲፋን ሐሰን ለኔዘርላንድ
🥈ቃልኪዳን ገዛኸኝ ለባህሬን
🥉ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ
✅ በ5000 ሜትር ወርቅ አመጣች
✅ በ10000 ሜትርም ወርቅ ደገመች
✅ 2008 ላይ ጥሩነሽ ዲባባ የሰራችውን ገድል ተጋርታለሽ
✅ አሁን ሲፋን ሐሰን ብቻዋን ሁለት የወርቅ ሜዳልያ በማምጣት በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአመራር ውዝግብ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሙሉ ቡድን የተሻለ ደረጃ አላት
👏👏👏 ሲፋን ሐሰንን አለማድነቅ አይቻልም 👏👏👏
#የአውሮፓ_የአመቱ_ምርጥ_ለመባል_3_ዕጩዎች_ታውቀዋል
🇧🇪 ኬቭን ዴብሬይን (ማንችስተር ሲቲ/ቤልጅየም)
🇫🇷 ንጎሎ ካንቴ (ቸልሲ/ፈረንሳይ)
🇮🇹 ጆርጂንሆ (ቸልሲ/ጣልያን)
#አስደናቂው_ሃላንድ
✅ ትላንት ዶርትሙንድ በጀርመን ቡንድስሊጋ የሲዝኑን የመክፈቻ ጫወታ ከፍራንክፈርት ጋር አድርጎ 5ለ2 ሲያሸንፍ አስደናቂው ወጣት ኤርሊንግ ሃላንድ 2 ጎል አስቆጥሮ 2 ለጎል አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
✅ ለዶርትሙንድ መጫወት ከጀመረ ገና 574 ቀኑ ነው
✅ በቆይታውም 61 ጫወታ አድርጎ 62 ጎል አስቆጥሯል
✅ በዚህ ሲዝን በ2 ጫወታው 5 ጎልና 3 assist አድርጓል
#ማንችስተር_ዩናይትድ_በይፋ_ራፋኤል_ቫራንን_አስተዋውቋል
✅ ፈተንሳዊው እስከ 2025 በኦልትራፎርድ ይቆያል
✅ ለዝውውሩም የማንችስተር ዩናይትድ ለ28 አመቱ የመሐል ተከላካይ እስከ £34 ሚልየን እንደሚከፍል ታውቋል።
✅ ሳምንታዉ ደሞዙ እስከ £210,000 ይሆናል ተብሏል
✅ በቆይታውም 19 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተተጋግጧል
#ማንችስተር_ዩናይትድ_ሲዝኑን_በጣፋጭ_ድል_ጀምሯል
📌 ተጠናቀቀ| ማንችስተር ዩናይትድ 5-1 ሊድስ
✅ የሲዝኑ የመጀመሪያ ሃትሪክ በፈርናንዴዝ ስም ሲመዘገብ ቀሪውን ጎሎች ግሪንውድ እና ፍሬድ ማስቆጠር ችለዋል።
✅ ሚገርመው ፖግባም 4 assist አድርጎ መውጣት ችሏል
✅ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ በመክፈቻ ጫወታ ለማንችስተር ዩናይትድ ሃትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
✅ በአንድ የፕሪምየር ሊግ ጫወታ 4 assist በማድረግም ፖል ፖግባ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኗል።
✅ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፕሪምየር ሊጉ መጫወት ከጀመረበት ፌብሯሪ 2020 ጀምሮ ከየትኛውም ተጫዋች በላይ 48 ጎሎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል (29 ጎል አስቆጥሮ 19 ለጎል አመቻችቷል )
✅ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ በአንድ ጫዋታ 4+ assist በማድረግ ፖል ፖግባ 7ኛው ተጫዋች ሆኗል
📆 1999 ዴኒስ ቤርካምፕ
📆 2006 ሆዜ አንቶኒዮ ሬይስ
📆 2008 ሴስክ ፋብሪጋስ
📆 2012 ኤማኑኤል አዴባየር
📆 2013 ሳንቲ ካዞርላ
📆 2020 ሃሪ ኬን
📆 2021 ፖል ፖግባ
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
#አርሰናል_ሲዝኑን_በሽንፈት_ጀምሯል
✅ ተጠናቀቀ| ብሬንትፎርድ 2-0 አርሰናል
✅ ብሬንትፎርዶች በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊገ ታሪክ የመጀመሪያ ጫወታቸውን አደረጉ የመጀመሪያ ድላቸውንም አሳክተዋል።
✅ 22' ሰርጂ ካኖስ እና 73' ኖርጋርድ ጎሎቹን አስቆጥረዋል
📌 አርሰናል በእንግሊዝ ዋናው ሊግ የመክፈቻ ጫወታውን አድርጎ በአዲስ አዳጊ ክለብ ሲሸነፍ ከ44 አመታት በኋላ ሆኗል።
📌 ሰርጂ ካኖስ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ የመክፈቻ ጎል ያስቆጠረ ሁለተኛው ስፔናዊ ተጫዋች መሆንም ችሏል። በ2012/13 ሲዝን ሚቹ ለስዋንሴይ እየተጫወተ QPR ላይ ማስቆጠሩ ይታወሳል።
📌 የብሬንትፎርድ ኮሚኒቲ ስታድየም በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ 60ኛው ስታድየም ሆኖ ተመዝግቧል። በሊጉ ታሪክ በርካታ ሜዳዎች ላይ በማሸነፍ ሊቨርፑል ቀዳሚ ነው (57) ፣ ማንችስተር ዩናይትድ (54) እንዲሁም አርሰናል (53)
📌 ብሬንትፎርድ አይደለም በፕሪምየር ሊጉ በእንግሊዝ ዋናው ሊግ ከተጫወተ 74 አመታት ወይም 27,110 ቀናት አልፎታል።
📌 አርሰናል በፕሪምየር ሊጉ የሲዝኑ የመጀመሪያ የመክፈቻ ጫወታ እንዲያደርግ ሲመደብ ለአራተኛ ግዜ ሲሆን ሽንፈት ያስተናገደው ግን በዚህኛው ጫወታ ብቻ ነው። 2008/09 ዌስትብሮምን ፣ 2017/18 ሌስተርን ፣ 2021/21 ፉልሃምን አሸንፎ ነበር።
📌 ብሬንትፎርድ በፕሪምየር ሊጉ ላይ መጫወት የቻለ 50ኛው ቡድን ነው። ከ50 ቡድኖች ውስጥ የመጀመሪያ ጫወታቸውን በማሸነፍ ብሬንትፎርድ 12ኛው ቡድን ነው።
📌 ብሬንትፎርድ በፕሪምየር ሊጉ ለንደንን ወክሎ የተጫወተ 10ኛው ክለብ ነው በምሽቱ ጫወታም ስምና ዝና ያለው የለንደኑ አርሰናልን አሸንፈው ጣፋጭ ምሽት አሳልፈዋል።
✅ አርብ ኦገስት 13- 2021 ለብሬንትፎርድ ደጋፊዎች ልዩ ቀን ሆኖ አልፏል
✍ Yisma Mo
✅ ኔዘርላንዳዊው የመሐል ተከላካይ ቨርጅል ቫን ዳይክ በሊቨርፑል እስከ 2025 የውድድር ዓመት ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል
@The_Beautiful_G
✅ ብሪጅ ላይ አለቃ ሆኖ ከመጣ ገና 8 ወሩ ነው
✅ በ31 ጫወታ ሁለት የአውሮፓ ክብሮችን አምጥቷል
✅ ቸልሲን በሊጉ ከ9ኛ አንስቶ ቶፕ 4 እንዲጨርስ አደረገ
✅ ኤፍኤ ካፕ ላይም ሰማያዉዎቹን እስከ ፍፃሜ አደረሳቸው
✅ በዚህ አጭር ግዜ ግን በቸልሲ ክለብ የ119 አመት ታሪኩ የሻምፒየንስ ሊግ እና የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ያሸነፈ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆኗል።
📌 በአሰልጣኝነት ዘመኑ ከስፔን ክለቦች ጋር 9 ግዜ የተገናኘ ሲሆን ተሸንፎ አያውቅም። አራት ድል አድርጎ በአምስቱ አቻ ተለያይቷል።
👏👏👏 #ቶማስ_ቱኼል 👏👏👏
#ቸልሲ_የአውሮፓ_ሱፐር_ካፕ_አሸናፊ_ሆኗል
📌ለቸልሲ ዚቺ ለቪላሪያል ደግሞ ጌራርዶ ሞሪኖ አስቆጥረው መደበኛው ደቂቃ አቻ ተጠናቆ በጭማሪው ደቂቃም የጎል ለውጥ ባለመኖሩ ወደ መለያ ምት የሄደውን ጫወታ በቸልሲ 6ለ5 በሆነ ውጤት አሸንፎ የ2021 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆኗል።
📌 የአለማችን ውዱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በምሽቱ ጫወታ 119ኛ ደቂቃ ላይ ለፔናሊቲ ተቀይሮ ገብቶ 2 መለያ ምቶችን በማዳን ታሪክ ሰርቷል።
📌 ቸልሲን መሪ ያደረገ ጎል ያስቆጠረው ሃኪም ዚች በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ታሪክ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው ሞሮኳዊ ተጫዋች ሲሆን ከጎሉ በኋላም ብዙ ሳይቆይ ተጎድቶ ወጥቷል።
📌 ቸልሲ ባለፉት 3 ተከታታይ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ያጣ ሲሆን ዛሬ ግን ተሳክቶለታል
❌ 2012 በአትሌቲኮ
❌ 2013 በባየር ሙኒክ
❌ 2019 በሊቨርፑል
✅ 2021 ቪላሪያልን
📌 ባለፉት 10 አመታት ቸልሲ በአውሮፓ መድረክ ከየትኛውም የእንግሊዝ ቡድን በተሻለ 5 ዋንጫዎችን አግኝቷል።
📌 ባለፉት ዘጠኝ አጣሚዎች ሻምፒየንስ ሊግን ያሸነፈ ቡድን በስምንቱ የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ማግኘት ችሏል።
📌 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ለ47ኛ ግዜ የተካሄደ ሲሆን 3 ግዜ ብቻ በመለያ ምት ተጠናቋል። የሚገርመው ሶስቱም ላይ ቸልሲ የተሳተፈ ሲሆን በሁለቱ ተሸንፎ ዛሬ ግን ድል ማድረግ ችሏል።
🔵🔵🔵 የቸልሲ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ🔵🔵🔵
#ሜሲን_ፓሪሶች_እንዴት_ተቀበሉት?
✅ የፒኤስጂ የኢንስታግራም ተከታዮች ከሜሲ በኋላ ከ19 ሚልየን ወደ 42 ሚልየን አድጓል
✅ ሜሲ ከፒኤስጂ በሳምንት እስከ €1,000,000 ሚልየን ሊያገኝ ይችላል
✅ ኔይማር 10 ቁጥር ሊሰጠው ፍቃደኛ ቢሆንም ሜሲ ግን አክብሮ 30 ቁጥር ማልያ ለመልበስ ተስማምቷል።
✅ የሊዮኔል ሜሲ ልዩ የፓሪስ አቀባበል በምስልና በቪዲዮ ይመልከቱ
#ይህችን_ለቅምሻ
📌ሮናልዲንሆ በ2001 ለፒኤስጂ ፈረመ በ2002 አለም ዋንጫን አነሳ
📌ሞፓፔ በ2017 ለፒኤስጂ ፈረመ በ2018 አለም ዋንጫን አነሳ
📌ሜሲ በ2021 ለፒኤስጂ ፈረመ በ2022 አለም ዋንጫን ...?
#ሊዮኔል_ሜሲና_ፒኤስጂ_ተስማሙ
✅ ለፊርማ €25 ሚልየን ከፒኤስጂ ያገኛል
✅ በአመት €35 ሚልየን የተጣራ ክፍያ ይከፈለዋል
✅ ሜሲ በፒኤስጂ ለሁለት አመት ለመጫወት የተስማማ ሲሆን የፈረንሳዩ ክለብ ከፈለገ ደግሞ አንድ ተጨማሪ አመት ለማቆየት ተሚያስችለውን ስምምነት አጠናቀዋል።
✅ ሊዮኔል ሜሲ ፊርማውን ለማኖርም ዛሬ ፓሪስ ይጓዛል
✅ ትላንት ገና ከባርሴሎና ሳይነሳ በርካታ ደጋፊዎች የፓሪስ አየር ማረፊያን አጨናንቀውት እንደነበር ይታወሳል።
✍ Yisma Mo
#ሊዮ_ልዩ
✅ ድንገት መጣህላቸው
✅ አንዱን ሻምፒየንስ ሊግ ወደ 5 ከፍ አደረክላቸው
✅ በ17 አመት ውስጥ ብቻ 34 ዋንጫ አሳየኃቸው
✅ የማድሪድን የበላይነት ገርስሰው በስፔን እና በአለም ላይ እንዲነግሱ አደረክ
✅ ባሎንዶር ያሸነፈ የመጀመሪያው የላሜሲያ ምሩቅ ሆንክላቸው
✅ 728 ጫወታ 672 ጎልና አልፍ አህላፍ ደስታ አይተውብሃል
📌 ሊዮ አንተ እኮ ባርሴሎና ከክለብም በላይ ነው ብለው በልባቸው ያተሙት የካታሎን ሕዝቦች እምነታቸውን ተፈታትነኸዋል። አው አንተን ከባርሴሎና ነጥለው አይተው የማያዉቁት የካምፕ ኑ ታዳሚያን ባርሴሎና ካንተ በላይ መሆኑን ማመን አቅቷቸዋል
✅ አሁን ሳትፈልግ አሰቃየኃቸው ምንም ማለት አይቻልም
✅ በኦሎምፒክ ታሪክ በወንዶች ማራቶን ሀገራችን 4 ወርቅ በማግኘት ከየትኛውም ሀገር በላይ በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ሶስቱ የአበበ ቢቂላ እና የማሞ ወልዴ ተከታታይ ድሎች ሲሆኑ በ2000 ገዛኸኝ አበራ ካሸነፈ በኋላ ባለፉት 20 አመታት ግን ክብራችንን ማስመለስ አቅቶናል።
🥇 1960 አበበ ቢቂላ
🥇 1964 አበበ ቢቂላ
🥇 1968 ማሞ ወልዴ
🥇 2000 ገዛኸኝ አበራ
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
#ሌስተር_ሲቲ_ዋንጫ_አገኘ
✅ የብሪንዳን ሮጀርሱ ሌስተር ሲቲ የጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲን 1ለ0 አሸንፎ የኮሚኒቱ ሺልድ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
📌 ኬሊቺ እሄናቾ በናይጄሪያ ተወልዶ በማንችስተር ሲቲ ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ለሌስተር ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልን በፔናሊቲ አስቆጥሯል።
✅ ሌስተር ሲቲ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫን ሲያገኝ ከ49 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ነው።
#LIKE እና #SHARE በማድረግ መረጃዎችን ቶሎ ማግኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/YismamoPost/
Yisma Mo
✅ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች እግር ኳስ ብራዚል ስፔንን 2ለ1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች።
✅ ዳንኤል አልቬስም 43ኛ የሻምፒዮንነት ክብሩን አግኝቷል
✍ Yisma Mo
#በቶኪዮ_አራተኛ_ሜዳልያ_አግኝተናል_እንኳን_ደስስስስ_አለን
✅ ለተሰንበት ግደይ የምትችለውን ሞክራ የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች። ወርቅ ጠብቀን ነሐስ ብናገኝም አትሌቶቻችን በውጥረት ውስጥ ሆነው ሜዳልያ ማግኘታቸው የሚበረታታ ነው።
✅ ከውድድሩ በኋላ ሀገሬ ከኔ ወርቅ ጠብቆ ነበር በሚል ስሜት እያለቀሰች ነው። ማበረታታት አለብን ይህ ስፖርት ነው
👏 እናመሰግናለን ለተሰንበት 👏