#አዲሱ_ጋርዲዮላ
✅ በ2018/19 አያክስን ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች ውስጥ አንዱ አንዲሆን አድርጎታል። በሻምፒየንስ ሊጉ ጥሎ ማለፍ ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንቱስን ከውድድሩ አስወጥቶ እስከ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችሏል።
✅ አለመታደል ሆኖ ያን ግሩም ሲዝን ከአያክስ ጋር ያሳለፉት አብዛኞቹን ተጫዋቾችን ግን በቀጣዩ አመት ታላላቅ ክለቦች ተቀራመቷቸው
✅ ይህ ሁሉ ሲሆን ሆላንዳዊው ባለ ምጡቅ አሰልጣኝ በክለቡ ነበር። እናም እንደገና በአያክስ አዲስ በወጣቶች የተዋቀረ ቡድን ገነባ
✅ ፍሬውን ይኽው እያየ ይገኛል። አው በዚህ ሲዝን በአውሮፓ 10ሩ ታላላቅ ሊጎች ውስጥ የአያክስን ያህል ጎል ያስቆጠረ የለም (37) እንዲሁም አነስተኛ ጎል የተቆጠረበት ቡድንም ነው (2)
✅ በዚህ ሲዝን በሻምፒየንስ ሊጉ ሶስቱንም ጫወታ ድል ካደረጉ አራት ክለቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን ታላላቅ ክለቦችን ከውድድሩ ማስወጣት የሚችል አቅም እንዳላቸውም እያሳዩ ይገኛል
✅ ዜግነቱ ከቶታል ፉትቦል ፈጣሪዋ ከሆላንድ ይመዘዛል .....የክራይፍ ደቀ መዝሙር በሙኒክ ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር አብሮ ሰርቷል ፣ የአያክስን ባህል ጠንቅቆ የተረዳና ባለፉት አመታት ቡድኑን ሁለት ግዜ ገንብቶ ለአለም ህዝብ ውብ እግር ኳስን ከውጤት ጋር አስመልክቷል
✅ አሁን የባርሴሎና እና የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ቡድናቸውን እንዲያሰለጥን የሚፈልጉት ዋነኛው ሰው ሆኗል።
#ኤሪክ_ቴን_ሃግ MASTERMIND 👏👏👏
#የባላቶሊ_ጣፋጭ_በቀል
✅ ትላንት ምሽት በቱርክ ሊግ ቤሽኪታሽ በሜዳው አዳና ዴሚርን አስተናግዶ እንግዳው ቡድን ባላቶሊን በ67ኛ ደቂቃ ቀይሮ እስከሚያስገባ ድረስ 3ለ1 እየተመራ ነበር ሱፐር ማርዮ ግን ከተቀያሪነት ተነስቶ 2 ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ከሽንፈት ታድጓል። የሚገርመው የቤሽኪታሽ አሰልጣኝ በአንድ ወቅት ማርዮ ባላቶሊን ጭንቅላት የለውም ሲሉ ተችተው ነበር ትላንት ምሽት ግን በገዛ ሜዳቸው ላይ ያውም ተቀይሮ ገብቶ 2 አስቆጥሮባቸው ጭንቅላቱን በማሳየት ጣፋጭ በቀል ተበቅሏቸዋል።
#ሱፐር_ማሪዮ 👏👏👏
@The_Beautiful_G
✅ በዛ ግዙፍ ሰውነቱ ያለው ፍጥነት አስገራሚ ነው። የላሜሲያ ምሩቅ ስለሆነ ተጫዋችን እየቀነሰ ለመሄድ ችግር የለበትም። ወደ ቦክስ ሲገባ አጨራረስ ላይ ያለውን ድክመት ቢያሻሽል የት በደረሰ።
✅ በዚህ ሲዝን በአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች ውስጥ ድሪብል በማድረግ የሚፎካከረው የለም። ገና በአራት ጫወታ 38 የተሳኩ የአንድ ለአንድ ግንኙነቶችን ማሸነፍ ችሏል። ከሱ ቀጥሎ የተቀመጠው እንኳን በ18 አንሶ ይከተለዋል።
🥇 38 አዳማ ትራኦሬ
🥈 20 አላን ሴንት ማክሲሚን
🥉 19 አልፎንሶ ዴቪስ
🏅 18 ኬይላን ሞፓፔ
#አዳማ_ትራኦሬ 🏃🏃🏃
Yisma Mo
@The_Beautiful_G
#የሜሲና_የሮናልዶ_ተፅዕኖ
✅ ሬምስ እና ፒኤስጂ ባደረጉት ጫወታ 10.5 ሚልየን ተመልካች በቲቪ የተከታተለው ሲሆን በፍሬንች ሊግ ታሪክ ሪከርድ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ግዜ ለፓሪሱ ክለብ መጫወቱን ተከትሎ ነው።
✅ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ሮናልዶን ማስፈረሙን አስመልክቶ የለጠፈው ምስል በኢንስታግራም ታሪክ ከፍተኛ Like ያገኘ ስፖርታዊ ፖስት የለጠፈ ቡድን ሆኗል (12,940,956)
Yisma Mo
@The_Beautiful_G
#ልዩነት
📌 ሮሜሎ ሉካኩ ከአመታት በፊት ከ13 አመት በታች ውድድር ላይ እንዲህ ሆኖ ይጫወት ነበር ብለን እንመን? ተከላካዮቹ አሰዘኑኝ።
#ፕሮፌሰሩ_ተናፍቀዋል
✅ እሳቸው በ22 አመት የአርሰናል ቆይታቸው እኮ በሲዝኑ የመክፈቻ 2 ተከታታይ ጫወታ ሽንፈት አስተናግደው አያውቁም ነበር
✅ በእሳቸው የ22 አመት የአርሰናል ቆይታ በሲዝኑ የመክፈቻ 2 ተከታታይ ጫወታ ላይ ጎል ማስቆጠር የተሳነው ቡድን አልገነቡም ነበር።
✅ ለሚኬል አርቴታ በፕሪምየር ሊጉ የትላንቱ በ6 ወሩ 20ኛ ሽንፈቱ ሆኗል። አርሰን ዌንገር ግን በመጨረሻዎቹ 6 አመት ነበር 20 ሽንፈት ያስተናገዱት
✅ አሁን የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ከምንግዜውም በላይ አስቸጋሪ ግዜን እያሳለፉ ነው።
❌ 2-0 በብሬንትፎርድ ተሸነፉ
❌ 2-0 በቸልሲ ተሸነፉ
⏳ ቀጣይ ቅዳሜ ደግሞ ቀን 08:30 ላይ ማንችስተር ሲቲን ከሜዳቸው ውጪ ይፋለማሉ።
#አስቀያሚ_ገፅታ_በፍሬንች_ሊግ
📌 ትላንት ምሽት ኒስ ኦሎምፒክ ማርሴይን 1ለ0 እየመራ ነበር። ዝነኛው የማርሴይ አማካይ ዴሚትሪ ፖየት የማዕዘን ምት ለመምታት እየተዘጋጀ እያለ ፅንፈኛ የኒስ ደጋፊዎች ፕላስቲክ ጠርሙስ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ወረወሩበት በሁኔታው የተናደደው ፖየትም ወደ ደጋፊዎቹ መልሶ ወረወረ። ከዛስ?
📌 ከዛማ ተወረወረብን ያሉ የኒስ ደጋፊዎች ጥበቃዎችን ጥሰው ሜዳውን አጥለቀለቁት። አንድ ደጋፊ ፖየትን ከጀርባው ሊረግጠው ሲሞክር ታይቷል። የማርሴይ የአሰልጣኞች አባል አንዱን ደጋፊ ቦክስ አቀመሰው። አንዱ አሳዳጅ ሌላው ተሳዳጅ በቃ ድብልቅልቁ ወጣና ጫወታው ተቋረጠ።
@The_Beautiful_G
🔵 ለንደን ሰማያዊ መሆን የጀመረችው ሮማን ኢብራሂሞቪች ብሪጅ ከደረሱ በኋላ ነው አይደል?
ተጠናቀቀ| አርሰናል 0-2 ቹልሲ
✅ 15' ሉካኩ ቸልሲን መሪ አደረገ ሬስ ጀምስ assist
✅ 35' ሬስ ጀምስ ለቸልሲ ሁለተኛ ጎል አስቆጠረ
✅ የለንደን ደርቢም በቸልሲ የበላይነት ተጠናቀቀ
✅ ቱኼል እና ልጆቹ በሲዝኑ የመክፈቻ ሁለት ተከታታይ የፕሪምየር ሊግ ጫወታ ግብ ሳይቆጠርባቸው ድል ማድረግ ችለዋል።
✅ ሉካኩ 114ኛ የፕሪምየር ሊግ ጎሉን በማስቆጠር በሊጉ 20ኛው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆን ሲችል በፕሪምየር ሊጉ አንግሊዛኢ ተጫዋች ሳይሆን በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ 50+ ጎል በማስቆጠር 8ኛው ተጫዋች ሆኗል።
✅ ሬስ ጀምስ በአርሰናል ሜዳ በፕሪምየር ሊጉ ጎል እና Assist በማድረግ ከሁዋን ማታ ቀጥሎ ሁለተኛው የቸልሲ ተጫዋች ሆኗል።
✅ በነገራችን ላይ ምስጋና ለጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኼል ይሁንና ቸልሲ በፕሪምየር ሊጉ የሲዝኑ ሁለት የመክፈቻ ጫወታዎችን ድል ሲያደርግ ከ10 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ነው።
@The_Beautiful_G
✅ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ሲጋራ ቶተንሃም ከሜዳው ውጪ በዴል አሊ ብቸኛ ጎል ወልቭስን አሸንፎ ወጥቷል
🤝 ተጠናቀቀ| ሳውዝሃምፕተን 1-1 ማንችስተር_ዩናይትድ
✅ ተጠናቀቀ| ወልቭስ 0-1 ቶተንሃም
🔴 ዛሬ ማንችስተር ዩናይትድን አቻ ያደረገ ጎል ያስቆጠረው ማሰን ግሪንውድ በፕሪምየር ሊጉ 19ኛ ጎሉ ሲሆን ዕድሜው 20 ሳይሞላ ብዙ ጎል በማስቆጠር 4ኛው ተጫዋች ሆኗል
40 ማይክል ኦዌን
35 ሮቢ ፎውለር
30 ዋይኒ ሮኒ
@The_Beautiful_G
#የሌስተር_ሲቲ_የአስር_አመት_ስኬት_አጭር_የሕይወት_ታሪክ
📆 2010 Vichai ሌስተር ሲቲን £39.ሚልየን ብቻ አውጥተው ገዙት
📆 2014: ሌስተር ሲቲ በሻምፒየን ሺፑ አንደኛ ሆኖ በመጨረስ ወደ ፕሪምየር ሊጉ አደገ
📆 2014: ወደ ሊጉ አንዳደጉ ባለሀብቱ Vichai " በ3 አመት ውስጥ የሊጉ ምርጥ 5 ቡድኖች ውስጥ መቀመጥ አንፈልጋለን " አሉ
📆 2016: ፕሪምየር ሊጉ ሲጀመር አቋማሪዎች 5000/1 ግምት የሰጡት ሌስተር ሲቲ ሻምፒዮን ሆኖ አለምን ግርምት ውስጥ ከተተ
📆 2017: በመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፏቸውም ሩብ ፍፃሜን ተቀላቀሉ
📆 2018 ራዕይ ይዞ እንግሊዝ ከትሞ በሌስተር ስኬታማ የሆነው የኪንግ ፓዎር ግሩብ መስራችና የሌስተር ሲቲ ክለብ ባለሀብት Vichai ዝነኛ በሆኑበት የሌስተር ሲቲው ኪንግ ፓወር ስታድየም ተነስተው ጉዞ በማድረግ ላይ እያሉ በ200 ሜትር ርቀት ላይ ሄሊኮፕተሩ አደጋ ደርሶበት ሕይወታቸው አለፈ
📆 2020: ሕይወት ከባለሀብቱ ቤተተብ ጋር የቀጠለው ሌስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ 2ኛ ምርጥ ደረጃቸውን 5ኛ ሆነው በማጠናቀቅ የአውሮፓ ተሳትፏቸውን አረጋገጡ
📆 2020: ባለሀብቶቹ £100 ሚልየን አውጥተው የሌስተር የልምምድ ማዕከልን በአዲስ መልክ አዋቀሩት
📆 2021: ሌስተር ሲቲዎች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አገኙ
📆 2021: በሊጉ 5ኛ ሆነው በማጠናቀቅ ለመጀመሪያ ግዜ ለተከታታይ ሁለት ሲዝን ቶፕ 6 ውስጥ ጨረሱ
📆 2021: የጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ ከ50 አመት በኋላ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫን አገኙ
📆 2021: አሁን ብሪንዳን ሮጀርስ በጄሚ ቫርዲ ስር ያዋቀሩት የቡድን ስብስብ ዋጋው £510 ሚልየን በመድረስ በክለቡ ታሪክ ሪከርድ ሆኗል
📆 2021 ይባስ ብለው የሟቹ ባለሀብት ቤተሰቦች የኮቪድ ተፅዕኖ የክለቦች ገቢን ባዳከመበት በዚህ ግዜ ኪንግ ፓወር ስታድየምን ወደ 40,000 መቀመጫዎች የማሳደግ ፕሮጀክትን ይፋ አድርገዋል
#ይህ_የሌስተር_ሲቲ_የአስር_አመት_የስኬት_ጉዞ_ይህ_ነው
@The_Beautiful_G
✅ ቨርጅል ቫንዳይክ ለሊቨርፑል መጫወት ከጀመረ በኋላ በፕሪምየር ሊጉ አንፊልድ ላይ ተሸንፎ አያውቅም።
🏟 48 ጫወታ
💪 43 አሸነፈ
🤝 5 አቻ
🥅 23 ጫወታ ላይ ጎል አላስተናገደም
⚽ 7 ጎል በስሙ አስቆጥሯል
📈 89.6% የማሸነፍ ስኬት አለው
#SUPER_VAN_DIJK
💚💛❤️ በቃ ሀበሻ ጓዙን ጠቅልል የአያክስ ደጋፊ ሊሆን ነው። ዕድሜ ለቦብ ማርሌ ''Three Little Birds'' በተሰኘው ዜዋው ኢትዮጵያን ፣ ጃማይካን እና አያክስን አስተሳሰረ። 💚💛❤️
Читать полностью…#ዕድለኛው_ጫማ
✅ ለቡድኑ አምበል ነው ግዜው በ2019 ሲሆን የ23 አመቱ አማካይ በሻምፒየን ሺፑ በሚሳተፈው አስቶን ቪላ ጉዳት ላይ ከከረመ በኋላ ሲመለስ £240 የተገዛ አዲስ የናይክ ጫማ አጥልቆ በመጫወት 2 ጎል አስቆጥሮ 2 ለጎል አመቻችቶ ሚገርም ብቃት አሳየ።
✅ በቀጣዩ ጫወታም በዚሁ ጫማ በርሚንግሃም ደርቢ ላይ የማሸነፊያ ጎል አስቆጠረበት። ከዛ በኋላ ለዚህ ጫማ ያለው ክብር ከፍ አለና " ድል አምጪው ጫማ " ብሎ አልቀይርም አለ
✅ የሚገርመው ቡድኑን በምበልነት እየመራ በዚሁ ጫማ እየተጫወተ ለ9 ተከታታይ ጫወታ አስቶን ቪላን ለድል አብቅቷል።
✅ በዚህ ጫማ ለ 1,140 ደቂቃዎች በእያንዳንዱ የአስቶን ቪላ ጫወታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቶበታል። በዛን ግዜ ከ13 ተከታታይ ጫወታ 11 አሸንፎ 2 አቻ ወጥቷል።
✅ ጫማው ቆዳው ተልጦ እግሩ በጨርቅ ውስጥ እስኪታይ ድረስ ተጫውቶበታል። ስለሁኔታው የስካይ ስፖርት ጋዜጠኛ ተገርሞ ላቀረበለት ጥያቄም ይህን ብሏል
" ከጉዳት ስመለስ ይህ ጥንድ ጫማ አዲስ ነበር። ሁለት ግቦችን እና 2 assist አደረኩ እና እነዚ ዕድለኛ ጫማዎቼ ስለሆኑ እነሱን መጠበቅ ነበረብኝ "
✅ ይህ ዕድለኛ ጫማ በመጨረሻም ደርቢ ካውንቲን 2ለ1 አሸንፈው ከሻምፒየን ሺፕ አውጥቶ ወደ ፕሪምየር ሊግ አሳደጋቸው
✅ የታሪኩ ባለቤት አሁን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ታሪክ ውዱ ተጫዋች ሆኖ £100 ሚልየን የወጣበት የማንችስተር ሲቲው አማካይ #ጃክ_ግሪሊሽ ነው።
✍ Yisma Mo
@The_Beautiful_G
#ባሎንዶር_ለምን_ጥቁሮችን_ያገላል ሊቨርፑላዊው ይናገራል
" አፍሪካዊ ተጫዋቾች ማሸነፍ የነበረባቸው ብዙ የባሎንዶር ሽልማቶች ነበሩ ግን አልተሸለሙም። የማትስማሙ ከሆነ እስኪ በአንድ የፕሪሚየር ሊግ 20+ ግቦችን ያስቆጠረ እና ሊጉን ያሸነፈ አፍሪካዊ ተጫዋች እንደነበረ ላስታውሳችሁ። እንዲሁም ቢያንስ አንድ አፍሪካዊ ተጫዋች በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ያልደረሰበትን እስኪ አስታውሱ።
የዓለም ዋንጫን ስለማሸነፍ የሚነሳ ከሆነ ይህ ማለት ባሎንዶር በየዓመቱ ማለት ይቻላል በስህተት ይሸልማል ማለት ነው ፣ ምክንያቱም የዚህ ሽልማት አብዛኛዎቹ አሸናፊዎች የዓለም ዋንጫ የላቸውም"
🗣 ሞሐመድ ሳላህ
ምን ትላላችሁ?
✅ በባሎንዶር ሽልማት የ64 አመት ታሪክ ውስጥ አፍሪካዊ የተሸለመው አንድ ግዜ ሲሆን በ1995 ጆርጅ ዊሃ ነበር።
@The_Beautiful_G
#የሞሪንሆ_ለድሮግባ_ያላቸው_ጥልቅ_ፍቅር
🗣 " በማርሴይ እያለ በሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በአምስተኛው ደቂቃ ዲዲየር ድሮግባ ወደ ሕይወቴ ገባ። 11 ቁጥር ማልያ የለበሰው ግዙፍ ሰውም ሜዳችን ላይ ቀድሞ ጎል ሲያስቆጥር ቁጭ ብዬ ተመለከትኩ።
“በእረፍት ሰዓት በኮሪደር ውስጥ አገኘሁት እና ' እንተን መግዛት የሚያስችል ገንዘብ የለኝም ፣ በኮትዲቯር እንደ አንተ መጫወት የሚችሉ የአጎት ልጆች የሉህም? " አልኩት እሱ ሳቀ አቅፎኝም ' አንድ ቀን እኔን ሊገዛኝ በሚችል ክለብ ውስጥ ትሆናለህ ' አለኝ
ከስድስት ወር በኋላ ነገሮች ተለወጡ ቡድኔ ፖርቶ የሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ሲሆን እኔም ለቼልሲ ፈረምኩ። አሁን ሁሉም ሊደራደርበት ፣ ሁሉም ስሙ እንዲገኛን የሚፈልግበት እና ሁሉም ለመጫወት የሚፈልግበት እጅግ በጣም ተፈላጊ ክበብ ውስጥ ነኝ
እናም እኔ ብዙ አማራጮች ቢኖሩኝም ግን እንደ ደረስኩ “ዲዲየር ድሮግባን እፈልጋለሁ” አልኩ። ጥርጣሬዎች እና ጥያቄዎች ከጥቂት ሰዎች ተነሱ
ለምን እሱን?
እንደሱ ዓይነት ለምን?
እሱ በእውነት ጥሩ ነው?
እርግጠኛ ነህ ቡድኑን ተላምዶ ከፍ ያደርገዋል?
በቃ እኔ ዲዲየር ድሮግባን እፈልጋለሁ አልኩ። ጥቂት ቀናት አለፉ እና በለንደን የግል አውሮፕላን ማረፊያ ከዲዲየር ጋር ተገናኘሁ። እንደገና አቀፈኝ ፣ በዚህ ጊዜ ግን በማይረሳ መንገድ የዚህን ሰው አመስጋኝነት ያሳየ እቅፍ ነበር ፣ እና ለእሱ ትልቅ ትርጉም ላላቸው ሰዎች የሚሰማውን ፍቅር አሳየኝ " ሊገለጽ የማይችል ነበር።
በመጨረሻም ሞሪንሆ እና ድሮግባ ቸልሲን ከ50 አመት በኋላ ለእንግሊዝ ሊግ አሸናፊነት አብቅተው አለም ላይ አነገሱት።
✍ Yisma Mo
@The_Beautiful_G
✅ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሰልጥኖ አብቅቶ ከሸጣቸው ተጫዋቾች €1,000,000,000 (አንድ ቢልየን) ገቢ ያመጣ ብቸኛ አሰልጣኝ ነው
✅ በአነስተኛ የቡድን ስብስብ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ባሉበት ሊግ ሁለት ግዜ የላሊጋ ዋንጫን የነጠቃቸው ድንቅ አሰልጣኝ ነው
✅ አትሌቲኮን ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ያደረሰ ብቸኛ አሰልጣኝ ነው። አስገራሚውን የክሎፕ ሊቨርፑልን በደርሶ መልስ አሸንፎ ከውድድሩ ያሰናበተበት መንገድም አይረሳም።
✅ አትሌቲኮ ማድሪድም ውለታውን ችላ አላለም ለክብሩ ሲባል የአለማችን ውድ ተከፋይ አሰልጣኝ አድርጎታል።
✅ ዛሬ ምሽትም የላሊጋው ሻምፒዮን በመሆኑ ሊቨርፑል ባለበት ምድብ ውስጥ አባት ኖኖ የሻምፒየንስ ሊግ ሲዝኑን ይጀምራል
🙏 RESPECT #ዲያጎ_ሲሞኒ
👏👏👏
Yisma Mo
@The_Beautiful_G
#ሮናልዶን_ለማየት_ለአንድ_ትኬት £2000 ???
✅ በማንችስተር ዩናይትድ በመደበኛው አመታዊ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ትኬት ለመግዛት የሚጠየቀው £532 መሆኑን ያውቃሉ?
✅ ከዘጠኝ ቀን በኋላ በኦልትራፎርድ ኒውካስትልን በሚጋብዘው ማንችስተር ዩናይትድ ቡድን ውስጥ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲጫወት ለማየት የጓጉ ደጋፊዎች በኦንላይን የትኬት መሸጫ ለአንድ ትኬት እስከ £2000 እየተጠየቁ ነው
✅ 207 ትኬቶች ለሽያጭ ቀርበው ከዝቅተኛ መነሻ ዋጋ £377 ጀምሮ እስከ £2000 ድረስ ዋጋ ተለጥፎባቸዋል።
✅ ለዚህ ጫወታ ብቻ በዝቅተኛ መነሻ ዋጋ ለአንድ ወንበር £377 የሚያስከፍል ሲሆን SIR ALEX FERGUSON STAND 1ST TIER ደግሞ ከአመታዊ ክፍያ በሚቀራረብ መልኩ £513 ያስከፍላል።
✅ ለዚህ ጫወታ ብቻ ለአንድ ትኬት ከፍተኛ ዋጋ የተጠየቀው MANCHESTER EXECUTIVE SUITE በሚባለው ቦታ ለፈለጉ ተመልካቾች £2,000 መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
Yisma Mo
@The_Beautiful_G @The_Beautiful_G
#ሳዲዮ_ማኔን_ለሴኔጋል_ፕሬዝዳንት?
📌 ወቅታዊው የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ሳዲዮ ማኔ ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ሲገለል የሴኔጋል ፕሬዝዳንት እንዲሆን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
📌 የእሱ ተወዳጅነት እና ልግስና በሀገራችን መሠረተ ልማት ላይ ፋይናንስ ለማድረግ ብዙ ባለሀብቶችን ያመጣል ብለው ያምናሉ
🗣 “ እሱ የወደፊቱ ተስፋችን ነው ፣ የዓለም ባለሀብቶች እምነት እንዲጥሉብን ያደርጋል ፣ ምክንያቱም ዓለም እርሱን እና መልካም ሥራዎቹን ስለሚያውቅ "
@The_Beautiful_G
#የእንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ_ከሁለተኛ_ሳምንት_በኋላ
✅ ከእንቅልፌ ስነቃ ዌስትሃም ድንገት የሊጉ መሪ ሆኖ አገኘሁት። የሞይስ ቡድን በጎዶሎ የተጫወተው ሌስተርን 4ለ1 አሸንፏል
✅ በሶስተኛ ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ 2 ተጠባቂ ጫወታ ይደረጋል ቀን 08:30 ላይ የጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ አርሰናልን ይጋብዛል
✅ ምሽት 01:30 ላይ ደግሞ አጀማመራቸውን ያሳመሩት የክሎፑ ሊቨርፑል እና የቱኼሉ ቸልሲ በአንፊልድ ይፋለማሉ
✅ 5 ቡድኖች ሁለቱንም ጫወታቸውን ሲያሸንፉ 5 ቡድኖች ደግሞ ሁለቱንም ጫወታ ተሸንፈዋል
✅ አርሰናል ፣ ክሪስታል ፓላስ ፣ ወልቭስ እና ኖርዊች እስካሁን ጎል አላስቆጠሩም። ቸልሲ ፣ ሊቨርፑል ፣ ቶተንሃም እና ብሬንትፎርድ ደግሞ ጎል አልተቆጠረባቸውም
✅ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና የዌስትሃሙ አንቶኒዮ በ3 ጎል ፖግባም በ5 assist ይመራሉ
✅ ከሁለተኛ ሳምንት በኋላ ያለው የደረጃ ሰንጠረዥ እና የሶስተኛ ሳምንት ሙሉ ጫወታዎች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአንድ ምስል ይኸው
Yisma Mo
───────────────────────────
#እግር_ኳስ_The_Bautiful_Game በልዩነት በጥራት
───────────────────────────
@The_Beautiful_G
#ሰውየው_ጆሴ_ነው
📌 በጣልያን ሴሪያ ታሪክ 50 ጫወታ ለማሸነፍ አነስተኛ ጫወታ የፈጀባቸው አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ ሆነዋል (77 ጫወታ)
📌 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም ሪከርዱ የጆሴ ነው (63 ጫወታ)
📌 በስፓኒሽ ላሊጋም ሪከርዱ የጆሴ ነው (62 ጫወታ)
📌 ትላንት ምሽት ጆሴ ሞሪንሆ በአዲሱ ክለባቸው ሮማ የሲዝኑ የመጀመሪያ የሴሪያ ጫወታ ፊዮረንቲናን ጋብዘው 3ለ1 ድል አድርገዋል
@The_Beautiful_G
✅ 60' ሮናልዶ ተቀይሮ ሲገባ ጁቬ በዲባላና ኳድራዶ ጎሎች 2ለ1 ይመራ ነበር
✅ 83' ዴሎፍ ለዩድኔዜ አስቆጠረና 2 አቻ ሆኑ
✅ 90+4' ሮናልዶ ጎል አስቆጥሮ ማልያውን አውጥቶ ጨፈረ
✅ 90+5' ዳኛው ማልያውን በማውለቁ ለሮናልዶ ቢጫ አሳዩት
✅ 90+7' ቫርም ጨክኖ ከጫወታ ውጪ ብሎ ጎሉን ሻረው
🤝 የጁቬንቱስ እና የሮናልዶ የሲዝኑ የመጀመሪያ የሴሪያ ጫወታም በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
@The_Beautiful_G
✅ ቸልሲ እና ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉ መሪነት ላይ ተቀምጠዋል
✅ ሁለቱም እኩል 2 ጫወታ አሸንፈው ፣ 5 ጎል አስቆጥረው ፣ ግብ ሳያስተናግዱ የሊጉ አናት ላይ ይገኛሉ
✅ አርሰናል ሁለቱንም ጫወታ ተሸንፎ 19ኛ ላይ ተቀምጧል
✅ ማንችስተር ዩናይትድ 5 ማንችስተር ሲቲም 8ኛ ላይ ይገኛሉ
✅ የቀድሞ ክለባቸውን ያሸነፉት ኑኖ ቶተንሃምን ለተከታታይ ድል አብቅተው 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
✅ ብራይተኖች ሁለቱንም ጫአታቸእን አሸንፈው 3ኛ ናቸው
@The_Beautiful_G
#ሉካኩ_ይመቸው
✅ለዌስትብሮም በመጀመሪያ ጫወታው ጎል አስቆጠረ
✅ለኤቨርተን በመጀመሪያ ጫወታው ጎል አስቆጠረ
✅ለማን ዩናይትድ በመጀመሪያ ጫወታው ጎል አስቆጠረ
✅ለኢንተር በመጀመሪያ ጫወታው ጎል አስቆጠረ
✅ይኸው ዛሬ ደግሞ እንደገና ወደ ቸልሲ ከተመለሰ በኋላ በመጀመሪያ ጫወታው ጎል አስቆጠረ
✍ Yisma Mo
@The_Beautiful_G
#ይህን_ያውቃሉ?
🔴 ፖል ፖግባ በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ በሲዝኑ የመጀመሪያዎቹ 2 ጫወታ 5 ጎል የሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
🆚 4 ሊድስ ላይ
🆚 1 ሳውዝሃምፕተን ላይ
✅ የሚገርመው ባለፉት 2 ሲዝኖች በድምሩ ለጎል ያመቻቸው 6 ብቻ ነበር።
✅ አሁን በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ 34 ጎል የሆኑ ኳሶችን በማመቻቸት ከቀድሞው የመድፈኞቹ አማካይ ፓትሪክ ቬራ ጋር መስተካከል ችሏል።
@The_Beautiful_G
#እናት_አለም
“ ትንሽ ገንዘብ ነበር የምናገኘው። ከዚያ አንድ ቀን ሞይስ ጠዋት ላይ ደውሎ እንዲህ አለ 'እናቴ አንድ ዜና አለኝ ' ከዛ እኔም ለጁቬ መፈረም አልተሳካልህም? አልኩት። እሱ ግን እንዲህ አለኝ ' እማዬ አደረኩት እናም ከዛሬ ጀምሮ ሥራሽን ትተሽ ነይ ከእኔ ጋር በቱሪን እንኖራለን ' "
🗣 የሞይስ ኬን እናት
@The_Beautiful_G
#የተጠናቀቁ_የፕሪምየር_ሊግ_ጫወታዎች
✅ የጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ኖርዊችን በሰፊ ጎል አሸንፏል
✅ የቤልሳው ሊድስ በሜዳው ሁለት ግዜ በኤቨርተን ከመመራት ተነስቶ አቻ ወጥቷል።
✅ ባለሜዳው አስቶን ቪላ ኒውካስትል ላይ ድል ተቀዳጅቷል
✅ የፓላስ እና ብሬንትፎርድ ጫወታ ደግሞ ያለ ጎል ተጠናቋል
📌 ማንችስተር ሲቲ ሜዳው ላይ ኖርዊችን በጋበዘበት ያለፉት 4 ጫወታው 19 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
☑️ 7-0 (ኖቬምበር 2013)
☑️ 2-1 (ኦክቶበር 2015)
☑️ 5-0 (ጁላይ 2020)
☑️ 5-0 (ዛሬ ጁላይ 2021)
Special One እኮ አይናገር
" የእኔ ፍልስፍና በጭራሽ አይለወጥም። የመሀል ተከላካዮቼ ከየትኛውም ቦታ ሊመጡ ይችላሉ አማካዮቼም እንደዛው። ነገር ግን ዋናው አጥቂዬ አፍሪካዊ የዘር ግንድ ሊኖረው ይገባል ፣ ያ ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ዕድለኛ ያደርገኛል። ለዚህ ነው ወጣቱ ታሚ አብርሃም እንዲቀላቀለኝ የገፋፋሁት። ካስታወሳችሁ በማንችስተር ዩናይትድ ራሽፎርድ በእኔ ስር ገና በለጋ ዕድሜው ወርልድ ክላስ ተጫዋች ነበር እናም ኢውሮፓ ሊግ እና ሌሎች ዋንጫዎችን አሸንፈናል። እኔ ስወጣ እሱ ከኦሌጉናር ሶልሻየር ጋር አዲስ ትምህርቶችን አገኘ ይህም ትንሽ ዝቅ እንዲል አድርጎታል ፣ ይህን ማየት በእውነቱ ያማል "
🗣 አዲሱ የሮማ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ
✅ በ2003/04 ጆሴ በፖርቶ ሲነግሱ በ20 ጎል የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የነበረው ደቡብ አፍሪካዊው ቤኒ ማካርቲ ነው
✅ ጆሴ ወደ ቸልሲ እንደመጡም ሮናልዲንሆ ይምጣልህ ሲባሉ አፍሪካዊው ዲድየር ድሮግባን መረጡና አኮራቸው
✅ ወደ ኢንተር ተጉዘውም ከባርሴሎና የተገፋው ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኤቶን ተጠቅመው ሻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ የሶስትዮሽ ዋንጫ አሳክተዋል
✅ ከላይ እንዳሉት ደግሞ ራሽፎርድን ይዘው ኢውሮፓ ሊግን አሸንፈዋል።
✅ የ22 አመቱ ኖርዌያዊ ማረፊያው ኤምሬትስ ሆኗል
✅ አርሰናል ለዝውውሩ £30 ሚልየን ለሪያል ማድሪድ ከፍሏል
✅ በአራት አመት ኮንትራት እስከ 2025 ይቆያል
✅ 8 ቁጥር ማልያም ተሰጥቶታል
@The_Beautiful_G
#የእንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ_የሁለተኛ_ሳምንት_ጫወታዎች
📅 #ቅዳሜ ነሐሴ 15-2013
⏰ 08:30
ሊቨርፑል 🆚 በርንሌይ
⏰ 11:00
አስቶን ቪላ 🆚 ኒውካስትል
⏰ 11:00
ክሪስታል ፓላስ 🆚 ብሬንትፎርድ
⏰ 11:00
ሊድስ ዩናይትድ 🆚 ኤቨርተን
⏰ 11:00
ማንችስተር ሲቲ 🆚 ኖርዊች
⏰ 01:30
ብራይተን 🆚 ዋትፎርድ
📅 #እሑድ ነሐሴ 16-2013
⏰ 10:00
ሳውዝሃምፕተን 🆚 ማን.ዩናይትድ
⏰ 10:00
ወልቭስ 🆚 ቶተንሃም
⏰ 12:30
አርሰናል 🆚 ቼልሲ
📅 #ሰኞ ነሐሴ 17-2013
⏰ 04:00
ዌስትሃም 🆚 ሌስተር ሲቲ
@The_Beautiful_G