thedayofpentecost | Unsorted

Telegram-канал thedayofpentecost - አዶናይ

3069

ኢየሱስ ዛሬም በፍፁም ፍቅሩ ይወዳቿል

Subscribe to a channel

አዶናይ

ታውቃላቹ አይደል እስከ አሁን በጌታ ቤት የቆየነው ጥሩ የፀሎት ህይወት ስላለን አይደለም ... ቸርች መሄድ ስላበዛንም አይደለም... ወይ ደግሞ ከጥሩ ክርስቲያን ቤተሰብም ስለተወለድንም አይደለም ግን እንዲሁ በብዙ ምህረቱ ዛሬም በቤቱ አለን... መንፈሳዊ ህይወቴ ሲደክም ከቤቱ ያሶጣ ይሆን ብዬ በፍፁም አልሰጋም እስከ ዛሬም በቤቱ የቆየሁት በእኔ ጥርትና ትጋት ሳይሆን በእርሱ ፍቅር እንደሆነ አውቀዋለሁ 😭

Читать полностью…

አዶናይ

እገረማለሁ ዝም ብዬ

እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ እኛ በልጁ በኩል ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል...ይሄ እውነት ሌሎቹን ግራ ያጋባል እኛን ግን ያስገርመናል

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ስለ አጉል ፍቅር...ሳምሶንን ጠየቁት ☺️

ስለ አጉል ፍቅር መዘዝ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ከሳምሶን በላይ ሊያስተምረን የሚችል ሰው ማግኘት ይከብዳል.... ሳምሶን የእግዚአብሔርን ክብር የተሸከመ ትልቅ የእግዚአብሔር ሰው እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን በአንዲት ደሊላ በምትባል ሴት ልቡ ተይዞ ያንን ትልቅ ክብር ከላው ላይ አሶስዷል ፤ በዚህም ዘመንም ልክ ሳምሶን ብዙዎቻቹ በ Relationship ጉዳይ ላይ ማንን ወደ ህይወታቹ ማስገባት እንዳለባቹ አታውቁም ለዚህም ይመስለኛል ብዙ ነገሮቻቹን የምታጡበት..... እናንተ የያዛቹትን ለማስለቀቅ የእናንተን ቀልብ የሚስቡ ወንድና ሴት ልጆችን ማምጣት ለሰይጣን በጣም ቀላል እንደሆነ እወቁ፤ ትናንት ላይ ሳምሶን አጥፍቶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ትልቅ ትምህርት ትቶልን አልፎል እናንተ ግን ዛሬ ላይ የሳምሶንን ህይወት መድገም የለባቹም... ማሰብ ባለባቹ ጉዳይ ላይ ቆም ብላቹ አስቡ ካለዚያ በዚህ ዘመን ደሊላዎች የከበረውን ነገራቹን ታጣላቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ቆይ እስቲ ልጠይቃቹ ?

በቀን ሶስት ጊዜ ከምትበሉት ምግብ ጋር ቀጠሮ የምትይዙት የእውነት ምግብ ለሰውነታቹ ጠቃሚ እንደሆነ ግብቷቹ ነው ወይስ ርሀቡ አስገድዷቹ ? በርግጠኝነት ርሀቡ እንደሚሆን ገምታለው......

መንፈስም አለምም እንዲሁ ነው... ውስጣቹ መንፈሳዊ ርሀብ ከሌለ ምንም ያህል ፀሎት ጠቃሚ እንደሆነ ብታውቁም ተግታቹ ለመፀለይ ግን አቅም አይኖራቹም፤ በቀን ሶስቴ ምግብና እናንተን የሚያናኛቹ የስጋቹ ርሀብ ነው ልክ እንዲሁ ደግሞ በየቀኑ በጌታ ፊት እንድቶኑ የሚያደርጋቹም በውስጣቹ የገባው መንፈሳዊ ርሀብ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኦኦኦ አምልኮ 😭

እቆያለሁ ፀሎቴ ጋር እቆያለሁ ክብርህ ውስጥ እቆያለሁ አንተ ያለህበት..... ፍሰሱ በዚህ ድንቅ አምልኮ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የመርከብ አሻራ ተመራማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ በማድረግ በጥናት ፈልገው ያገኙት የኖህ መርከብ አሻራ ነው፤ የሚገርመው ደግሞ የመርከቡ አሻራ የተገኘውም መጽሐፍ ቅዱስ መርከቧ አረፈችበት ባለበት በአራራት ተራራ ላይ መሆኑ ነው፤ የእኛ አምላክ እንዲሁ በእምነት ለሚያምኑ ብቻ ሳይሆን አንደ ቶማስ ካላየው አላምንም ለሚሉትም መልስ አለው☺️

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ትክክለኛ ዋጋቹን ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ ለናንተ ሲል ገና ከጅምሩ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ በጣም ዝቅ ብሎ ሰው ለመሆን የወሰነውን፤ በጌተሰማኔም በጭንቀት ብዛት የደም ላብ ያላበውን፤ የሁሉም የበላይ ሆኖ እንደ ወንጀለኛ በጥፊ የተመታውን ፣ በቀራኒዮም መስቀል ላይ ጎኑን የተወጋውን ኢየሱስ ጠይቁት

የትንሳኤን በዓል ስታከብሩ በዛውም ምን ያህል ውድ እንደሆናቹ አስተውሉ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የመዝሙር ግብዣዬ 😍

🎧 የቅርቤ ነህ

🎙️ Bereket Tesfaye

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ለምን ሲባል🤨

አንድ ጊዜ ሰይጣን ለምን አለምን አትመስልም፤ ለምን ሰው እንደሚሆነው አትሆንም ብሎ እኔን ለማታለል ቃጣው እኔ "ለምን ሲባል" ብዬ ዝም አሰኘሁት፤ የእውነት ግን ለምን ሲባል ነው ፀሎት የማቆመው ማንን ደስ ይበለው ብዬ ነው ውዱን ህብረቴን የማቋርጠው፤ ሰይጣንን በተግባራቹ ማናደድ መልመድ አለባቹ፤ አትፀልዩ ሲላቹ ተነስታቹ መፀለይ፣ ቃል አንዳብቡ ሲላቹ መጽሐፍ ቅዱሳቹን ገልጣቹ ማንበብ ከዛም ይህን ስደጋግሙበት አጅሬው አርፎ ይቀመጣልነፍሳቹ ፀሎት አስለምዷት ነፍሳቹን ዝማሬ አስለምዷት ነፍሳቹን ከኢየሱስ ጋር መዋል አስለምዷት፤ ከዛም ቀስ በቀስ ነፍሳቹ ራሷ ፀሎት... ፀሎት ...ቃል ...ቃል ማለቷን ትጀምራለች።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ጌታን ማገልገል ትፈልጋላቹ፤ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቿል

ጌታን በዝማሬ ማገልገል ትፈልጋላችሁ ፤ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቿል

ወንጌልን መስበክ ትፈልጋላችሁ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቿል


ብቻ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ካለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት የትኛውንም አገልግሎት ማገልገል አትችሉም፤

መንፈስ ቅዱስ ይሙላባቹ 🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🎙️የልጅነቴ አምላክ 😭

በዚህ መዝሙር ህብረታቹን አድሱ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ ራሱን ይግለጥላቹ🔥

Читать полностью…

አዶናይ

ይቺ ሴት ግን አትገርማቹም

ምን ቢገባት ነው አመቱን ሙሉ ሰስታ ያጠራቀመቺውን ውዷን መዋቢያዋን ሽቶ አምጥታ እግሩን ማበሻ ያደረገቺው፤ ኢየሱስ የኔ የሚላቸው ሰዎች ራሱ ለእግሩ እንኳን ውሀ አላቀረቡለትም፤ ይህቺ ሴት ግን ምርጡን፣ አለኝ የምትለውን ውዷን ሽቶ የእግሮቹ ማበሻ አደረገቺው።

ይቺ ሴት የገባት ነገር ይግባን🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ወይኔ ካንተ ጋር የዋለ ሰዉ 😭

ካንተ ጋር የዋለ ካንተ ጋር ያመሸ ካንተ ጋር ያደረ ሰው ምን ይፈልጋል፤ የአለም ደስታና ክብር በፊቱ የተናቁ ናቸው፤ ከህልውናህ ውጪ ምን ያረካዋል፤ ጠረንህን ያወቀ ወደ ደረትህ የተጠጋ ምን ያስፈራዋል፤ በግርታ መካከል ይለይሀል በጫጫታ ውስጥ ይፈልግሀልበዝምታ ውስጥ ይሰማሀል፤ እየፈለገክ ይናፍቅሀል ወይኔ ካንተ ጋር የዋለ ሰዉ ምነኛ ታደል ምነኛ ተወደደ😭😭

ከኢየሱስ ጋር የምቱሉበት ጊዜ ይርዘምላቹ!

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ጌታን ምን ልጠይቀው ከመንፈስ ቅዱስ ውጪ ጥያቄ አጣው

ጥያቄያቹን አስተካክሉ ጌታን ካገኛቹት ላይቀር መንፈስ ቅዱስን ጠይቁት መንፈስ ቅዱስን እስዲሰጣቹ ለምኑት፤ እርሱ ነው የሚያስፈልገን።

ጌታ ሆይ መንፈስ ቅዱስን ስጠን😭

Читать полностью…

አዶናይ

እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሀለሁ

Читать полностью…

አዶናይ

መሪውን የያዘው እኮ ጌታ ነው ☺️

በአንድ ጉዳይ ላይ 100% እርግጠኛ ሆናቹ ብዙ ርቀት ከሄዳቹ በኃላ መጨረሻው እንዳሰባቹት ላይሆንላቹ ይችላል በዚህ ጊዜ ደግሞ በህይወታቹ ተስፍ ልትቆርጡ ትችላላቹ ግን አንድ መዝሙር ላስታውሳቹ....." ነገሬ ያለው በእሱ እጅ ነው የሚያሰጋኝ የሚያስፈራኝ እስኪ ማነው... ነገሬ ያለው በእርሱ እጅ ነው"..... በማይመሽበት፣ በማይረፍድበት አባት እጅ.... የእውነት ነው የምላቹ ነገር እናንተ እንዳሰባቹት አልሆን ሲላቹ ነው ደስ ሊላቹ የሚገባው፤ "አባ ህይወቴን ሰጥቸሀለው እኔ ያልኩት ሳይሆን አንተ ያልከው በህይወቴ ይሁን" ብላቹ ስትፀልዩ እኮ ጌታ ልመናቹን ሰምቶ የህይወታቹን መሪ ይዞታል ታዲያ አሁን ፀሎታቿ ተሰምቶ እንዳሰባቹት ሳይሆን እንዳሰበው መሆን ሲጀምር ለምን ቅር ይላቿል ? በዚህ አይነትማ ገና ብዙ ጊዜ ተስፋ ትቆርጣላቹ ☺️ ነገር ግን አንድ ነገር እወቁ አሁን በእናንተ ህይወት የሚሆነው ሁሉ የሚሆነው ምራኝ ብላቹ በሰጣቹት በመሪው በጌታ እጅ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መንፈስ ቅዱስ እኩያችን አይደለም

አንዳንድ ሰዎች ባለማወቅ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ላይ ሲያሾፉና ሲቀልዱ ሰማለሁእውቀትም እየመሰላቸው ሊያበረታን በመጣው በእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ያላግጣሉ፤ መንፈስ ቅዱስ ዝቅ ብሎ በውስጣች መኖሪያውን ስላደረገ እኩያችን ሊመስለን በፍፁም አይገባም፤ በስጦታው ላይ አላገጣቹ ማለት በእርሱ ላይ አላገጣቹ ማለት ነው ለአንደበታቹ ገደብን አብጁለት ቀልድም ልክ አለው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መሀሉ ሚስጥር ነው 🤫

እግዚአብሔር እስራኤላውያን በግብጽ በባርነት እያሉ የነገራቸው መድረሻቸውን ማርና ወተት የምታፈልቀውን ከንአንን ነበር፤ አስባቹታል ግን እግዚአብሔር እንዲህ ቢላቸው..... ከግብጽ እንደወጣቹ የኤርትራ ባህር ከፊታቸው ይኖራል ከኃላቹም ደግሞ ፈርኦን ይከተላቿል .....ግን አትፍሩ .... ትንሽ ሄድ እንዳላቹ ደግሞ የውሀ ጥምና ድካም ይኖራል እሱንም በእኔ ጣሉት ታልፉታላቹ.....በጉዟቹም ላይ ደግሞ መሪያቹ ሙሴም ኢያሱን ተክቶ ይሞታል.....እያለ መሀል ላይ ያለውን ፈተና እና ውጣ ውረድ ቢነግራቸው ኖሮ በእርግጠኝነት ማንም ከግብፅ ንቅንቅ አይልም ነበር፤ ደግነቱ ግን መሀሉ ሚስጥር መሆኑ ነው ብዙዎቻችንም የጌታን ድምፅ ሰምተን የተቀበልነው መጨረሻውን ስለነገረን እንጂ የመሀሉን መከራና ስደት ቢነግረን ሀሳብ እንቀይር ነበር፤ ለምን ጌታ መሀሉን አይነግረንም የሚል ጥያቄ ከተነሳ መልሱ ስለማያስፈልገን ነው የሚሆነው መሀሉን የምናልፈው በእኛ አቅም ሳይሆን በጌታ ረዳትነት ስለሆነ የሚገጥመንን መከራና ችግር ማወቁ ለእኛ አይጠቅመንም።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በጣም ያሳዝናል

አንድ ወንድሜ አንድ የቤተ ክርስቲያን መስራችና ባለ ራዕይ ነብይ ነኝ ባይ ያወራለትን ሲነግረኝ የእውነት አልመሰለኝም " ነብይ ነኝ ባዩም በዚች ከተማ Business ምንም እንደማያዋጣና ምዕመኑም ምንም መባ ፣ አስራትና የፍቅር ስጦታ አልሰጥ ስላለኝ ከተማ ልቀይር ነው አለኝ ብሎ ነገረኝ " ይሄን ያህል የሂድን አልመሰለኝም ነበር፤ ቤተ-ክርስቲያን የክርስቶስ አካል መሆኗ ቀርቶ የገንዘብ መሰብሰቢያና የአገልጋዮችን ኪስ ማደለቢያ ስትሆን ማየትን የመሰል ውርደት የለም፤ በጣም ያሳዝናል.... ሌላው ደግሞ እንዳንድ ገንዘብ ጌታ የሆነባቸው ባለ ሀብቶች በየመንገዱ ትልቅ poster እያሰሩ ቤተ ክርስቲያንም የሚያፈልጋትን Sound system እነገዙ ነብይ ቀጥረው ጥሩ ትርፋማ እየሆኑም ነው ተብያለው.... የእውነተኛ ባለ ራዕዮችን ስራ ጥላሸት የሚቀቡ ህዝቡ ላይም በደልን የሚሰሩትን እግዚአብሔር አይታገሳቸውም፤ የተወደዳቹ እናንተ ግን የምትሄዱበትን Church ማንነት በደንብ እወቁ፤ በዚህ ዘመን Church ስለተባለ ብቻ አባል መሆን ብዙ ችግር አለው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የተወደዳቹ ለድካማቹ ቦታ አትስጡት ለስጋቹ ፍላጎት እንደምትጨነቁት ሁሉ ለነፍሳቹም ፍላጎት ትኩረት ስጡ።

ቃል ለማጥናትና ረጅም ጊዜ ለመፀለይ የግድ አገልጋይ መሆን አይጠበቅባቹም።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ፈንጅ አብካኙ ሰው

አስተውላቹ ከሆነ ወታደሮች ለውጊያ ሲጓዙ የሚሄዱት በሰልፍ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ድንገት ጥላት መንገድ ላይ ፈንጂ ሊጠምድ ስለሚችል ለጥንቃቄ በሚል ነው፤ እንደፈሩት ፈንጂ ከተጠመደ መጀመሪያ የሚያገኘው የሰልፉን መሪ ሰው ነው፤ እሱም ድንገት ሳያስበው ፈንጂ የተጠመደበትን ቦታ ላይ ደርሶ ፈንጂውን በእግሮቹ ይረግጠዋል፤ ከዛም ለዚያ ሁሉ ሰው የተጠመደው ፈንጂ በእርሱ ሞት ይከሽፋል፤ የቀሩት ወታደሮችም ፈንጂ ረግጦ የሞተውን ወታደር ፈንጂ አብካኝ ይሉታል፤ ልክ እንዲሁ ለሰው ልጆች ሁሉ የተጠመደ ዘላለማዊ ሞት የሚባል ፈንጂ ነበር ነገር ግን ኢየሱስ የሚባል ዘላለማዊ ሞት አብካኝ በጎሎጎታ ላይ ለእኛ የተገባውን ሞት ብቻውን ሞቶ ለሚያምኑበት ሁሉ ዘላለማዊን ህይወት ሰጠ፤ የኛ ሞት አብካኝ ኢየሱስ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ይህን ነገር አስተውሉ

አንድ በጣም የምትፈልጉትን እቃ ዋጋ ጠይቃቹ 20 ሺህ ብር ቢሏቹና እናንተ ግን ያላቹ ብር ከ10 ሺህ ብር የማይበልጥ ቢሆን፤ ምንድነው የምታደርጉት?.... እቃውን የምትፈልጉት ከሆነ እንደምነ ብላቹ ቀሪውን ብር ለማግኘት ትምክራላቹ አይደል ፤ ልክ እንዲሁ በመንፈሳዊ አለምም በእናንተ አገልግሎት ብዙ ድንቆችና ተአምራቶች እንዲሆኑላቹ ትፈልጋላቹ፤ ይህ የብዙ ወጣቶች ርሀብ ነው፤ ነገር ግን ለዚህ አገልግሎት የሚያስፈልገውን ጥረትና ፀሎት ብዙዎቻቹ አትከፍሉም፤ ይህ ማለት ደግሞ ለ 20 ሺህ ብር እቃ 10 ሺህ ብር ይዞ እቃውን ካልሸጥክልኝ እንደማለት ነው፤ የምትፈልጉት ትልቅ ነገር ከሆነ ትልቅ ዋጋ መክፈል አለባቹ። በዚች ምድር ስርአት ስኬት ካለስራ እንደማይመጣ ሁሉ በመንፈስም አለም የምትፈልጉትን ለማግኘት በብዙ መትጋትና መፈለገ ይኖርባቿል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ያባቴ ልጆች በርቱልኝ😍

አሁን በዚህ ሰዓት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላችሁ ቢሆንም ግን ከጌታ ጋር ያላቹን ህብረት ለአንድም ቀንም ቢሆን እንዳይቀዘቅዝ፤ የቀድሞ ህብረታቹን አድሱ፤ ጌታ ሁል ጊዜ በምትፀልዩበት ቦታ ላይ ሆኖ ይጠብቃቿል አትቅሩበት ደግሞም አታርፍዱበትከምንም በላይ አለመፀለይን ከህይወታቹ አስወግዱ፤ በዙሪያቹ ያሉት ሰዎች ቢደክሙም እንኳን እናንተ ግን ንቁ ዋጋ መክፈል ላለባቹ ነገር ዋጋ ክፈሉ፤ እያነከሳቹም ቢሆን መሄዳቹን ቀጥሉ፤ ዳዴ ላይም ከሆናቹ በሁለት እግሮቻቹ ለመቆም ሞክሩ እንጂ ተስፍ አትቁረጡ፤ አሁን ይህን የምፅፍላቹ ሰው ሁሉ በተኛበት ለሊት መንፈስ ቅዱስ ፃፍ ስላለኝ ነው፤ በርቱልኝ ያባቴ ልጆች ጌታ ከናንተ ጋር ነው 🙏😍

እወዳቿለሁ😍

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ሟች ለገዳዩ ዋስ ሆነ

ጳውሎስ የኢየሱስን ፍቅር ከመታወቅ የሚያልፍ ፍቅር ይለዋል፤ የኢየሱስ ፍቅር ከኛ የማወቅ አቅም በላይ ነው፤ ይህን የፍቅር ሃይል ልንረዳ የምንችለው በዚህ ጥልቅ ፍቅር ውስጥ ስንገባ ብቻ ነው፤ በዚህ የፍቅር አለም ውስጥ ሟች ለገዳዩ ዋስ ይሆናል፣ ንጉስም ከመንበሩ ወርዶ የባሪያን መልክ ይይዛል፤ በዚህ የፍቅር አለም ውስጥ አምላክ ሲቀጠቀጥና ሲተፋበትም ዝም ይላል፤ ይልኩንስ ጎኑን ለወጋው ለዛ ሰው ምህረት ይጠይቃል። እኛ ሁላችን በዚህ ምክንያት በሌለው ጥልቅ የፍቅር አለም ውስጥ መግባት እንዲሆንልን እናፍቃለሁ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ረጋ በሉ 😊

በአለም ደስታና የቤት ስራ ተይዛቹ በኢየሱስ የፍቅር ማዕበል ሳትወሰዱ ሊረፍድባቹ ነው፤ የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው እርሱም ከጌታ እግር ስር ሆኖ ቃሉን መስማትና ከጌታ ጋር የጠለቀ ህብረት ማድረግ ነው፤ ብዙዎቻቹ ግንማርታን ሆናቿል የሚጠቅማቹ ግን ማሪያምን መምሰል ነው፤ አለም የቤት ስራ መስጠት አይደክማትም እናንተ ግን አስተዋዮች ሁኑ የሚጠቅማቹን ምረጡ፤ እድሜቹን ሙሉ የልብ እረፍት ሳይኖራቹ ለአለም ደስታ መሮጥ ወይም ከኢየሱስ እግር ስር ሆናቹ በቃልና በፀሎት ውስጣቹን መገንባት፤ ምርጫው የናንተ ነው ማሪያም ግን መልካሙን መርጣለች።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እስቲ ቀና ብላቹ ደመናዎችን እዩ

በየአመቱ እጅግ በጣም ብዙ ደመናዎች ይፈጠራሉ፤ ሁሉም አንድ ስራ ታዘው ነው የሚላኩት ስራቸውም ዝናብን ማዝነብ ነው፤ ነገር ግን ብዙዎቹ በንፋስ ይበተናሉ፤ ይጠፋሉ ጥቂቶች ግን ንፋሱም እያለ የያዙትን ውሀ በሚገባ አዝንበው ይጠፋሉ፤ እናንተ ከየትኞቹ ናቹ ታይተው በፈተና ብዛት የተላኩበትን ስራ ሳይሰሩ ከሚሞቱ ወይስ ከባዱን ችግርና ፈተና ተቋቁመው የያዙትን መልዕክት ለአለም ከሚያደርሱት፤ ስኬታቹ ያለው ፈተናዎቻቹ ውስጥ ነው፤ በህይወት ጉዞ ላይ የመጣቹበትን አላማ የሚያስጥል ችግር ሊገጥማቹ ይችላል ቢሆንም ግን የተላካቹበትን አላማ ፈፅማቹ እንጂ እንዲው ታይታቹ የምትጠፉ ሰዎች መሆን የለባቹም።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እስቲ መዝሙር ልጋብዛቹ 😍

🎙️ በኃጢአተኛው ድንኳን

ትልቅ መልዕክት የያዘ ድንቅ ዝማሬ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ ግን.....

አውቀዋለሁ እኮ እንዴት እንደሚያስብልኝ፤ ለእኔ ያዳላ እስኪመስልበት ድረስ እንዴት እንደሚንከባከበኝ ልቤ ይነገረኛል፤ አንዳንዴ እንደውም በጣም በድዬው ይቀጣኛል በሰዎት ፊት ያዋርደኛል ብዬ ስትጠብቅ በብዙ ህዝብ ፊት ለክብሬ ይህን ሰው እፈልጋለሁ ክብሬን ይሸከማል ብሎ ይናገረኛል፤ እንደማይገባኝ እያወቀ መንፈሱን ይሰጠኛል፤ የቀን ህብረታችን በኔ ምክንያት ቀዝቅዞ እንኳን በለሊት አቅም በማይኖረኝ ጊዜ መቶ ነገዬን ይነግረኛል፤ ለፍቅሩ ምክንያት አይፈልግም ብበድለውም ይወደኛል ባልበድለውም ይወደኛል፤ አይባልም ግን እንደኔ ይህ ኢየሱስ ለኔ ያደላልለናንተም እንዲሁ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የመዝሙር ግብዣዬ 😍

🎙️የምፈራው ቦታ

ፀሎቴን ነው የዘመረቺው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…
Subscribe to a channel