ኢየሱስ ምን ነካው ?
ሁሉም ህዝብ ኢየሱስን ለመንካት ይገፋፋል ኢየሱስም ድንገት በትርምሱ መሀል "ማነው የነካኝ " ብሎ ህዝቡን ይጠይቃል...
በእርግጥ ጥያቄው ግራ ያጋባል ምን አይነት ጥያቄ ነው ሰዉ ሁሉ የእርሱን ሰውነት እየነካ ባለበት ሰዓት እንዴት ማነው የነካኝ ብሎ ይጠይቃል🤔 የእውነት ኢየሱስ ምነካው ? ጴጥሮስም የጌታ ጥያቄ ስላልተዋጠለት ጌታ ሆይ እንዴት " ማነው የነካኝ " ትላለህ ይሄ ሁሉ ህዝብ እየነካክ አይደል እንዴ ይለዋል፤ ኢየሱስም አንድ ሰው በእምነት ነክቶኛል ሀይል ከእኔ ወጥቷል ብሎ ሳይጨርስ አንዲት በበሽታዋ ምክንያት መልስ ያጣች ሴት እኔ ነኝ ብላ ጮኸች ....ለካስ ጌታ የሚነካው ሳይሆን የሚያምነው ሰው ነበር ያጣው፤ ይቺ ድንቅ ሴት ለእኛ ትልቅ ትምህርት ያስተማረችን ይመስለኛል ብዙ ሰዎች መንካትን ይነኩታል ግን ምን አይቀበሉም ጥቂት ሰዎች ግን በእምነት ነክተው ሀይልን ይቀበላሉ...
ወዳጆቼ በብዙ ሰዎች መካከል የኢየሱስን ቀልብ የሚሰርቀው በውስጣቹ ያለው እምነት ነው ለዚህም ነው በእምነታቹ ጠንካሮች መሆን ያለባቹ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
የተወደዳቹ ጌታ ህዝቡን እድታገለግሉ ፀጋን ከሰጣቹ በፍቅርና በትሁት ልብ የእግዚአብሔር ህዝብ አገልግሉ መታየቱና ለራስ ክብር መፈለጉ
ማንንም አልጠቀመም....
በዝማሬ፣ በመሪነት ፣ በነብይነት ፣ በአስተማሪነት ብቻ እግዚአብሔር ለመረጣቹ ለየትኛውም ስራ ታማኝ አገልጋዮች ሁኑ እግዚአብሔር ታማኝነታቹን አንድ ቀን ያየዋል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
🎙️በዝምታ አቀፈኝመዝሙሩን በደንብ እንድትሰሙት ስለፈለኩ ነው ያጓጓዋቹ 😍 መልዕክቱ እስኪገባቹ ድረስ ደጋግማቹ ስሙት
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ዛሬ ነፍሴ እንዲህ ብላ ጮኸች.
..
አባቴ ሆይ በደምህ ወዳነፅካት ቤተ ክርስቲያን እንደገና በክብር ና የጌታ መንፈስ ሆይ ና ወደ ሙሉ ወንጌል ና ወደ ቃለ ህይወት ና ወደ መሰረተ-ክርስቶስ ና ወደ መካነ ኢየሱስ ና ወደ ኦርቶዶክሳውያንና ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን ጌታ ሆይ መከፋፈሉ ይበቃና ዘረኝነቱ ና ጥላቻውም ሰልችቶናል ና በክብር ወደ መቅደሶችህ ያንተ ሽታ ናፍቆናል 😭
በመንፈስ ሙላኝ እንደገና 😭ይሄ መዝሙር ለእኔ ባለውለታዬ ነው
...
አውቃለሁ ሁላቹም ታውቁታላቹ ግን ስሙት አሁንም መንፈስ አለበት።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ዋናውን ፀሎት አስቀድሙ
ብዙ ሰዎች ፆም ፀሎት ይዘው አጥብቀው ፣ ጌታን የጠየቁበት ጉዳይ ሲመለስላቸው በተመለሰላቸው መልስ ላይ ፈዘው የጌታ መልክ ደምዝዞባቸዋል....
አስተውላቹ ከሆነ ጠቢቡ ሰለሞን ችግሩ ጥበብ መጠየቁ ላይ አልነበረም ጥበብን ከፀሎቶቹ መካከል ዋና ርዕሱ ማድረጉ ላይ እንጂ....
በዚህም ዘመን ልክ እንደ ሰለሞን ጥበብን ጠይቀው ጥበብን ሲያገኙ ጌታ የዘነጉ ሰዎች በዝተዋል ለዚህ ነው ጌታን ሁል ጊዜ " ከአንተ ጋር እንድንቆይ የሚረዳንን ፀጋ ስጠን " የሚለውን ፀሎታችንን ከሁሉም በፊት ማስቀደም የሚኖርብን ሌሎቹ ፀሎቶቻችን እና ጥያቄዎቻችን ከዚህ ፀሎት በኃላ ይደርሳሉ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ከደቂቃዎች በፊት ለአንዲት እህቴ ስፀልይላት ነበር እና ጌታ ተናገራት.....የምታምኑ ከሆነ አሁን ደግሞ ለእናንተ ፀልያለው በኢየሱስም ጌታ
ቤታቹን፣ ቤተሰባቹን ፣ ትምህርታቹን ፣ ስራቹን በክብር ይጓበኘዋል🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
Michuu Dhugaa
ይሄን ኦሮሚኛ መዝሙር ብዙ አመት ሰምቼዋለው በጣም ነው የምወደው....ስሙት
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ማነው ደክሞ የማያውቀው ?
የእውነት ነው የምላቹ እስከ ጥግ ድርስ በድካም ውስጥ ብቶኑም... በኃጢአት ልምምድ ውስጥ ተዘፍቃቹም መውጣት ቢያቅታቹም...
በስራ እና በቤተሰብ ጫናም ምክንያት ዝላቹ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ግን እናንተን ከጌታ ቤት እንድትርቁ በቂ ምክንያት መሆን አይችልም፤ ሲጀመር ማነው ባቅሙ በቤቱ መቆየት የሚችለው ሁላችንም እኮ ደካሞች ነን ነገር ግን ደግፎ የያዘን
የምህርት እጅ
አለ
....
አሁን ላይ በመንፈሳዊ ህይወታቸው ስኬታማ ናቸው የምትሏቸው ሰዎች ትናንት ላይ እንደናንተው ዝለውና አቅም አተው ያውቃሉ ነገር ግን ዳግም ለመነሳት አቅም ያገኙት ከወደቁበት የሚያነሳቸው
ፀጋ እንዳለ ስለገባቸው ነው....
የተወደዳቹ በጌታ ፍቅር ስሙኝና ዛሬ ያንን ውድ ህብረታቹን ዳግም አድሱት እመኑኝ ፀጋው ይረዳቿል
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
✅ የ Social media አጠቃቀም ለክርስቲያኖች
የሳምሶንን እና የሰለሞንን ታሪክ መድገም የለባቹም ብዙዎች ቢሰሙት የሚጠቀሙበት ትምህርት ነው.... በደንብ ስሙት
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እነኚን ቃሎች አንብቤ ነው መንፈስ ቅዱስን አምርሬ መጠማት የጀመርኩት... ኢየሱስ ትኩረት ሰጥቶ ያወራበት ጉዳይ ላይ እኔ ቸልተኛ መሆን አልችልም።
መንፈስ ቅዱስ የግድ ያስፈልገናል🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ😭 ይሄን መዝሙር ከፍታቹ መፀለይ ጀምሩ
.
...
እርዳኝ በሉት😭
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
የዮሴፍ ንግስና የተቀመጠው ግብፅ ነው
መቼም ሁላችንም ስኬታችንና ወግ ማረጋችን በቤተሰቦቻችና በወዳጆቻችን መካከል ቢሆንልን ነው ደስ የሚለን አንዳንዴ ግን እግዚአብሔር ስኬታችንን እኛ በማናውቀው ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል ለዚህ ደግሞ የዮሴፍ ታሪክ ትልቅ ምሳሌ ነው፤ እግዚአብሔር የዮሴፍን ንግስና ያስቀመጠው እኛ እንደምናስበው ደስታውና ምቾቱ ባለበት በአባቱ መንደር ሳይሆን በምንም ተአምር ይኖርበታል ተብሎ በማይታሰብበት የግብፅ ሀገር ነበር፤
እግዚአብሔር ሁላችንም ስኬታማ እንድንሆንለት ይፈልጋል ነገር ግን ሁላችንም ስኬታሞች አይደለንም ምክንያቱ ደግሞ ከምኖዳቸው ሰዎች ርቀን እኛ ወደማናውቀው እግዚአብሔር ግን ክብራችን ወዳስቀመጠልን ስፍራ መሄድ ስለማንፈልግ ነው ወዳጆቼ መቼም የከበረ ህይወት በእኛ ምቾትና ድሎት መካከል አይገኝም ለዚህ ነው እግዚአብሔር ያሰበልንን ክብር ለማየት ዋጋ መክፈል የሚኖርብን።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
አመለካከቴን የቀየረው ክስተት
አንድ እሁድ ጠዋት እንደተለመደው ወደ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጌታን ለማምለክ ሄድኩኝ ፤ ያው ሁላቹም እንደምታውቁት የቃል ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔር ቃል ይሰበካል በእዛም ቀን አንዲት አገልጋይ ወደ መድረኩ ወጥታ ጌታን ፀንቶ ስለመጠበቅ መስበክ ጀመረች፤ በጊዜው መድረኩ ላይ ምን የሚታይ መስቀል አልነበር እኔ ግን ድንገት አይኖቼ ተከፍተው ቃል እየሰበከች ካለችው ሴት ጀርባ ኢየሱስን መስቀል ላይ ተሰቅሎ
አየሁት በሰዓቱ
በጣም ስለደነገጥኩ ጎንበስ አልኩኝ በድጋሚም ነገሩ እውነት ስላልመሰለኝ ቀና ለማለት ሞከርኩ ነገር ግን አሁንም ያ ያየሁት ኢየሱስ መስቀል ላይ ተንጠልጥሎ ፊቱ ከበፊቱ ይልቅ ጎልቶ አየሁት እኔ ምንም እንቅስቃሴ ላለማድረግና ድምፅ ላለማሰማት አንደምንም ብዬ ራሴን ተቆጣጠርኩት ከዛም አንዲ የሚል ድምፅ ሰማሁ....
" በመስቀሉ ስራ ነው እንዲህ የተሰባሰባቹት " የሚል ድምፅ ሰማው 😭 ከዛም ቀን በኃል ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለኝ አመለካከት በሙሉ ተቀየር ለካስ ልማድ ስለሆነብን አይደለም ቸርች የምሄደው የእውነት ለካስ የመስቀሉ ስራ ነው ከዚም ከዛም አሰባስቦን አንድ ላይ ንጉሱን እንድናመልክ ያደረገን....
ወዳጆቼ በዚያ ቀን የሚያገለግሉን አገልጋዮች ምንም ሊሆኑ ይችላሉ የምናመልክበትም ቤት ብዙ ምቾት ላይሰጠን ይችላል ነገር ግን በእዛ ስፍራ ዋጋ ከፍሎ ያዳነን ጌታ ይገኛል ቸርች ለመሄድ ደግሞ ከዚህ በላይ ምክንያት አያስፈልግንም ኢየሱስ መኖሩ ብቻ በቂ ነው...
ቸርች የሰዎች መሰብሰቢያ ስፍራ ብቻ ሳይሆን የሰማይ መላእክት ማምለኪያም ስፍራ ጭምር ነው፤ የመሰባሰባችን ዋና ርዕስ ደግሞ የታረደው በግ ነው ይህን እውነት ነው ልንረዳው የሚገባን።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ምንም ያህል ቢያረፍድ ይሳቅ ይቀድማል
እስኪ መልሱልኝ እናንተ ከጓደኞቻቹ እኩል ሮጣቹ የምደርሱበት ስፍራ ይበልጥባቿል ወይስ ጌታን በፅድቅ ጠብቃቹ አርፍዳቹ የምትወርሱት ስፍራ ? የቱ ይበልጥባቿል ? ሲጀመር ሁላችንም በ 90 አመታችን ከምናገኘው ትልቅ ስኬት ይልቅ በ 30 አመታችን የምናገኘው ጥቂት ነገር ይበልጥብናል ነገር ግን ይሄ ለእኛና በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ነው የሚሰራው፤
ለእግዚአብሔር ግን ለአብርሃም በ 60 አመቱ እስማኤልን ከሚሰጠው ይልቅ በ 100 አመቱ ይሳቅን ቢሰጠው ይበልጥበታል....
የተወደዳቹ የእናንተ ጌታን ፀንቶ መጠበቅ ዙሪያቹ ካሉት ሰዎች አንፃር ሲታይ ስህተት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ምንም ያህል ስህተት ቢመስል ጠብቃቹ የምታገኙት ይሳቅ እነርሱ ጊዜው እና ህጉን ጠብቀው ካገኙት እስማኤል ሺ እጥፍ ይበልጣል።
ጌታን ጠብቁት 😍
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ጌታ ተሳስቶ ይሆን
እንዴ ?
ከጥቂት አመታት በፊት ጌታ ስለእኔ የወደፊት ህይወት የማይታመን ነገር ሲነግረኝ ጌታ ሆይ ተሳስተ ይሆን እንዴት እኔ እኮ ኤርሚ ነኝ ብዬው ትናንትናዎቼን ላስታውሰው እሞክር ነበር...
አይ እኔ😊 ብቻ ዛሬ እንደኔው ጌታ በሚነግራቹ ነገር ተገርማቹ እኔ እኮ እያላቹ ትናንትናቹን እንደ ሙሴ እግዚአብሔር ለማስታወስ የምትሞክሩ ሰዎች ካላቹ ይሄን እወቁ የተናገራቹ ጌታ በእርግጥ አልተሳሳተም....
ብዙዎቻችን ያደግነው ተስፋ የሚያስቆርጡና ለከበረ
ስፍራ እንደማንመጥን በሚነግሩን ሰዎችና ሁኔታዎች መካከል ነው እኛም እነኚ ሁኔታዎች የተናገሩንን ሰምተን ስላደግን ከጌታ የሚመጣው ድምፅ የተሳሳተ ድምፅ መስሎ ሊታየን ይችላል ነገር ግን እመኑኝ ካላቹበት ሁኔታ አንፃር ሲታይ ስህተት የሚመስለው የእግዚአብሔር ድምፅ እውነተኛና በግልፅ በእናንተው ህይወት ውስጥ የሚፈፀም ነው
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ማርታን መሆን አያዋጣም😊
ወዳጆቼ ጌታን ከሩቅ እያያቹት ስራቹ ላይ ብቻ ተፍ ተፍ ማለታቹ አያዋጣቹም የግድ ደግሞ ስኬታማና የተሳካለት ሰው ለመሆን ሁሉንም ነገር ማግበስበስ አይጠበቅባቹም.....የሚያዋጣው ማርታን መምሰል ሳይሆን ማሪያምን መሆን ነው
ጌታም ለዚህ ነው የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው ማርያምም መልካሙን መርጣለችና እርሱም ከእርሷ አይወሰድባትም ብሎ የተናገረው እውነት ነው የሚያስፈልገው አንድ ነገር ነው
እርሱም ለጌታ መሆን ፤ ይሄን ስል ደግሞ ቁጭ ብላቹ ተቀመጡ ማለቴ እንዳልሆነ መቼም
ትረዱኛላቹ
፤ አስተዋዎች ከሆናቹ አንድ ትልቅ ምክር ልምከራቹ ገንዘቡም...ድግሱም... ስራውም... ቡናውም... ጫወታውም... ሶሻል ሚዲያውም...ጓደኞቻቹም
ከጌታ በኃላ መድረስ ስለሚችሉ ቅድሚያቹን ሁሉ ለጌታ ስጡት።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው 💯
ዙሪያቹ ያሉት ሰዎች እናንተ ሲሳካላቹ፣ ፣ ጥሩ የሚባል ደረጃ ስደርሱ ብቻ ነው እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው የሚሏቹ ነገር ግን እነኚው ሰዎች እናንተ አቅም ስታጡ ፣ ስደክሙ ህይወታቹ በመከራ ሲሞላ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው ለማለት አቅም ያጣሉ፤ አስተውላቹ ከሆነ ዮሴፍ ሲጠላ፣ ሲገፍ ፣ሲሸጥ ፣ ሲፈተን፣ እስር ቤት
ሲገባ ማንም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ያለው አልነበረም ምክንያቱም ሁኔታው ሲታይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያለ ስለማይመስል ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ በግብፅ ሀገር ሁሉ ዮሴፍ ሲነግስ ሁሉም ስኬቱን አይተው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ብለው ሰገዱለት ከዛ ሁሉ በፊት ግን እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንደነበር መጽሐፍ ይነገረናል.....የተወደዳቹ ዛሬ እኔ በየትኛውም ሁኔታዎች ውስጥ ላላቹ ሰዎች አንድ መልዕክት አለኝ " እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ነው" አሁን በዚህ ሰዓት ደክማቹ ሊሆን ይችላል ቢሆንም ግን አሁንም ብቻቹን አይደላቹም፤ ህይወት እናንተ እንዳሰባቹት አልሄድ ብሏቹም ይሆናል እመኑኝ እግዚአብሔር ግን አሁንም ከእናንተው ጋር ነው ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ንገሯቸው ቁርጣቸውን ይወቁት 😍የተወደዳቹ
ነገሮች ከጌታ ከሚያርቋቹ እነርሱ ቀድመው ከእናንተ ቢርቁ ይሻላል
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ከንአን መግባቱም ይቅርብን
ሙሴ አንድ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ አብረህን ውጣ ካለዚያ ከዚህ ንቅንቅ አንልም፤ አንተ ከኛ ጋር ካልወጣህ ሌሎች ህዝቦች በምን ያውቁናል ብሎ ፀለየ....
ለካስ ሙሴ ማወቅ የሚፈልገው ከንአን መገባት አለመግባቱን ሳይሆን የእግዚአብሔር ሀልዎት ከእርሱ ጋር እስከ መጨረሻው መኖሩንና አለመኖሩን ነበር፤ የተወደዳቹ ምንድነው የምትፈልጉት.......
ስኬት... ሀብት.. ክብር.... ዝና.....ወይስ የእግዚአብሔርን ከናንተ ጋር መሆን....
እስቲ ልጠይቃቹ ለእናንተ ከንአን ይቀድማል ወይስ የእግዚአብሔር ከናንተ ጋር መሆን መልሱን ለናንተው ልተወው፤ እርሱ የሌለበት ከንአን ከምንገባ፣ እርሱ ያልደገፈው አገልግሎት ከምናገለግል እርሱ ያልከበረበት ሀብት ከምናካብት አስር ጊዜ ቢቀርብን ይሻላል.... ሁሉ ነገራችን ውበት የሚኖረው እርሱ ከእኛ ጋር ሲሆን ብቻ ነው።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
እንቆቅልሽ ?
ባለ አራት ፊደላት ድምር ውጤት ነው፤እነኚ 4 ፊደላት በሚገባ ከተጣመሩ በምድር ሁሉ ላይ ሀይል ያለውን አንድ ብርቱ ቃል ይፈጥራሉ፤ በነገራችን ላይ በጭለማው አለም ዘንድ እነኚ ፊደላት እንዳይጣመሩ ከፍተኛ ትግል ይደረጋል ነገር ግን እኛ ምንም ማድረግ ስለማንችል እነኚን ፊደላት በሚገባ አጣምረን በሽታችንን፣ ጭንቀታችንን፣ እንዲሁም ያስቸገሩንን ነገሮች ሁሉ ድራሻቸውን እናጠፋበታለን፤ ጥያቄው የነኚ 4 ፊደላት ድምር ቃል ምንድነው ነው???
ይህንን መልስ የሚመልስ ሰው ካለ ሽልማት አያስፈልገውም፤ ሽልማት የማይኖረው ጥያቄው ቀላል ስለሆነ ሳይሆን የጥያቄው መልስ እራሱ ሽልማት ስለሆነ ነው 😍
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አቁሙ 😠
አቅማቹንና ነጋቹን እንደ ቀልድ እየበሉባቹ ካሉ ነገሮች ለምን ራሳቹን አታድኑም ?
ቁም ነገር በሌለው ሳቅና ቀልድ በየቀኑ በየ ቲክቶኩ እና ፊስቡኩ ውድ ጊዜያቹን እንዲሁ ማባከን ኪሳራ እንጂ ትርፍ ያለው አይመስለኝም....
በዚህ እንኳን ቀልዳቹበት ሰርታቹበት እንኳን መለወጥ በማይቻልበት ጊዜ አጉል ስንፍና ውስጥ መቆየታቹን አቁሙ 😠 Social media ላይ ማፍጠጥ አቁሙ...
ላለመፀለይ ምክንያት መደርደራቹን አቁሙ.... ለውጣቹ
ላይ ሙድ ከሚይዙ ጓደኞቻቹ ጋር ያላቹን ህብረት አቁሙ
በቃ በህይወታቹ ላይ ወስኑ ትኩረታቹን ከሰዎች አስተሳሰብና ውሎ ላይ አንስታቹ ራሳቹ ላይ ማድረግ ጀመሩ፤ ጌታ እንጂ ጊዜ ምህረት አያቅም በጊዜያቹ ተጠቀሙ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
አንተስ ምን ትላለህ ?
ብቻዋን ያመነዘረች ይመስል እሷን ብቻ ይዘው ባንዴ ፀጥ የሚያደርጋትን ድንጋይ እየመረጡ በየአደባባዩ ትወገ ትወገ ብለው ሞቷን ደገሱላት......
ኢየሱስም አይቶ የድርሻውን ድንጋይ እንዲጥል ፈልገው ወደ እርሱ አመጧትና አንተስ ምን ትላለህ ? ብለው ጠየቁት፤ እርሱም ድንጋይ መወርወር ሲገባው ጥቂት ቃላት ወደ ከሳሾቿ ወርውሮ በድብቅ የሰሩትን ኃጢአት በግልፅ ገለጠባቸው ከዛም ድንጋይ ተሸክመው የመጡትን ሰዎች የሰሩትን ኃጢአት አሸክሟቸው ሸኛቸው ኃጢአቷን ይዛ የመጣችውን ሴት ግን የእርሱን ፅድቅ አካፍሏት በሰላም ሂጂ አላት.... የተወደዳቹ ሰዎች ስለናንተ ህይወት እድሉ ቢያገኙ ብዙ የሚያወሩት ይኖራቸዋል... ትወገር ፣ ትሙት
፣ ትጥፍ ፣ አይለፍላት ፣ አይሳካላት ፣ ብቻ ብዙ ነገር
ይላሉ ነገር ግን በእናንተ ህይወት ማንም ምንም ቢናገር መፍረድ እስካልቻለ ድረስ ምንም ማድረግ አይችልም፤ ለዚህ ነው ምን ይላሉ ሳይሆን ምን ይላል ብለን መጠበቅ የሚኖርብን።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
የእናንተ መኖር ትርጉም የለውም😥 ?
አንዳንዴ ዙሪያቹ ያሉት ሰዎች አፍ አውጥተው እንደ ማይነጋላቹ፣ ተስፋ እንደሌላቹ ይነግሯቿል እናንተም ያላቹበትን ሁኔታ ስታዩት ሰዎች የሚያወሩት ወሬ እውነት
እንደሆነ አምናቹ ትቀበላላቹ....
ሌላ ጊዜ ደግሞ ቆም ብላቹ ስታስቡት ጌታ ያወራቹ የተስፍ ቃል ትዝ ይላቹና ተንበርክካቹ ምነው ጌታ ሆይ ያ ያልከኝን ክብር ምነው ዘገነ ብላቹ ትፀልያላቹ....
ልክ ናቹ አንዳንዴ ህይወት እንዳሰባቹት አልሆን ሲላቹ የእናንተ መኖር ትርጉም የሌለው መስሎ ሊታያቹ ይችላል ደስ የሚለው ግን ይሄ ስሜት እናንተ ጋር እንጂ ጌታ ጋር አለመኖሩ ነው፤ ገምቱ እስቲ የዚህ ቃል ትርጉሙ ምን ይመስላቿል " Ոսկի " ☺️ ትርጉም የሌለው ይመስላል አይደል ? ነገር ግን ለእኛ ነው እንጂ ለአርሜንያን ይህ ቃል ወርቅ ማለት ነው፤ ልክ እንዲሁ የእናንተም ህይወት ትርጉም የማይኖረው የእናንተን ማንነት ለማያውቁት እንጂ ዋጋ ከፍሎ ለሰራቹ ጌታ ዛሬም መኖራቹ ትርጉም አለው።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ሰው ገድላቹ አታውቁም
እንደው ባጋጣሚ አንድ ነፍሰ ገዳይ አግኝታቹ ለምንድነው ሰውዬውን የገደልከው ብላቹ ብጠይቁት ብዙ ምክንያቶች ሊሰጣቹ ይችላል ነገር ግን ዋናው ምክንያት የሟች መኖር ለእርሱ ህይወት አደጋ ስለሚሆን ነው ሰውዬውን የገደለው....
እና ዛሬ አንድ አስቸጋሪ ሰው እንድትገሉ ትዕዛዝ ልስጣቹ.... ራሳቹን ግደሉ 😊 የተወደዳቹ እኛ አላወቅንም እንጂ የእኛ መኖር ነው ክርስቶስን በእኛ ውስጥ በሀይል እንዳይታይ ያደረገው.... ኢየሱስ አንድ ጊዜ እንዲህ አለ.... “ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነገር ግን ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ያድናታል።”
ወዳጆቼ ራሳቹን ማዳን የምትፈልጉ ከሆነ ነፍሳቹን ማለትም ፍቃዳቹን፣ ስሜታቹን፣ እውቀታቹን ለወደዳቹ ጌታ አሳልፋቹ መስጠት አለባቹ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
በቀይ ወጥ 😥?
አንድ ቀን ያዕቆብ እጅ የሚያስቆረጥም ቀይ ወጥ ይሰራል፤ ታላቅ ወንድሙም ኤሳው በሰዓቱ በጣም እርቦት ስለነበር " እባክህን ከዚህ ወጥ አብላኝ " ብሎ ይለምነዋል ያዕቆብም በሰራት ቀይ ወጥ ፋንታ ለድርድር የማይቀርበውን ብኩርና ሽጥልኝና እሰጥሀለው ይለዋል ኤሳውም ብኩርናው ቀሎበት ስለነበር በቀይ ውጥ ውዱን ብኩርናውን አሶልፎ ለታናሹ ያዕቆብ ሸጠለት....
በዚህም ምክንያት የኤሳው ታሪክ ከዛ ፈቀቅ ማለት አልቻለም የያዕቆብ ታሪክ ግን ታላቅ ህዝብ ሆኖ እስራኤል ለመባል በቃ....
የተወደዳቹ አሁን በክርስቶስ ያገኛቹት ህይወት ለድርድር የሚቀርብ ህይወት መሆን የለበትም አለም ውድ ነገር ስለሌላት እንደ ያዕቆብ ለስጋ በሚመች ጠፊ ነገር የከበረውን ነገራቹን ልትነጥቃቹ ትፈልጋለች፤ ግን ይሄን እውነታ እወቁልኝ አሁን ያገኛቹት የከበር ህይወት በእጃቹ ላይ ነው ያለው ከፈለጋቹ
በተራ ነገር ትቀይሩታላቹ ብልህ ከሆናቹ ደግሞ በፈተናም ፀንታቹ እስከ መጨረሻው ተይዙታላቹ.... ለዚህም ነው መጽሐፍ እስከ
መጨረሻው
የሚፀና
እርሱ ይድናል
የሚለን።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost