አንድ ሰሞን 💪🔥
..
...
😞🙇
መፀለይ ታዞትራላቹ ፣ ውስጣቹም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይቀጣጠላል የሚደንቁ ህልሞችንና ራዕዮችንም ማየት ትጀምራላቹ ፣🔥 ነገር ግን ይሄ ከአንድ ሰሞን አያልፍም ደግሞ ወደዛ ወደማቶዱት ህይወት ትመለሳላቹ... መድከም ትጀምራላቹ🙍 ያንን ትጋታቹን ትጥሉታላቹ፣ ኃጢአት Normal ይሆንባቿል ብቻ ብዙ
ነገር... አሁን በዚህ አይነት ድካም ውስጥ እያለፈ ያለ ሰው ካለ የምለው ነገር በደንብ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ ፤ " ግን ለምንድነው ምደክመው ? " የብዙዎቻቹ ጥያቄ ነው እስቲ ላንዳፍታ ይሄ ጥያቄ በውስጣቹ የሚፈጠርባቹ ልጆች ጥቂት ጊዜ ወስዳቹ ዙሪያቹን
ተመልከቱ
...
የአባቴ ልጆች እናንተ አላስተዋላቹም እንጂ እኮ የእናንተ አድካሚዎች በዙሪያቹ ነው ያሉት
ለምሳሌ ጓደኞቻቹ ፣ የ social media አጠቃቀማቹ እና ሌላም
...
የተወደዳቹ እንደ ወንድም የምትሰሙኝ ከሆነ አንድ ምክር ልምከራቹ፤ እንድትደክሙ ከሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ራሳቹን አርቁ በቃ ወስኑ ፤ አውቃለው ከለመዳቹት ነገር መለየቱ ያማል ነገር ግን እያመማቹም ቢሆን
ሳታውቁት አቅማቹን እየበሉባቹ ካሉ ነገሮች ፈጥናቹ ራሳቹን አግልሉ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
🎙️ ናፈቀኝ 😭
በዚህ መዝሙር እንደገና ውስጣቹ ርሀብ ይፈጠራል🔥🔥.. ከልባቹ ስሙት
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
በዚህ በእኛ ዘመን የከበደን፤ ትንቢት መናገር ፣ በጥሩ ድምፅ መዘመር እንዲሁም መድረክ ላይም ማይክ ይዞ መስበክ አይደለም...
ነገር ግን ትልቅ ስምና አገልግሎት አላቸው እስከሚባሉት አገልጋዮችም ድረስ እኔንም ትንሹን ጨምሮ አንድ ማድረግ የከበደን ነገር ያለ ይመስለኛል እርሱም መሞት ነው የእውነት መሞት ከብዶናል ...ክብራችንን ...ስማችንን.. የሰበሰብነውን ዝና ጥለን ለወደደን ጌታ መሞት ምጥ ሆኖብናል.... ነብዩም ክብሩን ይፈልጋል ዘማሪውም ስሙን ይጠብቃል፣ እኔን እዩኝ እኔ ብቻ ነኝ ልክ ባዩ በዝቷል ብቻ በአጭሩ እኛነታችንን ገለን ያንን ሩሩ ጌታ ማሳየቱ ላይ አቅም ያጣን ይመስለኛል😔
አውቃለው ሁላችንም መወደድ እና መከበር እንፈልጋለን ነገር ግን ከዚያ በላይ ሁሉን ነገራችንን ለወደደን ጌታ እንደ ጉድፍ መቁጠር ብንችል መልካም ነው።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አትደርቁም 🙅
አሁን በዚህ ሰዓት በብዙ ድካም ውስጥ ያላቹ፤ አቅም አታቹ መፀለይና መትጋት የከበዳቹ እንደውም መንፈሳዊ ህይወታቹ ራሱ የደረቀባቹ የሚመስላቹ የአባቴ ልጆች ዛሬ አንድ ህይወታቹን የሚያለመልም ቃል ልንገራቹ እመኑኝ
" አትደርቁም " ላነቃቃቹ ፈልጌ አይደለም የምሬን ነው የምላቹ የህይወት ውሀ ምንጭ ስር ተተክሎ የሚደርቅ ሰው የለም... ደካሞች ባንሆን ኖሮ ኑ ላሳርፋቿ ባላለን ነበር ፤ እንደክማለን ሀይሉ ግን ያበረታናል እንስታለን ምህረቱ ግን ይመልሰናል፤ ይሄ እውነት ነው ሁላችንንም እስከዛሬ በቤቱ እንድንቆይ የረዳን...
የተወደዳቹ ከሰይጣን ወደናንተ የሚመጡትን ክሶች ወደ ጎን ተዎቸውና የጌታ የማያልቅ ምህረት እና ገደብ የሌለውን ፍቅሩን እያሰባቹ ዳግም በፊቱ ለመቆም ወስኑ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
እኔ ከመንፈስ ቅዱስ አብሮነት ውጪ መኖር እንደማልችል ሰው ሁሉ እንዲያቅልኝ ፈልጋለው... በቃ አልችልም ከህልውናው ውጪ መኖር 😭 የእውነት ነው የምላቹ እኔ ጋር ውድ ናቸው የምላቸው ነገሮች ከእኔ ቢሄዱ ላዝን እችላለሁ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከእኔ ከራቀ የእኔ እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ገና ሳስበው ውስጤ ይደነግጣል
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምንም ያህል ጥቅምህ በደንብ ባይገባንም ፣ ፍቃድህንም ሳናደርግ ቀርተን ብናሳዝንህም ከቤታችን፣ ከህይወታችን እንድትርቅብን ግን አንፈልግም😭
መንፈስ ቅዱስ ይኑር ከእኛ ጋር🔥
ሞትን ፈርተን ይመስላቿል ☺️ ?
ጠዋት ገና ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ቁርስ ቁርስ የሚያስብለን፣ ገና 6 ሰዓት አከባቢ ሲሆን ምግብ ፊት ራሳችንን የምናገኘው፣ ምሽት ላይም እንደልማዳችን እራት እያልን ምግብ የምንበላው የእውነት ሞትን ፈርተን ይመስላቿል ☺️ በፍፁም አይደለም መቼም ለአንድ ቀን ምግብ ሳልበላ ብቀር ስለምሞት ነው በቀን 3 ጊዜ የምበላው የሚለኝ ሰው አለ ብዬ አላስብም ☺️ .... አመናቹም አላመናቹም ምግብና እኛን በየቀኑ የሚያገናኘን በውስጣችን ያለው ርሀብ ነው በቃ ለዚያ ነው ምሳችንን መዝለል የሚከብደን ፤ መንፈስም አለም ላይ ልክ እንዲሁ ነው የተወደዳቹ በውስጣቹ ዘውትር የሚነድ መንፈሳዊ ርሀብ ከሌለ በሳምንት አንዴ መፀለዩ ስራ ይሆንባቿል ፤ እንደውም ቀስ በቀስ ፀሎት ራሱ ይሰለቻቿል ቃሉን ማጥናትም እንደዛው....
ለምን ካላቹ መልሱ በውስጣቹ ዘውትር የሚነድ መንፈሳዊ ርሀብ ስለሌለ ነው፤
የስጋችን ርሀብ ሰዓት ጠብቀን እንድንበላ ካደረገን የነፍሳችን ርሀብ ደግሞ በየቀኑ እንድንፀልይ ያደርገናል።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ይሄ ቃል ለማን መልዕክት እንደሆነ አላውቅም ብቻ ግን ይሄን ቃል እንድልክላቹ መንፈስ ቅዱስ ልቤን አሳስቦታል፤
ዕንባቆም 3
¹⁷ ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
¹⁸ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
¹⁹ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤
እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።
ወዳጆቼ እግዚአብሔርን የደስታቹ ሁሉ ምንጭ አድርጉት... የዛኔ የጠበቃቹት ሁሉ ባይሆንም፣ ያመናቹት ቢከዳቹም፣ ጥያቄዎቻቹ መልስ ባያገኙም
እንኳን የእናንተ ደስታ አይነጠቅም፤ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ይሄው እኔ ይሄን ድንቅ መዝሙር ደጋግሜ መስማት ከጀመርኩ አመት አለፈኝ 🔥መዝሙሩን እየሰማቹ ርሀብ ውስጣቹ ይፈጠራል... ደጋግማቹ ስሙት
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ወዴት ናቹ 😢 ?
ታስታውሳላቹ አይደለ አዳም ከሳተ በኃላ በመጀመሪያ የሰማው ድምፅ አዳም ወዴት ነህ የሚል ነበረ፤ አዳምም ጥያቄው የቦታ ጉዳይ መስሎት የተደበቀበትን ስፍራ ተናገረ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጥያቄ " ቀድሞ ባስቀመጥኩ የክብር ስፍራ ላይ ጠፍተህብኛል አሁን ወዴት ሄደህ ነው
የሚል ሀሳብ ነበረው ...
የተወደዳቹ ይሄ ድምፅ ዛሬም በአንዳንዶች ልብ ላይ የሚጮህ ይመስለኛል ወዴት ነህ ልጄ 😭 ? ወዴት ነሽ ልጄ ? የእውነት ጌታ ወዴት ናቹ ሲለን እንደ አዳም ለመናገር የምናፍርበት ስፍራ ላይ ከመገኘት ይልቅ እርሱ ራሱ ባስቀመጠን ስፍራ ላይ መገኘት ትልቅ ዋጋ እንዳለው ማወቅ አለብን ወዳጆቼ እግዚአብሔር በአይኑ ሳይሆን በልቡ ፈልጎ ሊያገኛቹ በሚችልበት ስፍራ ላይ ዘውትር ተቀመጡ፤ ያኔ ነው እንደ ልጅ ለአባታቹ መልስ ለመስጠት ድፍረት የሚኖራቹ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ፍቅሩ
የገባው ሰው ብቻ ነው እንዲህ ሊል የሚችለው.
..
“በሌላ ስፍራ ሺህ ቀን ከመኖር፣ በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤ “ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።”
— መዝሙር 84፥10
ይሄን መልዕክት እዳታነቡት 😠
በቃ ራስህን የመግዛት ችግር አለብህ ኣ ወንድሜ፤ እህቴ አንቺስ ብቶኚ ማነው አንብቢው ያለሽ ☺️ ? ግን እኮ ያያቹት ርዕስ እዳታነቡት እንጂ እንዳታ
ነ
ቡት አይልም ርዕሱ ላይ ን ጎሏል ተበልታቿል😄 ....
እ ርዕሱን አይታቹት ተመለሳቹ ኣ እኮ መልሱልኛ አታብቡት እየተባላቹ ለምንድነው የምታነቡኝ ይላቿል ይሄ መልዕክት 😄 እሺ ልመለስ ብዙ ቦታ ወሰዳቹኝ 🚶🚶
የተወደዳቹ የአዶናይ ቻናል ቤተሰቦች መንፈሳዊነት እንዴት ነው፤ ፀሎትስ ሰላም ነው ✋ አንዳንዶቻቹ ፀሎትን አግኝታቹት አታውቁም መሰለኝ እሺ ቃሉስ እየተጠና ነው ወይስ ትታቹታል ? መልሱልኛ ምነው ዝም አላቹ 😊 ? ታውቃላቹ አይደል ጌታ ሁል ጊዜ እንድናገኘው እንደሚፈልግ ታዲያ ለምንድነው እኛ የማንገኝለት ? በሉ አሁን አንድ የምቶዱትን መዝሙር ከፍታቹ ለ 30 ደቂቃ ይሄን ጌታ አኙትና ተመለሱ፤ ግድ የላቹም ስሙኝ ደግሞ አታንብቡ ተብላቹ አሿፈረኝ ብላቹ መልዕክቱን ካነበባቹ ላይቀር የወነ ቁም ነገርማ መውሰድ አለባቹ ! በሉ የተባላቹትን አድርጉ .... ጌታ እየጠበቃቹ ነው
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ቃል በገባሁላቹ መሰረት ለሁላቹም መንፈስ ቅዱስ እንዳሳሰበኝ መጠን ፀልዬላቿለው፤ የጌታ ማዳን እጅ በግልፅ በህይወታቹ ላይ ይገለጣል 🔥🔥ይቺን ቀን ያዙ .... ደግሞ ዘወትር ፀልዩ መንፈሳዊ ዝለት ውስጥ አትግቡ ውስጣቹ ያለውን ርሀብ እንደገና አነቃቁት ጌታ ከእናንተ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ይፈልጋል...
እወዳቿለው ተባረኩልኝ😍
የተወደዳቹ የቻናሌ ቤተሰቦች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ 😍
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6
መልካም በዓል ብያለው ✋😍😍
" ጌታ ሆይ እባክህ ቅዱሱን ያንተን መንፈስህ ከእኔ አታርቅ😭 እኔ ካለ መንፈስህ ደካማ ነኝ የሰጠኽኝን መንፈስ ከአጠገቤ ለአንድ አፍታም ማጣት አልፈልግም
😭
ታውቃላቹ አይደል የሁላችንም ድፍረትና አቅም መንፈስ ቅዱስ ነው፤ እርሱን ነው በዘመናችን ሁሉ ማጣት የሌለብን
በኢየሱስም ልፀልይላቹ በእምነት ተቀበሉ 🖐️🔥
ዳዊት በጥላቶቹ የተማረኩበትን ንብረቶችና ልጆች በእግዚአብሔር ረዳትነት አንድም ሳያስቀር የተወሰዱበትን ሁሉ መልሶ ምርኮ በምርኮ እንደሆነ ልክ እንዲሁ ዛሬ እፀልይላቿለው የእናንተ ነበረ አሁን ግን የተወሰደባቹ
☞የጤንነት ምርኮ
☞የሰላም ምርኮ
☞የፀሎት ምርኮ
☞የትዳር ምርኮ
☞የስራ ምርኮ
☞የአገልግሎት ምርኮ
☞የስኬት ምርኮ
አንድም ሳይቀር ከቀድሞ በብዙ እጥፍ ይመለስላቹቹ 🔥🔥🔥 በኢየሱስም በእምነት ተቀበሉ ይመለስላቹቹ🔥🔥
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
" አንድ " ብላቹ የጀመራቹት ጉዳይ...
መቼም ሰለሞን ሲነሳ የእርሱ ጥበብና በጥበቡ ምክንያት ያገኛቸው የሚስቶቹ እና የውሽማዎቹ ብዛት አብረውት ይነሳሉ፤ እንደምታውቁት ሰለሞን አንድ ብሎ የጀመረው ጉዳይ ሁለት ፣ ሶስት እያለ 1000 ሴት ጋር አድርሶታል ነገር ግን ምን ዋጋ አለው አብዝቶ ወደ እርሱ ያስጠጋቸው ሴቶች ኋላ ላይ ልቡን ሰርቀው ለአማልዕክት እንዲያሸረግድ አደረጉት፤ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል " ጥልቅ ጥልቅን ይስባል " ይሄ ቃል ቀላል ሊመስላቹ ይችላል ነገር ግን በደንብ ካስተዋላቹ ህይወታቹን የምትመሩበት ትልቅ ስንቅ ይሆናቿ
ል፤ ጥልቅ ጥልቅን ይስባል ማለት ባጭሩ ...ዝሙት ዝሙትን ይስባል ... ኃጢአት ኃጢአትን ይስባል...ድካም ድካምን ይስባል ማለት ነው ወዳጆቼ የትኛውንም ነገር ስትጀምሩ አስተውላቹ ጀምሩ ካለዚያ እንደ ቀልድ ወደ እናንተ ያቀረባቹን ጉዳይ ቀስ በቀስ እኩዮቹን ሰብስቦ ነገ ላይ ህይወታቹን የመግዛት አቅም ያገኛል ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
እስቲ ይህን መዝሙር ልጋብዛቹ😍
🎙️የልብ ምቴ
እኔ እንዳንተ ጨርቄን የጣልኩለት የለም ....
እኔ እንዳንተ አቅም ያጣሁለት የለም....
እኔ እንዳንተ የተሸነፍኩለት የለም 😭
የጌታን ፍቅር እያሰባቹ ስሙት
@Adonaizema
@Adonaizema
አሳ ነባሪውና እኛ 🥰ከላይ በምስሉ ላይ ስለምትመለከቱት ሰማያዊ አሳ ነባሪ ስለሚባለው አሳ ዝርያ ሳነብ ያገኘሁትን ላካፍላቹ...
የአሳ ነባሪው ቁመት ቢያንስ 30 ሜትር ይደርሳል በአጠቃላይ ክብደቱ 180,000 ኪሎ ግራም ይሆናል ልቡ ብቻ ደግሞ ከ590 ኪሎ ግራም በላይ ይመዝናል (የአንድ ትንሽ መኪና መጠን ያክላል ማለት ነው) አስገራሚው ነገር ደግሞ የአንዳንድ ሰማያዊ አሳ ነባሪ ዝርያ የደም ማስተላለፊያ ትቦዎች ስፋት ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ጎረምሳ የሆነ ሰው ያስዋኛሉ 😊 ግን የሚያሳዝነው ነገር ይሄ ግዙፍና አስፈሪ አሳ ነባሪ ከውሀ ውጪ መኖር አለመቻሉ ነው 😢 ግዙፍ ነው ግን ውሀ ውስጥ ብቻ ፣ አስፈሪ ነው ግን ውሀ ውስጥ ብቻ ... ይሄን የሚያክል ፍጥረት ለትንሽ ደቂቃ ከውሀ ውስጥ ቢወጣ ይሞታል🤦 ልክ እንዲሁ እኛም ትልቅ ነን ግን በክርስቶስ ውስጥ፣ ለጭለማው መንግሥት አስፈሪዎች ነን ግን በክርስቶስ ውስጥ ፣ ከአሸናፊዎች ሁሉ እንበልጣለን ግን ሁሉም የሚሆነው በክርስቶስ ውስጥ ስንሆን ብቻ ነው።
ሀያላን የእናንተ ገዢነትና ጥንካሬ የቱ ጋር እንደሚሰራ ለዩና እወቁ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
R/Ship ከመጀመራቹ በፊት ☛ ለሴቶች
አብዛኛውን ጊዜ በፍቅር ግንኙነት ጅማሬ ወቅት ወንድ ጠያቂ ሴት ደግሞ የፍቅር ጥያቄውን መላሽ ነው የምትሆነው፤ ሴቶች ለቀረበላቸው የፍቅር ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ ደግሞ አሁን ያሉበትን የእድሜ ሁኔታ ፣ የጓደኛ ግፊት እንዲሁም ለቀረቡት ወንድ ካላቸው ስሜት አንፃር ነው ጥያቄውን ተቀብለው የፍቅር ግንኙነቱን የሚጀምሩት ፤ ነገር ግን ከነዚህ ምክንያቶች ባለፈ R/ship ለመጀመር በመንፈሳዊ እይታ ማየቱ መልካም ይመስለኛል፤ ይገባኛል ብዙዎቻቹ የ R/ship ጉዳይ የእናንተ ፍቃድ እና ስሜት ብቻ ላይ ነው የተመሰረተ የሚመስላቹ ነገር ግን ከናንተ ስሜትና ምርጫ በላይ በ R/Ship ሆነ በትዳር ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ የሚባል ነገር አለ፤ ቆይ እስቲ ለምን ይመስላቿል የብዙ ሰዎች የፍቅር ህይወት እንደነበረው ቀጥሎ ወደ ትዳር አለም የማይመጣው ? እናንተ እንደምታስቡት ተደባብረው ፣ የሀብት ጉዳይ ሆኖ ወይስ ቤተሰቦቻቸው በግንኙነታቸው ደስ ስላልተሰኙ.... No No ከነዚህ ምክንያቶች ባለፈ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ስላልሆነ ነው፤ የውላቹ ሴቶችዬ R/ Shipu ተጀምሮ ኃላ ላይ ከምትጎዱበትና ልባቹ ከሚሰበር ከዛ ሁሉ በፊት ጊዜ ወስዳቹ ከላይ ከጠቀስኩላቹ R/ship ለመጀመር ብዙ ሴቶች ምክንያት የሚያደርጉትን ነገር ወደጎን ትታቹ የጌታ ፍቃድ ያለበትን ለእናንተ ቢሆን ነገ ላይ ትዳር ሆኖ ክብራቹን የምታዩበትን ይሄን ትልቅ የጌታን ሀሳብ እንደ አንድ የህይወታቹ ጉዳይ ትኩረት ሰጥታቹ እንድታስቡበት እመክራቿለው።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ይሳቅን ፍለጋ...
እግዚአብሔር ለአብርሀም ልጅ እሰጥሀለው ብሎት ኪዳን ገባለት ነገር ግን የተነገረው የትንቢት ቃል ሳይፈፀም አመታቶች ተቆጠሩ በዚህም ምክንያት አብርሃም ትኩረቱ ልጅ ላይ ብቻ ስለነበር በዚያም በዚም ብሎ ይወርስሀል ተብሎ የተነገረውን ልጅ ፍለጋ ሚስቱን ሳራን ትቶ ሞግዚቷ አጋር ጋር ገባ ነገር ግን ይሳቅን አገኛለው ብሎ አጋር ጋር የሄደው አብርሃም ከአጋር ማግኘት የቻለው የተጠበቀውን ይሳቅን ሳይሆን ያልታሰበውን እስማኤልን ነበር ....
ለካስ የተስፍው ቃል ባለቤት ይስሀቅ ያለው ያረጀቺው ሳራ ጋር እንጂ ወጣቷ አጋር ጋር አልነበረም ፤ አብርሃም ተሸወደ 😊 የተወደዳቹ እግዚአብሔር የእናንተን ይሳቅ ጠብቃቹት እንጂ አቋራጭ መንገድ ተጠቅማቹ እንድታገኙት በፍፁም አይፈልግም፤ ጌታ የነገራቹን ቃል የሚፈፅምበት የራሱ ጊዜ አለው እናንተ ብቻ የተባላቹትን በተባላቹት ስፍራ ላይ ሆናቹ ጠብቁ
።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ለክብር ነው.
..
ሰውዬው አይነ-ስውር ነው፤ ስራውም ቢሆን ልመና እንደነበር መጽሐፍ ይነግረናል የሰፈሩ ሰዎችም ለምልክት ካልሆነ በስተቀር የእርሱን ስም መጥቀስ አይፈልጉም፤ ቢበዛ ያ የለማኙ ሰፈር ቢባልለት ነው ብቻ ምን ልበላቹ ሰውዬው ባጭሩ ብዙ ማማረሪያ ምክንያቶች ነበሩት ነገር ግን አንድ ቀን ኢየሱስ አይኖቼን ያበራቸዋል የሚል ተስፍ ነበረው ደስ የሚለው ተስፍውም ባዶ አልቀረም የሚፈልገው ኢየሱስ አንድ ቀን ይለምንበት በነበረበት ስፍራ በኩል አለፈ፤ እና ይሄም ሰው ይጠብቀው የነበርው እድል እንዲያመልጠው ስላልፈለገ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ብሎ መጣራት ጀመረ 🗣️ የሰውዬውም ድምፅ ድንገት ባለመፍትሄው ኢየሱስ ጆሮ ደረሰ፤ ኢየሱስም አይነስውሩን ሰው አስጠርቶ አይተው የማያውቁትን አይኖቹን አበራለት ጉዳዩ ተአምር ተባለ ፣ የሚያውቁት ሁሉ ግራ ተጋቡ፣ ቀስ በቀስ የዚህ ሰው ታሪክ ከተማውን አዳረሰ...
እድሜውን፣ ክብሩን ያጣበት ጉዳይ ኃላ ላይ የእግዚአብሔር ክብር የሚታይበት መንገድ ሆነ፤ የተወደዳቹ ጣፋጩ በለስ ሁሉ ጊዜ በመጥፎ እሾክ የተከበበ እንደሆነ አትርሱ፤ የትኛውም እናንተ የምታልፉባቸው መጥፎ የሚመስሉ ወቅቶች ሁሉ አንድ እግዚአብሔር የሚከብርበትን ጣፋጭ የምስጋና ርዕሶች በውስጣቸው ይዘዋል።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
አጉል ቁማር አትጫወቱ 😠
ቸርች ውስጥ ያሉ ነገር ግን በጉልበቶቻቸው መንበርከክ ያቆሙ፤ ፊት መቅደምና መታየት የሚፈልጉ፣ የተሰጣቸውን ፀጋ አቃለው በሌሎች ፀጋ ላይ ማፊዝ ስራቹ ያደረጉ አገልጋይ ነኝ ባዮች በዝተዋል፤ ቆይ ጌታ ካልከበረበት ነብይ መባሉስ ቢቀር፣ ገንዘብና ክብሩንም ብንተወው፤ ሁሉም እኮ የ 60 እና የ 70 አመት ጉዳይ ነው እንዴት ሰው ነፍሱን ለሚጠፋው የአለም ስርዓት ቁማር አሲዞ ይጫወታል....
ወዳጆቼ እኛ የምናውቀው ኢየሱስ እኮ ፍቅርና ቅን ልብ ያለው ጌታ እንጂ ለክብሩ ሰራዊት አሰልፎ የተዋጋ መሪ አይደለም፤ ያ በመስቀል ላይ ዳግም የወለደን ኢየሱስ በእናንተ ድካምና ስንፍና ብዛት ለአለም መልኩ መደብዘዝ የለበት፤ በገዛ ነፍሳቹ አጉል ቁማር አትጫወቱ
ኢየሱስን መምሰል ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለውም
ና
ኢየሱስን ምሰሉ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
የተወደዳቹ ከታች ከተዘረዘሩት የትምህርት ርዕሶች መካከል እናንተ የምትፈልጉትን
ርዕስ ነክታቹ ዋናውን ትምህርት
ማግኘት ትችላላቹ.... ሁሉም በጣም ጠቃሚ ሀሳቦችን ይዘዋል... እዩአቸው
⚡ ለምንድነው ብርት-ጥፍት የምትሉት
🌠 ተዉ ግን 🤔
✨ ሴቶች አትቸኩሉ 🤦
🙅 አለም አትቀያይሩ
💯 በእንባ የሰማሁት መልዕክት 😭
✨ አንዳንዴ ግን ነው
🌟 ትናንትናቹ ስለእናንተ ቢናገርስ ?
👌 መሀሉ ሚስጥር ነው 🤫
🥀 ስለ አጉል ፍቅር ሳምሶንን ጠይቁት
〽️ የእናንተ መኖር ትርጉም የለውም ?
💧 አቁሙ 😠
💫 ምንም ያህል ቢያረፍድ ይሳቅ ይቀድማል
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
🎙️ አልሄድም
እዚያው ኖራለው እግርህን አቅፌ፤
ያፈቀርኩበትን ፍቅር ተደግፌ፣
አልሄድም ከእግርህ ስር አልሄድም😭
የመዝሙሩ መልዕክት ልባቹ ላይ እስኪቀር ድረስ ደጋግማቹ ስሙት..
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
በ 4 ኛው ዙር ... ሁላቹንም በሚያካትት መልኩ ልፀልይላቹ ነው 😍
"ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።”
— ያዕቆብ 5፥16
በዚህ ቃል መሰረት ጌታ ረድቶኝ ከዚህ በፊት ለተከታትይ 3 ዙሮች ለብዙ ሰዎች ፀልዬ ጌታ ትልቅ ነገርን አድርጓል አሁን ደግሞ በ 4 ኛው ዙር መንፈስ ቅዱስ እንደመራኝ መጠን ለሁላቹም ልፀልይላቹ አስቤያለሁ፤ የምፀልይላቹ እንደተለመደው የእያንዳንዳቹ Telegram Account ( Profile picture ) ላይ ቃል በመናገር ነው ስለዚህ እንዲፀለይላቹ የምትፈልጉ የአባቴ ልጆች "ኢየሱስ እወድሀለሁ" ብላቹ Comment ላይ ፃፉ፤ እኔም ጌታ በረዳኝ መጠን እፀልይላቿለሁ። የተወደዳቹ እኔ ይህንን የማደርገው መንፈስ ቅዱስ የብዙዎችን ሕይወት በዚህ ፀሎት በኩል ከማንኛውም እስራት ነፃ እንደሚያወጣ ስለማምን ነው 🔥
"ኢየሱስ እወድሀለሁ" ብላቹ ስትፅፉ የእግዚአብሔር ሀይል እንዲገለጥበት የሚትፈልጉበትን ጉዳይ እያሰባቹ ፃፉ እመኑ ጌታ አልፎ ይሰራል
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
ጥሬው እኮ ነው ብስል የሚሆነው 😥
አንድ ዘመን አለ ልክ እንደ ዮሴፍ ህልም ይዛቹ እስር ቤት የምትገቡበት ደግሞ ሌላ ዘመን አለ የንግስና ዘውድ ጭናቹ በአደባባይ የምትነግሱበት.... አንድ ዘመን አለ ልክ እንደ ያዕቆብ ኪዳን ይዛቹ ባሪያ የምቶኑበት ደግሞ ሌላ ዘመን አለ ብቻቹን ሰራዊት ሆናቹ የምትቆሙበት፤ የተወደዳቹ አንድ ጣፋጭ ፍሬ ጣፍጦ የሚበላው ብስል ከሆነ በኃል ነው ከዛ በፊት ግን ያው ፍሬ ጥሬና መራራ ነበረ፤ አስባቹታል ግን ፍሬ ሁሉ ገና ከጅምሩ ጣፋጭ ቢሆን ኖሮ ወዲያው ነበር ምንም ያህል ሳይጠነክርና መጠኑ ሳይጨምር የምንበላው ነገር ግን ፍሬው ማደግና መስፍት ስላለበት ማንም እንዳይነካው መራራ እንዲሆን ተደረገ ልክ እንዲሁ ጌታ የእኛንም ህይወት ደስ የሚያሰኝና ለብዙዎች ሰዎች እንዲተርፍ ሊያደርገው ሲፈልግ እድገታችን ደስ በማይል መንገድ ውስጥ ያሳልፈዋል ኃላ ላይ ግን ለተፈለግንበት አላማ ብቁ መሆናችንን ሲያውቅ ህይወታችንን ልክ እንደ ፍሬው ጣፋጭና ውብ አድርጎ በአደባባይ ይገልጠዋል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
ዶሮ እንቁላሏን ድንጋይ ላይ አጥልም
አይታቹ ከሆነ ዶሮ እንቁላሏን ከመጣሏ በፊት ለእንቁላሉ ምቹ ስፍራን ትፈልግለታለች ከዛም ያገኘችውን ስፍራ ለጥቂት ደቂቃ ታሞቀውና የእርሷን ምቾት ትታ ሁኔታዎችን ሁሉ ለእንቁላሉ አመቻችታ እንቁላሏን በዚያ ስፍራ ትጥላለች... ዛሬ ስለ ዶሮ ህይወት ላወራቹ ፈልጌ አልነበርም ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከዶሮ ስርዓት አንድ ያስተማረኝን ትምህርት ልንገራቹ ....
እንቁላል እንደምታውቁት ለመሰበር ትንሽ ነገር ነው የሚበቃው ነገር ግን ይሄን እውነት እርሱ አያውቅም Even የት መወለድ እንዳለበት እንኳን አይነገረውም፤ ስንት ቀን ታቅፎ እንደሚፈለፈልም መረጃው የለውም....የሚገርመው እንቁላሉ የት ቦታ ቢጣል እንደማይሰበር ፤ ስንት ቀን ቢታቀፍ ደግሞ ጫጩት ሆኖ እንደሚፈጠር የምታውቀው ዶሮዋ ብቻ ናት። ልክ እንዲሁ ደግሞ እግዚአብሔርም እናንተን በየትኛው ቤተሰብ በኩል ቢያመጣቹ ፣ የት ከተማ ቢያሳድጋቹ ፣ የት ትምህርት ቤት ቢያስተምራቹ ፣ ምን ዓይነት ስራ ቢያሰራቹ ፣ ምን አይነት የትዳር አጋር ቢሰጣቹ ፣ የት ስፍራ ቢያኖራቹ የተፈጠራቹበትን ግብ እንደምትመቱለት በደንብ አድርጎ ያውቃል፤ ልክ ዶሮ እንቁላሏን ድንጋይ ላይ እንደማጥል ሁሉ እግዚአብሔርም እናንተን በምትሰበሩበትና ዋጋ በማይኖራቹ ስፍራ በኩል ወደዚች ምድር አያመጣቹም፤ እግዚአብሔር ታታሪ አምላክ ነው በእናንተ ህይወት የሚሰራውን ያውቃል ።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost