thedayofpentecost | Unsorted

Telegram-канал thedayofpentecost - አዶናይ

3069

ኢየሱስ ዛሬም በፍፁም ፍቅሩ ይወዳቿል

Subscribe to a channel

አዶናይ

የእግዚአብሔርን ክብር የተራቡ ህፃናት መንፈስ ቅዱስ በኃይል ሲነካቸው🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

#እኔ የምጮኋው እንዲህ ነው☝️
#ጩህ እሪሪሪ በል 🔥
ድንቅ ትምህርት #ከህይወቴ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@SisayAzusaRevivall
@SisayAzusaRevivall
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የናፈቀኝን🎵

ቀልቤን ከኔ የወሰደውን ሀሳቤን ከኔ የሰረቀውን እስኪ አንዴ ልየው ፊትህን ሌላው ሌላው ቀሎብኝ እንዳይ


@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ጊዜው የመንፈስ ቅዱስ ነው 🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ብቻ እኔ የማውቀው ክብር እንዳለ ነው
🔥🔥🔥🔥🔥🔥

“የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።”
— ኢሳይያስ 40፥5

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

በጣም የተባረኩበት መዝሙር ፀሎቴ-ጋ

ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ
ከእግሮችህ ስር መድሀኒትን ይዤ እንድነሳ


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ስለ ህዝባችን እንፀልይ

የጥይት ድምጽ በሰሙ ቁጥር ነገ የሚባለውን ቀን የማያዩ የሚመስላቸው የጭንቅ ለሊታቸው የማይነጋላቸው ብዙ ሰዎች አሉ በተለይ በሰሜኑ አከባቢ፤ ወዳጆቼ ለነዚህ ውድ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ልንፀልይላቸው ይገባል፤ ቢያንስ በቀን ለ 30 ደቂቃ በራችንን ዘግተን የእግዚአብሔር ምህረት እንድትቀድም በምልጃ መንፈስ እንበርከክ፤ እግዚአብሔር ለምድራችን መልካምን ነገር ያደርጋልና።

ይህንን የፀሎት ጥሪ ለሰዎች አጋሩ

አያለሁ ከደመናው ማዶ ብሩህ ፀሀይ ስትወጣ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ ነው እወድሀለሁ ቢለኝ የሚያምርበት፤ ሰው በከንፈሩ ቃላትን አሱቦ እወድሀለሁ ቢለኝ ብዙ አይገርመኝም፣ ትኩርትም አልሰጠውም ግን አንድ ወዳጅ አለኝ በበደሌ ብዛት ጎኑን የወጋሁት ኢየሱስ ይባላል፤ ይህ ወዳጄ እንደ ሰው በአንደበቱ ቃላትን አሳምሮ እወድሀለሁ አላለኝም፤ ይልቁኑ ነፍሱን ስለ እኔና ስለናንተ ሰጥቆ የመውድድን ጥግ በሞቱ ገለፀ እንጂ፤ ለዚህ ነው ኢየሱስ በሙሉ ድፍረት እወዳቿለው ቢለን የሚያምርበት።

ኢየሱስ በማይቀየረው ፍቅሩ ዛሬም ይወደናል

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ልጆች ነን

🔶 በቀድሞ ዘመን( በብሉይ ኪዳን) ማንም ደፍሮ እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለት አይችልም ነበር፤ ለአምላኩ ለእግዚአብሔርም መስዋዕትን የሚያቀርበው በፍርሀትና በታላቅ መንቀጥቀጥ ውስጥ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱሳችን ይናገራል፤ ይህ መስዋዕትን የማቅርብ ተገባርም በአዲሱ ኪዳን በእውነተኛ መንፈስ ሊሆን የተገባው ነው፤ በአንድ ቤት ውስጥ ባሪያ የልጅን ያህል ስልጣንና ከበሬታ ሊኖረው አይችልም ምክንያቱም ከሚሰራበት ቤተሰብ ጋር ያገናኘው ስጋ ሳይሆን ገንዘብ ስለሆነ ፤ ይህ ባሪያ ለመብላት የግድ መስራት ይኖርበታል፤ ልጅ ግን ልጅ ስለሆነ ብቻ ከባሪያው በላይ የቅንጦት ኑሮ ይኖራል።

🔶 ባሪያ ምንም ቢሰጠው ልጅ ሊሆን አይችልም፤ ልጅም እንዲሁ ምንም ቢደረግለት ባሪያ መሆን አይችልም፤ እግዚአብሔር አምላክ የሚወደውን አንድያ ልጁን አሳልፎ ሰጥቶን በእርሱ በኩል እኛም የልጅነት ስልጣን አግኝተናል ስለዚህ እንደ ባሪያ መኖር አንችልም ምክንያቱም የልጅነት ሕይወት ከክርስቶስ ስለተካፈልን፤ ከዚህ በፊት ወገን አልነበረንም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወግኖች ነን፤ ቀድሞ ሙት ሆነን ሳለን በክርስቶስ ህይወትን አገኘን፤ አሁን ያለማፈር እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ማለት እንችላለን እግዚአብሔር አምላክ አባታችን ሆኗልና።

🔸ልጅ ምን እበላለው ብሎ አይጨነቅም፤ ምክንያቱም ራበኝ ሳይለው በፊት የፊቱን መልክ አይቶ የሚራራለት አባት ስላለው

🔸ልጅ ግንዘብ የለኝም ብሎ ራሱን አይወቅስም ምክንያቱም የአባቱ የሆነ ሁሉ የእርሱ እንደሆነ ያውቃልና።

🔸ልጅ ምን እለብሳለሁ ፣ የትስ እኖራለው፤ ነገስ በህይወት እኖር ይሆን ብሎ አይጨነቅም ምክንያቱም እንደ አይኑ ብሌን በሚጠብቀው በአባቱ እቅፍ ውስጥ ስላለ።

ወዳጆቼ ምንስ እንለብሳለን፤ ምንስ እንበላለን፤ ምንስ እንጠጣለን ብላቹ አትጨነቁ መጽሐፍ ሲናገር እንዲህ ይላል

“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?”
— ማቴዎስ 6፥25

ነብስ የሰጠን ጌታ መብልን አይከለክለንም፤ ሰውነት የሰጠንም ጌታ ልብስን አይነሳንምና

🔶ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋቹም ያለን
እግዚአብሔር ወላጅ ስለሆነን ነው
፤ወላጅ ደግሞ ለልጆቹ ከራሱ በላይ ያስባል ስለዚህ ውድ የተባረካቹ የአባቴ ብሩካን ከኛ በላይ ስለኛ የሚያስብልንና የሚጨነቅልን አባት ስላለን እንደ ልጅነታች እንመላለስ።

“የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።”
— ሮሜ 8፥16

ጌታ ዘመናቹን ይባርክ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ስለኔ ክብሩን ጣለ ተናቀ ተተፋበት፤
እንደ በግ ተጎተተ እንደሌለው ረዳት፣
ተጠማ ተራቆተ እንደከንቱ ተቆጠረ
እንደሰው ሞትን ፈርቶ በልቡ ተሸበረ፤
😭😭😭😭😭😭😭😭😭

የእርሱ ሞት ለኛ ህይወት ሆነ
ወዳጆቼ የተከፈለልን ዋጋ ቀላል አይደለም፤ እኔ የተከፈለልኝን ዋጋ ባሰብኩ ቁጥር ዋጋዬ ምን ያህል ውድ እንደሆነ እረዳለሁ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ለምን እፈራለሁ

ሰዎች ከኔ ጋር አይደሉም፤ በምድረ በዳ ብቻዬን ቀረው🤦፤ ጥላቶቼም በዙራዬ እጅጉን በዝተዋል ብዬ ስተክዝ🙇 የሰማዩ አባቴ ህያው በሆነው ቃሉ እንዲ አለኝ.......

“እርሱም፦ እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፥ አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፥ ጽና አለኝ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና፦ አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር አልሁ።”
— ዳንኤል 10፥19


ወዮ ጠፋሁኝ፤ ጉልበቴም ዛለ ፣ የሚረዳኝ ወገን ዘመድ የለኝም፤ በቃ የኔ ነገር እዚ ጋር አበቃለት፤ ብዬ ደምድሜ ሳለው መጽሐፍ ቅዱሴን ሳነብ አምላኬ እንዲ አለኝ .......

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።”
— ኢሳይያስ 41፥10


ታዲያ ለምን ብዬ ልፍራ፤ ለማንስ ብዬ ልጨነቅ ከማንም በላይ የሚራራልኝ፤ልጄ ብሎ ሲጠራኝ የማያፍርብኝ ውድ አባት እያለኝ።

ውድ የአባቴ ብሩካን ከየትኛውም ፈተናና ችግር በላይ አምላክ ለናንተ የሰጠው የተስፍ ቃል ይበልጣል፤ ስለዚህ ነፍሱን ሳይቀር አሳልፍ በሰጠላቹ በአምላካቹ ቃል ታመኑ።

እወዳቿለው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

2014 ዓ.ም የመንፈስ ቅዱስ አመት ይሆናል🔥🔥🌧⛈🔥🔥⛈🌧🔥🔥🌧⛈🔥🔥⛈

እግዚአብሔር ሆይ ክብርህን አሳየኝ ብለው በራቸውን ዘግተው መንፈሱን ይጠሙ በነበሩት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ክብር ያለገደብ ይገለጣል፤ በየአደባባዩም ብዙ ሺዎችን በክርስቶስ ፍቅር እንማርካለን።

ሐዋርያት 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የበዓለ ኀምሳ ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድነት፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ነበር፤
² ድንገትም እንደ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጥቶ ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት እንዳለ ሞላው
³ የእሳት ምላሶች የሚመስሉም ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉ።
ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስም እንዲናገሩ በሰጣቸው መጠን በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር።

ግድየላቹም 2014 የሚነሳ ክብር 🔥🔥 አለ፤ ብቻ ተግታቹ ፀልዩ እግዚአብሔር አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ለአለም ይገልጣቿል።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እንዲሁ በፀጋ

ለምንድነው መዳናችን በነፃ የሆነው በሚል ያለማመን ድንዛዜ ብዙዎች በስራቸው መፅደቅ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን በስራው ማንም እንደማይፀድቅ መጽሐፍ ቅዱሳችን እውነትን መቀበል ለማይፈልጉትና በሀይማኖት ስርዓት ለታሰሩት ሰዎች በግልፅ እውነታውን ያስረዳል።

“እንግዲህ በጸጋ ከሆነ በሥራ አይደለም፤ በሥራ ቢሆንማ ኖሮ ጸጋ፣ ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር።”
— ሮሜ 11፥6 (አዲሱ መ.ት)


ግን ለምንድነው መዳናችን እንዲው በነፃ የሆነልን፤ ይህንን ጥያቄ ራሴን መጠየቅ ስጀምር አንድ መልስ የሚሆንልኝ ነገር ተረዳው.......

በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘናቸውን ነገሮች በገንዘብ መተመን ብንጀምር የዚች አለም የዘላለም ሀብት እንኳን ቢደመር አይበቃንም ፤ ስለዚህም ነው መዳናችን በነፃ የሆነው፤ ምክንያቱም ዘላለማዊ ህይወት በገንዘብ መግዛት ስለማንችል ልዑል እግዚአብሔር መተኪያ የለለውን አንዱን ልጁን ክርስቶስን መስዋዕት በማድረግ የኛን ሞት በህይወት ገዛው፤ ለዚህ ነው መዳናችን እንዲሁ በፀጋ ነው የምንለው።

በመዳኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያገኘነው ህይወት በነፃ ቢሆንም የተከፈለበት ዋጋ ግን ውድ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ክብሩ🌧ን... እንደተጠማሁ አልቀርም እንደተመኘው🔥 🌧🔥⛈

የእግዚአብሔርን ክብር⛈ ክብር🔥 ክብር🌨 ክብር 🔥ክብርር በኢትዮጵያ ላይ እንደተጠማሁ አልቀርም 2014 አያለሁ

የክርስቶስ አዳኝነት በግልጽ በየአደባባዩ የሚያስተጋቡና በክብር ለአለም ህዝቦች ድንገት የሚገለጡ እልፍ ብርቱ ሙሴዎች🔥እያሱዎች🔥 ኤልያሶች🔥 ኢልሳዎች🔥 ዮሐንሶች🔥 ጳውሎሶች🔥 ጴጥሮሶች🔥 ይነሳሉ ከነኚ አንዱ እኔ ነኝ።

“እርሱም፦ እባክህ ክብርህን አሳየኝ አለ።”
— ዘጸአት 33፥18


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

#ፈተናው_ግድ_ነው

አረ የኔስ ፈተና ያለቅጥ በዛ፤ እድሜዪን ሙሉ በፈተና!🤔 ለምንድነው ጌታ የጨከነብኝ፤ የኔስ ነገር እንዴት ግድ አይለውም ለምትሉ የአባቴ ብሩካን ይህ መልዕክት ለናንተ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በከባድ ፈተናዎች ውስጥ ካለፉ የእግዚአብሔር ሰዎች መካከል አብርሃም እና ዮሴፍን መመልከት እንችላለን

ዘፍጥረት 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ አለ።
² የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ።

እግዚአብሔር ለአብረሃም የገባለትን ኪዳን የሚያስፈፅምበትን አንዱን ልጁን ነበር ሰዋልኝ ያለው፤ አብረሃምም ከስጦታው ይልቅ ሰጪውን እግዚአብሔር ስለታመነ የሚወደውን አንድያ ልጁን ሊከለክለው አልፈለገም፤

በሌላ በኩል ደግሞ ዮሴፍን ማንሳት እንችላለን፤ ዮሴፍ ህልሙን ለወንድሞቹ ሲነግራቸው መጠላትንና መገፋትን ነው ያተረፈው፤ ነገር ግን በወንድሞቹ መገፋትና መጠላት የኃላ የኃላ የንግስናን አክሊል👑 ይዞለት መጣ።

እግዚአብሔር ለታላቅ ክብር ሲፈልገን በንደዚ አይነት ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች ውስጥ ያሳልፈናል፤ምክንያቱም ለሰዎች ሁሉ የሚታይ እንቁ💎 ሊያደርገን ስለፈለገ ነው።

🕳️ፈተናው የበረታብኝ እግዚአብሔር ለታላቅ ክብር ስለፈለገኝ ነው፤ ሰዎችን የሚያስገርም ክብር የሚመጣው በከባድ ፈተና ተጠቅልሎ ስለሆነ፤ ፈተናውን ማለፍ ግድ ነው።

ወርቅ ተፈላጊነቱ የሚጨምረው በእሳት ውስጥ ካለፈ በኋላ እንደሆነ፤ ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር ዋጋችንን ሊያገነውና ተፈላጊነታችንን በሰው ልጆች ሁሉ ፊት ሊገልጥ ሲፈልግ በከባድ ፈተና ውስጥ ያሳልፈናል።

#ጌታ_ዘመናቹን_ይባርክ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ክርስትና ያለ መንፈስ ቅዱስ ምንም ጎማ እንደሌለው መኪና ማለት ነው፤ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለውም፣ ይህ ነው ብለን እንኳን የምናወራው ራዕይ አይኖረንም፤ በቃ ስም ብቻ ይሆንብናል ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በክርስትናችን ህይወት ላይ የመሪነት ድርሻ ሲኖረው ትናንትናን አንደግመውም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን እንጂ🔥🔥🔥🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እንድረስላቸው

How many people in the world die every day?

Answer 170,000


ይህንን መረጃ ስመለከት መጀመሪያ ማሰብ የጀመርኩት ከሞት በኋላ ስላለው የሰው ልጆች ህይወት ነው፤ በአለም ላይ በቀን ብቻ ከመቶ ሰባ ሺ (170,000) ሰዎች በላይ ህይወታቸውን ያጣሉ፤ነገር ግን እነኚ ሁሉ ሰዎች ከስጋዊ ህይወት ወደ መንፈሳዊ አለም አድራሻ ቀየሩ እንጂ ከሞት በኃላ ምንም አይነት ፍርድ የለባቸውም ማለት አይደለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጆች ነፍስ ግድ ይለዋል ለዚህም ነው አንድያ ልጁን ክርስቶስ ለኛ መዳን አሳልፎ የሰጠው፤ ይሁን እንጂ የዚህ አለም ገዢ ዲያቢሎስ ይህንን እውነታ ሰዎች እንዲያውቁት አይፈልግም፤ በተለይ በዚህ ጊዜ ሃይማኖት በሚባል ስርአት ብዙዎችን ከፋፍሎ እውነተኛው መንገድ የትኛው እንደሆነ እንዳያውቁ ያደርጋል፤ አለም ግን እውነተኛው የህይወት መንገድ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች።

ውድ የአባቴ ብሩካን በቀን ከሚሞቱት 170,000 ሰዎች መካከል 10% የሚሆኑት እንኳን ዘላለማዊ ህይወትን አያገኙም፤ ከ90% በላይ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ የዘላለም ፍርድ ይጠብቃቸዋል ታዲያ እንዴት አስቻለን፤ የምኖዳቸው ወንድሞች ፣ እህቶች፣ ዘመድ አዝማድ እረ ብዙ መጥቀስ እንችላለን፤ ታዲያ እኛ የዘላለምን ሕይወት አግኝተን የምኖዳቸው ወዳጆቻችን የዘላለም ሞት እንደሚጠብቃቸው እያወቅን ለምን ዝምታን መረጥን መልሱን ለናንተው ልተወው??????

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ አደባባይ ወጥተን ወንጌልን ለፍጥርት መስበክ ባንችል እንኳን ለምኖዳቸው ሰዎች ግን እውነተኛውን የህይወት መንገድ በመንገር የተሰጠንን ኃላፊነት መወጣት አለብን፤
ያላመነ ሰው ለነገው ህይወቱ ዋስትና የለውም ስለዚህ በክርስቶስ ስራ የዘላለምን ህይወት አግኝቻለሁ የምንል ሁሉ በዚች 2 ቀናቶች ውስጥ ቢያንስ ለ 2 ሰው ወንጌልን በመናገር ከአስከፊው ሁለተኛ ሞት ወገኖቻችንን እንታደጋቸው፤
ግዴታ ነው አደራ አለብን ጌታ ሁላችንንም በፍርድ ቀን ይጠይቀናል።


@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

አይቻለሁ

¹¹ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል። ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ።

እኔም ........…..

🔥 እልፍ ሰዎች በአንተ ህይወት ሲያገኙ ፤ ፍጥረታት ሁሉ ክብራቸውን ትተው አንተን ሲያመልኩህ

🔥 በክብርህ መገለጥ አለም ስትደነግጥ፤ለዚህ አለም ገዢ የእሳት ረመጥ የሆኑ ልጆችህ ሲነሱ

🔥የሊቆች፣ የገዢዎችና የነገስታት ጉልበት ላንተ ክብር ሲንበረከክ

🔥 ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንተና የአንተ ስራ ብቻ ዜና ሲሆን

🔥ልጅነታቸውን በመንፈስ የተረዱ ማንም ሊያስቆማቸው የማይችሉ፤ ከአውሬው መንጋጋ ብዙዎችን የሚያስተፉ ብርቱ ልጆች ሲነሱ አያለሁ አልኩት

¹² እግዚአብሔርም፦ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ።

ወዳጆቼ እናንተ ምን ይታያቿል ፤ አምላካቹ እግዚአብሔር ያያቹትን ይፈፅም ዘንድ ይተጋልና።


@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢሳይያስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።
¹² አቤቱ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት

መደምደሚያዬ ገነቴ ውዴ ሽልማቴ

ፈገግታዬ መአዛዬ ማለፊያዬ

እንደገናዬ ደስታዬ ታሪኬ እረኛዬ

አድራሻዬ መኃደጃዬ ጋሻዬ ሳቄ

ፈላጊዬ ኃይሌ መንገዴ እውነቴ

ክብሬ ሚስጥረኛዬ ውበቴ

ደምግባቴ መቋጫዬ አቅሜ ሰላሜ

መድኔ ጠያቂዬ አለሜ ድፍረቴ

ፅድቄ ጉልበቴ ዓለቴ ህይወቴ

ዋስትናዬ አባቴ መድሀኒቴ ረዳቴ

መታመኛዬ የደኅንነቴ ቀንድ ዋሻዬ

መጠጊያዬ እጣዬ አምባዬ ብልጫዬ

ረድኤቴ


አባት ቢሉህ እናት ቢሉህ ወንድም ቢሉህ እህት ቢሉህ ወዳጅ ባልንጀራ ጌታ ሆይ ምን አለ የማትሞላው ስፍራ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ከአገልጋይ ዮኒ ጋር ስለ ምድራችን ኢትዮጵያ አብረን እንፀልይ🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

“በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።”
— 2 ዜና 7፥14 (አዲሱ መ.ት)

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

እኔን ላከኝ በሉት

አንተን ወደ ማያውቁህ፣ እውነተኛው መንገድ ጠፍቷቸው ለሚቅበዘበዙት፣ ባለማወቅ በዲያቢሎስ እስራት ወደተያዙት፣ በአለም ፍቅር ለታወሩት፣በዚህ ሰዓት በፍርድ ህይወት ውስጥ ላሉት ወንድምና እህቶቼ የምስራቹን ወንጌል እናገር ዘንድ ጌታ ሆይ እኔን ላከኝ ብዬ አባቴን ለመንኩት።

ኢሳይያስ 6 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት። እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” አልሁ።


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ

የታሰሩት ሁሉ ይፈታሉ ለአምላካቸው ክብር ይሰግዳሉ፤ አመፀኞች ሁሉ ይማረካሉ ለኢየሱሴ ክብር ይሰግዳሉ እናምናለን እናምናለን አዲስን ነገር እናያለን።

በፀሎት መንፈስ ስትሆኑ ይህንን መዝሙር ስሙልኝ😭😭፤ በጣም የምወደው መዝሙር ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የናፈቀኝ ያንተ መንፈስ ነው

አላስችልህም አለኝ የውስጤ ርሀቡ መንፈስህ በኔ ይፍሰስ በመቅደሱ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

መንፈስ ቅዱስ ካላንተ ምንም ነንና ከኛ አትራቅ ታስፈልገናለህ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🇪🇹በቅርብ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ላይ🇪🇹

አስደናቂ ትንቢት ለኢትዮጵያ !


በውጪው አለም እጅግ ተወዳጅ እና በቤተክርስቲያናቸው እጅግ ብዙ ሰዎች ያፈሩት የእግዚአብሔር ሰው Pastro Benin Hinn ለኢትዮጵያ አድሰናቂ ትንቢት አምጥተዋል።

እግዚአብሔር ሰው Pastro Benin Hinn እንዲ ሲሉ ትንቢታቸውን ለኢትዮጵያ ይናገራሉ:-

"በኢትዮጵያ ላይ አዲስ ብርሀን ሲወጣ አያለው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ብሎም ለአለም የሪቫይቫል ችቦ ይዛ የምትነሳበት ሰዓተ እንደደረሰ አያለው"።

"በአሁኑ በምድሪቷ ላይ ያለው ውጊያ በፍጥነት ይቆማል ምድሪቱ ወደ ብልጽግና ትሸጋገራለች በምድሪቱ ያላችሁ ቅድሳን አገልጋዮች እራሳችን ለሚመጣው የክብር ዘመን አዘጋጁ" 🔥🔥🔥🔥

ወገኖቼ አለም የሚጠብቀው እኛን ነው🔥


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ምህረቱ በዝቶልን ነው

ማንም በስራው አልፀደቀም፤የእያንዳንዳችን የቀን ውሏችን ቢፈተሽና የኃጢአት ፍይላችን ቢመረመር ማንም ደፍሮ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ባልቻለ ነበር፥

እግዚአብሔር አምላክ ልጆቹን የሚመለከተው ፃድቅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ስለሆነ፤እንደበደላችን ብዛት የቁጣ በትሩን ያላሳረፈብንም።

“ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።”
— ሰቆ. 3፥22

እግዚአብሔር አምላክ ስላበዛልን ምህረቱ የተመሰገነ ይሁን🙏

ጌታ ዘመናቹን ይባርክ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

የመንፈስ ቅዱስ ሙላት🔥🔥🔥

By apostle Tamrat Tarekegn

“ዮሐንስ መልሶ፦ እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤”
— ሉቃስ 3፥16

በኢየሱስ ስም ይህንን ዞይስ በሚያዳምጡት ሰዎች ሁሉ ላይ አይተውት የማያውቁት የእግዚአብሔር ክብር ይለፍ🔥🔥🔥🔥🔥🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

መንፈስ ቅዱስ ማነው?

ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ብዙ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ ጥቂቶች መንፈስ ቅዱስን እንደ ረቂቅ ኃይል ይመለከቱታል ሌሎች ደግሞ መንፈስ ቅዱስን እግዚአብሔር ለክርስቶስ ተከታዮች የገለጠው ማንነት የሌለው ኃይል እንደሆነ ይገረዳሉ፤

መጽሐፍ ቅዱስስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ምን ይላል?
በቀላሉ ሲቀመጥ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ያውጃል፤ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አካል፤ ማንነት ያለው ፤ ስሜት እና ፈቃድ ያለው እንደሆነ ይነግረናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር የመሆኑ እውነታ የሐዋሪያት ሥራ 5፡3-4ን ጨምሮ በብዙ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ በግልጽ ተቀምጧል ፤በዚህ ቁጥር ውስጥ ሐናንያ መንፈስ ቅዱስን ለምን እንደዋሸ ሊጠይቀው እንመለከታለን ፤ቀጥሎም
“እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን እንዳልዋሸ” ነገረው፤መንፈስ ቅዱስን መዋሸት እግዚአብሔርን መዋሸት እንደሆነ በግልጽ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ ማወቅ እንችላለን ምክንያቱም የመለኮትን ባህሪያት ይዟል፤ለምሳሌ ያህል መንፈስ ቅዱስ በሁሉ ሥፍራ የሚገኝ መሆኑን መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙሩ ገልጿል።

መዝሙር 139
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
⁸ ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ሁሉን አዋቂ እንደሆነ ጽፎላቸዋል፤ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ የመለኮት አካል የሆነና ያለና የሚኖር ዘላለማዊ፣ ሁሉን አዋቂና በሁሉም ስፍራ ባንድ ጊዜ መገኘት የሚችል እግዚአብሔር ነው

1ኛ ቆሮንቶስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።
¹¹ በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም።


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

ይህንን መዝሙር በፀሎት መንፈስ ስትሆኑ ስሙልኝ 😍

በመንፈስህ ሙላኝ
ዘማሪ አቤኔዘር ፍቅሩ

ካላቹበት የመንፈሳዊ ክብር ወደሌላ አዲስ የመንፈስ ከፍታ የሚያሸጋግር የእግዚአብሔር ክብር ያግኛቹ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…

አዶናይ

🔥ክብር ያለበትን የአስቴርን መዝሙር ልጋብዛቹ

ይህንን መዝሙር ከመውደዴ የተነሳ በቀን አንዴ ሳልሰማው አልቀርም

🎵 በዘመኔ አያለሁ

ደስታህ እንዲፈፀም ፊቶች አንተን አይተው፤
በዝቶ ተከታይክ ፈገግታህን ላየው
ስጋ ፀጥ ብሎ ጉልበት ተንበርክኮ
በልጆችህ ማሀል የሱስ ብቻ ልቆ
ይሄንንንን በዘመኔ አያለሁ......በዘመኔ አያለሁሁ.......በዘመኔ አያለሁ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Читать полностью…
Subscribe to a channel